- Последний пост
- 09:18
- Последнее чтение
- 18:33
- Постов за неделю
- 58
- Всего постов
- 61
- Тип
- открытый
- Язык
- арабский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 6 748
- 1/48двое суток
- 7 733
- 1/72трое суток
- 8 340
Медиана по постам, которые мы застали свежими и померили через сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ዛሬ ቅዳሜ ነሐሴ 09/2018 የኪታቡ ተውሒድ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ። * ቦታ፦ ሑዘይፋ መስጂድ (ከየሺ ደበሌ ከፍ ብሎ) * ጊዜ፦ ዘወትር ቅዳሜና እሁድ ከመግሪብ እስከ ዒሻ * ኪታቡ የሌላችሁ በዚህ ሊንክ pdf ፋይል ታገኛላችሁ:- https://t.me/IbnuMunewor/9564
የተጠናቀቀ የሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም ኪታብ ደርሶች:- ~ የኪታቡ ፒዲኤፍ ፋይል፦ https://t.me/IbnuMunewor/9250 ክፍል 1↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9271 ክፍል 2↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9299 ክፍል 3↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9309 ክፍል 4 ↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9316 ክፍል 5↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9320 ክፍል 6↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9323 ክፍል 7 ↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9343 ክፍል 8↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9344 ክፍል 9 ↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9349 ክፍል 10↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9361 ክፍል 11↓↓↓ https://t.me/IbnuMunewor/9395 ክፍል 12 https://t.me/IbnuMunewor/9396 ክፍል 13 https://t.me/IbnuMunewor/9401 ክፍል 14 https://t.me/IbnuMunewor/9415 ክፍል 15 https://t.me/IbnuMunewor/9424 ክፍል 16 https://t.me/IbnuMunewor/9430 ክፍል 17 https://t.me/IbnuMunewor/9436 ክፍል 18 https://t.me/IbnuMunewor/9439 ክፍል 19 https://t.me/IbnuMunewor/9445 ክፍል 20 https://t.me/IbnuMunewor/9512 ክፍል 21 https://t.me/IbnuMunewor/9520 ክፍል 22 https://t.me/IbnuMunewor/9524 ክፍል 23 https://t.me/IbnuMunewor/9563 ክፍል 24 https://t.me/IbnuMunewor/9608 ክፍል 25 https://t.me/IbnuMunewor/9626 ክፍል 26 https://t.me/IbnuMunewor/9646 ክፍል 27 https://t.me/IbnuMunewor/9654 ክፍል 28 https://t.me/IbnuMunewor/9667 ክፍል 29 https://t.me/IbnuMunewor/9671 ክፍል 30 https://t.me/IbnuMunewor/9681 ክፍል 31 https://t.me/IbnuMunewor/9705 ክፍል 32 https://t.me/IbnuMunewor/9712 ክፍል 33 https://t.me/IbnuMunewor/9722 ክፍል 34 https://t.me/IbnuMunewor/9739 ክፍል 35 https://t.me/IbnuMunewor/9748 ክፍል 36 https://t.me/IbnuMunewor/9755 ክፍል 37 https://t.me/IbnuMunewor/9781 ክፍል 38 https://t.me/IbnuMunewor/9789 ክፍል 39 https://t.me/IbnuMunewor/9794 ክፍል 40 https://t.me/IbnuMunewor/9818 ክፍል 41 https://t.me/IbnuMunewor/9822 ክፍል 42 https://t.me/IbnuMunewor/9829 ክፍል 43 https://t.me/IbnuMunewor/9872 ክፍል 44 https://t.me/IbnuMunewor/9887 ክፍል 45 (የመጨረሻ) https://t.me/IbnuMunewor/9898
видео или голосовое, без подписи
ሶሐቦች በያመቱ ረቢዑል አወል 12 ላይ በመሰባሰብ፣ ድግስ እያዘጋጁ፣ እየጨፈሩ መውሊድን ያከበሩ ነበር የሚል አንድ ማስረጃ የለም። አንድ እንኳ! ስለማይወዷቸው ነው ያላከበሩት? በፍፁም! እንዲያውም ስለሚወዷቸው ነው ያልታዘዙትን ከመፈፀም የተቆጠቡት። መቼም ከሶሐቦች በላይ ነብያችንን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እወዳለሁ የሚል አይኖርም። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
መውሊድ - በፉክክር የተጀመረ በዓል ነው! ~ መውሊድ ቀደምት የኢስላም ትውልዶች ዘንድ የማይታወቅ መጤ ፈጠራ መሆኑን ራሳቸው የመውሊድ አክባሪ የሆኑ አካላት የመሰከሩትን አሳልፌያለሁ። እነዚሁ አካላት መውሊድ ከክርስቲያኖቹ ገና ተኮርጆ በፉክክር እንደሚከበር የተናገሩቱን ደግሞ እናያለን። ዘግይተው የመጡ አንዳንድ ሱፍዮች ግን “መውሊድ በሀይማኖታችን መረጃዎች መሰረት የተፈቀደ በመሆኑ ላይ ከተግባባን ከክርስቲያን ወይም ከሂንዱ እምነት ጋር ባጋጣሚ ተመሳስሎ ቢገኝ ችግር የለውም” ይላሉ። በሀይማኖታችን መሰረት ቢኖረውማ እነ ኢብኑ ሐጀር “የመውሊድ ተግባር መሰረቱ ቢድዐ ነው። በሶስቱ ክፍለ ዘመናት ከነበሩት መልካም ቀደምቶች ከአንድም አልተላለፈም” አይሉም ነበር። እያከበሩ ያሉት ሌላ መልክ ያለው ገና ነው። ገና (chrismas) ማለት ልደት ማለት ነው። ልደት ማለት ደግሞ በዐረብኛው መውሊድ ማለት ነው። ስለዚህ የሚከበረው ማንነት እንጂ የተለየው የሚያከብሩት ገናን ነው። የክርስቲያኖች ገና = የሱፍዮች መውሊድ! የክርስቲያኖች መውሊድ = የሱፍዮች ገና! እንዲያውም መውሊድን የሚያከብሩት ከክርስቲያኖች ጋር ለመፎካከር ብለው ነው። የፉክክር ዒባዳ ማለት ነው! ይህንን ሐቅ በኪታብ ሳይቀር ያሰፈሩት አሉ። መረጃ እጠቅሳለሁ፡- 1. አስ-ሰኻዊይ ምን እንደሚል ተመልከቱ፡- “ባለ መስቀሎቹ (ክርስቲያኖች) የነብያቸውን ልደት ትልቁ ዒዳቸው አድርገው የሚይዙ ከሆነ ሙስሊሞችም (ነብያቸውን) በማክበርና በማላቅ ይበልጥ የተገቡ ናቸው።” [አት-ቲብሩል መስቡክ፡ 14] 2. ከጀዘሪም ቃል በቃል ተላልፏል። 3. አቡል ዐባስ አል-አዘፊይ (መውሊድን ለምዕራቡ ዐረቢያ ያስተዋወቀ ነው)፡- በክርስቲያን በዓላት ላይ የሚሳተፉ ወጣቶችን ለመመለስ ሲል እንደጀመረው በግልፅ ተናግሯል። 4. ዐብዱላህ አልሀረሪይ (የአሕባሾቹ መሪ):- ንጉስ ሙዞፈር መውሊድን የጀመረው ክርስቲያኖች የመሲሕ ልደትን በዓል ሲያከብሩ ተመልክቶ ነው። በዚህም ሳቢያ ሰይዳችንን ሙሐመድን ﷺ ስላወጣልን አላህን ለማመስገን ሲል መውሊድን ጀመረ ይላል። [ኢዝሃሩል ዐቂደቲ ሱንኒያህ፡ 240] ስለዚህ የመውሊድ ቢድዐን በፉክክር የተለከፉ ሰዎች የፈጠሩት መጤ ፈሊጥ ነው ማለት ነው። በዚህ መልኩ በሌሎች መመሳሰል ደግሞ የተወገዘ እንደሆነ ነብያችን ﷺ አጥብቀው አሳስበዋል። * ማስረጃ አንድ፦ مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ "አንድን ሕዝብ የተመሳሰለ (የተከተለ) ከእነርሱ ነው (እንደነርሱ ይቆጠራል)።" [አቡ ዳውድ ፡ 4031] * ማስረጃ ሁለት፦ በሌላም ሐዲሥ ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ لتتَّبعنَّ سَننَ من كانَ قبلَكم حذو القُذَّةِ بالقُذَّةِ حتَّى لو دخلوا جحرَ ضبٍّ لدخلتُموه. قالوا: اليَهودُ والنَّصارى؟ قالَ: فمَن “በርግጥ ከናንተ በፊት የነበሩ ሰዎችን ፈለጎች ስንዝር በስንዝር ክንድ በክንድ ትከተላላችሁ። የወከሎ ጉድጓድ ቢገቡ እንኳን በርግጥም ትገቡታላችሁ!” ሲሉ “አይሁድና ክርስቲያኖችን ነው (ትከተላላችሁ) የምትለን?” ብለው ቢጠይቁ “ታዲያ ማንን ነው?!” አሉ። [ቡኻሪይ፡ 7320] የተናገሩት በትክክል ተፈፀመ። ለብዙ ጥፋቶች የሚያጋልጠው በዓል ከክርስቲያኖች ተኮርጆ በ"ፋጢሚያ" ሺዐዎች ተጠንስሶ፣ በሱፍዮች ተዛምቶ ብዙ ሙስሊም ሊዘፈቅበት በቅቷል። የሚያሳፍረው “ክርስቲያኖቹ የነብያቸውን ልደት እያከበሩ የኛ ነብይ ከማን ያንሳሉ?” የሚሉት ነገር ነው። ሱብሓነላህ! ለመሆኑ ዒሳ የኢስላም ነብይ አይደሉም እንዴ?! ታዲያ ይሄ ምን የሚሉት አፀያፊ ሎጂክ ነው? ደግሞ ምንም ሳያፍሩ መውሊድን የሚቃወሙ ሙስሊሞችን “የነቢ ጠላቶች ናቸው!” እያሉ ከባድ ክስ ይከሳሉ። የነብዩን ﷺ መውሊድ አለማክበር እሳቸውን መጥላት ከሆነ እናንተም የክርስቲያኖቹን ገና (chrismasን) ባለማክበራችሁ የዒሳ ጠላቶች ናችሁ ማለት ነው። መውሊድን ማክበር ነብዩን ﷺ ማክበር ከሆነ የሌሎቹን ነብያት ልደቶች ስለማታከብሩ ለሌሎች ነብያት በሙሉ ክብር የሌላችሁ የነብያት ጠላቶች ናችሁ ማለት ነው። ከአንደበታችሁ በቀጥታ ባይወጣም አመክኗችሁ የሚሰጠው ይህንን ነው። አንዳንዶች "ገናን የማናከብረው የዒሳን ልደት ስለማናውቅ ነው" ይላሉ። የነብያችንም ﷺ የውልደት በየትኛው የረቢዕ ቀን ላይ እንደሆነ የሚያሳይ ሶሒሕ ማስረጃ የለም። በ12ኛው ቀን ነው የሚለው የሰነድ መቆረጥ እንዳለበት ኢብኑ ከሢር ገልፀዋል። [አልቢዳያ ወንኒሃያ፡ 3/109] = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
видео или голосовое, без подписи
የሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም ኪታብ ደርስ ተጠናቋል፣ አልሐምዱ ሊላህ። በቀጣይ የምንጀምረው የሉምዐቱል ኢዕቲቃድ ኪታብ ይሆናል። ኪታቡን በቀጥታ ይዛችሁ መከታተል የምትፈልጉ ከወዲሁ መግዛት ትችላላችሁ። ባረከላሁ ፊኩም። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
