ኤል- ቤቴል ሰ/ት/ቤት Official Chanal
СтатистикаበዚህChannel በፉሪ ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ እና በሌሎች የሚከናወኑ መንፈሳዊ አገልግሎቶች እና መረጃዎች በአጥቢያው ለሚገኙ ምእመናን እና የቤ/ክ ጉዳይ ይመለከተኛል ለሚሉ ምእመናን መልእክት እና አዳዲስ መረጃዎች የሚተላለፋበት ነው።
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 14
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 66
- 1/48двое суток
- 75
- 1/72трое суток
- 81
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
‛‛ትዕግስት ማለት መከራን መሸከም ብቻ ሳይሆን፥ በመከራ ውስጥ ሆነው ለሚያሳድዱህ መጸለይ ነው።’’ ✍️ቅዱስ ፖርፊሪዮስ
‛‛ትዕግስት ማለት ችግርን ዝም ብሎ መቀበል ብቻ ሳይሆን ችግር ውስጥም ሆኖም ፈገግ ማለት ነው።’’ ✍️ቅዱስ ዮሐንስ ዘሰላልዊ
"ሁለትን ነገር ከአንተ እሻለሁ፥ ሳልሞትም አትከልክለኝ፤ ከንቱነትንና ሐሰተኛነትን ከእኔ አርቃቸው፤ ድኅነትንና ባለጠግነትን አትስጠኝ፤ ነገር ግን የሚያስፈልገኝን እንጀራ ስጠኝ" ምሳ 30÷7-8
"ጠላቴ ሆይ ብወድቅ እነሳለሁና በጨለማ ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሀን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልህ" ። ሚክያስ 7፥8
"እግዚአብሔር እንደሚያይህ፣ እንደሚያደምጥህና ስለአንተ በፍቅር እንደሚጨነቅ እመን። የአንተ ቲኒኒሽ ጉዳዮች በፍቅሩ ፊት ትልቅ ናቸው፥ አንተን ሚያሳስቡህ ትልልቅ ጉዳዮች ደግሞ በፍጹም ኃይሉ ፊት ከቶ ምንም አይደሉም።" ቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ፮ተኛ የተናገሩት
"ስለ ሌላው ሰው ከመፍረድህ በፊት፣ በእርሱ ጫማ ውስጥ ገብተህ ለመራመድ ሞክር። ያኔ መፍረድ ትተህ መጸለይ ትጀምራለህ።" አባ ሙሴ ጸሊም
“እያንዳንዱ የባለንጀራውን ጥቅም እንጂ አንድ ስንኳ የራሱን ጥቅም አይፈልግ።’’ ✍️1ኛ ቆሮንቶስ 10፥24
"እግዚአብሔር በተነሣ ጊዜ ምን አደርጋለሁ ? በጎበኘኝ ጊዜ ምን እመልስለታለሁ ?" ኢዮብ 31÷14
"አንተ ባትረዳኝስ ማን ይረዳኛል? አንተ ባትጠብቀኝስ ማን ይጠብቀኛል? የሰው ረድኤት ከንቱ ነውና።" አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ (መጽሐፈ ሰዓታት)
"ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ወድቆ በሚለምነው ነዳይ ውስጥ ካላገኘኸው ውስጥ ገብተህ በመንበሩ ላይ ባለው ጽዋ ላይ አታገኘውም።" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ከእንቅልፌ ስነቃ ፈጥኜ ወደ አንተ አንጋጥጣለሁ አቤቱ የሰው ሁሉ ወዳጅ የሆንክ ጌታ በአንተ ፍቅርና ደግነት ወደ አንተ ለመጸለይና መንፈሳዊን ሥራ ለመሥራት እጥራለሁ።በሁሉም ጊዜ በማንኛውም ነገር እርዳኝ ከማንኛውም ከዓለም ክፋ ሥራና ከዲያብሎስ ጥቃት ሁሉ አውጣኝ ፤ወደ ዘላለማዊዉ መንግሥትህ ምራኝ ።አቤቱ ፈጣሪዬ አንተ የማንኛውም መልካም ነገር ሁሉ ምንጭ ነህና ፤ተስፋዬ ሁሉ በአንተ ላይ ነው።አቤቱ ለአንተ ምስጋና አቀርባለሁ ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።" ጸሎተ አባ መቃርዮስ
