Abu muhammed (አቡ ሙሀመድ
Статистикаበዚህ ቻናል የተለያዩ ኪታቦችን የምንቀራበት የቂርአት ቻናል ነዉ
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 18
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 215
- 1/48двое суток
- 246
- 1/72трое суток
- 265
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ፈጥኖ ማን ይመልስ ! ✈️✈️ ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ስንት ክንፎች አሉት ?
ኹጥባ ነቢዩን መከተልhttps://t.me/Abu_Mohammed_Seid
https://youtube.com/shorts/MdD5WtBOE1c?si=JRBbR9AdGH5tfUnv
🔖አዲስ ተከታታይ ትምህርት 📚رياض الصالحين من كلام سيد المرسلين 🎙በአቡ ሙሀመድ 📚የሪያዱ ሷሊሒን ኪታብ ማብራሪያ - ክፍል ( 5⃣9⃣ https://t.me/UstazAbuMuhammed
видео или голосовое, без подписи
https://t.me/merkez_ibnu_kesir?livestream=32cb3b56b024149cee
Live stream finished (1 minute)
Live stream started
Live stream finished (5 minutes)
https://t.me/Abu_Mohammed_Seid?livestream=cb4f0697ce5bb90808
Live stream started
1
መውሊድና ነባሩ እስልምና አይተዋወቁም! {ምስክር እራሳቸው!} ~ ቀደም ባለው ዘመን መውሊድን ደጋፊዎቹ ጭምር ቢድዐ መሆኑን ያምኑ ነበር። ክርክራቸው ቢድዐ ሐሰና (መልካም ቢድዐ) ነው የሚል ነበር። ዛሬስ?አይናቸውን በጨው አጥበው እነ አቡበክርንና እነ ዑመርን ሳይቀር መውሊድ አክባሪዎች እያደረጓቸው ነው። አንዳንዶቹማ ነብዩን ﷺ ሳይቀር መውሊድ አክባሪ ለማድረግ ሲንደፋደፉ ትንሽ እንኳን አይሰቀጥጣቸውም። ነብዩ ﷺ “በኔ ላይ ሆነ ብሎ የዋሸ ሰው መቀመጫውን ከእሳት ያዘጋጅ!” ብለዋል። [ቡኻሪና ሙስሊም] እልህ በሳቸው ላይ እስከሚዋሽ ያደረሰው ሰው ወዮለት! ለማንኛውም ቀደም ያሉት የመውሊድ #ደጋፊዎች ይሄ ድግስ ከነባሩና ከጥንቱ ኢስላም ውስጥ የማይታወቅ መጤ ፈሊጥ እንደሆነ አስረግጠው መስክረዋል። ንግግራቸውን እጠቅሳለሁ፡- 1. አቡ ሻመህ (665 ሂ.)