tgindex
5killo Jem'a official Channel

5killo Jem'a official Channel

Статистика
@fivekjemaaанглийский

This is the official channel of AAiT jem'a where we provide info abt 👉Jem'a Tutors 👉Trainings and Da'ewa programs 👉Weekly lunches and halaqas(circles) 👉qira'ts (Qur'an and other Kitabs) 👉Weekly Q&A sessions Group: https://t.me/+cw97UaRUF1YzMTg0

Последний пост
14:38
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
15
Всего постов
34
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 156
−2 за 3 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
170
26 постов
Вовлечённость
14,7%
к подписчикам
Постов в день
2,1
всего 34
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
141
1/48двое суток
161
1/72трое суток
174

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • የትምህርት ሚኒስቴሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኢንትራንስ የሚፈተኑ ተማሪዎችን ከመፈተኛ አዳራሽ ገብቶ እየዘየረ ኒቃቢስት ተማሪዎች አትገቡም ተብለው አንድ ሙሉ ፈተና እስኪያልፋቸው ድረስ ከውጭ እንዲቆዩ ተደርገው ነበር። የሗላ ሗላ ኒቃባቸውን ጥለው በማስክ እንዲገቡ ቢሆንም ከዚያ ቀን ቡሃላ ግን ማስኩንም እንደተከለከሉ ተናግረዋል። ይህ እና ሌሎች ነጥቦች፤ ብሎም የመፍትሔ አቅጣጫዎች በሱመያዎቹ ፖድካስት ተዳሷል። https://youtu.be/dwCvc9NIA90?si=p53yOcEtaA-m5mlq በመግባት ተመልከቱ። ለሌሎችም አሰራጩ። ©aaumsu @fivekjemaa

  • የኒቃቢስቷ ጥሪ፦ ኢማሞች በመስጂድ እንድንለብስ ያስተማራችሁንን ዩኒቨርስቲ ስንገባ እየተከለከልን ነው። ስለመብታችን ሊታገል የቆመው መጅሊስ ባለበት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሙስሊም ተማሪዎችን መብት ሲጥስ ከርሟል። ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ሁሉም ሀላፊነቱን ሊወጣ ግድ ነው። የአዳማ ከተማ መጅሊስ፦ ሁላችንም በያለንበት መታገል ግዴታችን ነው። መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ https://vt.tiktok.com/ZS4cKLF1Y/ በመግባት ሪፖስት አድርጉ። ©aaumsu @fivekjemaa

  • በምርቃታቸው ቀን ታሰሩ። ከተመረቁ ቡሃላ ደግሞ ዲግሪያቸውን ተከለከሉ። ይህ ሁሉ "ኒቃብ መልበስ መብት ነው!" - የሚል መልዕክት በለበሱት ሪቫን ላይ በማስቀመጣቸው ነው። ይህ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ቀጣይነት ያለው የመብት ጥሰት ያሳያል። የሐይማኖት ነፃነት መብታችንን እስኪያከብር ጥያቄ አለን። የመናገር ነፃነት መብታችንን እስኪያከብር ጥያቄ አለን። ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ጥያቄ አለን ! መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ https://vt.tiktok.com/ZS4nuKTRG/ በመግባት ሪፖስት አድርጉ። ©aaumsu @fivekjemaa

  • ከታሪክ ገጾች📖…እስካለንበት ተጨባጭ ✍️ ✨ሁሉም ትውልድ የራሱ ሀጃጅ ሲኖረው፤ ሁሉም ሀቅም የራሱ ባለቤት አለው። ✨ ክፍል 2 እውነትን ግፍ የተከተለበትና የሁለት ተቃራኒ ጎዳናዎች የተገናኙበት ታሪክ ነው። ፍሰቱን የጠበቀ በሚመስል መልኩ የጽናት ተምሳሌት የሆነውና እውነትን ለመናገር ሕይወቱን የሰጠው ታቢዒይ 💫 አቡ ዐብደላህ ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር አል-አሰድይ በተወለደ በ2 አመቱ ነበር ስልጣኑን በግፍ የጠመቀው ገዥ ሀጃጅ ኢብን ዩሱፍ አስ-ሰቀፊይ የተወለደው። አላህ ዱንያ ላይ የትኛውንም አይነት ፈተናን ለአንድ አማኝ ባሪያው መስጠቱ ግልጽ ሆኖ ሳለ፣ ባለህ ስልጣን ወይም ደግሞ በተቀመጥክበት ሃላፊነት ላይ ሌሎች ውድ የአላህ ባሮች ጋር መገናኘት ግድ ይሆንና ስልጣንህን ተጠቅመህ በደልህን በመዝራት ኢ- ፍትሃዊነትን ያሰፈንክ እለት ፈተናህን መውደቅህ ብቻ ሳይሆን እረፍት የሌለውና ዘላቂ የሆነ የቅጣት ማእበል ላይ ዘውታሪ እንደምትሆን ማሰቡ ደግ ነው።ሐጃጅ ኢብን ዩሱፍም ምናልባት ፈተናው ይህ ነበር❗️ ስልጣንን ለማግኘት ያለው መንገዱ ገራለት፣እያደገ ሲሄድም ከተወለደበት ከተማ ከጣኢፍ ወደ ሻም ተጓዘ።በዚያም ከኸሊፋው ዐብዱል መሊክ ኢብኑ መርዋን ጋር ተገናኘ። ዐብዱልመሊክ የሐጃጅን ጥንካሬና ቆራጥነት በማየት ከፍተኛ ኃላፊነት ሰጠው። በዚያን ዘመን በመካ የሙስሊሞች መሪ  የነበረው ታላቁ ሶሐቢ ዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይር (ረድየላሁ ዐንሁ) ነበር። እርሱ የታላቁ ሶሐቢ ዙበይር ኢብኑል ዐዋም ልጅ ሲሆን፣ እናቱም የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየላሁ ዐንሁ) ልጅ አስማእ (ረድየላሁ ዐንሃ) ነበረች። ዐብዱል መሊክ ሐጃጅን የሙስሊሞች መሪ  የነበረውን ታላቁን ሶሐቢ ዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይር እንዲገድል ወደ ሒጃዝ ላከው።ታላቅ ሠራዊት አሰልፎ በመሄድም ዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይርን ገደለ፤ የእርሱንም አስተዳደር አበቃ። ከዚያ በኋላ ዐብዱል መሊክ ሐጃጅን የሒጃዝ (መካ፣ የመዲና፣ የጧኢፍ)፤ በኃላም የዒራቅ አስተዳዳሪ አደረገው። ከዚያ ጀምሮ ሐጃጅ ሥልጣኑን በጥብቅ እጅ ማስፈጸም ጀመረ። ፊትነቱል-ቁራእ በተባለው ፊትና የተሳተፉ የታቢዒዮችን ዑለሞች ማሳደድ፣ማሰርና መግደል የዘወትር ሥራው ሆነ ፣በዚህ አደገኛ የስም ዝርዝር ውስጥም ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ይገኛል።     ሐጃጅ ሰዒድን ለመያዝ የጀመረው ፍለጋ አንድ ቀን ወይም አንድ ወር አልነበረም። 🔸 ከስምንት ዓመታት በላይ የቀጠለ ነበር። በቃ እውነታው ይህ ነው፤ዛሬ ላይ ምናልባት አንተ ለያዝከው ሀቅ ከምትከፍለው መስዋእትነት በላይ እጅ እንድትሰጥ፣ እንድትደክም እና ተስፋ እንድትቆርጥ ጠላት በጣም በተደራጀና እጥፍ በሆነ መልኩ ዝቅ ሊያደርግህ ይለፋ፣ ይተጋ ይሆናል። ነገር ግን አይደለም 1 ፣ 2 አመት ጽናቱ ካለህና በአላህ ከታገዝክ ፈተናህ የብዙ አመታት ቢሆን እንኳን ትወጣዋለህ። እናም ሀጃጅ ሰኢድን ማሰስ ከጀመረ ከ8 አመታት በኋላ በወታደሮቹ አማካኝነት በመካ አገኘው እነርሱም አሰረዉት ወደ ሐጃጅ ይዘውት መጓዝ ጀመሩ። በመንገድ ላይ ግን ልብን የሚሰብር ክስተት ተፈጠረ።ሴት ልጁ ከፊት ለፊቱ ተከትላ እየሮጠች ታለቅስ ጀመር።ሰዒድም እንደምንም ራሱን ለማጠናከር ከራሱ ጋር እየታገለ "ልጄ ሆይ! እናትሽን በአላህ ፈቃድ ጀነት ውስጥ እንገናኝ በያት!" አላት። እርሱ የሚሄደው ወደ እስር ብቻ እንዳልሆነ፣ ወደ ሸሂድነት ጉዞ መሆኑን ያውቅ ነበር… ሁኔታው በእርግጥ ከባድ ነው። ነገር ግን ዱንያ ላይ ያለ ነገር በሙሉ እንደ መስዋእትነት ቀርቦ ሀቅ ላይ መጽናት እንዳለብን የተማርንበት ትልቅ ክስተት ነበር። ዛሬ ላይ የአመታትን ልፋት እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ሊያስከፍለን ይችላል። ጽናትና ኢኽላስ ካለ ግን ከአላህ ጋር ሁሉም ይሳካል። የእውነት ድምጽ በስልጣን ፊት ምን ይመስል ይሆን? ክፍል 3 ይቀጥላል……… ✍️ታሪኩን በምን መልኩ ወሰዳችሁት ?! ✍️ምን ትምህርት አገኛችሁበት?! ✍️ ምንስ አስተዋላችሁበት ?! ከታች ባለው ሊንክ አስቀምጡልን @Niqab_issueBot ©aaumsu @fivekjemaa