"አቤቱ ጌታዬ በጥልቁ ቸርነትህ ታላቅ ርኀራኄን አድርግልኝ።እኔ ባሪያህን ከማንኛውም ከሰይጣን ፈተናና ተቃውሞ ጠብቀህ ይህን ሌሊት በሰላም አሳልፍልኝ።አቤቱ የሁሉ ፈጣሪና ጌታ የሆንክ በብሩህ ልቦና የአንተን ፈቃድ አደርግ ዘንድ እውነተኛውን ብርሃን ስጠኝ። ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።" ጸሎተ አባ መቃርዮስ
“አንተ ሰነፍ ባሪያ መክሊቴን በጊዜ ልትሰጠኝ በተገባህ ነበር እኔም ወጥቶ ወርዶ ለሚያተርፍ በሰጠሁት ነበር”፡፡ ኑ የዚህን ሀኬተኛ መክሊት ውሰዱና አስር መክሊት ላለው ስጡት፡፡ ላለው ይሰጡታል ይጨመርለታል ለሌለው ግን ያለውን ይቀሙታል፡፡ ኑ ይህን ሰነፍና ሃኬተኛ ባሪያ እጅ እግሩን አሥራችሁ ጽኑዕ ጨለማ ወደአለበት ውሰዱት ጩኸትና ጥርስ ማፋጨት ወዳለበት ጨምሩት” ማቴ. 25፥14-25፡
“ወደ ቤተ ክርስቲያን መጥተህ እግዚአብሔርን ለአምላክነቱ እንደሚገባ አምልከህ ከዚያ በኋላ ወደ ሥራህ ብትሔድ የምትሠራው ሥራ የተባረከና የሰመረ እንደሚሆንልህ አታውቅምን?" ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"ሰው ወደ ኃጢአት በተራመደ መጠን ሃሳቡ ደካማ ይሆናል። ወደ ኃጢአትም ያዘነብላል። በውስጡም ለኃጢአት ሥፍራ ያዘጋጃል። ተጨማሪ እርምጃ በተራመደ ቁጥር በልቡ ውስጥ የነበረው ፍቅረ እግዚአብሔር ይቀንሳል። መውደቁም ግልጽ እየሆነ ይሄዳል። ስለዚህም በመጽሐፍ "አንች ወራዳ የባቢሎን ልጅ ሆይ ሕፃናቶችሽን ይዞ በዓለት ላይ የሚፈጠፍጣቸው የተመሰገነ ነው" ተብሏል። (መዝ. 136፥8-9) የባቢሎን ልጅ (የምርኮ ሀገር) የተባለ ኃጢአት ነው። ልጆች የተባሉት ፈቃዳተ ኃጢአት ናቸው። እነዚህን ልጆች የተባሉ ፈቃዳተ ኃጢአት የሚፈጠፍጣቸው ዓለት የተባለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። (1ቆሮ. 10፥4) ስለዚህ ኃጢአትንና ፈቃዳቱን ሁሉ በክርስቶስ አጋዥነት የሚቋቋምና በአእምሮው ሲታሰብ ጀምሮ ኃጢአትን የሚጠላ ሰው ብፁዕ ነው።" አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
"ኃጢአት ለመሥራት ቀጠሮ ትይዛለህ፤ ጽድቅ ለመሥራት ግን ጊዜ የለኝም ትላለህ፡፡ ጓደኛህን ለማግኘት ጊዜ አለህ፤ ንስሐ አባትህን ለማግኘት ግን ጊዜ የለህም፡፡ በሥጋ ስትራብ ከየትም አምጥተህ (ለምነህም ቢኾን) ትበላለህ፤ ነፍስህ የክርስቶስ ሥጋ ከራባት ግን ዘመናት ተቆጠሩ፡፡ ወዳጄ ሆይ! እባብ አሳተኝ ያለችውንና፥ ከፍርድ ያላመለጠችውን ሔዋን ታስታውሳለህን? እንግዲያውስ፥ አንተም እንደ እርሷ ምክንያት በመደርደር ራስህን ለማጽደቅ አትሞክር፡፡ ይህ ሲነገርህም በተግባር እንጂ በከንፈርህ መልስ ለመስጠት አትጣር፡፡" (መቅረዝ ዘተዋሕዶ የተወሰደ)
“የባለንጀራህን ሸክም ተሸከም ያን ግዜ የክርስቶስን ሕግ ትፈፅማለህ።’’ ✍️አባ ዞሲማስ
“ክፋትን በክፋት አትመልስ፣ ጨለማን በጨለማ ማጥፋት አይቻልምና።’’ ✍️ቅዱስ አውግስጢኖስ
"የግርፋት ቁስል መግል ይይዛል የአንደበት ቁስል ግን አጥንትን ይሰብራል።" ሲራ 28÷17
“መቆጣት ወይም መበሳጨት በጀመርክ ጊዜ ስሜትህን ተቆጣጠር ምላሳህንም ግታ የፊት ግፅታህንም ሆነ እንቅስቃሴህን ሁሉ ተቆጣጠር። ምንም ያህል ቢበድሉህ እንኳ አንተ ግን ሌላውን ለመበደል ፍቃድ አትስጥ።’’ ✍️ብፁዕ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