፡- “በዘመናችን ከተፈጠሩ ከዚህ አይነት ነገሮች ያማረ ከሆነው የላቀው አላህ ይጠግናትና በኢርቢል ከተማ በያመቱ ከነብዩ ﷺ የልደት ቀን ጋር በሚገጥመው ቀን ይፈፀሙ የነበሩ ሶደቃዎች፣ በጎ ነገሮች፣ ጌጦችንና ደስታን ማንፀባረቅ ነው።” [አልባዒሥ ዐላ ኢንካሪል ቢደዕ ወልሐዋዲሥ፡ 95] 2. አት-ተዝመንቲይ (682 ሂ.)፡- “የመውሊድ ተግባር በመልካም ቀደምቶች የኢስላም ቀዳሚ ዘመን አልተከሰተም።” [አስ-ሲረቱ አሽ-ሻሚያህ፡ 1/441] 3. አቡ ዙርዐህ አል-ዒራቂይ (826 ሂ.)፡- “ይህንን ነገር ምግብ በማብላት መልኩ እንኳን ከሰለፎች አናውቀውም።” [ተሽኒፉል ኣዛን፡ 136] 4. ኢብኑ ሐጀር (852 ሂ.)፡- “የመውሊድ ድርጊት መሰረቱ ቢድዐ ነው። ከሶስቱም ክፍለ-ዘመናት መልካም ቀደምቶች አልተላለፈም።” [አልሓዊ ሊልፈታዊ፡ 1/188] 5. አስ-ሰኻዊይ (902 ሂ.)፡- “የተከበረው መውሊድ ተግባር በተከበሩት ሶስቱ ክፍለ-ዘመናት ይኖሩ ከነበሩት ደጋግ ቀደምቶች ከአንድም አልተገኘም። ይልቁንም የተከሰተው ከዚያ በኋላ ነው።” [ሱቡሉል ሁዳ ወረሻድ፡ 1/439] 6. አስ-ሲዩጢይ (911 ሂ.)፡- “የመጀመሪያው ይህን ስራ የፈጠረው የኢርቢሉ ንጉስ ሙዞፈር ነው።” [አል-ሓዊ፡ 1/189] (መጤ እንደሆነ መናገራቸውን ለመውሰድ ያክል እንጂ ንግግሩን ያጣቀስኩት መውሊድ የተጀመረው በሺዐዎች እንደሆነ በማስረጃ አሳልፌያለሁ።) 7. አዝ-ዘርቃኒይ (1112 ሂ.)፡- “መውሊድን መፈፀም ቢድዐ ነው።” [ሸርሑል መዋሂብ፡ 1/264] ይስተዋል። እነዚህ ሁሉም የመውሊድ ደጋፊዎች ከመሆናቸው ጋር ቢድዐ እንደሆነ ግን ባንድ ድምፅ እየመሰከሩ ነው። (وَشَهِدَ شَاهِدࣱ مِّنۡ أَهۡلِهَاۤ) እነዚህ ሁሉም የመውሊድ ደጋፊዎች ከመሆናቸው ጋር ቢድዐ መሆኑን በግልፅ ይናገራሉ። የድሮዎቹ መውሊድ አክባሪዎች ከነ ክፍተታቸው የሆነ ያክል ኢንሷፍ ነበራቸው፣ ሚዛናዊነት። ቢያንስ መጤ ቢድዐ መሆኑን እንዲህ እቅጩን ይናገራሉ። የዛሬዎቹስ? አይኔን ግንባር ያድርገው ካሉ አይመለሱም። ብቻ አንባቢ አንድ ቁም ነገር ይውሰድ። መውሊድ በደጋፊም በነቃፊም ኢጅማዕ (የጋራ ስምምነት) መጤ ፈሊጥ ነው፣ ቀደምት ሙስሊሞች ዘንድ የማይታወቅ ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ የተጠነሰሰ ቢድዐ!! በየመንደሩ ከዚህ የተለየ እያስተጋቡ ለሚበጠብጡ አካላት ይሄ አስደንጋጭ መብረቅ ነው! “ነባሩ እስልምና” እያሉ ልባችንን ለሚያደርቁ ሁሉ አንድ መልእክት ይድረሳቸው። ነባሩ ኢስላም ማለት የነብዩ ﷺ፣ የሶሐቦች፣ የታቢዒዮች፣ የአትባዑ ታቢዒን ኢስላም ነው። የአኢማዎቹ፣ የነ ቡኻሪ፣ የነ ሙስሊም፣… ኢስላም። ከዚህ ውጭ ያለ እምነት በኢስላም ስም ቢጠራም፣ "ነባሩ" እያሉ ቢያሽሞነሙኑትም ነባር ሳይሆን ፎርጂድ ነው። ስለዚህ መውሊድና ነባሩ እስልምና ፈፅሞ አይተዋወቁም። ስለሆነም መውሊድን የሚቃወመው የተሀድሶ እንቅስቃሴ ወዝጋባ ሱፍዮች እንደሚሉት የሃያና የሰላሳ አመት እድሜ ያለው ወይም በ “ወሃ.