  • ከታሪክ ገጾች📖…እስካለንበት ተጨባጭ ✍️ ✨ለመፈተን የመጀመሪያዎቹ አይደለንም፤ለመጽናትም የመጨረሻዎቹ አንሆንም።✨ ክፍል 1 << ዘንድሮ >> በውስጡ << ድሮ >> የሚለውን ቃል ይይዛል። ታሪክ ሲተረክ በድሮ ጊዜ ✍️እየተባለ ነው አይደል? ብዙ ድሮዎች ደግሞ አልፈዋል። ግን ያ ያማረው ፣ ድንቁና ወርቃማው በታሪክ ማህደር ውስጥ ውድ ሳሃቦችንና ታቢዒዮችን ያሰፈረው ድሮ ከሌላው በጣም የተለየ ነው። እንደ አንድ ዲኑን ለማወቅ የሚታትር፣ እስልምና ከፍ ብሎ ማየትን የሚሻ እንዲሁም መብቱን አስከብሮ መኖርን በራሱ ላይ ግዴታ ያደረገ ሙስሊም ደግሞ ዘንድሮም እንዳለፈው ድሮ ደምቆ ይሰፍር ዘንድ ካለፈው ታሪክ ያጤናል፣ ትምህርቱን ወስዶ የዛሬውን ጉዞ መስመሩ በተስተካከለው የቀደምቶች መንገድ ላይ ይቀጥላል….. ሂጃብ ለብሶ መማር መሰናክል ሲሆን፣ እህቶች በየመግቢያ በሩ ፣ካፌ እና ላይብረሪ ላይ ሲፈተኑ ማየት ከዛ ደግሞ ያለንበት እውነታን አለም ተረድቶ መፍትሄ ይሰጠን ዘንድ ስንቋምጥ አንድም በታወሩ ልቦች ሁለትም ውሸትን ቀለብ ባደረጉ ህሊናዎች ምን ሆናችሁ? ምን ነካችሁ? መባልና መካድ በጣም ያማል። ይህ ህመም ይሽር ዘንድ መድሃኒቱ የእውነት ደምቆ መታየት መሆኑ ደግሞ እሙን ነው። ግና ምን ያህል ዋጋ ያስከፍለን ይሆን? ለመክፈልስ ዝግጁ ነን❓ ……………………. ለእውነት ሲል በእውነት ላይ ከሞተ 1 ታላቅ ስብእና ፣ የእውነት ሰው እና የጽናት ተምሳሌት የምንወስደው ቁም ነገር አለ። ነገሩ እንዲህ ነው👇 በ38ተኛው ዓ.ሂ በኩፋ ከተማ አንድ ሕፃን ተወለደ። ይህ የሆነው በአራተኛው ኸሊፋ፣ በዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (ረድየላሁ ዐንሁ) ዘመን ነበር። በዚያን ጊዜ ማንም ይህ ሕፃን በኋላ ከታቢዒዮች እና ታላላቅ ዑለማዎች አንዱ እንደሚሆን፣ በተፍሲር፣ በሐዲሥና በፊቅህ ውስጥ የማይረሳ ስም እንደሚተው፣ እውነትንም ለመጠበቅ እስከሞት ድረስ እንደሚቆም አያውቅም ነበር። ……………………. ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ በጧኢፍ ሌላ ሕፃን ተወለደ። አንዱ በእውቀትና በኢማን ይታወቃል፤ሌላው በኀይልና በጭካኔ አንዱ ሰዎችን ወደ አላህ ይጠራል፤ሌላው በሥልጣኑ ያስፈራራል። የሁለቱ መንገድ ከዓመታት በኋላ ይገናኛል፤ ያ ግንኙነትም በእስልምና ታሪክ ውስጥ በጣም አስደናቂና ትምህርት የሞላበት ክስተት ይሆናል። የዚህ ባለሁለት መንገዱ አስደናቂ ታሪክና ክስተት ባለቤት የሆኑት ሁለቱ ህጻናት እነማን ይሁኑ?🤔 ክፍል 2 ይቀጥላል… ©aaumsu @fivekjemaa

