tgindex
Hunayn | ሑነይን | حنين

Hunayn | ሑነይን | حنين

Статистика

Welcome To ሑነይን!✨⚡️✨ በዚህ የቴሌግራም ቻነል ፦ 📌  አጫጭር እና ወሳኝ ማስታወሻዎች 📌  በሑነይን ሚዲያ የሚጋሩ ቪዲዮዎችን ማግኛ ሊንክ ከአጭር ማብራርያ ጋር ለተጨማሪ ሐሳብ እና አስተያየት፦ @Hunaynbot

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
212
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
185
21 постов
Вовлечённость
87,3%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 21
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
50
1/48двое суток
57
1/72трое суток
61

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • ተስፋ (Expectation) በሰዎች ላይ የምታደርገው ተስፋ በጨመረ መጠን፣ ሳያስቡት በሕይወትህ ላይ የሚኖራቸው ተፅዕኖ ይጨምራል። ቃል ይገባሉ፣ እድሎችን ያቀርባሉ። አንተም ቃላቸውን አምነህ እቅድህን ትቀይራለህ፣ ሌሎች እድሎችን ትተዋለህ፣ የወደፊት ዕቅድህንም በቃላቸው ላይ ትገነባለህ። ከዚያ ግን ሕይወት ይቀየራል። ይረሳሉ ወይም ሁኔታቸው በቅፅበት ይለወጣል። እነሱ ሕይወታቸውን ሲቀጥሉ፤ አንተ ግን ባልተፈጸሙ ተስፋዎች ላይ የተገነቡ ዕቅዶችህን ዋጋ ትከፍላለህ። ይህ በሥራ ዓለም ብቻ የሚከሰት አይደለም። በወዳጅነት፣ በቤተሰብ፣ በአብዛኛው ማህበራዊ ግንኙነት ውስጥ ይከሰታል። "ይመጣል" ብለህ የጠበቅኸው ሰው ላይመጣ፤ "ከጎኔ ይቆማል" ብለህ ያሰብከው ሰው ሊሄድ፤ በጣም ያመንከው ሰውም ሊለወጥ ይችላል። እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎች የሰው ተፈጥሮ አካል ናቸው። እውነተኛው የሕመም ምንጭ ግን የእነሱ ድርጊት ብቻ አይደለም። ሰላምህ ሙሉ ለሙሉ ሰዎች ቃላቸውን በመጠበቃቸው ላይ ከተመሠረተ፣ እያንዳንዱ የተሰበረ ቃል ያናውጥሃል። ነገር ግን ልብህ በአላህ ላይ ብቻ ከተደገፈ፣ የሰዎች ቃል መሠረት ሳይሆን ተጨማሪ ፀጋ ይሆናል። ቃላቸውን ከፈፀሙ አልሐምዱሊላህ፤ ካልፈፀሙም አቅጣጫህ፣ ሰላምህና ቁርጠኝነትህ አይለወጥም፤ ምክንያቱም ጉዞህን ከመጀመሪያው በሰዎች ላይ ሳይሆን በአላህ ላይ መሥርተሃልና። "የሰዎች ቃል እንደ አንድ ሊፈፀም የሚችል እድል እንጂ እንደ መሠረት ሊቆጠር አይገባም። ብቸኛው የማይናወጥ ቃል የአላህ እና ለአላህ ተብሎ የተገባ ነው።" https://t.me/Huneynn SHARE💥 for any comment: @hhuneyn

  • የሚዲያ ስንቅ ፡ ክፍል 2 "ከዙሪያህ በሸሹ ነበር ... " https://t.me/Huneynn SHARE💥 for any comment: @hhuneyn

  • እውነተኛ ሙስሊም‼ አንዳንዶች ከራስም በላይ የሚታመኑበት ጊዜ አለ። https://t.me/Huneynn SHARE💥 for any comment: @hhuneyn

  • ባህል Vs ፋሽን/Trend የነዚህ ግብግብ ደግሞ ይለያል። ሁለት የተለያዩ ትውልድ ሰዎች እርስበርሳቸው በጭፍን በሚከተሉት የሕይወት መንገድ ይናናቃሉ። በእድሜ ገፋ ያሉ አባቶች ሲወርድ ሲዋረድ የወረሱትን ባህል ብለው ለሚጠሩት ነገር ሁሉ ነገራቸውን ይከፍላሉ። ራሳቸውን እየጎዱ፥ ህዝቡ ባህሉን ጣሱ እንዳይላቸው ሁሉ ነገራቸውን ይሰጣሉ። በሌላኛው side ደግሞ ወጣቱ generation ፋሽን እና trend እያለ፥ ያስጠላ አያስጠላ ሳይለይ፤ ይጥቀም አይጥቀም ሳይገባው፤ አይኑን ጨፍኖ የሆነን trend ይከተላል። ሁለቱም ነገሮች ላይ ከዲን ካልተጋጨ እና ሌሎችን ካላመሳሰለ ሁለቱንም ማስኬዱ ችግር የለውም። ችግሩ የሚመጣው ራስን በሚጎዱ ባህሎች እና ከኢስላም በራቁ ፋሽኖች ተውጦ ችክ ያለ የባህል እና የፋሽን ተከታይ ሆኖ ሲቀረብ ነው። "ባህላችንን ነው የምንከተለው" የሚሉት ወጣቱን ስብስብ ከባህል የራቀ ባለጌ ያደርጉት እና የራሳቸውን ጎጂ እሳቤ ይረሱታል። ወጣቱ ደግሞ "ባህል ጎጂ ነው፤ ለሰው ተብሎ ማይሆን ነገር ይደረጋል።" ይልና ዞሮ ደግሞ ከእኩዮቹ ጋር በፋሽን እና trend ለመፎካከር ማንነቱን፣ ክብሩንና እምነቱን ይገብራል። ነገሩ ቀላል አይደለም። ማንንም አልሰማም በሚል ብቻ መፍታት የማይቻልበት ከባድ የማህበረሰብ ግፊቶች አሉት። መፍትሄው ምን ይሆን ከልምድ እና ከእውቀታችሁ አካፍሉ ? (@hhuneyn) የማይካደው እውነታ ግን ሁለት ጭፍን ተከታዮች እርስበርስ ሊበሻሸቁ አይገባም። በራስ እንደማሾፍ ይቆጠራል። SHARE💥 https://t.me/Huneynn

  • ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ የጁሙዐህ ኹጥባ ጠንቋይ፣ ድግምት፣ ሩቃ እና አዝካር

  • ሓጃዎቻችን እንዲሳኩ... ነቢያችን ላይ ሰለዋት ማብዛት ሓጃን (ጉዳይን) እንደሚያሳካ፣ ወንጀልን እንደሚያራግፍ ቲርሚዚይ በዘገቡት ሐዲሥ ተነግሯል። ጊዜው የግልም የጋራም (የዲንም የዱኒያም) ሓጃ የበዛባት ሆኗልና ለሱናውም ለጉዳዩም ስንል ነቢያችን ላይ ሰለዋት ማውረድ እናብዛ اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ. ✏️ ዛዱል-መዓድ

  • "አላህ ሆይ ከጥቂቶቹ ባሮችህ አድርገኝ❗️" 👤: فداء الدين يحيى

  • ይብራራ ወይስ ግልፅ ነው ? " ነብዩላህ አደም ጀነት ውስጥ ዘውታሪ መሆንን በዛፉ በኩል በፈለጉ ጊዜ ከሷ በመውጣት ተቀጡ። ነቢዩላህ ዩሱፍ ከእስር መውጣትን ሕልም በፈታላቸው ሳሂብ በኩል በፈለጉ ጊዜ አመታትን በእስር ቆዩ። " ኢብን አልቀይም በአልፈዋኢድ ኪታባቸው https://t.me/Huneynn SHARE💥 for any comment: @hhuneyn

  • TIMING ሰካራምን ሲሰክር ጠብቀህ ደዕዋ ብታደርግለት ትርፉ ጥል እንጂ አላማህን አትመታም። ከቻልክ ቀድመህ መስመር አስይዘው ካልሆነ እስኪረጋጋ ጠብቀው። ሌሎች ዘርፎችም ላይ እንደዚሁ ሰዎች በጋሉበት ሰዓት የሚደረግ ደዕዋ ብሽሽቅ እንጂ ትርፍ የለውም። ወይ ቀድመህ አስታውሳቸው ካልሆነ ሲረጋጉ ገስፃቸው። አመቱን ሙሉ ለጥፋት ሲያኮቦክቡ ዝም ብለህ መብረር ሲጀምሩ ብትጠራቸው አይሰሙህም። በዛው ሰዓት መጥራት ካለብህም ደግሞ ስሜታቸውን በሚገፋ መልኩ ሳይሆን የእውነት ሊሰሙ በሚችሉበት ወንድማዊ ምክር ... for any comment: @hhuneyn

  • የሚዲያ ስንቅ 1 SHARE💥 https://t.me/Huneynn for any comment: @hhuneyn

  • ደርስ vs ማነቃቂያ ብዙውን ጊዜ ሁለት ተደጋጋፊ ነገሮችን አብሮ ማስኬድ ይከብደናል። ያ ደግሞ ከሁለት ማግኘት የምንችለውን ጥቅም ያሳጣናል። ከዚህ በፊት ደዕዋ እና አኽላቅን አይተን ነበር። ሌላኛው ደግሞ ደርሶችን ማለትም የተለያዩ ኪታቦችን ስንቀራ እንደ ሙሐደራ ያሉ ቀልብን የሚያረጥቡ ነገሮችን መዘንጋታችን ነው። አብዝተን ሙሐደራዎችን እየሰማን ደግሞ ቀልባችን ይረጋጋና ቂርአቶችን ችላ ብለን ያለተግባር በነሻጣ እንቆያለን። ለዛም ነው ብዙውን ጊዜ ደርስ ላይ ያሉ ሰዎች የተግባር ዒባዳዎች ላይ ሲዘናጉ የሚስተዋለው፤ በተቃራኒው ደግሞ ብዙ ሰዎች በሚሰሟቸው ማራኪ ደዕዋዎች እና የሰለፎች ገድል ብዙ ጊዜ የተግባር ዒባዳ ላይ ሐይ ይሆናሉ። ለይል ለመስገድ የሚያነቃቃህን ሐዲስ እና የቀደምቶችን ሁኔታ ሁሌ እየሰማህ አሰጋገዱን ካላወክ .. በተቃራኒው ደግሞ አሰጋገዱን በደንብ ተረድተህ ለመስገድ በደንብ የሚያነቃህን ሐዲስ ካልደጋገምክበት በሁለቱም በኩል ይከብድሀል። 2ቱም እውቀቶች ናቸው። አንዱን ምረጡ ያለን የለም። ምናልባት ለዱሩሶች ረጅም ጊዜ መስጠት ሊኖርብን ይችላል፤ ትኩረት እና መገንዘብን ስለሚፈልጉ። ነገር ግን ስንተኛ፣ መንገድ ላይ፣ እረፍት ላይ ስንሆን ጀነትን የሚያስናፍቁ፣ ከጀሃነም የሚያስጠነቅቁ፣ ዒባዳን የሚያስወድዱ ሙሐደራዎችን መስማት ወሳኝ ነው። ቀልብ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አላቸው። ካልሆነ የነሕው ሊቅ፣ የፊቅህ ጎበዝ፣ የዐቂዳህ specialist ሆነህ information ብቻ ይሆንብሃል። በተቃራኒው ደግሞ በሞቅታ ትሰግዳለህ መስፈርት ጥሰህ "ሰላትህን ድገም" የተባለውን ሰው ትሆናለህ። https://t.me/Huneynn SHARE💥 for any comment: @hhuneyn

  • 1 авг.142из abdurezaq27

    ➖ይበልጥ ሊያሳስብና ሊያስለቅስ የሚገባው የወንጀል መደራረብና የስህተት መበራከት ሳይሆን፣ ጥፋትን ተላምዶ በቸልተኝነት መሳቅና የልብ መደንዘዝ ነው። ደጋግ ቀደምቶች በተቅዋና በንጽህና ማማ ላይ ሆነውም እንኳ ከፈጣሪ ፍርሃትና ክብር የተነሳ እንባቸው ይፈስ ነበር፤ ዛሬ ግን በወንጀል ባህር ውስጥ እየዋኙ በፈገግታ መኖር እራሱ በትልቅ የጸጸት እንባ ሊታጠብ የሚገባው የመንፈስ መክሰም ነው።  🎯ከኢብኑ ረጀብ ብዕር ➖صباح الخير ➖ 📱https://t.me/abdurezaq27

  • " እንዲ ብለኸኝ ነበር " የሆነ ጊዜ ላይ ቀለል አድርገህ ያነሳሀት ምክር ሌላኛው አካል ጋር እንደ መርህ ተቀምጣ "እንዲኮ ብለኸኝ ነበር" ብሎ ቃል በቃል እንዳልረሳው ይነግርሃል። ሌላኛውጋ ደግሞ እንደ ቀልድ የጣልካት ነቆራ ቁስል ሆናበት ባየህ ቁጥር በሱ ያስታውስሃል። በአንድ ንግግር የሰውን ቀልብ እና የራስህን አኺራ ታበላሻለህና ረሱል እንዳሉት መልካምን ተናገር አሊያም ዝም በል። ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ሰው፣ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል።» (ቡኻሪና ሙስሊም) https://t.me/Huneynn SHARE💥 for any comment: @hhuneyn

  • አብረው አይሄዱም በክርስትና አስተምህሮ ውስጥ "መርየም ንፁህ ነች"፤ "ዒሳም አይሁዶች በመጥፎ እንደሚገልጹት አይደለም"፤ "አትስረቁ"፣ "አትግደሉ"፣ "አታመንዝሩ" የሚሉ ትዕዛዞች አሉት፡፡ እነዚህን ነገር የሰማ አንድ ሙስሊም " እህ?! እንዲማ ከሆነ ኢስላምም ሚለው ይህን ነው እና እኔ ሙስሊምም ክርስትያንም ነኝ!" ማለት ይችላል? በፍጹም! ክርስቲያኑም ቢሆን እንዲህ አይልም፡፡ ምክንያቱም ስለ ዒሳ ያለን መመሳሰል እስከሆነች ደረጃ ድረስ ነው፡፡ ከዛ በኋላ እነሱ አምላክ ነው ይላሉ እኛ መልዕክተኛ ነው፡፡ ሁለታችንም ቅዱስ ብለን የምንመለስበት መመሪያ መፅሐፋችን የተለያየ ነው፡፡ በሁሉም እምነት ላይ ያሉ አስተማሪዎችም የሚያስቡት አንዱ የሌላኛው እምነት ልክ እንዳልሆነ ነው፡፡ ይሄ ማን ጠፋው እንዳትሉኝ ሀሳቤ እዚህ ላይ አይደለም፡፡ ልክ እንደ ክርስትና ሁሉ ፌሚኒዝምም ከኢስላም ጋር የሚያመሳስለው ጠንካራ መከራከሪያ ሃሳቦች አሉት፤ “ሴት መጨቆን የለባትም”፤ “አጥፊ ወንዶች አሉና ስርዓት መያዝ አለባቸው” እና የመሳሰሉ የሴትን ክብር የሚያስጠብቁ መንገዶች በመፈለግ ላይ ሊያመሳስላቸው ይችላል፡፡ ግና ይህ እምነት እየሆነ የመጣው ፌሚኒዝም ልክ እንደ ክርስትናው ሁሉ ስለ ሴት ልጅ ኢስላም ባስቀመጠው መንገድ ሳይሆን ብዙ ነገሮችን ልቅ በማድረግ፤ እንደዚሁም ከጅማሮው እስካሁን ድረስ ያሉ ዋና ዋና የፌሚኒዝም አቀንቃኞች ስለ ኢስላም የህይወት መንገድነት እምነታቸው -ve ነው፡፡ ሙስሊም ክርስቲያን የሚል የጋራ ስም እንደሌለው ሁሉ ሙስሊም ፌሚኒስት የሚባል ነገርም አይታሰብም፡፡ ሃሳባችን በትንሹ ተመሳሰለ ተብሎ ራስን ወደ ተመሳሰለው ነገር ማስጠጋትም ልክ አይደለም፡፡ ስለዒሳ ነቢይነት እና ክቡርነት ለማውራት ክርስቲያን መሆን እንደማይጠበቀው ሁሉ ስለ ሴት ልጅ ክብር ለማውራትም ፌሚኒስት መሆን የግድ አይደለም፡፡ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ግን አላህ ያግዛቸው የምንተባበርም ያድርገንና ስለ ሴት መብት የሚያወሩ ሁሉ ፌሚኒስት አይደሉም፡፡ ልክ ስለ ዒሳ ክብር ስናወራ ክርስቲያን እንደማያስብለን ማለት ነው፡፡ ስለሆነም ስለሴት መብት የምታወራን ሴት ሁሉ ፌሚንስት እያሉ ማሸማቀቅም ተገቢ አይደለም፡፡ ይልቅ በእንዲህ አይነት ትግል ላይ ያለን ሰዎች የዒሳን በኢስላም ያለውን ደረጃ መናገሩ ከግርግር እና ጥርጣሬ እንደሚያድነው ሁሉ ሌሎች ትግሎቻችንም ላይ ከትግላችን ጎን የሚመጡ አፀያፊ እና የተወገዙ ነገሮችን በግልፅ አውግዞ ራስን ማጥራቱ ተገቢ ነው፡፡ https://t.me/Huneynn SHARE💥 for any comment: @hhuneyn

