AMU MSJ Main Campus
СтатистикаThis is the channel of the AMU MSJ Main Campus. Sectors 👇 https://t.me/amumsjsmcs https://t.me/amu_mc_msj_supportivesector https://t.me/amu_dawa https://t.me/Amumuslimacademicsector https://t.me/zxdelivery https://t.me/amuziyaar https://t.me/ummumabd
- Последний пост
- 11:57
- Последнее чтение
- 08:44
- Постов за неделю
- 15
- Всего постов
- 37
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 138
- 1/48двое суток
- 158
- 1/72трое суток
- 170
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
🛡 በመውደቅና በመነሳት መካከል ያለው ጉዞ🛡 አንድ አማኝ በዚህች ምድር ላይ ያለው ቆይታ የዕድሜ ልክ "ጂሃድ" (ትግል) ነው። ይህ ትግል ከጠላት ጋር ሳይሆን ከገዛ ነፍሱ ጋር የሚደረግ የቤት ስራ ነው። ⚔️ ነፍስህ ሁልጊዜም ወደ ስሜትና ወደ ምቾት ታዘነብላለች፤ አንተ ደግሞ ወደ አላህ ትእዛዝ ትጎትታታለህ። አንዳንድ ጊዜ ታሸንፋታለህ፤ ብዙ ጊዜ ደግሞ ታሸንፍሃለች። ነገር ግን ዋናው ቁምነገር መሸነፍህ ሳይሆን፣ ተስፋ ቆርጠህ ትግሉን አለማቆምህ ነው። ትልቁ ስኬት አሸናፊ ሆነህ፣ ከነፍስህ ግፊት ነፃ ወጥተህ አላህን መገናኘት ነው። ⛔️ ከቀጥተኛው መንገድ (እስቲቃማ) በኋላ ወደ ኋላ መመለስ እጅግ ያማል። ምክንያቱም አንተ ቀደም ሲል የታዛዥነትን (ጧዓን) ጥፍጥና ቀምሰሃል፤ የሱጁድን ሰላም፣ የቁርአንን ብርሃንና የዱዓን እርካታ አውቀሃል። ከዚያ ብርሃን ወጥተህ ወደ ርቀት መራራነትና ወደ ጨለማው ስትመለስ የሚሰማህ የልብ ስብራት ከባድ ነው። ⚠️ ወዳጄ መለየት ያለብን ሁለት ነገሮች፦ "ፉቱር" መዘናጋት ድካም እና "ኢንቲካሳ" ወደኋላ መመለስ ብዙዎቻችን በሁለቱ መካከል ያለውን ልዩነት ባለመረዳት ሰይጣን እንዲያታልለን በር እንከፍታለን፦ 1. ፉቱር (መንፈሳዊ መዘናጋት/ድካም)፦ ይህ በሰው ልጅ ተፈጥሮ ውስጥ ያለ ነው። የትርፍ (ናፊላ) ስራዎች ላይ መስነፍ፣ ቁርአን የመሐፈዝ ፍላጎት መቀነስ፣ ዚክር ላይ መዛል... ይህ መንፈሳዊ ድካም ነው። መፍትሄውም ነፍስን መታገልና በትንሽ በትንሹ ወደ ነበረችበት መመለስ ነው። 2. ኢንቲካሳ (ወደ ኋላ መመለስ/ማፈንገጥ)፦ አደገኛ የሚሆነው ግን አላህ ግዴታ (ዋጅብ) ያደረገብህን ትተህ "መንፈሴ ደክሟል" ወይም "ኢንቲካሳ ውስጥ ነኝ" ብለህ ማመካኘት ስትጀምር ነው። አላህ የደነገገብህን "ፈርድ" ስራዎች ጥለህ ለወንጀልህ "ኢንቲካሳን" እንደ ሽፋን አትጠቀምበት። ድካምህ ለሀራም ስራዎች ሰበብ ሊሆን አይገባም። ⚠️ወዳጄ ሰላት የመጨረሻው ቀይ መስመርህ ናት! መንፈስህ ቢዝል፣ ልብህ ቢደርቅና ስሜትህ ቢያሸንፍህ እንኳ ሰላትህን በፍጹም እንዳትለቅ! ሰላት በአንተና በአላህ መካከል ያለ የመጨረሻው የቃል ኪዳን ገመድ ነው። ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ *«በእኛና በእነሱ(በካፊሮች) መካከል ያለው ቃል ኪዳን ሰላት ነው፤ የተዋትም በእርግጥ ካደ ከፈረ።»* ✨ በየቀኑ ለነፍስህ ንገራት!"ነፍሴ ሆይ! ብትደክሚም ዋጅቦችን አትተይ፤ ብትሰለችም ከአላህ አትራቂ። ዛሬ ብትወድቂ ነገ ተነስተሽ ታገዪ፤ ዋናው ነገር አላህ ዘንድ በሽንፈት ሳይሆን በሙከራና በትግል ላይ ሆነሽ መገኘትሽ ነው!"በላት አላህ በቀጥተኛው መንገድ ላይ የምንጸና፣ ስንወድቅም ፈጥነን የምንነሳ ባሮች ያድርገን።
🌹 አላህ አንድን ባሪያውን ሲወደው . . . አላህ (سبحانه وتعالى) አንድን ባሪያውን ሲወደው፤ በልቡ ውስጥ ደግነትን፣ ቅንነትንና እዝነትን (ራህመትን) ያሰፍንለታል። ይህ የልብ ስጦታ ከማንኛውም ዓለማዊ ሀብት በላይ ትልቅ የጌታ በረከት ነው፤ ምክንያቱም በደግነት የታነጸ ልብ የሰላም ሁሉ መገኛ ነውና። በአላህ ውዴታ የተከበበ ባሪያ፤ በሰዎች ላይ በደልን (ዙልምን) አይፈጽምም፣ በትዕቢት አይታበይም፣ ቃል ኪዳን አያፈርስም፣ ተንኮልን አይሸርብም፣ እንዲሁም ታማኝነትን እንጂ ክህደትን በፍጹም አያውቅም። ስብዕናው በአላህ ፍርሃትና ውዴታ የተገራ ነውና። የአንድ ሰው እውነተኛ ታላቅነት የሚለካው ለፍጡራን በሚያሳየው ርኅራኄ ነው። ልብ በአላህ ብርሃን ሲታጠብ፣ ተግባር ሁሉ ይቃናል፤ ያኔ አላህ የሰዎችን ልብ ለዚያ ባሪያ ታዛዥና አፍቃሪ ያደርጋቸዋል። የመልካም ስነ-ምግባር ምንጭ የአላህ ውዴታ ምልክት ነው። አንድ ሰው ከሰዎች ጋር ያለው ግንኙነት ሲያምር፣ ይህም አላህ በውስጡ የዘራው የእዝነት ፍሬ ውጤት መሆኑን ያስገነዝባል። አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) ለባሪያዎቹ ከሰጣቸው ትላልቅ ፀጋዎች መካከል በፍጥረታቱ እንዲወደዱ ማድረጉ ነው። 🌹አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) ለሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) እንዲህ አላቸው :- { وَأَلْقَيْتُ عَلَيْكَ مَحَبَّةً مني } سورة طه، الآية ٣٩. "ባንተ ላይም ከእኔ የኾነን መወደድ ጣልኩብህ።" ኢብኑ ከሲር ይህን የቁርአን አያህ ሲያብራሩ "አንድም ሰው ሙሳን አይመለከታቸውም የተመለከታቸው ሰው ሁሉ የወደዳቸው ቢሆን እንጂ" ብለዋል። ኢብኑ አል-ሙንከዲር ለአቢ ሐዚም እንዲህ አላቸው፦ ሰዎች ሲያገኙኝ በመልካም ነገር ዱዓ ያደርጉልኛል። እኔ አላውቃቸውም ከነርሱ ጋር በጋራ መልካም ተግባር ፈፅሜም አላውቅም። (ለነርሱም ያደረኩላቸው መልካም ነገር የለም) አቡ ሐዚምም እንዲህ ብለው መለሱላቸው፦ "ይህ የአላህ ችሮታ ነው።" { سَيَجْعَلُ لَهُمُ الرَّحْمَنُ وُدًّا } "አር-ረሕማን ለእነሱ ውዴታን ይሰጣቸዋል።" ኢላሒ...! አንተ ከምትወዳቸውና በልባቸው ውስጥ ደግነትን ካሰፈርክላቸው ምርጥ ባሮችህ መካከል አድርገን። آمين يارب 🤲
سلامٌ على مدينةٍ أضاءت بنور الحبيب ﷺ،🌙 وسلامٌ على كل قلبٍ اشتاق إليها. 🤍
سلام عليكم ورحمة الله وبركاته✨✨ እንደምን እንዴትስ ሰነበታችሁ??? እናማ ያው አናቀዋለን ግን እስኪ ትንሽ እናውጋው! ለምንድነው ለልብ ደስታና ሰላሟን በሚነፍግ ነገር ውስጥ ምንዘወትረው እእ?? ከወንጀል ምናተርፈው የደቂቃዎች እርካታ እንዴትስ አርገን ነው ከዘላቂው ፀፀት ጋ ያወዳደርነውስ??ልብ ላይ ሸክምን ጥሎ፣አጠልሽቶ፣የህይወትን መንገድ አቆላልፎ እንዴትስ ወደድነው እ ለምንስ ስሜት እስረኛ መሆንን ሻትን ሽተንስ አደለም ግን ከዚ አዙሪት ለመውጣት መጣርን ማን ወሰደብን?? ብዙ ተስፋን ያነገበ፣ነገውን ለማቅናት ያሰበ፣ ስኬትን የፈለገ፣ለልብ ሰላም፣ብርሀን የሚማስን፣ የነገሮችን መቻል የሻተኮ ረጂው፣ ደጋፊው፣መሪው፣ጠጋኙ በቃ የሁሉም ነገሩ እስተናባሪውን አብሮነት ወዳጅ ነው፡፡እንዴትስ ከሱ መራቅን ይሽታል? እንደው በሰዋዊነቱ ቢደናቀፍ እያነከሰም ቢሆን ሚያንኳኳው የሱን ደጃፍ ነው፡፡ለአጥፊነቱም መሀርታን ዘዉትር ፈላጊ ነው፡፡ እናማ ልቡን ሰላም የነሳውን፣እሱነቱን ሚነጥቀውን መዕሲያ መላቀቂያ መንገድን ፣መሀርታን ፍለጋ ጌታው ዘንድ ጠያቂ ነው እሱ አየሳፍረውምና!! እናማ ግዴለም እንመለስ ልባችንም ይርጋ ጂሙአም አይደል ሱናዎችን ሀይ እያረግን ያ ጀመአ 👉ገላን መታጠብ 👉ጥፍርን መቁረጥ 👉ጥሩ ልብስ መልበስ 👉 ሽቶ መቀባት(ለወንዶች) 👉 ሲዋክ መጠቀም 👉 በግዜ መስጂድ መግባት 👉ኢማሙ ሚንበር እስከሚወጣ ድረስ የሱና ሰላት መስገድ 👉ሰላዋት ማብዛት 👉 ሱረቱል ከህፍ መቅራት 👉ኹጥባ በጥሞና ማድመጥ ደሞ ደሞ ✨✨صل على النبي ىا جمع✨ ❤️ الَّلهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ عَلَى نَبَيِّنَا مُحَمَّد
የአላህ መልዕክተኛ ወንጀለኞችን እንዴት ያርሙ ነበር? 🥀የአላህ መልዕክተኛ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከወንጀለኞች ጋር እጅግ አዛኝ ነበሩ። ምክንያቱም እነኚህ ወንጀለኞች የሰው ልጅ እንደመሆናቸው መጠን ነፍሳቸው ደክማ በዛ ወንጀል ላይ እንደወደቁ ስለሚያውቁና ወደ አላህ የሚያቃርባቸው አካል እንደሚያስፈልጋቸው ሰለተረዱ ነው። ✔️ ከአጋጣሚዎቻቸውም መካከል፦ 1/ ኡማማተል ባሂሊ ባስተላለፈው ሀዲስ አንድ ወጣት ወደ ነብዩ(ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) መጣና እንዲህ አላቸው፦ " አንቱ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ዝሙትን ይፍቀዱልኝ" እንዲህ ሲል የአላህ መልዕክተኛ ባልደረቦች ተንጫጩ ወቀሱትም ።ከዛም የአላህ መልዕክተኛ "ወደኔ ተጠጋ" አሉት።ከዛም ይህ ወጣት ወደ ረሱል ተጠጋ። የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉት፦ "ይህን ተግባር ለእናትህ ትወደዋለህ? " ከዛም ወጣቱ " አላህ የርሶ ቤዛ ያደርገኝና በአላህ እምላለሁ አልወደውም " የአላህ መልዕክተኛ፦ " ሰዎችም እኮ ለእናቶቻቸው አይወዱትም " ቀጠሉ " ለሴት ልጅህስ ትወደዋለህ? " ወጣቱ፦ " አላህ የእርሶ ቤዛ ያድርገኝ በአላህ እምላለሁ አልወደውም " የአላህ መልዕክተኛ፦ " ሰዎችም አኮ ለሴት ልጆቻቸው አይወዱትም " ከዛም ለአክስትህ ለእህትህ እያሉ ቀጠሉ።በሁሉም ጊዜያት ታድያ ይህ ወጣት አይ የአላህ መልዕክተኛ አልወድም እያለ ይመልስ ነበር።ከዛም ረሱል እጃቸውን ደረቱ ላይ አደረጉና እንዲህ ብለው ዱኣ አደረጉለት፦ " ጌታዬ ሆይ! ወንጀሉን ማርለት ልቡን አንፃለት ብልቱን ጠብቅልት " ይህ ወጣት ከዚህ በኃላ ዝሙት እሱ ዘንድ እጅግ የተጠላ ሆነ! ** የምንረዳው ቁም ነገር ፦የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከሁሉም ሰው በላይ የአላህን ድንበሮች የሚጠባበቁ ሁነው ለእዚህ ወጣት ያደረጉትን ነገር ተመልክተናል።በእዝነትና በእርጋታ እንዲሁም በጥበብ የተሞላ ምላሽ ነበር የመለሱለት።እሱን ከመቆጣትና ከመጮኽ ይልቅ ድክመቱን ተረድተው በዘዴ ቀስ ብለው ያደረገው ድርጊት ትክክል እንዳልነበር አስተማሩት ከዛም ዱዓ አደረጉለት። 2/ በነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ዘመን አብደላህ የተባለ ሰው ረሱልን ያስቃቸው ነበር። በሆነ አጋጣሚ መጠጥ በመጠጣቱ ረሱል ቅጣት አቋቋሙበት ከዛም በሌላ ጊዜ ደግሞ ጠጥቶ መጣና ተገረፈ።ከዛ አንድ ሰው ተነሳና " ጌታዬ ሆይ! እርገመው! ስንት ጊዜ ነው የሚመጣው!? " ብሎ ሲረግመው ነብዩ ሰሙትና ፊታቸው ተቀያየረ " በአላህ እምላለሁ ከእሱ የማውቀው አላህና መልዕክተኛውን የሚወድ መሆኑን እንጂ ሌላን አላውቅም " አሉ ** የምንረዳው ቁም ነገር ፦ አንድ አማኝ ወንጀለኛ እንኳን ቢሆን መልካም የሚባል ነገር ስለሚኖረው ሰዎች በወንጀሉ ሲያነውሩት እኛም የምናውቀውን መልካም ነገር በማንሳት ልናስቆም እንደሚገባን ነው ። 