tgindex
AMU- Muslim Students Union

AMU- Muslim Students Union

Статистика
@amumsu1английский

أَعُوذُ بِاللَّـهِ مِنَ الشَّيْطَانِ الرَّجِيمِ وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا... "And hold firmly to the rope of Allah all together and do not become divided..." 👉 This is official AMU-MSU

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
31
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
597
+1 за 3 дн.
Сутки
+1
+0,17%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
241
31 постов
Вовлечённость
40,4%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 31
Упоминаний
1
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
72
1/48двое суток
82
1/72трое суток
88

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • ​«አንድ ሰው ጠላቱን ሊገጥም በጉዞ ላይ እያለ፤ የጦር ልብሱ (መከላከያው) ሲከብደው ቢያወልቀው፣ ሰይፉ ሲከብደው አውልቆ ቢጥለው፣ እንዲሁም ምግቡና መጠጡ ሲከብደው ቢተወው፤ ከዚያም ምንም ዓይነት መከላከያና ትጥቅ ሳይኖረው፣ በዚያውም ላይ ተርቦ ጠላቱን ቢገናኝ፤ ታዲያ እንዴት አድርጎ ሊያሸንፍ ይችላል?! ​ልክ እንደዚሁ ዚክር (አላህን ማውሳት) ከብዶት የተወ፣ የሱና ሶላቶች (ሱነኑ ረዋቲብ) ከብደውት ቸል ያለ፣ ግዴታ (ፈርድ) ተግባራትን ከብደውት ያዘገየ፣ እንዲሁም አላህ ያዘዛቸውና የከለከላቸው ነገሮች ከብደውት ያቃለለ ሰውም ከዚህ አይለይም፤ ይህን ሁሉ አድርጎ ከዚያም ሰይጣን ልቡ ላይ እንደሰለጠነበት ያማርራል! ይህ ሰው እኮ ጠላቱ ሳይጥለው በፊት ራሱን በራሱ ነው የጣለው።» ​➖ኡወይስ አል-ቀረኒይ(አላህ ይዘንላቸው) Copied

  • ሓጃዎቻችን እንዲሳኩ... ነቢያችን ላይ ሰለዋት ማብዛት ሓጃን (ጉዳይን) እንደሚያሳካ፣ ወንጀልን እንደሚያራግፍ ቲርሚዚይ በዘገቡት ሐዲሥ ተነግሯል። ጊዜው የግልም የጋራም (የዲንም የዱኒያም) ሓጃ የበዛባት ሆኗልና ለሱናውም ለጉዳዩም ስንል ነቢያችን ላይ ሰለዋት ማውረድ እናብዛ اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ، وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ. ዛዱል-መዓድ

  • 🚫የሃራም ግንኙነት… ❉አላህን የሚያስቆጣ ነገር ፍሬ አፍርቶ አያውቅም አላህ ያልወደደው መንገድ አንሸራቶ ከመጣል ውጪ አዛልቆ አያውቅም። ✔️ለወደፊት ብዙ የታለመበት፣ያታቀደበት የሃራም ግንኙነት የገዛ እግርንን ጠልፎ የሚጥል ረዥም እና አሰቃቂ ግመድ እንጂ እንደሚመስለው ወደ ሃላል የሚያዳርስ ድልድይ አይደለም፤አሁን ላይ ከወላጆች እና ከሚቀርቡ አካላት የተደበቀው ድብቅ የሃራም ዋሻ ተደርምሶ ቆሻሻን እና ከባባድ ድንጋዮችን አናት ላይ የሚጥል ሊወድቅ የተቃረበ የተገነባ የሚመስል ጨለማ ዋሻ ነው። ሃራም እና አላህን የሚያስቆጣ ተግባር ላይ መዝለቅ አይታሰብም፤አላህን የሚያስቆጣ ተግባር ላይ መውደቅ እንጂ መዝለቅ አይጠበቅም። ሃራም ምን ጊዜም ሃራም ነው! በዱንያም በአኺራም ውርደትን፣የልብ መረበሽን፣የውስጥ መቆሸሽን፣አለመረጋጋትን፣ጭንቀትን እንጂ ሌላ አያተርፍም !

  • على هامان يا فرعون؟؟ ፈገግታ ከፊርዓውን ጅልነት ጋ… ♾️♾️♾️♾️♾️♾️♾️♾️ ፊርዓውን ከነበረበት ድንበር ያለፈ ጥመት ጋ ጅል (ፋራ) ነገር ነበር አሉ። አማካሪው ሃማን ደግሞ እንደ የትኛውም የንጉሶች አማካሪ ብልጣብልጥ ነበር አሉ። እናም ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት በፊርዓው “የጌትነት ሙገታ” ያመነች አሮጊት ፍየልዋ ይሞትባትና ወደ ፊርዓውን ቤት ትመጣለች። ስትመጣ ፊርዓውን አልነበረም ሃማንን አገኘችው። "ጉዳይሽ ምን ነበር?" ሲላት "ፍየሌ ሞታብኝ ፊርዓውን ሕያው እንዲያደርጋት ነበር የመጣሁት።" ትለዋለች ሃማን ብልጥ ነበር;  ብለን የለ? "ነይ በቃ ፊርዓውን አሁን ግመል እየፈጠረ ስለ ሆነ ይቆይብሻል። ስለዚህ ሌላ ፍየል ልስጥሽ።" ይላትና ሌላ ፍየል ሰጥቷት ትሄዳለች። ፊርዓውን ወደ ቤቱ ሲመለስ ሃማን "አንዷ አሮጊት ፍየሏ ሙቶባት ሕያው እንድታደርግላት መጥታ ነበር።" ሲለው ፊርዓውን ደነገጠ። ሃማን "አይዞህ! ፊርዓውን ግመል እየፈጠረ ነው። ብያት ሌላ ፍየል ሰጥቻት ሄዳለች። አትመጣም።" አለው። በዚህ ጊዜ ፊርዓውን እንደ መረጋጋት አለና በረጅሙ ተንፍሶ…………   «ግመል መፍጠር እኮ እንዴት እንደ ሚያደክም ብታይ» አለው። ሃማን ፈገግ አለና… …      على هامان يا فرعون ኧረ ፍርዓውን! በሃማን ላይ❓አለው በሃማን ላይ ሙድ ትይዛለህ ወይ እንዴ ጭራሽ ልትሸውደኝ ያምርሃል ማለቱ ነው። ከዛኔ ጀምሮ ሰዎች በሚያውቁት ነገር ላይ  ሊሸውዳቸው ለሞከረ ሰው على هامان يا فرعون ኧረ ፍርዓውን! በሃማን ላይ❓አለው እያሉ አባባል አድርገው ይዘውታል። copied

  • "የ19 ዓመት የዩንቨርስቲ ተማሪ ወደ ህክምና ማዕከል በሄደችበት ማደንዘዣ በመውጋት አስገድዶ መድፈር የፈፀመው ዶ/ር በ21 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ" የሚል ዜና አየሁኝ። "በሃኪም እንዴት ይሄ ይፈጸማል?" ማለት ሞኝነት ነው። በሃኪም ቀርቶ በሃይማኖት አስተማሪም ይፈጸማል። መፍትሄው አጭርና ቀላል ነው። ማንኛዋም ሴት ከባዳ ወንድ ጋር ተገልላ ልትገኝ አይገባትም። ነብያችን ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ لا يخلوَنَّ رجلٌ بامرأةٍ فإنَّ الشيطانَ ثالثُهما "አንድ ወንድ ከባዕድ ሴት ጋር ብቻውን አይነጠል፤ ምክንያቱም ሶስተኛቸው ሸይ^ጧን ነውና።" [ቲርሚዚይ፡ 2165] "ሶስተኛቸው ሸይ^ጧን ነው" የሚለው አጉል መልካም እምነት እንዳያዘናጋን ጥብቅ ማሳሰቢያ ነው። ስለዚህ ያልታሰበ ከባድ ጥፋት የመድረስ እድሉ ከፍተኛ ነው ማለት ነው። ህክምናን በተመለከተ ሴቶች አማራጭ ካለ በሴቶች ታከሙ። አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠመ ከቤተሰብ ጋር እንጂ ብቻችሁን ወንድ ሃኪም ዘንድ አትግቡ። ወይም ሴቶች ነርሶች ካጠገባችሁ እንዲሆኑ አናግሩ። እዚህ ላይ "ውጭ ቆዩ" የሚሉ ሃኪሞች ይኖራሉ። (መግቢያየ ላይ የጠቀስኩትም ክስተት በዚህ መልኩ የተፈፀመ ነው።) እንዲህ አይነት ሃኪም ሲገጥመን ቢቻል ማስረዳት፣ ካልሆነ መጋፈጥ ይገባል። ፈቃደኛ የማይሆኑ ሃኪሞችና ሃኪም ቤቶች ዘንድ አትሂዱ። ቆራጥ ከሆንን ለራሳቸው ሲሉ ያስተካክላሉ። ለሃኪሞች ማሳሰቢያ፦ ከባዳ ሴት ጋር ተገልሎ መቆየት እንደማይቻል አትዘንጉ። ስለዚህ ስታክሙ ቤተሰብ በቅርብ እንዲኖር አድርጉ። ወይም ረዳቶች ባቅራቢያችሁ ይኑሩ። አስገዳጅ ሁኔታ ከገጠማችሁ የምትሰሩበትን ክፍል በሩን ክፍት አድርጉት። በነገራችን ላይ እንኳን ባዳ የሆነ አካል በቤተሰብ መሀል ራሱ መጥፎ ነገር ሊከሰት ይችላል። ለዚያም ነው ኢስላም በዚህ ጉዳይ ላይ ጥብቅ መመሪያ ያስቀመጠው። ነብያችን ﷺ ልጆችን አስር አመት ሲሆናቸው መኝታቸውን ለያዩዋቸው ብለዋል። ለአስር ዓመት ልጆች! ስለዚህ ቤተሰብ አላህ ባገራለት ልክ መኝታቸውን ሊለያያቸው ይገባል። ሁሉም አንድ ክፍል ውስጥ የሚተኙ ከሆነ ሴቶችን አንድ ጥግ፣ ወንዶችን ደግሞ ሌላ ጥግ ማድረግ ይገባል። በቂ ክፍሎች ካሉ ሴቶችን የብቻ አንድ ክፍል፣ ወንዶችን የብቻ ሌላ ክፍል ማድረግ ይገባል። ከተቻለ ወንዶችን ከወንዶች፣ ሴቶችንም ከሴቶች ፍራሻቸው ቢለያይ ጥሩ ነው። አጉል መልካም ግምት ሊያዘናጋን አይገባም። "የዘመድ ልጅ ነው"፣ "ቤተሰብ ነው"፣ "ሸይኽ/ ኡስታዝ ነው"፣ "የጎረቤት ልጅ ነው"፣ "እንግዳ ነው"፣ "ስርአት ያለው ጨዋ ልጅ ነው"፣ "ትልቅ ሰው ነው"፣ የመሳሰሉ የዋህ ድምዳሜዎች ከባድ ዋጋ ያስከፍላሉ። እንኳን ሴቶችን ከወንድ፣ ወንዶችን ከወንድም መኝታቸውን መለየት ይገባል። ሌላው ቀርቶ አባት ወይም ወንድም ቢሆኑ እንኳ ጥሩ ያልሆነ አዝማሚያ የሚያሳዩ ከሆነ የሚቻለውን ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ ይገባል። ©: ኢብኑ ሙነወር

  • 🔖ዒልም የማይጠገብ ስብእና..!! አምሮታቸው ፣ጉጉታቸው ፣ኢልም መቅስም ፣ ኢልም ማስራጨት ነበር። ለኢልም ሲሉ የለበሱት ልብስ ከላያቸው ላይ ከሚያድፍ ትተውታል። ለዒልም ሲሉ ከፍተኛ ስልጣንን አሽቀንጥረው ጥለዋል። ኢብኑ ተይሚያ ባሉበት የሆድና የሴት ጉዳይ አይነሳም። አጥጋቢ ድምዳሜ ላይ ያልደረሱበትን ጉዳይ ከጫፍ ሳይደርሱ ልባቸው አያርፍም። አንዳንዴ አንዲትን የቁረአን አንቀጽ እያጠናሁ ምናልባትም ወደ መቶ አካባቢ ተፍሲሮችን የማገላብጥበት ጊዜ አለኝ" ይላሉ። ምክር እንኳን አያሳፍራቸውም።እንዲያውም በአንድ ወቅት የሆነ ህመም ስላደረባቸው ይሄ ጥናትህ እና እውቀት ማስተማርህ ህመምህን እያባባስው ነው"አላቸው ሀኪም ። ግና አልሆነም " ይህን እንኳን አልታገስም አሉት። ቀጥለውም እንዲያውም እኔ በእውቀትህ እፈርድሃለሁ። ነፍስ ስትደስት ተፈጥሮዋ ጠንክሮ ህመሟን ትከላከል የለምን? አሉት። በሚገባ አላቸው። እንዲያውስ ነፍሴ በእውቀት ስለምትደስት ተፈጥሮዋ ይበርታል።እፎይታም አገኛለሁ " አሉት ።ሃኪሙ ግራ ቢጋባው ይሄ ከኛ ህክምና ውጭ ነው" አላቸው።` ኢብኑ ተይሚያ ረሂመሁላህ Copied

  • አሰላሙዓለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካትሁ ​📢 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ቻናል የሚካሄድ ታላቅና ልዩ የሁለት ቀናት የኦንላይን ስልጠና ! ​በሀገራችንም ሆነ በዩኒቨርስቲያችን አውድ ውስጥ በስፋት ከሚነሱና በሙስሊም ተማሪዎች ዘንድ ከፍተኛ ግራ መጋባትና ተፅዕኖ ከሚፈጥሩ አጀንዳዎች መካከል ሴኩላሪዝም በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው። ይህ አይዲዮሎጂ በበቂ ሁኔታ ግንዛቤ ያልተፈጠረበት እና የድንበር ወሰኑ ያልተለየ በመሆኑ ብዙ ጊዜ የሃይማኖት ነፃነትን ከማስከበር አልፎ ሙስሊም ተማሪዎች እምነታዊ መብቶቻቸውን በነፃነት እንዳይጠቀሙና በግቢ ሕይወታቸው ውስጥ አላስፈላጊ ጫናዎች እንዲደርሱባቸው ሲያደርግ ይስተዋላል። ​ስለሆነም ተማሪዎች ስለ ሴኩላሪዝም ግልጽና መረጃን መሠረት ያደረገ እውቀት እንዲኖራቸው፣ በሕግና በተቋማዊ አውድ ውስጥ እንዴት እንደሚተገበር እንዲረዱ እንዲሁም መብትና ግዴታቸውን ለይተው በእምነታቸውና በአቋማቸው ላይ በጽናት እንዲቆሙ ለማስቻል የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት በመጪው ቅዳሜ እና እሁድ (ሐምሌ 25 እና 26) ልዩ ስልጠና አዘጋጅቶላችኋል! ​📌 የመርሃ-ግብሩ ዝርዝር መረጃዎች፦ 📝​ርዕስ ፦ ሴኩላሪዝም — ትርጉሙ፣ በሀገራዊና በዩኒቨርስቲ አውድ ያለው ተፅዕኖ፣ እና የተማሪዎች መብትና ግዴታ 👤 ​አሰልጣኝ ፦ በሕግ ዘርፍ ሰፊ ልምድ ያላቸው የሕግ ባለሙያው ሙስጠፋ ሽፋ 🎙 ​የፕሮግራሙ አስተባባሪ ፦ ወንድማችን ሙሐመድ አሚን ካሳው (የኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ፕሬዝዳንት) 🗓 ​ዕለት ፦ መጪው ቅዳሜ እና እሁድ (ሐምሌ 25 እና 26) ⏰ ​ሰዓት ፦ በሀገር ውስጥ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 3:00 ሰዓት ጀምሮ 📍​ቦታ ፦ በ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ሕብረት ዋና ቴሌግራም ቻናል ላይ (@aaumsu) ​ይህ ስልጠና እያንዳንዱ ተማሪ በግቢ ሕይወቱ የሚያጋጥሙትን አላስፈላጊ ጫናዎችና የሕግ/አስተሳሰብ ግራ መጋባቶች ለመቅረፍ እጅግ ወሳኝና አስፈላጊ ስልጠና ነው!  ​ስለሆነም በርካታ ተማሪዎች የዚህ ትልቅ መርሃ-ግብር ተካፋይ እንዲሆኑና መብቶቻቸውን በግልጽ እንዲረዱ ​ይህንን ማስታወቂያ በቴሌግራም ስቶሪ ላይ በመልቀቅ፣ ​ለቅርብ ጓደኞቻችሁ እና በምትገኙባቸው የተለያዩ ግሩፕ እና ቻናሎች ሁሉ ሼር በማድረግ የበኩላችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን! ​ቅዳሜ ምሽት 3:00 ሰዓት ላይ በሕብረቱ ቻናል እንገናኝ! ​ © aaumsu @AAU6kilojemea

  • በሂፍዝ እና በሙራጃዐ መካከል ሆነሽ ድካምና ጫና ሲሰማሽ ይህን አስቢ ፦ ~ ከቁርአን ዊርድ የተለየሽ፣ ሩጫሽም ለዚች ጠፊ ዱንያ ብቻ ቢሆን ኖሮ... ለነገው አኺራሽ የሚሆን ምን ዛድ(ስንቅ) ይኖርሽ ነበር? በርግጥስ ያኔ ህይወትሽ የኢማን ጣዕም ይኖረዋል? አላህ ወደ ሐለቃው  ባይጠራሽ፣ የቁርኣንን ብርሃን በልብሽ ባያሳድርብሽ ኖሮ፤ እውነት ያኔ እረፍት ታገኚ ነበር? እህቴ ሆይ!  ከማሰማትሽ በፊት የሚሰማሽ ጭንቀትና የልብ ትርታ ራሱ ታላቅ ኒዕማ ነው። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የተነፈጉት፣ አንቺ ግን በአላህ ተውፊቅ የታደልሽው ታላቅ ስጦታ ነው። ስለዚህ በዚህ የኑር መንገድ ላይ ስለመራሽ አላህን አመስግኚ"አልሐምዱሊላህ"በይ። ጫናው ቢበዛብሽም፣ ያለ ቁርአን ቢሆን ኖሮ የህይወት ሸክሙ ይበልጥ በከበደሽ ነበር። ምክንያቱም፦ "ቁርአን በማንኛውም ነገር ውስጥ አይገባም በረካን ቢያሰፍንበት እንጂ።"🌾 አላህ በቁርአን ያፅናሽ፣ ሂፍዙንም ያግራለሽ! Copied

  • 🔘በመታገስና በመስገድ       ጭንቀትን አስወግድ! ​▪️ የችግሮች ሁሉ መፍትሄ -በአላህ ፈቃድ- ትዕግስትና ሰላት ነው። ​አላህ እንዲህ ይላል፥ ​( وَٱسۡتَعِینُوا۟ بِٱلصَّبۡرِ وَٱلصَّلَوٰةِۚ )   سُورَةُ البَقَرَةِ: ٤٥ > (በመታገስና ሰላት በመስገድ የአላህን እርዳታ ፈልጉ) አልበቀረህ: 45 ​▪️ የአላህ እርዳታ ሁሌም ከትክክለኛ አማኞች ቅርብ ነው። የትክክለኛ አማኝ አንዱ መገለጫ ደግሞ ሰላት ነው። ​▪️ ነቢዩ ሙሐመድም ﷺ ችግር ሲገጥማቸውና የሆነ ነገር ሲያሳስባቸው ፈጥነው ሰላት ይሰግዱ ነበር (አቡ ዳውድ: 1319) ​▪️ بالصبر والصلاة تتيسر الحياة. በትዕግስትና በሰላት ሕይወት ይቀላል። ያለ ሁለቱ ደግሞ ሕይወት ይከብዳል።​ስለሆነም ችግር ሲያጋጥመን መታገስና ከፈርድ አልፎ ሱንናህ ሰላቶችን ማብዛት ነው የሚጠቅመን! ​ይህን ማድረግ ትቶ ማዘን፣ መተከዝ፣ ማማረር፣ ተስፋ መቁረጥና ምንም ማድረግ ለማይችሉ ደካማ የሰው ልጆች ችግሮቻችንን መዘርዘር የኢማንም የዐቅልም ድክመት ነው። ​መታገስ፣ ዚክር፣ ዱዓና ሰላት ማብዛት፣ ሕይወት ላይ የኢስላምን አስተምህሮት መከተል ሰላምና የውስጥ መረጋጋትን፣ በሕይወት ደስተኛ መሆንን ያስገኛል። ​🤲 አላህ ከታጋሾችና ሰላትን አዘውትረው ከሚሰግዱ ባሮቹ ያድርገን! ​✍ ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም  ዛዱል መዓድ

  • ከአላህ በስተቀር ሁሉም ምትክ አለው! የሰው ልጅ ላጣቸው ነገሮች ሁሉ ይብዛም ይነስ ምትክ ( አማራጭ ) ሊያገኝ ይችላል፤ አላህን ያጣ ( ከርሱ የራቀ፣ እሱን ያስቆጣ ) ሰው ግን ምንም ዓይነት ምትክና አማራጭ መቼም ማግኘት አይችልም። ስለዚህ መቼም ቢሆን፣ ለማንም ለምንም ብለህ አላህን እንዳታጣ ተጠንቀቅ! ዛዱል መዓድ

  • أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏"‏ إِذَا كَانَ يَوْمُ الْجُمُعَةِ كَانَ عَلَى كُلِّ باب مِنْ أَبْوَابِ الْمَسْجِدِ الْمَلاَئِكَةُ، يَكْتُبُونَ الأَوَّلَ فَالأَوَّلَ، فَإِذَا جَلَسَ الإِمَامُ طَوَوُا الصُّحُفَ وَجَاءُوا يَسْتَمِعُونَ الذِّكْرَ ‏ [صحيح البخاري] አቡ ሁረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ መሰረት  ጁምዓ ቀን መላዒኮች በሁሉም መስጂድ በሮች ዳር እና ዳር ሆነው ለሰላት የሚገባውን ሰው ስም በደረሰበት ሰዓት መሰረት አከታትለው በመዝገባቸው ላይ ያሰፍራሉ። ኢማሙ ኹጥባ በጀመረበት ቅጽበት ግን መመዝገባቸውን አቋርጠው ኹጥባውን ለመታደም መስጅድ ውስጥ ይገባሉ። ጁምዓ ስንሄድ ከኹጥባ በፊት መስጂድ መድረስን ልምዳችን እናድርግ ያኔ ስማችን በመላዕክት የመመዝገብ እጣ ፈንታን እና ከእነርሱ ጋር እኩል መታደምን እንወፈቃለን። ውብ የሆነ ጁምዓን ተመኘን✨

  • ▼ماتت؟!! ▼ሞተች?!! 💥نعم ماتت !! وڪانت تظن أن عُمرها طويل.... አዎ ሞተች!! ዕድሜዋ ረጅም እንደሆነ ታስብ ነበር፤ • وسترتدي الحجاب...• ሂጃብም እንደምትለብስ፣• وتقطع تلك العلاقة المحرمة... ያንንም የተከለከለ (ሐራም) ግንኙነት እንደምትቆርጥ፣ وتڪُف عن سماع الموسيقي.... • ሙዚቃ መስማትም እንደምትተው (ታስብ ነበር)። لڪنها الآن ميتة!!! አሁን ግን እሷ ሞታለች!!! بالله لا تؤجلوا التوبة لا ندري متي تقبض أرواحنا ነፍሳችን መቼ እንደምትወሰድ አናውቅምና ተውባን (ንስሐን) አናዘግይ። copied

  • видео или голосовое, без подписи

  • ከቁርኣን ማዕድ ወጥተን ወዴት?! ~ ​ ታላቁ ዓሊም ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ (ረሒመሁሏህ) በሕይወታቸው ማጠቃለያ ላይ እንዲህ ብለው ነበር፦ ​💬 "አብዛኛውን ጊዜዬን በቁርኣን ማዕዶች፣ ትርጉሞችና ምስጢሮች ላይ ባለማዋሌ ተጸጽቻለሁ።" ​📚 (ዘይሉ ጠበቃቲል ሐናቢላ - ኢብኑ ረጀብ፡ 2/402) ​ልብ በሉ! ይህንን ተጽዕኖ ፈጣሪ ንግግር የተናገሩት እኮ ሙሉ ሕይወታቸውን በቁርኣን፣ በዲን እውቀት፣ በጂሃድ እና ህዝብን በማስተማር ያሳለፉ ታላቅ ሰው ናቸው! ​🍂 ትልቅ የቁጭት መልእክት፦ እሳቸው ያንን ሁሉ የዕውቀትና የጂሃድ ዘመን አሳልፈው ይህ ከተሰማቸው... የእኛ ውድ ጊዜ ከቁርኣን ርቆ በከንቱ ሲያልፍ ምን ያህል ልንቆጭ እና ልናዝን ይገባ ይሆን?! Copied

  • *ثلاثة أشياء تهدئ الأعصاب:* 1- الزواج 2- الزوجة الصالحة 3- الزوج الصالح ومن قال لك: *النعناع والليمون والزنجبيل* قل له: أشربهم أنت✅ ነርቭን የሚያረጋጉ (ጭንቀትን የሚቀንሱ) ሶስት ነገሮች፦ 1. ​ጥሩ ትዳር ​2. መልካም ሚስት ​3. መልካም ባል ​እናም ማንም መጥቶ " የናና ሻይ፣ ሎሚ እና ጅንጅብል" ነው ብሎየነገረህን ሰው... "አንተ ራስህ ጠጣው!" በለው። ✅ Copied

  • ዓሊይ ቢን አቢ ጣሊብ እና ሙዓዊያህ ቢን አቢሱፍያን መካከል በነበረው አለመግባባት ፤ የቢዛንታይን ንጉስ ሂረቅል እንዲህ ብሎ ፃፈለት ለሙዓዊያህ "قد علمنا بما وقع بينكم وبين علي بن أبي طالب، وإنّا لنرى أنكم أحق منه بالخلافة، فلو أمرتني أرسلت لك جيشاً يأتون إليك برأس علي". "በእናንተ እና በዓሊይ ቢን አቢጣሊብ መካከል የተከሰተውን አውቀናል። እናተ ከእርሱ የተሻለ መሪነቱ(ኺላፋው) ይገባቹሀል ብለን እናስባለን። ከፈለክ እዘዘኝ ሰራዊት ልላክልህ እና የዓሊይን ጭንቅላት(ገድለውት) ያምጡልህ።" ብሎ ፃፈለት። ሙዓዊያህ እንዲ ብሎ መለሰለት "أخوان تشاجرا، فما بالك تدخل فيما بينهما؟ إن لم تخرس أرسلت إليك بجيش أوله عندك، وآخره عندي، يأتونني برأسك أُقدِّمه لعلي". "ሁለት ወንድማማቾች ተጣሉ፤ ምናገባህ አንተ መሀላቸው የምትገባው?፤አፍህን ካልዘጋህ ሰራዊት እልክልሀለው ፊትለፊቱ አንተ ጋር መጨረሻው እኔ ጋር የሆነ፤ ጭንቅላትህን ያመጡልኝ እና ለዐሊይ እሰጠዋለሁ (ስጦታ) " መሀላቸው የነበረው:- ~ ወንድነት ያለው አለመግባባት፤ ~ መከባበር ያለው ልዩነት፤ ለዚህ ነው ስትጣላ ዐቅል ያለው ሰው ጋር መጣላት ያለብህ  ። علي بن أبي طالب و معاوية بن أبي سفيان أصهار رسول الله ﷺ كاتبان الوحي لرسول اللهﷺ copied

  • ልቤ ሆይ!! ~ ልቤ ሆይ ልብ አድርግ - ለመልካሙ ትጋ - ከክፋት ተገታ ምላሴ ሆይ እረፍ - ጦስህ ያስፈራኛል - በጧትም በማታ እጄ ሆይ ተመከር - "እጄን በ’ጄ" እንዳልል - በሚያስጨንቅ ቦታ እግሬ እግር አታብዛ - ታዋርደኛለህ - በጭንቁ ቀን ለታ አዋጅ ሰምቻለሁ - እጅግ የሚያስፈራ - ከሰማዩ ጌታ። (يَوْمَ تَشْهَدُ عَلَيْهِمْ أَلْسِنَتُهُمْ وَأَيْدِيهِمْ وَأَرْجُلُهُمْ بِمَا كَانُوا يَعْمَلُونَ) "በእነሱ ላይ ምላሶቻቸው፣ እጆቻቸውና እግሮቻቸውም ይሰሩት በነበሩት ነገር በሚመሰክሩባቸው ቀን (ከባድ ቅጣት አላቸው)፡፡"  [አንኑር: 24] (ኢብኑ ሙነወር፣ ሚያዚያ 7/2016 )

  • ይህ ሱዳናዊ ህፃን እንዲህ ከፍቶት ሚያነባው በነብዩ መስጂድ ላይ ሆኖ ካለው ናፍቆት የተነሳ የሳቸው መሞት ሲያውቅ ነው። ያአላህ………ዛሬም ድረስ የረሱል ሞት ለትልቁም ለትንሹም አዲስ ነው እጅግ ልብን ይሰብራል!......ናፍቆታቸውም ቀን ከቀን ይበረታል! በአላህ ይሁንብኝ ልቦች እንደሳቸው ማንንም አልወደዱም ማንንም አልናፈቁም አይኖች እሳቸውን ናፍቀው እንዳነቡት ለማንም ፍጡር አላነቡም ልቦችም እሳቸውን እንደማጣት በምንም አልተጎዱም اللهم صل وسلم وبارك على نبينا وحبيبنا وشفيعنا محمد ﷺ رزقنا اللَّٰـه وإياكم شفاعته ومرافقته في الجنة !

AMU- Muslim Students Union — tgindex