tgindex
Yegna Tikuret - የኛ ትኩረት

Yegna Tikuret - የኛ ትኩረት

Статистика
Последний пост
27 дек. 2024 г.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 572
−1 за 5 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 034
20 постов
Вовлечённость
65,8%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የቁልቢ ገብርኤል ዓመታዊ የንግስ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቋል ተባለ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ሜታ ወረዳ ቁልቢ 01 ቀበሌ ሐምሌ 19 ቀን 2017 ዓ.ም በታላቅ ድምቀት ለሚከበረው የቁልቢ ገብርኤል ንግስ በዓል አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የድሬዳዋ ፖሊስ አስታወቀ።እንደ ድሬዳዋ ከተማ በምስራቅ አጎራባች ሀይሎች መውጫ እና መግቢያ ቦታዎች ላይ አስፈላጊው ስራዎች እየተከናወነ መሆኑ ተገልጿል። በዓሉ ከመከበሩ በፊት የድሬዳዋ ፖሊስ በትራፊክ መስተንግዶ እና በወንጀል መከላከል ስራ ላይ የበዓል አከባበሩ  ፍፁም ሰላማዊ እና ከትራፊክ አደጋ የፀዳ ለማድረግ እንግዶች በመቀበል ላይ ነን ሲሉ የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ የሚዲያ እና ገጽታ ግንባታ ዲቪዥን ኃላፊ ኢንስፔክተር ዳግም ተፈራ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ። በዓሉን ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች በከተማው ውስጥ ያሉ ፖሊስ ጣቢያዎች፣የትራፊክ ክፍሎች ስልክ ቁጥር የያዘ በራሪ ወረቀቶች እና ስቲከሮች በመበተን ህብረተሰቡ ማንኛውም ዓይነት ጥቆማ መስጠት ሲፈልግ ለፖሊስ ጥቆማ መስጠት እንዲችል መመቻቸቱ ተገልጿል።በተጨማሪም ምዕመናኑ በበዓሉ ወቅት የኪስ ቦርሳቸውን ፣ ሞባይል ስልካቸውን እና ሌሎች ንብረታቸውን እንዳይሰረቁ እና እንዳይጥሉ በጥንቃቄ እንዲይዙ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል። ከዚህ ባለፈ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያዎች ፣ ዓቃቤ ህግ እና ጊዜያዊ ፍርድ ቤት የተቋቋመ ሲሆን ተጠርጣሪ ወንጀለኞች ሲያዙ የምዕመናን መጉላላት እንዳይኖር የምርመራ መዝገብ ተጣርቶ በጊዜያዊ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ በማድረግ አፋጣኝ የፍርድ ሂደቱን መሠረት  ውሳኔ ይሰጣል ተብሏል። ወንጀል ፈፃሚዎችን ወይም ለመፈፀም የተዘጋጁ ተጠርጣሪዎች ሲያጋጥሙ ምዕመናኑ በአቅራቢያቸው ለሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ጥቆማ መስጠት እንዳለባቸው እና በአጭር የስልክ መስመር 620 በመደወል ማሳወቅ ይችላል ሲሉ ኢንስፔክተር ዳግም ተፈራ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በሳምራዊት ስዩም Join: @yegnatikuret

  • Join: @yegnatikuret

  • በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት እንዲሰሩ ተወሰነ በአዲስ አበባ ከተማ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት በመደበኛው ታሪፍ መሰረት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ የከተማዋ ትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል፡፡ በመዲናዋ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አካላት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ አስተዳደሩ ካቢኔ መወሰኑ ይታወሳል፡፡ በውሳኔው መሠረት አውቶቡሶች፣ ሚድ ባስ እና ሚኒ ባሶች መደበኛ በሚሰሩበት መስመርና ቀን ላይ በሚከፈለው ሕጋዊ ታሪፍ መሠረት እስከምሽቱ 4 ሰዓት አገልግሎት እንዲሰጡ ቢሮው አሳቧል፡፡ ስለሆነም የትራንስፖርት አገልግሎት ተጠቃሚዎች ይህን በሚገባ በመረዳት እስከምሽቱ 4 ሰዓት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ የትራንስፖርት ቁጥጥር ሠራተኞች እንዲሁም የሚመለከታችሁ አካላት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ለተግባራዊነቱ የበኩላችሁን ሚና እንድትወጡ ሲል ጥሪ ቀርቧል፡፡ በጉዳዩ ላይ ለበለጠ መረጃና ለትራንስፖርት ጉዳይ ጥቆማ ለመስጠት በነፃ የስልክ ጥሪ መስመር 9417 ላይ መደወል እንደሚቻልም ቢሮው አስታውቋል፡፡ Join: @yegnatikuret

  • ዩክሬን የተጎዳ የሰሜን ኮሪያ ወታደርን በቁጥጥር ስር ማዋሏን ሴኡል አስታወቀች የዩክሬን ጦር የሩስያን ጦርነት ለመደገፍ የተላከውን የተጎዳ የሰሜን ኮሪያ ወታደር መያዙን የደቡብ ኮሪያ የስለላ ድርጅት ዛሬ አርብ እለት አረጋግጧል። ወታደሩ ፒዮንግያንግ ዩክሬን ውስጥ የሩስያን ጦርነት ለመደገፍ ጦሯን ካሰማራችበት ከታህሳስ ወር ጀምሮ የተማረከ የመጀመሪያው የሰሜን ኮሪያ የጦር እስረኛ እንደሆነ ይታመናል። ማረጋገጫው ይፋ የተደረገው የቆሰለውን ወታደር የሚያሳይ ፎቶ በቴሌግራም ከተሰራጨ በኋላ ነው። ሰሜን ኮሪያ ሩሲያን ለመርዳት ከ10,000 በላይ ወታደሮችን ልካለች።ሞስኮ እና ፒዮንግያንግ ስለ ሰሜን ኮርያ ወታደሮች ወደ ሩሲያ መላክ ባያረጋግጡም መረጃውን አላስተባበሉም።በአሳን የፖሊሲ ጥናት ተቋም ተመራማሪ ያንግ ዩክ እንደተናገሩት ለዩክሬናውያን እነዚህን የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች መያዝ እና በእስረኛ ልውውጥ ወቅት ለመለዋወጥ መሞከር የበለጠ ጠቃሚ ነው ብለዋል። ሩሲያውያን ለዩክሬን የጦር እስረኞች " ከሩሲያ እና ዩክሬን ጦርነት የወጡ የቅርብ ጊዜ ምስሎች “የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በሩሲያ ትዕዛዝ ለሚሰነዘረው ጥቃት በብዛት ይሰፍራሉ” የሚል መላምት አረጋግጠዋል። አክለውም “የሰሜን ኮሪያ ዜግነታቸውን ማረጋገጥ ፈታኝ ነው” ብለዋል። የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች ሀሰተኛ የሩሲያ መታወቂያ ተሰጥቷቸዋል ሲሉ የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዜለንስኪ ባለፈው ሳምንት መናገራቸው ይታወሳል። ይህም የሩሲያ ወታደሮች የተገደሉትን የሰሜን ኮሪያውያንን ማንነት ለመደበቅ ፊታቸውን ሲያቃጥሉ ያሳያል ብለዋል። የዩክሬን እና የደቡብ ኮሪያ የስለላ አገልግሎቶች እንዳስታወቁት ወደ ሩሲያ ከተሰማሩት ወታደሮች መካከል ብዙዎቹ የፒዮንግያንግ ምርጦች የሚባሉት የ11ኛው ጓድ አባላት ናቸው። ይህው የ11ኛው ክፍለ ጦር ሰርጎ መግባት፣ መሠረተ ልማትን ማበላሸት እና ግድያ ላይ የሰለጠነ ነው።ከ3,000 የሚበልጡ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮች በሩሲያ ኩርስክ ክልል ውስጥ ሲዋጉ ሞተዋል ወይም ቆስለዋል ሲሉ ዘለንስኪ ሰኞ ዕለት መናገራቸው ይታወሳል። በሞስኮ እና በፒዮንግያንግ መካከል ያለው ትብብር በኮሪያ ልሳነ ምድር ዙሪያ ያለውን "የመረጋጋት አደጋ" ከፍ ያደርገዋል ሲሉ የጦር ተንታኞች ስጋታቸውን ይገልጻሉ። እ.ኤ.አ. በየካቲት 2022 ሩሲያ በዩክሬን ላይ ሙሉ ወረራ መጀመሯ ይታወሳል።የሰሜን ኮሪያ ጦር በቅርቡከገቡ ማ ወደ ኃይሉን በሩሲያ ማሰማራቱ በሁለቱ መንግስታት መካከል ያለውን ትብብር የሚያሳይ ነው። ሰሜን ኮሪያ ከደቡብ ኮሪያ ጋር ውጥረት ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት የመጣው ይህ ትብብር በምዕራቡ ዓለም ስጋት ፈጥሯል። የሁለቱም ወገኖች የረጅም ጊዜ አጋር የሆነችው ቻይናም የሩሲያ እና የሰሜን ኮርያ ወዳጅነት በጥንቃቄ እየተከታተለችው ሲሆን ለቤጅምግ ግንኙነታቸው ምቾት እንዳልሰጣት ይታመናል። በስምኦን ደረጄ Join: @yegnatikuret

