Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union
СтатистикаThis is the official Channel of Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union.
- Последний пост
- 10:07
- Последнее чтение
- 12:02
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Видео (по похожим)
- В каталоге с
- 12 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 228
- 1/48двое суток
- 1 407
- 1/72трое суток
- 1 517
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
2) ኢትዮጵያስ ሁሉንም ዜጎቿን በእኩልነት እያገለገለች ነውን? 3) የኢትዮጵያ የሆኑ ነገሮች ሁሉ በእኩልና በፍትሃዊ መልኩ ሁሉም እየተወከሉበት፣እኩል ተጠቃሚ ሆነውበታል? ሁሉንስ ከግምት ያስገቡ ሆነው ተዋቅረዋልን? የሙስሊሞች ጥያቄ ከመስጂድ ቅጥር ውጭ ይዘልቃል። ወደ ታሪክ አካታችነት ይሄዳል። ወደ ትምህርት ስርዓትና አተገባበር ያመራል። ወደ አካታች ኢኮኖሚም ይገባል። ወደ የቅርስና የባህል ጥበቃ ይሄዳል። ወደ ሀገራዊ ምልክቶችና መገለጫዎችም ይደርሳል። ወደ ሴቶችና ህፃናት መብትም ይዘልቃል። የ ሰብዓዊ መብት ጉዳይም ነው። ወደ አሳታፊና አካታች የተቋማት ግንባታ ይሄዳል። ፍትሃዊ ውክልናንም ይመለከታል። ወደ ፍትሕ ስርዓቱ ይገባል። በዜግነት ጉዳዮች በኩል ይመዘዛል። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ከመስገድና ከመነገድ በላይ የዘለቁ ጥያቄዎች የፍትሕ፣ የእኩልነት፣ የውክልና እና የሙሉ ዜግነት ጉዳዮች ናቸው! ይህ የሙስሊሞች ጥያቄ ብቻ አይደለም። ይህ የኢትዮጵያ የሀገር ግንባታ ጥያቄዎች ናቸው። የአካታችነትና በሁሉም እርከን በፍትሃዊነት የመወከል ጥያቄ ነው። የሀገር ባለቤትነት ጥያቄ ነው። ይድረስ ለኮሚሽነሮቹ! 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 በሀገራዊ የምክክር ሂደት ውስጥ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ጥያቄዎች በስምንቱ አጀንዳዎች ዉስጥ የተዘረዘሩትን ሰብስቦ በአንድ “የሃይማኖት ጉዳይ” ሳጥን ውስጥ መክተት የመፍትሔ መንገድ ሳይሆን የመዋቅራዊ ችግሩን ሥር የሚያስቀጥል አካሄድ ነው። እውነተኛ ሀገራዊ መግባባት የሚገኘው የዜጎችን መብት በአስተዳደራዊ ማጣሪያዎች ወይም በሃይማኖታዊ ሳጥኖች ውስጥ በመክተት ሳይሆን፣ እውነተኛ አካታችነት ማለት የሙስሊሞችንም ሆነ የየትኛውም ወገንን በየተነሱበት አጀንዳዎች ስር ከነአውዳቸው ሳይሸፋፈኑና በጥቅል ገለጻ ስር ሳይደበቁ በዚያው በተጠቀሱበት አኳኋን ምክረ ሀሳቦቹ በየተገቢው አጀንዳ ውስጥ ማስቀመጥና መፍትሄ እንዲያገኝ ማድረግ ሲቻል ብቻ ነው። እውነተኛ ፍትሕ ማለት በየተቋሙ ያለውን መዋቅራዊ እንቅፋት መለየትና ማስወገድ ነው። እውነተኛ ሀገር ግንባታ ማለት ሁሉም ዜጎች በሀገራቸው ውስጥ እኩል ባለቤትነት እንዲሰማቸው ማድረግ ነው።
በእውነት የሚገርመው ምንድን ነው? አንዲት ሙስሊም ተማሪ በሂጃቧ ምክንያት ብትገለል፣ ይህ የሴቶች መብት ጉዳይ ነው ወይስ የመጅሊስ ጉዳይ? የሙስሊሞች ታሪካዊ ቅርሶች በብሔራዊ ትረካ ውስጥ ቢጠፋ፣ ይህ የባህልና ቅርስ ጉዳይ ነው ወይስ የሃይማኖት ጉዳይ? ከወለድ ነፃ ፋይናንስ በበቂ ሁኔታ አለመዳረሱ የአሳታፊ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጉዳይ ነው ወይስ የሃይማኖት ጉዳይ? አንድ ሙስሊም ዜጋ በመንግሥት ተቋማት ውስጥ እኩል ዕድል እንዲኖረው ሲጠይቅ ይህ የዜግነት ጥያቄ ነው ወይስ የሃይማኖት? በፌደራልም ሆነ በክልል በቢሮክራሲ፣ በዳኝነት፣በሕዝብ ተወካዮች ተቋማት ወይም በውሳኔ ሰጪ መድረኮች የሚነሱ የውክልና ጥያቄዎች የሃይማኖት ጉዳይ ናቸውን? እነዚህ ጥያቄዎች መልሳቸው ግልጽ ነው። ችግሩ የሃይማኖት ተቋማት ችግር አይደለም። ችግሩ የሀገራዊ ተቋማት አካታችነት ችግር ነው። "ጥያቄ ስታነሱ ሴኩላሪዝም ትዝ አለኝ" 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 በሀገራችን የታዘብኩት አንድ የቆየ አሳሳቢ አዝማሚያ አለ። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በታሪክ፣ በፍትሕ፣ በውክልና፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በሰብዓዊ መብቶች፣ በተቋማት አካታችነት ወይም በሕገ-መንግሥታዊ መብቶች ዙሪያ ማንኛውንም ጥያቄ ሲያነሱ፣ ወዲያውኑ “ሴኩላሪዝም” ትዝ የሚላቸው መገኖች አሉ። በሁሉም መስክና ስፍራ እኩልነት በተግባር ጥያቄ ሲነሳ እነዚህ ወገኖች ሴኩላሪዝምን (የመንግስት ነፃ በመሆን ዓለማዊነትን) ጉዳይ በማንሳት ውይይቱን ወደ “ሃይማኖት ጉዳይ” ብቻ ለመግፋት የሚሞክሩ አካላትን ደጋግመን ታዝበናል። እነዚህ አካላት ጉዳዩን በዜግነት፣ በሰብዓዊ መብት፣ በሕገ-መንግሥታዊ እኩልነት፣ በተቋማዊ ፍትሕ ወይም በሀገር ግንባታ ማዕቀፍ ከማየት ይልቅ ወደ ሃይማኖታዊ ማዕቀፍ ብቻ ለማሳነስ ይሞክራሉ። በዚህ ሂደት የሙስሊሞች ጥያቄ ዜጎች የሚያነሱት ሀገራዊ ጥያቄ ሳይሆን የአንድ ሃይማኖት ውስጣዊ ጉዳይ እንደሆነ ለማቅረብ ይሞክራሉ። ይህ ግን ለሴኩላሪዝም ጥብቅና መቆም አይደለም፤ የዜግነት ጥያቄን ባህሪ መቀየርና በሴኩላሪዝም ስም ማፈን ነው። ሴኩላሪዝም ማለት መንግሥት ሃይማኖት ሳይኖረው በገለልተኛነት የሁሉምና ለሁሉም የሚመች፣ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት በሀገራቸው ጉዳዮች እንዲሳተፉ የሚያስችል የገለልተኝነት መርህ እንጂ ማንኛውንም ማህበረሰብ ከሀገራዊ ጉዳዮች ማግለል ወይም ጥያቄዎቹን ወደ ሃይማኖት ሳጥን ውስጥ መክተት አይደለም። የሙስሊሞችን ማንኛውንም ጥያቄዎች ወደ “ሃይማኖት” ማውረድ የእኩል ዜግነትን ክርክር ከመሰረቱ ማዛባት ነው። የሀገራዊ የምክክሩ ትምህርት 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 በቅርቡ በተካሄዱ ሀገራዊ ውይይቶች አንድ አሳሳቢ አዝማሚያ ታይቷል። ከሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚነሱ የታሪክ፣ የፍትሕ፣ የውክልና፣ የኢኮኖሚ፣ የሴቶች መብት፣ የትምህርት፣ የባህል፣ የመሬት አጠቃቀም፣ የፋይናንስ፣ የሲቪክ ተሳትፎ እና የተቋማት አካታችነት ጥያቄዎችን በሙሉ “የሃይማኖት ጉዳይ” በሚል ርዕስ ስር ለማጠቃለል የተደረገ ጥረት ታይቷል። ይህ ከቀላል የአጀንዳ አመዳደብ ስህተት በላይ ነው። ይህ የታሪካዊ ማግለል ዘመናዊ ቅጂ ነው። ጥያቄዎችን “ባለቤት አልባ” ማድረግ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የተደራጁ በርካታ ሚኒስቴሮችና ተቋማት አሏት። የንግድ ጉዳይ የንግድ ተቋማትን ይመለከታል። የባህልና ቱሪዝም ጉዳይ ተቋማቱን ይመለከታል። የትምህርት ጉዳይ የትምህርት ተቋምን ይመለከታል። የሙስሊም ሴቶች መብት ጉዳይ የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትርን ይመለከታል። አይመለከተኝም ካለ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስያሜውን "የሙስሊም ያልሆኑ ሴቶች ጉዳይ ሚኒስቴር" ብሎ ይቀይር።የሙስሊም ሴቶች ጉዳይ የመጅሊስ ጉዳይ ብቻ የሚሆንበት ሁኔታ ማብቃት አለበት። የአካታች ፋይናንስ ጉዳይ የፋይናንስ ተቋማትን ይመለከታል። የተቋማት አካታችነት ጉዳይ የመንግሥት ተቋማትን ይመለከታል። እነዚህን ሁሉ በ“ሃይማኖት” ስም ወደ አንድ ተቋም መግፋት ማለት ጥያቄውን ከሚመለከተው ዋና ተቋም የማራቅ ስልት ነው። በዚህ ሁኔታ ተጠያቂ የሆኑ ተቋማት ከኃላፊነታቸው ይሸሻሉ።በተጨማሪም ጥያቄው መፍትሔ የሚያገኝበትን መንገድ ያጣል። ምክንያቱም የሃይማኖት ጉዳይ ተቋም በካቢኔ ውክልና፣ በመከላከያ ፖሊሲ፣ በትምህርት ሥርዓት፣ በመሬት አጠቃቀም ወይም በብሔራዊ ታሪክ አጻጻፍ ላይ ውሳኔ የመስጠት ሕጋዊ ሥልጣን የለውም። ስለዚህ ጥያቄው ከአንድ ቢሮ ወደ ሌላ ሲዘዋወር ይቆያል፤ መፍትሔ ግን አያገኝም። የታሪክ ጥያቄ የኢትዮጵያ ታሪክ ሲጻፍ ሙስሊሞች በምን ያህል ተካተዋል? የሀገሪቱ የንግድ ታሪክ፣ የስልጣኔ ታሪክ፣ የሙስሊም ሊቃውንት ታሪክ፣ የሙስሊም መሪዎች አስተዋጽኦ፣ የሙስሊም ማህበረሰቦች የሀገር ግንባታ ሚና በብሔራዊ ትረካ ውስጥ ምን ያህል ቦታ አግኝተዋል? ይህ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። ይህ የታሪክ ፍትሕ ጥያቄ ነው። "ሙስሊሞች እኩል ዜጎች ከሆኑ" ✅✅✅✅✅✅✅✅✅ 1) በሀገራዊ ታሪክ ውስጥ እኩል ተወክለዋልን? 2) በባህልና ቱሪዝም ተቋማት ሥራዎች ውስጥ እኩል ተካተዋልን? 3) በትምህርት መጻህፍት ትረካዎች ውስጥ እኩል ተገልጸዋልን? 4) በፖሊሲ ውሳኔዎች ውስጥ እኩል የመወሰን ድምፅ አላቸውን? 5) በተቋማት ውስጥ እኩል ውክልና አላቸውን? 6) በውሳኔ ሰጪ መድረኮች ውስጥ እኩል ተሳትፎ አላቸውን? 7) በሀገራዊ ምልክቶችና መገለጫዎች ውስጥ እኩል ታይተዋልን? 