Mekin Mohammed | መኪን ሙሀመድ
Статистикаትውልድን የመቅረፅ ፤ የአረዳድ አቅጣጫን የማስተካከል ፤ ሀሳብን የማንገስና የተዛቡ አመለካከቶችን የማረም ግብ ያነገበና እውነተኛ ችግሮቻችንን በመንቀስ መፍትሄ-ወለድ ሰው ለመፍጠር ያለመ ጉዞ......
- Последний пост
- 28 июн.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
Huge congratulations to all my brothers and sisters who graduated from AAU yesterday! 🎓, So proud of everyone’s hard work! A special shoutout to two of my brothers who absolutely crushed it: Salman Ali: My visionary brother, who graduated in Software Engineering with great distinction! We’ve planned so much together, and this is just your first major milestone. The future is ours, habibi. Arefat Mohammed: My brilliant co-founder, who graduated as the top scorer from Lideta Gbi! 🏆 Your commitment to ihsan in everything you do inspires me, and it shows. Having you by my side means our venture is destined for greatness inshallah. proud of you All.
ደሞ ሳልነግራችሁ… አቦ አላህ ሀጅ ይውሰደንና ለተፋኡሉ ሰሞነ ሀጅ የተሰኘና ሀጅ እስኪጠናቀቅ የሚቆይ ፕሮግራም ሚንበር ቲቪ ላይ እየተላለፈ ይገኛል። ሰኞ እሮብ ጁምዐ ማታ 3:00 አየር ላይ ይውላል። ተጋበዙልኝ…
ሆኖም ዛሬ ደቡብ አፍሪካ ያሳለፈችውን የመከራ ታሪክ ባለመርሳትና ለጊዜያዊ ጥቅም ባለመታለል ዋጋ በመክፈል ጭምር በእስራኤል ላይ በዓለም አቀፉ ፍርድ ቤት የጀመረችውን የዘር ማጥፋት (Genocide) ክስ ኢትዮጵያ መቀላቀል ቢያቅታት እንኳ በጄኔቫው መድረክ ድጋፍ መስጠት አለመቻሏ ፣ ያንን ታላቅ የፓን አፍሪካዊነት መሪነትና ለተገፉ ወገኖች የመቆም የታሪክ ባለቤትነት የሚያሳንስ እጅግ አሳዛኝ ክስተት ሆኖ አግኝቼዋለሁ። የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየምን የመሰለ ታላቅ የነፃነት ምልክት ያስገነባ መሪ፣ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ መድረክ ለፍትህ የተሟገተች ሀገርን የሚመራና ከመሬቴ አታፈናቅሉኝ በሚል ተቃውሞ መነሻነት በመጣ ለውጥ ወደ ሥልጣን የመጣ መሪ፤ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚፈጸምን የመሬት ነጠቃ፣የማፈናቀልና የመሬት ወረራ የመቃወም ታሪካዊና ሞራላዊ ግዴታ አለበት ብዬ አምናለሁ። ስለሆነም፣ ኢትዮጵያ ከነጃሺ ዘመን ጀምሮ ለተገፉ ወገኖች ከለላና አጋር የመሆን፣ የእውነት ድምፅ ሆኖ የመቆምና የፍትህ ፋና ወጊነት ታሪኳን በዓለም መድረክ እንድትቀጥል፤ አስተዳደርዎ የወሰደውን ይህንን አቋም በድጋሚ እንዲመረምረውና አስፈላጊውን የታሪክ እርምት እንዲያደርግ በታላቅ አክብሮትና በዜግነት ኩራት እጠይቃለሁ። አሕመዲን ጀበል
