G-Tutorialclass
описание
Impossible is possible with learning & reading.
Лучшие посты
за три месяцаውጤትዎን ይመልከቱ! 📄 ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም ከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ✅ ውጤትዎን ለማየት 👇 https://result.ethernet.edu.et ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'Exit Examination' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ። 📝🔍
gro-evergreen-share-content https://www.binance.com/referral/earn-together/refer2earn-usdc/claim?hl=en&ref=GRO_28502_QE3WJ&utm_source=referral_entrance&utm_medium=app_share_link_telegram Get free Payment here.
#በአማራ ክልል የ2018 #የትምህርት ዘመን #የ8ኛ ክፍል #ክልላዊ ፈተና #ውጤት ይፋ ሆነ። በአማራ ክልል የ2018 የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ክልል #አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል። ከሰኔ 3-5/2018ዓ.ም ለተከታታይ ሶስት ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት በቴክኖሎጅ ታርሞ ይፋ የተደረገ ሲሆን በክልሉ 173699 ተማሪዎች ፈተናውን መውሰዳቸው ይታወቃል። ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች መካከልም 135003(77.72%)ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት አስመዝግበዋል። ተማሪዎችም ውጤታቸውን በሁለት አማራጮች ማየት የሚችሉ ሲሆን:- 🔴 በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ 1) ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ 2) በሚመጣው ቅጽ (form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት 3) ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡ 🔴 በተጨማሪም @emacs_ministry_result_qmt_bot በሚለው የቴሌግራም ቦት ላይ በመግባት ተማሪዎች ውጤታቸውን መመልከት የሚችሉ ሲሆን መጀመሪያ 1) start የሚለውን ይጫኑ! 2) በመቀጠልም ክፍልዎን ይምረጡ 3) ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ 4) በመቀጠል የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ። ተማሪዎች ማንኛውም ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ካላቸው ቅሬታ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ይችላሉ። ቅሬታቸውንም ለማቅረብ 🔴 በኮምፒውተር ወይም ስልካቸው ላይ ባለዉ የድር መፈለጊያ መተግበሪያ ( Web browser Application ) ላይ 1) ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች https://amhara.ministry.et/#/complaint የሚለውን አድራሻ በመፃፍ 2) በሚመጣው ቅጽ(form) ላይ የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) እና የተማሪውን የመጀመሪያ ስም (First Name)በማስገባት 3) የትምህርት ዓይነት አሳይ(Fetch course) የሚለውን ቁልፍ በመጫን 4) ቅሬታ ማቅረብ የሚፈልጉበትን ይምረጡ 5) በመጨረሻም ሪፖርት (Add Complaint) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ቅሬታቸውን ማቅረብ ይችላሉ። 🔵ማስታወሻ ፡ በቅድሚያ ቪፒኤን ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡ ⚛ 2018ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ ይደረጋል። ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
ተጨማሪ መረጃ‼️ ዛሬ ነሐሴ 4/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት አካባቢ በራያ አላማጣ ወረዳ በመረዋ ንዑስ ወረዳ የተፈፀመው የድሮን ጥቃት በአራት ዙር መሆኑን የአካባቢው ምንጮች ገልፀውልናል። እንደ የአካባቢው ምንጮች ገለጻ፣ ጥቃቱ:- 📌በመረዋ 2ኛ ደረጃ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተሰበሰቡ ታጣቂዎች ላይ ▪️📌በችግኝ ጣቢያው አካባቢ በተሰበሰቡ ታጣቂዎች ላይ ▪📌ከቤተ-ክርስቲያን አለፍ ብሎ ባለው ዋርካ (ዳዕሮ) ዛፍ ስር በተሰበሰቡ ታጣቂዎች ላይ 📌ሚይ ሓርማዝ በሚገኙ ተሽከርካሪዎች ላይ ነው የተፈፀመው። ጥቃቱ በአራት ዙር የተፈፀመ ሲሆን ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ታጣቂዎች ተሰውተዋል። የተጎዱ ታጣቂዎች ደግሞ ወደ አላማጣ ለህክምና ተወስደዋል። መረዋ አካባቢ በሚገኝ በአንድ የቤተክርስቲያን ዋሻ ውስጥ የህክምና አገልግሎት መስጫ አዘጋጅተው ነበር ተብሏል። Please Strive for👉🕊🕊🕊🕊🕊 ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇 @Gtutorialclass @Gtutorialclass