8) በብሔራዊ ትረካዎች ውስጥ እኩል ቦታ አግኝተዋልን?... በርካታ ጥያቄዎችን ጨምሩበት። እነዚህን ጥያቄዎች ማንሳት ልዩ ጥቅም መጠየቅ አይደለም። እነዚህን ጥያቄዎች ማንሳት የእኩል ዜግነት ጥያቄ ነው። የሙስሊሞች ጉዳይ የሃይማኖት ጉዳይ ነውን? ⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕ የጥያቄውን ትክክለኛ ባህሪ መለየት አስፈላጊ ነው። አንድ ሙስሊም ዜጋ ሀገሩን በወታደራዊ ተቋማት ለማገልገል ሲፈልግ ከእምነቱ ወይም ከሙስሊምነቱ አንዳንድ መገለጫዎች እንዲተው ከተጠየቀ፣ ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የተቋማት አካታችነት፣ የእኩል ዕድል እና የዜግነት ጥያቄ ነው። አንዲት ሙስሊም ሴት በአለባበሷ ወይም በሃይማኖታዊ ማንነቷ ምክንያት በሥራ ቦታ ዕድል ከተነፈገች፣ ይህ የሠራተኛ መብት፣ የእኩልነት እና የሕገ-መንግሥታዊ መብት ጉዳይ ነው። አንድ ሙስሊም ተማሪ በሙስሊምነቱ ወይም በሃይማኖታዊ መገለጫው ምክንያት ከትምህርት ቤት ከተገለለ፣ ይህ የመጅሊስ ጉዳይ ሳይሆን የትምህርት መብት፣ የዜግነት እና የሕግ የበላይነት ጉዳይ ነው። መስጂዶች ሲቃጠሉ፣ሲፈርሱ ወይም ኢማሞች ሲገደሉ፣ ይህ የሀገሪቱ የሰላምና የደህንነት አጀንዳ እንጂ የሙስሊሞች ጉዳይ አይደለም። የሕግ ማስከበር እና የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለባቸው ተቋማትን የሚመለከት ጉዳይ ነው። በአጠቃላይ ጥያቄውን የሚወስነው ጉዳዩን ያነሳው ሰው ሙስሊም መሆኑ ሳይሆን የተጣሰው መብት፣ የተፈጠረው ችግር እና መፍትሔ የሚሰጠው ተቋም ነው። ስለዚህ ሙስሊሞች የሚያነሱትን እያንዳንዱን ጥያቄ “የሃይማኖት ጉዳይ” ብሎ መፈረጅ የጥያቄውን እውነተኛ ባህሪ መሸፈን እና ከተጠያቂ ተቋማት ማራቅ ነው። ኢትዮጵያ እኩል የሁላችንም ነች? ከቃል ባሻገር በተግባር እንዴት ይገለጻል? 🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒 “እስላም ከሰገደና ከነገደ ሌላ ምን ይፈልጋል?” የሚለው ጥያቄ በመሠረቱ የተሳሳተ ጥያቄ ነው። መቅረብ ያለባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። 1) ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውንና ወገናቸውን የማገልገል እኩል እድል አግኝተዋልን?
"እስላም ከሰገደና ከነገደ ሌላ ምን ይፈልጋል?" 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 የዜግነት ጥያቄዎችን በ“ሃይማኖት ጉዳዮች” ሳጥን ውስጥ የማፈን መዋቅራዊ አደጋ እና የተቋማዊ ማግለል አሰራር አደጋ። 📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶 በአሕመዲን ጀበል 🔴🔴🔴🔴🔴🔴 “እስላም ከሰገደና ከነገደ ሌላ ምን ይፈልጋል?” የሚለው አባባል አዲስ አይደለም። በዘመናት የተወረሰ፣ በትውልዶች የተደጋገመ፣ ዛሬም በይፋ ባይነገርም በተለያዩ መንገዶች የሚገለጽ የሚታይ አመለካከት ነው። በቀድሞ ዘመን በቀጥታ ይነገር ነበር፤ ዛሬ ግን በተቋማት አሰራር፣ በፖሊሲ አቀራረብ፣ በሚዲያ ትረካዎች፣ በሀገራዊ ውይይቶች እና በውሳኔ ሰጪ መድረኮች ውስጥ በዘመናዊ መልክ ተሸፍኖ መቀጠሉን እናያለን። ይህ አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ጥያቄዎች ወደ መንፈሳዊና ኢኮኖሚያዊ ብቻ የማድረግ ስልታዊ ማግለል መገለጫ ነው። በምክክሩ ሙስሊሞች የገጠማቸው ተግዳሮቶች 📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶 እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ ምክክር ሙስሊም ተሳታፊዎችን ከገጠሟቸው ተግዳሮቶች አንዱና ዋነኛው በርካቶች ዘንድ "ሙስሊም ከሰገደና ከነገደ ሌላ ምን ይፈልጋል?" የሚለው እይታ መኖሩን መታዘቡና ከዚሁ እይታ የተነሳ ሙስሊሞች ከሃይማኖት ጉዳዮች አጀንዳ ውጭ ባሉ ጉዳዮች የሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ምክረ ሀሳቦች በሚያዙ ቃለጉባኤዎች ዉስጥ እንዳይካተቱ የሚታገሉ አካላትን በግልጽ መጋፈጣቸው ነው። የሚገርመው አብዛኞቹ መሰል አካላት የራሳቸው አንዳች አጀንዳዎች፣ጥያቄዎች የሌላቸውና የነርሱ አጀንዳ የሙስሊሞች አጀንዳ እንዳይካተት ማድረግ እስኪመስል ራሳቸውን አጋልጠዋል። በዚህ ስንኩል አመለካከት ባለቤቶች መካከል በሀላፊነት ላይ ያሉትም ጭምር ሆነው መገኘታቸው አሳዛኙ ሁኔታ ነው። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በሀገር ግንባታ፣ በሀገር ባለቤትነት ጉዳዮች፣በታሪክ ፣የጋራ ሀገራዊ ማንነት እና እሴቶች፣ብዝኃነት እና አስተዳደር ጉዳዮች፣ የባህል፣ ታሪክ እና ቅርስ ጥበቃ ጉዳዮች ጥያቄዎች አሏቸው። በመንግሥት ምሥረታ፣ በተቋም ግንባታ፣ሰላም ግንባታ፣ግጭት መንስኤዎች እና አፈታት መንገዶች፣ ማህበራዊ ኢኮኖሚ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶአደሮች ጉዳዮች፣ህገ መንግስታዊ እና ህጋዊ ማዕቀፍ በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ፣የመልካም አስተዳደር ችግር እና የሙስና ጉዳዮች ምክረሀሳብ አሏቸው። ሙስሊሞች በ8ቱም አጀንዳዎች የሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ምክረ ሀሳቦች ከየአጀንዳዎቹ ስር ተሰርዘው ወደ ሃይማኖት አጀንዳ ብቻ ይሂዱ የሚለው እይታ የተሳታፊዎች ብቻ አልነበረም። ኮሚሽኑ በመደባቸው ጥቂት አወያዮች፣ አስተባባሪዎችና ጥቂት ኮሚሽነሮች ዘንድም ተንጸባርቋል። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በየአጀንዳዎቹ ሥር ያነሷቸውን ምክረ ሀሳቦች ለቃቅሞ ወደ የሃይማኖት አጀንዳ ሥር ለመውሰድ መሞከር ማለት ተራ የአሰራር ጉዳይ አይደለም።እንድምታው አደገኛ ነው። "ከሀገራዊ አጀንዳዎች ለማራቅ ወደ ሃይማኖት ጉዳዮች ግፏቸው!" ✅✅✅✅✅✅💢💢💢💢💢💢💢 አንድም የናንተን ሀሳብ ከሃይማኖት አንፃር ብቻ ነው የምናየው እያሉ ነው።አልያም ከሃይማኖት ጉዳይ በቀር ስለሌላው አይመለከታችሁም ፣ወይም ከሃይማኖት አጀንዳ እንድትወጡ አንፈቅድላችሁም ነው። ይህ በራሱ ሌላ ሀገራዊ ምክክር የሚፈልግ ሸውራራ እይታ ነው። በመጀመሪያ እይታ ይህ አባባል ቀላል ጥያቄ ሊመስል ይችላል። ግን በውስጡ ጥልቅ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና መዋቅራዊ እሳቤ ይዞ ይመጣል። ለምን? ምክንያቱም ይህ አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ከሀገሪቱ አጠቃላይ ጉዳዮች እየገፋ ወደ “ሃይማኖት” ብቻ ለመወሰን ይሞክራል። በፍትሕ ላይ ጥያቄ ቢያነሱ ወደ ሃይማኖት ይገፋሉ። በታሪክ ላይ ቢናገሩ ወደ ሃይማኖት ይገፋሉ። በኢኮኖሚ ላይ ቢጠይቁ ወደ ሃይማኖት ይገፋሉ። በተቋማት ውክልና ላይ ቢወያዩ ወደ ሃይማኖት ይገፋሉ። የጥያቄው ርዕስ ቢቀየርም የሚቀርበው መልስ አንድ ነው፤ “ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ነው” የሚለው።ነገር ግን ይህ የችግሩ መፍትሔ አይደለም፤ የችግሩ መሸፈኛ ነው። ሁለቱ አደገኛ እሳቤዎች ❌❌❌❌❌❌❌ “እስላም ከሰገደና ከነገደ ሌላ ምን ይፈልጋል?” የሚለው አባባል ሁለት አደገኛ እሳቤዎችን ይሸከማል። ሀ) ሙስሊሞችን ማሳነስ 🔶🔶🔶🔶🔶🔶🔶 ይህ አባባል ሙስሊሞችን ከሀገር ግንባታ፣ ከእውቀት ምርት፣ ከሳይንስ፣ ከፖለቲካ፣ ከባህል፣ ከተቋማት ግንባታ፣ ከውሳኔ ሰጪነት እና ከሀገራዊ አጀንዳዎች ውጭ ያሉ ሰዎች እንደሆኑ ያቀርባቸዋል። ሙስሊሙ እንደ መምህር አይታይም። እንደ ሳይንቲስት አይታይም። እንደ ዳኛ አይታይም። እንደ ፖሊሲ አውጪ አይታይም። እንደ ታሪክ ባለቤት አይታይም። እንደ ሙሉ ዜጋም አይታይም። እንደ ሃይማኖታዊ ማህበረሰብ ብቻ እንዲታይ ይደረጋል። ለ) ሙስሊሞችን በሁለት መስኮች ብቻ መገደብ 🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺 ሁለተኛው አደገኛ እሳቤ ሙስሊሞችን በሁለት መስኮች ብቻ በመስገድና በመነገድ ለመገደብ ያለ ፍላጎት ነው። ይህ አመለካከት ሙስሊሞች በመስጂድ ውስጥ እንዲቆዩ ወይም በንግድ እንዲሰማሩ ሊፈቅድ ይችላል። ነገር ግን በታሪክ አጻጻፍ፣ በሀገራዊ ትረካ፣ በትምህርት ፖሊሲ፣ በተቋማት ግንባታ፣ በመከላከያ፣ በዳኝነት፣በሲቪል ሰርቪስ፣ በሚዲያ ፣ በባህል ተቋማት፣ በውሳኔ ሰጪ መድረኮች፣ በሀገራዊ ምልክቶች እና በሀገር ባለቤትነት ስሜት ውስጥ እኩል ተሳታፊ እንዳይሆኑ በተዘዋዋሪ መንገድ ይገፋፋል። የዜግነት ጥያቄን ወደ ሃይማኖት ነጻነት ማውረድ ⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕ የችግሩ መሠረት አንድ ነው፤ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሚያነሱትን ማንኛውንም ጥያቄ እንደ “ሃይማኖታዊ ጥያቄ” ብቻ መመልከት። ነገር ግን እውነተኛው ጥያቄ ይህ ነው፦ ሙስሊሞች በዚህች ሀገር ላይ የሚያነሱት ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ ብቻ ነውን? መልሱ ግልጽ ነው። አይደለም። ሙስሊሞች የሚያነሱት ጥያቄ የዜግነት ጥያቄ ነው። ስለ ፍትሕ ሲናገሩ፣ ስለ ተቋማዊ ውክልና ሲጠይቁ፣ ስለ ታሪክ አጻጻፍ ሲከራከሩ፣ ስለ ባህል ቅርስ ሲጠይቁ፣ ስለ ኢኮኖሚ ተሳትፎ ሲወያዩ፣ ስለ ኢስላማዊ ፋይናንስ ሲነሱ፣ ስለ እኩል ትምህርት ዕድል ሲናገሩ፣ ስለ አሳታፊ የሥራ ዕድል ሲጠይቁ፣ ስለ ሴቶች መብት ሲያነሱ፣ ስለ ሰብዓዊ መብቶች ሲወያዩ፣ ስለ መሬት አጠቃቀም ሲከራከሩ፣ ስለ ተቋማት አካታችነት ሲጠይቁ፣ ስለ ውሳኔ ሰጪነት ሲወያዩ፣ የሚያነሱት ጥያቄ የዜግነት ጥያቄ ነው። ይህ የመስጂድ ጥያቄ ብቻ አይደለም። ይህ የሂጃብ ጥያቄ ብቻ አይደለም። ይህ የመጅሊስ ጥያቄ ብቻ አይደለም። ይህ የእኩል ዜግነት ጥያቄ ነው። የጥያቄውን ባህሪ የመቀየር አደገኛነት 💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥 አንድ ማህበረሰብ የሚያነሳውን የመብት ጥያቄ “ሃይማኖታዊ” ብቻ ብሎ መፈረጅ በእውነቱ የጥያቄውን ባህሪ መቀየር ነው። የፍትሕ ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። የኢኮኖሚ ተሳትፎ ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። የባህልና ቅርስ ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። የታሪክ ውክልና ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። የመንግሥት ተቋማት አካታችነት ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ ሊሆን አይችልም። የሙስሊም ይሁን የክርስቲያን የሴቶች መብት ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። የትምህርት ፖሊሲ ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። የውክልና ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ እንዴት ሊሆን ይችላል? እነዚህ ሁሉ የዜግነት፣ የፍትሕ፣ የእኩልነት እና የሀገር ግንባታ ጥያቄዎች ናቸው።
ሀገራዊ ምክክሩ ዘመናትን ለተሻገረው የሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያመጣ እንጠይቃለን። መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ በኢንስታግራም https://www.instagram.com/reel/Db_G8VCMmHu/?igsh=aHJiMHNvMmZyaGs2 በመግባት ያሰራጩ። https://t.me/EHEMSU
በምርቃታቸው ቀን ታሰሩ። ከተመረቁ ቡሃላ ደግሞ ዲግሪያቸውን ተከለከሉ። ይህ ሁሉ "ኒቃብ መልበስ መብት ነው!" - የሚል መልዕክት በለበሱት ሪቫን ላይ በማስቀመጣቸው ነው። ይህ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ቀጣይነት ያለው የመብት ጥሰት ያሳያል። የሐይማኖት ነፃነት መብታችንን እስኪያከብር ጥያቄ አለን። የመናገር ነፃነት መብታችንን እስኪያከብር ጥያቄ አለን። ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ጥያቄ አለን ! መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ https://vt.tiktok.com/ZS4nuKTRG/ በመግባት ሪፖስት አድርጉ። ©️ aaumsu https://t.me/EHEMSU
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ ተማሪዎቹ እየደረሰባቸው ስላሉ የመብት ጥሰቶች አቤቱታ ለማቅረብ ከ20 በላይ ተቋማት ዘንድ ሄዶ ነበር። ቅሬታዎቹ፤ ብሎም የተቋማቱ ምላሽ ምን ነበር ስለሚለው በቅርቡ በትንታኔ የሚቀርብ ይሆናል። እስከዚያ https://www.tiktok.com/@aaumsu/video/7669761759632264469?is_from_webapp=1&sender_device=pc በመግባት መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ እናድርግ። እኛ የጥያቄ አለን ትውልዶች ነን! https://t.me/EHEMSU
"ሴኩላሪዝም አልጠራልንም። ሴኩላሪዝም Atheism (ሀይማኖት የለሽነት) የሚመስላቸው አሉ። አንድ ተማሪ አልሐምዱሊላህ ሲል ሴኩላሪዝም የተጣሰ የሚመስላቸው አሉ። በምሳ ሰዓት አንድ ተማሪ ሶላት ልስገድ ሲል ልምን አትሰግድም ይባላል። ምን አገባው? ይህ እኮ ሰብዓዊ መብቴ ነው።" - አልዩ ሰዒድ (በፌደራል መጅሊስ የትምህርት ክፍል ዳይሬክተር) ከበር አውልቀነው የምንገባው ሀይማኖት የለንም። ሴኩላሪዝም የትምህርት ስርዓቱን ከሐይማኖት ተፅዕኖ ነፃ ያወጣል እንጅ፤ በሴኩላሪዝም ስም እኛ ከሀይማኖት ነፃ እንድንሆን አንገደድም። ለሁላችንም የሚሆን ቻለንጅ፦ መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ https://vt.tiktok.com/ZSXwfPJ2n/ በመግባት ኮፒሊንክ ሪፖስት አድርጉ። ይህ ለጥያቄ አለን ትውልድ ቀላሉ ሀላፊነት ነው። ወደ ተግባር ! ! ! https://t.me/EHEMSU