  • Join: @yegnatikuret

  • በሸገር ከተማ ለልማት በሚል ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ሰብስበው ለግል ጥቅማቸው ያዋሉ አመራሮች በእስራት ተቀጡ በኦሮሚያ ክልል በሸገር ከተማ አስተዳደር ሱሉልታ ክፍለ ከተማ ለልማት በሚል ከማህበረሰቡ  ከሦስት ሚሊየን ብር በላይ በመሰብሰብ ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው በእስራት ሊቀጡ ችለዋል።  በሸገር  ከተማ ቅርንጫፍ አቃቤ ህግ  አንደኛ ወንጀል ችሎት እንዳስታውቀው የወሠርቢ  ወረዳ አስተዳዳሪ ሲፊለቴ  ከበደ፣  የፋይናስ ፅ/ቤት ኃላፊ አሸብር ኦልጅራ፣ የማዘጋጃ ኃላፊ ጐታ ኤጀሪ፣ የወረዳው ገቢዎች ቢሮ ኃላፊ ገመቹ ማሞ የተባሉ አራት አመራሮች የሙስና ወንጀል ለመከላከል የወጣውን አዋጅ በመተላለፋቸው ክስ ተመስርቶባቸዋል። ተከሳሾቹ ከሸገር ከተማ አስተዳደር እና ከክፍለ ከተማው ፍቃድ ሳይሰጣቸው  በሱሉልታ ከተማ ወሰርቢ ወረዳ ከተለያዩ ባለሀብቶች እና ከሌሎች ማህበረሰብ ክፍሎች  ለልማት በሚል በህገ ወጥ መንገድ በራሳቸው ስም በከፈቱት የባንክ ሂሳብ 3 ሚሊየን 80 ሺ ብር ሰብስበው ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው አቃቤ ህግ ክስ መስርቶባቸዋል። በቀረበባቸው ክስ 2ተኛ እና 3ተኛ ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ውለው የወንጀል ድርጊቱ አልፈፀምንም በማለት የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጥተዋል።በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹ በተከሰስኩበት ክስ ጥፋተኛ መሆናቸውን በማረጋገጥ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ተከሳሾችን በ5 አመት እስራት አና በ5 ሺ ብር የገንዘብ መቀጮ እንዲቀጡ መወሰኑ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታውቋል።በአንደኛ እና በአራተኛ ተከሳሾች ላይ ተለዋጭ ቀጠሮ መሰጠቱ ተገልጿል። በሳምራዊት ስዩም Join: @yegnatikuret

  • 4.9 በሬክተር ስኬል የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ አጋጠመ ዛሬ ሌሊቱንም በድጋሚ በሬክተር ስኬል 4.9 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ተሰምቷል። 11 ሰዓት ገደማ ላይ የተሰማዉ ንዝረቱ እስካሁን ከታዩት የመሬት መንቀጥቀጦች ዘለግ ላሉ ሰከንዶች የቆየም እንደነበር ዳጉ ጆርናል ታዝቧል። የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ የመሬት መንቀጥቀጡ ከመተሃራ አቅጣጫ በስተሰሜን 26 ኪሜ ርቆ መሆኑን እና 4.9 በሬክተር ስኬል የተለካ መሆኑን አሳዉቋል። በበረከት ሞገስ Join: @yegnatikuret

  • ▪️ 7 ግቦች ▪️ 4 ለግብ የተመቻቸ ኳስ በቦክሲንግ ደይ ጨዋታዎች እንደ ሞ ሳላህ ቀጥተኛ የግብ ተሳትፎ ያደረገ አንድም የፕሪሚየር ሊግ ተጫዋች የለም 🎁 Join: @yegnatikuret

  • ምን አይነት ምትሀተኛ ተጫዋች ነው !?😳 🚨ሊቨርፑል 3-1 ሌሲስተር ⚽️አይው ⚽️ጋክፖ ⚽️ጆንስ ⚽️ሳላህ ጎሎቹን 👉 Join: @yegnatikuret

  • የአሰልጣኝ አርን ስሎት ቡድኑ አጨዋወት አስደማሚ ነው 🔥 Join: @yegnatikuret

  • 🚨ሊቨርፑል 2-1 ሌሲስተር ⚽️አይው ⚽️ጋክፖ ⚽️ጆንስ ጎሎቹን 👉 Join: @yegnatikuret

  • በውጤት ቀውስ ውስጥ የሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ የፈረንጆቹን ገና 14ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ለማሳለፍ ተገዷል Join: @yegnatikuret

  • የቀደመው ዘገባ የኢዲቶርያል ስታንዳርዳችን የሚያሟላ አልነበረም ለዚህም ይቅርታ እንጠይቃለን - ቢቢሲ ሶማሊ 👉 ቢቢሲ ሶማሊ ኤርትራ ከሶማልያ ጋር ያላትን ዲፕሎማስያዊ ግኑኙነት ልታቋርጥ ትችላለች ብሎ ለሰራው ዘገባ ይቅርታ ጠየቀ ቢቢሲ ሶማሊ የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካሪ ናቸው ያላቸውን አብዲቃድር ኢድሪስን በመጥቀስ ኤርትራ የአንካራው ስምምነት እንዳሳሰባት በዚህ ሳብያም ከሀገሪቱ ጋር ያላትን ዲፕሎማስያዊ ግኑኙነት ልታቋርጥ እንድምትችል መግለፆን መዘገቡ አይዘነጋም። ይህ ዘገባ ከተጋራ በኃላ በርካታ ተቃውሞና ትችት ሲያስተናግድ የቆየ ሲሆን በለንደን የሚገኘው የኤርትራ ኤምባሲም ቅሬታውን ለቢቢሲ ማቅረቡ ተሰምቷል። ኤምባሲው የተጠቀሱት ግለሰብና የሚሰሩበት ተቋም በመሬት ላይ የሌሉ መሆናቸውን በመግለፅ የፈጠራ ዘገባ ነው ማለቱ ተነግሯል። ይህን ተከትሎ ቢቢሲ ሶማሊ ባወጣው የእርምት ዘገባ ለአንባቢዎቻችንን ከተለያየ አቅጣጫ የሚያሳትፉ ታሪኮችን ለማድረስ ይጥራል፣ ይህንንም የምናደርገው ጥብቅ የአርትዖት መርሆችና መመሪያዎችን በማክበር ነው ብሏል።  ሆኖም፣ በዚህ አጋጣሚ እነዚያ መመሪያዎች የጣሰ ስራ ሰርተናል ለዚህ ስህተትም ከልብ ይቅርታ እንጠይቃለን ሲል ቢቢሲ ሶማሊ ተደምጧል። Join: @yegnatikuret

  • без подписи

  • ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ከአየር ጥቃት ተረፉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በየመን በአየር ማረፊያ ሳሉ በደረሰ የአየር ጥቃት መትረፋቸውን ገለጹ፡፡ እስራኤል በየመን ዋና ከተማ ሰነዓ በሚገኙት የሀውቲ አማፂያን ወታደራዊ መሰረተ ልማቶች ላይ መጠነ ሰፊ የአየር ጥቃት መፈፀሟ ተሰምቷል፡፡ በዚህም በሰንዓ አየር ማረፊያ የነበሩት ዳይሬክተሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት እርሳቸውና ባልደረቦቻቸው ከጥቃቱ መትረፋቸውን ገልጸዋል፡፡ የሰነዓ አየር ማረፊያ ተጠግኖ አገልገሎት መስጠት እስከሚጀምርም ዋና ዳይሬክተሩ እና ቡድናቸው በሰነዓ እንደሚቆዩ ጠቁመዋል፡፡ ዶክተር ቴድሮስ በአደጋው ህይዎታቸው ላለፉትና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡ ዋና ዳይሬክተሩ ወደ የመን ያቀኑት በሀገሪቱ የታሰሩትን የተባበሩት መንግስታት ሰራተኞች እንዲለቀቁ ለመደራደርና በየመን ያለውን የጤና እና ሰብዓዊ ሁኔታን ለመገምገም እንደነበር ገልጸዋል። Join: @yegnatikuret

  • без подписи

  • без подписи

  • የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ውጤት ቦርንመውዝ 0 - 0 ክሪስታል ፓላስ ኒውካስል 3 - 0 አስቶንቪላ ቼልሲ 1 - 2 ፏልሀም ፎረስት 1 - 0 ቶተንሀም Join: @yegnatikuret

  • ታላቅ ድል ከወደ ለንደን ቼልሲ 1-2 ፉልሀም     ⚽ ፓልመር       ⚽ ዊልሰን ⚽️ሙኒዝ   ጎሉን ለመመልከት 👉 Join: @yegnatikuret

  • ኢትዮጵያ ባለፋት አምስት ወራት ከእንስሳት ምርት ማቀነባበር የወጪ ንግድ ከ40 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ አገኘች ኢትዮጵያ ባለፋት አምስት ወራትለውጪ ገበያ ካቀረበችዉ 8ሺህ 4 መቶ 21 ቶን የተቀነባበረ የእንስሳት ምርት ከ40 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የእንስሳት ልማት ኢንስቲትዮት አስታውቋል።በኢንስቲትዮቱ የማህበራዊና ኢኮኖሚክስና እሴት ሰንሰለት አስተዳደር  ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ሳህሉ ሙሉ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ባለፋት አምስት ወራት ኢትዮጵያ ለውጪ ገበያ ከላከችዉ የተቀነባበረ የእንስሳት ምርት 43 ነጥብ 44 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት አቅዳ ነበር። በዚህም 43 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘት ችላለች ሲሉ ገልፀዉ አፈፃፀሙ የእቅዱን 91 በመቶ እንደሆነ ተናግረዋል።በዚህ ጊዜ ውስጥ ለዉጪ ገበያ ከተላኩት ምርቶች መካከል የበግና የፍየል ስጋ፣የዳልጋ ከብት ስጋ፣ የዶሮ ምርት ፣የአሳ ምርት፣የተቀነባበረ ማርና ሰም፣የግመል ወተትና የወተት ተዋፅኦዎችን ጨምሮ የእርድ ተረፈ ምርት ተጠቃሾች ናቸዉ።በምርቶቹ ላይ እሴት በመጨመር በማቀነባበሪያ ኢንዱስትሪዎች እንዲቀነባበሩ ተደርገው ለገበያ እንዲቀርቡ ተደርጓል ሲሉ የገለፁት ዶክተር ሳህሉ ወደ ተለያዮ የገበያ መዳረሻ ሀገራት መላካቸዉን አሰረድተዋል። የስጋ ምርቶችን በዋናነት ወደ ገልፍ ሀገራት፣የእርድ ተረፈ ምርትን ደግሞ ወደ ሩቅ እና መካከለኛው ምስራቅ  ሀገራት፣እንዲሁም ሌሎች ምርቶችንም ወደ ተለያዩ የገበያ መዳረሻ ሀገራት መላክ ተችሏል ።ከማክሮ ኢኮኖሚዉ ሪፎርም ወዲህ ለማዕከላዊ ገበያና ለኢንዱስትሪዎች የቀረቡት ጥሬ እቃዎች በመጨመራቸዉ በአፈፃፀም ረገድ ጥሩ ውጤት ተመዝግቧል፡፡ መፍትሄ ያላገኘዉ ህገወጥ የእንስሳት ንግድ ዘርፋን እየተፈታተነዉ ያለ ችግር ስለመሆኑ አንስተዋል።በተጨማሪም የሀገር ውስጥ የምርት ጥሬ እቃ ዋጋ መናር ባለፋት አምስት ወራት በአፈፃፀም ረገድ ካጋጠሙ ችግርች መካከል ይጠቀሳል። ኢንስቲትዮቱ በዘርፋ ያጋጠሙትን እነዚህን ችግሮች ሙሉ ለሙሉ ለመፍታት ከሌሎች የሚመለከታቸዉ አካላት ጋር  በጋራ ለመስራት የሚያስችለዉን እቅድ አውጥቶ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል። በቅድስት ደጀኔ Join: @yegnatikuret