3/ ሙአዊያህ ቢን አልሀከም ባስተላለፈው ሀዲስ እንዲህ ይላል ፦ "ረሱል (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር እየሰገድኩ ሳለ ከሰጋጆች መካከል ዘንድ ሰው ያስነጥሳል ። ከዛም ሙአውያህ ለሰጋጁ አካል "አላህ ይዘንልህ " ይለዋል። ሰጋጆች እንዲህ ስል በውግዘት አስተያየት ተመለከቱኝ ። ከዛም " ምን ሁናችሁ ነው ምንድን ነው ጉዳያችሁ እኔን የምትመለከቱኝ!?" አልኳቸው። ሰጋጆች ዝም ሊያሰኙኝ ታፋቸውን ይመታሉ። ከዛ ሰላቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ዝም አልኩኝ ። እናቴም አባቴም ለአላህ መልዕክተኛ ቤዛ ይሁንላቸው በአላህ እምላለሁ አልገላመጡኝም ፣ አልመቱኝም ፣ አልሰደቡኝምም " ከዛም የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለው አረሙት ፦ " ይች ሰላት እኮ ከሰዎች ንግግር አንዳችም አይሆንባትም። እሷ እኮ አላህን ለማጥራትና ለማላቅ እንዲሁም ቁርዓንን ለመቅራት ናት " ** የምንረዳው ቁም ነገር ፦ ባለማወቅ የሚሳታቱ ሰዎችን በለዘብተኝነት መመከር እንዳለብንና ፈጥነን ወደ ቁጣ ወይም ወደ እርምጃ መሄድ እንደሌለብን በዚህ ሀዲስ እንረዳለን።
ረሱል (S.A) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿يقولُ اللهُ تَعالى: أنا عِنْدَ ظَنِّ عَبْدِي بي، وأنا معهُ إذا ذَكَرَنِي، فإنْ ذَكَرَنِي في نَفْسِهِ ذَكَرْتُهُ في نَفْسِي، وإنْ ذَكَرَنِي في مَلَإٍ ذَكَرْتُهُ في مَلَإٍ خَيْرٍ منهمْ، وإنْ تَقَرَّبَ إلَيَّ بشِبْرٍ تَقَرَّبْتُ إلَيْهِ ذِراعًا، وإنْ تَقَرَّبَ إلَيَّ ذِراعًا تَقَرَّبْتُ إلَيْهِ باعًا، وإنْ أتانِي يَمْشِي أتَيْتُهُ هَرْوَلَةً.﴾ “የላቀው አላህ እንዲህ ይላል፦ እኔ ልክ ባሪያዬ እንደጠረጠረኝ ነኝ። እኔን በሚያወሳ ጊዜ ከእሱ ጋር ነኝ። እኔን ለብቻው የሚያወሳኝ ከሆነ እኔ ብቻዬን አወሳዋለሁ። እኔን በሕብረት የሚያወሳኝ ከሆነ ደግሞ እኔ ከእሱ በተሻለ ስብስብ አወሳዋለሁ። ወደ እኔ የአንድ ስንዝር ርዝመት ከቀረበ እኔ ወደርሱ የአንድ ክርን ያህል እቀርበዋለሁ። ወደኔ የአንድ ክንድ ያህል ከቀረበ ደግሞ እኔ ወደርሱ የእርምጃ ያህል እቀርበዋለሁ። ወደኔ እየተራመደ የሚመጣ ከሆነም እኔ ወደርሱ በፍጥነት እሄዳለሁ።” 📚 ቡኻሪ (7405) ሙስሊም (2675) ዘግበውታ
«አንድ ሰው ጠላቱን ሊገጥም በጉዞ ላይ እያለ፤ የጦር ልብሱ (መከላከያው) ሲከብደው ቢያወልቀው፣ ሰይፉ ሲከብደው አውልቆ ቢጥለው፣ እንዲሁም ምግቡና መጠጡ ሲከብደው ቢተወው፤ ከዚያም ምንም ዓይነት መከላከያና ትጥቅ ሳይኖረው፣ በዚያውም ላይ ተርቦ ጠላቱን ቢገናኝ፤ ታዲያ እንዴት አድርጎ ሊያሸንፍ ይችላል?! ልክ እንደዚሁ ዚክር (አላህን ማውሳት) ከብዶት የተወ፣ የሱና ሶላቶች (ሱነኑ ረዋቲብ) ከብደውት ቸል ያለ፣ ግዴታ (ፈርድ) ተግባራትን ከብደውት ያዘገየ፣ እንዲሁም አላህ ያዘዛቸውና የከለከላቸው ነገሮች ከብደውት ያቃለለ ሰውም ከዚህ አይለይም፤ ይህን ሁሉ አድርጎ ከዚያም ሰይጣን ልቡ ላይ እንደሰለጠነበት ያማርራል! ይህ ሰው እኮ ጠላቱ ሳይጥለው በፊት ራሱን በራሱ ነው የጣለው።» ➖ኡወይስ አል-ቀረኒይ(አላህ ይዘንላቸው) Copied
ኢማማችን ዘገየና እኔን አስቀደሙኝ ...እዳሰግድ ዋናዉ ነገር ሱረቱል ዩሱፍን ቀራሁኝ በየቦታዉ እየጠፍኝ ነበር በርካታ ቦታ ጠፍኝ ልክ እንደጨረስን አንድ አባት ልጄ ሆይ ዩሱፍን ወንድሞቹ ያላደረጉትን አደረከዉ አሉኝ😭¡...
#ከሀራም_ለመላቀቅ_ይፈልጋሉን ? 🤔 هل تريد الإقلاع من الذنوب 🤲 ከሀራም (ከአላህ ክልከላዎች) መራቅና ወደ ሐላል ማዘንበል የጠንካራ እምነት (ኢማን) ምልክት ነው ✨። በዚህ መልካም መንገድ ላይ ለመጽናትና መንፈስዎን ለማጠናከር የሚረዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ 📝 1️⃣ ሶላትን በወቅቱ በጀመዓ መስገድ፦ ሶላት ከእኩይና ከሀራም ነገሮች ሁሉ የሚከለክል ትልቁ መከላከያ ነው 🕌። 2️⃣ መጥፎ አጋጣሚዎችንና ቦታዎችን መሸሽ፦ ወደ ሀራም የሚወስዱ መንገዶችን (ማህበራዊ ሚዲያ📱፣ መጥፎ ጓደኞች🚫፣ ወይም አላስፈላጊ ቦታዎች) መራቅ። 3️⃣ ጥሩ ጓደኞችን መያዝ፦ ወደ መልካም ነገር የሚያስታውሱዎትና ወደ አላህ መንገድ የሚወስዶትን መልካም ጓደኞችን መርጦ መያዝ 👫። 4️⃣ ዱዓ ማብዛት፦ አላህ ከሀራም ነገሮች እንዲያርቆትና በሐላሉ እንዲያብቃቃዎት በቋሚነት እሱን ይለምኑት 🤲። 5️⃣ ጊዜን በጠቃሚ ነገር ማሳለፍ፦ ትርፍ ጊዜዎን መስጅዱ ውስጥ በመሆን 🕌: በቁርዓን📖፣ በትምህርት📚 ፣ በዚክር📿 : በኢስቲግፉር : በስራ🔧 ወይም በስፖርት⚽️ በማሳለፍ አእምሮዎ ወደ ሀራም እንዳያስብ ማድረግ። 6️⃣ ተውበት ኢስቲግፋር ማድረግን ማብዛት 🔄: በሆነ አጋጣሚ ᵗህተት ቢሰሩ እንኳ ተስፋ ሳይቆርጡ ወዲያውኑ ወደ አላህ ተመልሰው ምህረትን መጠየቅ። 7️⃣ መልካም ስራዎችን አቅሞ በፈቀደው መጠን ማዘውተር 🎯 ለምሳሌ:- ሰላት 🕌 : ጾም ☀️ : ሰደቃ 🤝 : የቀብር ዚያራ : የታመመን መጠየቅ ... ወዘተ 8️⃣ በዚህ መንገድ ላይ መጽናት ትዕግስት ማድረግ ዋናው ቁልፍ ነው 🔑። ያ አላህ በሀቅ መንገድ ላይ አጽናን 🤲 ያ አላህ ከሀራም መንገድ አርቀን ✨ ያ አላህ ዱንያ አኼራችንን አሳምርልን 🌍 ኡስታዝ ሙሀመድ ፈረጅ
ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለትና እንዲህ ብሏል። አላህን በብዛት የምታመልክ የነበረች አንድ ሴት ነበረች....ወድቃ ጣቷ ተቆረጠ። እሷ ግን ትስቃለች። በዚህ ጊዜ ከሷ ጋር የነበሩ ሰዎች ጣትሽ ተቆርጦ ምን ያስቅሻል? አሏት። እሷም እንዲህ አለች፦ [ሶብር አድርጌ የማገኘውን አጅር ጥፍጥና የህመሙ መራራነት አስረሳኝ አለች ሱብሀነላህ] 📚[ ﻣَﺪﺍﺭِﺝ ﺍﻟﺴَّﺎﻟِﻜِﻴﻦ (2/167)
በዚህ እድሜ ይሄን ማድረግ አለብህ፣ በዚህ እድሜ ደግሞ እዚህ መድረስ አለብህ የሚባል ቋሚ የህይወት ህግ የለም። እነ እከሌ በሆነ የእድሜያቸው ወሰን ላይ የሆነ ነገር ስላሳኩ ወይም ስላደረጉ፣ አንተም ማድረግ አለብህ ማለት አይደለም። ሁላችንም አንድ አይነት የህይወት መስመር የለንም፤ በተመሳሳይ እድሜ ላይም ብስለትና ክህሎት አይኖረንም። ዕጣ ፈንታችንም አንድ መልክ የለውም። ቁም ነገሩ ተጨባጭህ በፈቀደልህ የእድሜህ ወሰን ላይ ማድረግ ያለብህን ማድረግህ እንጂ ቁጥሩ አይደለም። لكل أوان قطاف، ولكل شيء إوان
