AASTU Muslims union
Статистикаይህ የቴሌግራም ቻናል ሁሉንም የ አአሳቴዩ ሙስሊም ተማሪዎች የሚመለከት ቻናል ነው። በዚህ ቻናል ኢስላማዊ ትምህርቶች፣ የተለያዩ ዳእዋና ሙሃደራዎች እንዲሁም ጀመዓውን የሚመለከቱ መልእክቶች ይለቀቁበታል። ከዚህ ውጪ ሌላ ቻናል የሌለን መሆኑን እና የትኛውም ከዚህ ቻናል ውጪ የሚለቀቅ ነገር እኛን እንደማይወክል እናሳስባለን። ለማንኛውም አስተያየት @abdua00 @abduw99
- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 200
- 1/48двое суток
- 229
- 1/72трое суток
- 247
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
صلُّوا على غيث القلوب وريِّها خيرُ الخلائقِ رحمة الرحمنﷺ اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ
💍💍ሰበር የኒካህ ዜና 💍💍 بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في الخير በጀማዓችን ምክትል አሚር ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ውዱ ወንድማችን ፋሩቅ በህሩ ከእህታችን ሀድራ ኑሩ ጋር ኒካህ በማሰር እነሆ በአላህ ፈቃድ አዲስ የህይወት ምዕራፍ ጀምረዋል። ወንድማችን ፋሩቅ ጀማዓችንን በትጋትና በቅንነት ሲያገለግል የቆየ እንደመሆኑ አላህ (ሱ.ወ) ያደረገውን ጥረት እንደ…
ዜና ኒካህ💍💍💍💍 بَارَكَ الله لَكُما، وَبَارَكَ عَلَيْكُما، وَجَمَعَ بَيْنَكُمَا فِي خَيْر 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 የጀመዐችን በ Da'wah and Qira'at sector በኩል የሹራ አባል የሆነችው አሁንም አብሮነቷ ያልተለየን ውዷ እህታችን ሪም አቡልመሓሲን ኒካህ አስራለች :: 💍💍💍 ኒካሓችሁ የተባረከ ለሙእሚኖች ተምሳሌት የምትሆኑበት ፍቅራችሁም እስከ ወዲያኛው የሚዘልቅ ያደርግላችሁ ዘንድ በጥንዶች መካከል ውዴታና እዝነት ያደረገዉ ጌታችን አላህን እንማፀነዋለን። ውድ የኣ.ሳ.ቴ.ዩ ሙስሊም ተማሪዎች እና የቻናላችን ተከታዩች መልካም ምኞታችሁን እየገለፆችሁላቸዉ በዱአም እንዳትረሷቸዉ መልእክታችን ነው::
💍💍ሰበር የኒካህ ዜና 💍💍 بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في الخير በጀማዓችን ምክትል አሚር ሆኖ ሲያገለግል የነበረው ውዱ ወንድማችን ፋሩቅ በህሩ ከእህታችን ሀድራ ኑሩ ጋር ኒካህ በማሰር እነሆ በአላህ ፈቃድ አዲስ የህይወት ምዕራፍ ጀምረዋል። ወንድማችን ፋሩቅ ጀማዓችንን በትጋትና በቅንነት ሲያገለግል የቆየ እንደመሆኑ አላህ (ሱ.ወ) ያደረገውን ጥረት እንደ መልካም ስራ አድርጎ እንዲቀበለውና አዲስ በጀመረው ትዳር ላይም በረካን ፍቅርንና እዝነትን እንዲያፈስስለት እንመኛለን። በጥንዶች መካከል ፍቅርን የሰጠው አላህ ኒካሃችሁን የተባረከ ለሌሎች መልካም አርአያ የምትሆኑበትና ፍቅራችሁም እስከ ጀነት የሚዘልቅ ያድርግላችሁ።
የሌላ እምነት ተከታይ ጥምጣም ሲለብስ ዝም፤ ሙስሊም ተማሪ ጥምጣም ሲለብስ ሴኩላሪዝምን ጣስክ ሲባል አስተውለናል። የሌላ እምነት ተከታይ እምነታቸውን የሚገልፅ ምልክት ሲያደርጉ የሐይማኖት ነፃነት፤ ሙስሊም ተማሪዎች ሒጃብ ሲለብሱ ሴኩላሪዝምን ጣሳችሁ ተብሎ ነበር። የስሁር ምግብ ይቅረብልን ሲባል እንኳ ሴኩላሪዝምን ይጥሳል የተባለበት ጊዜ ነበር። ይህ ሴኩላሪዝም ምንድን ነው? ሴኩላሪዝምስ ምንድን ነው? መብቶቻችንስ ምንድን ናቸው? ቀጠሯችንን ምሽት 3:00 አብረን እናድርግ። መልዕክቱም ለምናውቀው ሰው ሁሉም እናድርስ። @aaumsu
﴿إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ صَلُّواْ عَلَيْهِ وَسَلِّمُواْ تَسْلِيمًا ﴾ قَالَ ﷺ: «مَنْ صَلَّ عَلَيَّ صَلاةً صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشَراً» በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ 🍃🍂 ሱረቱል ካህፋንም መቅራት አንርሳ መልካም ጁምኣ ‼
~ከ ሁለት ዓመት በፊት በ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ(AASTU) ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪዎች የተደረገ ምክር ቢጤ! ወንድም አቡ ሱፍያን
ታላቁ የቲክቶክ መድረክ ደረሰ _ ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ ! ! ! ስለኒቃብ መጠየቅ በምርቃት ቀን እስከ ማሳሰር ከመድረሱ በፊት ጀምሮ ስላለው የሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥሰት ታሪካዊ ዳራ በሰፊው ይዳሰሳል። ሕገ- መንግስቱን ጥሰው ስለሚጥሱት መብት ሕጋዊ ቦታ በሰፊው ይተነተናል። ከእኛ ስለሚጠበቀው ነገርም በደንቡን ውይይት ይደረጋል። ሙባረክ አደም፦ በድምፃችን ይሰማ የመብት ትግል እንቅስቃሴ ፈርቀዳጅ ታጋይ፤ አክቲቪስት፤ ቲክቶከር፤ ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብዕና፤ የሂባ ፋውንዴሽን መስራች ነው። ፕሮግራማችንን በመድረክ መሪነት የሚያስተናብርልን ይሆናል። ሙስጠፋ ሺፋ፦በድምፃችን ይሰማ የመብት ትግል እንቅስቃሴ ወቅት ለታሰሩት ጠበቃ ሆኖ አገልግሏል፤ አሁንም በጥብቃና ሙያው አንቱታን ካተረፉ ባለሙያዎች መካከል ነው። ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥያቄ ሕጋዊ መሠረት ያብራራልናል። የሕያ ኢብኑ ኑሕ፦የንፅፅር ትምህርት መምህር፤ የሒዳያ ኢስላማዊ ማህበር መስራች እንዲሁም ተፅዕኖ ፈጣሪ ስብዕና ነው። ስለሙስሊም ተማሪዎች የመብት ጥሰት ታሪካዊ ዳራ ያብራራልናል። ሁሴን ዩሱፍ፦የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ፀሐፊ ሲሆን ከማን ምን ይጠበቃል የሚለውን በዝርዝር ያስቀምጣል። መቅረት አይታሰብም። ጀመዓዎች በቻናሎቻችሁ ላይ አሰራጩት። ሁሉም ለሁሉም ያድርስ። በአንድነት በአንድ መድረክ ተሰባስበን ስለመብቶቻችን እውቀትን እንጨብጥ። 🗓 ቀን፡ ሰኞ፣ ሰኔ 22 (Monday, 29 June) ⏰ ሰዓት፡ ከምሽቱ 03፡00 ሰዓት እውቀትን መፈለግ መብት ነው፤ እምነትንም በክብር መተግበር እንዲሁ! የቲክቶክ ገፃችንን Follow በማድረግ ዝግጅቱን ይጠብቁ፦ https://www.tiktok.com/@aaumsu ጥያቄ አለን _ ፍትሐዊ መልስ እስኪመጣ ! ! ! @aaumsu
በዛሬው ቀን ከአዲስ አባባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለምትመረቁ ጓደኞቼ እንዲሁም ወንድምና እህቶቼ እንኳን ደስ አላችሁ! 🎓🎉 ለኣ.ሳ.ቴ.ዩ ጀማዓ መቼም የማይረሳ አሻራን በመጣል ከናንተ በታች ላሉ ታናናሽ እህትና ወንድሞቻችሁ አርአያ መሆን ችላቿልና አሏህ መልካም ተግባራችሁን ዘውታሪ ያድርግላችሁ! ✨ ብዙ ለፍታቿልና ከእንግዲህ በሗላ ያለውንም ረበና አግርቶላችሁ ሀገርና ወገንን የምትጠቅሙ ያድርጋችሁ 🇪🇹🚀 مبارك التخرج! 🎓🎉 أسأل الله العظيم أن يفتح لكم أبواب الرزق والتوفيق في حياتكم المهنية القادمة، وجعل الله كل جهد بذلتموه في ميزان حسناتكم وأنار دربكم، ونفع بعلمكم وابتكاراتكم البلاد والعباد. 🤲✨ اخوكم عبد الوكيل
ሰሞኑን ዛሬን ጨምሮ ከተለያዪ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂ ለሆናችሁ ሙስሊም ወንድምና እህቶቼ እንኳንም ለዚህ የልፋታችሁን ውጤትና ደስታ በከፊል ለምታዩበት ቀን በሰላም አደረሳችሁ! 🎓✨ እንኳንም ደስ አላችሁ! 🎉 ባገኛችሁት እውቀትና ተሞክሮ ሙስሊሙን ኡማ የምትጠቅሙ፣ ዳግማዊ ነፃነቱና ልእልናውንም የምታውጁ አሏህ ያድርጋችሁ! 🤲🌟 Abdulwekil gezu
በድጋጋሚ የተለቀቀ ♻️ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ለምትመረቁ ውድ ጓደኞቼ ፣መላው የአስቱ ሙስሊም ተማሪዎች ፣ በተለይም ትልቅ አሻራ እሳርፋቹ ጀመአውን ተረክባቹ፣ የምችሉትን ሁሉ ሰጥታቹት (ቀን ለሊት ስለ ጀመአው እያሰባቹ) ፣ ከበታቹ ላላቹት አስረክባቹ በመሄድ ላይ ትልቅ አሻራ የአሳረፋቹ ወንድሞች እና እህቶች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለው። ቀጣይ ህይወታችሁ ያማረ ለኢስላምም የምትሰሩበት አሏህ ያድርጋችሁ!አሚን🤲🤲 ♻️ماشاء الله تبارك الله مبارك عليكم أيها الخريجون جميعا سعدنا بفرحتكم، جَعَلَ اللهُ حَيَاتَكُمْ حياة طيبة وَجَعَلَكُمْ مِمَّنْ يَعْمَلُونَ لِخِدْمَةِ الْإِسْلَامِ،والمسلمين ✅ይህች ግጥም ለናንተ ናት👇👇👇 አራት አምስት አመት ስንሰራ ስንለፋ፣ ስንቱን ችግር አየን ህይወትን ልንገፋ ፣ አልፎ ከራሳችን ቤተሰብ ሊደሳ ፣ እንዴት ልብ ይነካል ያ ታሪክ ሲነሳ ። ግባችን ደረሰ ዓላማችን ቀና ያመታት ልፋቱ ተተካ በፋና ለዚህ ላደረሠን ላለማቱ ጌታ ሃምድን አድርሰናል ለቸረን ፈገግታ ማብቂያው ዛሬ መሠል ቢመርጠን ጀሊሉ ፣ ለመመረቅ በቁ ደስ ይላል መባሉ፣ ቀናችን በርቶልን መድመቁ መኳሉ፣ ደስታችን ዛሬ ነው ሹክረን ሊላህ በሉ ። በካምፓስ ህይወት ላይ… አንዱ ሆኖ ከንቱ፣ ሌላው ቀድሞ ነቅቶ… ሸሽቶ ከጠላቱ፣ ከፊሉ ለነፍሱ የቀረው ሲል ኡማ፣ ይሰቅላል ከፍ አርጎ… የኢስላምን አርማ ፣ ሞልተዋል ብርቱዎች የታገሉ ብዙ ፣ በአላህ መንገድ ላይ ኢብሊስ ያፈዘዙ፣ ሰዎችን አመስጋኝ እኔን የሃመደ፣ ይለናል ጌታችን በኔ ተወደደ፣ እህት ወንድሞቼ ቀናችን ነው ዛሬ ፣ በግዜው ሲቀምሱት ይጣፍጣል ፍሬ ፣ ምንም ብንለያይ ቀናችን ተቆርጦ፣ መገናኘት አለ ለጀነት ተመርጦ ። አላህ ያገናኘን !!!! ✍️ወንድማቹ አቡ ሀሪስ (አይመን ሁሰይን)
AASTU Muslims union pinned «🎉 Congratulations to the AASTU Muslim Graduates! 🎉 To all the AASTU Muslim students graduating today, we extend our heartfelt congratulations on your remarkable success and achievements. Your hard work, dedication, and resilience have brought you to this…»
🎉 Congratulations to the AASTU Muslim Graduates! 🎉 To all the AASTU Muslim students graduating today, we extend our heartfelt congratulations on your remarkable success and achievements. Your hard work, dedication, and resilience have brought you to this beautiful milestone. As you step into the next chapter of your lives, we pray that Allah (SWT) blesses your journey ahead, grants you barakah in your knowledge, and opens doors to endless opportunities. May He make you a source of pride and benefit to your families, your community, and the Ummah. 🎓 Barakallahu Lakum! 🎓 — AASTU Muslim Students Union @aastumuslims
﴿إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ صَلُّواْ عَلَيْهِ وَسَلِّمُواْ تَسْلِيمًا ﴾ قَالَ ﷺ: «مَنْ صَلَّ عَلَيَّ صَلاةً صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشَراً» በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ 🍃🍂 ሱረቱል ካህፋንም መቅራት አንርሳ መልካም ጁምኣ ‼
የክረምት soft skill ስልጠና ዕድል ለ AASTU ሙስሊም ተማሪዎች! ●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●● ውድ የAASTU ሙስሊም ተማሪዎች የዘንድሮውን የክረምት እረፍትዎን አዳዲስ ጠቃሚ ክህሎቶችን እና የኮዲንግ ቋንቋዎችን በመማር ያሳልፉ! Habesha Tech አዲስ የፕሮግራሚንግ ቋንቋ እንዲማሩ እና እራስዎን እንዲያበቁ የሚያስችል ታላቅ የነፃ ትምህርት ዕድል (Scholarship) አዘጋጅቶላችኋል። ይህንን ወርቃማ ዕድል ተጠቅመው የክረምት ጊዜዎን በዕውቀት ለመቀየር ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሙሉ በጥንቃቄ በመሙላት በአስቸኳይ ያመልክቱ፡- ✅ ለHabesha Tech Full Stack Web Development Course Scholarship የመወዳደሪያ መስፈርቶች 📌 10 top scoring and skilled students will be granted scholarships 👉 Full Name 👉 Email 👉 Department 👉 Year 👉 CGPA 👉 Programming languagea you know: ‼️ (አንድ ላንጉጅ አውቀዋለሁ ለማለት ቢያንስ በዛ ላንጉጅ የተፃፈ ቀለል ያለ ኮድ ምን እንደሚሰራ መረዳት ምትችሉ ከሆነ ነው) 👉 Choose those which you know from the following: ✅ React.js ✅ Node.js ✅ Express.js ✅ PostgreSQL ✅ MySQL ‼️ If you don't know all of them, it is okay. 👉 Latest grade report (Take photo and send it as evidence) ⏰ Application Deadline: This coming Sunday night‼️ 🎤 Send all of the above required fields, and becareful not to miss any detail. 💥 Send to: @Zuzenith Join our channel and get the website: https://t.me/habesha_tech_lessons
◼️የአሹራ ቀን ፃም በተመለከተ ➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖ አቢ ቀታዳ አል አንሷርይ አላህ መልካም ስራውን ይውደድለትና እንዲህ አለ። ✅ የአላህ መልእክተኛ ስለ አሹራ ቀን መፃም ተጠይቀው እንዲህም አሉ፦ 【ያለፈውን አንድ አመት ወንጀል ያብሳል】ብለዋል። 📚(ሙስሊም ዘግቦታል።) ◼️መቼ ነው የሚጀመረው⁉️ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰 የአሹራ ቀን ፃም የሚጀመረው፦ አሁን ያለንበት የሙሀረም ወር አስረኛው ቀን ላይ ነው። ይህም ማለት የፊታችን ሐሙስ ሰኔ 18 / 2018 ይሆናል ። ◼️እንዴት ነው የሚፃመው⁉️ 〰〰〰〰〰〰〰〰〰 ↪️ አህለል ኪታቦችን ለመ ኻለፍ ዘጠነኛውን ቀን መፃም የፈለገ (በላጩም ይህ ነውና) የፊታችን እሮብ ሰኔ 17 / 2018 ላይ ይጀምርና እሮብ ና ሐሙስን በተከታታይ ይጾማል ። ↪️ ዘጠነኛው ቀን መጨመር ያልተመቸው አስረኛውና አስራ አንደኛው ቀን ማለትም ሀሙስና ጁማዓ መፃም ይችላል። አላህ ይወፍቀን... መረጃውን ለሌሎችም በማጋራት ከወዲሁ እናስታውስ
﴿إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ صَلُّواْ عَلَيْهِ وَسَلِّمُواْ تَسْلِيمًا ﴾ قَالَ ﷺ: «مَنْ صَلَّ عَلَيَّ صَلاةً صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشَراً» በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكْ عَلَى نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ ﷺ 🍃🍂 ሱረቱል ካህፋንም መቅራት አንርሳ መልካም ጁምኣ ‼
⚠️ የጥንቃቄ መልእክት السلام عليكم ورحمة الله وبركاته، ውድና የተከበራችሁ ወንድም እህቶች፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በዚህ የቴሌግራም ፕላትፎርም እግባብነት የሌላቸው ማስፈንጠሪያዎች (links) እየተዘዋወሩ እንደሆነ ግልጽ ነው። ሊንኮቹ የሚነክስቸውን ሰው አካውንት በመመንተፍ ለኮንታክቶቻቸው ራሳቸውን እንዲልኩ ኦቶሜት ተደርገው የተዘጋጁ ናቸው። ከላያቸው ላይ "ፕሪሚየም በነጻ" እና መሰል አጓጊ መልእክቶችን ያዘሉ ጽሑፎች (click baits) አሉባቸው። እኛ እነዚህን ማስፈንጠሪያዎች በምንነካበት ወቅት ትላልቅ ጥፋቶች እንዲከሰቱ ሰበብ እንሆናለን፦ 1. ያንኑ ተመሳሳይ ሊንክ በመበተን የሌሎች ሰዎች አካውንቶች እንዲጠለፉ እና እንዲመነተፉ እናደርጋለን። 2. እነኚህ ሊንኮች ባብዛኛው ነውር አዘል ይዘት ስለሚኖራቸው ሌሎችን ወንጀል ውስጥ እንከታለን፣ የራሳችንን ክብር በገዛ እጃችን እናጎድጋለን፣ ነገሩን ካልተረዱ ሰዎች ጋር እንድንጋጭ ይሆናል። 3. መንታፊዎቹ አካውንታችንን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር ስለሚችሉ ልወዳጅ ዘመዶቻችን ውደነሱ የባንክ አካውንቶች ብር እንዲልኩ የሚጠይቁ መልእክቶችን በመላክ ሰውን የሚያሳስቱበት እድል እንዲኖር እናደርጋለን። እሁን ላይ ትዝ ያሉኝን ጉዳቶች ነው የጠቀስኩት። ከጠቀስኳቸውም ሌላ ከህግና ከሸሪዓ አንጻር መጥፎ የሆኑ መዘዞችን ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ጥንቃቄ በማድረግ ራሳችንንም ሌሎች ወንድም እህቶቻችንንም እንጠብቅ። ይህን ሁሉ ለመከላከል የሚከተሉትን ነጥቦች ትኩረት ብንሰጣቸው ጥሩ ነው እላለሁ፦ 1. ቴሌግራም ላይ የምናገኛቸውን ማስፈንጠሪያዎች ከምናምነው አካል ያውም ለአስፈላጊ ቁም ነገር ካልሆነ በስተቀር አለመንካት። (እዚህጋ ማስተዋል የሚገባችሁ ነገር "ነጻ ገንዘብ" የሚባል ነገር አለመኖሩን ነው።) 2. የቴሌግራም መተግበሪያዎቻችን ላይ "Two-step Verification" የሚለውን የsecurity ማስተካከያ አማራጭ መጠቀም። ይህ የሚረዳን ሰዎች ወይም ኦቶማቲክ ቦቶች ዘው ብለው ወደ አካውንታች እንዳይገቡ ተጨማሪ የይለፍ ቃል በመጠየቅ ነው። 3. ይህ ነገር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ በድንገት ከተከሰተብን 24 ሰዓት ሳይሞላው በፊት በፍጥነት "Terminate All Other Sessions" የሚለውን የማስተካከያ አማራጭ በመጠቀም ከኛ ዲቫይስ ውጪ ያሉ ሌሎች ዲቫይሶችን ከአካውንታችን ማገድ። (እዚህ ጋር መጠንቀቅ ያለብን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ እኛ ቀድመን ካላቋረጥንባቸው እነሱ በተቃራኒው እኛን ከአካውንታችን በማስወጣት እድሜልክ የአካውንታችንን ባለቤትነት ይወርሱታል። ማለትም ዳግመኛ ያንን አካውንት መጠቀም የማንችልበት ሁኔታ ይፈጠራል።) መልእክቱን ለሌሎች በማስተላለፍ ግዴታችንን እንወጣ!
﴿إِنَّ ٱللَّهَ وَمَلَٰٓئِكَتَهُۥ يُصَلُّونَ عَلَى ٱلنَّبِىِّ ۚ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُواْ صَلُّواْ عَلَيْهِ وَسَلِّمُواْ تَسْلِيمًا ﴾ قَالَ ﷺ: «مَنْ صَلَّ عَلَيَّ صَلاةً صَلَّ اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشَراً» በኔ ላይ አንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ አላህ በርሱ ላይ አስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል اللهم صل وسلم وبارك على نبينا محمدﷺ 🍃🍂 ሱረቱል ካህፋንም መቅራት አንርሳ መልካም ጁምኣ ‼
ማሳሰቢያ ⁉️ በአሁኑ ሰዓት ባለው ወቅታዊ የነዳጅ እጥረት ምክንያት ዩኒቨርሲቲው የባስ (የአውቶቡስ) አገልግሎት ማቅረብ የማይችል መሆኑን እናሳውቃለን። በመሆኑም የዒድ ሰላት የሚሰገደው ኮዬ ንፋስ ስልክ በመሆኑ እና ሰላቱ በጧት 2:00 ሰዓት ስለሚጀምር፣ ከኮዬ አደባባይ የንፋስ ስልክ ታክሲዎችን በመያዝ መሄድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። ●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●●● Notice ⁉️…