tgindex
Great_Abyssinia

Great_Abyssinia

Статистика

የታላቋ አቢሲኒያ መንደርደሪያ . . . ያላችሁን መልዕክት ጥያቄ በ @Tekit_leEthiopia_bot እና @Great_Abyssinia ማድረስ ይችላሉ

Последний пост
10 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
hu
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 087
−2 за 4 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
191
21 постов
Вовлечённость
17,6%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
54
1/48двое суток
61
1/72трое суток
66

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ዕድሜ ባለፈ ቁጥር የሚመጣ ከባድ ጸጸት ብዙዎቻችን ጊዜን ልክ እንደማያልቅ ማለቂያ የሌለው መስመር አድርገን እንቆጥራለን፤ ነገር ግን ጊዜ የምናጠፋው እና ቀሪ ሂሳባችንን በፍጹም የማናውቀው ብቸኛ ውድ ንብረታችን ነው። ሰዓቱ ያለማቋረጥ ሳያርፍ ይንቀሳቀሳል፣ ያለፈው የህይወት ዘመን እየጨመረ ይመጣል የወደፊቱ ዕድል ደግሞ በዝግታ እየራቀ ይሄዳል። ዕድሎች ባክነው ሲቀነሱ የጸጸት ስሜት በሂደት እየተከመረ ይመጣል። በዘመናዊው ዓለም ውስጥ የሚታየው ትልቁ ስህተት ሰዎች ጊዜን «እንዴት ማሳለፍ ወይም መግደል እንዳለባቸው» ማሰባቸው ነው። ነገር ግን ጊዜን ስንገድል ራሳችን ጊዜ በጸጥታ እየገደለን መሆኑን አንገነዘብም። ያለማቋረጥ ያለአላማ የሚባክን እያንዳንዱ ሰዓት ሊመጣ የሚችለውን የወደፊት ዕድል ወደ የማይለወጥ ያለፈ ጊዜ እንዲቀየር ያደርገዋል። የጊዜ አጠቃቀምን በተመለከተ የጸጸት ክብደት ከዲሲፕሊን (ራስን ከመግዛት) ክብደት ሁልጊዜ ይከብዳል። ራስን በዲሲፕሊን መምራት ጊዜያዊ አለመመቸት ሊኖረው ይችላል፤ ነገር ግን እድሜ ባለፈ ቁጥር የሚመጣው ጸጸት ከማንኛውም ከባድ ሐዲድ በላይ ሰውን ያደቅቀዋል። ይህ ጥልቅ ፍልስፍና ጊዜን በአግባቡ የመጠቀምን አስፈላጊነት፣ ሕይወት በአጭር ጊዜ ውስጥ ልትፈስ እንደምትችል እና የዘመኑን የብክነት ፍጆታ በመተው ትርጉም ያለው ተግባር ላይ ማተኮር እንደሚገባን ትልቅ ትምህርት ይሰጠናል። በዘመናዊው የዕለት ተዕለት ሕይወትዎ ውስጥ ጊዜን «ለመግደል» ወይም ያለአላማ ለማሳለፍ ከሚዳርጓችሁ ነገሮች ራስዎን እንዴት ነፃ እያወጡ ነው?

  • ‹‹አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ፡፡ መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት። ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ፡፡ የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት፡፡ ወዲያው ወታደሮቸ በሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው፡፡ ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ። ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት ‹‹በዚህ ቄስ መገደል እኮ ሕዝቡ ተደስቷል›› አለኝ፡፡ ‹‹እንዴት?›› ብለው ‹‹አላየህም ሲያጨበጭብ?›› አለኝ፡፡ ‹‹ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል›› አልኩት፡፡ ‹‹እንዴት?›› ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት፡፡" አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ በቦታው ሆነው የተከታተሉት ሙሴ ፓይላክን የተባሉ ግለሰብ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ለጳውሎስ ኞኞ ከነገሩት የተወሰደ፡፡ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ/ም    የታላቋ አቢሲኒያ መንደርደሪያ . ያላችሁን መልዕክት  ጥያቄ በ @Tekit_leEthiopia_bot እና @Great_Abyssinia  ማድረስ ይችላሉ https://t.me/GreatAbyssiniaEmpireን የሚያዜምልን ነው።"

  • አዕምሮ! አንድ ትንሽዬ ፍሬ ጥሩ መሬት ካገኘች ከአመታት በኋላ ጫካ ልትሆን ትችላለች፤ ወሳኙ የፍሬዋ ማነስ አይደለም፤ የመሬቱ የማብቀል አቅም ነው። አዕምሮህን እንደ መሬቱ ለማብቀል የሚመች ከሆነ በሰዎች ዘንድ የተናቀ ተራ ሀሳብ አስበህ እንኳን ታላቅ የሀገር መሪ ወይ ባለፀጋ ወይ ጠቢብ ልትሆን ትችላለህ። አዕምሮህን በይቅርታ፣ በፍቅርና በበጎነት ከሞላኸው የዘራኽበትን ትንሽም ትልቅም ምኞት ሁሉ አብቅሎ ተዓምር ያሳይሀል!

