አርቶፊያ (ARTOPHIA) ✍
Статистикаጥበብ ባህር ነው ነፍስን ያለመልማል። ገጣሚያን ቃላቶቻቸውን ሰዓሊያን ብሩሽ እና ቀለማቸውን ጸሐፍት ብዕራቸውን ፤ ሁሉም ወደ ባህሩ ይዞ ይጓዛል ከባህሩም ይረካል ። ባህሩ ግን አይጎድልም ፣ ቃላቶችም ፣ ቀለማትም አይነጥፉም ፣ አይወይቡም!!!
- Последний пост
- 3 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 144
- 1/48двое суток
- 165
- 1/72трое суток
- 177
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Trust God through the process.
ገበሬውና ያልተሟላው ሰብል አንድ ገበሬ ሁልጊዜ አምላክን ያማርር ነበር። "አንተ ተፈጥሮን አታውቅባትም፤ ዝናብ ሲያስፈልግ ፀሐይ ታወጣለህ፣ ፀሐይ ሲያስፈልግ ዝናብ ታዘንባለህ" ይለው ነበር። አንድ ቀን አምላክ ተገለጠለትና፦ "እሺ፣ ለአንድ ዓመት የአየር ሁኔታውን አንተ ተቆጣጠረው" አለው። ገበሬው በጣም ደስ አለው! ሰብሉን ዘራ። ዝናብ ሲፈልግ "ሁን" ይላል፤ ይዘንባል። ፀሐይ ሲፈልግ "ውጣ" ይላል፤ ትወጣለች። ነፋስና ብርድ ግን ሰብሌን ይጎዱብኛል ብሎ ስለፈራ ከለከላቸው። ሰብሉ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ረዝሞና አምሮ በቀለ። ገበሬው በደስታ ተሞላ። ነገር ግን የመከር ወቅት ደርሶ ሰብሉ ሊታጨድ ሲል አንድ አስደንጋጭ ነገር ተከሰተ። እያንዳንዱ የጤፍና የስንዴ ዘለላ ውስጥ "ፍሬ" አልነበረም፤ ሁሉም ባዶ ነበሩ! ገበሬው በሐዘን ተሰብሮ "ለምን እንዲህ ሆነ?" ብሎ አምላክን ጠየቀ። አምላክም እንዲህ አለው፦ "አንተ ፀሐይና ዝናብ ብቻ ሰጠኸው፤ ሰብሉ ግን ጠንካራ እንዲሆንና ፍሬ እንዲያወጣ የነፋስ ግፊትንና የብርድ ፈተናን መቋቋም ነበረበት። አንተ ፈተናውን ስለከለከልከው ሰብሉ ታላቅ መስሎ ታየ እንጂ ውስጡ ባዶ ሆነ።"
ህይወት እኮ መለወጥ እንደምትችል በየጊዜው አንድ የተለየ ነገር እያደረክ ማረጋገጥ ነው።ማፍቀር እንደምትችል አረጋግጠሀል።መርሳት እንደምትችል አረጋግጥ። መረቅ አዳም ረታ https://t.me/yeesua_queen
“If there is a good will, there is great way.”
አንዳንዴ ለመዳን ስንል እያመመንም ቢሆን ቁስላችንን እየነካን አልኮል ማፍሰስ አለብን...
