tgindex
Ibnu Ahmed
@ibnuahmed11английский

"وَمَا تَوْفِيقِي إِلَّا بِاللَّهِ عَلَيْهِ تَوَكَّلْتُ وَإِلَيْهِ أُنِيبُ" " "I want to reform to the best of my capability, and my success is only through Allah; on Him I rely and to Him I return" (11:88)

Последний пост
16 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
610
−3 за 5 дн.
Сутки
−1
−0,16%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
201
23 постов
Вовлечённость
33,0%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 23
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
67
1/48двое суток
76
1/72трое суток
82

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ሁሉ ነገር በአስባብ አይገኝም። በዱዓ አንጂ የማይገኙ ነገሮች አሉ። እነሱን በዱዓ እንፈልጋቸው። @to2success

  • ብዙዎቻችን ያልተገራንለት ጉዳይ ነው። አምልኮ (ዒባዳ) እራሳችንን የምናጨናንቅበት ጉዳይ ሳይሆን የቀልብ እረፍት የምናገኝበት ነው። አምልኮ አላህን ስለማላቅና እርሱን ከልብ ስለማፍቀር እንጂ ጭንቀትና ጥበት አይደለም። አምልኮ (ዒባዳ) ላይ መሰላቸትና የቀልብ እርጋታን አለማግኘት አንዱ የኢማን መድከም ማሳያና የሙናፊቆች አንዱ መገለጫ ነው። አማኝ ወደ አላህ ሲቃረብ፣ አምልኮን ሲፈፅም ደስታና የልብ ስክነት ሊሰማው ይገባል። ለዛም ነው የዓለማት እዝነቱ ነቢያችን የሆነ ነገር ሲጨንቃቸውና የልብ እረፍት ለማግኘት ሲፈልጉ ቢላልን: "በርሷ (በሰላት) እረፍት እንድናገኝ አድርገን" ይሉ የነበሩት!! @to2success

  • አሁን ላይ ብዙ ሰዎች ዘንድ የተለመደ አንድ ቃል አለ "እየሞከርኩኝ ነው!" ሰዎች ይህን ቃል ከብዙ ነገር አኳያ ሊሉት ይችላሉ። ከሁሉ በላይ ግን " ለተፈጠርኩበት አላማ ለመኖርና ህይወቴን አላህ በሚፈልገውና ባዘዘኝ ሁኔታ ለመኖር እየሞከርኩኝ ነው!" የሚለው ነው። ከዚህ በላይ ልንጥር፣ ልንሞክርለት የሚገባ ጉዳይ የለም። ሁሉም የሚሞከርለት ጉዳይ ከዚህ በታች ነው። ለምን እየሞከራችሁ ነው!! @to2success

  • አላህ ላንተ መልካሙን ሲሻልህ ከመጥፎ ነገር ይጠብቅሃል። ልትራመድ ብትሞክርም እግርህን ይይዝሃል፤ ምላስህ እንዳያወራ ያደርገዋል። ሰንት መልካም የመሰሉን ዛሬ ላይ ስናስባቸው ለኛ መጥፎ እንደነበሩ የተረዳናቸው ጉዳዮች አሉ። @to2success

  • ለናንተ ደስተኛ ህይወት ማለት ምን አይነት ህይወት ነው? * ጥሩ ነገር እየለበሱ፣ እየተመገቡ፣ እየተዝናኑ በምቾት መኖር ብቻ ወይስ * ብዙ ሀብት ማካበት ላይ ብቻ ቢዚ ሆኖ መኖር ወይስ * ሰዎች ዘንድ ዝነኛ ሆኖ መኖር ወይስ * አላህን ፈርቶ አላህ ባዘዘው ልክ መኖር ምናልባት የብዙዎቻችን መልስ አላህን ፈርቶ አላህ ባዘዘው ልክ መኖር የሚለው ሊሆን ይችላል። ግን በእውነት እኛ እንደዛ ለመኖር እየሞከርን ነውን? መልሳችንና ተግባራችን የተለያዩ አይደለምን?? መልሳችን ይሄ ሆኖ ተግባራችን ግን ሌላውን አይሰጥምን? መልሱን ለናንተው ተውኩት? መልካም ጁመኣን ተመኘሁላችሁ!!! @to2success

  • ትጠቀሙበታላችሁ እስከመጨረሻ አንብቡት!! ማግባት ብርቅ ነው እንዴ?! አይደለም! ማግባት ብርቅ አይደለም። ትዳር ግን ብርቅ ነው። መኗኗር ብርቅ ነው። ከመጋባት በኋላ መተዛዘን መተሳሰብ መፈላለግ መፋቀር ግን ብርቅ ነው! አዎ ይህ ኸይራት እየሸሸ መጥፎ ነገሮች ምድርን እያመሱ ባሉበት በዚህ ዘመን ትዳር ብርቅ ነው። ደግሞም ትዳር አማና ነው። አማናውን ያጎደለ ግን ብዙ ነው። ከወንድ ከሴት የሚል መደብ የለውም። ሁሉም አጉድሏል ሁሉም አጥፍቷል አማናን አበላሽቷል። የአማናን ክብደት አልተረዳነው ይሆን ወይ ደግሞ ባልና ሚስት ጋር ሲኮን አማናነቱ ይጠፋናል መሰል እንጃዕ ለትዳር ያለን ነገር ወርዷል ። አንድ ወንድ አንዲትን ሴት ከእናት አባቷ ቤት ሲወስዳት እንደ እናት አባቷ ቤት ሊያኖራት እንዳልሆነ ግልፅ ነው። ግን አማናው ናት! እናት አባቷ ቤት ሃላፊነቱ የ'ሷ አልነበረም ቤት ማስተዳደር ልጅ መውለድ ለልጅ መድከም ባልን ለማስደሰት ማሰብ የ'ሷ ድርሻዎች አልነበሩም። የ'ሷ ድርሻ ምን አልባትም መብላት መጠጣት ብቻ ሊሆን ይችላል። ምን አልባትም እየዘነጡ እራስን እየጠበቁ መውጣት መግባት ህይወትን ኢንጆይ ማድረግ ብቻ ሊሆንም ይችላል። እናት አባት ቤት አስቤዛ አለቀ ልብስ ቆሸሸ ቤት ተዝረከረከ ላይባል ይችላል። ዛሬ ግን የዚህ ሁሉ ሃሳብ ባለቤት እሷ ትሆናለች። ስለ'ዛ ቤት ስለ'ዛ ማጀት ስለባል ስለማስደሰት ስለመደሰት ስለመኖር ሁሉንም ታስባለች። ትጨነቃለች አለቀ ጎደለ ሞላ ተገኘ ጠፋ ሁሉንም ዓይነት እሳቤዎች በህይወቷ ውስጥ ታስተናግዳለች። ሌላ ማንነት ሌላ ሴትነት ሌላ ህይወት ትጀምራለች። ታዲያ የዚህን ጊዜ የባል ሚና ብዙ በጣም ብዙ ይሆናል። እነዚህን የእሳቤ መለዋወጦችን ጭንቅላቷ በአንዴ መርሃባ ብሎ መቀበል ሊከብደው ይችላል። ከዚህ ህይወት ጋር እስክትግባባ እስክትላመድ ጊዜ ሊፈጅባት ይችላል። በተለይ በትዳር የመጀመሪያው ዓመት ይሄ መፈጠሩ አይቀሬ ነው። ይሄንን ግራ መጋባቶች በእርጋታ ወደ መረጋጋት ለማምጣት የሁለቱም ሚና ወሳኝነት አላቸው። ወንዱም ከእናት አባቱ ቤት ወጥቶ አንቺ ጋር ሲመጣ ብዙ የተወጫበሩ እሳቤዎችን ይዞ ነው ሚመጣው። ቢሆንም ያ' ሰው አማናሽ ነው። ምን አልባትም እናቱ ለአባቱ የምታደርግለትን እያንዳንዱን ነገር ካንቺ ጠብቆ ምን አልባትም ልክ እንደ እናቱ የምትሰስቺለት ዓይን አይኑን እያየሽ የምትረጂው አይነት አድርጎ አስቦሽ ይሆናል። ወይ ደግሞ የጓደኞቹን የወንድሞቹን ትዳር አይቶ ዛሬውኑ ያንን ሃያት መጀመርን አስቦ ይሆናል የመጣው። አልያም የሆኑ የሚፋቀሩ ህይወትን በመዝናናት እያለፉ ያሉ ጥንዶችንም አይቶ ይሆናል። ያንን በህይወቱ ሊደግም ከጅሎ ዛሬ አግብቶሽ ነገ ያቺን ሴት እንድትሆኚለት እየከጀለሽም ይሆናል። ግንሳ..... ለሁሉም #ጊዜ ይፈልጋል። መጋባቱ ብቻ ሳይሆን ተግባብቶ ለመኖር ወቅት ይጠበቃል። አዲስ ነገር አዲስ ማንነት አዲስ መጋራት አይተነው የማናውቀው የሆነ ከሩቅ ሰው ጋር በአንድ አንሶላ መታጠር ብዙ ትርምስሞችን ይዘን በአንድ ጣሪያ ስር ማደር ይህ ቀላል አይደለም። አዎ ቀላል አይደለም። መረጋጋት ይፈልጋል መታገስ ይፈልጋል መቻል ይፈልጋል መከባበር መተዛዘን መተሳሰብ ይፈልጋል። አንዱ አንዱን እስኪያውቀው እስኪዋሃደው አንደበትን ሰበር ማንነትን ገለጥ እያደረጉ መተያየትን ይፈልጋል። አዎ ተጋብተናል አግብተናል አልሐምዱሊላህ ትድረት ከምርጦች ሁሉ ምርጡ ውህድ ነው። ይህንን ውህድ ለማቆየት ግን ፈተና አለ መውደቅ አለ ማለፍ አለ እየደጋገሙ መፈተን እየደጋገሙ መውደቅ እየደጋገሙ  መነሳት አለ። ማጣት ይጎበኘናል ማግኘትም ይመጣል ህመም ወደ ጎጆአችን ጎራ ይላል ደስታ ድንገት ከጓዳችንም ይገኛል። ያ'ኔ ማንነታችን ይፈተናል። ለትዳራችሁ መስመር የእናት አባቶቻችሁን ጎጆ አጢኑት። ዛሬ ወጣቶች ሁነን የጀመርነው ህይወት መዳረሻው እንደ እናት አባቶቻችን ነው። ሌላ ተአምር የለውም። የእናት አባታችን ትድረት ያላማረ ከነበረም ለምን እንዳላማረና እንዳልሰመረ ፈትሹት። ያንን ስህተት በህይወታችሁ በቤታችሁ እንዳትደግሙት ይረዳችኋል። #አይብ ተሰታተሩ ሁሉንም በአንዴ ካላየን ካላወቅን አትበሉ። አፍላ ፍቅራችሁ ላይ ነገን ማሰቢያ ጥቂትን ቦታ አኑሩ። አትፈራሩ አትተፋፈሩ ብዙም አትገላለጡ 🎯አደራ አደራ ህይወታችሁን ትዳራችሁን ቤታችሁን ከsocial media ህይወት ጋር አታነፃፅሩት። በመከባበር በመዋደድ በመተዛዘን አጥር እጠሩት! አላህዬ ትድረታችንን ያስውብልን ላላገቡ እህት ወንድሞችም ማረፊያ መሻሪያ የሆነ ትድረት ይመንዳልን © @to2success

  • " ህይወት ከምናስባት በላይ በጣም አጭር ናት፤ ይህችን አጭር ህይወት በሀሳብ፣ ጭንቀትና ትካዜ አታሳጥራት። ካለፈው ህይወት ውጣና የዛሬህን ህይወት አጣጥመህ ኑር። መጪውን ደግሞ እስኪመጣ ተወው የተሻለ ይሆናል። " © @to2success

  • በሴት ልጅ ላይ ከመጫወት እንጠንቀቅ‼ አንዳንዶቻችን ወደ ትዳር ዓለም ለመግባት መንገድ እንጀምራለን። አካባቢዋን እናጠራለን፣ ቤተሰብ እናስተዋውቃለን፣ ሽማግሌ እንልካለን፣ የኒካሕ ቀን እንቆርጣለን። በዚህ ሂደት ውስጥ እህቷ የራሷን ህልም ትገነባለች፣ ቤተሰቧ ለትልቅ ቀን ይዘጋጃል፣ በደስታ ይዋጣሉ። ከዛም ባልታሰበ ሁኔታ፣ ያለበቂ ምክንያት እና እሷም ምንም አይነት በደል ሳትፈጽም፣ «አልፈልግሽም፣ አይሆንልኝም» ብለን እንተዋታለን። ወንድሞቼ፣ ልብ በሉ! ያንን ትተን ስንሄድ ለእኛ ቀለል ያለ ነገር ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ለሷ፣ ለቤተሰቧ የተሰበረ ልብ እና የማይሽር ጠባሳ ትተን እየሄድን ነው። እስቲ ራሳችንን በእሷ ቦታ እናስቀምጠው፡ 1. ዲን ያላት እህት ናት ብለን አጣርተን፣ ሰርተን፣ ተረጋግተን መርጠን ወደ ቤተሰብ እናስተዋውቃታለን። ከዚያም የገዛ ምርጫችንን ራሳችን እንሰብረዋለን። ይህ ምርጫችንን እራሳችንን እንደመካድ ይቆጠራል። 2. ቤተሰብ እስካወቀ ድረስ ነገሩ የህዝብ ሆኗል። የሰዎችን ቀልብ እና ተስፋ እንጫወታለን። በኢስላማዊ አስተምህሮ የሰውን ተስፋ ማጨለም እና ልብ መስበር ምን ያህል ከባድ እንደሆነ እናውቃለን። 3. ምክንያቶቻችን አሳማኝ አይደሉም። "አንቺ እኔ ከማኖረሽ በላይ ትበልጫለሽ" ወይም "አቅሜ አይፈቅድም" የሚሉ ሰበቦች ወይም በዘመናዊ ዘዴ «ለአንቺ አልመጥንሽም፣ ከኔ የተሻለ ይገባሻል!» በሚል የማስመሰል ዘዴ፣ ቀድሞ አጣርቶ ከገባ በኋላ የሚነገሩ ከሆኑ ተገቢ አይደሉም። ብዙውን ጊዜ እነዚህ ሰበቦች ሌላ ቦታ ለማግባት ስንወስን የሚደበቁባቸው እውነታዎች ናቸው። 4. የሴት ልጅ ልብ አደራ ነው። አላህ በፈቀደው መሰረት ያንን ቀልብ አሸንፈን፣ የትዳር ጓደኛ እንድትሆነን ተስፋ ሰጥተናት፣ ከዚያ በኋላ ያንን ተስፋ ማጨለም ትልቅ ኃላፊነት ያስጠይቃል። ወንድሞቼ፣ ከልቤ የምመክራችሁ አግቡ፣ ይህ ትልቅ ሱንና ነው። ነገር ግን ለማግባት ከወሰናችሁ፣ ቤተሰብ እስካስተዋወቃችሁ ድረስ ከባድ እርምጃ ላይ ናችሁ ማለት ነው። ይህንን እርምጃ ከማድረጋችሁ በፊት በመቶዎች የሚቆጠሩ ጊዜ አስቡ። እርግጠኛ ካልሆናችሁ፣ የሰዎችን ልጅ ተስፋ አትቁረጡ። አንዴ ከተዋደዳችሁ በኋላ፣ ከኒካሕ በኋላም ሊሆን ይችላል፣ ትተውት ለሚሄዱት ሁሉ አላህ ይጠይቃችኋል። እስቲ ልባችሁን በእውነት እያዩ አላህን ፍሩ። በቃሏ የማትፀና ከሆነች ሴት ጋር ስትጣሉ የምትፈፅሙትን ግፍ እንዳለ ሁሉ፣ በማይገባ ምክንያት የሰውን ተስፋ ሰብራችሁ መሄድም ተመሳሳይ ግፍ ነው። የማግባት መንገድን ጀምራችሁ፣ በሰው ልጅ ተጫውታችሁ ያለ በቂ ምክንያት አትተዉ። የሴት ልጅን ቀልብ ጠብቁ፤ ይህ ከአላህ የተሰጣችሁ አደራ ነው። © @to2success

  • " አንድ ባሪያ እስልምናን ከመሰጠት ቀጥሎ ጥሩ ወንድም እንደማግኘት ትልቅ ነገር የለም። አንዳችሁ ጥሩ ወዳጅ ማግኘት ከቻለ አጥብቆ ይያዘው። " ዑመር (ረ.ዐ) @to2success

  • አላህ ሆይ ! ለምኞታችን ስንል ያንተን ፈቃድና ትዕዛዝ ከመተላለፍ ጠበቀን ! © @to2success

  • ከማህበራዊ ሚዲያ እብደትና ሱስ ስታገግም... በርካቶች ቀድመውህ የራቀ ጉዞ እንደተጓዙ ታያለህ። አንደኛው ቁርዓን ሲሃፍዝ፣ ሌላው መሠረታዊ የእስልምና እውቀቶችንና ልዩ ልዩ ጥበቦችን ሲቀስም አንተ ግን ስልክህ ላይ እንደተደፋህ ጊዜህ በከንቱ ያልፋል፤ ዕድሜህ ሲነጉድ እንኳ አይሰማህም። በአንተና በመቃብርህ መካከል ግን የቀረችው አንዲት እርምጃ ብቻ ልትሆን ትችላለች! © @to2success

  • የወደፊቱን እያሰቡ መጨነቅ ተገቢ አይደለም። ስለ ወደፊታችን ስለ ሲሳያችን በአላህ እጅ ያለ ጉዳይ በመሆኑ እኛን ከዚያ በላይ ሊያሳስበንና ሊያስጨንቀን የሚገባው ጉዳይ ስለ ተፈጠርንበት ትልቁ አላማና አላህን ስለ መገዛት፣ የርሱን ሀቅ ስለ መወጣት ነው። ሌላው በአላህ እጅ ያለ ነው!!

  • አላህ ልቡን በአሳባቦች ያንጠለጠለን ሰው ለሰበቡ ይተወዋል ወደ አላህ ልቡን ያንጠለጠለ ግን ሰበቡንም ያገራለታል!! @to2success

  • ሀቅ!! ወደ ቁርአን እንመለስ!!

  • ከ 25-30 እድሜ ያላችሁ ወጣቶች ይህ ነገር እውነት ነው?!! እስቲ አንብቡት ይህ የእድሜ ክልል እውነተኛ መፈተና የሚጀመርበትና ለትላልቅ ሀላፊነት ዝግጅት የሚደረግበት ነው ይላል!! ከምንግዚውም በላይ ወድቆ መነሳት የሚታይበትና ለቀጣይ ህይወት መሰረት የሚጣልበት ግዜ ነው የሚል ነው!! @to2success

  • የሚወድ ልብ ያላችሁ፣ ሰውን ለመውደድም የማትቸጋገሩ፣ ቀልባችሁ ንፁህ የሆነ፣ ውስጣችሁ ጥላቻ የሌለ ሁሉ እንኳን ደስስስስ አላችሁ ። "ሙእሚን የሚወድም የሚወድድም/ በቀላሉ የሚለምድም የሚለመድም ነው። " ብለዋል ነቢያችን ሰ.ዐ.ወ. መውደድ ወጪ አያስወጣም፣ አያለፋም። የሰውን ድካም የምትጋሩ፣ ሸክማቸውን የምታቀሉ፣ የቤት ሥራዎቻቸውን የምትካፈሉ፣ የማትከብዱ የማታካብዱ ቀለል ያለ ተግባቢ ሰው ሁኑ ይላል እስልምናችን። የጀነት መንገዱም ይኸው ነው። ©ABX @to2success

  • ኢስላም በማስመሰል ሳይሆን በመሆን የሚኖር እምነት ነው። በየቦታውና በየሚዲያው ኢስላም እንዲህ ነው ከምንለው በላይ ተግባራችን የበለጠ ሰዎች ዘንድ መልዕክት አለው። ትልቁ እውቀትም በተግባር የተደገፈ እውቀት ነው። ለሰዎች የምናስተምረውና የምናውራው የምንኖረውና ተግባራችንን የሚቃረን ከሆነ አስተምህሮታችን ብዙም ፍሬያማ መሆን አይችልም። ኢስላምን ከማውራት በላይ እንኑረው!! @to2success

  • без подписи

  • "ለሁሉም ነገር አላህ አለ" ይላሉ እናቶቻችን። አዎ ለሁሉም ነገር አላህ አለ። አላህ ለሁሉም ነገራችን በቂ ነው። አንዳንድ ጉዳዮቻችንን ሰዎች መረዳት ቢከብዳቸውም አላህ ግን አዋቂ ነው እርሱ አለ። @to2success

  • A little more Sabr, your happiness will come soon Insha’Allah. ትንሽ መታገስ ለትልቅ ድል ያጫል እና ታገስ!! @to2success