ብዮች” የተጀመረ አዲስ ፈሊጥ ሳይሆን ስሩ ከነብዩ ﷺ ዘንድ የሚዘልቅ ከሱፍ .ዮቹ የተንሻፈፈ አረዳድ የቀደመ ጥንታዊ ነው ማለት ነው። ማምታቻ! - መውሊድ ራሳቸው በሚያከብሯቸው የመውሊድ ደጋፊዎች ቢድዐ መሆኑ ሲነገር ጊዜ እንደ ሐሰን ታጁ ያሉ የዚህ ቢድዐ ደጋፊዎች ሌላ ማምታቻ አምጥተዋል። ይኼውም ቢድዐ የሆነው በኦፊሴል ማክበሩ እንጂ ቀድሞም ነበር የሚል። ይሄ የለየለት ማምታታት ነው። 1ኛ፦ በቁርኣንም በሐዲሥም የመውሊድ በዓል ፈፅሞ አልተወሳም። ቢወሳ ኖሮ ቀደምቶች በተፍሲራቸውና በሐዲሥ ድርሳኖቻቸው ይገልፁት ነበርና። 2ኛ፦ ከሰለፎች ውስጥ አንድ እንኳ ኦፊሴል ባልሆነ መልኩ እንኳ ያከብሩ እንደነበር መረጃ የለም። 3ኛ፦ በቁርኣንና በሐዲሥ የሚገኝ፣ በሰለፎች የተፈፀመ ቢሆን ኖሮ ከላይ የዘረዘርኳቸው የመውሊድ ደጋፊዎች ቢድዐ ነው ብለው አይደመድሙም ነበር። አንዳቸውም በኦፊሴል ከመከበሩ በፊት በግል ወይም በማህበረሰብ ደረጃ ይከበር ነበር አላሉም። = የቴሌግራም ቻናል ፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
видео или голосовое, без подписи
ሸውካኒ እና መውሊድ (ወሳኝ ነጥቦች የተዳሰሱበት) ~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~ ሙሐመድ ኢብኑ ዐሊ አሽሸውካኒ በ1250 ሂ. የሞቱ ታላቅ የመናዊ ዓሊም ናቸው፡፡ በሰፊው የሚታወቁ ስለሆኑ እሳቸውን በማስተዋወቅ ፅሑፌን ማስረዘም አልሻም፡፡ ሸውካኒ መውሊድ ላይ እጅግ የሰላ ትችት ሰንዝረዋል፡፡ ዛሬ በተደጋጋሚ ከምንሰማቸው መውሊድ ተኮር ጥያቄዎች ውስጥ የተወሰኑትን በመምዘዝ በሸውካኒ ንግግር ምላሽ ለመስጠት ሞክሬያለሁ፡፡ ሙሉ ንግግራቸውን መመልከት የፈለገ ሰው “አልፈትሑ ረባኒ ሚን ፈታወል ኢማሚ ሸውካኒ” በተሰኘው የፈትዋ መድብላቸው ውስጥ ሁለተኛውን ጥራዝ ከገፅ 1087-1101 ድረስ መመልከት ይችላል፡፡ ፅሑፉ ስለ ረዘመ ዐረብኛውን ማካተት አልቻልኩም፡፡ 1. መውሊድ የሸሪዐ መነሻ አለውን? ሸውካኒ፡- “እስካሁን ድረስ ከቁርኣንም፣ ከሱናም፣ ከኢጅማዕም፣ ከቂያስም (ንፅፅራዊ ምልከታም) መሰረት እንዳለው የሚያመላክት መረጃ አላገኘሁለትም፡፡” [ገፅ፡ 2/1087] 2. መውሊድን ሰለፎች ያውቁታል? ሸውካኒ፡- “እንዲያውም ከዘመናት ሁሉ ምርጡ በሆነው (የሶሐቦች) ዘመንም፣ ከነሱ ቀጥሎ በነበሩትም፣ ቀጥሎ በነበሩትም (ዘመን) እንዳልነበር ሙስሊሞች ወጥ አቋም ይዘዋል (ኢጅማዕ አድርገዋል፡፡)” [ገፅ፡ 2/1087] 3. ቢድዐ በመሆኑ ላይ ልዩነት አለ? ሸውካኒ፡- “ቢድዐ በመሆኑ ላይ ከሙስሊሞች አንድ እንኳን የተቃወመ የለም፡፡” [ገፅ፡ 2/1088] “ይሄ ነገር ቢድዐ በመሆኑ ላይ ከሁሉም ሙስሊሞች ኢጅማዕ እንዳለበት አረጋግጠንልሃል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091] 4. መውሊድን በሚደግፉ መሻይኾች ማስፈራራት ያዋጣል? ሸውካኒ፡- “በምርጡ ነብይ ﷺ የማያሻማ ምስክርነት ቢድዐ ሁሉ ጥመት እንደሆነ ተነግሮ ሳለ የመውሊድን ቢድዐ መሆን ካመነ በኋላ ይፈቀዳል የሚል ሰው የተናገረው ከንፁሁ ሸሪዐ ጋር የሚፃረር ንግግር ነው፡፡ ያለ አንድ ተጨባጭ እውቀታዊ መነሻ ቢድዐን ወደተለያዩ ክፍሎች ለከፈለ ሰው በጭፍን ከመከተል ያለፈ ነገርም የለውም፡፡ የትኛውንም አቋም ይቻላል የሚልን ሰው ይህንን ቢድዐ በተለየ የሚመለከት ማስረጃ ካቀረበ በኋላ እንጂ አንቀበለውም፡፡ … እንጂ ‘እከሌ እንዲህ አለ’፣ ‘እከሌ እንዲህ አይነት ኪታብ አዘጋጅቷል’ የሚል ባዶ ንግግር ፋይዳ የለውም፡፡ ሐቅ ከየትኛውም አካል ይበልጣልና፡፡” [ገፅ፡ 2/1088 - 1089] “ከነሱ (ከፈቃጆቹ) ውስጥ ቢድዐነቱን አምኖ መጥፎ ነገር ካልተቆራኘው በሚል መስፈርት የፈቀደው አለ፡፡ ምንም ማስረጃ ግን አላመጣም፡፡” [ገፅ፡ 2/1094] ኢብኑ ሐጀር እንዳደረገው የዓሹራን ፆም ማስረጃ ማድረግ፣ ወይም ሲዩጢ እንዳደረገው ከነብይነት በኋላ ለራሳቸው ዐቂቃ ማውጣታቸውን መመርኮዝ ቢድዐን የማፅናት ፍቅር እንዲህ አይነት ነገር ላይ እንደሚጥል ከሚያሳዩ አስገራሚ ነገሮች ውስጥ ነው፡፡ [ገፅ፡ 1095] 5. መውሊድ የብዙሃን ሙስሊሞች ድጋፍ ነበረውን? ሸውካኒ፡- “በሰዎች ንግግሮች ላይ የምንመረኮዝ ከሆንና የእንቶ ፈንቶ ጅራቶችን የምንጨብጥ ከሆንን መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር ‘ይፈቀዳል’ ባዮቹ ከሙስሊሞች በአቋም ያፈነገጡ ናቸው፡፡ …” [ገፅ፡ 2/1087-1089] “ሲጨመቅ የመውሊድ ፈቃጆች ከከልካዮቹ አንፃር ሲታዩ ጥቂቶች ናቸው፡፡ ለዚያውም እነሱም ቢሆኑ ምግብ ለማብላትና ለዚክር ካልሆነ በስተቀር እንደማይቻል ተስማምተዋል፡፡” [ገፅ፡ 1095–1099] (አስተውሉ! ይህ እንግዲህ በሸውካኒ ዘመን ነው፡፡ የሞቱት በ1250 ሂ. ሲሆን ሁለት መቶ አመት ሊሞላቸው ጥቂት ነው የቀራቸው፡፡ አሕባሽ ደፋር ነውና የዛሬን የመውሊድ ጨፋሪዎች በመመልከት ሸውካኒን “ውሸታም ነው” እንዳይሉ እሰጋለሁ፡፡) 6. መውሊድ እንዴት ተስፋፋ? ሸውካኒ፡- “ግና ቢድዐን በማፅናትም ሆነ በማውደም ላይ ለንጉሳን ተፅእኖ አላቸው፡፡ ይህንን ቢድዐ (በሱኒው ዓለም ውስጥ) የፈጠረው ያ ንግስ (ሙዞፈር) ሲሆን ኢብኑ ዲሕያ ደግሞ ‘አትተንዊር ፊ መውሊዲል በሺር አንነዚር’ የተሰኘ ኪታብ በማዘጋጀት አግዞታል፡፡ ሰውየው በዘገባ እውቀት ላይ የጠለቀ ከመሆኑም ጋር በዚህ ኪታቡ ግን ግልፅ ማስረጃ አላቀረበም፡፡ ለዚህ ስራው - ኢብኑ ኸሊካን እንዳወሱት - አንድ ሺህ ዲናር በንጉሱ መሸለሙ ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ የዱንያ ፍቅር ከዚህም በላይ ያደርሳል፡፡” [ገፅ፡ 2/1091] “የቢድዐ ስርጭት ከእሳት ስርጭት የፈጠነ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ መውሊድ፡፡ ምክንያቱም የመሃይማን ነፍሶች ጥግ የደረሰ መናፈቅን ይናፍቁታልና፡፡ በተለይ ደግሞ ከምሁራን፣ ከክቡራንና መሪዎች በርከት ያለ ሰው ከተካፈለበት በኋላ ይሄ ቢድዐ ወሳኝ ከሆኑ ሱናዎች ይመስላቸዋል፡፡ … እንደ መውሊድና አምሳያዎቹ ያሉ ለሐራም ነገሮች የሚያመቻቹ የጥፋት መዳረሻዎች መሃይሞች ፈጥነው እንደሚገቡባቸው አያጠራጥርም፡፡ በዚህ ላይ ደግሞ በዒልም፣ በክብርና በስልጣን ዝና ያለው ሰው መካፈል ሲታከልበት ሐራም ነገሮችን እንደ ፈጣሪ ትእዛዛት ሲፈፅሙ፣ በድንቁርናና በጥመት ሸለቆች ውስጥ ገብተው ሲዘባርቁ፣ “የተከበሩ እከሌ፣ እከሌ፣ እከሌ፣… ተገኝተዋል” እያሉ ከተቃውሞ ሲያመልጡ የባሰ ይሆናል፡፡ መሃይሙ ህዝብ ይቅርና አንዱ በዒልም ፍለጋ ላይ ገኖ የወጣ ሰው አንዳንድ የኢጅቲሃድ እውቀቶችን ለመማር ከፊቴ ተቀምጦ ነበር፡፡ በዚህ ወር ከተከናወኑ መውሊዶች ውስጥ በአንዱ አዳር ላይ እንደተካፈለ ሲነግረኝ ተቃወምኩት፡፡ አንገሸገሸኝ፡፡ በዚህን ጊዜ ‘ሰዪዲ እከሌ፣ እከሌ፣ እከሌ፣… ተካፍለዋልኮ’ አለኝ፡፡ በነዚህ ታዋቂ ሰዎች ፊት የነበረውን አፈፃፀም ስጠይቀው እንዲህ አለኝ፡- ‘እነዚያ ታዋቂ ሰዎች እየዘፈኑና እያዳመጡ መንዙማውን አንድ ሱቂ አነበበ፡፡ ከዚያም አንዱ ልክ ከእስር የተነሳ ይመስል አፈፍ ብሎ ተነስቶ “መርሐባ ያ ኑረ ዐይኒ፣ መርሐባ” (እንኳን መጣህ ያይኔ ብርሃን እንኳን መጣህ!) ሲል ታዳሚው በመላ ታዋቂዎቹን ጨምሮ ተከትለውት ቆሙ፡፡ እነሱ በዚህ ሁኔታ ላይ እያሉ ቆሞ ማጓራት ያዘ፡፡ አንዱ ታዳሚ ደክሞት ቢቀመጥ ከታዋቂዎቹ ውስጥ አንዱ ንዴቱ ከፊቱ ላይ እየታየ ተነስ ጨዋታኮ አይደለም! ብሎ ጮኸበት፡፡ ቃል በቃል!