፡ "በእያንዳንዱ አጋጣሚ ማሰብ የቻለ፡ ሙሉ ሰው የመሆን እድል ይኖረዋል፡፡በእያንዳንዱ አጋጣሚ ማሰብ ያቃተው ደግሞ፡ እንደ በጋ ምንጭ እያደር ይደርቃል፡ እንደ በጋ ቅጠል አድሮ ይጠወልጋል፡፡ ማሰብ ብቻ፡ ሙሉ ሰው፡ ያደርጋል፡፡" "አለማወቅ"
Watch Your Thoughts; They Become Words. Watch Your Words; They Become Actions. Watch Your Actions; They Become Habits. Watch Your Habits; They Become Character. Watch Your Character; It Becomes Your Destiny. #Mqquotes
ልንገርህ...... .....በብዙ ትርምሶች መሀል ብዙ መረጋጋቶችን ባለማየት ታልፋለህ ፡ በብዙ ወጎች መሀል ብዙ ቁም ነገሮችን ባለ ማወቅ ታሳልፋለህ ፡ በብዙ ጥላቻወች መሀል ብዙ ፍቅሮችን ባለ ማስተዋል ታልፋለህ ፡ በብዙ ሞቶች መሀል ብዙ ህይወቶች ባለማወቅ ታልፋለህ ፡ በብዙ ግጭቶች መሀል ብዙ ደግነቶችን ባለማየት ታልፋለህ፡ እናም እልሀለሁ የምታየው የምትሰማው ይሆናል ብለህ ያሰብከውን ነው ። አንተ ባላየህበት መንገድ ሰወች ማየት ባይችሉ አትኮንናቸው ሁሉም በራሱ የራሱን ያያል ይላሉ
ማሸነፍ ምንድነው የምኞት ኣዝመራ የደስታ መከራ የታጨደ ጣጣ የታወቀ ችግርየሞት የመከራ² የሚነድ እሳት ነው ተዳፍኖ የበራ እያደር _ ጠፊ ነው እያደር ቀሪ ነው ሲቆይ ይሰለቻል ዋጋው ይቀንሳል። ሁልግዜ በማግኘት ዘወትር በማሸነፍ ዘወትር በመመካት በመግዛት በመቅጣት፥ ደስታ ኣይገኝም፤ ሌላ ይፈልጋል የሰው ልብ ኣይጠግብም። ለጥቅሙ የሚያስብ የተስገበገበ መንገዱን የማያቅ ግቡ የጠበበ፥ ስስታም…
ማሸነፍ ምንድነው የምኞት ኣዝመራ የደስታ መከራ የታጨደ ጣጣ የታወቀ ችግርየሞት የመከራ² የሚነድ እሳት ነው ተዳፍኖ የበራ እያደር _ ጠፊ ነው እያደር ቀሪ ነው ሲቆይ ይሰለቻል ዋጋው ይቀንሳል። ሁልግዜ በማግኘት ዘወትር በማሸነፍ ዘወትር በመመካት በመግዛት በመቅጣት፥ ደስታ ኣይገኝም፤ ሌላ ይፈልጋል የሰው ልብ ኣይጠግብም። ለጥቅሙ የሚያስብ የተስገበገበ መንገዱን የማያቅ ግቡ የጠበበ፥ ስስታም ይሆናል፤ ለፍቶ ጥሮ ግሮ ሲያጋጥመው እድል፥ እረፍት ኣያገኝም፤ ሲስብ ሲጠነጥን ሲታትር ሲደክም። ኣንዱን በመጨረስ ወጥኖ ሌላውን ያንን በመሰልቸት ሲጀምር _ ኣዲሱን ያቅበዘብዘዋል ትእግስት ይነሳዋል። ትንሽ መሰናክል እሾህ መንገዱ ላይየኑሮው ህመም ነው የህይወቱ ስቃይ ያሲዘዋል እልህ ደሙን ኣስቆጥቶ ንዴቱን ኣምጥቶ። ይተዋል ይሉኝታን ከግቡ ለመድረስ ወዲያ ወዲህ ብሎ ሃይሉን እስኪጨርስ።
፡ "ሰው ወደ ቀደመው ዘመኑና ልጅነቱ ሲመለስ ወደ ማንነቱ ይቀርብ ይሆናል፡፡ ... ሁላችንም የሰው ልጆች ነን፡፡ ከዚያ የተለየ ማንነት ከየት ሊመጣ ይችላል፡፡" "አለመኖር"
፡ "ሰው በእድሜው ገንዘብ ፡ ፍቅር ፡ ዘመድ ፡ ጓደኛ በተለያየ ምክንያት ላያፈራ ይችላል፡፡ ግን ለዕድሜው የሚገባ ጥሩ ባህሪ መኖር ማንን ገደለ?" "ዙቤይዳ"
መቼስ ልብ የለኝም ልብ እንዳለው ስሆን መቼስ ነፍስ የለኝም ነፍስ እንዳለው ስሆን መቼስ ህዝብ የለኝም የጥንድ አልቃሽ ምሆን እና ምኑ ይገርማል እየኖርኩኝ እንኳ እንዳልኖርኩኝ ስሆን በትንንሽ ድምፆች አምላኬ በሚሉት ሶቆቃ ብቻ ነው ምእመን ሚያሰሙት በጨቅላ ህፃናት ቆመው በሚሰግዱት ጫንቃቸው ሞትን ነው ነጠላ ያረጉት ይሄ ሁሉ ምእመን ለአምላክ የሚነግረው ኑሮን አቅል ነው ወይ መሪን ቀንሰው እኔ ግን ደስታ ነው ላንተ የማቀርበው እኔ ስለት አለኝ ልሞት ስለሆነ ጥላ አለኝ ማስገባው ኑሮ በሚያስፈራው ዋይታ በደፈረው በጭንቅ ለቅሶ ድምፅ ዝምታ ይበላል ያለምንም ፍትህ ከኖረ እንደምስፅ አለም ትንሽ ገብታኝ ሀገር በደንብ ገብታኝ እኛሳ ስላልናት ስትጋረፍ አየሁ በምእመን ልጇ ጨካኝ ሁና እናት እናት በጨከነች አባት በደበቃት በግራ እግር ሀገር ሞት ቀጠሮ ማወቅ ደስታ ሆኖ ቀረ ተሳቆ ከማደር እናማ ጌታዬ በዚህ ሺህ ምእመን የጭንቅ መሃል ለቅሶ አንዲት ነፍስ አለች ደስታ ያፈነዳት የሞት ክሬም ልሶ ኗሪው በሚፈራት መሪው በሚንቃት በግራ እግር ሀገር፣ ሞት ቀጠሮ ማወቅ ደስታ ሆኖ ቀረ ተሳቆ ከማደር ፣ @geez_mulat ግዕዝ ሙላት
ሁሉም እያነሳ ብረት እና ዘገር ሰው ህግን ሲተካ ሂደት እርቃን ሲቀር ውጊያው ሁለት ሲሆን በነፍስና ፣ ሥጋ ምሽት አይኑን ከድኖ ቀንቶለት ያነጋ ይቅረብልን ባዋጅ ይዘገብ ፣ ይነገር ... ማሸነፍ ነውና ሰላም ውሎ ማደር!! (ሚካኤል አ)
“Can I go forward when my heart is here? Turn back, dull earth, and find thy centre out.” - Romeo and Juliet
без подписи
የተዘለለ የታሪክ ገጽ (በእውቀቱ ስዩም) ግዙፉ ጎልያድ፥ ያህዛብ ጀግና -አስገመገመ ዳዊትም ሰምቶ ፥ጎንበሰ አለና -ጠጠር ለቀመ፤ እናም በእለቱ ገበጣው ቀርቦ፤ ገጥመው ሁለቱ ከግድግዳው ላይ፥ ሳይወርድ ወንጭፉ ከየሰገባው፥ ሳይወጣ ሰይፉ ተሸናነፉ;; የቆፈሩትን፥ ጉድጓዱን ደፍነው የገበጣውን ፥ጠጠር በትነው ያወጁት አዋጅ ፥ አንድ ላይ ሆነው፥ ይሄ ነው ቃሉ ፦ “ የተከተልኸኝ ሰራዊት ሁሉ ዋንጫህን አንሳ ፤ጦር ጋሻህን ጣል የትኛው ሀገር የትኛው ሀሳብ ከህይወት በልጦ አንገት ያሰጣል?
የማይበርደው የራእይ ብርታት ተስፋ መቁረጥ በፍጹም ራእይን አያጠፋውም፣ የራእይ መጥፋት ግን ተስፋ መቁረጥን ያባብሰዋል፡፡ ብቸኝነት በፍጹም ራእይን አያደበዝዘውም፣ የራእይ አለመኖር ግን ብቸኝነታችንን ያጎላዋል፡፡ የሁኔታዎች መበላሸት ራእይን አያዳክመው፣ የራእይ መዳከም ግን የተበላሹ ሁኔታችን ጉዳት ጽኑ ያደርጋቸዋል፡፡ ስራ ማጣት በፍጹም ራእያችሁን አያሳጣችሁም፣ ራእይ ማጣት ግን ስራ እያላችሁ ዓላማ ያሳጣችኋል፡፡ ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍላችሁም፣ ራእያችሁን ለዩና እወቁ፡፡ የኋላ ኋላ መልሶ በእጥፍ ይከፍላችኋል፡፡ Dr.Eyob
"ብልግናዬ ላይ ትንሽ መርህ እና ርህራዬ አለበት መሰለኝ" አለ... ", ሴቶቹ ያሳዝናሉ።እምናገባቸው መስሏቸው፣ ከከተማ ሰው ጋር፣ መኪና ካለው ሰው ጋር ፣የተማረ ከሚመስል ሰው ጋር መተኛት ብርቅ መስሏቸው ይሆናል።ዐይናቸው ላይ ገዝፈንባቸው ለመቀላቀል ሲሽኮረመሙ ዐይቻቸዋለሁ። ልጅነታቸው ያሳዝናል።ለአንድ ቀን ፣ ለትንሽ ደቂቃ፣ ለስሜቴ ብዬ የቤት ልጆችን ሴተኛ አዳሪ የማድረግ ሂደት ላይ ላለመሳተፍ ...ድንገት ድንግል ከሆነች ክብሯን እንደዋዛ ላለመውሰድ ነው ባክህ። እንጂ አፍላ፣ትርፍርፍ ያላለ ገላ፣ያልቦረጨጨ ሆድ፣ትኩስ ገላ፣ ያልወረደ ጡት ማን ይጠላል ብለህ ነው" ብሎ ሳቀ።እኔ መሳቅ አልቻልኩም። በመኖር በኩል - ከአድኃኖም ምትኩ! ══════ @═════ @ ══════ @open_reading1 @open_reading1
ቅዳሜ ቀትር ላይ፡፡ ባለትዳሮች ቤት፡፡ እሷ- ዛሬ ቅዳሜ ነው፡፡ በዚያ ላይ ውጪ ከበላን ስንት ጊዚያችን! እስቲ ምሳ ጋበዘኝ? እሱ- ደስ ይለኛል፡፡ የት ልውሰድሽ? እሷ- እ…ታቦር ጋር ሸክላ ጥብስ ብንበላስ? እሱ- አሪፍ! በይ ቶሎ ልበሺና እንሂዳ..አርፍደን ደህና ስጋ እንዳናጣ፡፡ እሷ- እሺ…ማሬ…ከምሳ በኋላ ሌላ ቦታ ሄደን አሪፍ ቡና ትጋብዘኛለህ፡፡ እሱ- ታቦር ጋር ምን የመሰለ ቡና አለልሽ አይደል…? ሁሌ የምታደንቂው ቡና ከነጭሱ፡፡ በልተን ስንጨርስ እዛው ብትጠጪስ? እሷ- እሱማ አሪፍ ቡና አላቸው ግን ያው ከወጣን ላይቀር ቤት ቀይረን ትንሽ እንድንዝናና..ፈታ እንድንል ብዬ ነው… እሱ- አሪፍ ቡና ከፈለግሽ የምታውቂው ቦታ እያለ…ለዚያውም እዛ ምሳ እየበላን ለምን ሌላ ቦታ እንንከራተታን ብዬ እኮ ነው፡፡ እሷ- አንተ ደግሞ… አዲሳባ የጀበና ቡና እዚያ ብቻ ነው እንዴ ያለው..? ምን ችግር አለው ዞር ዞር ብንል…ትንሽ ንፋስ ቢመታን? እሱ- በዚህ ፀሃይ ንፋስ ነው ጸሃይ የሚመታን…?እንግልቱ አይበልጥም? እሷ-እኔ እኮ የሚገርመኝ… ለምንድነው ቀላሉን ነገር የምታወሳስበው…? እዚያ ምሳ በልተን ምናለ ሌላ ቦታ ሄደን ቡና ብንጠጣ…? ተሸከመኝ አላልኩህ…በራሴ እግር ነው የምሄደው…፡፡ እሱ- ሆይ ሆይ….እኔ አሁን እንደዚያ ወጣኝ..? በይ እሺ ቶሎ ልበሺና እንሂድ…ደስ እንዳለሽ እናደርጋለን፡፡ እሷ- ኤጭ! ተወው እንደውም እሱ- እንዴ…ምኑን የምተወው…? እሷ- ምሳውን…መውጣቱን… እሱ- እንዴ ለምን…? እሷ- ደግሞ ለምን ትለኛለህ…እየተነጫነጭክ ይዘኸኝ ከምትወጣ ቢቀርብኝ አይሻልም…? ይሻልሃል፡፡ እሱ- ኦኬ! ደስ እንዳለሽ…. እሷ- አየህ…ትንሽ እንኳን ልታባብለኝ ልታግደረድረኝ አልሞከርክም… እሱ- እንዴ! እሷ- አስሬ እንዴ እንዴ አትበልብኝ…መውጣት ካልፈለግህ መጀመሪያውኑ እምቢ…አልፈልግም አትልም… እሱ - -------- እሷ- በል ተወው…የትላንቱን ሹሮ አሙቄ እበላለሁ…ሰው ሲሸልስ ሄዶ ቢች ዳር ይጋበዛል ለእኔ የሰፈር ጥብስ አረረብኝ…. እርግማን አለብኝ መቼስ…አትዝናኚ…አትደሰቺ ..እርር እንዳልሽ ሙቺ የሚል… እሱ- ------- By Hiwot Emishaw