ይህንን አቤቱታ በግንባር ቀደምትነት የመሩት ሊቀመንበሩ ኤርዊን ክራፍት (Erwin Kraft)፣ ዋና አራማጁ ኸርማን ፉርንበርግ (Hermann Fuernberg) እና ማሪ ጊንስበርግ (Marie Ginsberg) ሲሆኑ፣ ጥያቄያቸውን ለማስፈጸም እንደ ጆን ደብሊው ፔህሌ (John W. Pehle) ካሉ የአሜሪካ የጦርነት ስደተኞች ቦርድ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር የቅርብ ግንኙነት ነበራቸው። በቀረበው ዕቅድ መሠረት ከ60,000 እስከ 70,000 ስኩዌር ማይል የሚሸፍን ሰፊ የሐረርጌ መሬት ለአይሁድ ሰፋሪዎች እንዲሰጥና ግዛቱ የራሱ ሕገ-መንግሥትና በእንግሊዝኛ የሚመራ አስተዳደር እንዲኖረው የሚጠይቅ ነበር። ይህ የሰፈራ ዕቅድ ሐረርጌን ለኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሉዓላዊነት በስም አስገዝቶ፣ በውስጥ ግን በሕዝብ በሚመረጥ ምክር ቤት የምትመራና በብሪቲሽ ሶማሊላንድ በኩል በበርበራና ዘይላ ወደቦች የባሕር መውጫ እንዲኖራት የታቀደ ራስ-ገዝ ግዛት ለመመሥረት ያለመ ነበር። ሐረርጌ ለዚህ ፕሮጀክት የተመረጠችው የአየር ንብረቷ ለአውሮፓውያን ሰፋሪዎች ምቹ በመሆኑ፣ ምድሪቱ "ሰው ያልሰፈረባት" (sparsely populated) ናት ተብሎ በመታመኑና በዞሀር (Zohar) መጽሐፍ "የአይሁድ ስደት በኩሽ ምድር ያበቃል" ተብሎ ስለተጻፈ ሲሆን፣ ዕቅዱን ያቀረቡት ወገኖችም ንጉሠ ነገሥቱ የአሁድ ዘር ነኝ(ዘእምነ ነገደ ይሁዳ) ይኑ ስለነበር ለአይሁድ ሰፋሪዎቹ በጎ አመለካከት ይኖራቸዋል የሚል ጽኑ እምነት ነበራቸው። በተጨማሪም ግዛቱ ለእህል፣ ለፍራፍሬና ለአትክልት ምርቶች አመቺ መሆኑ ተጠቅሶ፣ እያንዳንዱ ሰፋሪ ለንጉሠ ነገሥቱ ታማኝነት እንዲምልና ግዛቱ የተወሰነ የግብር ድርሻ እንዲከፍል ሐሳብ ቀርቦ ነበር። የኢትዮጵያ መንግሥት እ.አ.አ. በሐምሌ 4 ቀን 1944 በሰጠው ይፋዊ ምላሽ ይህንን ጥያቄ ሙሉ በሙሉ ውድቅ በማድረግ የሐረርጌን ሕዝብ ከታላቅ የታሪክ አደጋ ታድጓል። የአጼ ኃይለ ሥላሴ መንግሥት ምላሽ ሲሰጥ፣ ሀገሪቱ በጣሊያን ወረራና ውድመት ምክንያት በሺዎች የሚቆጠሩ የገዛ ዜጎቿ መጠለያ አጥተው ባለበት ሁኔታ፣ አንድን ሙሉ ጠቅላይ ግዛት ለስደተኛ ቡድን አሳልፎ መስጠት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ አደጋ ላይ የሚጥልና የማይቻል ተግባር እንደሆነ በግልጽ አስታውቋል። ንጉሠ ነገሥቱም ፕሮጀክቱና ለፕሮጀክቱ የተሰጠው ስያሜ ጭምር ሙሉ በሙሉ እንዲተውና እንዲቆም ጥብቅ ትእዛዝ ማስተላለፋቸው፣ ዛሬ በሐረርጌ ምድር ላይ ሊከሰት ይችል የነበረውን መጠነ-ሰፊ መፈናቀል፣ የዘር ፍጅትና የማንነት መጥፋት አደጋ የቀለበሰ ታላቅ ብሔራዊ ውሳኔ ሆኖ በታሪክ ተመዝግቧል። ይህ በሆነ ከአራት ዓመታት በኋላ የፍልስጤም ምድር በወረራ ተይዞ እ አ አ በ1948 የአይሁድ ግዛት በመሬታቸው ላይ ተመሰረተ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ፊሊስጤሞች በገዛ ሀገራቸው መሬታቸው የመሬት ወረራ፥ መፈናቀልና ግድያ እያስተገዱ ይገኛሉ። ዛሬ በፍልስጤም ምድር ላይ የሚታየውን የሰፈራ ወረራና የዘር ማጥፋት ድርጊት ያ የሰፈራ ዕቅድ በወቅቱ ውድቅ ባይደረግ ኖሮ፣ ዛሬ በጋዛና በዌስት ባንክ በፍልስጤማውን ላይ የሚፈጸመው ጭፍጨፋ በሐረርጌ ኦሮሞ አርሶ አደሮች፥ በሱማሌና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ላይ አየተፈጸመ ይገኝ ነበር። ፍልስጤማውያን በነጻነት እየነሮ ሰቆቃው የእኛ የኢትዮጵያውያን እጣ ፈንታ፣ የሰሞኑን በጄኔቫ የተካሄደው ስብሰባ በቀጥታ ስለ እኛ ይሆን ነበር። በመሆኑም በጄኔቫው ጉባዔ ላይ ሀገራችን የሰፈራ ግንባታን የሚቃወመውን ውሳኔ "አይ" (No) ስትል፣ በታሪክ መነፅር ግን የገዛ መሬታችን የሆነችውን ሐረርጌን ለባዕድ ወረራ አሳልፎ ለመስጠት የሚደረግን ጥረት "አልቃወምም" እንደማለት ይቆጠራል። የገዛ መሬታችን በባዕዳን ሲወረርና ሕዝባችን ሲፈናቀል ሌሎች ሀገራት በዝምታ ቢያልፉት የሚሰማንን ስሜት ማሰብ፣ ዛሬ ለወሰድነው አቋም ትልቅ የታሪክ እርምትና የሞራል ማነጻጸሪያ ሊሆነን ይገባል። የ"አባ ለፉማ" እሴት እና የጄኔቫው ድምፅ አሰጣጥ የታሪክ እርምት ጥሪ ♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦♦ ክቡር ጠቅላይ ሚ/ር እርስዎን ወደ አመራርነት ያመጣዎት ታሪካዊ ለውጥ መሠረቱ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የመብት ንቅናቄ (ድምፃችን ይሰማ) ተጀምሮ፣ ለዓመታት ዘልቆ ተቃውሞ የበረታበት የኢህአዴግ መንግስት በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በሚል የነደፈው እቅድ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚኖሩ የኦሮሞ ገበሬዎችን ከገዛ መሬታቸው ያፈናቅላል በሚል በተነሳው የኦሮሞ ተቃውሞ (Oromo Protest) ነበር። የኦሮሞ ወጣቶች “Lafti keenya lafee keenya!” (መሬታችን አጥንታችን ነው!) በሚል መሪ ቃል በጽኑ በመቃወማቸው የተቀጣጠለው ተቃውሞ ወደ ሌሎች አከባዎች ተስፍቶ በሀገራችን የመንግሥት ለውጥ እንዲመጣ ምክንያት ሆኗል። በመሆኑም በማስተር ፕላን ስም የመሬት ወረራ ሊደረግ ነው በሚል ተቃውሞ መነሻነት በፈነዳ ሕዝባዊ ተቃውሞ ወደ ሥልጣን የመጣ መሪ፣ ዛሬ በሌላ ሕዝብ መሬት ላይ የሚፈጸመውን የሰፈራ ወረራ በጄኔቫ መድረክ "ተቃውሞን አለማሳየት" እጅግ የሚቆረቁር የታሪክ ተቃርኖ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። እርስዎ ከኦሮሞ ማህበረሰብ የወጡ መሪ እንደመሆንዎ፣ የመሬት ባለቤትነት ጥያቄ በኦሮሞ ሕዝብ ያለውን የ"አባ ለፉማ" (Abbaa lafummaa)/ የመሬት ባለቤትነት ክብርና የሞት ሽረት ትግል ጠንቅቀው ያውቃሉ። በሌሎች መሬት ላይ የሰፈራ ግንባታ ማለት ቀጥተኛ የመሬት ነጠቃና ማንነትን የማጥፋት ሂደት በመሆኑ፣ የመሬት ባለቤትነት መብታችን ተከብሮና ማንነታችን ጸንቶ እንድንኖር የተደረገው ትግል በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ ለተገፉ ወገኖች ድምፅ እንድንሆን የሚያስገድደን የ"አባ ለፉማ"(Abbaa lafummaa)/ የመሬት ባለቤትነት ታሪክ ቃል-ኪዳን ሊሆነን ይገባል። ማጠቃለያ 🎒🎒🎒🎒 ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ፤ በዚህ ውስብስብ ጂኦ-ፖለቲካዊና ወቅታዊ የዓለም አቀፍ ሁኔታ ውስጥ ሀገርን በጥበብ መምራት፥ ጥቅሟን ማስጠበቅ እና በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ እሴትን ያማከለ እና ጥቅምን የራስን ጥቅም ሚዛን የጠበቀ ጽኑ አቋም መያዝ ከፍተኛ ጥንቃቄን የሚጠይቅ መሆኑን አረዳለሁ። በአስተዳደርዎ ላይ ልዩ ልዩ ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎች ቢኖሩ እንኳ ከአፍሪካ ሕብረት የቆየና የጸና አቋም ጋር ፍጹም የሚቃረንና ወደ ጽንፍ የሄደ፥ ከብዙሃን በተራቃኒ ሀገሬን ከቼክ ሪፐብሊክና ከሰሜን ሜቀዶኒያ ጋር ብቻ በመቆም የ"ተቃውሞ" (No) ውስጥ መግባት ግን እጅግ አሳዛኝ የታሪክ ክስተት ነው። ቢያንስ ቢያንስ እንደው በማናውቀው ምክንያት በዚያ ሰሞን በይፋ መደገፉ መዘዙ ቢያይል እንኳ ለጊዜው በድምፅ አሰጣጡ ላይ "ድምፀ ተዓቅቦ" (Abstain) ማድረግ ወይም በስብሰባው ላይ ባለመገኘት ዲፕሎማሲያዊ ሚዛኑን መጠበቅ ይቻል ነበር፤ ሆኖም አሁን የታየው ከድጋፍና ከአጋርነት ወደ ግልጽ ተቃውሞ የተደረገው ሽግግር፣ ሀገራችን ለዘመናት ለተገፉ ወገኖች የነበራትን የሞራል መሪነት ዋጋ ያሳነሰና እጅግ የሚቆረቁር ውሳኔ ነው። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ሆይ፤ 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 ኢትዮጵያ በአፓርታይድ ትግል ወቅት ለኔልሰን ማንዴላ የወታደራዊ ስልጠና በመስጠት፣ የኢትዮጵያ የጉዞ ፓስፖርትና የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ ለደቡብ አፍሪካ ነፃነት የነበራት ግንባር ቀደም ሚና የሀገራችን የታሪክ ኩራት ነው።
የሐረርጌው የዘር ፍጅትና የጄኔቫው ተቃውሞ 💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥💥 ከአሕመዲን ጀበል 🔴🔴🔴🔴🔴🔴 ይድረስ ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) 💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢💢 ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር፤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ያላት ክብር የሚመነጨው ለዘመናት ካካበተችው የነፃነት ታሪክ እና ለፍትህ ከምትሰጠው ጽኑ ድምፅ እንደሆነ አምናለሁ። ሆኖም በቅርቡ በጄኔቫ በተካሄደው 61ኛው የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት (UNHRC) መደበኛ ስብሰባ ላይ፣ በእስራኤል ሕገ-ወጥ የሰፈራ ግንባታና በወረራ በተያዙ የፍልስጤም ግዛቶች ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን የሚኮንነው የውሳኔ ሐሳብ (Resolution A/HRC/61/L.36) ቀርቦ ነበር። በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ 34 ሀገራት ለፍትህና ለዓለም አቀፍ ሕግ የበላይነት ድምፃቸውን ሲሰጡ፣ የእርስዎ አስተዳደር ግን ይህንን የሰፈራ ግንባታ የሚቃወመውን ውሳኔ ባለመደገፍ "አልቃወምም" (No) የሚል ድምፅ መርጧል። ይህ በኢትዮጵያ ስም የተሰጠው ድምፅ ከሀገራችን ታሪካዊ ስነ-ልቦና፣ ከዲፕሎማሲያዊ እሴቶቻችን እና ከገዛ ሕዝባችን ቀኝ አልገዛም በሚል ሲፋለም ካሳለፋቸው የመከራ ጋር ፍጹም የሚጋጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ስለሆነም፣ ይህንን ውሳኔ በሚከተሉት ታሪካዊ፣ ሞራላዊና ፖለቲካዊ መሠረቶች ላይ ተመርኩዤ እንደ አንድ ዜጋ እንዲታረም በታላቅ አክብሮት መጠየቅ እወዳለሁ። የአድዋ ውርስ፣ የመታሰቢያ ሙዚየሙ ኩራትና የጄኔቫው ድምፅ አሰጣጥ የታሪክ ተቃርኖ ✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅✅ የኢትዮጵያዊ ማንነታችንን ካጸኑ መሠረቶች አንዱ በአድዋ ፍልሚያ ሜዳ የጸናው 'ለእውነት መቆም' እና 'ወረራን በጽኑ መቃወም' የሚለው የቆየ እሴታችን እንደሆነ አምናለሁ። ይህ በ1896 አባቶቻችን ያስመዘገቡት የአድዋ ድል ለእኔ የአንድ ሀገር ስኬት ብቻ ሳይሆን፣ የመላው ጥቁር ሕዝቦችና በዓለም ዙሪያ የሚገኙ የተገፉ ወገኖች ሁሉ የነፃነት ፋና እንደሆነ ይሰማኛል። አዲስ አበባም የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫ እንድትሆን የተመረጠችው በአድዋ ላይ ከቀኝ ገዢዋ ጣሊያን ጋር በመፋለም ለነጻነቷ ባስመዘገበችው አነቃቂ ድልና ለሌሎች ሕዝቦች ለነፃነትና ለፍትህ ባላት ጽኑ አቋም መሆኑን ጠንቅቄ አውቃለሁ፤ ሆኖም በጄኔቫው የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጉባዔ ላይ፣ በእስራኤል የሰፈራ ግንባታ ላይ የቀረበውንና ድርጊቱ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ሕገ-ወጥ መሆኑን የሚያረጋግጠውን የውሳኔ ሃሳብ ሀገሬ ለመደገፍ ፈቃደኛ አለመሆኗ እጅግ አሳዝኖኛል። የአድዋ ድልን ለማሰብና የጀግኖች አባቶቻችንን ገድል በትውልዱ ለማስረጽ ተምሳሌትነትን ለማጉላት የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም በእርስዎ መሪነት በአዲስ አበባ እምብርት ፒያሳ ላይ "የአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም" መገንባትና ለነጻነት ትግል ከፍያለ ስፈራ መሰጠቱ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በአዎንታዊ ጎኑ ከሚያዩነት ነኝ። በተለይ «አድዋ ዜሮ ዜሮ» የሚል ስያሜ መያዙ ደግሞ የርቀት መለኪያ ጅማሮ ስፍራ ለሀገራችን እና ለህዝችን ነጻነት በጋራ ዋጋ የተከፈለበት ስፍራ መሆኑ ልዩ ትርገም አለው። ይህ ግዙፍ ማዕከል የጀግኖች አርበኞች ታሪክ በዘመናዊ መንገድ የሚዘክር የኪነ-ሕንጻ ጥበብ ውጤት በመሆኑ እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው። በተለይም ልዩ ልዩ የዓለም ሀገራት መሪዎችና ከፍተኛ ልዑካን ይህንን ማዕከል ሲጎበኙ ስመለከት፣ የአድዋን ትርጉም ለዓለም በማሳወቅዎና የድል ታሪካችንን በክብር ለማስተዋወቅዎ እንደ ዜጋ ታላቅ የባለቤትነት ስሜት ይሰማኛል። ይህ ሙዚየም ለኔ ለነጻነታችንን ዋጋ ለመፈክል ወደ ኋላ የማይል ማንነት እንዳለን በድንጋይ ላይ የታተመበት እና ለዓለም ሁሉ ድምፃችንን ከፍ አድርገን የምናሳይበት ታላቅ መድረክ ነው። እንዲህ ያለውን ታላቅ ማዕከል ያስገነባ መሪ የአድዋ ድልን መሠረታዊ ትርጉም ከማንም በላይ ይገነዘባል ብዬ እገምታለሁ። ሆኖም ግን፣ በጄኔቫው ድምፅ አሰጣጥ የታየው አቋም ግን ካገኘሁት ብሔራዊ ኩራት ጋር የሚጋጭ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ለእኔ የአድዋ ትርጉም "መሬቴን አላስካም፤ ነፃነቴንም አላስደፍም" የሚል ጽኑ የሉዓላዊነት እና የፍትህ መልዕክት ነው። በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ የፍልስጤም ህዝብ የዘር ማጽዳት እየተካሄደበት በሚገኝበት የታሪክ ወቅት ላይ መሬቱን በሰፈራ የመንጠቅ ተግባር በሚወገዝበት መድረክ ሀገሬ ተቃውሞን አለማሳየቷ፣ ካስገነቡት የአድዋ መታሰቢያ ሙዚየም መንፈስ ጋር ፍጹም የሚቃረን ሆኖ ይታየኛል። 34 ሀገራት ለፍትህ ድጋፋቸውን ሲሰጡ፣ ሀገሬ ከሁለት ሀገራት ጋር ብቻ ተነጥላ በወረራ ተግባር ላይ ተቃውሞዋን አለመግለጿ፣ የተገነባውን ታሪካዊ ስም የሚሸረሽርና ኢትዮጵያ ለዘመናት ለተገፉ ወገኖች የነበራትን የሞራል መሪነት ዋጋ የሚያሳጣ የታሪክ ግድፈት እንደሆነ ይሰማኛል። ሊግ ኦፍ ኔሽንስ የጋራ ደህንነት መርህ እና የጄኔቫው ድምፅ አሰጣጥ ተቃርኖ 📮📮📮📮📮📮📮📮📮📮📮📮📮 ኢትዮጵያ በ1935 በፋሺስት ኢጣልያ ወረራ ሲፈጸምባትና ሉዓላዊነቷ በኃይል ሲደፈር፣ በሊግ ኦፍ ኔሽንስ መድረክ በመገኘት ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ያቀረበችው የፍትህ ጥያቄ የሀገራችን የዲፕሎማሲ ታላቅ መሠረት እንደሆነ አምናለሁ። በወቅቱ ንጉሠ ነገሥቱ 'ዛሬ በእኛ ላይ የደረሰው ነገ በእናንተ ላይ ይደርሳል' በማለት ያስጠነቀቁበት የ'ጋራ ደህንነት' (Collective Security) መርህ፣ ማንኛውንም ዓይነት ወረራንና የመሬት ነጠቃን በጽኑ የሚቃወም ነበር። ሆኖም በጄኔቫው የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ በፍልስጤም ምድር የሚፈጸመውን ሕገ-ወጥ የሰፈራ ግንባታና ወረራ ለመቃወም ፈቃደኛ አለመሆን ግን፣ ሀገራችን በፋሺስት ወረራ ወቅት የተሟገተችለትን ታሪካዊ እሴትና የሉዓላዊነት መርህ የሚንድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። ይህንን የውሳኔ ሐሳብ ለመደገፍ ፈቃደኛ አለመሆን፣ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ፊት ቀርበው ፋሺስት ኢጣልያ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ግፍና ወረራ ሲያጋልጡ የነበረውን የሞራል ልዕልና የሚቃረንና ሀገራችን ለዘመናት ለፍትህ የነበራትን ጽኑ አቋም የሚሸረሽር ነው። በወቅቱ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በወራሪዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድና ለተገፉ ወገኖች እንዲቆም ስትሟገት የነበረው ያ የሞራል መሠረት፣ ዛሬ በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኝ የፍልስጤም ሕዝብ የእውነት ድምፅ እንድንሆን ታሪክ ያስገድደናል። ከሐረርጌ እስከ ጋዛ፡ የአይሁድ ሰፈራ ዕቅድ 🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴 የአይሁድ ሀገር ለመመስረት ታጭተው ከነበሩት ስፍራዎች መካከል አንዷ የኛዋ ሐረርጌ ነበረች። ይህ እቅድ እውን ሆኖ ቢሆን ኖሮ ዛሬ በፍልስጤም ምድር ላይ የምናየው የመሬት ወረራ፣ የሰፈራ፥ የመፈናቀልና የጅምላ ፍጅት ሂደት በኛው ሀገር በሀረርጌና አከባቢው ይሆን ነበር። ታሪኩ እንዲህ ነበር። እ.አ.አ. በጥር 26 ቀን 1944 "የሐረር ምክር ቤት" (Harrar Council) በሚል ስያሜ በኒው ዮርክ ከተማ የተደራጁ ከአውሮፓ የመጡ አይሁዳውያን በሐረርጌ ጠቅላይ ግዛት ውስጥ ራስ-ገዝ የሆነ የአይሁድ ግዛት ለመመሥረት ለንጉሠ ነገሥቱ መንግስት ጥያቄ አቅርበው ነበር።
без подписи
Eid Mubarak! May your heart be filled with joy and your home with laughter. Bewide Technologies Be Wide - Be Wise @BeWide_Tech
ሰዒድ ኢብኑ ዘይድ : ያልተነገረለት ኮኮብ በሚንበር ቲቪ ከሚተላለፈው የአብሮነት በረመዳን 10 መሰናዶ መካከል ከሸኽ መሀመድ ኢብራሂምና ከወንድም ፈድሉ አሊ ጋር በሁለት ክፍል ስለ ታላቁ ሰሀባ ሰዒድ ኢብኑ ዘይድ አወጋግተናል። ተጋበዙልኝ https://youtu.be/D70Eo7LKJuQ?si=mkGkOkx_3PIi9wsO https://youtu.be/IHNHuGvL45U?si=VpkWxR5HnRc_m3Xk
без подписи
ንባብ፣ ስነፅሁፍ፣ ነገረ-ጥበብ ለአንድ ሐገርም ሆነ ማህበረሰብ ትልቅ መሰረት ከሚጥሉ ነገሮች ቀዳሚዎቹ ናቸው። ኢስላምም አስተምህሮቱን መስበክ ሲጀምር 'አንብብ' በሚል መለኮታዊ ትዕዛዝ ነበር። የሐገራችን የንባብ ባህል ደካማ ቢሆንም አሁን ላይ ግን በከፊል መነቃቃት እያሳየ ይገኛል። ለዛሬ በአላህ ፈቃድ የረመዳን ዋዜማ ላይ በወንድማችን ነጃሽ ሸምሱ ተተርጉሞ ለገበያ የቀረበውን መፅሐፍ ይዘንላችሁ መጥተናል። ለወዳጅ ዘመድ በመጋበዝ ንባብን እንድታበረታቱ እንጠይቃለን። መፅሐፉን ለማግኘት በሚከተለው አካውንት አስገብታችሁ Screenshot (Telegram: @nejashi3 or 0913480804) ላኩልን ያሉበት ድረስ እንልካለን። CBE 1000269765236 ነጃሽ ሸምሱ TELEBIRR 0913480804 ወይም በአካል - ቤተል ተቅዋ መስጅድ ፊትለፊት አላሐሺሚ ባቅላቫ ቤት - ጀሞ ሰንሙን ህንፃ 0928562018 - አለምገና ማማ መስጅድ 0901077810 - ጦርሃይሎች ረያን መስጅድ 0913480804 የአንድ መፅሐፍ ዋጋ 450 ብር