  • 22 июн.135из ETHIO_PDF_BOOKS1

    "ለመሆኑ እግዚአብሔር ምን እየሰራ ነው።" አፄ ቴዎድሮስ አንድ አዲስ አድማስ አምድ ላይ ያነበብኩት ፍቅር ለይኩን የፃፈው አፈ-ታሪክ አለ። “አፄ ቴዎድሮስ ብዙ ከተባለለትና ከተጻፈለት አፍሪካዊው ናፖሊዮን ካሰኛቸው ከጀግንነታቸው፣ ከጭካኔያቸው፣ ከፍርድ አዋቂነታቸውና ኢትዮጵያን ለማዘመን ከነበራቸው ታላቅ ራእይ ባሻገር በተለያዩ ጊዜያት ስለ ፈጣሪ ህልውና ከቤተ ክህነቱ ተጠሪዎች ነን ባዮች ደብተራዎችና ካሕናት ጋር ያደረጓቸው እንደ አንዳንድ የዋኃን አገላለጽ ‹‹ፈጣሪን መፈታተን›› ዓይነት ጥያቄዎችን እያነሱ ካሕናቱንና የቤተ ክርስቲያኒቱን ሊቃውንቶች በጥያቄ በማጣደፍ ያስጨንቁ ነበር ይባላል፡፡ እናም በአንድ ወቅት አፄ ቴዎድሮስ በዙፋናቸው በተሰየሙበት ግብር ገብቶ መኳንንቱና መሳፍንቱ፣ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንቱና ካሕናት በታደሙበት ግብዣ ላይ ንጉሡ አንድ ጥያቄ አነሱ እንዲህ ሲሉ፡- ‹‹ለመሆኑ እግዚአብሔር አለ… ካለስ ምን እየሰራ ነው…!? በማለት ጥያቄያቸውን ወርወር አድርገው የሊቃውንቱንና የካሕናቱን መልሳቸውን ለመስማት ጓጉተው መይሳው ካሳ ከዙፋናቸው ላይ ተመቻቹ፡፡ሊቃውንቱና ካሕናቱ ሁሉ የመሰላቸውንና የንጉሥን ልብ ያሳርፋል ያሉትን መልስ ሁሉ ወደ አፄ ቴዎድሮስ መወርወር ጀመሩ፤ ይሁን እንጂ ከእነዚህ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ነን ከሚሉ ሊቃውንትና ካሕናት ዘንድ ንጉሡ ቴዎድሮስ ልባቸውን የሚያሳርፍ በቂ ምላሽ አላገኙም፡፡ እናም በቁጣ ሆነው ሊቃውንቱንና ካሕናቱን በመገላመጥ ከግብር ቤቱ በራፍ ላይ ደበሎውን ለብሶ አኩፋዳውን ይዞ ከንጉሥ ገበታ የሚተራርፈውን እንጀራ የሚጠብቀውን አንድ ምስኪን የቆሎ ተማሪ ወደ ዙፋናቸው አስጠርተው ‹‹እግዚአብሔር አለን… ካለስ ለመሆኑ ምን እየሰራ ነው…!? አሉት፡፡ ተማሪውም ለጥ ብሎ እጅ ከነሳ በኋላ ‹‹ንጉሥ ሆይ ሺህ ዓመት ይንገሱ! እግዚአብሔር መንግሥትዎን ያስፋ፣ ጠላትዎን ያጥፋ! ጃንሆይ እግዚአብሔርማ አለ! የቀን ተሌት ሥራውም ለእያንዳንዳችን መልካም ሆነ ክፉ ስራችን ምላሽ/ብድር/ ሰፍሮ የሚመልስበትን ቁና ሲሰፋ መኖር ነው!›› በማለት መለሰ፡፡ ለአንዳንዱ አምላክ ብልፅግናና ስልጣን የሚያስገኝ ጌታ ነው። ለአንዳንዶች አምላክ ደናግላትን እንደ ሽልማት የገሀነም እሳትን እንደ ቅጣት ቆጥሮ የሚከፍል ነው። ለአንዳንዶች አምላክ ፆማቸውን ስግደታቸውን አይቶ የሚደሰት እንጉርጉሮአቸውንና ሙዚቃቸውን ሰምቶ የሚቆጣ ነው። @ETHIO_PDF_BOOKS1

  • ​በአንድ ወቅት ቶሎ የመናደድ እና ሰዎችን የማስቀየም መጥፎ ባህሪ ያለው አንድ ወጣት ነበር። አባቱም ይህን ባህሪውን እንዲያስተካክል አስቦ አንድ ከረጢት ምስማር ሰጠውና፣ "በተናደድክ እና ቁጣህን መቆጣጠር ባቃተህ ቁጥር ግቢያችን ባለው የእንጨት አጥር ላይ አንድ ምስማር ምታ" አለው። ​በመጀመሪያው ቀን ወጣቱ አጥሩ ላይ 37 ምስማሮችን መታ። በቀጣዮቹ ሳምንታት ግን ቁጣውን መቆጣጠር እየተማረ ሲመጣ፣ በየቀኑ የሚመታቸው ምስማሮች ቁጥር እየቀነሰ መጣ። ምስማር አጥር ላይ ከመምታት ይልቅ ቁጣውን መቆጣጠር ቀላል እንደሆነ ተረዳ። በመጨረሻም ፈጽሞ ሳይናደድ ሙሉ ቀን መዋል ቻለ። ​ይህንኑ ለአባቱ ሲነግረው፣ አባቱ ደግሞ "አሁን ደግሞ ሳትናደድ በዋልክበት እያንዳንዱ ቀን አንድ ምስማር ከአጥሩ ላይ እየነቀልክ አውጣ" አለው። ቀናት አለፉ፣ ወጣቱም ሁሉንም ምስማሮች ነቅሎ እንደጨረሰ በደስታ ለአባቱ ነገረው። ​አባቱም ልጁን እጁን ይዞ ወደ አጥሩ በመውሰድ እንዲህ አለው፦ "ልጄ ሆይ፣ በጣም ጥሩ ሰርተሃል፤ ነገር ግን በአጥሩ ላይ ያሉትን ቀዳዳዎች ተመልከት። አጥሩ መቼም እንደ ቀድሞው ሙሉ አይሆንም። በንዴት የምትናገራቸው ቃላትም ልክ እንደነዚህ ቀዳዳዎች በሰዎች ስሜት ላይ ጠባሳ ይተዋሉ። ሰውን በስለት ወግተህ ይቅርታ ብትጠይቅም ቁስሉ ግን መኖሩ አይቀርም።" ​ መልእክት፦ ቃላት ትልቅ ሃይል አላቸው። በንዴት የምንናገራቸው ነገሮች በሰዎች ልብ ላይ የማይጠፋ ጠባሳ ሊተዉ ስለሚችሉ፣ ሁሌም ከመናገራችን በፊት እናስብ!    የታላቋ አቢሲኒያ መንደርደሪያ . ያላችሁን መልዕክት  ጥያቄ በ @Tekit_leEthiopia_bot እና @Great_Abyssinia  ማድረስ ይችላሉ https://t.me/GreatAbyssiniaEmpireን የሚያዜምልን ነው።"

  • "ታላቅ ዘፋኝ የሚባለው ዝምታችንን የሚያዜምልን ነው።" ካህሊል ጂብራን እናመሰግናለን ቴዎድሮስ ካሳሁን 🙏 የታላቋ አቢሲኒያ መንደርደሪያ . ያላችሁን መልዕክት  ጥያቄ በ @Tekit_leEthiopia_bot እና @Great_Abyssinia  ማድረስ ይችላሉ https://t.me/GreatAbyssiniaEmpire

  • "ሰውን በትክክል ማወቅ ከፈለግክ የሚናገረውን ቃል ብቻ አትስማ፤ ዝም የሚልበትንም ምክንያት መርምር። አብዛኛው እውነት ያለው በሰዎች ጩኸት ውስጥ ሳይሆን፣ በጥልቅ ዝምታቸው ውስጥ ነው... ብዙዎቻችን ከራሳችን ጋር መገናኘት ስለሚያስፈራን፣ ከሌሎች ጋር ለመሆን እንጣደፋለን።" 📖 የመፅሐፉ ስም፦ አለመኖር