  • ጠያቂ ትውልድ¿ የሃሳብ ትውልድ፣ ጠያቂ ትውልድ መፈጠር አለበት። "1+1 = 2, 2+1= 3" ... እንደሆነ ተማር መሰረቱን እወቅ ሲባል አሻፈረኝ ያለ ወጣት ... "1+1+1 = 3" ነው። ሲባል ጠያቂ ሆኖ ብቅ ይላል። ... ወይም በማያውቀው ሂሳብ የራሱን ሕግ ፈጥሮ ድምሩን 4 ሊያደርገው ይጣጣራል። የሚገርመው ይሄ አይደለም፤ "3 ነው" ብለው ታማኝ አዋቂዎችን የተከተሉ በሌላ ዘርፍ ያሉ ወገኖችን "መንጋ" ብሎ ሊያራክስ ይፈልጋል። "ህዝቡ አይጠይቅም"፣ "ሃሳብ ይፈራል" እያለም ሊያሸማቅቅ ይሞክራል። ያልነቃን ሰው ማንቃት ቀላል ነው። ነገር ግን አለመንቃቱን አለማወቁ ላይ እንዳወቀ የሚያስብ ሰውን ማንቃት ግን አድካሚ ትግል ነው። አይሰማህም + ኩራት አለ .... ሌላም ሌላም ነገሩ "የሃሳብ ትውልድ መፈጠር የለበትም" እና "ጠያቂ ትውልድ አያስፈልግም" ለማለት አይደለም። መጠየቅም፣ ሃሳብ ማፍለቅም የቁርአን ትእዛዞች ናቸው። ችግሩ ያለው ሁለት ነገር ላይ ነው። 1. ምን መጠየቅ እንዳለበት የማያውቅ፤ ብታስረዳውም base የሌለው ሰው ዝቅ ብሎ ከመማር ይልቅ፥ "ከባባድ" የመሰሉትን ነገሮችን በመጠየቅ ራሱን smart አድርጎ እየቆጠረ፥ ምንም ላይ የሚደርስ ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑ ነው። 2. ሌላው ደግሞ ይህን ዘመቻ እያስጮሁ ያሉ ዋነኛ አካላት ገና የእውቀት ብስለት ላይ ያልደረሱ፤ ከ ሊቃውንት ጋር ያልተገናኙ፤ ሚዲያ በሰጣቸው ነፃነት ብቻ የሚዳፈሩ የኛው ቢጤዎች መሆናቸው ነው። ከዛስ? እነዚህን መሰል ሰዎች ምንም ከማያውቅ ሰው ጋር ተሰባስበው "ጠያቂ" እና "አሳቢ" ሲሆኑ -ve ፍልስፍና ይዘው ቁጭ ይላሉ። አብዝተው ዑለማዎችን ሲያናንቁ እና የራሳቸውን ፊክራ ሲያሰማምሩ የሚታዩትም ዋነኛ ደቋሻቸው የዒልም ሰዎች ስለሆኑ ነው። ጠያቂ ትውልድ ያስፈልጋል። ነገር ግን ምን መጠየቅ እንዳለበት የሚያውቅ፤ የተመለሰን ጥያቄ ደጋግሞ እንዳልገባው የሚጠይቅ ሳይሆን ትክክለኛ ጠያቂ‼ ካልሆነ ግን 3ኛ ክፍል ላይ፥ የማያውቀውን እና ያልደረሰበትን calculus ጠይቆ smart ለመምሰል መሞከር ጠያቂነት ሳይሆን Showoff ያስመስለዋል። SHARE💥 for any comment: @hhuneyn