በፈረንሳይ ሀገር ሙስሊም ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ሲገቡ ሒጃባቸውን ጥለው እንዲገቡ ይገደዳሉ። ልክ በአክሱም እንደተደረገው፤ በጉንችሬ እንደተደረገው፤ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሊደረግ መመሪያ እንደወጣለት ማለት ነው። የሀይማኖት ነፃነት መብት የት ነው? የመማር ነፃነት የት ነው? ሰብዓዊ መብት የት ነው? ዛሬ ኒቃብን ካስወለቁ ነገ ፀጉር ግለጡ ማለታቸው አይቀርም። ሆኖም ግን ፈፅሞ አይሆንም!!! ቻሌንጅ ለሁላችን፦ መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ በቲክቶክ በመግባት ኮፒሊንክ ሪፖስት እናድርግ። ሊንኩ https://vt.tiktok.com/ZSXcA1HkJ/ ነው። ይህ በዚህ መንገድ ትንሹ ሀላፊነታችን ነው ! ወደ ተግባር !! ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! ! https://t.me/EHEMSU
"የሀይማኖት ጉዳዮች በሀገራዊ ምክክሩ ላይ አጀንዳ ይሆን ዘንድ ሕዝበ ሙስሊሙ ታግሏል። ሙስሊም ተማሪዎችም ዘርፈብዙ የሆነ ንቅናቄ አድርገዋል። ሀገራዊ ምክክሩ እንደተቋጨ የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄዎች ዘላቂ፣ ፍትሐዊ እና ተፈፃሚ ምላሽ ሊያገኙ ይገባል።" - ሙሐመድአሚን ካሳው ቻሌንጅ ለሁላችን፦ መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ በቲክቶክ በመግባት ኮፒሊንክ ሪፖስት እናድርግ። ሊንኩ https://vt.tiktok.com/ZSX7DFQ2R/ ነው። ይህ በዚህ መንገድ ትንሹ ሀላፊነታችን ነው ! ወደ ተግባር !! ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! ! https://t.me/EHEMSU
Ethiopian Higher Education Institutions Muslim Students' Union pinned a photo
በአምቦ ዩኒቨርስቲ የወሊሶ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድን በጋራ እንገንባ !!! መስጂዱ በጥቂት ተማሪዎች እና በኸይር ሰሪዎች ርብርብ ከተጀመረ 13 አመታትን አስቆጥሯል። አሁን ላይ ግራውንዱ ወደ መጠናቀቅ ሄዶ ሁለተኛው floor ተጀምሯል። እንደዚሁም ሆኖ የታችኛውን ክፍል በመጋረጃ ከፍለው ነው የሚጠቀሙት። የጁምዓ ቀን እና ረመዳን ሲገባ ግን ከቦታ ጥበት አንፃር ለሁሉም ሰጋጅ አይብቃቃም። ይህ መስጂድ ተጠናቆ የታሰበለትን ዘርፈብዙ አገልግሎት ለሁሉም ይሰጥ ዘንድ ብዙ ሚልዬን ብሮች ያስፈልጋል። ይህ ይሆን ዘንድም ከቻልነው፤ በአቅማችን ልክ አስተዋፅዖ እንድናደርግ ጥሪ አቅርበዋል። የአላህን ቤት ዱንያ ላይ የገነባ አላህ የአኼራ ቤቱን ይገነባለታል። የተማሪዎችን መስጂድ በጋራ በመገንባት የሚሰግዱበትን፤ የሚማማሩበትን፤ ዱንያ አኼራቸውን የሚሰሩበትን ቦታ እናስረክብ። መስጂድ ትውልድ የሚሰራበት ማዕከል ነው። አካውንት፦ 1000542634417 (አምቦ ዩኒቨርስቲ ወሊሶ ካምፓስ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ)። ያስገባችሁበትን screenshot @eheimsubot ላኩልን። ለሒሳብም ለማነቃቂያም ይውላልና:: አላህ በጀነተል-ፊርደውስ ይሰብስበን! አላህ ለመልካም ለውጥ ሰበብ ያድርገንም!! https://t.me/EHEMSU
በሀገራዊ ምክክር ላይ የሕዝበ ሙስሊሙን አጀንዳዎች ይዘው ለቀረቡ ተወካዮች ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት የተላለፈ መልዕክት፦ ሀገራዊ ችግሮችን በምክክር ለመፍታት እና የሀገራችንን እጣፋንታ በውይይት ለማስመር የተጀመረው እና ለ30 ቀናት የሚቆየው ሀገራዊ ምክክር በታሪክ ስለሀገራዊ ችግሮቻችን ውይይት ለማድረግ የመጣ ታሪካዊ እድል፤ በአግባቡ ከተጠቀምንበት ደግሞ ጥያቄዎቻችን በውይይት ምላሽ የሚያገኙበት የድል መድረክ ነው። በተለይም ከ8ቱ የምክክር አጀንዳዎች 4ተኛ እና 5ተኛ የሆኑት የሀይማኖት ጉዳዮች፤ የተቋማት ግንባታ የሕግ የበላይነት እና ሰብዓዊ መብቶች አጀንዳዎች ሙስሊሙ ማህበረሰብ ከትምህርት ቤቶች ጀምሮ በሴኩላሪዝም እና መሰል የዳቦ ስሞች እየደረሱበት የነበሩትን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ተከትሎ ያደረገውን ሰላማዊ ትግል ተከትሎ ወደ መድረክ የመጡ ናቸው። ከምክክሩ ቡሃላ በሀይማኖት ነፃነት እና በሴኩላሪዝም መካከል ያለው ቅርርብ እና ርቀት፤ ትክክለኛው ኢትዮጵያዊ ሴኩላሪዝም፤ የሙስሊም ተማሪዎች የሀይማኖት ነፃነት መብቶቻቸው እንደሚበየኑ እና ፍትሐዊ በሆነ መልኩ ተግባራዊ የሚደረጉበት መንገድ እንደሚቀመጥ እናምናለን። ስለሆነም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ተወክላችሁ ወደ ምክክሩ ለገባችሁ የሚከተሉት መልዕክቶች አሉን፦ ፨ ሀገራችን ሴኩላር ሆና ሙስሊሙ ማህበረሰብ የሐይማኖት ነፃነት መብቱ ተከብሮለት ይኖር፣ ይማር እና ይሰራ ዘንድ በአባቶቻችን የተከፈለው መስዋዕትነት በታሪክ መዝገብ ደምቆ ያለ ነው። ለዚህ ጉዳይ መሳካት የነበረውን መስዋዕትነት፣ መናበብ፣ ቁርጠኝነት እና ህዝባዊ ተሳትፎ እነ ሐጂ ሙሐመድ ሳኒ ሀቢብ (ረህመቱላሂ ዐለይህ) በየቢሮው እየዞሩ ከሚያስገቡት ደብዳቤ፣ ከሚያቀርቡት ቅሬታ፣ ከሚያደርጉት ክርክር ባሻገር በሚያዚያ 12 / 1966 ሕዝበ ሙስሊሙ መቶ ሺዎችን ሆኖ ሰልፍ በማድረግ ባሰማው ተቃውሞ፤ ይህንንም ተከትሎ የነበሩ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን በሰለጠነ መንገድ ማካሄዳቸው የሚጠቀስ ነው። የነበረው ስኬት የሐይማኖት ነፃነት እና እኩልነት መብቶቻችንን በወረቀት እንዲሰፍሩ ማድረግ ቢችልም እነዚህ መብቶቻችን ግን የትምህርት ተቋማትን አጥር ማለፍ ሳይችሉ፤ ወደ ሕዝብ አደባባዮች እና የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሳይሻገሩ፤ ከአየር መንገድም ሳይገቡ ሙስሊሙ ማህበረሰብ ለተደጋጋሚ ጭቆና እና ትግል እንዲጋለጥ አድርጎታል። እንደ ሙስሊም ተማሪ ከቅርብ ጊዜያት ጀምሮ በትምህርት ተቋማት ውስጥ እያገረሸ በመጣው ሙስሊምጠልነት ለመሠል የመብት ጥሰቶች እና ጥያቄዎች ተጋላጭ መሆናችንን ተከትሎ መፍትሔ ለመሻት ወደተለያዩ ተቋማት ስናቀና እንድንጠብቅ ከተነገሩን መድረኮች መካከል የሀገራዊ ምክክሩ ዋነኛው ነው። ስለሆነም በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የሚደርሰው መዋቅራዊ መድሎ እና ጭቆና ታሪክ ሆኖ ያልፍ ዘንድ የተገኘውን ታሪካዊ መድረክ በአግባቡ መጠቀም የሁላችንም ሀላፊነት ነው። እድል ሆኖም ለምክክሩ የታጫችሁ ሰዎች አማና ነውና ሙሉ ትኩረታችሁን ከምክክሩ ላይ አድርጋችሁ፤ ስለሕዝበ ሙስሊሙ ዘርፈብዙ ጥያቄዎች ትሟገቱ፤ መብቶቻችን በዘላቂነት የሚተገበሩበት መንገድ እንዲፀኑ ትሰሩ ዘንድ ሀላፊነታችሁ ነው። አላህ ያግዛችሁ። መብቶቻችን ተከብረው በነፃነት በእኩልነት እና በፍትሕ የምንኖርባትን ሀገር ይስጠን። ©️ aaumsu @EHEMSU
"ሕልሜ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲን መቀላቀል ቢሆንም ኒቃብን የሚከለክልን መመሪያ ማውጣቱ እና በኒቃቢስቶች ላይ የሚደርሰው እንግልት ግን ሌላን እንዳስብ እያደረገኝ ነው። ስለሆነም የሚመለከታችሁ አካላት መብታችንን አስከብሩና ሕልማችንን እናሳካ።" - ከ Moonlight አካዳሚ እንደ አጠቃላይ አንደኛ ወጥታ የወርቅ ተሸላሚ የሆነችው ኒቃቢስቷ አስማ አህመድ ዩኒቨርስቲው ያወጣው ጨቋኝ መመሪያ ተፅዕኖ በውስጡ ከሚማሩት ተማሪዎች አልፎ ሕልማቸውን በዩኒቨርስቲው ለመማር ለሚያደርጉት ጭምር ነው። "ኒቃብን ለብሶ መማር አይቻልም!" - የሚልን መመሪያ ሲያወጣ ኒቃባቸውን ለብሰው የሚማሩትን ሁሉ ወደ ዩኒቨርስቲው አትምጡ የሚል መከልከያ እያስቀመጠ ነው። ለዚህም ነው ጥያቄው የሁሉም ሙስሊም ማህበረሰብ የሆነው። ለዚህም ነው ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ጀምሮ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፤ ከወላጅ እስከ ሰራተኛ ስለ ሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጉዳይ መጠየቅ ያለበት። አንድም ተማሪ ቢሆን ሙስሊም ስለሆነ ከትምህርት ሊጨናገፍ አይገባም። አንድም ተማሪ ቢሆን በእስልምናው ምክንያት ከትምህርት ሊታገድ አይገባም። አንዲት እህትም ብትሆን በኒቃቧ ምክንያት ህልሟ ሊከስም አይገባም። መብቷ ተከብሮ እንድትማር ማድረጉ የመንግስት ግዴታ ነው። ኒቃቧን እንደለበሰች እንድትማር ማመቻቸቱ የመጅሊስ ሀላሊፊነት ነው። ምንም አይነት የመብት ጥሰት ሳይደርስባት በነፃነት እንድትማር ማድረጉ የእኔ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የሁላችን ሀላፊነት ነው። የዚህ ትውልድ፤ የጥዬቄ አለን ትውልድ ሀላፊነት ነው። በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የሚደርሰው የመብት ጥሰት ወደ ቀጣዩ ትውለድ አይሻገርም! ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! ! @EHEMSU
