Vocal Clinic
СтатистикаVocal Clinic Project is a music project which aims at providing music training resources for singers and musicians. Welcome to @MyVocalClinic_bot
- Последний пост
- 4 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Музыка
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 388
- 1/48двое суток
- 444
- 1/72трое суток
- 479
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
"ሰላም! እንኳን ወደ አጋር ኢትዮጵያ ቻሪታብል ሶሳይቲ ኦፊሴላዊ የቴሌግራም ቻናል በሰላም መጡ።ስለ ድርጅታችን መረጃ ማግኘት እና የበጎ አድራጎት ስራዎቻችን አካል መሆን ይችላሉ።” Agar Ethiopia inspires and empowers elders, mentally affected people, refugees, returnees, internally displaced persons, victims of trafficking, and survivors of violence to improve their livelihood by themselves. Programs of Agar Ethiopia rest or founded on three pillars represented by “3Rs”. “Respond! Renew! Rebuild!”
https://t.me/officialagarethiopia
Channel name was changed to «Vocal Clinic»
Keyboard for sell Brand: Yamaha Model: Portable Grand DGX-305 Size: 6 - Octaves Touch Response: Yes Pitch Bend: Yes Condition: Used Price: 70,000 Birr Call: +251911697704
የግል የቮካል ትምህርት (በአካልም ሆነ ኦንላይን) መማር ከፈለጉ ፈጥነው ይደውሉ +251911697704
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
መንፈስ-መር የዝማሬን እሳት ዳግም መለኮስ (ካለፈው የቀጠለ...) 4. የድጋሚ-መዝሙር (Cover Song) መበራከት ከዚህ ጋር አብረን ልናነሳው የምንችለው አንድ ትልቅ ሃሳብ ደግሞ የድጋሚ-መዝሙርን (cover song) ጉዳይ ነው። 'ከቨር ሶንግ' አላማውን ሳይስት ጥቅም ላይ ቢውል ጠቃሚ እንደሆነ ባምንም በአንጻሩ ግን ዘማሪያን ጥሩ የሆኑና የበሰሉ መዝሙሮችን እንካችሁ እንዳይሉን እንደ ዋነኛ እንቅፋት እያገለገለ እንደሆነ ይሰማኛል። ያለቀንና በአድማጩ ልብ ውስጥ ቦታ የያዘን አንድ መዝሙር ድጋሚ መዘመርና በቀላሉ ስኬታማ መሆን እየተቻለ ምን ትግል ውስጥ አስገባን አይነት አመለካከትን ያንጸባርቃል። ይህ ደግሞ የዜማና የግጥም የፈጠራ አቅማችንን በእጅጉ አቀጭጮታል፤ ውጤቱም የአዳዲስ ዝማሬ ድርቅን አስከትሏል ብዬ እሞግታለሁ። ከዚህ በተጨማሪም ዘማሪዎች በራሳቸው መንገድ አዳዲስ መዝሙሮችን ለመጻፍ እንዳይነሳሱ እንቅፋት በመሆን መዝሙር አድማጩም በተወሰኑ የግጥም ሃሳቦችና ለጆሮ በተለመዱ የዜማ ፍሰቶች ላይ ብቻ እንዲወሰንና አዳዲስ መዝሙሮችን እንዳይቀበል እንዳደረገው አምናለሁ። 5. የቤተክርስቲያን የአምልኮ ባህል መቀየር በኢትዮጵያ የወንጌላውያን አማኞች የአምልኮ ስርዓት ጉዞ ውስጥ ሃላፊነትን የሚወስድና መመሪያን የሚሰጥ አንድ ጠንካራ አካል አለመኖሩ የዝማሬ አገልግሎት እድገታችንን እንደገታው አምናለሁ። በየአካባቢው የሚከፈቱ አብያተክርስቲያናት በሙሉ በራሳቸው መልክና ቅርጽ የዝማሬን ባህል የመፍጠርን መብት ስላገኙ ቀስ በቀስ የሶሎና የኳየር አገልግሎትን ከመድረክ በማስወጣት የአምልኮ መሪ ወይም የአምልኮ ህብረቶች በሚሰጡት አገልግሎት ላይ ብቻ ተወስነው ይታያል። አንድ ዘማሪ ለአገልግሎት ተጋብዞ የራሱን መዝሙር መዘመር እስከማይችል ድረስ (በተለይም አዳዲስ ዘማሪያን) ቢዘምርም ተቀባይነት እስከማያገኝ ድረስ አዳዲስ መዝሙሮችንና ዘማሪዎችን ተስፋ የሚያስቆርጥ ስርዓት መፈጠር በርካታ አዳዲስ ዝማሬዎችን እንዳናገኝ ትልቅ ተግዳሮትን ፈጥረዋል እላለሁ። በቀጣዩ ክፍል እነዚህን ችግሮች ከመቅረፍ አንጻር ይጠቅማሉ ብዬ የማስባቸውን የመፍትሔ ሃሳቦች በተወሰነ መልኩ ለመዳሰስ እሞክራለሁ። ይቀጥላል...