ኢስላም የቤተሰብ ስርዐትን አስመልክቶ ቋሚና የማይቀር ህግ አለው ። ይህ ህግና ስርዐት ከእስልምና ሰዋቢቶች ውስጥ የሚጠቃለል ነው ። አንድ ወንድ ከአንዲት ሴት ጋ በትዳር ጎጆ ውስጥ ሲጣመር ኢስላም ለነዚህ ሁለት ሸሪኮች የየራሳቸውን ኃላፊነት ሠጥቷቸዋል ። ይህ የኃላፊነት ክፍፍል ባዩሎጂካል ተፈጥሮኣቸውን እና ሳይኮሎጂካል ስሪታቸውን መሰረት ያደረገ ነው ። እነዚህ ሁለት የተለያዩ ፆታዎች በአንድ ጎጆ ውስጥ ተመሳሳይ ሚና ሊኖራቸው አይችልም ። ወንድ ልጅ ቤቱ ያመጣትን ሴት የመቀለብ የማልበስ ፣ የመንከባከብ እና የሚያስፈልጋትን ነገር ሁሉ የማሟላት ኃላፊነት አለበት ። ልጆቹንም እንደዛው ። ይህን ቤተሰባዊ ግዴታውን ለመወጣት በየዕለቱ ሰርቶ መግባት ይኖርበታል ። ከዚህም ውጪ ወንድ ልጅ ማህበራዊ ኃላፊነቶች ላይም ከፊት ተሰላፊ ነው ። እነዚህን ከግንዛቤ በማስገባት ኢስላም ባሎችን ቀዋም/መሪ/አስተዳሳሪ እንዲሆኑ አድርጓል ። ይሄ ከላይ እንዳነሳሁት ቤት የሚቆምበት መሰረታዊና የማይሻር የአላህ ድንጋጌ ነው ። ሚስት ደግሞ ይህን ኃላፊነቱን በአግባቡ ለሚወጣው ባለቤቷ እንደ መሪነት ላለበት ኃላፊነት ቀናኢና ታዛዥ (ቃኒታህ) መሆን ይገባታል ። በዚህ ሂደት ባለቤቷ ቤት ውስጥም ከቤት ውጪም ላሉበት ማህበራዊ ኃላፊነቶች አጋዥ ትሆናለች ፣ እራሷንም ሆነ የሱንም ሚልኮች ትጠብቃለች ። እነዚህ ሷሊሃት የሚባሉ ሚስቶች መገለጫዎች ናቸው ። ይህን እንደ አስል/መሰረት ከተቀበልን ፣ ከአንዳንድ ተጨባጮች አንፃርና አሁን ካለንበት የኑሮ ሁኔታ አንፃር ሚስት ኑሮኣቸውን ለማሻሻልና ባለቤቷንም ለመርዳት ወይም በገንዘብ እራሷን ለመቻል ወጥታ ሀላል ብትከስብና በገንዘቧ ብትነግድ የሚከለክላት ነገር እንደሌለ የታወቀ ነው ፣ ባልም እንዲሁ ቤት ውስጥ ባሉ ስራዎች በቅንነት ሚስቱን ቢያግዝ የመልካምነቱ መገለጫ ነው .........ልጆቿን በቅርበት እየተከታተለች በእናትነት እቅፏ ስር አድርጋ በተርቢያ ብታሳድጋቸውና እሷም ሆነች ልጆቹ ችግር ሚባል ሳይነካቸው ተቀማጥለው እንዲኖሩ እሱ ብቻ ወጥቶ ቢለፋ የተሻለና መሰረት ከመሆኑ ጋ ማለት ነው ። የሞራል ልዕልና ያለውን ማህበረሰብ ለመገንባት ከፈለግን ሚናዎች ሊደበላለቁ አይገባም ። እኛ እንደ ኢስላም ቁርዐን ያስቀመጥልን መስመር አለ የቤተሰብ ህይወት ላይ ደግሞ ምርጥ ሞዴል አለልን ። ሴት እናት ሆና ሚስት ሆና እህትና አክስት ሆና ስላላት ሁቁቆች ማንም ሊያስተምረን አይችልም ። ከሁሉም የሚያብቃቃ በጣም በቂ የሆነ አስተምህሮ አለን !!!
የኛ ወንጀልና ዝናቡ መጥፋት‼️➚➚➚➚➚➚➚➚➚➚➚➚➚ ➛ በአብዛኛው የሀገራችን ክፍል ገበሬው ዘሩን ዘርቶ፣ አፈሩን አዘጋጅቶ ዓይኑን ወደ ሰማይ አንጋጦ ዝናብ እየጠበቀ ይገኛል። እውነታው ግን መራራ ነው፤ ገበሬው ካላመረተ ከተሜው አይበላም! የገበሬው ማሳ ሲደርቅ، የሁላችንም ጉሮሮ አብሮ ይደርቃል። 🌥 ነገር ግን ዝናብ መዘግየቱንና መከልከሉን ተፈጥሯዊ የየአየር ንብረት መዛባት ብቻ አድርገን ማሰብ የለብንም። በእስልምና አስተምህሮ፣ ሰማይ ዝናቧን ስትነፍግ ዋነኛው ሰበብ የአደም ልጆች ወንጀልና ሐጢአት መብዛት ነው! ➊ አራዊትና ነፍሳት ሳይቀሩ ይረግሙናል! 📋 እኛ ሰዎች ወንጀል ስንሰራ የምንጎዳው ራሳችንን ብቻ አይደለም፤ በኛ ጥፋት ምክንያት መላው የተፈጥሮ ስርዓት ይዛባል፣ ሚስኪን እንስሳትም አብረው ይራባሉ፣ ይጠማሉ። በዚህም የተነሳ ነፍሳት ሳይቀሩ ይረግሙናል! ከሰለፎች አንዱ የሆነው ታላቁ ዓሊም፣ የኢብኑ ዐባስ ተማሪ የሆኑት ዒክሪማህ ይህንን አስደንጋጭ እውነታ እንዲህ ይገልጹታል፦ «دَوَابُّ الْأَرْضِ وَهَوَامُّهَا، حَتَّى الْخَنَافِسَ وَالْعَقَارِبَ يَقُولُونَ: مُنِعْنَا الْقَطْرَ بِذُنُوبِ بَنِي آدَمَ» “የምድር እንስሳትና ተሳቢዎች፣ ጢንዚዛዎችና ጊንጦች ሳይቀሩ (ዝናብ ሲጠፋ) እንዲህ ይላሉ፡- «በአደም ልጆች ወንጀል ምክንያት ዝናብ ተከለከልን!»” 📚 [ምንጭ፡- ኢማም ኢብኑል ቀይም፣ 'አድ-ዳእ ወድ-ደዋእ' (አል-ጀዋብ አል-ካፊ)፣ ገፅ 57] 🧠አስቡት! እባብና ጊንጥ ሳይቀሩ በድርቅ ሲሰቃዩ፣ «ይህ የደረሰብን በእገሌ ሐሜት፣ በእገሌ ዚና፣ በእገሌ ሌብነት፣ እና በእገሌ ግፍ ምክንያት ነው» ብለው አላህ ፊት ይከሱናል! የሰው ልጅ በፈጸመው ወንጀል፣ ቋንቋ የሌላቸው ሚስኪን እንስሳት አብረው ዋጋ ይከፍላሉ! ➋ አንዳንዴ ራሳችንን እንጠይቃለን፤ «ይህ ሁሉ ግፍ፣ ደም መፋሰስ እና ወንጀል እያለ አላህ እንዴት ዝናብ ይሰጠናል?» መልሱን ታላቁ ነብይ ﷺ ነግረውናል። አላህ ዝናብ የሚሰጠን እኛ ተገቢ ሆነን ሳይሆን፣ ለማይናገሩት እንስሳት አዝኖ ነው! ረሱሉ-ል-ሁዳ ውዱ ነብያችን ሙሐመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «...وَلَمْ يَمْنَعُوا زَكَاةَ أَمْوَالِهِمْ إِلَّا مُنِعُوا الْقَطْرَ مِنَ السَّمَاءِ، وَلَوْلَا الْبَهَائِمُ لَمْ يُمْطَرُوا...» «…የገንዘባቸውን ዘካ አይከለክሉም፣ ከሰማይ ዝናብን የተከለከሉ ቢሆን እንጂ። እንስሳት ባይኖሩ ኖሮ ፈጽሞ ዝናብ አይዘንብላቸውም ነበር!» 📚 [ምንጭ፡- ሱነን ኢብኑ ማጃህ፡ 4019፣ ሸይኽ አል-አልባኒ 'ሶሒሕ' ብለውታል] ❸ መፍትሄው ምንድን ነው? ✍️ መፍትሄው አንድ እና አንድ ነው፦ ወደ አላህ መመለስ (ተውበት) እና ኢስቲጝፋር (ምህረት መለመን)! የሰማይን በር የቆለፈው ወንጀላችን ከሆነ፣ መክፈቻውም ቁጭ ብሎ በፀጸት አላህን መለመን ነው። አላህ በነብዩ ኑሕ አንደበት ይህን መፍትሄ እንዲህ ያስቀምጠዋል፦ ﴿ فَقُلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّارًا * يُرْسِلِ السَّمَاءَ عَلَيْكُم مِّدْرَارًا ﴾ትርጉም፡- «(ኑሕም) አልኩኝ፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፤ እርሱ በጣም መሓሪ ነውና። ሰማይን በእናንተ ላይ ተከታታይ ዝናብ አድርጎ ይልካል።» 