https://youtu.be/3bfxHygKBcQ?si=pGZeAY7VFFhvJt3Q https://youtu.be/gGRyAe5_mZ8?si=LEYJb_MJJ-3oyyqO በሚንበር ቲቪ ከሚተላለፈው የአብሮነት በረመዳን 10 መሰናዶ መካከል ከኡስታዝ ካሚል ሸምሱና ከፉአድ በሺር ጋር በሁለት ክፍል ስለ ታላቁ ሰሀባ ዙበይር ኢብኑል አዋም አወጋግተናል። ተጋበዙልኝ
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
አልሀምዱሊላህ ዛሬ የአምስት ትላልቅ መሻይኾቻችን ሞባይል መተግበሪያ ከአፍሪካ ቲቪ ጋር በመተባበር አስመርቀናል። የዕዉቀት ቅርስ ላይ በመሳተፋችን ከፍ ያለ ደስታ ይሰማናል። የተሰሩት መተግበሪያዎች የሸኽ መሀመድዘይን ዘህረዲን ሸኽ መሀመድ ሀሚዲን ሸኽ ኢብራሂም ሲራጅ(ረ.ዐ) ሸኽ ሀሚድ ሙሳ ኡስታዝ መሀመድ ፈረጅ ናቸዉ። ኢንሻአላህ ይህ ጅማሮ ነው። ቀጣይ በሌሎች ስራዎች የምንመጣ ይሆናል።
📢Urgent Openings for Health Professionals and Service Staff 🩺 Nurse (5 Positions) • Bachelor’s Degree or Diploma • Full-time • Junior level 🩺 General Practitioner (GP Doctor) (1 Position) • Bachelor’s Degree in Medicine • Full-time • Junior level ☕ Café Staff (2 Positions) Cook and Server • Full-time • Can work interchangeably in these two positions. 💻 Data Entry Officer (1 Position) • Bachelor’s Degree • Full-time • Junior level • Excellent English (Mandatory) • Arabic language (Preferred +) • Female (Preferred +) 🗂️ Secretary (1 Position) • Bachelor’s Degree or Diploma • Full-time • Junior level • Female (Mandatory) 📊 Accounting & Finance Officer (1 Position) • Bachelor’s Degree in Accounting, Finance, or related field • Full-time • Experienced 🩻 X-Ray Radiographer (1 Position) • Bachelor’s Degree in Radiography or related field • Experienced • Part-time or Full-time 🧾 Receptionist (3 Positions) • Full-time • Junior level • Female (Mandatory) • Good computer skills(Computer Skills Certifications are a plus) 📩 Interested candidates are encouraged to apply by submitting their CV and relevant documents to @Mekin_Mohamed