ደርስ ~ • ሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም • ክፍል:- 45 (የመጨረሻ ደርስ) • የኪታቡ ፋይል በpdf መልኩ በዚህ ሊንክ ይገኛል:- https://t.me/IbnuMunewor/9421 • የእለቱ ደርስ መነሻ፦ ገፅ፡ 118
Live stream finished (1 hour)
አስቸኳይ የትብብር ጥያቄ ~ አንዲት እህታችን "ማህበረሰቤን ልጥቀም" ብላ አንድ ኸይር አሰበች። ወለኔ ውስጥ ቤደር የምትባል መንደር ላይ አንድ መርከዝ ማሰራት አስባ ሞከረች ሞከረች ሞከረች ግን ግቡን ሊመታ ቀርቶ ሩቡን ማሳካት አልቻለችም። ወላሂ የተፈለገው ገንዘብ ትንሽ ነው። ነገር ግን የረባ ትብብር ባለመኖሩ እዚህ ግባ የሚባል ድጋፍ አልተሰበሰበም። እውነት ብንረባረብ ሁለት ሚሊዮን ብር ብዙ ነው ወይ? ለዚሁ አላም ታስቦ ዛሬ ጁምዓ ማታ 3 ሰዓት ላይ የተወሰኑ ኡስታዞች የሚሳተፉበት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም ይኖራልና በመገኘት የድርሻቸውን እንድትወጡ አደራ እላለሁ። የግሩፑ ሊንክ 👉 https://t.me/+h5YVkNAk55hkYWI8 ፕሮግራሙ ላይ መገኘት የማትችሉም ትንሽ ትልቅ ሳትሉ በዚህ አካውንት በማስገባት አግዙ:- 1000675591664 ሱፍያን ሱልጣን እና ቀድሪያ ኸድር አላህ ይቀበላችሁ። ከተባበርን በጣም ትንሽ ነው። ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ፣ ለሃምሳ ሰው ደግሞ ጌጡ ነው።
Live stream started
Live stream finished (16 seconds)
Live stream started
ዛሬ ሃሙስ ጁሙዐ 08/2018 የሒልየቱ ጧሊቢል ዒልም ኪታብ ደርስ ይኖራል፣ ኢንሻአላህ። * የሚሰጥበት ቦታ:- አሸዋ ሜዳ መስጂደል ዋሊደይን * ጊዜ:- ከመግሪብ እስከ ዒሻእ * የኪታቡን pdf ፋይል በዚህ ታገኙታላችሁ፦ https://t.me/IbnuMunewor/9421 * የዛሬ ደርስ መነሻ:- ገፅ፡ 118 * ቦታው ላይ መገኘት ለማትችሉ ደርሱ በዚህ የቴሌግራም ቻናል ይተላለፋል፡- https://t.me/IbnuMunewor
14. በመውሊድ በዓላት የተከበሩ የአላህ ቤቶች በጭብጨባ፣ በውዝዋዜና በጭፈራ ክብራቸው ይረከሳል። ይሄ ደግሞ አላህ ከሃዲዎችን እንዲህ ሲል ከወቀሰባቸው ነገሮች ውስጥ ነው፡- (وَمَا كَانَ صَلَاتُهُمۡ عِندَ ٱلۡبَيۡتِ إِلَّا مُكَآءٗ وَتَصۡدِيَةٗۚ) {በቤቱ ዘንድም ስግደታቸው ማፏጨትና ማጨብጨብ እንጂ ሌላ አልነበረም።} [አል-አንፋል፡ 35] ሃያሉ ጌታ እንዲከበሩና ስሙ እንዲወሳባቸው ባዘዘባቸው መስጂዶች ውስጥ ድቤ መደብደብ፣ ማጨብጨብና መጨፈር በአራቱም መዝሀብ የተወገዘ እጅግ አስነዋሪ ተግባር ነው። ይህን ቆሻሻ ተግባር መቃረቢያ አድርጎ ማሰብ ደግሞ የለየለት ጥመት ነው። ኢብኑል ጀውዚይ፡ “ዳንስን ወደ ላቀው አላህ መቃረቢያ ነው ብሎ የሞገተ ሰው ከኢስላም እንደሚወጣ የዑለማዎች ኢጅማዕ ተቋጭቷል” ብሏል። [ሶይዱል ኻጢር፡ 168] 15. ብዙ የመውሊድ ዝግጅቶች የሴትና የወንድ ቅልቅል በብዛት አለባቸው። የብል -ግና መናሃሪያ እየሆኑም ነው። በእለቱ እቃ እያዞሩ የሚሸጡ ሰዎች ሲጋራ፣ ኮንዶምና መሰል ነገሮችን እንደሚይዙ ተጨባጭ መረጃ አለ። በአንዳንድ አካባቢዎች ሴተኛ አዳሪዎች መውሊድ በሚከበርበት አካባቢ የተለያዩ ነገሮችን ለመሸጥ በሚል ሽፋን ጊዜያዊ ዳስ በመቀለስ ለጥፋት እንደሚሰማሩ ከሰበሰብኳቸው መረጃዎች አረጋግጫለሁ። አል-መቅሪዚይ በ790 ሂጅሪያ በዒማዱል አንባኒይ በተዘጋጀው መውሊድ ላይ የታዘበውን እንዲህ ሲል ይገልፀዋል፡- “ሜዳው በዓሊሞች እስከሚጨናነቅ ህዝብ ጎረፈ። በዚያች ሌሊት ሴቶችና ወጣቶች ከባለጌዎች ጋር በመቀላቀላቸው ምክንያት ብዙ አይነት ብልግናዎች ተፈፀሙ። ማለዳ ላይ ሌሊቱን የተጠጡ ከሃምሳ በላይ የአስካሪ መጠጥ እንስራዎች በዛውያው ዙሪያ በነበሩ እርሻዎች ውስጥ ተጥለው እንደተገኙ፣ በርካታ ደናግላንም ክብረ-ንፅህናቸው እንደተገሰሰ፣ በጣም ብዙ ገንዘብ የወጣባቸው ሻማዎችም እንደተለኮሱ እጅግ በርካታ መረጃ ወጥቷል። በማግስቱ ጧት አላህ የንፋስ ጥቃት ላከባቸውና ከቦታው የነበሩ ሰዎችን ፊታቸውን አፈር አለበሳቸው። ድንኳኖቹንም ቆራረጣቸው። አንድም ሰው ባህር መሳፈር አልቻለም። ከዚያን ጊዜ በኋላ መውሊድ አልተዘጋጀም።” [ዱረሩል ዑቁዲል ፈሪዳህ፡ 2/501] 16. የመውሊድ ጨፋሪዎች በውዝውዛኔና መሰል ነገሮች ሰውነታቸው ዝሎ ሌሊቱን ገፍተው ስለሚተኙ አብዛኞቹ የፈጅር ሶላትን የተወሰኑት ደግሞ ዙህርንም ጭምር አይሰግዱም። ለነገሩ ክፍለ - ሃገር ላይ አብዛኛው ታዳሚ ከነጭራሹ ሶላት ሰጋጅ አይደለም። 17. መውሊድ ለማክበር አገር አቋርጠው ረጃጅም ርቀቶችን የሚጓዙ ሰዎች ሞልተዋል። ነብዩ ﷺ ግን ለቢድዐ ቀርቶ ለአላህ ታስቦ ለሚፈፀመው አምልኮት እንኳን ከሶስቱ መስጂዶች (መስጂደል ሐራም፣ መዲና የነብዩ መስጂድ እና አቅሷ) ውጭ አገር አቋርጦ መጓዝ እንደማይገባ አሳስበዋል። [ቡኻሪ፡ 1189] [ሙስሊም፡ 3450] አገር አቋርጠው ያለ መሕረም የሚጓዙ ሴቶችም ቀላል አይደሉም። ነብዩ ﷺ ግን “ማንኛዋም ሴት ከቅርብ ወንድ ቤተሰቧ ጋር እንጂ እንዳትጓዝ” ብለዋል። [ቡኻሪ፡ 1862] 18. መውሊድ የልዩነት መንሰኤ ነው። ለዚህም መውሊድ በተቃረበ ቁጥር የሚነሳውን ውዝግብ መስማቱ ብቻ በቂ ነው። በመውሊድ ላይ ስላልተጋሯቸው ብቻ “ወሃ ~ ቢ”፣ “የነቢ ጠ ^ላት”፣ “ከአይ ^ ሁድ በከፋ ዲን ያበላሹ” እያሉ ሙስሊሞችን መወንጀል የተለመደ ዘመቻ ነው። ኢብኑ ተይሚያ ረሒመሁላህ እንደሚሉት “ቢድዐ ከልዩነት ጋር የተቆራኘ ነው።” ስለዚህ ቢድዐው እስካለ ድረስ መለያየቱ አይቀርም። ሸውካኒይ እንዲህ ይላሉ፡- “ደግሞም ይሄ መውሊድ ከተከሰተ በኋላ ውዝግቡ ተጧጡፏል። በዚህም ላይ የሚፃፉት ኪታቦች ከከልካዩም ከፈቃጁም በዝተዋል። … ከነሱ ውስጥ እንደማይፈቀድ ቁርጥ አድርጎ የተናገረ ሲኖር ከነሱ ቢድዐነቱን አምኖ መጥፎ ነገር ካልተቆራኘው በሚል መስፈርት የፈቀደው አለ፣ ምንም ማስረጃ ግን አላመጣም።” [አልፈትሑ ረባኒይ፡ 2/1091 - 1095] ጥፋቶቹ እነዚህ ብቻ አይደሉም። ይህን ሁሉ ጉድ አጭቆ የያዘ ቢድዐ ከጥቃቅን ነገሮች ነውን? ህሊና ያለው ይፍረድ። በርግጥ ከነዚህ ጥፋቶች ውስጥ ከፊሎቹን የሚርቁ አሉ። ግና አንደኛ ጥቂት ናቸው። ሁለትኛ እነዚህ እራሱ ድግሳቸውን በሺርክ የተቀላቀለ መንዙማ ባዮችን ይጋብዙበታል። ከሺርኩ ቢጠራም ድርጊቱ በራሱ መረጃ የለውምና ከቢድዐነት አይዘልም። ሶስተኛ በጥፋት የተወረረውን መውሊድ ሊያወግዙ ቀርቶ የሚያወግዙትን የሚነቅፉ ናቸው። ስለሆነም ጥፋታቸው ከነዚያኞቹ ጥፋት ብዙም የራቀ አይደለም። = ኢብኑ ሙነወር የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor