tgindex
AAU - Muslim Students Union

AAU - Muslim Students Union

Статистика
@aaumsuВидеоанглийский

This is the official channel of AAU-MSU. Group: @aaumsu_discussion Youtube: youtube.com/@aaumsu Twitter: x.com/aaumsu12 Facebook: facebook.com/profile.php?id=100087931837303 Contact us: @Aaumuslimstudentsunion1 Email: aaumsu12@gmail.com

Последний пост
12:44
Последнее чтение
14:43
Постов за неделю
11
Всего постов
37
Тип
открытый
Язык
английский
Категория
Видео
В каталоге с
12 авг.
Подписчики
7 174
+18 за 3 дн.
Сутки
+11
+0,15%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 794
31 постов
Вовлечённость
25,0%
к подписчикам
Постов в день
1,6
всего 37
Упоминаний
20
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 474
1/48двое суток
1 689
1/72трое суток
1 821

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 12:4422853

    ከታሪክ ገጾች📖…እስካለንበት ተጨባጭ ✍️ ✨ሁሉም ትውልድ የራሱ ሀጃጅ ሲኖረው፤ ሁሉም ሀቅም የራሱ ባለቤት አለው። ✨ ክፍል 2 እውነትን ግፍ የተከተለበትና የሁለት ተቃራኒ ጎዳናዎች የተገናኙበት ታሪክ ነው። ፍሰቱን የጠበቀ በሚመስል መልኩ የጽናት ተምሳሌት የሆነውና እውነትን ለመናገር ሕይወቱን የሰጠው ታቢዒይ 💫 አቡ ዐብደላህ ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር አል-አሰድይ በተወለደ…

  • 10:0337884

    2) ኢትዮጵያስ ሁሉንም ዜጎቿን በእኩልነት እያገለገለች ነውን? 3) የኢትዮጵያ የሆኑ ነገሮች ሁሉ በእኩልና በፍትሃዊ መልኩ ሁሉም እየተወከሉበት፣እኩል ተጠቃሚ ሆነውበታል? ሁሉንስ ከግምት ያስገቡ ሆነው ተዋቅረዋልን? የሙስሊሞች ጥያቄ ከመስጂድ ቅጥር ውጭ ይዘልቃል። ወደ ታሪክ አካታችነት ይሄዳል። ወደ ትምህርት ስርዓትና አተገባበር ያመራል። ወደ አካታች ኢኮኖሚም ይገባል። ወደ የቅርስና የባህል ጥበቃ ይሄዳል። ወደ ሀገራዊ ምልክቶችና መገለጫዎችም ይደርሳል። ወደ ሴቶችና ህፃናት መብትም ይዘልቃል። የ ሰብዓዊ መብት ጉዳይም ነው። ወደ አሳታፊና አካታች የተቋማት ግንባታ ይሄዳል። ፍትሃዊ ውክልናንም ይመለከታል። ወደ ፍትሕ ስርዓቱ ይገባል። በዜግነት ጉዳዮች በኩል ይመዘዛል። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎች ከመስገድና ከመነገድ በላይ የዘለቁ ጥያቄዎች የፍትሕ፣ የእኩልነት፣ የውክልና እና የሙሉ ዜግነት ጉዳዮች ናቸው! ይህ የሙስሊሞች ጥያቄ ብቻ አይደለም። ይህ የኢትዮጵያ የሀገር ግንባታ ጥያቄዎች ናቸው። የአካታችነትና በሁሉም እርከን በፍትሃዊነት የመወከል ጥያቄ ነው። የሀገር ባለቤትነት ጥያቄ ነው። ይድረስ ለኮሚሽነሮቹ! 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 በሀገራዊ የምክክር ሂደት ውስጥ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ጥያቄዎች በስምንቱ አጀንዳዎች ዉስጥ የተዘረዘሩትን ሰብስቦ በአንድ “የሃይማኖት ጉዳይ” ሳጥን ውስጥ መክተት የመፍትሔ መንገድ ሳይሆን የመዋቅራዊ ችግሩን ሥር የሚያስቀጥል አካሄድ ነው። እውነተኛ ሀገራዊ መግባባት የሚገኘው የዜጎችን መብት በአስተዳደራዊ ማጣሪያዎች ወይም በሃይማኖታዊ ሳጥኖች ውስጥ በመክተት ሳይሆን፣ እውነተኛ አካታችነት ማለት የሙስሊሞችንም ሆነ የየትኛውም ወገንን በየተነሱበት አጀንዳዎች ስር ከነአውዳቸው ሳይሸፋፈኑና በጥቅል ገለጻ ስር ሳይደበቁ በዚያው በተጠቀሱበት አኳኋን ምክረ ሀሳቦቹ በየተገቢው አጀንዳ ውስጥ ማስቀመጥና መፍትሄ እንዲያገኝ ማድረግ ሲቻል ብቻ ነው። እውነተኛ ፍትሕ ማለት በየተቋሙ ያለውን መዋቅራዊ እንቅፋት መለየትና ማስወገድ ነው። እውነተኛ ሀገር ግንባታ ማለት ሁሉም ዜጎች በሀገራቸው ውስጥ እኩል ባለቤትነት እንዲሰማቸው ማድረግ ነው።