  • "የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ እያለሁ ሁለት ቁልፍ ፈተናዎች ነበሩብኝ ሆኖም ሁለቱንም ወደኩ….የመካከለኛ ደረጃ ተማሪ እያለሁም ፈተና ከመውደቅ አልዳንኩም ለውድቀት ሶስት ጊዜ እጄን ሰጠሁ፡፡ ኮሌጅ ለመግባት ፅኑ ፍላጎት ቢኖረኝም መግቢያ ፈተናዎቹን ሁለቴ ወስጄ በሽንፈት ተመለስኩ፡፡ የሚገርመው ደግሞ ያመጣሁት ውጤት  አሳዛኝ ነበር። መውደቅ አንድ ነገር ቢሆንም በሂሳብ ትምህርት  ከ120 ነጥብ 1 ማምጣት ግን  በርግጥም ከባድ ነበር፡፡ ውድቀቴ ይቀጥላል…ሃርቫርድ ዩኒቨርሲቲ 10 ጊዜ አመልክቼ ውድቅ ተደርጎብኛል፡፡ ከኮሌጅ ተመርቄ ከወጣሁ በኋላ ስራ የመቀጠር ፅኑ ፍላጎት ቢኖረኝም 30 ስራ እድሎች በተከታታይ ብሞክርም አልተሳካልኝም፡፡ KFC ስራ አወጣ ተደሰትኩ በዚህኛው ግን ስራ ለማግኘት የማደርገው ጥረት በድል እንደሚደመደም አስቤ ተራመድኩ፡፡ ብዙ ፈተናዎችን አልፈን ለስራ የመጣነው 24 ነን፡፡ 23 ሰው አለፈ በሚደንቅ ሁኔታ የወደቀው አንዱ ሰው እኔ ነበርኩ፡፡"   ይህንን ያለው ጃክ ማ ነው። ይህ ሰው ከዚህ ሁሉ ውድቀት በኋላ ቻይናን የቀየረ አማዝኦንን መሰል የአሜሪካ ካምፓኒዎችን የሚገዳዳረውን አሊባባን የመሰረተ እና እዚህ ያደረሰ ስኬታማ ሰው ነው፡፡   "በፍጹም ተስፋ አትቁረጥ! ዛሬ ከባድ ነው…ነገም የከፋ ሊሆን ይችላል… ከነገወዲያ ግን መልካም ይሆናል!!!" – Jack Ma👏 መልካም ቀን🥰🥰

  • አዲስ ሳምንት፣ አዲስ ዕድል! ዛሬን ለነገ ስኬታችን ጠንካራ መሰረት እናድርገው። ስኬት በአጋጣሚ የሚገኝ ሳይሆን በየቀኑ በምናደርገው ጥረትና በምናሳየው ጽናት የሚገነባ ውጤት ነው። ስለዚህ ይህንን ሳምንት በታላቅ ራዕይና በጠራ ዕቅድ በመጀመር ህልሞቻችንን ወደ እውነት እንቀይር። መልካም የሥራ ሳምንት!

  • «ኬንያ ናይሮቢ አንዲት መዝናኛ ቤት ተገኝቼ እየተዝናናሁ ነው። ቤቱ እንደ ፓርቲ ቤት ያለ ነው። ባንዱ ጥግ መጠጤን ይዤ፣ የዳንሱ ወለል ላይ ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚደንሱ ወጣቶችን አያለሁ። በዚህ መሃል የባሕር ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ እንግሊዛዊያን ነጮች ገቡ። አንዱ እንግሊዛዊ ቀጥታ ወደ ዳንስ ወለሉ ሄደና ከወዳጁ ጋር እየደነሰ ያለውን ኬንያዊ በካልቾ መታው። ኬንያዊው ተርበድብዶ የሴት ወዳጁን ጥሎ ገሸሽ አለ። እንግሊዛዊውም ከዛች ኬንያዊት ጋር መደነስ ጀመረ። በእንግሊዛዊው ድርጊት በጣም ተናደድኩ። ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁና ወደ ዳንስ ወለሉ አመራሁ። እኔም እንግሊዛዊውን በካልቾ ጠልዤ ኬንያዊቷን ተቀበልኩ። ጥቂት ካስደነስኳትም በኋላ ለተቀማው ኬንያዊ አስረከብኩ። ይህን ፈፅሜ ወደ መቀመጫዬ ሳመራ እንግሊዛዊው የጠየቀኝ አንድ ጥያቄ ነበር ፦ "ኢትዮጵያዊ ነህ?" የሚል።» #ፕሮፌሰር_መስፍን_ወልደማርያም። የፍትህ! የርትእ! አስፋኝ ልጆች ነን!። #የእምዬ ምኒሊክ ልጆች ነን!✊✌ የታላቋ አቢሲኒያ መንደርደሪያ . ያላችሁን መልዕክት  ጥያቄ በ @Tekit_leEthiopia_bot እና @Great_Abyssinia  ማድረስ ይችላሉ https://t.me/GreatAbyssiniaEmpire

  • #አድዋ ‼️ እንኳን ለ130 ኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ ። #አድዋ #ኢትዮጵያ

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • #እንኮዬ አዲስ ሀገርኛ ተከታታይ ድራማ በፍካት ፊልም ፕሮዳክሽን እና በሐምሌት ፊልም ፕሮዳክሽን ተዘጋጅቶ በዓባይ ቴሌቪዥን የቀረበው የአማኑኤል ንጉሴ /አማኒ/ ድንቅ ድራማ አርብ የካቲት 20 ከምሽቱ 3 ሰአት ይጀምራል

  • без подписи

  • 19 февр.214из Historical_Ethiopia

    የሰማዕታት ቀን !! እንኳን ለ ሰማእታት መታሰቢያ እለት አደረሰን፤ አደረሳችሁ! የካቲት 12 ቀን 2015 ዓ/ም 1929 ዓ/ም - ለኢጣሊያ ንጉሣዊ ቤተሰብ አንድ ልዑል በመወለዱ ምክንያት በጄነራል ግራዚያኒ ትዕዛዝ በቀድሞው የገነተ ልዑል ቤተ መንግሥት (የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቅጽር ግቢ ከተሰበሰቡት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች፤ ለፋሺስቶቹ ያደሩ ከሀዲ ባንዳዎችና መኳንንት፤ የፋሺስት ባለ ሥልጣናት ወታደሮች በተሰበሰቡበት መሀል፣ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም የእጅ ቦምብ ወርውረው አደጋ ሲጥሉ ግራዚያኒን ጨምሮ ብዙ ሰዎች ተጎድተዋል። ይህንን ድርጊት በመበቀል ሰበብ እዚያው ግቢ ውስጥ ከሶስት መቶ በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን ተጨፈጨፉ፤ ቀጥሎም የተማሩ ወጣቶች፣ የጦር መኮንኖችና ካህናት ፣ የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት በሙሉ እየተለቀሙ ተጨፈጨፉ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በቤት ውስጥ እያስገቡ ከውጭ ቆልፈው ቤንዚን እያርከፈከፉ አቃጠሉአቸው። በአካፋ፣ በዶማ፣ በመጥረቢያ በተገኙበት ኢትዮጵያውያንን እየቆራረጡ የደም ጎርፍ አወረዱ። ፋሽስቶች የአዲስ አበባንና የአካባቢውን ሕዝብ በጅምላ ጨፈጨፉት። በሶስት ቀናት 30 ሺህ ሕዝብ የሰማዕትነትን ተቀበለ። በየአዝማናቱ ለፍትኅ፣ ነፃነት እና እኩልነት ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን ለሰጡን ወገኖች መታሰቢያ  ይሆን ዘንድ ኢትዮጵያን ከአስከፊ ድኅነትና ለከት የለሽ ጭቆና  ማላቀቅ ላይ እንበረታ ዘንድ መልእክቴን አስተላልፋለሁ። ክብር  ለሰማዕታት !! ኢትዮጵያ  ለዘላለም  ትኑር!! ✅የቴሌግራም ቻናል - @Historical_Ethiopia ✅ጥያቄ ካለዎት❓ 👉 @Historical_Ethiopia_Discussion

  • 15 февр.168из yetselot_ekub

    ሠናይ ጾም ❤️

  • የካቲት መሰብሰብ፣ መክተት፣ አምርቶ ማከማቸት የሚል ትርጓሜ አለዉ። የዓመቱ ስድስተኛዉ ወር የኾነዉ ወርኀ የካቲት “ከቲት ከቲቶት” ከሚለዉ የግእዝ ንኡስ አንቀጽ የወጣ ቃል ነዉ። የካቲት የመከር መካተቻ የበልግ መባቻ በመባልም የሚታወቅ ነዉ። “የካቲት እንደመጠሪያዉ አምርቶ የማከማቸት ወር ይኹንላችሁ” የወጣት ምርቃት ነዉ ብላችሁ ደግሞ አሜን ከማለት እንዳትቆጠቡ። መልካም ሰንበት።