- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 22
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 12
- 1/48двое суток
- 13
- 1/72трое суток
- 14
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
❤️🤌
የምንድ ነው የታጠረ የወፍ ጎጆ ውስጥ ያለሽው? ምክንያቱም ስለማወራ።
"ብቻህን ለመቆም ተዘጋጅ፤ ልጅ፣ወንድም፣እህት፣ዘመድ..የሚባሉት ነገሮች የምቾት ጊዜ ጌጦች እና አጫፋሪዎች ናቸው።"
ከህይወቴ ያስወጣዋቸው ሰዎች ሁሉ የጠላኋቸው አይደሉም...but honestly? it's always about hate. አንዳንድ ጊዜ መንገዳችሁ ይለያያል፣ፍላጎታችሁ ይጋጫል No hard feelings,just different paths,በሰላም መለያየት እና "wish u a good luck"ብሎ መራቅ ትልቅ ብስለት ነው choosing yourself is never a crime.😌
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
👆የቀጠለ እኒኽም ቅዱሳን ይኽንን በሚነጋገሩበት ጊዜ በውስጡ አንገትን የሚቆለምም ልብንም የሚያቀልጥ ሆድን የሚሰነጥቅ ሥርን የሚበጣጥስ መሳሪያ ካለበት የብረት ጋን ውስጥ ጨመራቸው፡፡ ከዚህ በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወረደና የብረቱን ጋን እሳት አጠፋው፡፡ ከቅዱሳኑም አንዳቸውንም ሳያቃጥላቸው የብረቱ ጋር ማቃጠሉና መፍላቱ ጸጥ አለ፡፡ ወንድሞቻችን ሆይ እንግዲህ በጭንቃቸው ጊዜ ገድላቸውን እስኪፈጽሙ ድረስ ይህ መልአክ ከሰማእታትና ከጻድቃን ጐን እንደማይለይ እወቁ ለኃጥአንም ኃጢአታቸውን ይቅር ይላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ይጸልይላቸዋል፡፡ እኛም የዚህ የሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል በዓሉን እያከበርን አማላጅና ወዳጅ እናድርገው። በዚህም በሚመጣውም ዓለም ሊረዳን ይችላልና፡፡ ዳግመኛም መስፍኑ ሐሳቡ ሳይሳካለት ስለቀረ 14 የሾሉና የጋሉ የብረት ችንካሮች አምጥተው ሰባቱን በእናቱ በኢየሉጣ አካል ሰባቱን በራሱ በቂርቆስ አካል ማለት ሁለቱን በጆሮዎቹ ሁለቱን በዐይኖቹ ሁለቱን በአፍንጫዎቹ አንዱን በልቡ ይቸነክራቸው ዘንድ ጭፍሮቹን አዘዘ፡፡ ዳግመኛም የህፃኑን የእራስ ቆዳ ገፈው እሳት ውስጥ ይጨምሩ ዘንድ አዘዘ፡፡ አሁንም መልአኩ መጥቶ ይህንን መከራ ከእርሱ አራቀለት፡፡ ቀጥሎም በመቃን ውስጥ ጨምረው በገመድ እንዲጎትቱት አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ መልአኩ አዳነው፡፡ ሕዝቡም ይህንን ሁሉ ተአምር ባዩ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑት ቅዱስ ገብርኤልንም አከበሩት፡፡ ቅዱስ ቂርቆስና