  • 10:0329943

    በእውነት የሚገርመው ምንድን ነው? አንዲት ሙስሊም ተማሪ በሂጃቧ ምክንያት ብትገለል፣ ይህ የሴቶች መብት ጉዳይ ነው ወይስ የመጅሊስ ጉዳይ? የሙስሊሞች ታሪካዊ ቅርሶች በብሔራዊ ትረካ ውስጥ ቢጠፋ፣ ይህ የባህልና ቅርስ ጉዳይ ነው ወይስ የሃይማኖት ጉዳይ? ከወለድ ነፃ ፋይናንስ በበቂ ሁኔታ አለመዳረሱ የአሳታፊ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ጉዳይ ነው ወይስ የሃይማኖት ጉዳይ? አንድ ሙስሊም ዜጋ በመንግሥት ተቋማት ውስጥ እኩል ዕድል እንዲኖረው ሲጠይቅ ይህ የዜግነት ጥያቄ ነው ወይስ የሃይማኖት? በፌደራልም ሆነ በክልል በቢሮክራሲ፣ በዳኝነት፣በሕዝብ ተወካዮች ተቋማት ወይም በውሳኔ ሰጪ መድረኮች የሚነሱ የውክልና ጥያቄዎች የሃይማኖት ጉዳይ ናቸውን? እነዚህ ጥያቄዎች መልሳቸው ግልጽ ነው። ችግሩ የሃይማኖት ተቋማት ችግር አይደለም። ችግሩ የሀገራዊ ተቋማት አካታችነት ችግር ነው። "ጥያቄ ስታነሱ ሴኩላሪዝም ትዝ አለኝ" 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 በሀገራችን የታዘብኩት አንድ የቆየ አሳሳቢ አዝማሚያ አለ። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በታሪክ፣ በፍትሕ፣ በውክልና፣ በትምህርት፣ በኢኮኖሚ፣ በሰብዓዊ መብቶች፣ በተቋማት አካታችነት ወይም በሕገ-መንግሥታዊ መብቶች ዙሪያ ማንኛውንም ጥያቄ ሲያነሱ፣ ወዲያውኑ “ሴኩላሪዝም” ትዝ የሚላቸው መገኖች አሉ። በሁሉም መስክና ስፍራ እኩልነት በተግባር ጥያቄ ሲነሳ እነዚህ ወገኖች ሴኩላሪዝምን (የመንግስት ነፃ በመሆን ዓለማዊነትን) ጉዳይ በማንሳት ውይይቱን ወደ “ሃይማኖት ጉዳይ” ብቻ ለመግፋት የሚሞክሩ አካላትን ደጋግመን ታዝበናል። እነዚህ አካላት ጉዳዩን በዜግነት፣ በሰብዓዊ መብት፣ በሕገ-መንግሥታዊ እኩልነት፣ በተቋማዊ ፍትሕ ወይም በሀገር ግንባታ ማዕቀፍ ከማየት ይልቅ ወደ ሃይማኖታዊ ማዕቀፍ ብቻ ለማሳነስ ይሞክራሉ። በዚህ ሂደት የሙስሊሞች ጥያቄ ዜጎች የሚያነሱት ሀገራዊ ጥያቄ ሳይሆን የአንድ ሃይማኖት ውስጣዊ ጉዳይ እንደሆነ ለማቅረብ ይሞክራሉ። ይህ ግን ለሴኩላሪዝም ጥብቅና መቆም አይደለም፤ የዜግነት ጥያቄን ባህሪ መቀየርና በሴኩላሪዝም ስም ማፈን ነው። ሴኩላሪዝም ማለት መንግሥት ሃይማኖት ሳይኖረው በገለልተኛነት የሁሉምና ለሁሉም የሚመች፣ ሁሉም ዜጎች በእኩልነት በሀገራቸው ጉዳዮች እንዲሳተፉ የሚያስችል የገለልተኝነት መርህ እንጂ ማንኛውንም ማህበረሰብ ከሀገራዊ ጉዳዮች ማግለል ወይም ጥያቄዎቹን ወደ ሃይማኖት ሳጥን ውስጥ መክተት አይደለም። የሙስሊሞችን ማንኛውንም ጥያቄዎች ወደ “ሃይማኖት” ማውረድ የእኩል ዜግነትን ክርክር ከመሰረቱ ማዛባት ነው። የሀገራዊ የምክክሩ ትምህርት 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 በቅርቡ በተካሄዱ ሀገራዊ ውይይቶች አንድ አሳሳቢ አዝማሚያ ታይቷል። ከሙስሊሙ ማህበረሰብ የሚነሱ የታሪክ፣ የፍትሕ፣ የውክልና፣ የኢኮኖሚ፣ የሴቶች መብት፣ የትምህርት፣ የባህል፣ የመሬት አጠቃቀም፣ የፋይናንስ፣ የሲቪክ ተሳትፎ እና የተቋማት አካታችነት ጥያቄዎችን በሙሉ “የሃይማኖት ጉዳይ” በሚል ርዕስ ስር ለማጠቃለል የተደረገ ጥረት ታይቷል። ይህ ከቀላል የአጀንዳ አመዳደብ ስህተት በላይ ነው። ይህ የታሪካዊ ማግለል ዘመናዊ ቅጂ ነው። ጥያቄዎችን “ባለቤት አልባ” ማድረግ ኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች የተደራጁ በርካታ ሚኒስቴሮችና ተቋማት አሏት። የንግድ ጉዳይ የንግድ ተቋማትን ይመለከታል። የባህልና ቱሪዝም ጉዳይ ተቋማቱን ይመለከታል። የትምህርት ጉዳይ የትምህርት ተቋምን ይመለከታል። የሙስሊም ሴቶች መብት ጉዳይ የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትርን ይመለከታል። አይመለከተኝም ካለ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስያሜውን "የሙስሊም ያልሆኑ ሴቶች ጉዳይ ሚኒስቴር" ብሎ ይቀይር።