የጉራጌ ዞን ፍትህ መምሪያ/Gurage Zone Justice Department
Статистикаየዚህ ቻናል ዓላማ ህግና ህግ ነክ ጉዳዮችን በቻናሉ በመልቀቅ ህብረተሰቡ በህግ ላይ እንዳይሳሳት፣ህግ የሚያዘውን እንዲፈፅምና ሙሉ ጊዜው ለልማት እንዲያውል ለማስቻልና በመምሪያው የተከናወኑ አበይት ተግባራት ለህ/ሰቡ ግልፅ ለማድረግ ነው።
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 134
- 1/48двое суток
- 153
- 1/72трое суток
- 165
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
ነሐሴ 01/2018 (ወልቂጤ) የማዕከላዊ ኢትየዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ65 እጩ ዳኞችን ሹመት አጸደቀ ዛሬ በነበረው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ ም/ቤቱ ሹመታቸው ካፀደቀው 65 ዳኞች መካከል ለጉራጌ ዞን ፍ/ቤት ወክለው ሁለት የከፍተኛና አምስት የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች አሹሟል። ሁለቱ ለጉራጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተሾሙት ዳኞቻችን አስቀድሞም ለአንድ ዓመት ያህል በትውስት ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተስበው እንዲሰሩ በዳኞች አስተዳደር ንዑስ ጉባኤ በወሰነው መሠረት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆኑ በዳኝነት ሥራቸው በፍተኛ ዕውቀት፣ በጠንካራ የችሎት አመራር እና የባለጉዳይ አያያዝ እንዲሁም በሥነ ምግባራቸው የተመሠከረላቸው ዳኞች ሲሆኑ አምስቶቹ ለስር ወረዳ ፍርድ ቤቶች የተሾሙት በፍትህ ተቋም ውስጥ በዐቃቤ ሕግነት ሙያቸው እጅግ የተመሠከረላቸው ናቸው። የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ ለምክር ቤቱ እጩ ዳኞችን አቅርበዋል። እጩ ዳኞች በትምህርት ዝግጅት፣በስራ ልምድ፣ በስነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው እና ለዳኝነት ብቁ የሚያደርጋቸውን መስፈርት ያሟሉ ስለመሆኑም ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል። ለክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ፣ለዞኖች፣ለልዩ ወረዳ፣ለረዳ እና ለከተማ አስተዳደር ፍ/ቤቶች በእጩነት የቀረቡት ዳኞች በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሐላ ፈጽመዋል። ምክር ቤቱ በክልሉ ዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በእጩነት የቀረቡ የ65 እጩ ዳኞች ሹመት አጽድቋል። ለሁሉም ተሿሚ ዳኞች የጉራጌዞን ፍትህ መምሪያ እንኳን ደስ አላችሁ ፤መልካም የሥራ ጊዜ ይሁንላችሁ ለማለት ይወዳል።
ምክር ቤቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2019 ዓ/ም ጠቋሚ እቅድ ላይ ተወያይቶ አጸደቀ ነሐሴ 1/2018(ወልቂጤ)፦የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዙር 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 6ኛ መደበኛ ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ እየተካሔደ ነው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት አቶ ኤርሲኖ አቡሬ ለምክር ቤቱ የ2018 በጀት ዓመት አፈጻጸም እና የ2019 ዓ/ም ጠቋሚ እቅድ አቅርበዋል። በክልሉ ካለፈው የተላለፈ 581 አዲስ የቀረበ 26 ሺ391 በጠቅላላ 26 ሺ972 መዛግብት መቅረባቸውን ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል። ከዚህ መካከል 26ሺ475 መዛግብት ላይ ውሳኔ መስጠት ተችሏል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል፡፡ 497 መዛግብት ወደ ቀጣዩ ዓመት የተላለፉ ናቸው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ካለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ 502 መዛግብት ብልጫ አለው፡፡ በፍትሐብሔር ጉዳዮች ካለፈው ዓመት የተላለፈ 1ሺ469 አዲስ 44ሺ 845 በጠቅላላ 46ሺ264 መዛግብት መቅረባቸውን ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል። በፍትሀብሔር ጉዳዮች ላይ 44 ሺ744 መዛግብት ላይ ውሳኔ መስጠት ተችሏል ሲሉም ፕሬዝዳንቱ ጠቁመዋል፡፡ እንደ አቶ ኤርሲኖ ገለጻ 1ሺ520 መዛግብት ወደ ቀጣዩ ዓመት የተላለፉ ናቸው ብለዋል። አፈጻጸሙ ካለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በፍትሀብሔር ከቀረቡ መዛግብት የውሳኔ አሰጣጡ የ7ሺ918 ብልጫ አለው ብለዋል። የፍርድ ቤቶች ውጤታማነትና ቅልጥፍና ከሚለካባቸው ዘዴዎች አንዱ የመዛግብትን የማጣራት አቅም ከፍ አድርጎ መገኘት ነው ሲሉም ፕሬዝዳንቱ አብራርተዋል፡፡ ምክር ቤቱ ለ2019 ዓ/ም ለጠቅላይ ፍ/ቤት እና ለሸሪአ ፍ/ቤት ማስፈጸሚያ 134 ሚሊየን ብር በጀት በሙሉ ድምጽ አጽድቋል። መረጃው የክልሉ መንግስ ኮሚዩኒኬሽን ነው‼
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи