tgindex
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ

የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀማዓ

Статистика

💥ይህ ቻናል የወልቂጤ ዩነቨርሲቲ ሙስሊም ጀማዓ ዋናው ቻናል ነው ። ስለጀማዓው ያሉ መረጃዎች፣ አስተማሪ እና መሳጭ እስላማዊ ትምህርቶች በዚሁ ቻናል ይለቀቃሉ ። ይከታተሉን ፣ለሌሎችም ይጋብዙት አላህ የሱን ፊት ፈልገንበት የምንሰራ እና ሙስሊሙን ኡማ የምንጠቅምበት ያድርግልን! 📩ማንኛውም ሀሳብ አስተያየት ጥያቄ ካላቹ በ @wkumuslimsbot መላክ ትችላላችሁ

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
6
Всего постов
29
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 380
+3 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
288
29 постов
Вовлечённость
20,9%
к подписчикам
Постов в день
0,9
всего 29
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
141
1/48двое суток
161
1/72трое суток
174

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • አንድ ሰው ወደ ጀላሉዲን ሩሚ መጥቶ ስለነፍሱ ወዳጅና ስለ ውድ መምህሩ ሸምስ ጠብሪዝ አልኮሆል መጠጣት ሊነግረው ሞከረ። [በዘመናቸው በሁለቱ መካከል ችግር ለመፍጠር ብዙ ሰዎች እንደሞከሩ የታሪክ ድርሳናት ያትታሉ] መውላና እንዲህ አለው!... "ወላሂ የሸምስ ልብስ በኸምር ተለውሶና ተነክሮ ባየው የሰውነቱ ሽቶአማ ጠረን ቀድሞ ስለሚደርሰኝ 'ሽቶ ተደፍቶበት ነው' እላለው !... ከተራራው ጫፍም ወጥቶ 'እኔ ጌታችሁ ነኝ!' ሲል ብሰማው ፈርዖን ለህዝቡ የተናገረውን እያስታወሰን እንደሆነ እንጂ ሌላን አልረዳም!..." አስከትሎም አለው... "መጥፎ ጥርጣሬ በዓይን ብቻ ለሚተዋወቁ ሰዎች ነው! ከልብ ለተግባቡና ለተቀማመጡት ግን... ዓይን ያየውን ልብ የሚተረጉምበትን መንገድ ብታውቅ ኖሮ እጅጉን ትደነቃለህ!"

  • 🍀 🍀 ✨ مَا كُلُّ مَا يَتَمَنَّى الْمَرْءُ يُدْرِكُهُ رُبَّ امْرِئٍ حَتْفُهُ فِيمَا تَمَنَّاهُ ምናልባት የተመኘነው ነገር ሁሉ ለኛ ጥሩ መስሎ ግን መጥፊያችን ሊሆን ይችላል ። :¨·.·¨: 💚juma'a  `·. @fewz_ahmed

  • سلام عليكم ورحمة الله وبركاته✨✨ እንደምን እንዴትስ ሰነበታችሁ??? እናማ ያው አናቀዋለን ግን እስኪ ትንሽ እናውጋው! ለምንድነው ለልብ ደስታና ሰላሟን በሚነፍግ ነገር ውስጥ ምንዘወትረው  እእ?? ከወንጀል ምናተርፈው የደቂቃዎች እርካታ  እንዴትስ አርገን ነው ከዘላቂው  ፀፀት ጋ  ያወዳደርነውስ??ልብ ላይ ሸክምን ጥሎ፣አጠልሽቶ፣የህይወትን መንገድ አቆላልፎ  እንዴትስ ወደድነው እ ለምንስ ስሜት እስረኛ መሆንን ሻትን  ሽተንስ አደለም ግን ከዚ አዙሪት ለመውጣት መጣርን ማን ወሰደብን?? ብዙ ተስፋን ያነገበ፣ነገውን ለማቅናት ያሰበ፣ ስኬትን የፈለገ፣ለልብ ሰላም፣ብርሀን  የሚማስን፣ የነገሮችን መቻል የሻተኮ ረጂው፣ ደጋፊው፣መሪው፣ጠጋኙ በቃ የሁሉም ነገሩ እስተናባሪውን አብሮነት ወዳጅ ነው፡፡እንዴትስ ከሱ መራቅን ይሽታል? እንደው  በሰዋዊነቱ ቢደናቀፍ እያነከሰም ቢሆን ሚያንኳኳው የሱን ደጃፍ ነው፡፡ለአጥፊነቱም መሀርታን ዘዉትር ፈላጊ ነው፡፡ እናማ ልቡን ሰላም የነሳውን፣እሱነቱን ሚነጥቀውን መዕሲያ መላቀቂያ መንገድን ፣መሀርታን ፍለጋ  ጌታው ዘንድ ጠያቂ ነው እሱ አየሳፍረውምና!! እናማ ግዴለም እንመለስ ልባችንም ይርጋ ጂሙአም አይደል ሱናዎችን ሀይ እያረግን ያ ጀመአ 👉ገላን መታጠብ 👉ጥፍርን መቁረጥ 👉ጥሩ ልብስ መልበስ 👉 ሽቶ መቀባት(ለወንዶች) 👉 ሲዋክ መጠቀም 👉 በግዜ መስጂድ መግባት 👉ኢማሙ ሚንበር እስከሚወጣ ድረስ የሱና ሰላት መስገድ 👉ሰላዋት ማብዛት 👉 ሱረቱል ከህፍ መቅራት 👉ኹጥባ በጥሞና ማድመጥ    ደሞ ደሞ  ✨✨صل على النبي ىا جمع✨ ❤️ الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد

  • 👉ያ ለረጅም ዘመን ጭርታህን አስወጋጅ የነበረው ውዱ ጌታህ 👉ያ በተለያዩ አጋጣሚ ወድቆብህ ተስፋ ስትቆርጥበት የነበረው ጭንቀትህ ሁሉ ሲገላግልህ የነበረው ውዱ ጌታህ 👉ያ ስጋትህን ወደ ሰላም ሲቀይርልህ የነበረውና ህይወትህን ሙሉ በጥበብ ሲያስኬድልህ የነበረው ውዱ ጌታህ 👉ያ ዎች ሁሉ ሲርቁህ ሚያስጠጋህና አብሽር ሲልህ የነበረው ውድ ጌታህ 👉ያ ምንም ያንተ ብልሀትና ጥንካሬ ሳይታከልበት ስትታመም የፈወሰህ ስትራብ የመገበህ ስትጠማ

  • без подписи

  • ሳምንታዊ የንባብ ጥቆማ | Weekly Book Recommendation 📚 ለወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች ጀምዓ (WKU MSJ) አባላት በሙሉ፤ እራሳችንን በኢስላማዊ እውቀት የምናንጽበትና ወደ አላህ (ሱ.ወ) የምንቀርብበት አዲስ የንባብ መርሃ-ግብር ይዘንላችሁ መጥተናል። 📖 የመጽሐፉ ርዕስ: The Causes of Istighfar (የእስቲግፋር መንስኤዎች) ይህ መጽሐፍ የእስቲግፋርን (ምህረት የመጠየቅን) ታላቅነት፣ ለምንና እንዴት እስቲግፋር ማድረግ እንዳለብን እንዲሁም የልብን መረጋጋት በምን መልኩ ማግኘት እንደምንችል በሰፊው የሚያብራራ ድንቅ መጽሐፍ ነው። => ዋና ዋና የመጽሐፉ ነጥቦች (Key Takeaways): => የልብ ጥራትና መረጋጋት: እስቲግፋር የልብን ዝግ፣ አቧራ እና ወንጀል የሚያጥር ሁነኛ መድኃኒት ነው። => የነብዩ (ﷺ) ሱና: ነብዩ (ﷺ) ከወንጀል የጠሩና ያለፈውም የፊቱም ጥፋታቸው የተማረላቸው ሲሆኑ እንኳን በቀን ከ70 እስከ 100 ጊዜ እስቲግፋር ያደርጉ ነበር። => የአላህ እዝነት ማግኛ: ስራችን ምንም ቢበዛ የአላህን ጀነት ለመግባት የእሱ እዝነት ስለሚያስፈልገን በየእለቱ ወንጀላችንን እያሰብን ምህረት መለመን ይኖርብናል። ወንድሞችና እህቶች! በትምህርት፣ በፈተና እና በካምፓስ ህይወት ውጥረት ውስጥ ልባችን ሰላምና መረጋጋት እንዲያገኝ፣ እንዲሁም የአላህን እዝነትና ባረካ እንድናገኝ የዘወትር እስቲግፋርን ልማዳችን እንድናደርግ አደራ እንላለን። 📲 ይህንን መልእክት ለሌሎች ወንድሞችና እህቶች ሼር (Share) በማድረግ የኸይር ስራው ተካፋይ ይሁኑ!

  • ⚖️ እውነተኛው ሚዛንና የነፍስ ትግል ⚖️ 🍃 በዚህ ዓለም ላይ ሰዎች እርስ በእርስ ሲኖሩ አንዱ ሌላኛውን መወንጀልና መክሰስ እጅግ ቀላል ነው። ራሳችንን ንጹሕ አድርገን ሌላውን ማጠልሸት፣ ወንጀለኛና ጥፋተኛ ማድረግ የሰዎች የዘወትር ተግባር ሆኗል። በዱንያ ላይ ስንኖር ለጊዜው ሰዎችን በማታለልና ራስን በማጽደቅ መኖር ቢቻልም፤ ነገ ግን የማይታለል ጌታ ፊት መቆማችን አይቀሬ ነው። 🍃 አላህ (سبحانه وتعالى) በቁርአኑ እንዲህ ይላል፦ "በትንሣኤ ቀን ትክክለኛዎቹን ሚዛኖች እናስቀምጣለን፤ አንዲትም ነፍስ ምንም አትበደልም..." (አል-አንቢያእ፡ 47)። በዚያ ታላቅ ቀን የሰዎች እውነተኛ ማንነት ይወጣል። በዳይና ተበዳይ በግልጽ ይታወቃሉ፤ በአፈር የተሸፈነው ምስጢር ሁሉ ለዓይን ይቀርባል። 🍃 ታማኙ ነቢያችን (صلى الله عليه وسلم) በዳይ ከመሆን ይልቅ ተበዳይ መሆን እንደሚሻል መክረውናል። ምክንያቱም በዳይ ሆነህ አላህ ዘንድ የቀረብክ ቀን ውርደትና ጸጸት እንጂ ሌላ አትታቀፍም፤ ስብራትህም አይጠገንም። በተቃራኒው ግን ተበዳይ ሆነህ ከቀረብክ፤ በዓለማቱ ጌታ ዘንድ ትልቅ ካሳና ምንዳ ይጠብቅሃል። 🍃 ራሳችንን ዝቅ እንድንል፣ ቻይና ታጋሽ እንድንሆን፣ ስሜታችንን እንድንቆጣጠርና ከበደል እንድንርቅ የሚያደርገን ትልቁ መሣሪያ አላህን (عز وجل) መፍራት ነው። ለሰዎች ሐቅ መጠንቀቅና ነፍስን ከጥፋት መታገል የአማኝ መታወቂያ ነው። 🍃 ወዳጄ ሆይ! የዛሬው ጊዚያዊ ትርፍ ነገ የዘላለም ኪሳራ እንዳይሆንብህ ተጠንቀቅ። ሰውን ከመበደል ይልቅ መበደልን ምረጥ፤ ያኔ አላህ ይካስሃል። የነፍስያህን ግፊት አሸንፈህ በሰዎች ሐቅ ላይ ታማኝ ሁን። ዛሬ የምትዘራው እዝነት ነገ በጀነት ውስጥ የሚያምር ፍሬ ሆኖ ይጠብቅሃል።

  • የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- مَنْ أحبَّ أن يَصِلَ أباهُ في قبرِهِ، فلْيَصِلْ إخوانَ أبيهِ مِن بَعدِه "በመቃብሩ ውስጥ ላለ (ለሞተ) አባቱ መልካም መዋል የሚወድ ሰው፣ ከእርሱ በኋላ ለአባቱ ወንድሞች (ወዳጆች) መልካም ይዋል።" [ሶሒሑል ጃሚዕ ፣ አልአልባኒይ ፡ 5960] የወላጆች ሐቅ በመሞታቸው አይቋረጥም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚህ ሐዲሥ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላም ቢሆን ለእርሱ መልካም ነገርንና ምንዳን ማብዛት የሚቻልበትን ተግባራዊ መንገድ ያሳዩናል። እርሱም የአባትን ወዳጆችና የቅርብ ዘመዶች መዛመድ/መንከባከብ፣ መጠየቅ ነው። ለአባት መልካም ማድረግ በእርሱ ህልፈት የሚያበቃ ሳይሆን፣ በሕይወት እያለ ይወዳቸውና ይዛመዳቸው የነበሩትን ሰዎች ሁሉ የሚያጠቃልል ነው። ከዚህም ባሻገር ለወላጆች በማሰብ ሶደቃ ማውጣት፣ ዱዓእ ማድረግ፣ ዑምራ ማድረግ፣ ... ከሞቱም በኋላ አጅራቸው እንዲቀጥሉ ከሚያደርጉ ተግባራት ውስጥ ናቸው። ኢብኑ ሙነወር

  • ወንጀል ከሰራህ በኋላ ምንም እንኳን ትንሽ ገንዘብ ቢሆን ሰደቃ ስጥ፤ ምክንያቱም ሰደቃ የኃጢአቱን መጥፎ ተጽእኖና መዘዝ በአላህ ፈቃድ ታስወግዳለች። — ሸይኽ ዐብዱስሰላም አሽ-ሹወይዒር

  • 🍀 🍀 ✨ ﴿وَاللَّهُ خَيْرُ حَافِظا﴾ "Allah is the Best Guardian." Yusuf 12:64 :¨·.·¨: 💚juma'a  `·. @fewz_ahmed

  • ትልቁ ሙሲባ ብሎ ማለት ሶብርን ማጣት ነው ። የሙሲባን አይነት የምናስተናግደው አንድ መከራ ሲገጥመን ካለመታገሳችን ቆም ብለን ካለ ማሰባችን ነው። ሶብር ከማጣት ጀርባ ብዙ ችግሮች አሉ ሚፈጠሩ አላህ በሁሉም ነገር ላይ ታጋሾች ያድርገን !!

  • አላህ እንዲህ ይላል፦ { یَوۡمَىِٕذࣲ تُحَدِّثُ أَخۡبَارَهَا } "በዚያ ቀን (ምድር) ወሬዎቿን ትናገራለች።" [አዝ-ዘልዘለህ፡ 4] ወሬዎቿን ማለት በገጿ ላይ የተፈፀመን ሁሉ ማለት ነው። በቂያማ ቀን ምድር በላዩዋ ላይ የተፈፀመን ክፉም ሆነ ደግ ትናገራለች። ምድር ላይ ስንትና ስንት ተመልካች ምስክር የሌለባቸው ወንጀሎች ተፈፅመዋል?! ስንት ነፍስ ጠፍቷል?! ስንት ንብረት ተወስዷል/ ወድሟል?! ስንት ግፍ ተፈፅሟል?! ቢሆንም ሁሉ ከንቱ አይቀርም። ያኔ ምድር ትናገራለች፣ አካላት የሰሩትን ይመሰክራሉ። ከፍጡር እይታና ትዝብት፣ ከፍትህ የተረፉ የመሰላቸው ሰዎች የሚያፍሩበት ቀን ነው

  • 2 авг.4015из aaumsu

    ዛሬ ምሽት 3:00 እንገናኝ! ትላንት ምሽት በነበረን መድረክ የሴኩላሪዝምን ምንነት፤ በአሜሪካ ፈረንሳይ እና ጀርመን ያሉትን የሴኩላሪዝም ሞዴል፤ በኢትዮጵያ ሕገ- መንግስት ውስጥ የሰፈረውን ሴኩላሪዝም ትርጓሜ እንዲሁም ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች ስልጣናቸውን አለአግባብ በመጠቀም እንዴት እየጨቆነን እንዳለ በጥልቀት ተዳሷል። ዛሬ በሚቀጥለው ውይይት ያልተነሱ ነጥቦችን እና የተጠየቁ ጥያቄዎችን በጥልቀት እንዳስሳለን። በሰዓቱ እንገኝ፤ ሌሎችን እናስታውስ። @aaumsu

  • ወደ አላህ የምታዞርህ ሙሲባ ከአላህ ዚክር ከምታርቅህ ኒዕማ ትሻላለች ይላሉ። ኢብኑ ተይሚያህ رحمه الله

  • 🍀 🍀 ✨ ﴿فَاذْكُرُونِي أَذْكُرْكُمْ﴾ "So remember Me; I will remember you." Baqarah 2:152 :¨·.·¨: 💚juma'a  `·. @fewz_ahmed

  • ከትንሳዔ መድረስ ምልክቶች ውስጥ! ረሱል እንዲህ ብለዋል፦ ﴿لَا تَقُومُ السَّاعَةُ حَتَّى يَكُونَ أَسْعَدَ النَّاسِ بِالدُّنْيَا لُكَعُ بْنُ لُكَعَ﴾ ​“ትንሳዔ (ቂያማ) አይቆምም፤ በዱንያ (በዚህች ዓለም) ከሰዎች ሁሉ ይበልጥ ደስተኛው (ተጠቃሚው) ስነ‐ምግባር የጎደለው (ወራዳ አላዋቂ የነበረ ሰው ወይም የአላዋቂ ልጅ) እስከሚሆን ድረስ።” ቲርሚዚ ዘግበውታል፡ 2209

  • ‏صفحة واحدة من القرآن كم فيها من مثاقيل الحسنات التي لا يحصيها إلا الله. فكيف بالجزء، بالجزئين، وبأكثر من ذلك؟ اللهم لا تحجبنا عن كتابك بذنوبنا وفساد قلوبنا. 👉አንድ ገጽ ቁርዓን ምን ያህል ምንዳ (ሀሰናት) አለው? ​በአላህ ፈቃድ በአንድ ገጽ ቁርዓን ውስጥ አላህ እንጂ ማንም የማይቆጥራቸው እጅግ ብዙ ሀሰናቶች ይገኛሉ። ​• ነቢዩ (ﷺ) እንዳሉት፦ "ቁርዓንን ያነበበ ለእያንዳንዱ ፊደል 10 ምንዳዎችን ያገኛል። • በቁርዓን አንድ ገጽ ውስጥ በአማካይ 500 ያህል ፊደላት ይገኛሉ። ይህ ማለት አንድ ገጽ ብቻ ሲቀሩ ቢያንስ 5,000 ሀሰናቶችን ያገኛሉ ማለት ነው! ​ታዲያ አንድ ጁዝ (20 ገጽ) ሲቀሩስ? 👉 ከ100,000 በላይ ሀሰናት! ​ሁለት ጁዝ ወይም ከዚያ በላይ ሲያነቡስ ሀሰናቱ ምን ያህል ይበዛ ይሆን? አላህ ለፈለገው ሰው ምንዳውን አጣጥፎ ይሰጣል። ​ አላህ ሆይ! በወንጀላችንና በልባችን መበላሸት ምክንያት ከኪታብህ (ከቁርዓን) እንዳትከለክለን።

  • ለአላህኮ ባሮች አሉት 😥 ​አንድ ወጣት አንዲትን ሴት ለማጨት (ለጋብቻ ለመጠየቅ) ሄደ። በሕጋዊው የእጮኝነት እይታ (ሩእያ) ወቅት ሴቷ እንዲህ ስትል ጠየቀችው፡ ​«ከቁርኣን ምን ያህል ሀፍዘሃል?» ​ወጣቱም በትህትና፡ «ብዙ አልሃፈዝኩም፤ ነገር ግን ሷሊህ ባሪያ የመሆን ፍላጎት አለኝ» ሲል መለሰላት። ​በመቀጠልም እርሱ ጠየቃት፡ «አንቺስ ምን ያህል ሀፍዝሻል?» እርሷም፡ «ጁዝኡ ዐማህ ሀፍዣለሁ» አለችው። ​ሴቲቱም በውስጡ ያየችውን እውነተኝነትና ቅንነት በመመልከት በጋብቻው ተስማማች። ከጋብቻ በኋላ ቁርኣንን በመሃፈዝ እንዲረዳት ጠየቀችው፤ እርሱም፡ «ችግር የለውም፤ አብረን በመተጋገዝ እንሃፍዛለን» አላት። ​ጉዞአቸውን ከሱረቱ 'መርየም' አብረው ጀመሩ። በሂደትም ሱራዎችን እየተከታተሉ ሙሉ ቁርኣንን በእርሱ ፊት አጠናቀቀች። የቁርኣን ሀፊዝነት ማረጋገጫ - ኢጃዛም አገኘች፤ እርሱም በተመሳሳይ አገኘ። ከዚያም በመቀጠል «አሁን ደግሞ የሶሒሕ አል-ቡኻሪን ሐዲሶች መሃፈዝ እንጀምር?» ስትል ሀሳብ አቀረበችለት 🥰 ​ * * * ከዕለታት አንድ ቀን ​የወላጆቿን ቤት በጎበኙበት ወቅት፣ ባልየው ለአባቷ በኩራት እንዲህ አላቸው፡ ​«ምስጋና ለአላህ ይሁን፤ ልጅዎ ቁርኣንን ሙሉ በሙሉ ሃፍዛ አጠናቃለች!» ​አባትየው በንግግሩ ተገረመ፤ ወደ ልጅቱ ክፍል ገብቶ በርካታ የምስክር ወረቀቶችን (ሸሃዳዎችን) ይዞ በመውጣት በባልየው ፊት አስቀመጣቸው። ​የባልየው ድንጋጤና መገረም ምንኛ ድንቅ ነበር! ሚስቱ እርሱን ከማግባቷ በፊት ሙሉ ቁርኣንን ያፈዘችና ስድስቱን (ኩቱቡ ሲታህ) ያጠናቀቀች እንደነበረች ታወቀ! ​🌿 ከታሪኩ የምንማረው ጥበብ ​አላህ ጥራት ይገባው! በመጀመሪያው ቀን በእውቀት ማነሱ ምክንያት አላሳፈረችውም ነበር! ይልቁንም በውስጡ ያለውን ደግነትና ቅንነት ስለተረዳች፣ በእውቀትና በጥበብ እርሷ ደረጃ እንዲደርስና እንዲሃፍዝ አደረገች። ​«ጁዝኡ ዐምን ሃፍዣለሁ» ስትል አልዋሸችም፤ ምክንያቱም ከእርሱ ውጪ ያለውን ክፍል አላፈዘዝኩም ብላ አልካደችምና። 👉የት ነው ያለችው ይች አይነቷ....🤔

  • ጥሩ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት ብለህ አትዘናጋ፡፡ ከጀነት የበለጠ ጥሩ ቦታ የለም፡፡ አባታችን አደም በሷ ዉስጥ ሆነው ጭምር ፈተና አግኝቷቸዋል። በዒባዳህ ብዛትም አትጃጃል፣ ኢብሊስ ከዚያ ረጅም የዒባዳ ሕይወት በኋላ ምን እንዳጋጠመው ይታወቃል፡፡

  • እውነተኛ ፍቅር ያ አንተን ከሀራም ሚጠብቅህ እንጂ ወደ ሀራም ሚጎትትህ አይደለም