የሙስሊም ሴቶች ጉዳይ የመጅሊስ ጉዳይ ብቻ የሚሆንበት ሁኔታ ማብቃት አለበት። የአካታች ፋይናንስ ጉዳይ የፋይናንስ ተቋማትን ይመለከታል። የተቋማት አካታችነት ጉዳይ የመንግሥት ተቋማትን ይመለከታል። እነዚህን ሁሉ በ“ሃይማኖት” ስም ወደ አንድ ተቋም መግፋት ማለት ጥያቄውን ከሚመለከተው ዋና ተቋም የማራቅ ስልት ነው። በዚህ ሁኔታ ተጠያቂ የሆኑ ተቋማት ከኃላፊነታቸው ይሸሻሉ።በተጨማሪም ጥያቄው መፍትሔ የሚያገኝበትን መንገድ ያጣል። ምክንያቱም የሃይማኖት ጉዳይ ተቋም በካቢኔ ውክልና፣ በመከላከያ ፖሊሲ፣ በትምህርት ሥርዓት፣ በመሬት አጠቃቀም ወይም በብሔራዊ ታሪክ አጻጻፍ ላይ ውሳኔ የመስጠት ሕጋዊ ሥልጣን የለውም። ስለዚህ ጥያቄው ከአንድ ቢሮ ወደ ሌላ ሲዘዋወር ይቆያል፤ መፍትሔ ግን አያገኝም። የታሪክ ጥያቄ የኢትዮጵያ ታሪክ ሲጻፍ ሙስሊሞች በምን ያህል ተካተዋል? የሀገሪቱ የንግድ ታሪክ፣ የስልጣኔ ታሪክ፣ የሙስሊም ሊቃውንት ታሪክ፣ የሙስሊም መሪዎች አስተዋጽኦ፣ የሙስሊም ማህበረሰቦች የሀገር ግንባታ ሚና በብሔራዊ ትረካ ውስጥ ምን ያህል ቦታ አግኝተዋል? ይህ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። ይህ የታሪክ ፍትሕ ጥያቄ ነው። "ሙስሊሞች እኩል ዜጎች ከሆኑ" ✅✅✅✅✅✅✅✅✅ 1) በሀገራዊ ታሪክ ውስጥ እኩል ተወክለዋልን? 2) በባህልና ቱሪዝም ተቋማት ሥራዎች ውስጥ እኩል ተካተዋልን? 3) በትምህርት መጻህፍት ትረካዎች ውስጥ እኩል ተገልጸዋልን? 4) በፖሊሲ ውሳኔዎች ውስጥ እኩል የመወሰን ድምፅ አላቸውን? 5) በተቋማት ውስጥ እኩል ውክልና አላቸውን? 6) በውሳኔ ሰጪ መድረኮች ውስጥ እኩል ተሳትፎ አላቸውን? 7) በሀገራዊ ምልክቶችና መገለጫዎች ውስጥ እኩል ታይተዋልን? 8) በብሔራዊ ትረካዎች ውስጥ እኩል ቦታ አግኝተዋልን?... በርካታ ጥያቄዎችን ጨምሩበት። እነዚህን ጥያቄዎች ማንሳት ልዩ ጥቅም መጠየቅ አይደለም። እነዚህን ጥያቄዎች ማንሳት የእኩል ዜግነት ጥያቄ ነው። የሙስሊሞች ጉዳይ የሃይማኖት ጉዳይ ነውን? ⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕ የጥያቄውን ትክክለኛ ባህሪ መለየት አስፈላጊ ነው። አንድ ሙስሊም ዜጋ ሀገሩን በወታደራዊ ተቋማት ለማገልገል ሲፈልግ ከእምነቱ ወይም ከሙስሊምነቱ አንዳንድ መገለጫዎች እንዲተው ከተጠየቀ፣ ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ብቻ አይደለም፤ የተቋማት አካታችነት፣ የእኩል ዕድል እና የዜግነት ጥያቄ ነው። አንዲት ሙስሊም ሴት በአለባበሷ ወይም በሃይማኖታዊ ማንነቷ ምክንያት በሥራ ቦታ ዕድል ከተነፈገች፣ ይህ የሠራተኛ መብት፣ የእኩልነት እና የሕገ-መንግሥታዊ መብት ጉዳይ ነው። አንድ ሙስሊም ተማሪ በሙስሊምነቱ ወይም በሃይማኖታዊ መገለጫው ምክንያት ከትምህርት ቤት ከተገለለ፣ ይህ የመጅሊስ ጉዳይ ሳይሆን የትምህርት መብት፣ የዜግነት እና የሕግ የበላይነት ጉዳይ ነው። መስጂዶች ሲቃጠሉ፣ሲፈርሱ ወይም ኢማሞች ሲገደሉ፣ ይህ የሀገሪቱ የሰላምና የደህንነት አጀንዳ እንጂ የሙስሊሞች ጉዳይ አይደለም። የሕግ ማስከበር እና የዜጎችን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለባቸው ተቋማትን የሚመለከት ጉዳይ ነው። በአጠቃላይ ጥያቄውን የሚወስነው ጉዳዩን ያነሳው ሰው ሙስሊም መሆኑ ሳይሆን የተጣሰው መብት፣ የተፈጠረው ችግር እና መፍትሔ የሚሰጠው ተቋም ነው። ስለዚህ ሙስሊሞች የሚያነሱትን እያንዳንዱን ጥያቄ “የሃይማኖት ጉዳይ” ብሎ መፈረጅ የጥያቄውን እውነተኛ ባህሪ መሸፈን እና ከተጠያቂ ተቋማት ማራቅ ነው። ኢትዮጵያ እኩል የሁላችንም ነች? ከቃል ባሻገር በተግባር እንዴት ይገለጻል? 🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒🎒 “እስላም ከሰገደና ከነገደ ሌላ ምን ይፈልጋል?” የሚለው ጥያቄ በመሠረቱ የተሳሳተ ጥያቄ ነው። መቅረብ ያለባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። 1) ኢትዮጵያውያን ሀገራቸውንና ወገናቸውን የማገልገል እኩል እድል አግኝተዋልን?