ት የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚያች ሰዓት ከነሱ ዘንድ እንደደረሱ ጭራሽ አይጠራጠሩም፡፡ ከዚያም ተጨባበጡ፡፡ ከተራው ሰዎች ከፊሎቹ በእጆቻቸው ሽቶ በመያዝ በፍጥነት ቀቡ፣ ተቀቡ፡፡ ልክ የሳቸውን ﷺ መገኘት ለመጠቀም፡፡’ ኢንና ሊላሂ ወኢንና ኢለይሂ ራጂዑን! የዲን ክብር የት ገባ?! ይህም ከጠፋ አይናፋርነት፣ ግብረ ገብነት፣ ህሊና የት ገባ?” [ገፅ፡ 2/1089-91] 7. መውሊድን የነብዩ ﷺ ቤተሰቦች ይደግፉታል? መውሊድን የሚያከብሩ ሰዎች “ከኛ በላይ ነብዩን ﷺ የሚወድ ላሳር!” የሚሉ ናቸው፡፡ እውነት ለመናገር የነብዩ ﷺ ዘሮች ሙእሚኖች ከሆኑ ለነብዩ ﷺ ያላቸው ፍቅር ልዩ ነው፡፡ መውሊዱ የፍቅር መገለጫ ቢሆን ኖሮ ከማንም ቀድመው ባከበሩት ነበር፡፡ ግን ከነሱ የተገኘው መውሊድን ማክበር፣ ማስከበር፣ ለሱ ሽንጥን ገትሮ መሟገት ነውን? ሸውካኒ፡- “ከነብዩ ﷺ ንፁሕ ቤተሰብም ይሁን ከተከታዮቻቸው ይህ ነገር እንደሚፈቀድ የተናገረ አንድም ፊደል አላገኘንም፡፡ እንዲያውም ይህቺ ቢድዐ ከተከሰተች ጀምሮ ወደ ጥፋቶች ከሚያሻግሩ አስቀያሚ መዳረሻዎች አንዷ እንደሆነች ንግግሮቻቸው ከሞላ ጎደል ተስማምተዋል፡፡” [ገፅ፡ 1089] “ከነብዩ ﷺ ቤተሰቦች እና ከተከታዮቻቸው ውስጥ ‘መውሊድ ይፈቀዳል’ ያለ አንድ እንኳን እንደሌለ ከተገለፀልህ ከነሱ ውጭ ያሉትን አቋም ልታውቅ ከፈለግክ ከሁሉም ሙስሊሞች ዘንድ ቢድዐ በመሆኑ ላ
አንድ ሰው ከሞተ ቡሃላ መላኢኮች "ምን ስራ ይዞ መጣ?" እያሉ ይጠያየቃሉ። ሰዎች ደግሞ "ምን ጥሎ ሄደ?" ይባባላሉ። አቡ ሁረይራ رضي الله عنه
https://t.me/merkez_ibnu_kesir?livestream=3d20090b21becdbc55
🔖ሰላሰቱል ኡሱል ደርስ ተ ጀ መ ረ https://t.me/+xmn5IYWebiMyNmM0
ውስጥህ ተበላሽቶ አላህን ፈሪ ከመምሰል ተጠንቀቅ ❤️🩹 ማንም አይከተልህም ፣ ስራህን አሁኑ አሳምር ፣ ለአኼይራህ ስንቅ ማዘጋጀትን አትርሳ፣ የኋላኛው ቤትህ ጥሩ ማረፊያህ ይሆን ዘንድ ....‼https://t.me/Abu_Mohammed_Seid
📌ለደረቀችው ልቤ! 🎙በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቀጥታ ስርጭት ተጀመረ! 👇👇 https://t.me/Sle_qelbachn1?livestream=4b7952a17ac57f8cf5