ŘïĤü ÏSLÄMÏČ PÖST🇵🇸
Статистикаከናንተም ወደ በጎ ነገር የሚጠሩ በመልካም ሥራም የሚያዙ ከክፉ ነገርም የሚከለክሉ ሕዝቦች ይኑሩ፡፡ እነዚያም እነሱ የሚድኑ ናቸው፡፡[3:104] ስህተቶች ስታገኙ አስታከክሉን በረከሏሁ ፊኩም GP @Rihu_islamic_Discussion
- Последний пост
- 12 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 73
- 1/48двое суток
- 83
- 1/72трое суток
- 90
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
እስከመቼ በሰዎች ጥገኛ እንሆናለን?? ለምን ራሳችንን አንችልም?? ለምንስ ራሳችንን አንመስልም??? ሰው በመጣ በሄደ ቁጥር ለምን ልባችን ከዚያ ሰው ጋር ይዋልልብናል??? ለምን ጠንካራ መሆን አቃተን??? ለምንስ ልባችንን ለማይሆነንና ለማይጠቅመን ነገራቶች አሳልፈን ሰጠን?? ለምን አሏህን ብቻ መመኪያችን አናደርገውም??? እስቲ መልሱን ለራሳችን!!
✨ 5 ሊርቋቸው እና ሊጠነቀቋቸው የሚገቡ የሰዎች ዓይነቶች ✨ መልካም ጓደኛ እና መጥፎ ጓደኛ ምሳሌያቸው እንደ ሽቶ ሻጭ እና እሳት ነፊ ነው... — ነቢዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በዱንያ ህይወታችን የዲናችንን እና የልባችንን ሰላም ለመጠበቅ ልንርቃቸው የሚገቡ 5 የሰዎች ዓይነቶች፡ 👇 1️⃣ በጀርባዎ የሚሙሙ (ሐሜተኞች) 🗣️ እርስዎ በሌሉበት ስምዎን የሚያጠፉ። ሐሜት (ጊባ) በዲናችን ከተከለከሉ እና ልብን ከሚያደርቁ ታላላቅ ወንጀሎች አንዱ ነው። 2️⃣ በእርስዎ ፊት ሌሎችን የሚፈርዱ/የሚነቅፉ ⚖️ ከእርስዎ ጋር ተቀምጠው የሌሎችን ጉድለት ብቻ የሚያወሩ። ዛሬ በእርስዎ ፊት ሌላውን ያማ ሰው፣ ነገ የእርስዎን ጉድለት ለሌላው ያወራል። 3️⃣ አሉታዊ ነገሮችን ብቻ የሚያሰራጩ 🌧️ ምንጊዜም ተስፋ የሚያስቆርጡ፣ ጨለማውን ብቻ የሚያሳዩ እና የአላህን እዝነትና አዎንታዊ አስተሳሰብ የሚያስረሱዎት። 4️⃣ መልካም ባህሪዎን ለራሳቸው ጥቅም የሚያውሉ 🎭 የእርስዎን የዋህነት፣ ትዕግስት እና መልካምነት እንደ ድክመት በመቁጠር ለራሳቸው ፍላጎት ብቻ የሚጠቀሙብዎት። 5️⃣ ጉዳይ ሲኖራቸው ብቻ የሚያስታውሱዎት 📲 እርዳታ ወይም ፍላጎት ሲኖራቸው ብቻ ፈልገው የሚያገኙዎት፣ በሌላ ጊዜ ግን የማይጠይቁዎት። አላህ (ሱ.ወ) ልባችንን እና ዲናችንን የሚያንጹ፣ ወደ መልካም ነገር የሚመሩን እና ለአኺራችን የሚጠቅሙን መልካም ጓደኞችን ይግጠመን! 🤲✨ #መልካም_ጓደኛ #ኢስላማዊ_ምክር #የዱንያ_ህይወት #IslamicReminders
ሒጃብሽን ልበሽ ሂጃብሽን ልበሽ ጌታሽ ያዘዘሽን ፣ ከዓጅነቢ ወንድ የሚሸፍንሽን ፣ ከባለጌ ወንዶች የሚጠብቅሽን ፣ ዱንያ ላይ ስትኖሪ የሚያስፀከብርሽን ፣ ነገ በአኼራ ምንዳ የሚያስገኝሽን ፣ አጥብቀሽ ያዥው ውዱ ሂጃብሽን ። እኒያ አላዋቂወች ሂጃብ የአረቦች ነው ብለው የሚያወሩት ፣ ዋጅብም አይደለ ሱና ነው የሚሉት ፣ ያለ እውቀት መናገር ስራቸው ያረጉት ቁርአንን ሀዲስን በደንብ ያልተረዱት ፣ ስሜት ተከታዮች ኡማውን ያስተኙት ፣ በሱና እንዳይጓዝ መሰናክል ሆኑት ሌላም ሲሉ ሰማሁ አንች መች አገባሽ ለምን ተሸፈንሽ ፣ ባልም አይመጣልሽ እንደዚህ ለብሰሽ ፣ እስከምታገቢ ተኳኩለሽ ይዩሽ ፣ ብለው ይሰብኩሻል ከጌታሽ ሊያጣሉሽ ብዙ ያወራሉ ሂጃብሽን ለማስጣል ፣ ከሱና እርቀሽ ወንጀል ላይ ለመጣል አዳምጭኝ እህቴ እውነቱን ልንገርሽ ፣ እነዚህ ጃሂሎች ያሉትንም ቢሉሽ ፣ በሂጃብሽ ፅኚ አላህ ነው ያዘዘሽ ፣ ሁሉ በሱ እጅ ነው ሪዚቅ ሆነ ባልሽ ፣ ዱንያ ላይ ስትኖሪ በሂጃብ ተውበሽ ፣ በዒባዳሽ ጠንክሪ ለአላህ ተናንሰሽ ፣ ሱና ላይ ቀጥ በይ ከወንጀል እርቀሽ ፣ እስከ የውመል ቂያማ አንች የበላይ ነሽ ፣ ነገ በአኼራም ተሸላሚ ሴት ነሽ!!!
" እንዲ ብለኸኝ ነበር " የሆነ ጊዜ ላይ ቀለል አድርገህ ያነሳሀት ምክር ሌላኛው አካል ጋር እንደ መርህ ተቀምጣ "እንዲኮ ብለኸኝ ነበር" ብሎ ቃል በቃል እንዳልረሳው ይነግርሃል። ሌላኛውጋ ደግሞ እንደ ቀልድ የጣልካት ነቆራ ቁስል ሆናበት ባየህ ቁጥር በሱ ያስታውስሃል። በአንድ ንግግር የሰውን ቀልብ እና የራስህን አኺራ ታበላሻለህና ረሱል እንዳሉት መልካምን ተናገር አሊያም ዝም በል። ረሱል ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «በአላህና በመጨረሻው ቀን ያመነ ሰው፣ መልካምን ይናገር ወይም ዝም ይበል።» (ቡኻሪና ሙስሊም) https://t.me/Huneynn SHARE💥 for any comment: @hhuneyn
ጠያቂ ትውልድ¿ የሃሳብ ትውልድ፣ ጠያቂ ትውልድ መፈጠር አለበት። "1+1 = 2, 2+1= 3" ... እንደሆነ ተማር መሰረቱን እወቅ ሲባል አሻፈረኝ ያለ ወጣት ... "1+1+1 = 3" ነው። ሲባል ጠያቂ ሆኖ ብቅ ይላል። ... ወይም በማያውቀው ሂሳብ የራሱን ሕግ ፈጥሮ ድምሩን 4 ሊያደርገው ይጣጣራል። የሚገርመው ይሄ አይደለም፤ "3 ነው" ብለው ታማኝ አዋቂዎችን የተከተሉ በሌላ ዘርፍ ያሉ ወገኖችን "መንጋ" ብሎ ሊያራክስ ይፈልጋል። "ህዝቡ አይጠይቅም"፣ "ሃሳብ ይፈራል" እያለም ሊያሸማቅቅ ይሞክራል። ያልነቃን ሰው ማንቃት ቀላል ነው። ነገር ግን አለመንቃቱን አለማወቁ ላይ እንዳወቀ የሚያስብ ሰውን ማንቃት ግን አድካሚ ትግል ነው። አይሰማህም + ኩራት አለ .... ሌላም ሌላም ነገሩ "የሃሳብ ትውልድ መፈጠር የለበትም" እና "ጠያቂ ትውልድ አያስፈልግም" ለማለት አይደለም። መጠየቅም፣ ሃሳብ ማፍለቅም የቁርአን ትእዛዞች ናቸው። ችግሩ ያለው ሁለት ነገር ላይ ነው። 1. ምን መጠየቅ እንዳለበት የማያውቅ፤ ብታስረዳውም base የሌለው ሰው ዝቅ ብሎ ከመማር ይልቅ፥ "ከባባድ" የመሰሉትን ነገሮችን በመጠየቅ ራሱን smart አድርጎ እየቆጠረ፥ ምንም ላይ የሚደርስ ትውልድ እየተፈጠረ መሆኑ ነው። 2. ሌላው ደግሞ ይህን ዘመቻ እያስጮሁ ያሉ ዋነኛ አካላት ገና የእውቀት ብስለት ላይ ያልደረሱ፤ ከ ሊቃውንት ጋር ያልተገናኙ፤ ሚዲያ በሰጣቸው ነፃነት ብቻ የሚዳፈሩ የኛው ቢጤዎች መሆናቸው ነው። ከዛስ? እነዚህን መሰል ሰዎች ምንም ከማያውቅ ሰው ጋር ተሰባስበው "ጠያቂ" እና "አሳቢ" ሲሆኑ -ve ፍልስፍና ይዘው ቁጭ ይላሉ። አብዝተው ዑለማዎችን ሲያናንቁ እና የራሳቸውን ፊክራ ሲያሰማምሩ የሚታዩትም ዋነኛ ደቋሻቸው የዒልም ሰዎች ስለሆኑ ነው። ጠያቂ ትውልድ ያስፈልጋል። ነገር ግን ምን መጠየቅ እንዳለበት የሚያውቅ፤ የተመለሰን ጥያቄ ደጋግሞ እንዳልገባው የሚጠይቅ ሳይሆን ትክክለኛ ጠያቂ‼ ካልሆነ ግን 3ኛ ክፍል ላይ፥ የማያውቀውን እና ያልደረሰበትን calculus ጠይቆ smart ለመምሰል መሞከር ጠያቂነት ሳይሆን Showoff ያስመስለዋል። SHARE💥 for any comment: @Hunaynbot
🍃 "እንተዛዘን" 🍃 ─━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─ ✨ የህይወት ምልከታዎች እና ወርቃማ ምክሮች ✨ 🔸 ምቀኝነት፡ ጥሩ ለሰራ፣ በጎ ነገር ላበረከተና መክሮ ላስተካከለ ሰው በድብቅም ሆነ በይፋ ዱዓ የማያደርግ ሰው... እሱ ትክክለኛ ምቀኛ ነው። 🔹 እውነተኛ ወዳጅነት፡ ለሰው ትንሽ ውለታ ውሎ፣ መልሱን በበለጠና በተሻለ ሁኔታ ከጓደኛው የሚጠብቅ ሰው... ጓደኛ ሳይሆን አትራፊ ነጋዴ ነው! 🔸 የውሸት ሙገሳ፡ ባልሰራነውና በሌለን ነገር የሚያሞካሸን ሰው ካለ... ከእኛ የሆነ ነገር ሊወስድብን ያሰበ ሊሆን ስለሚችል እንጠንቀቀው። 🔹 የኒያ (አላማ) ጥራት፡ በዲን ውስጥ ለሚሰራው ማንኛውም መልካም ስራ ክፍያውን ከአላህ መፈለግ ሲገባው ከሰው የሚጠብቅ፣ ካልተከፈለውም ሞራሉ የማይነሳሳ ሰው... ከሸይጧንም ቢከፈለው ከመስራት አይመለስም። 🔸 ስንፍና እና ብክነት፡ ጠንክሮ የማይሰራ፣ ባገኘውም ነገር ላይ ብኩን የሆነ ሰው... ድህነት ለሱ በጣም ቅርብ ናት። 🔹 እውነተኛ አድናቆት፡ ስራችንን አይቶ "አላህ ይጨምርልህ፡ አላህ ያቆይህ" ከማለት ይልቅ "አድናቂህ ነኝ" እያለ የሙገሳ ቃላትን ብቻ የሚደረድርልን ሰው... እያሰራን ሳይሆን ስራችንን እያበላሸብን ነው። 👑 ከታላቁ ሶሃባ አብዱላህ ኢብን መስዑድ (ረ.ዐ) አንደበት፡ አንድ ቀን ከአንድ መጅሊስ ሲነሱ ሰዎች ታላቅነታቸውን አውቀው ተከተሏቸው። እርሳቸውም በፍጹም መተናነስ እንዲህ አሏቸው፦ ሰዎች ሆይ! አትከተሉኝ... ወይ እኔ እጠፋለሁ፣ ወይ እናንተ ትጠፋላችሁ! 💡 ጥሩ ነገር ለሰዎች ማጋራት በራሱ በጎ ስራ ነውና ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር (Share) ያድርጉ! ─━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━─
📖 «የብርሃን መንገድ» - ከእንቅልፍ ከነቃንበት የመጀመሪያ ቅጽበት ጀምሮ ማታ ወደ መኝታ እስከምንመለስ ድረስ ሙሉ ቀንን በሱና እንዴት ማሳለፍ እንደምንችል የሚያሳይ መፅሐፍ ... - 1000 ሱናዎች በ24 ሰዓት - አንብቡት፣ ተግብሩት ... ለሌሎችም አጋሩት አላህ በዚህ ጥረት ላይ በረካውን ይክተትበት፤ በዕለት ተዕለት ሕይወታችንም ሱናን የምናድስ ያድርገን!!!
አዕምሮሽን ከውጥረት ነፃ አውጪ! ያልተጨረሱ ስራዎች በአዕምሮሽ ውስጥ እየተመላለሱ የሀሳብ ውጥረት እና የጥፋተኝነት ስሜት ይፈጥራሉ። ወጥነት (consistency) ማለት ስራን መጨረስ ብቻ ሳይሆን ለአዕምሮ ሰላም መስጠትም ነው። በየቀኑ የምትሰሪው ትንሽ እርምጃ እንኳን "ይሄን ጨርሻለሁ" የሚል ትልቅ የአዕምሮ እረፍት ይሰጥሻል። የጀመርሽውን ስትጨርሺ አዕምሮሽ ቀጣዩን ነገር በነፃነት እንዲያስብ እድል ትሰጪዋለሽ። ለአዕምሮሽ ሰላም ስጪው Reset' ማድረግን ተለማመጂ! አንድ ቀን አልሰራሽም? ችግር የለውም። ብዙዎች የሚሰናከሉት በአንድ ስህተት ሳይሆን "አንዴ ካቋረጥኩኝ ምን ዋጋ አለው" በሚል አጥፊ አስተሳሰብ ነው። ይህን አስተሳሰብ በ'Reset' ቁልፍ ቀይሪው። ልክ ስህተትሽን እንዳወቅሽ 'እሺ፣ ያ አልፏል፤ አሁን እንደ አዲስ ልጀምር' በይ። የስኬት ሚስጥር በፍፁም አለመውደቅ ሳይሆን በወደቁ ቁጥር በፍጥነት መነሳት ነው። አላህ ምርጥ ቀን ያድርግልሽ
አንተን እንድትፈራህ አታድርጋት፤ ይልቁኑ ስትፈራ ወደ አንተ እንድትጠጋና እቅፍህ ውስጥ እንድትሸሸግ አድርጋት። ምክንያቱም እውነተኛ ፍቅር ማለት የነፍስ ሰላምና የመንፈስ መረጋጋት እንጂ የፍርሃትና የጥርጣሬ እስር ቤት አይደለም!። ©
🌿 የጁምዓ መልዕክት 🌿 اللهم صل وسلم على نبينا محمد ﷺ ዛሬ ጁምዓ ነው፤ የምህረት፣ የዱዓ እና የአላህን ዝክር የምናበዛበት ቀን። 🤲 ሰላዋትን እናብዛ። 📖 ሱረቱል ካህፍን እናንብብ። 🕌 ወደ ጁምዓ ሰላት ቀድመን እንሂድ። 🤍 ለራሳችን፣ ለወላጆቻችን እና ለመላው ኡማ ዱዓ እናድርግ። اللهم اغفر لنا ولوالدينا ولجميع المسلمين. آمين. 🤍 አላህ የዛሬን ጁምዓ የይቅርታ፣ የረህመት እና የበረካ ቀን ያድርግልን።
የምስራች ለአጋሮ ከተማ ሙስሊም እህቶች! 🌿 ከኡሙ መርየም መድረሳ የተዘጋጀ ልዩ የክረምት የቁርዓንና የሸሪዓ ትምህርት ፕሮግራም 🌿 ክረምትዎን በቁርዓን ብርሃን፣ በጠቃሚ የዲን እውቀት እና በመልካም ስነ-ምግባር ያሳልፉ! 🌸 መድረሳችን ለሁሉም ሙስሊም እህቶች ክፍት ሲሆን፣ የክረምት ትምህርት ምዝገባ በይፋ ተጀምሯል። 📚 የሚሰጡ ትምህርቶች፦ 📖 ቁርዓን 💎 አቂዳ (ትክክለኛ የእምነት መሠረቶች) 🕌 ፊቅህ (የዕለት ተዕለት ኢባዳ ህጎች) 🤝 አዳብ (እስላማዊ ስነ-ምግባር) 🗓 የትምህርት ቀናት፦ ከቅዳሜ እስከ ረቡዕ ⏰ የትምህርት ሰዓት፦ ከሰዓት በኋላ 9:00 – 12:00 📍 አድራሻ፦ አጋሮ ከተማ፣ ተምሳ ሰፈር፣ ወደ ቁጆ ትምህርት ቤት መሄጃ፣ አል-አማን መስጂድ ። 🎯 ዓላማችን፦ ትክክለኛ የዲን እውቀት ያላቸው፣ በቁርዓን የተገነቡ እና ለማህበረሰባቸው ጠቃሚ የሆኑ ሙስሊም እህቶችን ማፍራት ነው ። 📞 ለበለጠ መረጃና ምዝገባ፦ @Bint_Abiha1 @Rihu_Creative እድሉ አያምልጥዎ! ክረምትዎን በእውቀት፣ በኢማን እና በቁርዓን ያሳልፉ! https://t.me/ummumeryemmedresa https://t.me/ummumeryemmedresa
ከሚከተሉት መካከል በአረበኛ ሚዲያ የዩቱዩብ ቻናል የትኛውን ጠቃሚ ትምህርት መማር ይፈልጋሉ ✍የአረበኛ የእጅ ፅሁፍ ትምህርት ✍የአረበኛ ፊደላቶች አነባበብ ትምህርት ✍ሶርፍ/متن البناء في علم التصريف / ✍ነህው/متن الآجرومية/ ✍አረበኛ ቋንቋ/دروس اللغة العربية / ✍ተጅዊድ/تيسير أحكام التجويد / ✍ቁረአን / القرآن الكريم / ✍ሁሉንም በደረጃ ለመማር ወደ ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል https://t.me/arabicmedia1
✍️ ስለ ዓሹራ ጥቅል መረጃዎች!! 💫የዓሹራ ቀን ማለት; አላህ ካተለቃቸውና ዕርም ካደረጋቸው ከአራቱ ወራቶች ውስጥ አንዱ በሆነው በሸህሩል ሙሐረም ውስጥ የሚገኝ ዐስረኛው ቀን ነው። 💫ይህ ቀን; ሙስሊሞች የሚደሰቱበትና ደስታቸውን ለጌታቸው በመጾም የሚያሳልፉበት የሆነ ትልቅ ቀን ነው። 💫የዓሹራ ቀን ማለት; አላህ ነብዩላህ ሙሳ እና ተከታዮቹ ነፃ ያወጣበትና ፊርዓውንና ተከታዮቹን ያጠፋበት የሆነው ቀን ነው። በሓዲስ እንደ መጣው፦ «هذا يوم عظيم أنجى الله فيه موسى وقومه وأغرق فرعون وقومه» «ይህ ቀን አላህ ሙሳንና ህዝቦቹን ነፃ ያወጣበት, ፊርዓውንና ህዝቦቹን ያሰመጠበት የሆነ ትልቅ ቀን ነው።» 💫የዓሹራ ጾም በጃሂሊያ ጊዜ ይጾም ነበር፤ ረመዷን ከመደንገጉ በፊትም በግዴታነት ይጾም ነበር፤ ረመዷን ከተደነገገ በኋላም በተወዳጅነት ይጾማል። በሓዲስ እንደ መጣው፦ « أن قريشا كانت تصوم عاشوراء في الجاهلية ثم أمر رسول الله صلى الله عليه وسلم بصيامه حتى فرض رمضان فقال رسول الله صلى الله عليه وسلم : من شاء فليصمه ومن شاء فليفطره» «ቁረይሾች በጃሂሊያ ጊዜ ሳሉ ዓሹራን ይጾሙ ነበር። ከዝያም ረመዷን እስከ ሚደነገግ ድረስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲጾም አዘዙ። ረመዷን ከተደነገገ በኋላ የፈለገ ይጹመው የፈለገ ይብላበት አሉ።» 💫ዓሹራን የሚጾምበት ምክንያት…… አላህ ለሙሳና ለህዝቦቹ በዋለው ውለታና ፊርዓውንና ህዝቦቹ ለቀጣበት ቅጣት ሙስሊሞች ደስታቸውን ለመግለፅ ነው። የአላህ መልዕክተኛ ለአይሁዶች እንዳሏቸው፦ «فنحن أحق وأولى بموسى منكم فصامه وأمر بصيامه» «እኛ ከእናንተ በላይ ለሙሳ የተገባን (የቀረብን) ሰዎች ነን። ብለው ጾሙት ሌሎችም እንዲጾሙት አዘዙ።» 💫የዓሹራ ቀን መጾም ያለፈውን ዓመት (የአንድ ዓመት) ወንጀል ያስምራል። የአላህ መልዕክተኛ እንዳሉት፦ «صِيَامُ يَوْمِ عَاشُورَاءَ أَحْتَسِبُ عَلَى اللَّهِ أَنْ يُكَفِّرَ السَّنَةَ الَّتِي قَبْلَهُ» «የዓሹራ ቀን ጾም ያለፈውን ዓመት ወንጀል እንዲያስምርልኝ አላህ ዘንድ እከጅላለሁ (ታሳቢ አደርጋለሁ)።» 