DA'WAH WEL IRSHAD
СтатистикаAMU MUSLIM JEMA SUPPORT HUB 💫አሰላሙ አለይኩም እንኳን ወደ መርከዛችን በደህና መጣችሁ። قال رسول الله ﷺ: "طلب العلم فريضة على كل مسلم" በማዕከላችን ውስጥ 1ኛ/በተለያዩ መሻይሆች እና ኡስታዞች ተቀርተው የተጠናቀቁ ዱሩሶች 2ኛ/በሁሉም ፈኖች በደረጃ የተቀመጡ ደርሶች
- Последний пост
- 5 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 28
- 1/48двое суток
- 32
- 1/72трое суток
- 34
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሰውነታችን ሲዝል በተለያዩ ነገራቶች እንጠግነዋለን በምግብ በማረፍ....ወዘተ ግን ቀልባችን ሲደክም መጠገኛው አንድ እና አንድ ነው እሱም ወደ አሏህ መሸሽ ....ففروا الى الله https://t.me/amu_dawa
የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- مَنْ أحبَّ أن يَصِلَ أباهُ في قبرِهِ، فلْيَصِلْ إخوانَ أبيهِ مِن بَعدِه "በመቃብሩ ውስጥ ላለ (ለሞተ) አባቱ መልካም መዋል የሚወድ ሰው፣ ከእርሱ በኋላ ለአባቱ ወንድሞች (ወዳጆች) መልካም ይዋል።" [ሶሒሑል ጃሚዕ ፣ አልአልባኒይ ፡ 5960] የወላጆች ሐቅ በመሞታቸው አይቋረጥም። የአላህ መልእክተኛ ﷺ በዚህ ሐዲሥ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላም ቢሆን ለእርሱ መልካም ነገርንና ምንዳን ማብዛት የሚቻልበትን ተግባራዊ መንገድ ያሳዩናል። እርሱም የአባትን ወዳጆችና የቅርብ ዘመዶች መዛመድ/መንከባከብ፣ መጠየቅ ነው። ለአባት መልካም ማድረግ በእርሱ ህልፈት የሚያበቃ ሳይሆን፣ በሕይወት እያለ ይወዳቸውና ይዛመዳቸው የነበሩትን ሰዎች ሁሉ የሚያጠቃልል ነው። ከዚህም ባሻገር ለወላጆች በማሰብ ሶደቃ ማውጣት፣ ዱዓእ ማድረግ፣ ዑምራ ማድረግ፣ ... ከሞቱም በኋላ አጅራቸው እንዲቀጥሉ ከሚያደርጉ ተግባራት ውስጥ ናቸው። = ©️ኢብኑ ሙነወር https://t.me/amu_dawa
❝ዛሬ ላይ ብዙ ሰዎች ሁለተኛ ሴት ማግባትን ይፈልጋሉ፤ ነገር ግን የፍትሕንና የኃላፊነትን ትርጉም አያውቁትም። ተአዱድ(ከ አንድ በላይ ማግባት) ለሁሉም ሰው በሩ የተከፈተ አይደለም። አንድ ሰው አካላዊ፣ ፋይናንሳዊና አእምሮአዊ ብቃት ሳይኖረው፣ የሁለተኛዋንና የመጀመሪያዋን ሀቅ ሳይጠብቅ አገባለሁ ማለቱ ወደ አደጋና ወደ ወንጀል መግባት ነው።❞ ✅ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁልላህ)
ትልቁ ኪሳራ ማለት...ጀናዛው ላይ ሊሰገድበት ብቻ ተብሎ መስጊድ የገባ ሰው ነው። ልትቀበር ተብላ በከፈን ጊዜ ብቻ ሒጃቧን ፀጉሯን የሸፈነ ሴት ናት።ጌታዬ ሆይ በዲንህ ላይ አጽናን።መልካም መመለስን ወዳንተ መልሰን። https://t.me/amu_dawa
.......ለወላጆችህ የምታሳየው በጎነትና ክብር አንተ ራስህ የምትጽፈው ታሪክ ነው፤ ነገ ደግሞ ልጆችህ መልሰው ያነቡልሃል። ስለዚህ ዛሬውኑ ታሪክህን በጥሩ ሁኔታ ጻፍ.......