  • 10:0331943

    "እስላም ከሰገደና ከነገደ ሌላ ምን ይፈልጋል?" 🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥 የዜግነት ጥያቄዎችን በ“ሃይማኖት ጉዳዮች” ሳጥን ውስጥ የማፈን መዋቅራዊ አደጋ እና የተቋማዊ ማግለል አሰራር አደጋ። 📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶 በአሕመዲን ጀበል 🔴🔴🔴🔴🔴🔴 “እስላም ከሰገደና ከነገደ ሌላ ምን ይፈልጋል?” የሚለው አባባል አዲስ አይደለም። በዘመናት የተወረሰ፣ በትውልዶች የተደጋገመ፣ ዛሬም በይፋ ባይነገርም በተለያዩ መንገዶች የሚገለጽ የሚታይ አመለካከት ነው። በቀድሞ ዘመን በቀጥታ ይነገር ነበር፤ ዛሬ ግን በተቋማት አሰራር፣ በፖሊሲ አቀራረብ፣ በሚዲያ ትረካዎች፣ በሀገራዊ ውይይቶች እና በውሳኔ ሰጪ መድረኮች ውስጥ በዘመናዊ መልክ ተሸፍኖ መቀጠሉን እናያለን። ይህ አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ጥያቄዎች ወደ መንፈሳዊና ኢኮኖሚያዊ ብቻ የማድረግ ስልታዊ ማግለል መገለጫ ነው። በምክክሩ ሙስሊሞች የገጠማቸው ተግዳሮቶች 📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶📶 እየተካሄደ ባለው ሀገራዊ ምክክር ሙስሊም ተሳታፊዎችን ከገጠሟቸው ተግዳሮቶች አንዱና ዋነኛው በርካቶች ዘንድ "ሙስሊም ከሰገደና ከነገደ ሌላ ምን ይፈልጋል?" የሚለው እይታ መኖሩን መታዘቡና ከዚሁ እይታ የተነሳ ሙስሊሞች ከሃይማኖት ጉዳዮች አጀንዳ ውጭ ባሉ ጉዳዮች የሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ምክረ ሀሳቦች በሚያዙ ቃለጉባኤዎች ዉስጥ እንዳይካተቱ የሚታገሉ አካላትን በግልጽ መጋፈጣቸው ነው። የሚገርመው አብዛኞቹ መሰል አካላት የራሳቸው አንዳች አጀንዳዎች፣ጥያቄዎች የሌላቸውና የነርሱ አጀንዳ የሙስሊሞች አጀንዳ እንዳይካተት ማድረግ እስኪመስል ራሳቸውን አጋልጠዋል። በዚህ ስንኩል አመለካከት ባለቤቶች መካከል በሀላፊነት ላይ ያሉትም ጭምር ሆነው መገኘታቸው አሳዛኙ ሁኔታ ነው። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በሀገር ግንባታ፣ በሀገር ባለቤትነት ጉዳዮች፣በታሪክ ፣የጋራ ሀገራዊ ማንነት እና እሴቶች፣ብዝኃነት እና አስተዳደር ጉዳዮች፣ የባህል፣ ታሪክ እና ቅርስ ጥበቃ ጉዳዮች ጥያቄዎች አሏቸው። በመንግሥት ምሥረታ፣ በተቋም ግንባታ፣ሰላም ግንባታ፣ግጭት መንስኤዎች እና አፈታት መንገዶች፣ ማህበራዊ ኢኮኖሚ እንዲሁም የአርሶ አደሮች እና አርብቶአደሮች ጉዳዮች፣ህገ መንግስታዊ እና ህጋዊ ማዕቀፍ በሰብአዊ መብቶች ጥበቃ፣የመልካም አስተዳደር ችግር እና የሙስና ጉዳዮች ምክረሀሳብ አሏቸው። ሙስሊሞች በ8ቱም አጀንዳዎች የሚያነሷቸው ጥያቄዎችና ምክረ ሀሳቦች ከየአጀንዳዎቹ ስር ተሰርዘው ወደ ሃይማኖት አጀንዳ ብቻ ይሂዱ የሚለው እይታ የተሳታፊዎች ብቻ አልነበረም። ኮሚሽኑ በመደባቸው ጥቂት አወያዮች፣ አስተባባሪዎችና ጥቂት ኮሚሽነሮች ዘንድም ተንጸባርቋል። ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በየአጀንዳዎቹ ሥር ያነሷቸውን ምክረ ሀሳቦች ለቃቅሞ ወደ የሃይማኖት አጀንዳ ሥር ለመውሰድ መሞከር ማለት ተራ የአሰራር ጉዳይ አይደለም።እንድምታው አደገኛ ነው። "ከሀገራዊ አጀንዳዎች ለማራቅ ወደ ሃይማኖት ጉዳዮች ግፏቸው!" ✅✅✅✅✅✅💢💢💢💢💢💢💢 አንድም የናንተን ሀሳብ ከሃይማኖት አንፃር ብቻ ነው የምናየው እያሉ ነው።አልያም ከሃይማኖት ጉዳይ በቀር ስለሌላው አይመለከታችሁም ፣ወይም ከሃይማኖት አጀንዳ እንድትወጡ አንፈቅድላችሁም ነው። ይህ በራሱ ሌላ ሀገራዊ ምክክር የሚፈልግ ሸውራራ እይታ ነው። በመጀመሪያ እይታ ይህ አባባል ቀላል ጥያቄ ሊመስል ይችላል። ግን በውስጡ ጥልቅ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊ እና መዋቅራዊ እሳቤ ይዞ ይመጣል። ለምን? ምክንያቱም ይህ አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን ከሀገሪቱ አጠቃላይ ጉዳዮች እየገፋ ወደ “ሃይማኖት” ብቻ ለመወሰን ይሞክራል። በፍትሕ ላይ ጥያቄ ቢያነሱ ወደ ሃይማኖት ይገፋሉ። በታሪክ ላይ ቢናገሩ ወደ ሃይማኖት ይገፋሉ። በኢኮኖሚ ላይ ቢጠይቁ ወደ ሃይማኖት ይገፋሉ። በተቋማት ውክልና ላይ ቢወያዩ ወደ ሃይማኖት ይገፋሉ። የጥያቄው ርዕስ ቢቀየርም የሚቀርበው መልስ አንድ ነው፤ “ይህ የሃይማኖት ጉዳይ ነው” የሚለው።ነገር ግን ይህ የችግሩ መፍትሔ አይደለም፤ የችግሩ መሸፈኛ ነው። ሁለቱ አደገኛ እሳቤዎች ❌❌❌❌❌❌❌ “እስላም ከሰገደና ከነገደ ሌላ ምን ይፈልጋል?” የሚለው አባባል ሁለት አደገኛ እሳቤዎችን ይሸከማል። ሀ) ሙስሊሞችን ማሳነስ 🔶🔶🔶🔶🔶🔶🔶 ይህ አባባል ሙስሊሞችን ከሀገር ግንባታ፣ ከእውቀት ምርት፣ ከሳይንስ፣ ከፖለቲካ፣ ከባህል፣ ከተቋማት ግንባታ፣ ከውሳኔ ሰጪነት እና ከሀገራዊ አጀንዳዎች ውጭ ያሉ ሰዎች እንደሆኑ ያቀርባቸዋል። ሙስሊሙ እንደ መምህር አይታይም። እንደ ሳይንቲስት አይታይም። እንደ ዳኛ አይታይም። እንደ ፖሊሲ አውጪ አይታይም። እንደ ታሪክ ባለቤት አይታይም። እንደ ሙሉ ዜጋም አይታይም። እንደ ሃይማኖታዊ ማህበረሰብ ብቻ እንዲታይ ይደረጋል። ለ) ሙስሊሞችን በሁለት መስኮች ብቻ መገደብ 🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺🔺 ሁለተኛው አደገኛ እሳቤ ሙስሊሞችን በሁለት መስኮች ብቻ በመስገድና በመነገድ ለመገደብ ያለ ፍላጎት ነው። ይህ አመለካከት ሙስሊሞች በመስጂድ ውስጥ እንዲቆዩ ወይም በንግድ እንዲሰማሩ ሊፈቅድ ይችላል። ነገር ግን በታሪክ አጻጻፍ፣ በሀገራዊ ትረካ፣ በትምህርት ፖሊሲ፣ በተቋማት ግንባታ፣ በመከላከያ፣ በዳኝነት፣በሲቪል ሰርቪስ፣ በሚዲያ ፣ በባህል ተቋማት፣ በውሳኔ ሰጪ መድረኮች፣ በሀገራዊ ምልክቶች እና በሀገር ባለቤትነት ስሜት ውስጥ እኩል ተሳታፊ እንዳይሆኑ በተዘዋዋሪ መንገድ ይገፋፋል። የዜግነት ጥያቄን ወደ ሃይማኖት ነጻነት ማውረድ ⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕⭕ የችግሩ መሠረት አንድ ነው፤ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የሚያነሱትን ማንኛውንም ጥያቄ እንደ “ሃይማኖታዊ ጥያቄ” ብቻ መመልከት። ነገር ግን እውነተኛው ጥያቄ ይህ ነው፦ ሙስሊሞች በዚህች ሀገር ላይ የሚያነሱት ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ ብቻ ነውን? መልሱ ግልጽ ነው። አይደለም። ሙስሊሞች የሚያነሱት ጥያቄ የዜግነት ጥያቄ ነው። ስለ ፍትሕ ሲናገሩ፣ ስለ ተቋማዊ ውክልና ሲጠይቁ፣ ስለ ታሪክ አጻጻፍ ሲከራከሩ፣ ስለ ባህል ቅርስ ሲጠይቁ፣ ስለ ኢኮኖሚ ተሳትፎ ሲወያዩ፣ ስለ ኢስላማዊ ፋይናንስ ሲነሱ፣ ስለ እኩል ትምህርት ዕድል ሲናገሩ፣ ስለ አሳታፊ የሥራ ዕድል ሲጠይቁ፣ ስለ ሴቶች መብት ሲያነሱ፣ ስለ ሰብዓዊ መብቶች ሲወያዩ፣ ስለ መሬት አጠቃቀም ሲከራከሩ፣ ስለ ተቋማት አካታችነት ሲጠይቁ፣ ስለ ውሳኔ ሰጪነት ሲወያዩ፣ የሚያነሱት ጥያቄ የዜግነት ጥያቄ ነው። ይህ የመስጂድ ጥያቄ ብቻ አይደለም። ይህ የሂጃብ ጥያቄ ብቻ አይደለም። ይህ የመጅሊስ ጥያቄ ብቻ አይደለም። ይህ የእኩል ዜግነት ጥያቄ ነው። የጥያቄውን ባህሪ የመቀየር አደገኛነት 💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥 አንድ ማህበረሰብ የሚያነሳውን የመብት ጥያቄ “ሃይማኖታዊ” ብቻ ብሎ መፈረጅ በእውነቱ የጥያቄውን ባህሪ መቀየር ነው። የፍትሕ ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። የኢኮኖሚ ተሳትፎ ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። የባህልና ቅርስ ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። የታሪክ ውክልና ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። የመንግሥት ተቋማት አካታችነት ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ ሊሆን አይችልም። የሙስሊም ይሁን የክርስቲያን የሴቶች መብት ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። የትምህርት ፖሊሲ ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ አይደለም። የውክልና ጥያቄ የሃይማኖት ጥያቄ እንዴት ሊሆን ይችላል? እነዚህ ሁሉ የዜግነት፣ የፍትሕ፣ የእኩልነት እና የሀገር ግንባታ ጥያቄዎች ናቸው።

  • 🔥نحن قومٌ أعزَّنا اللهُ بالإسلام! 🔊አዲስ መድረክ፣ አዲስ ግንዛቤ፣ አዲስ ከፍታ!             🗯 ሕያው ምስክር❕🗯 የ ስኬት መጎናጸፍያ ጎዳና የሆነው እስልምና ላይ እስከ ዘመናችን ድረስ በመንገዱ ከቀደሙን ታላላቅ ሰዎች ስንቅ እንወስድ ዘንዳ ጉዟቸውን፣ ትግላቸውንና ልምዳቸውን ምንቃኝበት ታላቅ መድረክ!! በ ሀገራችን ውስጥ የተለያዩ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ስለ እውነት፣ ስለ መብት፣ ስለ ማንነት፣ ስለ እስልምና ሲደረጉ የነበሩ መሰል ጉዞዎች፣ ስለ ሙስሊሙ ማህበረሰብ እና ስለ ተማሪዎች ጥያቄ፣ ስለተደረገው ትግል እና ስላስገኘው ውጤት በ ጥልቀት ምናይበት፣ እንዲሁም በተለያዩ ጽንሰ ሃሳቦች ዙርያ ዕይታን በማስፋት ረገድ አንገብጋቢ የሆኑ ርዕሶች ላይ ግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራሞች ሚቀርቡበት፣ ወደ ሗላ ራቅ ብሎም እስልምና ለመፍጠር ሚተጋለትን ማህበረሰብ በተግባር ኖረው ካሳዩን ወርቃማ ትውልድ እና ጊዜያት በተለያዩ ምሁራን አማካኝነት ምንቃኝበት ፕሮግራም ነው። ሕያው ምስክር በየ ሶስት ሳምንቱ በ አአዩሙተህ ይፋዊ ቴሌግራም ቻናል በ ቋሚነት ሚቀርብላችሁ ልዩ የ ቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ! የመጀመሪያው ታሪካዊ መድረካችን መቼ ነው ?! በምን ዙሪያስ ይሁን ሚቀርበው ?! በቅርብ ቀን ይጠብቁን✨ @aaumsu

  • 13 авг.1 118214

    ሀገራዊ ምክክሩ ዘመናትን ለተሻገረው የሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄ ዘላቂ መፍትሔ እንዲያመጣ እንጠይቃለን። መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ በኢንስታግራም https://www.instagram.com/reel/Db_G8VCMmHu/?igsh=aHJiMHNvMmZyaGs2 በመግባት ያሰራጩ። @aaumsu

  • 13 авг.1 241145

    #ሕያው_ምስክር❕ 🔥 ••በ ቅርብ ቀን ይጠብቁን•• 🔥 @aaumsu

  • 12 авг.1 662235

    የትምህርት ሚኒስቴሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኢንትራንስ የሚፈተኑ ተማሪዎችን ከመፈተኛ አዳራሽ ገብቶ እየዘየረ ኒቃቢስት ተማሪዎች አትገቡም ተብለው አንድ ሙሉ ፈተና እስኪያልፋቸው ድረስ ከውጭ እንዲቆዩ ተደርገው ነበር። የሗላ ሗላ ኒቃባቸውን ጥለው በማስክ እንዲገቡ ቢሆንም ከዚያ ቀን ቡሃላ ግን ማስኩንም እንደተከለከሉ ተናግረዋል። ይህ እና ሌሎች ነጥቦች፤ ብሎም የመፍትሔ አቅጣጫዎች በሱመያዎቹ ፖድካስት ተዳሷል። https://youtu.be/dwCvc9NIA90?si=p53yOcEtaA-m5mlq በመግባት ተመልከቱ። ለሌሎችም አሰራጩ። @aaumsu

  • 11 авг.1 821345

    የኒቃቢስቷ ጥሪ፦ ኢማሞች በመስጂድ እንድንለብስ ያስተማራችሁንን ዩኒቨርስቲ ስንገባ እየተከለከልን ነው። ስለመብታችን ሊታገል የቆመው መጅሊስ ባለበት አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሙስሊም ተማሪዎችን መብት ሲጥስ ከርሟል። ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ሁሉም ሀላፊነቱን ሊወጣ ግድ ነው። የአዳማ ከተማ መጅሊስ፦ ሁላችንም በያለንበት መታገል ግዴታችን ነው። መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ https://vt.tiktok.com/ZS4cKLF1Y/ በመግባት ሪፖስት አድርጉ። @aaumsu

  • 10 авг.2 3803310

    በምርቃታቸው ቀን ታሰሩ። ከተመረቁ ቡሃላ ደግሞ ዲግሪያቸውን ተከለከሉ። ይህ ሁሉ "ኒቃብ መልበስ መብት ነው!" - የሚል መልዕክት በለበሱት ሪቫን ላይ በማስቀመጣቸው ነው። ይህ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እያደረሰ ያለውን ቀጣይነት ያለው የመብት ጥሰት ያሳያል። የሐይማኖት ነፃነት መብታችንን እስኪያከብር ጥያቄ አለን። የመናገር ነፃነት መብታችንን እስኪያከብር ጥያቄ አለን። ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ጥያቄ አለን ! መልዕክቱ ለሁሉም ይደርስ ዘንድ https://vt.tiktok.com/ZS4nuKTRG/ በመግባት ሪፖስት አድርጉ። @aaumsu

  • 9 авг.1 664155

    ከታሪክ ገጾች📖…እስካለንበት ተጨባጭ ✍️ ✨ሁሉም ትውልድ የራሱ ሀጃጅ ሲኖረው፤ ሁሉም ሀቅም የራሱ ባለቤት አለው። ✨ ክፍል 2 እውነትን ግፍ የተከተለበትና የሁለት ተቃራኒ ጎዳናዎች የተገናኙበት ታሪክ ነው። ፍሰቱን የጠበቀ በሚመስል መልኩ የጽናት ተምሳሌት የሆነውና እውነትን ለመናገር ሕይወቱን የሰጠው ታቢዒይ 💫 አቡ ዐብደላህ ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር አል-አሰድይ በተወለደ በ2 አመቱ ነበር ስልጣኑን በግፍ የጠመቀው ገዥ ሀጃጅ ኢብን ዩሱፍ አስ-ሰቀፊይ የተወለደው። አላህ ዱንያ ላይ የትኛውንም አይነት ፈተናን ለአንድ አማኝ ባሪያው መስጠቱ ግልጽ ሆኖ ሳለ፣ ባለህ ስልጣን ወይም ደግሞ በተቀመጥክበት ሃላፊነት ላይ ሌሎች ውድ የአላህ ባሮች ጋር መገናኘት ግድ ይሆንና ስልጣንህን ተጠቅመህ በደልህን በመዝራት ኢ- ፍትሃዊነትን ያሰፈንክ እለት ፈተናህን መውደቅህ ብቻ ሳይሆን እረፍት የሌለውና ዘላቂ የሆነ የቅጣት ማእበል ላይ ዘውታሪ እንደምትሆን ማሰቡ ደግ ነው።ሐጃጅ ኢብን ዩሱፍም ምናልባት ፈተናው ይህ ነበር❗️ ስልጣንን ለማግኘት ያለው መንገዱ ገራለት፣እያደገ ሲሄድም ከተወለደበት ከተማ ከጣኢፍ ወደ ሻም ተጓዘ።በዚያም ከኸሊፋው ዐብዱል መሊክ ኢብኑ መርዋን ጋር ተገናኘ። ዐብዱልመሊክ የሐጃጅን ጥንካሬና ቆራጥነት በማየት ከፍተኛ ኃላፊነት ሰጠው። በዚያን ዘመን በመካ የሙስሊሞች መሪ  የነበረው ታላቁ ሶሐቢ ዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይር (ረድየላሁ ዐንሁ) ነበር። እርሱ የታላቁ ሶሐቢ ዙበይር ኢብኑል ዐዋም ልጅ ሲሆን፣ እናቱም የአቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረድየላሁ ዐንሁ) ልጅ አስማእ (ረድየላሁ ዐንሃ) ነበረች። ዐብዱል መሊክ ሐጃጅን የሙስሊሞች መሪ  የነበረውን ታላቁን ሶሐቢ ዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይር እንዲገድል ወደ ሒጃዝ ላከው።ታላቅ ሠራዊት አሰልፎ በመሄድም ዐብዱላህ ኢብኑ ዙበይርን ገደለ፤ የእርሱንም አስተዳደር አበቃ። ከዚያ በኋላ ዐብዱል መሊክ ሐጃጅን የሒጃዝ (መካ፣ የመዲና፣ የጧኢፍ)፤ በኃላም የዒራቅ አስተዳዳሪ አደረገው። ከዚያ ጀምሮ ሐጃጅ ሥልጣኑን በጥብቅ እጅ ማስፈጸም ጀመረ። ፊትነቱል-ቁራእ በተባለው ፊትና የተሳተፉ የታቢዒዮችን ዑለሞች ማሳደድ፣ማሰርና መግደል የዘወትር ሥራው ሆነ ፣በዚህ አደገኛ የስም ዝርዝር ውስጥም ሰዒድ ኢብኑ ጁበይር ይገኛል።     ሐጃጅ ሰዒድን ለመያዝ የጀመረው ፍለጋ አንድ ቀን ወይም አንድ ወር አልነበረም። 🔸 ከስምንት ዓመታት በላይ የቀጠለ ነበር። በቃ እውነታው ይህ ነው፤ዛሬ ላይ ምናልባት አንተ ለያዝከው ሀቅ ከምትከፍለው መስዋእትነት በላይ እጅ እንድትሰጥ፣ እንድትደክም እና ተስፋ እንድትቆርጥ ጠላት በጣም በተደራጀና እጥፍ በሆነ መልኩ ዝቅ ሊያደርግህ ይለፋ፣ ይተጋ ይሆናል። ነገር ግን አይደለም 1 ፣ 2 አመት ጽናቱ ካለህና በአላህ ከታገዝክ ፈተናህ የብዙ አመታት ቢሆን እንኳን ትወጣዋለህ። እናም ሀጃጅ ሰኢድን ማሰስ ከጀመረ ከ8 አመታት በኋላ በወታደሮቹ አማካኝነት በመካ አገኘው እነርሱም አሰረዉት ወደ ሐጃጅ ይዘውት መጓዝ ጀመሩ። በመንገድ ላይ ግን ልብን የሚሰብር ክስተት ተፈጠረ።ሴት ልጁ ከፊት ለፊቱ ተከትላ እየሮጠች ታለቅስ ጀመር።ሰዒድም እንደምንም ራሱን ለማጠናከር ከራሱ ጋር እየታገለ "ልጄ ሆይ! እናትሽን በአላህ ፈቃድ ጀነት ውስጥ እንገናኝ በያት!" አላት። እርሱ የሚሄደው ወደ እስር ብቻ እንዳልሆነ፣ ወደ ሸሂድነት ጉዞ መሆኑን ያውቅ ነበር… ሁኔታው በእርግጥ ከባድ ነው። ነገር ግን ዱንያ ላይ ያለ ነገር በሙሉ እንደ መስዋእትነት ቀርቦ ሀቅ ላይ መጽናት እንዳለብን የተማርንበት ትልቅ ክስተት ነበር። ዛሬ ላይ የአመታትን ልፋት እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ሊያስከፍለን ይችላል። ጽናትና ኢኽላስ ካለ ግን ከአላህ ጋር ሁሉም ይሳካል። የእውነት ድምጽ በስልጣን ፊት ምን ይመስል ይሆን? ክፍል 3 ይቀጥላል……… ✍️ታሪኩን በምን መልኩ ወሰዳችሁት ?! ✍️ምን ትምህርት አገኛችሁበት?! ✍️ ምንስ አስተዋላችሁበት ?! ከታች ባለው ሊንክ አስቀምጡልን @Niqab_issueBot @aaumsu

  • 8 авг.1 629226

    ከታሪክ ገጾች📖…እስካለንበት ተጨባጭ ✍️ ✨ለመፈተን የመጀመሪያዎቹ አይደለንም፤ለመጽናትም የመጨረሻዎቹ አንሆንም።✨ ክፍል 1 << ዘንድሮ >> በውስጡ << ድሮ >> የሚለውን ቃል ይይዛል። ታሪክ ሲተረክ በድሮ ጊዜ ✍️እየተባለ ነው አይደል? ብዙ ድሮዎች ደግሞ አልፈዋል። ግን ያ ያማረው ፣ ድንቁና ወርቃማው በታሪክ ማህደር ውስጥ ውድ ሳሃቦችንና ታቢዒዮችን ያሰፈረው ድሮ ከሌላው በጣም የተለየ ነው። እንደ አንድ ዲኑን ለማወቅ የሚታትር፣ እስልምና ከፍ ብሎ ማየትን የሚሻ እንዲሁም መብቱን አስከብሮ መኖርን በራሱ ላይ ግዴታ ያደረገ ሙስሊም ደግሞ ዘንድሮም እንዳለፈው ድሮ ደምቆ ይሰፍር ዘንድ ካለፈው ታሪክ ያጤናል፣ ትምህርቱን ወስዶ የዛሬውን ጉዞ መስመሩ በተስተካከለው የቀደምቶች መንገድ ላይ ይቀጥላል….. ሂጃብ ለብሶ መማር መሰናክል ሲሆን፣ እህቶች በየመግቢያ በሩ ፣ካፌ እና ላይብረሪ ላይ ሲፈተኑ ማየት ከዛ ደግሞ ያለንበት እውነታን አለም ተረድቶ መፍትሄ ይሰጠን ዘንድ ስንቋምጥ አንድም በታወሩ ልቦች ሁለትም ውሸትን ቀለብ ባደረጉ ህሊናዎች ምን ሆናችሁ? ምን ነካችሁ? መባልና መካድ በጣም ያማል። ይህ ህመም ይሽር ዘንድ መድሃኒቱ የእውነት ደምቆ መታየት መሆኑ ደግሞ እሙን ነው። ግና ምን ያህል ዋጋ ያስከፍለን ይሆን? ለመክፈልስ ዝግጁ ነን❓ ……………………. ለእውነት ሲል በእውነት ላይ ከሞተ 1 ታላቅ ስብእና ፣ የእውነት ሰው እና የጽናት ተምሳሌት የምንወስደው ቁም ነገር አለ። ነገሩ እንዲህ ነው👇 በ38ተኛው ዓ.ሂ በኩፋ ከተማ አንድ ሕፃን ተወለደ። ይህ የሆነው በአራተኛው ኸሊፋ፣ በዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (ረድየላሁ ዐንሁ) ዘመን ነበር። በዚያን ጊዜ ማንም ይህ ሕፃን በኋላ ከታቢዒዮች እና ታላላቅ ዑለማዎች አንዱ እንደሚሆን፣ በተፍሲር፣ በሐዲሥና በፊቅህ ውስጥ የማይረሳ ስም እንደሚተው፣ እውነትንም ለመጠበቅ እስከሞት ድረስ እንደሚቆም አያውቅም ነበር። ……………………. ከሁለት ዓመታት በኋላ ደግሞ በጧኢፍ ሌላ ሕፃን ተወለደ። አንዱ በእውቀትና በኢማን ይታወቃል፤ሌላው በኀይልና በጭካኔ አንዱ ሰዎችን ወደ አላህ ይጠራል፤ሌላው በሥልጣኑ ያስፈራራል። የሁለቱ መንገድ ከዓመታት በኋላ ይገናኛል፤ ያ ግንኙነትም በእስልምና ታሪክ ውስጥ በጣም አስደናቂና ትምህርት የሞላበት ክስተት ይሆናል። የዚህ ባለሁለት መንገዱ አስደናቂ ታሪክና ክስተት ባለቤት የሆኑት ሁለቱ ህጻናት እነማን ይሁኑ?🤔 ክፍል 2 ይቀጥላል… @aaumsu

  • 8 авг.1 701163

    ‹‹በታሪካቸው ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች በእርግጥ መገሠጫ ነበር፡፡›› (ዩሱፍ 12፡ 111) የሕይወት መመሪያና መርህ የሆነው ቁርኣን፣ አንድ ሦስተኛው ያህል በተለያዩ ታሪኮች የተሞላ ነው። ታሪኩን ከተረከልን በኋላ ከትረካው እውቀት እንቀስም ዘንድ ያመላክተናል ‹‹ይህን ሁሉ (የቀደምት) መልእክተኞች ታሪክ በርሱ ልብህን ልናፀና ተረክንልህ።›› (ሁድ 11፡ 120) (አስተዋይ) ልቦና ላለው፣ (ተግሳጽንም ለማድመጥ) ጆሮውን ለከፈተ፣ (እውነትን) ለመሰከረ በዚህ (ታሪክ) ውስጥ ተግሳጽ አለበት::›› (ቃ9: 50:37) 🍂ከትናንት ጥልቀት የተገኙ፣ ዛሬን የሚያበሩ•• 🍂ህይወትን በአዲስ መልክ ማየትን የሚያስችሉ ልዩ ታሪኮች! 💥ከ ዛሬ ጀምሮ ዘውትር ቅዳሜ እና እሁድ ይከታተሉ ~> @aaumsu መልካም ሙሉ ሰው መሆኛ ጊዜ!!✨ @aaumsu

  • 7 авг.1 649175

    💭ሚሽካት!! የ ታሪክን ገጾች ስላደመቁ ጊዜያት እና ስብዕናዎች ምንመለከትበት ልዩ መድረክ ✨ ታሪክ•• ታሪክ ትናንትን ለማወቅ፤ ዛሬን ለመረዳትና ለነገ ለማቀድ ያግዛል። ታሪክ ያለው ሕዝብ በአግባቡ ከተጠቀመበት ታሪክ ይሠራል! ወደፊት መጓዝ የፈለገ መጀመሪያ ወደ ኋላ ተመልሶ ታሪኩን ይፈትሻል:: የአባቶቹንና የአያቶቹን ገድል ሲረዳ በምን ሁናቴ ውስጥ እንዳለፉ ግልጽ ብሎ ይታየዋል። የዛሬው እርሱነቱ የበርካታ…

  • 5 авг.2 269248

    "የራበን ፍትሕ እንጂ ዳቦ አይደለም።"- የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ይህ በዘንድሮው አመት ሙስሊም ተማሪዎች ያሳለፉትን በጥቂቱ የሚያስቃኝ ነው። https://www.tiktok.com/@aaumsu/video/7670594379068820744?is_from_webapp=1&sender_device=pc በመግባት ለሁሉም ይደርስ ዘንድ ሪፖስት ያድርጉ። @aaumsu

  • 5 авг.2 179212

    💭ሚሽካት!! የ ታሪክን ገጾች ስላደመቁ ጊዜያት እና ስብዕናዎች ምንመለከትበት ልዩ መድረክ ✨ ታሪክ•• ታሪክ ትናንትን ለማወቅ፤ ዛሬን ለመረዳትና ለነገ ለማቀድ ያግዛል። ታሪክ ያለው ሕዝብ በአግባቡ ከተጠቀመበት ታሪክ ይሠራል! ወደፊት መጓዝ የፈለገ መጀመሪያ ወደ ኋላ ተመልሶ ታሪኩን ይፈትሻል:: የአባቶቹንና የአያቶቹን ገድል ሲረዳ በምን ሁናቴ ውስጥ እንዳለፉ ግልጽ ብሎ ይታየዋል። የዛሬው እርሱነቱ የበርካታ ሂደቶች ውጤት መሆኑን ይረዳል፡፡ የአባቶቹንም ስህተት አይደግምም! የነርሱ ጠንካራ ተሞክሮ ኃይል ይሆነዋል። እሴቶቻቸውን ለማስከበር ስለከፈሉት መስዋዕትነት ሲያነብ የርሱ ድርሻ ምን እንደሆነ ይረዳል፡፡ ታሪክ ትናንትን እየነገረን ነገ ወዴት እንደሚሄድ ያመላክተናል፡፡ ትናንትን የማያውቅ ትውልድ ዛሬን እርግጠኛ አይደለም። ስለነገውም ቢሆን ግልጽ እይታ የለውም፡፡ ይላሉ Dr. አህመዲን ጀበል ! إِنَّ ٱللَّهَ لَا يُغَيِّرُ مَا بِقَوْمٍ حَتَّىٰ يُغَيِّرُوا۟ مَا بِأَنفُسِهِمْ ۗ አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን (ኹኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም፡፡ "ውስጣቸው ያለውን ሁኔታ እስኪለውጡ ድረስ" ተብለናል! እነሆ እኛም ከተለያየ ዘመን ክፍል፣ ውስጣችንን ሊገነቡ ይችላሉ ብለን ያሰብናቸውን ታሪኮች በ ተከታታይ ፕሮግራም ልናቀርብላችሁ ወደድን። 🗓 ቀን: ዘውትር ቅዳሜ እና እሁድ! @aaumsu

  • 5 авг.1 765511

    ሴኩላሪዝም እና የሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄ - ክፍል 2 ቆይታ ከጠበቃ ሙስጠፋ ሺፋ ጋር @aaumsu

  • 4 авг.2 1131212

    ሴኩላሪዝም እና የሙስሊም ተማሪዎች ጥያቄ - ክፍል 1 ቆይታ ከጠበቃ ሙስጠፋ ሺፋ ጋር @aaumsu

  • 4 авг.2 0052

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 авг.1 855182

    "በሀገራዊ ምክክሩ ለሙስሊም ተማሪዎች ታሪካዊ ጥያቄ ዘላቂ መፍትሔ የሚሰጥበት አቅጣጫ ሊቀመጥ ይገባል።" - በድሬዳዋ የከዋኪብ ሙስሊም ወጣቶች የከዋኪብ ሙስሊም ሴቶች ከኢማሙ ነወዊ ኮሌጅ ተማሪዎች ጋር ባዘጋጁት መድረክ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጀምሮ ባሉ የትምህርት ተቋማት በሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ስላለው የመብት ጥሰት ያነሱ ሲሆን መሠል የመብት ጥሰት ሙስሊም ተማሪዎችን ከትምህርት ከማግለሉ ባሻገር ሀገር የተማረ ዜጋ እንዳይኖራት የሚያደርግ ስለሆነ በሀገራዊ ምክክሩ ለዘላቂው መፍትሔ አቅጣጫ እኖዲቀመጥ ጠይቀዋል። በመፍትሔው የሙስሊም ተማሪዎችን መብት የሚጠብቁ ሕጎች ይወጡ ዘንድ የተጠቆመ ሲሆን ዋስትና ይሆን ዘንድም መሠል የመብት ጥሰቶችን የሚፈፅሙ አካላት የሚጠየቁባቸው ማዕቀፎች ይዘረጉ ዘንድ ተጠቁሟል። @aaumsu