💫የዓሹራ ጾም ከረመዷን በኋላ በላጩ ጾም በሚለው ይገባል። የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ስላሉ፦ «أَفْضَلُ الصِّيامِ، بَعْدَ رَمَضانَ، شَهْرُ اللهِ المُحَرَّمُ» «ከረመዷን በኋላ በላጩ ጾም ማለት የአላህ ወር የሆነው የሙሐረም ጾም ነው።» 💫የዓሹራ ጾም ማለት የአላህ መልዕክተኛ በጉጉት የሚጠባበቁትና የሚከታተሉት ጾም ነበር። «ما رأيت النبي صلى الله عليه وسلم يتحرى صيام فضله على غيره إلا هذا اليوم يوم عاشوراء وهذا الشهر يعني شهر رمضان» «የአላህ መልዕክተኛﷺ ከሌሎች በተለየ መልኩ የጾሙን ቱሩፋቱን ፈልገውና አስበልጠው እንደ ዓሹራ ቀንና እንደ ረመዷን ወር የሚጠባበቁት ጾም አላየሁም።» 💫የዓሹራ ጾም ካለው አሳሳቢነትና ደረጃ አንፃር ቀኑ የዓሹራ ቀን መሆኑን ሳያውቅ የበላ ሰው ካለ ራሱ የአላህ መልዕክተኛ የተቀረው ቀኑን እንዲጾም ያዙት ነበር። ከባልደረቦቻቸው ለአንዱ እንዲህ ብሎ እንዲጣራ ያዙታል፦ «أن من كان أكل فليصم بقية يومه ومن لم يكن أكل فليصم فإن اليوم يوم عاشوراء» «የበላ ሰው ካለ የተቀረው ቀኑን ይጹም። ያልበላ ሰው ካለም ይጹም። ምክንያቱም ዛሬ ቀኑ የዓሹራ ቀን ነው።» 💫የዓሹራ ጾም ማለት ከሙሐረም ዐስረኛው ቀን ሲሆን በአላህ መልዕክተኛ ትዕዛዝ ወይም ምኞት መሰረት የሁዳዎችን ለመቃረን ተብሎ ዘጠነኛውና ዐስረኛው ቀን ይጾማል። 👉በትዕዛዛቸው ሲባል፦ በየትኛውም ሁኔታ አህለል ኪታቦችን ተቃርነን እንድንገኝ ያዙን ስለ ነበር። 👉በምኞታቸው መሰረት ሲባል፦ ከሕይወታቸው የመጨረሻ የሆነው የዓሹራ ጾም ከጾሙ በኋላ ለቀጣይ ዓመት ግን አይሁዶችን ለመቃረን «ዘጠነኛውም ቀን ጨምረን እንጾማለን» ብለው ነበር። የአላህ ውሳኔ ሆኖ ሳይደርሱ ሞቱ። በዚህም መሰረት፦ የዘንድሮው የዓሹራ ቀን የሚሆነው በአላህ ፍቃድ የፊታችን ሐሙስ ነው። ስለሆነም፦ 👇 👉 እሮብ እና 👉ሐሙስ የምንጾም ይሆናል!! ⛔️ጥብቅ ማሳሰቢያ!! «ዓሹራን ከበስተ ፊቱ አንድ ቀን ወይም ከበስተ ኋላው አንድ ቀን ጹሙ» የሚለው ሐዲስ ዑለሞቻችን እንዳስቀመጡት ሐዲሱ ደዒፍ (ከነብዩ ሙሐመድ ያልተረጋገጠ) ነው። በመሆኑም "ዐስረኛውና ዐስራ አንደኛው እጾማለሁ" በሚል የእሮብ ጾም ማስመለጥ የለብንም። ኢንሻ አላህ 👉እሮብ እና 👉ሐሙስ የዓሹራ ጾማችን እንጾማለን!!
ከሚከተሉት መካከል በአረበኛ ሚዲያ የዩቱዩብ ቻናል የትኛውን ጠቃሚ ትምህርት መማር ይፈልጋሉ ✍የአረበኛ የእጅ ፅሁፍ ትምህርት ✍የአረበኛ ፊደላቶች አነባበብ ትምህርት ✍ሶርፍ/متن البناء في علم التصريف / ✍ነህው/متن الآجرومية/ ✍አረበኛ ቋንቋ/دروس اللغة العربية / ✍ተጅዊድ/تيسير أحكام التجويد / ✍ቁረአን / القرآن الكريم / ✍ሁሉንም በደረጃ ለመማር ወደ ቴሌግራም ቻናል ለመቀላቀል https://t.me/arabicmedia1
✿ የቂያማ ቀን የሚሰጥህ መፅሀፍ ደራሲው አንተ ነህ 🌱 @TewhedandSuna
🌸ከሲስተር ሰባህ ኮርስ የተማርኩት፦ ከጭንቀት ወደ ተረጋጋ ሕይወት 🌸 ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች፣ በተከታተልኩት የሲስተር ሰባህ ስልጠና ላይ ልቤን የነካኝን እና ሁላችንም ልንማረው የሚገባውን አንድ ታላቅ ስነ-ልቦናዊና መንፈሳዊ እውነት ላካፍላችሁ። እሱም በማህበረሰባችን ውስጥ ያለውን ትልቅ የተሳሳተ አመለካከት—«ሴት ልጅ ጀግና የምትባለው ስሜት የሌላት ስትሆን ነው» የሚለውን (Superwoman Schema)…
🌸ከሲስተር ሰባህ ኮርስ የተማርኩት፦ ከጭንቀት ወደ ተረጋጋ ሕይወት 🌸 ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች፣ በተከታተልኩት የሲስተር ሰባህ ስልጠና ላይ ልቤን የነካኝን እና ሁላችንም ልንማረው የሚገባውን አንድ ታላቅ ስነ-ልቦናዊና መንፈሳዊ እውነት ላካፍላችሁ። እሱም በማህበረሰባችን ውስጥ ያለውን ትልቅ የተሳሳተ አመለካከት—«ሴት ልጅ ጀግና የምትባለው ስሜት የሌላት ስትሆን ነው» የሚለውን (Superwoman Schema) አስተሳሰብ ነው። ስሜትን ማፈን «ጀግንነት» ሳይሆን በሽታ ነው! በባህላችን "ጠንካራ ሴት" ለመባል ስንል ከባድ ሐዘን፣ ፍርሃት ወይም ንዴት ሲሰማን ምንም እንዳልተፈጠረ ሆነን በውስጣችን እንቃጠላለን። ነገር ግን ስሜትን ወደ ውስጥ መጫን አእምሯችንን ሁልጊዜ በ «Emergency Mode» ውስጥ ይቆልፈዋል። ይህ ታፍኖ የተቀመጠ ስሜት ደግሞ በውስጣችን እየተጠራቀመ ሄዶ መጨረሻው ለጽኑ ራስ ምታት፣ ለጨጓራ ቁስለት እና ለከፍተኛ የአካል ድካም ይዳርገናል
ሰላት
☀️ የማለዳ ስንቅ ሰው ሆይ! የዛሬ አበባ ነገ አፈር መሆኑን አትርሳ። ህይወት አጭር ናት፤ ሞት ግን አይቀሬ ነው። ﴿كُلُّ نَفْسٍ ذَائِقَةُ الْمَوْتِ﴾ "ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት።" የሞታችንን ቀንና ሰዓት አናውቅም፤ ስለዚህ ከጤንነታችን ለበሽታችን፣ ከህይወታችንም ለአኺራችን እንዘጋጅ። ዱንያ የማይቀር መኖሪያችን ሳይሆን የጉዞ መንገዳችን ብቻ ናት። ከእኛ ጋር የሚሄደው መልካም ሥራችን ብቻ ነው። 🍃 ሰባሐል ኸይር 🍃 @Rihu_islamic_post
🏆 አሁኑኑ ይመዝገቡ! 🏆 👉 12ኛ ዙር – Personal Development (ራስን ማሳደግ) ስልጠና ⏳ ምዝገባው ሊጠናቀቅ 3 ቀን ብቻ ቀረው ‼️ ✨ በዚህ 6 ሳምንት የሚቆይ ስልጠና ውስጥ የምንማራቸው: ✍ ራስን ማሳደግ እና የህይወት እይታ መቀየር ✍ ተግባራዊ ልምምዶች እና የቤት ስራዎች ✍ ራስ መተማመን እና የህይወት ክህሎቶች 📜 ማሳሰቢያ: ስልጠናውን በተሳካ ሁኔታ ለሚጨርሱ ሰልጣኞች ሰርቲፊኬት ይሰጣል ‼️ 🗓 መጀመሪያ: ሐሙስ – ሰኔ 11 🕒 ሰዓት: ምሽት 3:00 📩 ለበለጠ መረጃ: 👉 @Rihu_Creative