🔵 የሚገርም ነው ነገሩ እንዲህ ነው ✴️ በአንድ ቀበሮ ጭራ ላይ ከባድ ድንጋይ ወድቆ ጭራውን ቆረጠው። ✨ ሌላ ቀበሮ አየውና፦ “ጭራህን ለምን ቆረጥከው?” ብሎ ጠየቀው። ✨ እርሱም፦ “በአየር ላይ እንደምበር ያህል ይሰማኛል፤ ምንኛ ታላቅ ደስታ መሰለህ!” አለው። 🔴 ይህንን ሲሰማ (ሁለተኛውም) ጭራውን እንዲቆርጥ አደረገው! ነገር ግን ብርቱ ሕመም በተሰማውና እንደተባለውም ምንም ዓይነት ደስታ ባላገኘ ጊዜ፦ “ለምን ዋሸህብኝ?” ሲል ጠየቀው። ✨የመጀመሪያው ቀበሮ እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ለሌሎቹ ቀበሮዎች ስለ ሕመምህ ከነገርካቸው ጭራቸውን አይቆርጡም፤ በእኛም ላይ ያፌዙብናል።” ⚫️ በመሆኑም ያገኙትን ቀበሮ ሁሉ ስለሚያገኙት (የሐሰት) ደስታ መናገራቸውን ቀጠሉ፤ ይህም በመሆኑ አብዛኞቹ ቀበሮዎች ጭራ አልባ እስኪሆኑ ድረስ ሆነ! ከዚያ በኋላ ጭራ ያለው ቀበሮ ባዩ ቁጥር ያፌዙበትና ይንቁት ጀመር! (ብልሽት (ፈሳድ) በሰፈነ ጊዜ፣ ሰዎች ደጋግ ሰዎችን በበጎነታቸውና በደግነታቸው ማነወሪያ ያደርጓቸዋል! መሃይማንና ሞኞቹም መሳለቂያ ያደርጓቸዋል።) 🔵 ኢማም ሹረይሕ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦ “በሰዎች ላይ አንድ ዘመን በእርግጥ ይመጣል፤ ዛሬ አመጸኛ (ፋጂር) በአመጽነቱና በክፋቱ እንደሚነቀፈው ሁሉ፣ አማኝም በእምነቱ የሚነቀፍበት፤ እንዲያውም አንድን ሰው ለማጣጣል ሲባል ‘አንተ እኮ አማኝና አሊም ደረሳ ነህ’ እስኪባለው ድረስ።” 🔷ብልሹ ማኅበረሰብ ለሚያስተካክሉና ለሚገሥጹ ሰዎች የሚለጥፍላቸው መጥፎ ነገር በታጣ ጊዜ፣ በእነርሱ ውስጥ ባለው እጅግ ውብና መልካም በሆነው ነገር ያነውራቸዋል... ✴️(የሉጥ ሕዝቦች):- የሉጥን ቤተሰቦች ከመንደራችሁ አስውጡ፤ እነሱ ንጽሕናቸውን የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው አሉ ንፅህናቸውን በመጠበቃቸው ብቻ በአካባቢው ባይተዋር ተደረጉ 🔴 ዛሬም ወደ እርቃንነት (መገላለጥ) መጣራትና መሸፈኛን(ኒቃብን)ና ጥንቁቅነትን (ዒፋን) ወደ መጣል ከሚደረገው ጥሪ ጋር እየሆነ ያለው ነገር በትክክል ይህንን ነው። ⚫️ ነገሩማ አማኝ ሴትን በመሸፈኗና በጥንቁቅነቷ ወደ ማስወለቅና መውቀስ ደረጃ ይደርሳል፤ ሒጃቧንና ጠንካራ መሸፈኛዋን አጥብቃ ስትይዝ ባዩዋት ጊዜ በኋላቀርነት፣ በመሀይምነት፣ በትዕቢትና በስነ-ልቦና መዛባት ይፈርጇታል። ✴️ እንዲሁም ብልሁ፣ ጥንቁቁና አማኙ ወንድ በጥንቃቄው፣ በብልህነቱ፣ በእምነቱና አላህን በመፍራቱ ይወቀሳል። በዚያን ጊዜ “(ዲኑን አጥብቆ የያዘ ሰው ልክ የጋለ ፍም እንደጨበጠ ነው)” የሚለውን ሐዲሥ እውነተኛ ትርጉም ትረዳለህ፤ ✨ ምክንያቱም ከዚህች የስቃይ ምድር በኋላ ስፋቷ እንደ ሰማያትና ምድር የሆነች፣ ለአላህ እሱን ለሚፈሩት የተዘጋጀች ጀነት እንዳለች ያውቃልና። 📝 ወንድሞቼ እና እህቶቼ ሆይ ✴️ሐራም የሆነ ነገር ሰዎች ሁሉ ቢፈጽሙትም እንኳ ዘላለም ሐራም ሆኖ ይቀጥላል፤ ✴️ሒጃብ ሴቶች ሁሉ ቢያወልቁትም እንኳ ግዴታ ሆኖ ይቀጥላል፤ ✴️ሞት በሕይወት ያሉ ሁሉ ቢረሱትም እንኳ እውነት ሆኖ ይቀጥላል፤ ✴️ በመጨረሻም የተውበት በር አንድ ባሪያ ወደ ወንጀል ሺህ ጊዜ ቢመለስም እንኳ ክፍት ሆኖ ይቀጥላል። ✨ አላህ ሆይ! ጥራት ይገባህ፣ ክብርህ ምንኛ ታላቅ ነህ 📝إبن أبي الدنيا الحبشي : محرم ١٤٤٨
⚡️ብቻህን ስትሆን የሚያየኝ የለም ብለህ ወንጀል አትስራ 🌑ጨለማ ውስጥ እንኮ ብትሆን ጨለማን የፈጠረው ጌታ ያየሀልን ©️tulab_ibnumurad
ዛሬ ላይ ሶሻል ሚዲያ የሁላችንም ትልቅ ፈተና ሆኗል። በቤትም ሆነ በመስጊድ ሳይቀር ቀልባችንን ሰርቆት ውድ ጊዜያችንን እየወሰደብን ይገኛል። አንዳንዴ በሚዲያ ላይ የምናሳልፈው ጊዜ ለኽይር ነገር ቢሆን እንኳ፤ ቆም ብለን ራሳችንን መፈተሽ ብልህነት ነው። «ከዚህ ሚዲያ በስተጀርባ የተሻሉ መልካም ነገሮችን እያሳለፍኩ ይሆን? የዕለት ተዕለት ኃላፊነቴን በአግባቡ እየተወጣሁ ነው? ለልጆቼና ለትዳር አጋሬ የሚገባቸውን ትኩረትና ጊዜ እየሰጠሁ ነው ወይስ ማኅበራዊ ሚዲያው ሐቃቸውን እንዳጓድል መሰናክል ሆኖብኛል?» ብለን ራሳችንን እንጠይቅ። በተለይ ይህንን የክረምት ወቅት በተሻለና ይበልጥ ፍሬያማ በሆነ መልኩ ለመጠቀም አሁኑኑ ፕሮግራም ብናወጣ መልካም ነው። አላህ ይገዘን! ©️Sle_qelbach
Be smart https://t.me/amu_dawa
ትዳርን ከዕድሜ እና ከዓመታት ቁጥር ጋር ማገናኘት ሁልጊዜም ትክክል ላይሆን ይችላል። ትክክለኛው የጋብቻ ጊዜ በአሥራዎቹ፣ በሀያዎቹ ወይም በሰላሳዎቹ ዕድሜ ውስጥ መሆኑ መስፈርት አይደለም።ግዴታም አይሆንም። ዋናው ጥያቄ «መቼ ላግባ»ሳይሆን «ማንን ላግባ» የሚለው ነው። እውነተኛው የትዳር ጊዜ የሚጀምረው፣ ልክ የተፈጠረልህና አብሮህ ሊዘልቅ የሚችል ትክክለኛው ሰው በሕይወትህ ውስጥ ሲከሰት ነው። ያኔ ዕድሜው ሀያ፣ ሰላሳ ወይም አርባ ቢሆን እንኳ አልሐምዱ ሊላህ ብለህ ወደ ሕይወትህ ታስገባዋለህ። እናማ…ትዳር ሪዝቅ ነውና በጊዜው ይመጣል ከዕድሜያችሁ ጋር አታያይዙት። t.me/Sle_qelbachn1 t.me/Sle_qelbachn1