የመሬት መንቀጥቀጥ‼️ በዛሬዉ እለት በመተሃራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ ነበር። በዛሬዉ እለት ምሽት 2 ሰዓት ከ 11 ደቂቃ ላይ በመተሃራ አካባቢ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ዳጉ ጆርናል ሰምቷል። የመሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.6 የተለካ መሆኑን ቮልካኖ ዲስከቨሪ የተሰኘዉ የመሬት መንቀጥቀጥ እና የእሳተገሞራ ፍንዳታዎችን የሚከታተል ተቋም በገጹ አሳዉቋል። የመሬት መንቀጥቀጡ በአዲስአበባም አንዳንድ ቦታዎች ላይ ተሰምቷል። ===================== 💎⬇👇👇👇👇👇👇👇 የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇 @Gtutorialclass
የኤሌክትሪክ ኃይል አዲስ ኃይል ማስገቢያ የዱቤ ክፍያ ወለድ ሙሉ በሙሉ ተነሳ። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አዲስ ኃይል ማስገቢያ ክፍያን በዱቤ ለሚከፍሉ ደንበኞች ይጠየቅ የነበረውን ከ3 እስከ 9 በመቶ የወለድ ክፍያ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንጅነር ጌቱ ገረመው አስታወቁ። ቀደም ሲል የዱቤ ክፍያ ጊዜው እስከ 24 ወራት ሲሆን፣ ከ6 ወራት በላይ ለሚቆይ ክፍያ ወለድ ይጣል ነበር። አሁን ወለዱ መነሳቱ ክፍያውን በአንድ ጊዜ መፈጸም ለማይችሉ ዜጎች የምስራች መሆኑንና አገልግሎቱን ይበልጥ ተደራሽ እንደሚያደርግ ገልጸዋል። በተጨማሪም ከሰኔ 2018 ዓ.ም. ጀምሮ በተጀመረው የአዲስ ቆጣሪ የዱቤ አሰራር በሁለት ሳምንታት ብቻ 19,231 አዳዲስ ደንበኞች ኤሌክትሪክ ማግኘት ችለዋል። ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት 664,505 አዳዲስ ደንበኞችን ያገናኘ ሲሆን፣ በ2019 ዓ.ም. ደግሞ 1.1 ሚሊዮን አዳዲስ ደንበኞችን ለማገናኘት አቅዷል። ኢንጅነር ጌቱ እንደገለጹት፣ አገልግሎቱ በ70 ዓመታት ታሪኩ 5.88 ሚሊዮን ደንበኞችን ማገናኘት ችሏል፤ አሁን ግን በዓመት እስከ 1 ሚሊዮን ደንበኞችን የማገናኘት አቅም ላይ ደርሷል። ነሐሴ 4 ቀን 2018 ዓ/ም @Gtutorialclass
ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የ11 የሥራና ተግባር ትምህርት የሙያ አይነቶችን ዝርዝር አሳውቋል። በአዲሱ የትምህርትና ሥልጠና ፓሊሲ ላይ "የሙያና ቴክኖሎጅ ትምህርት ከቅድመ አንደኛ ደረጃ ጀምሮ ከእድሜያቸው ጋር የተመጣጠነ ሆኖ እንዲሰጥ ይደረጋል" በሚል አቅጣጫ መቀመጡን ያመለክታል። በዚህ መሰረት በየደረጃው የሥራና ተግባር ትምህርት ከሌሎች ትምህርቶች ጋር ተቀናጅቶ እንዲሁም 7ኛ እና 8ኛ ክፍል ራሱን ችሎ ተማሪዎች በቀጣይ የሚፈልጉትን ሙያ እንዲመርጡ በሚያስችል መልኩ እየተሰጠ ይገኛል ብሏል፡፡ ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ደግሞ በሁለተኛው ዙር እንዲተገበሩ ለተለዩት 11 የሙያ አይነቶች ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል መርሐ ትምህርቶች እንዲሁም ለ11ኛ ክፍል የተማሪ ሞጁሎችና የመምህር መምሪያዎች ዝግጅት ማጠናቀቁን ገልጿል። በመሆኑም እነዚህን ተጨማሪ የሙያ አይነቶች ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በ11ኛ ክፍል ለማስጀመር :- • የክልሉ/የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት እና እቅዱን ለማከናወን በጀት በመያዝ የሙያ አይነቶችን በትምህርት ቤት እና በተማሪዎች ደረጃ በማስመረጥ፣ • የየሙያ አይነቱ መምህራንን በመቅጠር፣ • የመማሪያ ማስተማሪያ ግብዓት በሂደት በማሟላት፣ • መምህራንን እና የትምህርት አመራሮችን በማሰልጠን እና የህዝብ ንቅናቄ ስራዎችን በማከናወን ትምህርቱን ለማስጀመር ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል። ትምህርት ሚኒስቴር ከ2019 የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረጉ የ11 የሙያ አይነቶችን ዝርዝር አሳውቋል። @Gtutorialclass
- 13 авг.45 просмотров
без подписи
- 13 авг.44 просмотров
без подписи
- 13 авг.44 просмотров
без подписи
без подписи
без подписи