በመመረቂያ ቀኗ ሽልማቷን የተነፈገችው የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪ ሁዳ በቀለ ዝርዝር ጉዳይ ምንድን ነው? ከተማሪዋ አንደበት ያዳምጡ። የዩኒቨርስቲው ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ አቋምስ ምንድን ነው? የጀመዓው ምክትል አሚር ማብራሪያ ሰጥቷል። የሚጠበቀው መፍትሔስ ምንድን ነው? የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ህብረት ፕሬዚዳንት ሙሐመድአሚን ካሳው ዳስሷል። ሙሉውን https://youtu.be/MO2v5Kn7_Uo?si=VHIlLQLiVbYuynz5 በሙባረክ ፖድካስት ያዳምጡ። ለሌሎችም share ያድርጉ። @EHEMSU
видео или голосовое, без подписи
የአምቦ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ 3.93 በማምጣት ሰቃይ ሆና ሳለ በሽልማት መድረክ ላይ ሽልማቷን ለተነፈገችው ተማሪ ሁዳ በቀለ እውቅና ሰጠ!!! ተማሪ ሁዳ (መቅደስ) በቀለ በ2018 ዓ.ል ከአምቦ ዩኒቨርስቲ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ተሸላሚ የነበረች ቢሆንም ዩኒቨርስቲው በተማሪዎች ምረቃ እለት እውቅናም ሽልማትም ሳይሰጣት አልፏል። ይህ መሆኑ በተማሪዋ ስነ-ልቦና ላይ ከፍተኛ ጫና ከመፍጠር ባሻገር የተፈጠረው ክፍተት በማህበረሰቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ቅሬታ ፈጥሯል። ይህንንም ተከትሎ ዩኒቨርስቲው ለአንድ ሚዲያ በሰጠው ቃል የተፈጠረው የቴክኒክ ችግር መሆኑን ተከትሎ ቢሮ ጠርቶ ይቅርታ እንደጠየቃት አሳውቋል። ሆኖም ግን ማህበረሰቡ የጠየቀው ጥያቄ በአደባባይ የተነፈገው ክብር፣ እውቅና እና ሽልማት በአደባባይ እንዲመለስ፤ የሚገባት ሽልማት ሙሉ ለሙሉ እንዲመለስ እንዲሁም ለተፈጠረባት የሞራል ጉዳት ካሳ እንዲከፈላት ሆኖ ሳለ ቢሮ ላይ ይቅርታ ጠይቄያለሁ ብሎ ማለፍ የማህበረሰቡን ጥያቄ ችላ ማለት እንደሆነ ተገልጿል። የዩኒቨርስቲው ሙስሊም ተማሪዎች ጀመዓ እውቅና እና መጠነኛ ሽልማት ያበረከተላት ሲሆን ፍትሕ እንዲሰፍንም ጥሪ አቅርቧል። @EHEMSU
ዛሬም ኒቃባቸውን በአደባባይ አውልቀው እንዲገቡ ተገደዋል! በትላንትናው እለት የ12ተኛ ክፍል ኢንትራንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በአብርሆት ቤተመፅሐፍት እየተፈተኑ ባለበት ከ20 በላይ ሙስሊም ተማሪዎችን "ኒቃባችሁን ካላወለቃችሁ አትገቡም!" - ተብለው ጓደኞቻቸው ውስጥ እየተፈተኑ እና በትምህርት ሚኒስቴሩ ሚንስትር ብርሃኑ ነጋ እየተጎበኙ ለ3 ሰዓታት ያክል ከውጪ እንዲሆኑ ተደርጎ ነበር። የሗላ ሗላ እንዲገቡ ቢደረግም ኒቃባቸውን አውልቀው እና ጥለው በማስክ ነበር። መፍትሔ እንደሚመጣ የተገለፀ ቢሆንም በዛሬው እለትም በተመሳሳይ ኒቃባቸውን በአደባባይ እያወለቁ እንዲገቡ ነው የተደረጉት። ይህ ግልፅ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ነው። ይህ ግልፅ የሆነ የሀይማኖት መብት ጥሰት ነው። ይህ ግልፅ የሆነ የነፃነት መብት ጥሰት ነው። ኒቃብን መልበስ መብት ነው። መብት ስለሆነም ለብሳው ስትማር ነበር። አሁን ላይ እየተፈፀመ ያለው ውንብድና ተማሪዎችን የስነ-ልቦና መቃወስ ውስጥ እየከተታቸው ነው። ተማሪዎችም አስቸኳይ መፍትሔ እንዲመጣላቸው እየጠየቁ ነው። መጅሊስ መፍትሔ ይመጣ ዘንድ ይስራ። መንግስት ተጠያቂ መደረግ ያለባቸውን አካላት ተጠያቂ ያድርግ። ዘላቂ መፍትሔም ይምጣ!!! @EHEMSU
አምቦ ዩኒቨርስቲ ምላሽ ሰጥቷል። ዩኒቨርስቲው 3.93 በማምጣት ከሁሉም ተማሪ ቀዳሚ ብትሆንም በመመረቂያ አዳራሽ ሽልማቷን ስለተነፈገችው እህታችን ሁዳ (መቅደስ) በቀለ ለABDII SABAA ሚዲያ ምላሽ ሰጥቷል። ሚዲያው እንደገለፀው በስልክ ላቀረበላቸው ጥያቄ "የተፈጠረው ችግር ሀይማኖትን መሰረት አድርጎ አይደለም። የሲስተም ችግር ነው። ይህንንም ተከትሎ ተማሪዋን እና ቤተሰቧን ጠርተን ይቅርታ ጠይቀናታል። ሜዳልያም እንዲሰጣት ሆኗል። መሰል ስህተቶች እንዳይደጋገሙም አበክረን እንሰራለን።" - ብሏል። አሁንም ቢሆን ዩኒቨርስቲው ጥያቄያችንን አልመለሰም። ጥያቄዎቻችን የሚከተሉት ናቸው። ፨ በአደባባይ የተነፈገችውን ክብር እና ሽልማት በአዳባባይ ይቅርታ በመጠየቅ ይሸልም። በአደባባይ የተነፈገ ክብር በቢሮ አይመለስም። ፨ ተማሪዋ እንደ ኮሌጅ፤ እንደ ሴቶች እና እንደ አጠቃላይ ቀዳሚ ነች። ሶስቱም ሽልማት ሊሰጣት ይገባል። ፨ ለደረሰባት የሞራል ስብራት ተገቢው የሆነ ካሳ ያስፈልጋል። ሲቀጥል እስካሁን ድረስ ዩኒቨርስቲው በይፋው ገፁ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ የሰጠው ማብራሪያም ሆነ የጠየቀው ይቅርታ የለም። ለምን? ሕዝቡ ከዳር እስከ ዳር እየጠየቀ ባለበት የሕዝብን ድምፅ መናቅ ምን ይሉታል?! @EHEMSU
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи