دُرُوسُ عَقِيدَةِ الْإِسْلَامِيَةِ فِي ضَوْءِ الكِتــَابِ وَالسُّــنَــة
Статистика- Последний пост
- 11 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- арабский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 419
- 1/48двое суток
- 480
- 1/72трое суток
- 517
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በነገራችን ላይ ዐረብኛ ቋንቋ የዐረቦች ብቻ አይደለም፣ የመላው ዓለም ሙስሊሞችም ጭምር እንጂ። 0ረብኛ የቁርኣን፣ የሐዲሥ፣ የፊቅህ የኢስላም ቋንቋ ነው። ዐረብኛ የሶላት፣ የዚክር ቋንቋ ነው። ስለዚህ ኢስላም ማንነታችን እስከሆነ ድረስ ዐረብኛ ቋንቋ የማንነታችን አካል ነው። ስለሆነም የማንችለው ለመቻል፣ የምንችለው ለማሻሻል ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል። በአራቱም የቋንቋ ክህሎቶች (መናገር፤ ማዳመጥ፣ መፃፍ እና ማንበብ) ላይ አቅማችንን ለማዳበር ብንጥር እንጠቀማለን። አላህ አግርቶለት ቋንቋውን የቻለ ደግሞ በሂደት እንዳይረሳው የሚችሉ ሰዎች ጋር ሲገናኝ ቢጠቀምበት መልካም ነው። ዛሬ ደግሞ ዐረብኛ ለሚሊዮኖች የእንጀራ ሰበብም ሆኗል። ስለዚህ ከራሳችን አልፎ ልጆቻችንም እንዲማሩት ትኩረት ብንሰጥ መልካም ነው። = የቴሌግራም ቻናል፡- https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
الشيخ صالح بن فوزان الفوزان «اشْتَرَطَ الفُقَهَاءُ فِي الزَّوْجِ أَنْ يَكُونَ كُفْءاً، وَمِنَ الكَفَاءَةِ القُدْرَةُ عَلَى النَّفَقَةِ وَقِيَامُهُ بِأَمْرِ بَيْتِهِ. فَالْمُتَطَفِّلُ الَّذِي يَعِيشُ عَلَى نَفَقَةِ زَوْجَتِهِ أَوْ أَهْلِهِ بِلاَ عُذْرٍ لَيْسَ بِكُفْءٍ لِلْمَرْأَةِ الصَّالِحَةِ.» ሸይኽ ሷሊሕ ቢን ፈውዛን አል-ፈውዛን (ሐፊዞሁሏህ) «የፊቅህ ሊቃውንት (ፉቀሃዎች) በትዳር አጋር ላይ ብቁ መሆንን መስፈርት አድርገዋል። ከብቃት መካከል ደግሞ ወጪ ማውጣት መቻሉ ና የቤቱን ነገር ማስተካከል መቻሉ ነው። ያለ ምንም ምክንያት በባለቤቱ ወይም በቤተሰቦቹ ወጪ ላይ ጥገኛ ሆኖ የሚኖር ወንድ ለደግ ና አሏህን ለምትፈራ ሴት ብቁ አይደለም።» ምንጭ፦ [አል-ሙንተቃ ሚን ፈታዋ አል-ፈውዛን 3/225] ========> የዛሬ ወንድ እንኳን ወንድ ሊሆን ሚስቱን ዐረብ ሀገር ልኮ እሱ እማንም በረንዳ ቅጠሉን ይበላል!! ----------------------------------------------- ===በጥቅሉ አሏህን የሚፈራ የተቅዋ ባለቤት መሆን አለበት እህት ዝም ተብሎ ድምፁ አማረኝ፡ቆንጆ ነው፡ሀብታም ነው፡የተማረ ዶክተር ነው፡ሸይኽ ነው ፡ኡዝታዝ ነው وووووووووووووووو አይሰራምምም!! ኢማም አል-ሀሰን አል-በስሪይ ረሂመሁሏሁ እንድህ ይላሉ «زَوِّجْهَا مَنْ يَتَّقِي اللَّهَ؛ فَإِنْ أَحَبَّهَا أَكْرَمَهَا، وَإِنْ أَبْغَضَهَا لَمْ يَظْلِمْهَا» («ልጅህን አሏህን የሚፈራ ሰውን አጋባት፤ ቢወዳት ያከብራታል፣ ቢጠላት እንኳ አይበድላትም») — [አል-ዒያል ሊ-ኢብኒ አቢ አድ-ዱንያ] እህቴ እነዚህን ከላይ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ከአሟላልሽ فَتَوَكَّلِي عَلَى اللَّهِ فَتَزَوَّجي. በአሏህ ላይ ተመኪና አግቢው!!- ================== አቡ ዐብዲላህ Yasin mohammed 3/12/2018 --------------------------------------- https://t.me/durusuAqidetileslamiya
ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ቢን ባዝ (ረሂመሁሏሁ) «ወላጆችን ማመፅ (ሐቃቸውን አለመጠበቅ) ከታላላቅ ወንጀሎች (ከከባኢር) አንዱ ነው፤ መጥፎ ሥነ-ምግባር ደግሞ ከሰውየው ያሸሻል። ወላጆቹን የሚያምፅ ና መጥፎ ሥነ-ምግባር ያለው ወንድን ወላጅ/አስተዳዳሪ ልጁን ሊያጋባው አይገባም። ምክንያቱም ለመልካም ውለታቸው እጅግ ባለሐቅ ለሆኑት ወላጆቹ መልካም ያልሆነ ሰው፣ ለሚስቱ በፍፁም መልካም ሊሆን አይችልምና።» ምንጭ፦ [መጅሙዑ ፈታዋ ቢን ባዝ: 21/140] الشيخ محمد بن صالح العثيمين «عَاقُّ الْوَالِدَيْنِ سَيِّئُ الْخُلُقِ لاَ تُكْفَلُ السَّعَادَةُ مَعَهُ. وَالْمَرْأَةُ إِذَا تَزَوَّجَتْ بِمَنْ لاَ يُرَاعِي حَقَّ وَالِدَيْهِ وَلاَ يَحْسُنُ خُلُقُهُ، فَإِنَّهَا سَتَعِيشُ فِي نَكَدٍ وَعَذَابٍ. فَالنَّصِيحَةُ بِعَدَمِ الْقَبُولِ بِهِ حَتَّى يَتُوبَ وَيَصْلُحَ.» ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን «ወላጆቹን የሚያምፅና መጥፎ ሥነ-ምግባሩ ያለው ሰው ጋር የትዳር ደስታ ሊረጋገጥ አይችልም። ሴት ልጅ የወላጆቹን ሐቅ የማይጠብቅ ና አኽላቁ የወደቀን ወንድ ካገባች፣ በችግር ና በመከራ ውስጥ ነው የምትኖረው። ስለዚህ እስከ ሚቶብት ና እስኪስተካከል ድረስ እርሱን አለመቀበል ይመከራል።» ምንጭ፦ [አል-ሊቃኡል ሸህሪይ: 67] الشيخ صالح بن فوزان الفوزان «اشْتَرَطَ النَّبِيُّ ﷺ فِي الْخَاطِبِ أَنْ يَكُونَ مَرْضِيَّ الدِّينِ وَالْخُلُقِ. فَمَنْ كَانَ سَيِّئَ الْخُلُقِ أَوْ عَاقًّا لِوَالِدَيْهِ فَلَيْسَ بِمَرْضِيِّ الدِّينِ وَلاَ الْخُلُقِ، فَلَا يُزَوَّجُ.» ሸይኽ ሷሊሕ ቢን ፈውዛን አል-ፈውዛን (ሐፊዞሁሏህ) «ነቢዩ (ﷺ) ለትዳር በሚመጣው ሰው ላይ ሃይማኖቱ ና ሥነ-ምግባሩ የተወደደ መሆን አለበት ሲሉ መስፈርት አስቀምጠዋል። ስለዚህ መጥፎ ሥነ-ምግባር ያለው ወይም ወላጆቹን የሚያምፅ ሰው ሃይማኖቱም ሆነ አኽላቁ የተወደደ ስላልሆነ ማጋባት የለበትም።» ምንጭ፦ [አል-ሙንተቃ ሚን ፈታዋ አል-ፉውዛን: 3/212] 5ኛ ==>ወንድነት እና ኃላፊነት መሸከም (الرَّجُولَةُ وَتَحَمُّلُ الْمَسْؤُولِيَّةِ) هَلْ هُوَ مُتَحَمِّلٌ لِلْمَسْؤُولِيَّةِ وَكُفْءٌ، وَلَيْسَ مُتَطَفِّلًا وَعَالَةً عَلَى غَيْرِهِ؟ ኃላፊነቱን የሚወጣ(ሀላፊነት መሸከም የሚችል)፣ ብቁ ና በራሱ የሚቆም ነውን? ወይስ በሰው ላይ ጥገኛ ና ጥገኝነትን የሚፈልግ ነውን? الرِّجَالُ قَوَّامُونَ عَلَى النِّسَاءِ بِمَا فَضَّلَ اللَّهُ بَعْضَهُمْ عَلَىٰ بَعْضٍ وَبِمَا أَنفَقُوا مِنْ أَمْوَالِهِمْ ۚ فَالصَّالِحَاتُ قَانِتَاتٌ حَافِظَاتٌ لِّلْغَيْبِ بِمَا حَفِظَ اللَّهُ ۚ وَاللَّاتِي تَخَافُونَ نُشُوزَهُنَّ فَعِظُوهُنَّ وَاهْجُرُوهُنَّ فِي الْمَضَاجِعِ وَاضْرِبُوهُنَّ ۖ فَإِنْ أَطَعْنَكُمْ فَلَا تَبْغُوا عَلَيْهِنَّ سَبِيلًا ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ عَلِيًّا كَبِيرًا ወንዶች በሴቶች ላይ ቋሚዎች (አሳዳሪዎች) ናቸው፡፡ አሏህ ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ በማብለጡና (ወንዶች) ከገንዘቦቻቸው (ለሴቶች) በመስጠታቸው ነው፡፡ መልካሞቹም ሴቶች (ለባሎቻቸው) ታዛዦች አሏህ ባስጠበቀው ነገር ሩቅን ጠባቂዎች ናቸው፡፡ እነዚያንም ማመፃቸውን የምትፈሩትን ገስፁአቸው፡፡ በመኝታዎችም ተለዩዋቸው፡፡ (ሳካ ሳታደርሱ) ምቱዋቸውም፡፡ ቢታዘዟችሁም (ለመጨቆን) በእነርሱ ላይ መንገድን አትፈልጉ፤ አሏህ የበላይ ታላቅ ነውና፡፡4፣34 ኢብኑ ቀይም አል-ጀውዚይ እንድህ ይላሉ «الرَّجُولَةُ لَيْسَتْ بِالشَّكْلِ وَلاَ بِالْقُوَّةِ الْبَدَنِيَّةِ، وَإِنَّمَا هِيَ بِقُوَّةِ الدِّينِ وَتَحَمُّلِ الْمَسْؤُولِيَّةِ وَالْقِيَامِ بِالْوَاجِبَاتِ» («ወንድነት በቅርፅ ወይም በኣካል ጥንካሬ አይደለም፤ ይልቁንም በሃይማኖት ጥንካሬ፣ ኃላፊነትን በመሸከም ና ግዴታዎችን በመወጣት ነው») الشيخ عبد العزيز بن باز «الرَّجُلُ هُوَ القَوَّامُ عَلَى أَهْلِهِ، وَمِنْ شَرْطِ القَوَامَةِ القُدْرَةُ عَلَى النَّفَقَةِ وَتَحَمُّلِ المَسْؤُولِيَّةِ. فَالَّذِي لاَ يَعْمَلُ كَسَلاً، وَيَعِيشُ عَالَةً عَلَى غَيْرِهِ، أَوْ لاَ يَقُومُ بِمَسْؤُولِيَّاتِ الزَّوَاجِ، لاَ يَنْبَغِي لِلْوَلِيِّ أَنْ يُزَوِّجَهُ؛ لِأَنَّهُ سَيُضَيِّعُ أَهْلَهُ.» ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ቢን ባዝ (ረሂመሁሏሁ) «ወንድ በቤተሰቡ ላይ አስተዳዳሪ (ቀዋም) ነው፤ ከአስተዳዳሪነት መስፈርቶች መካከል ደግሞ ለቤተሰብ ወጪ የማውጣት (ነፈቃ የመስጠት) እና ኃላፊነት የመሸከም ብቃት አንዱ ነው። በሰነፍነቱ ምክንያት የማይሰራ፣ በሰው ላይ ጥገኛ ሆኖ የሚኖር፣ ወይም የትዳርን ኃላፊነት የማይወጣን ወንድ ወላጅ/አስተዳዳሪ ልጁን ሊያጋባው አይገባም፤ ምክንያቱም ቤተሰቡን ያጠፋልና።» ምንጭ፦ [መጅሙዑ ፈታዋ ቢን ባዝ: 21/148] الشيخ محمد بن صالح العثيمين «الرَّجُولَةُ لَيْسَتْ مُجَرَّدَ ذُكُورَةٍ، بَلْ هِيَ حَمْلٌ لِلْمَسْؤُولِيَّةِ وَقِيَامٌ بِالْوَاجِبَاتِ. وَالرَّجُلُ الَّذِي لاَ يَعْتَمِدُ عَلَى نَفْسِهِ وَلاَ يَقْدِرُ عَلَى الإنْفَاقِ وَالرِّعَايَةِ لاَ تَحْصُلُ مَعَهُ المَقَاصِدُ الشَّرْعِيَّةُ مِنَ النِّكَاحِ، فَالنَّصِيحَةُ عَدَمُ التَّزْوِيجِ بِهِ.» ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን «ወንድነት ማለት ወንድ ሆኖ መወለድ ብቻ አይደለም፤ ይልቁንም ኃላፊነትን መሸከም እና ግዴታዎችን መወጣት ነው። በራሱ የማይቆም፣ ወጪ ማውጣት ና ቤተሰብን መንከባከብ የማይችል ወንድ ጋር ህጋዊው የጋብቻ ዓላማ አይሳካም። ስለዚህ እርሱን አለማጋባት ይመከራል።» ምንጭ፦ [አል-ሊቃኡል ሸህሪይ: 72]
الشيخ صالح بن فوزان الفوزان «مَنْ فَسَدَتْ عَقِيدَتُهُ لَمْ تُقْبَلْ أَعْمَالُهُ، وَلَا يَجُوزُ تَزْوِيجُهُ بِالْمُسْلِمَاتِ الصَّالِحَاتِ. لِأَنَّ الصَّلَاحَ يَبْدَأُ مِنْ صَلَاحِ الْعَقِيدَةِ، وَالْعَقِيدَةُ هِيَ الأَسَاسُ.» ሸይኽ ሷሊሕ ቢን ፈውዛን አል-ፈውዛን (ሐፊዘሁሏህ) «ዐቂዳው የተበላሸ ሰው ሥራዎቹ አሏህ ዘንድ ተቀባይነት የላቸውም፤ ለደግ ና ለታዛዥ ሙስሊም ሴቶችም ማጋባት አይፈቀድም። ምክንያቱም ደግነት ና መልካምነት የሚጀምረው ከዐቂዳ መስተካከል ሲሆን፣ ዐቂዳ ደግሞ መሠረት ነው።» ምንጭ፦ [አል-ሙንተቃ ሚን ፈታዋ አል-ፈውዛን: 3/221] 3ኛ===> ሶላት (الصَّلَاةُ) هَلْ يُحَافِظُ عَلَى الصَّلَوَاتِ الْخَمْسِ فِي جَمَاعَةٍ مَعَ الْمُسْلِمِينَ؟ የአምስቱን ወቅት ሶላቶች በጀማዐ (በህብረት) መስጊድ ውስጥ ይሰግዳልን? «صَلَاةُ الْجَمَاعَةِ تَفْضُلُ صَلَاةَ الْفَذِّ بِسَبْعٍ وَعِشْرِينَ دَرَجَةً» "የጀመዓ ሶላት ከብቻ ሶላት በሃያ ሰባት (27) ደረጃዎች ይበልጣል።" (ቡኻሪና ሙስሊም ) «الْعَهْدُ الَّذِي بَيْنَنَا وَبَيْنَهُمُ الصَّلاَةُ، فَمَنْ تَرَكَهَا فَقَدْ كَفَرَ» «በእኛና በእነሱ (በሙናፊቆች/ካፊሮች) መካከል ያለው ቃል ኪዳን ሶላት ነው፤ እሷን የተወ በእርግጥ ካደ») — [ቲርሚዚ፡ 2621] عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ -رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ- أَنَّ أَعْمَى قَالَ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنَّهُ لَيْسَ لِي قَائِدٌ يَقُودُنِي إِلَى الْمَسْجِدِ، فَهَلْ لِي رُخْصَةٌ أَنْ أُصَلِّيَ فِي بَيْتِي؟ فَقَالَ: «هَلْ تَسْمَعُ النِّدَاءَ بِالصَّلَاةِ؟» قَالَ: نَعَمْ، قَالَ: «فَأَجِبْ». [رواه مسلم] ከአቡ ሁረይራ (ረድየሏሁ ዐንሁ) እንደተወራው አንድ ዓይነ ስውር ወደ ነቢዩ (ﷺ) መጥቶ፦ “ያ ረሱለሏህ! ወደ መስጂድ የሚመራኝ መሪ የለኝም፤ በቤቴ እስገድ ዘንድ ፈቃድ አለኝን?” አላቸው። እሳቸውም፦ “የሶላት አዛን ትሰማለህን?” አሉት። እርሱም፦ “አዎ” አለ። እሳቸውም፦ “እንግዲያውስ ጥሪውን ተቀበል (ወደ መስጂድ ሂድ)” አሉት። [ሙስሊም ዘግበውታል] =====> መሪ ለሌለው ዓይነ ስውር እንኳ በቤቱ እንዲሰግድ ፈቃድ ካልተሰጠው፣ ጤነኛ ና ዓይኑ የሚያይ ወንድ በቤቱ መስገዱ በፍፅም አይፈቀድለትም። ዑመር ኢብኑል