📖 (ሱረቱ ኑሕ፡ 10-11) 📣 ዛሬ ገበሬው ዘሩን ዘርቶ በጭንቀት ሰማይ ሰማዩን እያየ ነው። እኛ ከተማ ውስጥ ሆነን፣ የዝናቡ መዘግየት ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚያጠፋው የገበሬውን ተስፋና የሁላችንንም የነገ ጉርስ መሆኑን ልንዘነጋ አይገባም። እባካችሁ በዱዓችን አንርሳቸው። በግላችንም ሆነ በጀማዓህ ሶላተል ኢስቲስቃእ፣ ኢስቲጝፋር፣ ተውባ፣ ሶደቃ… እናብዛ። 🤲አላህ ሆይ! (اللهم اسقنا غيثاً مغيثاً هنيئاً مريئاً...) ዝናብህን አጠጣን፣ መሬቷን አርጥብልን፣ ለገበሬው አዝመራ በረካ አድርግለት፣ በኛ ወንጀል ምክንያት ምስኪን ባሮችንህና እንስሳትን አትቅጣብን!
ኢብኑል ጀውዝይ እንዲህ ይላሉ 👉ኢብሊስ ለመጀመሪያ ሰውን ከሚያስርቀው ነገር ውስጥ እውቀት ነው ምክንያቱም እውቀት ለሰው ልጆች ብርሀናቸው ነው ይህን ብረሀናቸውን ካጠፋባቸው በጨለማ ውስጥ እንደፈለገው ያንቦጫርቃቸዋል። 📚تلبيس إبليس (1/289)
видео или голосовое, без подписи
" ለጇንም ታሳድጋልች እውቀቷንም ታደብራልች! ጥሩ ሴት ስትባል ልክ እንዚህ ሸንቃጣ ነች በአንድ እጇ ልጇን በአንድ እጇ ብዕሯን ትጨብጣልች ልብ ካለሽ መወሰንን ከታጠቅሽ ግብሽን ከመረጥሽ ቆራጥነትን ከታጠቅሽ በአሏህ ፍቃድ የማይቻል የለም ኡማ ትገነቢያልሽ ሴት ልጅ አትችልም የሚባለውን ትርክት 100 ሴት ከማስቀራት 1 ወንድ የሚበለውን ወሬ ፍቀሽ ትገኝያልሽ ስምሽ በታሪክ ይጻፋል የአለም(ህዝብ) ትሆኛልሽ ። ወንድሜ አለምህ ምረጥ ባይሆን ከቀለሟ በላይ ለማንነቷ ጣር የተኛዋም ሴት ቀጥ ስል በእውቀት ስትፈካ ቆንጆ ናት አንዳንድ ወንድ የምንባል ደሞ አለን ጥሩ የሚባሉ ሴቶችን አግብተው የሚያፈዙ አንተም ጎብዝ እሷም ትጣር ።
🎉ዛሬ ጁመዓ ነው በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን እናብዛ🎉 إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ﷺ 🌟🌟اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم في العالمين إنك حميد مجيد🌟🌟 ۩ ከጁምዓ ቀን ሱናዎች፦ ➊ መታጠብ ➋ ሽቶ መቀባት(ለወንዶች) ➌ መፋቂያ(ሲዋክ) መጠቀም ➍ ቆንጆ ልብስ መልበስ ➎ ሱረቱል ካህፍ መቅራት "ሱረቱል ካህፍን በጁምዓ ቀን መቅራት፤ በሁለቱ ጁምዓዎች መካከል የሚበራ ብርሃን (ኑር) ይሆንልሃል/ ይሆንልሻል።" ይህ ማለት አላህ እስከሚቀጥለው አርብ ድረስ ልባችንን በብርሃን ይሞላዋል፣ ትክክለኛውንና ስህተቱን የምንለይበትን ጥበብ ይሰጠናል ማለት ነው። ➏ በጊዜ መስጂድ መግባት ➐ ዱዓ እና ሰለዋት ማብዛት ﷺ በውዱ ነብያችን ላይ ሶለዋት ማብዛትንም አንርሳ❤️ اللهم صلِّ وسلم وبارك على سيدنا وحبيبنا ونبينا محمد وعلى آله وصحبه وسلم تسليماً كثيراً ﷺ 🌟 መልካም ጁምአ🌟