  • 🔵 ( الدُنيا تَقولُ بِمِلءِ فيها حَذارِ حَذارِ مِن بَطشي وَفَتكي وَلا يَغرُركُم حُسنُ اِبتِسامي فَقَولي مُضحِكٌ وَالفِعلُ مُبكي)  ⚪️ ​هِيَ الدُنيا تَقولُ بِمِلءِ فيها ⚫️ ያቺ ዱንያ በሙሉ አፏ አውጥታ (በጎላ ድምፅ) ትናገራለች፦ ⚪️ ​حَذارِ حَذارِ مِن بَطشي وَفَتكي ⚫️ «ተጠንቀቁ! ተጠንቀቁ ከኃይሌና ከጥቃቴ (ከጥፋቴ)! ⚪️ ​وَلا يَغرُركُم حُسنُ اِبتِسامي ⚫️ በፈገግታዬ ማማርና ውበት አትታለሉ፤ ⚪️ ​فَقَولي مُضحِكٌ وَالفِعلُ مُبكي ⚫️ ንግግሬ የሚያስቅ ቢሆንም፥ ድርጊቴ ግን የሚያስለቅስ (የሚያስከፋ) ነውና።» ©

  • አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ የዐቂደቱ ጠሀዊያ ኪታብ ተጠናቋል ‼️ አልሐምዱሊላህ! ከወራት በፊት የጀመርነው የኢማም አቡ ጃዕፈር አጠሓዊ رحمه الله የዐቂዳ ኪታብ የሆነው «አቂደቱ ጠሓዊያ» (العقيدة الطحاوية) ደርስ በአላህ ፈቃድ ተጠናቋል። በመጀመሪያ ያስጀመረንና እስከ መጨረሻው ያደረሰን አላህን እናመሰግናለን፣ ጊዜያቸውን ለእኛ በመስጠት፣ ኪታቡን በጥልቀት በማስተማር በተነሱት ርዕሶች ዙሪያ በርካታ መሠረታዊ ቃዒዳዎችን በማስጨበጥ ለወራት ላስተማሩን ኡስታዝ ዘንጀቢል ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን። አላህ በያስተማሩት እያንዳንዱ ዕውቀት ታላቅ ምንዳን እንዲፅፍላቸው እንከጅላለን፣ ያስተማሩትንም ዕውቀት ለእነርሱ የሚያስቀጥል ሰደቃ ጃሪያ ያድርግላቸው። 💬 ኡስታዛችን በደርሱ ወቅት የሚያስታውሱን አንድ ውብ ንግግር አለ፦ “ሁሌም ከፍታን ለመውጣት በማሰብ ብዙዎች ይጀምራሉ፤ ነገር ግን በጣም ጥቂቶች ብቻ ከከፍታው ጫፍ ይደርሳሉ።” እናንተም ይህንን ደርስ ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው በጽናትና በትጋት የተከታተላችሁ ተማሪዎች፣ ለዚህ ታላቅ ጉዞ ምስጋና ይገባችኋል። ነገር ግን የተማርነው እዚህ ላይ አያበቃም። የዐቂዳ ዕውቀት የሚጠይቀው መማር፣ መረዳት፣ መጠበቅ እና በእርሱ መሥራት ነው። ስለዚህ የተማራችሁትን በተደጋጋሚ ሙራጀዓ (مراجعة) ማድረግን አትዘንጉ። አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ይላል፦ ﴿فَاعْلَمْ أَنَّهُ لَا إِلَٰهَ إِلَّا اللَّهُ وَاسْتَغْفِرْ لِذَنبِكَ﴾ “ከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ እንደሌለ እወቅ፤ ለኃጢአትህም ምሕረትን ለምን።” 📌 ሙሐመድ 47፥19 ይህ አያህ በመጀመሪያ “እወቅ” ብሎ የተውሒድን ዕውቀት ያስቀድማል። ትክክለኛ ዐቂዳን መማርና መረዳት የሙስሊም ሕይወት መሠረት ነው። ውድ ተማሪዎቻችን! አላህ በተማራችሁት ላይ ይጨምርላችሁ፤ የተማራችሁትን በሕይወታችሁ ላይ የምትተገብሩበት፣ ለሌሎችም የምታስተላልፉት ያድርጋችሁ። 🤲 አላህ ዕውቀታችንን ይጨምርልን ፣ በተማርነውም ላይ እንድንሠራ ያግዘን። አሚን። 📢 ኢንሻአላህ የኦንላይን ቂርዓታችን ይቀጥላል! 👉 5 ኪሎ ጀማዓ ቂርዓት Channel https://t.me/qirat_channel_5k ይቀላቀሉ! ‼️ @fivekjemaa