መንፈስ-መር የዝማሬን እሳት ዳግም መለኮስ (ካለፈው የቀጠለ...) በአሁኑ ወቅት ተጽዕኖ አምጪ አዳዲስ መዝሙሮች እጥረት ያጋጠመን ለምንድን ነው? ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት ከምንግዜውም በላቀ መልኩ የዘማሪዎችና የመዝሙሮች ጎርፍ ያጥለቀለቀን ቢመስልም፣ ልብን የሚነኩ፣ ሕይወትን የሚቀይሩ፣ የሚያንጹ፣ ከእግዚአብሔር ጋር በአምልኮ የሚያገናኙን እንዲሁም ዘላቂ የሆነ መንፈሳዊ ተጽዕኖን የሚያመጡ መዝሙሮችን በብዛት ለማግኘት ግን የታደልን አንመስልም። ለዚህ ምክንያት ሊሆኑ ከሚችሉት ጥቂቱን እንመልከት፡- 1. የመንፈሳዊ ብስለት ማጣት (Lack of Spiritual Maturity and Spiritual Discipline) ብዙ መዝሙሮች ከእግዚአብሔር ጋር ካለ ጥልቅ ግንኙነት የመነጩ አይመስሉም፤ ዘማሪው ባግባቡ ካልተረዳቸው ወይም በደንብ ካላጠናቸው ሃሳቦች ተነስቶ የጻፋቸው እንጂ። በሌላ መልኩ ደግሞ የመዝሙር ግጥሞችና ዜማዎች ስሜትን የሚገዙና የሚማርኩ ሆነው ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነትን የማያንጸባርቁ ሲሆኑ ይስተዋላል። አንድ ዘማሪ ከቃሉ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ጥልቅ ግንኙነት ከሌለው መዝሙሮቹ ለጊዜው ስሜትን ቀስቃሽ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል እንጂ ዘላቂ የሆነን መንፈሳዊ ተጽዕኖ አይፈጥሩም። ብዙ ወጣት ዘማሪዎችና ሙዚቀኞች መንፈሳዊ መሪ/አማካሪ የላቸውም። መሪ ወይም መካሪ ከሌለ ደግሞ የመዝሙሮቻቸው ሥነ-መለኮታዊ ጤናማነት እና ተልእኮ በቀላሉ ለአደጋ ሊጋለጥ ይችላል። 2. ከፍተኛ የሆነ የክብርና የዝና ጥማት (Focus on Fame and Recognition) ዛሬ ብዙ ዘማሪዎች ትኩረታቸው ከዝማሬአቸው መልእክትና ከሚያመጣው ተጽዕኖ ይልቅ ውጫዊ በሆነው የሙዚቃና የክሊፕ የፕሮዳክሽን ጥራት ላይ ሆኗል። እንደ ዩቲዩብ፣ ቲክቶክና የመሳሰሉት የማህበራዊ ሚድያዎች የተከታዮች ብዛት፣ የእይታና የላይክ መጠን የአገልግሎቱ ትኩረትና መለኪያዎች ከሆኑ ሰነባብቷል፤ ይህ ደግሞ ከዋነኛው የአገልግሎቱ ተልዕኮ ሊያዘናጋ የሚችል አደጋ ሆኖ ብቅ ብሏል (ማህበራዊ ሚድያ ያለው ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ሳይዘነጋ)። ከዚህም ባለፈ ጥቂት የማይባሉ አገልጋዮች ከፍተኛ በሆነ የክብርና የዝና ጥማት ተጠፍረው እሱን ጥማት ለማርካት ሲባዝኑ ይስተዋላል። እንዲያውም አሁን አሁን