«አህሉል አሠር» የሞባይል አፕልኬሽን ይህ መተግበሪያ የተለያዩ ኢስላማዊ ደርሶችን በደረጃና በስርዓት ለመማር እጅግ አመቺ ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን፣ የሚከተሉትን ጠቃሚ ይዘቶች በአንድ ላይ አካቶ ይዟል፦ ዘርፈ-ብዙ የኪታብ ደርሶች፦ የዐቂዳ፣ የመንሀጅ፣ የሲራ፣ የአደብ፣ የሐዲሥ፣ የፊቅህ፣ የነሕው እና የሶርፍ ትምህርቶች። እያንዳንዱ የድምፅ ቅጂ (ኦዲዮ) ከኪታቡ ሶፍት ኮፒ (PDF) ጋር አብሮ የተያያዘ ነው። አፑን ለአጠቃቀም ልዩ እና ምቹ የሚያደርጉት ባህሪያት፦ • ደርሶችን ከጀማሪ ጀምሮ ደረጃ በደረጃ በቅደም-ተከተል የሚያስተምር። • ትምህርቱን ሲጨርሱ ራሶን የሚፈሹበት ፈተናዎች ያሉት። • በትምህርቱ መሃል አስፈላጊ ነጥቦችን በቀላሉ መፃፍ የሚያስችል ጥሩ ማስታወሻ መያዣ ያለው። • የደርሶች ማውጫ በየዘርፉ በጥራት የተከፋፈለበት። • የፈለጉትን ደርስ በቀላሉ መልሰው ለማግኘት ምልክት ማድረግ የሚያስችል። • ከቅጅዎቹ መካከል የመረጡትን ለሌሎች ማጋራት (Share) የሚያስችል አማራጭ። • አፑን ለአጠቃቀም አመቺ የሚያደርጉት ማስተካከያዎች ያሉት። • ደርሱን አቋርጠው በሌላ ጊዜ ማዳመጥ ቢፈልጉ በትክክል ካቆሙበት ሰከንድ የሚጀምር። የአፕሊኬሽን አዘጋጅ፦ HUDASOFT https://t.me/hudasoft ይህ ስራችን የላቀው አላህን ፊት ብቻ ተፈልጎበት የተሰራ (የጠራ) ይሆን ዘንድ፤ በዚህ ስራ ላይ ለተባበሩትም ሆነ ይህንን ስራ ለሚያሰራጩት በሙሉ አላህ መልካም ስራችንን እንዲቀበለን እንማፀነዋለን። አፑን አሁኑኑ አውርደው ይጠቀሙበት፦ 🔗 የማውረጃ ሊንክ (Google Play Store)፦ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.ahlulaser.hs.app
ትምህርት የጨርሳችሁ ተማሪዎች ካላችሁ ይቺን አጭር ምክር ስማኝ ክረምት መጣ ማለት ለተማሪዎች ትልቅ ዕድል ነው! ይህንን የክረምት እረፍት በፊልምና በጌም ብቻ እንዳያባክኑት 🎒 ✅ክረምት መጣ፣ ትምህርት ተዘጋ! አንዳንዶቻችሁ ገና ከወዲሁ የክረምቱን 3 ወር ሙሉ የሚያስረግጥ የፊልም እና የቪዲዮ ጌም "Folder" አዘጋጅታችሁ ስልካችሁና ኮምፒውተራችሁ ላይ መሸጎጣችሁ አይታወቅም እንዳትሉ! ግን ጥቅሙ ምንድን ነው? ፊልሙ ያልቃል፣ ጌሙ ይሰለቻል፣ መስከረም ላይ ደግሞ ባዶ እጅህን ወደ ትምህርት ቤት ትመለሳለህ። ይልቅ ይሄንን አስብበት፡ ✅አዲስ Skill (ክህሎት) ተማር ይሄ የ2 ወር እረፍት በአሁኑ ዘመን በጣም ተፈላጊ የሆኑትን እንደ Graphic Design, Coding, Accounting Softwares, የቋንቋ ማሻሻያ (English) ወይም የዲጂታል ማርኬቲንግ ክህሎቶችን የምትሰርቅበት ወርቅ እቅድ ነው። ✅በቀን 1 ሰዓት ብቻ አዲስ ነገር ለመማር ብትሰጥ፣ ክረምቱ ሲያልቅ አንተ የድሮው ተማሪ አይደለህም፤ አዲስ አቅም ያለውና ራሱን ያሳደገ "VIP" ተማሪ ነህ! በጌም ላይ "Level 100" መድረስህ ወይም የፊልሙን ገጸ-ባህሪ በደንብ ማወቅህ ለወደፊት ህይወትህ የሚጨምረው "ሲቪ" (CV) የለም! እውነታው ግን... ክረምቱ ሲያልቅ ጓደኞችህ አዲስ ክህሎት ለምደውና ተለውጠው ሲመጡ፣ አንተ ግን አሁንም በፊልም ገጸ-ባህሪ ስም ስትቀልድ መኖር የለብህም። ስለዚህ ፊልሙንም፣ ጌሙንም ተወውና ህይወትህን የሚቀይር አንድ ስኪል (Skill) ዛሬውኑ መማር ጀምር! በእርግጥ ምክር ቀላሉ ነው ግን ዘመኑ በጣም እየከበደ ነው እራስህን ነፃ ማውጣት አለብህ
👉በጣም ትልቁ አይብ (ወርደት) ማለት የራሱን አይብ ረስቶ የሰዎችን አይብ የሚከታተል ሰው ነው 👇 قَبِيحٌ عَلَى الإِنْسَانِ يَنْسَى عُيُوبَهُ وَيَذْكُرُ عَيْباً فِي أَخِيهِ قَدِ اخْتَفَى فَلَوْ كَانَ ذَا عقلِِ لَمَا عَابَ غَيْرَهُ وَفِيهِ عُيُوبٌ لَوْ رَآهَا بِهَا اكْتَفَى https://t.me/amu_dawa
ዱንያ ላይ ምን ደስ እንደሚል ታውቃለህ…? 🤍 አላህ ሷሊሕ ልጆችን ሰጥቶህ፣ የፈጅር አዛን ሲል ትልልቆቹን ቀስ ብለህ ቀስቅሰህ፣ እጅ ለእጅ ተያይዛችሁ ወደ መስጂድ ስታቀኑ… ከሶላት በኋላ አብራችሁ የጠዋት ደርስ ቀርታችሁ፣ ወደ ቤት ስትመለሱ ከምትወዳት ሚስትህ ጋር የተዘጋጀውን ቁርስ በልታችሁ፣ ልጆችህን መርቀህ ወደ ትምህርት ቤት ስትሸኛቸው… ቀኑን ሙሉ ስትለፋ ውለህ ማታ ወደ ቤትህ ስትመለስ፤ ገና በር ሊከፈት ሲል ድምፅህን ሰምተው "አቢ መጣ! ባባ መጣ!" እያሉ እየተሻሙ ሲሮጡ… አንዱ በቀኝህ፣ ሌላኛው በግራህ ሲንጠለጠል፣ ትንሹ ደግሞ እግርህ ላይ ሲጠመጠም… ጠዋት ለስራ ስትወጣ "አቢ ሄደብን" ብለው ሲያለቅሱና ሲያኮርፉ ስታይ… ያኔ ነው ዱንያ እውነተኛ ጣዕሟ የሚገባህ! ያኔ ነው ጠዋት ስትወጣ ለምንና ለነማን ብለህ እንደምትወጣ፣ ምን ዓይነት ትልቅ ዓላማ እንዳለህ የሚሰማህ። ውዷን ሚስትህንና እነዚህን የአላህ ስጦታዎች አንደላቅቀህ ለማኖር ስትለፋ ድካምህ ሁሉ ወደ ደስታ ይቀየራል፤ ማታ ስትመለስም ቤትህ ከምንም በላይ ይናፍቅሃል። ቤታችሁ ራሱን የቻለ የዒባዳህ፣ የቁርኣን ቂርኣት፣ የዚክር፣ የመዝናኛ፣ የጥናትና የጨዋታ ጊዜ አለው። ሚስትህም የቤቱ ብርሃን ሆና፣ የልጆቹ መምህርና ሙረቢ፣ ያንተ የልብ እረፍት ትሆናለች። ላጤ ከሆንክ ግን ስትወጣም ስትገባም ማንም አይጠብቅህም፤ የለፋህበትም ድካም የዚህን ያህል ጥልቅ ትርጉም አይሰጥህም! ስለዚህ… አግባ ሐቢቢ! ዲን ያላትን ምረጥ፤ አላህ የዚህች ዱንያ ጀነት የሆነውን ያማረ ትዳርና ሷሊሕ የሆኑ ልጆችን ይወፍቅህ! 🤍💓 ©️Murad Tadesse
👌ሁለት አይነት ሰዎች ኢልምን አያገኙም 1ኛ ፈሪ (ኢልም እየተማረ ጥያቄ መጠየቅ እየፈለገ ለመጠየቅ የሚፈራ) 2ኛ ኩራተኛ መማር እየፈለገ ኩራት ይዞት እገሌ እበልጠዋለሁ እሱ ላይ አልማርም ብሎ የማይማር 🌱...ሰለፎች ኢልም ሲማሩ በጣም ይጠይቁ ነበረ እንደዚሁም ኢልምን ከሚበልጣቸውም ከሚያንሳቸውም ይማሩ ነበረ https://t.me/amu_dawa