  • ‹‹በታሪካቸው ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች በእርግጥ መገሠጫ ነበር፡፡›› (ዩሱፍ 12፡ 111) የሕይወት መመሪያና መርህ የሆነው ቁርኣን፣ አንድ ሦስተኛው ያህል በተለያዩ ታሪኮች የተሞላ ነው። ታሪኩን ከተረከልን በኋላ ከትረካው እውቀት እንቀስም ዘንድ ያመላክተናል ‹‹ይህን ሁሉ (የቀደምት) መልእክተኞች ታሪክ በርሱ ልብህን ልናፀና ተረክንልህ።›› (ሁድ 11፡ 120) (አስተዋይ) ልቦና ላለው፣ (ተግሳጽንም ለማድመጥ) ጆሮውን ለከፈተ፣ (እውነትን) ለመሰከረ በዚህ (ታሪክ) ውስጥ ተግሳጽ አለበት::›› (ቃ9: 50:37) 🍂ከትናንት ጥልቀት የተገኙ፣ ዛሬን የሚያበሩ•• 🍂ህይወትን በአዲስ መልክ ማየትን የሚያስችሉ ልዩ ታሪኮች! 💥ከ ዛሬ ጀምሮ ዘውትር ቅዳሜ እና እሁድ ይከታተሉ ~> @aaumsu መልካም ሙሉ ሰው መሆኛ ጊዜ!!✨ ©aaumsu @fivekjemaa

  • 💭ሚሽካት!! የ ታሪክን ገጾች ስላደመቁ ጊዜያት እና ስብዕናዎች ምንመለከትበት ልዩ መድረክ ✨ ታሪክ•• ታሪክ ትናንትን ለማወቅ፤ ዛሬን ለመረዳትና ለነገ ለማቀድ ያግዛል። ታሪክ ያለው ሕዝብ በአግባቡ ከተጠቀመበት ታሪክ ይሠራል! ወደፊት መጓዝ የፈለገ መጀመሪያ ወደ ኋላ ተመልሶ ታሪኩን ይፈትሻል:: የአባቶቹንና የአያቶቹን ገድል ሲረዳ በምን ሁናቴ ውስጥ እንዳለፉ ግልጽ ብሎ ይታየዋል። የዛሬው እርሱነቱ የበርካታ…

  • 🎉ዛሬ ጁመዓ ነው በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን እናብዛ🎉 ۝ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ۝ ﷺ 🌟🌟اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم في العالمين إنك حميد مجيد🌟🌟 ۩ ከጁምዓ ቀን ሱናዎች፦ ➊ መታጠብ ➋ ሽቶ መቀባት(ለወንዶች) ➌ መፋቂያ(ሲዋክ) መጠቀም ➍ ቆንጆ ልብስ መልበስ ➎ ሱረቱል ካህፍ መቅራት "ሱረቱል ካህፍን በጁምዓ ቀን መቅራት፤ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል የሚበራ ብርሃን (ኑር) ይሆንልሃል/ ይሆንልሻል።" ይህ ማለት አላህ እስከሚቀጥለው አርብ ድረስ ልባችንን በብርሃን ይሞላዋል፣ ትክክለኛውንና ስህተቱን የምንለይበትን ጥበብ ይሰጠናል ማለት ነው። ➏ በጊዜ መስጂድ መግባት ➐ ዱዓ እና ሰለዋት ማብዛት ﷺ በውዱ ነብያችን ላይ ሶለዋት ማብዛትንም አንርሳ❤️ اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم تسليماً كثيراً ﷺ 🌟 መልካም ጁምአ🌟 @fivekjemaa

5killo Jem'a official Channel — tgindex