በስፋት የተለመደ አንድ ቃል አለ - ልህቀት (excellence)። በእርግጥ ልህቀት በዝማሬ አገልግሎት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ ነገር ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም ነገር ግን ይሄ የራስን ስምና ዝና ለመገንባት እንደ ሽፋን ሊሆን አይገባም። ስለ ልህቀት ካሰብን መጀመር ያለብን ከዝማሬአችን ግጥምና ዜማ ውበትና ጥራት መሆን ይኖርበታል። 3. ከፈጠራ ይልቅ የኩረጃ መበራከት (Copying: Lack of Originality) ብዙ መዝሙሮች ጆሮአችን የናፈቀውን አይነት አዲስ አይነት የዜማና የምት ፍሰት ሊያስደምጡን አልቻሉም። ለመዝሙር ባዕድ የሆኑ የሙዚቃ ስልቶችን፣ የግጥም ስንኞችንና የድምጽ ቴክኒኮችን መስማት እየተለመደ መጥቷል። የዜማ፣ የአዘማመር ስልትና የሙዚቃ ቅንብር ማስመሰል ወይም ኩረጃም ሲበረታታ ይስተዋላል፤ አንዳንዶች ከራሳቸው፣ አንዳንዶች ደግሞ ከሌላ ዘማሪያን ሲኮርጁ አንዳንዶች ደግሞ አለፍ ብለው ከዘፈኑ አለም እየኮረጁ ያስደምጡናል። አንዳንድ ሙዚቃዊ መመሳሰሎች ሆን ተብሎ ያልሆኑና አይቀሬ መሆናቸውንም መዘንጋት የለብንም። ለኩረጃ ያነሳሱንን ዝርዝር ምክንያቶች ለጊዜው እናቆያቸውና የኩረጃ መበራከት አዳዲስ የመዝሙር አይነቶችን ከመስማት እንደገደበን አንስተን እንለፍ። ይቀጥላል...
መንፈስ-መር የዝማሬን እሳት ዳግም መለኮስ መግቢያ ባለፉት ጥቂት አስርት ዓመታት እግዚአብሔር በየዘመናቱ ቀብቶ በሰጠን ውድ ዘማሪያን አማካኝነት በርካታ ድንቅ ዝማሬዎች ወደኛ ደርሰው ለብዙዎቻችን የመዳን፣ የማደግና የመታነጽ ምክንያት ሆነዋል። እነዚህ ዝማሬዎች በአንድ ወቅት መነቃቃትን ያመጡ፣ ልብን የነኩ እና ብዙዎችን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት የማረኩ ነበሩ። ሁሉም በሚባል ደረጃም የኢትዮጵያ ክርስቲያኖችና አብያተ ክርስቲያናት እነዚህን ተወዳጅ መዝሙሮች በግላቸውም ይሁን በጋራ ሲጠቀሙባቸውና በእያንዳንዱ የአምልኮ ፕሮግራሞቻቸው ሲደጋግሟቸው ኖረዋል። ዛሬም በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ውስጥ የዘማሪዎችና ሙዚቀኞች ቁጥር ከምንጊዜውም በተለየ መንገድ እየጨመረ ቢመጣም የመዝሙራችን መንፈሳዊ ተፅእኖና ተወዳጅነት እየቀነሰ የመጣ ይመስላል። እንግዲህ ይህ እውነታ አንድ ወሳኝ ጥያቄ እንድናነሳ ግድ ይለናል፡ በየአምልኮ ፕሮግራሞቻችን ልንዘምራቸው የምንችላቸው በቂ አዳዲስ ዝማሬዎችን ያጣነው ለምንድነው? ቅደም ተከተላቸው እንኳን ሳይዛነፍ አብረን ቀጣጥለን መዘመር እስክንችልና በድግግሞሽ ብዛት እስክንሰላች ድረስ የቀደሙት ዝማሬዎች ላይ ብቻ (በእርግጥ ከቀደሙትም ዝማሬዎች ውስጥ የተወሰኑት ላይ ብቻ) የሙጥኝ ያልነው ለምንድነው? በየጊዜው አዳዲስ መዝሙሮች ወደኛ ቢደርሱም መንፈሳዊ ተጽዕኖና ተወዳጅነትን ያጡትስ ለምንድነው? መጽሐፍ ቅዱስ አዲስ ዝማሬን እንድንዘምር ይጋብዘናል፣ ያዝዘናል፤ “ለእግዚአብሔር አዲስ ምስጋናን አመስግኑ፤ ምድር ሁሉ፥ እግዚአብሔርን አመስግኑ።” — መዝሙር 96፥1 “አዲስ ዝማሬን ለአምላካችን ምስጋና በአፌ ጨመረ፤ ብዙዎች ያያሉ ይፈሩማል፥ በእግዚአብሔርም ይታመናሉ።” — መዝሙር 40፥3 እነዚህ ጥቅሶች እንደሚያሳዩት አዲስ ዝማሬን መዘመር ከፈለግን እንድናደርገውና ካልፈለግን እንድንተወው ሳይሆን እንደ መመሪያ የተሰጠን ነገር ነው። አዳዲስ ዝማሬዎች የእግዚአብሔርን አዳዲስ መገለጦች ያሳዩናል፣ እኛም እግዚአብሔርን በራሳችን አውድ እንድናመልከው እድል ይሰጡናል። ታዲያ በዚህ በፍጥነት እየተለወጠ በሚገኝ አለም ውስጥ ሁሉም ነገር በከፍተኛ ለውጥ ላይ ሆኖ ሳለ መዝሙሮቻችን ብቻ የማያድጉና የማይለወጡ ከሆነ ዝማሬአችን አደጋ ላይ መውደቁ አይቀሬ ነው የሚል ስጋት አለኝ። ቤተክርስቲያን አዳዲስ ዝማሬዎችን የማትለማመድ ከሆነ ደግሞ የአሁን ወቅታዊ ድምጽ መሆኗ ቀርቶ ያለፈውን ብቻ የምታስተጋባ የገደል ማሚቶ ወደመሆን የምትደርስ ይመስለኛል። መንፈስ-መር የዝማሬ አገልግሎት እጥረት መንስኤዎችንና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን በተመለከተ ደግሞ በቀጣዩ ክፍል ይዤ እቀርባለሁ። ይቀጥላል...
https://youtu.be/S3RrNIEV4g0?si=lq6-RGUedsX74b6T
ከእነዚህ መጻሕፍት ውስጥ በsoft copy ያሏችሁ ካሉ ብታጋሩኝ 1. አምልኮ - Bob Serg/ገዛኸኝ ሙሴ 2. ጋሽ ደበበ ለማ 3. እንዳልካቸው ሐዋዝ 4. ረታ ጳውሎስ 5 ቤት ያጣው ቤተኛ - ዮናስ ጎርፌ እና ሌሎችም ካሉ... . . . ተባረኩ አማን
Vocal Clinic pinned a photo
ለሙዚቃ አሬንጅመንት፣ የድምጽ ቅጂና ሚክሲንግ ፍላጎትዎ ተዘጋጅተን እየጠበቅንዎ ነው። ፈጥነው ይደውሉሉን 0911697704
Revelation Studio Call +251911697704
A huge opportunity for singers, choirs and worship leaders overseas. Vocal Clinic Project presents you an online vocal lessons at your convenience. Call +251911697704