ቅድስት እየሉጣ ብዙ መከራ ከተቀበሉ በኋላ ጥር 15 በሰይፍ ተመትተው ስማትነትን ተቀብለዋል። የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል ፣ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት እየሉጣ ተራዳኢነት ጸሎት አይለየን። ከዚህ በኋላ ሕፃኑን አስፈልገው ቢጠይቁት ነቢዩ ዳዊት የተናገረው ኃይለ ቃል መንፈስ ቅዱስ ተገልጾለት፤ ‹‹የአሕዛብ ጣዖታት የወርቅና የብር የሰው እጅ ሥራዎች ናቸው፡፡ የሚታመኑባቸውም ሁሉ እንደ እነርሱ ይሁኑ›› መዝ. ፻፴ በማለት ሲዘልፏቸው አገር ገዥው ሰምቶ ተቆጣና የብረት ጋን አስመጥቶ ውኃ ሞልቶ ከዕቶን እሳት ላይ ጥዶ ልዩ ልዩ ማገዶዎች በመጨመር ነበልባሉ ከመጠን በላይ ሆነ፡፡ የብረት ጋኑም ድምፅ እንደ ክረምት መብረቅና ነጎድጓድ እስኪያስፈራ ድረስ አስነድዶ ሕፃኑን ከነእናቱ ወስዳችሁ ጨምሩአቸው ብሎ አዘዘ፡፡ በዚህ ጊዜ ቅድስት ኢየሉጣ በጣም ፈራች፡፡ የእግዚአብሔር ሥራ እፁብ ድንቅ ግሩም ረቂቅ ነው፡፡ ገና አፉን ያልፈታ የሦስት ዓመት ሕፃን ‹‹እናቴ ሆይ! ገድላችን እንፈጽም ዘንድ ጨክኝ በርቺ›› አላት፡፡ ቅድስት ኢየሉጣም ‹‹ልጄ የነፍስ አባት ሁነኝ›› አለችው፡፡ ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስም ከዘመናቸው ሳይደርስ፣ ታሪካቸውን ሳይማር የሠለስቱ ደቂቅን ታሪክ መንፈስ ቅዱስ ገልጾለት ‹‹አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል›› ቢላት ፍርሃቱ ሊለቃት ባለመቻሉ፣ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፡፡ ‹‹ጌታ ሆይ! የወይኑን ፍሬ ስትሻ ግንዱን ታጠፋለህን? እንደዚህስ ሁሉ እኔን አድነህ እናቴን ታጠፋታለህን?›› ብሎ በጸለየጊዜ መንፈስ ቅዱስ አደረባትና መንግሥተ ሰማያትን በዓይነ ሥጋ እንድታይ አደረጋት፡፡ ከዚህ በኋላ ፍርሃቱ ለቀቃትና ‹‹ልጄ ሆይ! ከዛሬ ጀምሮ መምህሬ፣ አባቴ፣ መካሪዬ እልሃለሁ እንጂ ልጄ አልልህም›› ብላ በጭካኔ ከልጅዋ ጋር ወደ ፈላው የብረት ጋን ገባችበት፡፡ በዚህ ጊዜ ሕፃኑ ቂርቆስ አናንያን፣ አዛርያንና ሚሳኤልን ያዳነ አምላክ ያድነናል ያለውን ቃል ለመፈጻም እግዚአብሔር አምላክ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው፡፡ መልአኩም በትእምርተ መስቀል እሳቱን ቢባርከው እንደ በረዶ ቀዝቅዞላቸዋል፡፡ በመልካቸውም እንደ ፀሐይ አበራ፡፡ ከእግር ጥፍራቸው እስከ ራስ ጠሩራቸው አንድም ሳይጎዳቸው በደህና ወጡ፡፡ በመጨረሻም ሕፃኑ ሰማዕት ቅዱስ ቂርቆስ እንዲህ አለ፡፡ ይህን ያህል ገድል ተጋድዬ ምን ዋጋ ትሰጠኛለህ ቢለው፣ ጌታ በልብህ ያለውን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው፡፡ ዳግመኛም ሥጋህ በምድር ላይ እንዳይፈርስ እንዳይበሰብስ በኤልያስ ሠረገላ ላይ አኖርሃለሁ አለው፡፡ ስለሆነም በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያናችን መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ለእናታችን ለቅድስት ኢየሉጣ እና ለሕፃኑ ለቅዱስ ቂርቆስ ያደረገውን ይህን ታላቅ ተአምር ድንቅ ሥራ በማሰብ ከዋዜማው ጀምራ እግዚአብሔርን ስታመሰግን ትውላለች ታድራለች፡፡ የመልአኩ የቅዱስ ገብርኤል በረከት ተራዳኢነት ከሁላችን ጋር ይኑር አሜን፡፡ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ሐምሌ 19 ቅዱስ ገብርኤል እንኳን ለታላቁ መልአክ ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ አደረሰን!!! በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት መሠረት ሐምሌ 19 የቅዱስ ገብርኤል አመታዊ በዓል ነው፡፡ ይህ ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት እየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት የሚታሰብበት ዕለት ነው። የሐምሌ 19 ስንክሳርና የሐምሌ ወር ድርሳነ ገብርኤል እንዲህ ተርከውታል፡፡ በዘመነ ሰማእታት ከሐድያን ነገሥታትና መኳንንት በክርስቲያኖች ላይ መከራ አጽንተውባቸው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙዎች ሰማእትነትን ሲቀበሉ የተቀሩት አገር ጥለው ተሰደዱ። እየሉጣም የሦስት ዓመት ህፃን የነበረውን ቅዱስ ቂርቆስን ይዛ ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኮንን አገኘችው ሰዎችም ነገር አሰሩባት ወደእርሱ አስቀረባት እና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኮንን ሆይ ዕድሜው ሦስት አመት የሆነው ህፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እሱን ጠይቅ አለችው፡፡ ህፃኑም ወዳለበት ጭፍራውን ልኮ ወደእርሱ አስመጣው ህፃኑም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ህፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው፡፡ ህፃኑም መልሶ አዎ ለኔ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ሐዘንና ለቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው፡፡ መጻሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏል እና አለው፡፡ እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስካስደነገጣቸው ድረስ ንጉሱን መኳንንቱንና ጣኦታቱን ረገማቸው፡፡ከብርታቱም የተነሳ አደነቁ፡፡ መኮንኑም በአፈረ ጊዜ በያይነቱ በሆነ ስቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ስቃይን አሰቃየው እናቱንም ከእርሱ ጋር አሰቃያት፡፡ እግዚአብሔርም ያለ ምንም ጉዳት ያነሳቸው ነበር፡፡ ብዙዎች አህዛብም ይኸንን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማእትነት አረፉ፡፡ የሰማእትነትንም አክሊል ተቀበሉ፡፡ በህፃኑም ላይ የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት፡፡ ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው፡፡ መስፍኑም በውስጡ ሰም፣ ጨው፣ ባሩድ፣ ሙጫ የዶሮ ማር፣ እርሳስ፣ ብረት፣ ቅንጭብ፣ ቁልቋል ጨምራችሁ ታላቅ የብረት ጋን አንጡልኝ ብሎ ጭፍሮቹን አዘዛቸው፡፡ ጭፍሮቹም እንዳዘዛቸው ካአደረጉ በኋላ ያዘዝከንን ሁሉ ፈጽመን እሳቱ ነዶ ፈልቷል፡፡ ድምፁ እንደነጐድጓድ ይጮኸል ወላፈኑም እንደጸሐይ ነጸብራቅ በሩቁ ይጋረፋል፡፡ የፍላቱም ኃይል በ14 ክንድ ያኽል ከፍታ ወደ ላይ ይዘላል፡፡ እንግዲህ በውስጡ የሚጣሉትን እዘዝ አሉት በዚህ ጊዜ ህፃን ቂርቆስና እናቱ እየሉጣ በክርስቶስ ስም ስለሚያምኑ አስረዋቸው ነበርና ከፍላቱ ሊጨምሯቸው ከእስር ቤት አወጧቸው፡፡ በዚያም ፍላቱ ወደላይ በሚዘል ብረት ጋን ውስጥ ለመጨመር ሲወስዷቸው የነዚህን ቅዱሳን አሟሟት ያዩ ዘንድ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው፡፡ በዚህን ጊዜ ቅድስት እየሉጣ የፍላቱን ጩኸት በሰማችና ባየች ጊዜ ተሸበረች፡፡ ተዘጋጅቶላት ከነበረው ክብር ልታፈገፍግ ሞከረች፡፡ ልጇ ቅዱስ ቂርቆስ ግን እናት ሆይ ከዚህ የብረት ጋን ግርማ የተነሳ አትፍሪ ድንጋጼም አይደርብሽ አናንያንና አዛርያን ሚሳኤልንም እግዚአብሔር ከእቶነ እሳት እንዳወጣቸው ሁሉ እኛንም ከዚህ ከብረት ጋን ሊያወጣን ችሎታ ያለው መሆኑን አትጠራጠሪ፡፡ እናት ሆ ከዚህ ከሚያልፈው ዓለም ጭንቅና መከራ ለመዳን ስትይ በማያልፈው ዘላለማዊ እሳት ለመቀጣት ትመርጫለሽን ይኽስ አይሆንም ይቅርብሽ፡፡ በአሁኑ ጊዜ እግዚአብሔር በመካከላችን አለና ይረዳናል፡፡ እናት ሆይ ሶስናን ከእደ ረበናት /መምህራነ አይሁድ/ ዳንኤልን ከአፈ አናብስት ያዳነ እርሱ እኛንም ከጋን ፍላት ያወጣናል፡፡ ይልቁንም እግዚአብሔር በዚህ የብረት ጋን ውስጥ ግዳጃችንን ልንፈጽም ፈቅዶ ከሆነ ኢዮብ ንብረቱንና ገንዘቡን ልጆቹንና ሚስቱን በመጨረሻም የተፈጥሮ አካሉን ባሳጣው ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግነዋለሁ እግዚአብሐር ሰጠ እግዚአብሔር ነሳ እግዚአብሔርም እንደወደደ አደረገ ከማለት በስተቀር ምንም የተናገረው ነገር እንደሌለ ሁሉ እኛም የሱን ዓላማ በመከተል ይኽንን መከራ ልንታገስ ይገባናል፡፡ ነገር ግን እናቱ በዚህ ምክር ልትጽናና ባለመቻሏ ቅዱስ ቂርቆስ ዐይኑን ወደ ሰማይ አቅንቶ አቤቱ አምላክ ሆይ ይችን ባሪያህን ከርስትህ የምትለያት ከሆነ ከባለሟልነትህ መጽሐፍ ፋቀኝ፤ አቤቱ አዝመራውን አቃጥለ ፍሬውን ልትባርክ ትወዳለህን ይኽን እንዳታደር ግን ቸርነትህ ትከለክልኸለች አቤቱ እንጨቱን ቆርጣችሁ አንድዱት ቅጠሉን ግን ጠብቁት ብለኽ ልታዝ መለኮታዊ ባሕሪህ አይደለም፡፡ ነገር ግን እንጨቱንም ቅጠሉንም በአንድ ጠብቁት ብለኽ ታዝዛለኽ እንጂ፡፡ እንግዲህ በዚህ ምክንያት ይኽንን ያየ ሁሉ ማዳን የሚችል አምላክ ቢኖራቸውስ ኖሮ ከእሳት ባልሸሹም ነበር ብሎ አይጠራጠር፡፡ አቤቱ ዲያብሎስም ከባለስልጣኑ ይልቅ እኔ በረታሁ ቅዱሳኖቹንም ድል ነሳኋቸው ብሎ እንዳይመካ ከመንጋውም አንድ በግ ቀማው በማለት እንዳይደነፋ ለእናቴ ጽኑ የሆነ ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ስጣት ብሎ በጸለየ ጊዜ ዲያብሎስ ከእየሉጣ አጠገብ ብን ብሎ ጠፋ፡፡ ከዚህ በኋላ ቅድስት እናቱ በሰማያዊ መንግሥት አባት የሆንከኝ ልጄ ሆይ ጌታኽ ኃይልን ሰጥቶኛልና የሚጠብቀንን ገድላችንን ፈጽመን ድል እናድርግ እነሆ በብረት ጋን ውስጥ የሚነደውን እሳት በማይበት ጊዜ በለምለም /በምንጭ/ ላይ እንደሚወርድ ጠል ሆኖ አይቸዋለሁና አለችው፡፡ 💚 @ortodoxmezmur 💚 💛 @ortodoxmezmur 💛 ❤️ @ortodoxmezmur ❤️
ያልተኖረ.... አንዳንዶች መኖር እንደእነ እከሌ መስሎን ያልኖር ን ይመስለናል።እንደ እነሱ አለመሆንን ከህይወት እንደ መጉደል እንቆጥራለን።እንደ አነሱ መኪና አለመግዛትን:እንደ እነሱ አይነት ውብ ቤት ውስጥ አለመኖርን፣እንደ እነሱ በአለም አህጉራት ላይ እየዞርን ብርጭቆ አለማጋጨትን፣እንደ እነሱ brand አለመልበስ አለመዋብን ባሰብን ቁጥር እኛ እየኖርን አይመስለንም። እንደ እነሱ እንጂ እንደ እኛ የለንም።የመጨረሻ እንጥፍጣፊ ተስፋችን እንደ እራሳችን መኖር ሳይሆን በአለም ላይ እንደተሳካላቸው ሰዎች መኖር ነው። ዘለአለም ጥላ መሆን።የሆነን አካል መከተል።የመምራት ሀይላችንን የቀማን የሆነ ሀይልማ አለ። እስኪ እንደ እራሳችን እንኑር። እኛ ያልተቀበልነውን የራሳችን ማንነት ማንም አይቀበለውም።አንተ ያልተቀበልከውን ማንነትክን ማንም አይቀበለውም።አንቺ ያላከበርሽውን ሴትነትሽን ማንም አያከብረውም። የራስሽን ዘመነ ፍዳ ከመገንባት ውጪና እንደ እራስሽ ደስተኛ ሁኚ።የአለም ትልቁ ስኬት መኪና እና ቤት አይደለም።የአለም ትልቁ ስኬት ዝና እና ቅራቅንቦ ማካበት አይደለም።የአለም ትልቁ ስኬት የምታያቸው ባለ ብዙ ተከታይ ሰዎች ደረጃ ላይ መድረስ አይደለም ወይም ምሁር መሆን አልያም ማግባትና መውለድ አይደለም። የዓለም ትልቁ ስኬት በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ አለመረበሽ እና አለመደንገጥ ነው።በምንም ሁኔታ ውስጥ ደስቸኛና አመስጋኝ መሆን ነው። ችግሩ ለማመስገንም የሆኑ የሆኑ ቁሳቁሶች ሊኖሩን እንደሚገባ ነው የምናስበው።በባዶ መደሰት ምን ሊረባኝ ይላሉ አብዛኞቹ። በዚህ ጊዜ ለተሰጠክ ነገር ማመስገን ካልቻልክ ነገም ወርቅ ላይ ተኝተክ በቃኝ የማትል ስግብግብ እንደሆንክ ትሞታለክ።🙅♀️ ብዙ ነገር ኖሯቸው አንተ ያለክበትን ደስታ ያላገኙ ሰላም ያላገኙ ወርደው ህይወትክን እንደሚመኙት አትርሳ። ክርስቶስ በምድር ሳለ ላልቀያየረው ልብስ አንቺ ከእሱ በልጠሽ ነው የሌለሽን ቡቱቱ በመናፈቅ ደስታሽን የምታጪው?፤ክርስቶስ በምድር ሲኖር ቤት አልነበረውም።አንተ ግንብ በመመኘት አመስጋኝነትን ትተህ ማማረር ላይ የተጠመድከው ከእሱ በልጠክ ነው? ለመደሰት የሚያስፈልግህ የመጨረሻው ነጥብ ሀብት ከመሰለክ አይደለም።የሆነ ያክል ልትደሰት ትችል ይሆናል ባሰብከው ልክ ግን አይሆንም። ጎድለክም ሳለክ ሙሉነት እንዲሰማክ ከፈለክ እንደ እነሱ ማለት ትተክ እንደ አንተ እንደ እራስክ ተደሰት።ጊዜክን አታባክን። ✍️Giya Join & Share @FreamaHasaboch @FreamaHasaboch @FreamaHasaboch
видео или голосовое, без подписи
ነጭ ውሸት '''''''''''''''''''''''''''''''' ከእነ ዝባዝንኬው ወሬ አይታመንም።ሙሉውን አዳምጪ መርጠሽ እመኚ ትለኝ ነበር ጓደኛዬ። በቅርቡ የሆነ ሰው የሆነ ቦታ ተዋውቄ ነበር።ግርማ አለው ሞገሱን ማን እንደወሰደበት ባላውቅም። መንቀዥቀዥ ያበዛል።እኔ ደሞ መንቀዥቀዥ በሴት ነው የሚያምረው ከሚሉት ወገን ነኝ። ጥሎብኝ ብዙ የሚያወራ ወንድም አልወድም።እሱ ደግሞ ብዙ ከማውራቱ አልፎም ወሬው በሙሉ በሬ ወለደ ነው። እጅ እጅ አለኝ።ሰው እንዴት በዚህ ልክ ይዋሻል! አብሬው ልሆን ቀርቶ አልፎ አልፎ እንኳ ላገኘው የማልፈልገው አይነት ሰው ነው። ኤጭ! ምነው ሸዋ።ወንዱ ሁሉ ምን ነካው?! ✍️Giya @FreamaHasaboch
видео или голосовое, без подписи
ሀዘኗ --------- ጥሩነትን ከማን ልማር?የክፋት በር ''ሀ'' ተብሎ በእኔ ባይከፈትም ለእኔ አለመከፈቱን ግን እርግጠኛ መሆን አልቻልኩም። ሰዎች ውሎዋቸውን ይመስላሉ ይባላል።እኔ ከየቱ ደግ ጋር ውዬ የቱን ልምሰል?የእናቴን ርህራሄ አልበኝነት አለመውረስ ይቻላል?፣የአባትን መጥፎነት መሸሽ ይቻላል?፣የወንድሞችን የምት ቁስል በምን አክሜ ልርሳና ደግ ልሁን?? አንቺ አይገባሽም አለችኝ አምባ ካቀረሩት አይኖቿ ጋር እየታገለች። እውነትም መጥፎ ነሽ እንስከምላት እየተጠባበቀች ይመስላል። ንግግሯን ግን ቀጠለች... በአባትሽ ተገርፈሽ እንጂ ተረግጠሽ ከቤት ተባረሽ አታውቂም።በእናትሽ ተመክረሽ እንጂ ባልተወለድሽ ተብለሽ መፈጠረሽ አልተጠላም።ገደል ግቢ ተብለሽ እንደ አሮጌ ፔስታል መንገድ ዳር አልተጣልሽም።በቤትሽ እንጀራ ከሻገተ አትበይም ፣መሬት ከነካ ትፀየፊያለሽ።ከውሻ አፍ ነጥቀሽና ተጋፍተሽ የመብላት ስሜቱን አታውቂም።ታመሽ መድሀኒት ትወስጂያለሽ፤ታሞ መራብን አታውቂውም።ሲዘንብ አልጋሽ ውስጥ ነሽ፤በበረዶ እየተመቱ ማደርን አታውቂም።ሰርቀሻል ብትባዪ ዋስ የሚሆንሽ ብዙ ነው፤እንደ እኔ ጠሪ አታጪም😢ሰው 'ርቦሽ አያውቅም ይሄ ላንቺ አይገባሽም። ለዚህ ነው የወደቀን የማላነሳ ጨካኝ የሆንኩት።ከየት ያየሁትን ፍቅር ላስተጋባ?🥺 ምራቋን ውጣ ዝም አለች።ከንግግሯ ይልቅ ዝምታዋ ያስፈራኛል።አንዳች መጥፎ ነገር የምታሰላስል ይመስለኛል። ግን እኮ እውነቷን ነው........... (✍️Giyanna) Join & Share @FreamaHasaboch