  • ትዳር፣ ነፍስ እና ጓደኛ ወንዶች ጥንቁቅ እና ጥብቅ ከሚሆኑበት ነገር አንዱ እህታቸውን ወይም ልጃቸውን ለትዳር ጠይቆ የሚመጣን አካል የሚያጠኑበት መንገድ ነው። (ሁሉም ባይሆንም¡) የማስተዳደር አቅሙ፣ ከሰዎች ጋር ያለው ሁኔታ፣ ብስለቱ፣ በአጠቃላይ ምን ያክል አማናውን ለመወጣት ብቁ ነው የሚሉ ነገሮችን አገላብጠው ያጣራሉ። አሁን ግን ስለ ትዳር አጠናናቸው ልናወራ ሳይሆን ከዚህ ሁኔታችን ተነስተን ራሳችንን አና ጓደኞቻችንን በተመለከተ 2 ጥያቄዎች እናንሳ: 1. ጓደኛህ አሁን ያለው ማንነቱ ማለትም ባህሪው፣ ብስለቱ፣ ለዲኑ ያለው ቦታ፣ ግቦቹ እና ሌሎችም መገለጫዎቹ ለልጅህ ወይም ለእህትህ የትዳር አጋርነት ብቁ የሚያደርገው ደረጃ ላይ ነውን? ማለትም ለልጄ የማስበው ወንድ እንደምትለው አይነት ማንነት አለው? 2. አንተስ? ... ያንተን ሙሉ ማንነት የያዘ ካንተ ምንም ያልተለየ ኮፒ ሰው መጥቶ ለትዳር ከቤተሰብህ አንዷን ቢጠይቅ ያለ ምንም ማንገራገር እሺ ትላለህ? NB: በሁለቱም ጥያቄዎች ላይ "ማስተዳደር ይችላል" በሚለው ያዘው እና ትኩረትህን ማንነቱ ላይ አድርግ አዎ ካልክ አዎ ላልክበት ምክንያት አይ ካልክም እንደዚሁ ምክንያት ከዛ ግን የጓደኞችህ ሲሆን አንተም ላይ ተፅዕኖ እየፈጠረ ከሆነ እንዲስተካከል ጥረት አድርግ የራስህም ማንነት ብቁ አይደለም ብለህ ካሰብክ እነዛን ጉድለቶች ለመሙላት ጣር ... አላህ ትዳርን እንዲወፍቅህ እንደምትለምነው ሁሉ ያሉብህን እንከኖችህንም እንዲያጠራልህ ለምነው ... ታገልም! SHARE💥 for any comment: @hhuneyn

  • የሚዲያ ስንቅ በቅርብ ቀን (إن شاء الله) - እስከዛሬ በነበራችሁ የሚዲያ ቆይታ ሙስሊሞች በሁሉም ዘርፍ ቢያስተካክሉት የምትሉት አካሄድ፣ ባህሪ/መገለጫ ምንድን ነው? (ከማብራሪያ ጋር ቢሆን ይመረጣል) @hhuneyn @Hunaynbot

  • 📖 «የብርሃን መንገድ» - ከእንቅልፍ ከነቃንበት የመጀመሪያ ቅጽበት ጀምሮ ማታ ወደ መኝታ እስከምንመለስ ድረስ ሙሉ ቀንን በሱና እንዴት ማሳለፍ እንደምንችል የሚያሳይ መፅሐፍ ... - 1000 ሱናዎች በ24 ሰዓት - አንብቡት፣ ተግብሩት ... ለሌሎችም አጋሩት አላህ በዚህ ጥረት ላይ በረካውን ይክተትበት፤ በዕለት ተዕለት ሕይወታችንም ሱናን የምናድስ ያድርገን!!!

  • "ኢስላም ላይ መቅጠፍ " Propaganda የጁሙዓህ ኹጥባ ሸይኽ ኢልያስ አሕመድ