ኸጧብ - ረድየሏሁ ዐንሁ): ለአሚሮቹ በፃፉት ደብዳቤ ላይ እንዲህ ብለዋል፦ «إِنَّ أَهَمَّ أُمُورِكُمْ عِنْدِي الصَّلاَةُ، مَنْ حَفِظَهَا وَحَافَظَ عَلَيْهَا حَفِظَ دِينَهُ، وَمَنْ ضَيَّعَهَا فَهُوَ لِمَا سِوَاهَا أَضْيَعُ» («እኔ ዘንድ ከነገሮቻችሁ ሁሉ ዋናው ነገር ሶላት ነው፤ እሷን የጠበቀና የተንከባከበ ሃይማኖቱን ጠበቀ፤ እሷን ያጠፋ(ያጓደላት) ደግሞ ከእሷ ውጭ ላሉት ነገሮች እጅግ በጣም አጉዳይ ነው») — [ሙወጦእ ሊኢማሚ ማሊክ] الشيخ عبد العزيز بن باز «صَلَاةُ الْجَمَاعَةِ فِي الْمَسَاجِدِ وَاجِبَةٌ عَلَى الرِّجَالِ. وَالَّذِي يَتْرُكُ صَلَاةَ الْجَمَاعَةِ وَيُصَلِّي فِي بَيْتِهِ قَدْ عَصَى اللَّهَ وَرَسُولَهُ، وَتَشَبَّهَ بِالْمُنَافِقِينَ. فَلَا يَنْبَغِي وَلَا يَجُوزُ لِلْوَلِيِّ أَنْ يُزَوِّجَهُ، وَلَا لِلْمَرْأَةِ أَنْ تَرْضَى بِهِ؛ لِأَنَّ مَنْ ضَيَّعَ حَقَّ اللَّهِ فَهُوَ لِحَقِّ زَوْجَتِهِ أَضْيَعُ.» ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ቢን ባዝ (ረሒመሁሏህ) «የጀመዓ ሶላትን በመስጂድ መስገድ በወንዶች ላይ ግዴታ (ዋጅብ) ነው። የጀመዓ ሶላትን ትቶ በቤቱ የሚሰግድ ሰው አሏህን ና መልእክተኛውን አምፇል፤ ከሙናፊቆች ጋርም ተመሳስሏል። ስለዚህ ወላጅ/አስተዳዳሪ (ወሊይ) ልጁን ለእርሱ ሊያጋባው አይገባም (አይፈቀድለትም)፤ ሴቷም እሺ ብላ ልትቀበለው አይገባም። ምክንያቱም የአሏህን ሐቅ (መብት) ያጠፋ ሰው የባለቤቱን (የሚስቱን) ሐቅ ይበልጥ አጥፊ ነውና።» ምንጭ፦ [መጅሙዑ ፈታዋ ቢን ባዝ: 21/133] الشيخ محمد بن صالح العثيمين «تَرْكُ صَلَاةِ الْجَمَاعَةِ كَبِيرَةٌ مِنْ كَبَائِرِ الذُّنُوبِ، وَالَّذِي يُصَلِّي فِي بَيْتِهِ بِلاَ عُذْرٍ فَهُوَ فَاسِقٌ. وَالْفَاسِقُ لاَ يَنْبَغِي أَنْ يُزَوَّجَ لِلْمَرْأَةِ الصَّالِحَةِ؛ لِأَنَّهُ لاَ يُؤْمَنُ عَلَيْهَا فِي دِينِهَا وَخُلُقِهَا.» ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁሏህ) «ያለ ምንም ምክንያት (ዑዝር) የጀመዓ ሶላትን መተው ከታላላቅ ወንጀሎች (ከከባኢር) አንዱ ነው፤ ያለ ምክንያት በቤቱ የሚሰግድ ሰው ፋሲቅ ነው። ፋሲቅ የሆነን ወንድ ደግሞ ለደግ ና አሏህን ለምትፈራ ሙስሊም ሴት ማጋባት አይገባም፤ ምክንያቱም በሃይማኖቷ ና በሥነ-ምግባሯ ላይ አይታመንምና።» ምንጭ፦ [ፈታዋ ኑሩን ዐለድ-ደርብ: 10/182] 4ኛ ===>መልካም ስነ-ምግባር እና የወላጆች ሐቅ (الأَخْلَاقُ وَبِرُّ الْوَالِدَيْنِ) كَيْفَ تَعَامُلُهُ مَعَ أَبِيهِ وَأُمِّهِ؟ وَهَلْ هُوَ كَرِيمٌ وَسَخِيٌّ وَأَخْلَاقُهُ عَالِيَةٌ؟ ከእናቱና ከአባቱ ጋር ያለው ግንኙነት እንዴት ነው? ለጋስ፣ ቸር ና መልካም ስነ-ምግባር ያለው ነውን? وَقَضَىٰ رَبُّكَ أَلَّا تَعْبُدُوا إِلَّا إِيَّاهُ وَبِالْوَالِدَيْنِ إِحْسَانًا («ጌታህም (እንዲህ ሲል) አዘዘ፡- እርሱን እንጂ ሌላን አታመልኩ፤ በወላጆቻችሁም መልካምን ሥራ ሥሩ») — [ሱረቱ አል-ኢስራእ፡ 23] «خَيْرُكُمْ خَيْرُكُمْ لأَهْلِهِ وَأَنَا خَيْرُكُمْ لأَهْلِي» («ከእናንተ ውስጥ በላጩ ለቤተሰቡ (ለእናት፡ለአባት፡ለሚስቱ፡ለልጆቹ) መልካም የሆነው ነው፤ እኔ ደግሞ ከእናንተ ይበልጥ ለቤተሰቤ መልካም ነኝ») — [ቲርሚዚ፡ 3895] الشيخ عبد العزيز بن باز «عُقُوقُ الْوَالِدَيْنِ مِنْ كَبَائِرِ الذُّنُوبِ، وَسُوءُ الْخُلُقِ يُنَفِّرُ مِنَ الرَّجُلِ. فَالَّذِي يَعُقُّ وَالِدَيْهِ وَسَيِّئُ الْخُلُقِ لاَ يَنْبَغِي لِلْوَلِيِّ أَنْ يُزَوِّجَهُ كَرِيمَتَهُ؛ لِأَنَّ مَنْ لَمْ يُحْسِنْ إِلَى وَالِدَيْهِ اللَّذَيْنِ هُمَا أَحَقُّ النَّاسِ بِبِرِّهِ، فَلَنْ يُحْسِنَ إِلَى زَوْجَتِهِ.»
ክፍል 3 ማንንንንንንን እናግባ? «لَا تَتَزَوَّجِي رَجُلًا قَبْلَ أَنْ يَجْتَازَ خَمْسَةَ اخْتِبَارَاتٍ؛ إِذَا أَرَدْتِ السَّعَادَةَ وَالرَّاحَةَ وَالْهَنَاءَ فِي حَيَاتِكِ الزَّوْجِيَّةِ: በትዳር ህይወትሽ ደስታንና እፎይታን ከፈለግሽ፣ ከመጋባትሽ በፊት አምስት ፈተናዎችን ማለፉን አረጋግጪ። 1===> ሃይማኖት (الدِّينُ) هَلْ هُوَ مُسْلِمٌ مُتَمَسِّكٌ بِأَرْكَانِ الْإِسْلَامِ وَبِشَرَائِعِ الدِّينِ الْقَوِيمِ؟ የኢስልምናን ማዕዘናት ና ህጎች በአግባቡ ጨብጦ የያዘ እና የሚተገብር ሙስሊም ነውን? وَلَا تَنكِحُوا الْمُشْرِكَاتِ حَتَّىٰ يُؤْمِنَّ ۚ وَلَأَمَةٌ مُّؤْمِنَةٌ خَيْرٌ مِّن مُّشْرِكَةٍ وَلَوْ أَعْجَبَتْكُمْ ۗ وَلَا تُنكِحُوا الْمُشْرِكِينَ حَتَّىٰ يُؤْمِنُوا ۚ وَلَعَبْدٌ مُّؤْمِنٌ خَيْرٌ مِّن مُّشْرِكٍ وَلَوْ أَعْجَبَكُمْ ۗ أُولَٰئِكَ يَدْعُونَ إِلَى النَّارِ ۖ وَاللَّهُ يَدْعُو إِلَى الْجَنَّةِ وَالْمَغْفِرَةِ بِإِذْنِهِ ۖ وَيُبَيِّنُ آيَاتِهِ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَذَكَّرُونَ (በአሏህ) አጋሪ የሆኑ ሴቶች እስከሚያምኑ ድረስ አታግቡዋቸው፡፡ ከአጋሪይቱ ምንም ብትደንቃችሁም እንኳ ያመነችው ባሪያ በእርግጥ በላጭ ናት፡፡ ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው፡፡ ከአጋሪው ምንም ቢደንቃችሁ ምእምኑ ባሪያ በላጭ ነው፡፡ እነዚያ (አጋሪዎች) ወደ እሳት ይጣራሉ፡፡ አሏህም በፈቃዱ ወደ ገነትና ወደ ምሕረት ይጠራል፡፡ ሕግጋቱንም ለሰዎች ይገልፃል እነርሱ ሊገሰፁ ይከጀላልና፡፡ «إِذَا خَطَبَ إِلَيْكُمْ مَنْ تَرْضَوْنَ دِينَهُ وَخُلُقَهُ فَزَوِّجُوهُ، إِلاَّ تَفْعَلُوا تَكُنْ فِتْنَةٌ فِي الأَرْضِ وَفَسَادٌ عَرِيضٌ»(«ሃይማኖቱንና ሥነ-ምግባሩን የምትወዱለት ሰው (ሴት ልጅችሁን/እህታችሁን) ሊያገባ ቢጠይቃችሁ አጋቡት፤ ይህንን ካላደረጋችሁ በምድር ላይ ፈተና ና ትልቅ ጥፋት ይሆናል») — [ቲርሚዚ፡ 1084] 2ኛ===> ዐቂዳ ና መንሃጅ (العَقِيدَةُ وَالْمَنْهَجُ) هَلْ عنده صَافِي الْعَقِيدَةِ وَالْمَنْهَجِ، مُتَمَسِّكٌ بِكِتَابِ اللَّهِ وَسُنَّةِ رَسُولِ اللَّهِ - صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ - عَلَى فَهْمِ سَلَفِ هَذِهِ الْأُمَّةِ؟ ዐቂዳው (እምነቱ) የጠራ ነውን፣ የአሏህን መፅሐፍ (ቁርአንን) እና የነብዩን (ﷺ) ሱና (ሀድስን) በዚህ ኡማ ቀደምት ደጋግ አበው (ሰለፎች) ግንዛቤ ላይ የጨበጠ (የያዘ) ነውን? አሏህ እንድህ ይላል فَإِنْ آمَنُوا بِمِثْلِ مَا آمَنتُم بِهِ فَقَدِ اهْتَدَوا ۖ وَّإِن تَوَلَّوْا فَإِنَّمَا هُمْ فِي شِقَاقٍ ۖ فَسَيَكْفِيكَهُمُ اللَّهُ ۚ وَهُوَ السَّمِيعُ الْعَلِيمُ ። በርሱ ባመናችሁበት ብጤ ቢያምኑ በእርግጥ ተመሩ፡፡ ቢዞሩም እነርሱ በጭቅጭቅ ውስጥ ብቻ ናቸው፡፡ እነርሱንም አሏህ ይበቃሃል፤ እርሱም ሰሚው ዐዋቂው ነው፡፡2፣137 ታላቁ ታቢዒይ አርዋህ ቢን አዝ-ዙበይር (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦ «الإِنْكاحُ عُبُودِيَّةٌ، فَلْيَنْظُرْ أَحَدُكُمْ أَيْنَ يَضَعُ كَرِيمَتَهُ» ««ሴት ልጅን ማጋባት ማለት አሳልፎ መስጠት(ማስረከብ) ማለት ነው፤ ስለዚህ ከእናንተ አንዳችሁ የተከበረችውን (ልጁን ወይም እህቱን) ለማን እንደሚሰጣት ና የት እንደሚያስቀምጣት በጥንቃቄ ይመልከት!» ስለሆነም፡ አንዲት ሴት የትዳር አጋር ስትመርጥ የገንዘቡን፣ የቁመናውን ወይም የሥራውን ደረጃ ከመመልከት በፊት ትክክለኛ ተውሂድ፡ ዐቂዳ ያለው፣ በሱና የሚመራና ሰለፊያዊ መንሃጅን የሚከተል መሆኑን ማረጋገጥ ሃይማኖቷን ለመጠበቅ ዋናው መስፈርት ነው። የትዳር ዓላማ የዱንያ ደስታ ብቻ ሳይሆን አብሮ ወደ ጀነት መጓዝ ነው። ዐቂዳው የተበላሸ ሰው ደግሞ መጨረሻው አደጋ ላይ ስለሆነ ለሚስቱም ሆነ ለቤተሰቡ የጀነት መንገድ መሪ መሆን አይችልም።ይልቁንም እሷንም ልጆቿንም ሊያጠማቸው ይችላል!! الشيخ عبد العزيز بن باز «لَا يَجُوزُ تَزْوِيجُ الْمُسْلِمَةِ لِلْكَافِرِ وَلَا لِمَنْ لَدَيْهِ عَقِيدَةٌ شِرْكِيَّةٌ؛ كَالَّذِينَ يَسْتَغِيثُونَ بِالأَمْوَاتِ وَيَدْعُونَهُمْ مِنْ دُونِ اللَّهِ. وَكَذَلِكَ تَرْكُ الصَّلَاةِ كُفْرٌ، فَلَا يُزَوَّجُ مَنْ لَا يُصَلِّي. وَالْوَاجِبُ عَلَى أَوْلِيَاءِ الأُمُورِ التَّثَبُّتُ فِي عَقِيدَةِ الْخَاطِبِ.» ሸይኽ ዐብዱልዐዚዝ ቢን ባዝ (ረሒመሁሏሁ) «ሙስሊም ሴትን ለካፊርም ሆነ ከአሏህ ውጭ ያሉ ሙታንን እንደሚጠሩት ና እንደሚማፀኑት ዓይነት የሽርክ ዐቂዳ ላለው ሰው ማጋባት አይፈቀድም። እንዲሁም ሶላትን መተው ኩፍር (ከእስልምና የሚያስወጣ) ስለሆነ ሶላት የማይሰግድን ሰው ማጋባት አይቻልም። የወሊዮች (የአስተዳዳሪዎች) ግዴታ ለትዳር የሚመጣውን ሰው ዐቂዳ ማረጋገጥ ነው።» ምንጭ፦ [መጅሙዑ ፈታዋ ቢን ባዝ: 21/118] الشيخ محمد بن صالح العثيمين «إِذَا كَانَ الرَّجُلُ مُبْتَدِعًا بِدْعَةً مُكَفِّرَةً، فَإِنَّ النِّكَاحَ بَاطِلٌ وَلَا يَصِحُّ؛ لِأَنَّهُ كَافِرٌ. وَإِنْ كَانَتْ بِدْعَتُهُ غَيْرَ مُكَفِّرَةٍ، فَالْأَوْلَى بَلِ الْوَاجِبُ عَدَمُ تَزْوِيجِهِ؛ لِمَا فِي ذَلِكَ مِنَ الْخَطَرِ عَلَى دِينِ الْمَرْأَةِ وَذُرِّيَّتِهَا.» ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁሏህ) «ሰውየው ከእስልምና የሚያስወጣ (ኩፍር የሆነ) ቢድዓ ና የተበላሸ ዐቂዳ ካለው ጋብቻው ባጢል (ውድቅ) ነው፤ አይበቃምም፤ ምክንያቱም እርሱ ካፊር በመሆኑ ነው። ቢድዓው ከእስልምና የማያስወጣ ከሆነ በላጩ እድያውም ግደታው እርሱን አለማጋባት ነው፤ ምክንያቱም በሴቲቱ ና በሚወለዱት ልጅች ሃይማኖት ላይ ትልቅ አደጋ ስላለው።» ምንጭ፦ [አል-ሊቃኡል ሸህሪይ: 58]
أَلا يَا نَفْسُ وَيْحَكِ فَاسْتَقِيمِي أَمَا تَرْجِينَ جَنَّاتِ النَّعِيمِ؟ وَتُوبِي.. تُوبِي، إِنَّ يَوْمَ الْفَصْلِ آتٍ فَلا يُغْنِي حَمِيمٌ عَنْ حَمِيمِ وَمَا هَذِهِ الْحَيَاةُ سِوَى مَتَاعٍ وَلَيْسَ الْعَبْدُ فِيهَا بِالْمُقِيمِ غَفَلْتِ.. غَفَلْتِ، وَكُنْتِ فِي لَعِبٍ وَلَهْوٍ وَمِلْتِ عَنِ الصِّرَاطِ الْمُسْتَقِيمِ አዋጅ! ነፍሴ ሆይ! ወዮልሽ.. ቀጥ በይ (ተስተካከይ)፤ የ ፀጋ ገነቶችን አትመኚምን? ተመለሺ.. (ወደ አሏህ) ተውበት አድርጊ! የቂያማ ቀን ይመጣል፤ በዚያ ቀን ቅርብ ወዳጅ ለቅርብ ወዳጁ ምንም አይጠቅምም። ይህች ህይወት ጊዜያዊ መጣቀሚያ እንጂ ሌላ አይደለችም፤ ባሪያ በውስጧ ቋሚና ዘውታሪ ኗሪ አይደለም። ዘነጋሽ.. ዘነጋሽ! በጨዋታ ና በከንቱ መዝናናት ውስጥ ነበርሽ፤ ቀጥተኛ ከሆነውም መንገድ (ሲራጥ) አዘነበልሽ። ﴿وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْكِتَابِ آمَنُوا وَاتَّقَوْا لَكَفَّرْنَا عَنْهُمْ سَيِّئَاتِهِمْ وَلَأَدْخَلْنَاهُمْ جَنَّاتِ النَّعِيمِ﴾ ﴿إِنَّ الَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ يَهْدِيهِمْ رَبُّهُم بِإِيمَانِهِمْ ۖ تَجْرِي مِن تَحْتِهِمُ الْأَنْهَارُ فِي جَنَّاتِ النَّعِيمِ﴾ ----------------------------------------------------- አቡ ዐብዲላህ ያሲን ሙሐመድ 30/11/2018
تَزَوَّجْ إِنَّمَا العُزَّابُ مَوْتَى فَلَا تَكُ مَيِّتًا قَبْلَ المَمَاتِ وَعَجِّلْ فِي الزَّوَاجِ فَفِيهِ رُوحٌ لِحَيٍّ لَمْ يَذُقْ طَعْمَ الحَيَاةِ فَسُنَّةُ خَيْرِ خَلْقِ اللَّهِ أَهْدَى لِمَنْ يَبْغِي اعْتِنَاقَ المَكْرُمَاتِ وَلَنْ تَلْقَى السَّكِينَةَ دُونَ زَوْجٍ سَتَبْقَى فِي ضَيَاعٍ أَوْ شَتَاتِ فَإِنْ لَمْ تَسْتَطِعْ لِضِيقِ حَالٍ فَتَقْوَى اللَّهِ مِفْتَاحُ الهِبَاتِ فَلَا تَيْأَسْ وَعِشْ حُرًّا عَفِيفًا فَعِفَّتُكَ السَّبِيلُ إِلَى النَّجَاةِ አግባ! ያላገቡ (ላጤዎች) ሙታን ናቸውና፤ ከመሞትህ በፊት የሞትክ አትሁን! በጋብቻ ላይ ፍጠን፤ በእርሱ ውስጥ ህይወት አለና፣ የህይወትን ጣዕም ላልቀመሰው በህይወት ላለ ሰው! ከፍጥረታት ሁሉ በላጭ የሆኑት (የነቢዩ ﷺ) ሱና እጅግ በጣም ቅን መሪ ነው፤ የተከበሩና መልካም ነገሮችን መላበስ ለሚፈልግ ሰው። ያለ ትዳር ሰላምና እርካታን አታገኝም፤ በመበታተንና በመጠፋፋት ውስጥ ትኖራለህ። በችግር ምክንያት(ማግባት) ካልቻልክ ደግሞ አሏህን መፍራት (ተቅዋ) የስጦታዎች ሁሉ ቁልፍ መክፈቻ ነው! ተስፋ አትቁረጥ! ነፃና እራስህን የጠበቅክ (ዐፊፍ) ሆነህ ኑር፤ እራስን መጠበቅህ ለመዳን ትክክለኛው መንገድ ነውና! https://t.me/durusuAqidetileslamiya
يَا أَخِي، إِذَا رَأَيْتَنِي عَلَى مَعْصِيَةٍ أَوْ غَيْرِ حَقٍّ، فَانْصَحْنِي وَأَرْشِدْنِي، وَلَا تَخْشَ مُضَايَقَتِي! أَضِيقُ يَوْمًا فِي الدُّنْيَا، وَلَا أَضِيقُ دَهْرًا مِنْ نَارِ الآخِرَةِ! وَإِلَّا بِمَاذَا تَكُونُ أَخِي؟!» «ወንድሜ ሆይ! በኃጢአት/በጥፋት ወይም ከዕውነት ውጭ በሆነ መንገድ ላይ ካየኸኝ፣ ምከርኝ፣ ምራኝም፤ መከፋቴንም (መበሳጨቴን) አትፍራ! በዱንያ (በዚች ዓለም) ላይ ለአንድ ቀን ብከፋ ይሻለኛል—ከአኺራ (ከወዲያኛው ዓለም) እሳት ለዘላለም ከመከፋት! ይህ ካልሆነማ በምን ምክንያት ነው ወንድሜ የምትሆነው?!» https://t.me/durusuAqidetileslamiya
قَالَ الحَسَنُ البَصْرِيُّ رَحِمَهُ اللهُ: «لَوْلَا العُلَمَاءُ لَصَارَ النَّاسُ مِثْلَ البَهَائِمِ» [مختصر نصيحة أهل العلم 167] አል-ሐሰን አል-በስሪ (ረሒመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፦ «ዑለሞች ባልኖሩ ኖሮ፣ ሰዎች እንደ እንስሳት በሆኑ ነበር።» -https://t.me/durusuAqidetileslamiya
«فِي كُلِّ مَرَّةٍ تَفْتَحُ هَذَا الجَوَّالَ لِلتَّوَاصُلِ، أُذَكِّرُ بِالآيَةِ الكَرِيمَةِ: {وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ} [المائدة: 2] فَاحْذَرْ أَنْ يَكُونَ مِنْكَ مِنْ خِلَالِ هَذَا الجِهَازِ أَيُّ شَيْءٍ فِي بَابِ التَّعَاوُنِ عَلَى الإِثْمِ وَالعُدْوَانِ، وَكُنْ حَرِيصًا أَشَدَّ الحِرْصِ عَلَى أَنْ تَكُونَ مِنْ خِلَالِهِ مِنَ المُمُتَعَاوِنِينَ عَلَى البرِّ وَالتَّقْوَى. فَهُوَ يُسْتَعْمَلُ فِي هَذَا وَفِي هَذَا، يُعِينُكَ عَلَى ذَلِكَ أَمْرٌ أُنَبِّهُكَ عَلَيْهِ، يَنْفَعُكَ اللَّهُ سُبْحَانَهُ وَتَعَالَى بِهِ: فِي كُلِّ مَرَّةٍ تَفْتَحُ فِيهَا هَذَا الجِهَازَ، تَذَكَّرْ أَنَّ مَا سَيَكُونُ فِيهِ جُزْءٌ مِنْ عَمَلِكَ الَّذِي يَسْأَلُكَ اللَّهُ عَنْهُ يَوْمَ القِيَامَةِ. هَذَا مُهِمٌّ جِدًّا.. جُزْءٌ مِنْ عَمَلِكَ الَّذِي يَسْأَلُكَ اللَّهُ عَنْهُ يَوْمَ القِيَامَةِ. كَثِيرٌ مِمَّنْ يَسْتَعْمِلُونَ الجَوَّالَ يُدَقِّقُونَ فِي اسْتِعْمَالِهِ خَوْفًا مِنَ الفَاتُورَةِ وَالرَّصِيدِ وَنَفَاذِهِ، فَيَضْبِطُ نَفْسَهُ مُرَاعَاةً لِهَذَا! وَمُرَاعَاةُ الحِسَابِ يَوْمَ القِيَامَةِ مِنْ بَابِ أَوْلَى. هَذَا التَّدْقِيقُ الَّذِي يَكُونُ فِي الجِهَازِ مِنْ أَجْلِ رِعَايَةِ الرَّصِيدِ.. التَّدْقِيقُ فِيهِ مِنْ أَجْلِ رِعَايَةِ رَصِيدِ الحَسَنَاتِ أَوْ السَّيِّئَاتِ -وَالعِيَاذُ بِاللَّهِ- يَكُونُ مِنْ بَابِ أَوْلَى. وَلِهَذَا فِي كُلِّ مَرَّةٍ تُسْتَخْدَمُ هَذَا الجِهَازَ، يَنْبَغِي أَنْ تَحْرِصَ عَلَى هَذِهِ الوَصِيَّةِ العَظِيمَةِ لِابْنِ القَيِّمِ -رَحِمَهُ اللَّهُ تَعَالَى- فِي مَعْنَى قَوْلِهِ تَعَالَى: {وَتَعَاوَنُوا عَلَى الْبِرِّ وَالتَّقْوَىٰ وَلَا تَعَاوَنُوا عَلَى الْإِثْمِ وَالْعُدْوَانِ}. سُبْحَانَ اللَّهِ، مِنْ خِلَالِ الأَجْهِزَةِ أَصْبَحَ الأَمْرُ فِي غَايَةِ الخُطُورَةِ مِنْ حَيْثُ التَّأْثِيرِ فِي الخَيْرِ أَوْ التَّأْثِيرِ فِي الشَّرِّ. الآنَ الفَائِدَةُ الطَّيِّبَةُ عِنْدَمَا تَنْشُرُهَا مِنْ خِلَالِ هَذِهِ الوَسَائِلِ، تَجِدُهَا فِي اللَّحْظَةِ الوَاحِدَةِ الَّتِي وَضَعْتَهَا فِي جِهَازِكَ وَضَغَطْتَ عَلَيْهَا زِرًّا وَاحِدًا، وَصَلَتْ إِلَى آَفَاقِ الدُّنْيَا وَأَطْرَافِ الأَرْضِ! وَمِثْلُ ذَلِكَ فِي الشَّرِّ الَّذِي قَدْ يَضَعُهُ الإِنْسَانُ! قَدِيمًا كَانَ الوَاحِدُ إِنْ تَكَلَّمَ بِكَلِمَةٍ طَيِّبَةٍ سَمِعَهَا مَنْ حَوْلَهُ، بِالكَادِ أَنْ تَصِلَ إِلَى بُلْدَانٍ بَعِيدَةٍ، لَكِنِ الآنَ فِي اللَّحْظَةِ نَفْسِهَا تَصِلُ الدُّنْيَا كُلَّهَا! فَإِذَا كَانَتْ تَصِلُ إِلَى هَذَا الخَلْقِ، احْذَرْ أَنْ يَصِلَ إِلَيْهِمْ مِنْ طَرَفِكَ شَرًّا، لَا ابْتِدَاءً وَلَا تَسَبُّبًا! انْتَبِهْ: ابْتِدَاءً أَنْ تُنْشِئَ كَلَامًا أَنْتَ تَكْتُبُهُ أَوْ تَقُولُهُ بِلِسَانِكَ ثُمَّ تُرْسِلُهُ إِلَى النَّاسِ، وَلَا تَسَبُّبًا مِنْ خِلَالِ الرَّسَائِلِ الَّتِي تَأْتِيكَ وَيُقَالُ لَكَ: (انْشُرْ)، لَا تَنْشُرْ إِلَّا مَا يَكُونُ عِنْدَكَ تَحَقُّقٌ. كَمْ مِنَ الأَحَادِيثِ المَوْضُوعَةِ تُنْشَرُ وَيُكْتَبُ تَحْتَهَا: (انْشُرْ تُؤْجَرْ)! وَكَمْ مِنَ التَّحْقِيقَاتِ الفَاسِدَةِ، وَالآَرَاءِ الكَاسِدَةِ، وَالأَقْوَالِ الضَّعِيفَةِ الَّتِي تُنْشَرُ مِنْ خِلَالِ هَذِهِ الأَجْهِزَةِ! فَلَا تَنْشُرْ شَيْئًا مِنْهَا، لَا ابْتِدَاءً وَلَا تَسَبُّبًا. وَاذْكُرْ أَنَّ مَا يَكُونُ فِي هَذَا الجِهَازِ كُلُّهُ مِنْ عَمَلِكَ الَّذِي سَتُحَاسَبُ عَلَيْهِ يَوْمَ القِيَامَةِ፤ سَوَاءً مَا كَتَبْتَهُ فِيهِ، أَوْ سَجَّلْتَهُ فِيهِ بِصَوْتِكَ، أَوْ نَظَرْتَ إِلَيْهِ بِعَيْنِكَ، أَوْ سَمِعْتَهُ بِأُذُنِكَ، أَوْ أَيِّ وَسِيلَةٍ كَانَتْ مِنْكَ مِنْ خِلَالِ هَذَا الجِهَازِ.. كُلُّ ذَلِكَ مِنْ عَمَلِكَ: {إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا} [الإسراء: 36]» — الشَّيْخُ عَبْدُ الرَّزَّاقِ البَدْرُ (حَفِظَهُ اللَّهُ)
видео или голосовое, без подписи
ኢምሬትስ(dubai) ውስጥ የምትገኙ እስቲ ምግብ ስራ ካለ ንገሩኝ አንድት እህት በጣም ተጨንቃለች ክፍያው ከአሏህ ነው ኮሚሽን እንዳትጠይቁ የኮሚሽን የላትም!! @Yasinmohammed1
! ፈጥኖ የመለስ ምርጥ ቻናል ይሸለማል •┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈• በኢስላም አንድ ወንድ ከቻለ እስከ ስንት ማግባት ይቻላል ?
صَلَّى عَلَيْكَ اللهُ يَا خَيْرَ الْوَرَى مَا حَنَّ مُشْتَاقًا إِلَيْكَ فُؤَادُ صَلُّوا عَلَيْهِ فَبِالصَّلَاةِ ذُنُوبُكُمْ تُنْحَى وَتُلْقَى عَنْكُمُ الْأَنْكَادُ الْإِمَامِ ابْنِ بَازٍ رَحِمَهُ اللهُ «فَأَهْلُ السُّنَّةِ يُؤْمِنُونَ بِأَنَّ الرَّسُولَ ﷺ أَحَبُّ إِلَيْهِمْ مِنْ كُلِّ شَيْءٍ بَعْدَ اللهِ. فَأَحَبُّ شَيْءٍ إِلَى أَهْلِ السُّنَّةِ اللهُ وَحْدَهُ جَلَّ وَعَلَا، ثُمَّ النَّبِيُّ ﷺ هُوَ أَحَبُّ النَّاسِ إِلَيْهِمْ، فَوْقَ مَحَبَّةِ النَّفْسِ وَالْمَالِ وَالْوَلَدِ، ثُمَّ الْأَنْبِيَاءُ بَعْدَهُ عَلَيْهِمُ الصَّلَاةُ وَالسَّلَامُ. وَنَحْنُ عَلَى ذَلِكَ، وَنَحْنُ عَلَى طَرِيقِهِمْ، نُشْهِدُ اللهَ أَنَّهُ أَحَبُّ إِلَيْنَا مِنْ كُلِّ شَيْءٍ بَعْدَ اللهِ، نُشْهِدُ اللهَ أَنَّهُ أَحَبُّ إِلَيْنَا مِنْ أَنْفُسِنَا وَأَمْوَالِنَا وَأَوْلَادِنَا وَكُلِّ شَيْءٍ. فَحُبُّ النَّبِيِّ ﷺ بِاتِّبَاعِهِ، وَالسَّيْرِ عَلَى مِنْهَاجِهِ، وَتَعْظِيمِ سُنَّتِهِ، وَالدَّعْوَةِ إِلَى ذَلِكَ، وَالذَّبِّ عَنْهَا، هَذَا هُوَ حُبُّهُ عَلَيْهِ الصَّلَاةُ وَالسَّلَامُ. {قُلْ إِنْ كُنْتُمْ تُحِبُّونَ اللهَ فَاتَّبِعُونِي يُحْبِبْكُمُ اللهُ وَيَغْفِرْ لَكُمْ ذُنُوبَكُمْ}»
صلوا عليه (8) - صلى الله عليه وسلم
🎙ተደምጦ የማይጠገብ ሙሓደራ! _ 🚢 «መርከቧ ከመስመጧ በፊት» —በዳዒ ሀዊ_መሀመድ—(ረሂመሁላሁ) t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1
видео или голосовое, без подписи
Live stream finished (14 minutes)
Live stream started
Live stream finished (11 seconds)