ውበት ማነው አሉኝ እሱነው አልኳቸው ፍቅር ማነው ሲሉ አንተን ጠቆምኳቸው እምነትን ጠየቁ እኔም ነገርኳቸው አንተን በምልክት እያሳየኋቸው ውበትም እምነትም ፍቅርም መሆንክን ማን በነገራቸው!። ✍️Giya Join & Share @Myppoem @Myppoem
"ዶሮ አማረኝ" ሲሉ ሁሉንም እንዳልሆነው ነው የምትናፍቀኝ....አለ አይደል አንድ የዶሮ ብልት በልተው እንደሚያስጠላቸው አይነት....ፈረሰኛውን በልተው መረቁን "ሽንኩርት ምን ያደርግልናል" ብለው ለኔ ቢጤ እንደሚያከፋፍሉት አይነት.... ያንተ ናፍቆትም እንዲህ ነው.... ጣዕምህም እዚህ ድረስ ነው.... እንደ ዶሮው.... ጥቅም አልባ መረቅ እንደሚበዛው ዶሮ ነው ያንተ መልክ.... ሊበሉት አሰፍስፈው እንደሰፈሩበት ቅባታማ ጥብስ....ጥቂት በልተውት ብዙ እንደሚዘጋ.... ሙሉውን አትናፍቀኝም....ጉርሻህ ብቻውን ይናፍቀኛል....በእጄ መጉረስ ሲያንገሸግሸኝ እንደናፈቅከኝ ይሰማኛል....መለስ እልና ደግሞ 'ጉርሻ ለይቶ መናፈቅ ምንድን ነው' እላለሁ.... "እሱ አልናፈቀሽም....Act of service ነው የናፈቀሽ....".....ያለችኝ ጓደኛዬን ላምናት ጫፍ እደርሳለሁ.... (ልክ ልኩን ነገርኩት😁) ✍Shewit https://t.me/shewitdorka https://t.me/shewitdorka https://t.me/shewitdorka
እንክርዳድ መሀል የበቀለ ስንዴ ቢሸፈንም እንክርዳድ አይሆንም።🙅♀
አለም ዘጠኝ ናት አትሞላም አስር ብዬ የማይሆኑ ሰዎችን ጭቃ እንደነካው ጫማ ማሽቀንጠር ከጀመርኩ ቆየሁ። ያኔ ታዲያ ሰው እንደ ሁለት መቶ ብር እንደማይበረክት ገባኝ።ለመዘርዘር ፣ለመመንዘርም ጭምር የሰው ልጅ ከሁለት መቶ ብር ይፈጥናል። ለካስ ጓደኛ አርጌ ያቆየኋቸው ጓደኛ አልነበሩም።እኔ ለእነሱ እንጂ እነሱ ለእኔ መሆን አይችሉም ነበር። ይሄ ሲገባኝ ግን አልረፈደም።እናም በእሾህ ዳር እንደበቀለ ቁልቋል በእነሱ እያለቀሱ መኖር አንገሽግሾኝ ከእራሴ ለየኋቸው።ያለምንም ነፃ አውጪ ድርጅት ነፃነቴን አወጅኩ። አንዳንድ ሰዎች እንደ ማስታወቂያ ነው ወደ ህይወታችን የሚገቡት።ሳናስበው ይመጣሉ፣በሁለተኛው ደቂቃ ይጠፋሉ።ይመጣሉ ይሄዳሉ። ሲመጡ መቀበል ሲሄዱ መሸኘት ሰውኛ ግዴታ አይደለም።ልባዊ ትዕዛዝ እንጂ። እና ምን ለማለት ነው ህይወታችሁ ውስጥ ብቅ ጥልቅ እያሉ የሚረብሿችሁን ሰዎች ቻው ለማለት ጊዜ አትውሰዱ። ከስንብቱ በኋላ የነፃነት ቀናችሁን አክብሩ።🤜🤛 ✍️Giya @FreamaHasaboch @FreamaHasaboch
https://kiosk.market?affiliate_keyword=wOgkpTVj