🌷 የዕለቱ ሐዲስ 🌷 ከአቡ ሁረይራ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተወራው፣ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ አሉ፦ «ነፍሴ በእጁ በሆነችው ጌታ እምላለሁ! በሰዎች ላይ አንድ ዘመን በእርግጥ ይመጣል፤ ገዳይ በምን ምክንያት እንደገደለ የማያውቅበት፣ ተገዳይም በምን ምክንያት እንደተገደለ የማያውቅበት።» 📚 ረዋሁ ሙስሊም ━━━━━━━━━━━━━━ 💎 ከሐዲሡ የምንቀስማቸው ትምህርቶች 🔸 የመጨረሻው ዘመን ፈተና (ፊትና) ሐዲሡ በመጨረሻው ዘመን ሊበራከት ስለሚችለው ብጥብጥና ያለ ምክንያት የሚፈሰው ደም ያስጠነቅቃል። 🔸 የሰው ሕይወት ክቡር ነው ኢስላም የሰውን ሕይወት ይጠብቃል፤ ያለ ሐቅ ሕይወትን ማጥፋት ታላቅ ወንጀል ነው። 🔸 ከጭፍንነትና ከድንቁርና መጠንቀቅ ሰው በማያውቀው ጉዳይ መከተልና በቁጣ መወሰን ወደ ከባድ ጥፋት ሊያመራ ይችላል። 🔸 በፈተና ጊዜ መጠንቀቅ ሙስሊም በፊትና ጊዜ ራሱን ከግጭትና ከደም መፋሰስ በመጠበቅ ወደ አላህ መሸሸግ ይገባዋል። ━━━━━━━━━━━━━━ 🌹 አጭር ምክር "በፊትና ጊዜ እጅህንና ምላስህን ጠብቅ፤ የሰውን ደም በግፍ ከማፍሰስ ራቅ።" ━━━━━━━━━━━━━━ 🤲 ዱዓ اللَّهُمَّ إِنَّا نَعُوذُ بِكَ مِنَ الْفِتَنِ، مَا ظَهَرَ مِنْهَا وَمَا بَطَنَ "አላህ ሆይ! ከታየውም ሆነ ከተሰወረው ፈተና በአንተ እንጠበቃለን። አሚን።" 🤲 ━━━━━━━━━━━━━━ ©️ https://t.me/amumsu1
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته ኢንሻአላህ ነገ ከexit ፈተና ጋር ተያይዞ ጁሙዓ ሰላት በቶሎ ስለሚያልቅ ሁላችንም ቀደም ብለን ለመገኘት እንሞክር:: ይሄንን መልዕክት ለሁሉም GC ተማሪዎች #share አደርጉ ባረከላሁ ፊኩም። © GC COMMITTEE
kureja! be sheikh ahmed adem yetesete fetwa.
видео или голосовое, без подписи
ኸበር-ኒካህ ከነጭ ሳር ካምፓስ አልፍ ሚልዮን መብሩክ አልፍ ሚልዮን መብሩክ !!! 🌷🌺🌷🌺🌷🌺🌷🌺🌷 🌺 ባረከሏሁ ለኩማ .🌺 🌷 .🌷 🌺 ወባረከ አለይኩማ . 🌺 🌷 .🌷 🌺 ወጀመዓ በይነኩማ .🌺 🌷 .🌷 🌺 ፊኸይር .🌺 🌷🌺🌷🌺🌷🌺🌷🌺🌷 ትላንት ማለትም 08/10/2018 አ.ል የውድ ወንድማችን እና የኡስታዛችን ነጂብ ረሻድ (12 batch MLS) እና የእህት ሮዛ ነስሬ የኒካህ ፕሮግራም ተፈፅሟል። ትዳራችሁን አሏህ ያማረ እና የሰመረ, ለኡማው የሚጠቅሙ ሷሊህ ልጆችን የምታፈሩበት የተባረከ ያድርግላችሁ ። بارك الله لكما وبارك عليكما وجمع بينكما في خير