tgindex
Meron's school of thoughts😊

Meron's school of thoughts😊

Статистика
@JALSMyFанглийский

This is where i aim to share my insights and stories in a more meaningful way.

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
563
+1 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
292
23 постов
Вовлечённость
51,9%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 23
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
104
1/48двое суток
119
1/72трое суток
128

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • እንደ ዘላለም የረዘመ፣ ደስ የሚል ፣ሰላማዊ ና ትርጉም ያለው፣ ኮሽታ(Insecurtiy) የሌለበት፣ ቀብራራ የአምላክ አይነት ዝምታ....ደግሞ ዝምምምምምምምም ✍ሜሮን አለማየሁ ኪቲላ @JALSMyF

  • የወንድ ልጅ ነኝ!! ስለ ሴት ና ስለ ወንድ እኩልነት ማውራት በተለይ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ የማልፈልገው ርዕስ ነው ።ለሴትነት ና ለሴቶች ያለኝ ፍቅር ፣ክብር ና ዋጋ መሬት ላይ በተግባር መኖሩን መርጬ በዛ ጉዳይ ላለመተንፈስ ወስኜ ነበር ።ይሁን እንጂ ውሸት መናገር ብቻ ሳይሆን እውነትን መደበቅም ውሸታምነት ስለሆነ ሀሳቤን እንደዚህ አሰፍራለሁ ። አሁን ለምናየው ብሽሽቅ ምክኒያቶቹ ሴት መሆን የከበዳቸው ሴቶች ሳይሆኑ ወንድ መሆን የተሳናቸው አባወራዎች ናቸው ። እውነቱን ለመናገር ጤናማ ወንድ ሁን ብሎ ጆሮአቸው እስኪደማ ድረስ አከባቢያችን ላይ ላሉት አዳማዊያን ሁሉ መናገር እጅግ አስፈላጊ ነው ፤የሴት ዓመጽ ሴትን መውደድ፣መንከባከብ፣መጠበቅ፣መከላከል የሚችል ወንድ ቢፈጠር ይረግባል ። ለዚህ ሁሉ ትርምስምስ ና መመሰቃቀል ምክኒያቶቹ ወንዶች ናቸው ።ስለዚህ ምክሩም ፣ግሳፄውም አስተያየቱም ከሴቶች ይልቅ ለወንዶች ነው የሚያስፈልገው ። የሴቶቹ በተለምዶ ሴትነት በሚታሰብበት መንገድ አንመላለስም ማለት ና እነሰደ ወንድ ካልሆንን ማለት መነሻ ምክኒያቱ ብሶት ነው ፣ኩርፊያ ነው ፣የዘመናት ግፍ ና በደል የወለደው ቁጣ ነው (ቁጣው ልክ ነው ወይ?ዳኝነቱን ለየግለሰቡ ልተወው) ግን ቁጣውን ለማረም ከመሞከር የቁጣውን መነሻ ምክኒያት ለማከም መሞከር የተሻለ ትርፋማ ነው ፤ጽድቅም ከእውነት ና ከተበዳይ ጎን መቆም ነው ብዬ አምናለሁ። ሴት መሆን የከበዳቸው ሴቶች ቁጥር ቢያንስ በሀገራችን አውድ እጅግ አናሳ ነው ፤መልካም ወንድ መሆን የተሳናቸው አባወራዎች ቁጥር ግን ለመቁጠር አታካች ነው ። የሴት አመጽ ሳሉ ነው የበሽታው ምልክት ፤መነሻው ግን ግፍ ና ጭቆና የበዛበት አባወራዊ ስርዓት ነው (የሳምባ ምቹ ወይም ዋና በሽታው)..ስለዚህ ለምን አሳለሽ ከማለት ይልቅ ና ወንድምዓለም የሳምባ ምችህን ታከም ማለት እውነተኝነት ነው ። አባወራዊ ስርዓት መልካም ነው ነገር ግን ሴቶች እስካልተጠቁ፣እስካልተደፈሩ፣እስካልተጨቆኑ፣እስካልተደበደቡ፣እስካልተለከፉ፣በማታ ብቻቸውን መሄድ ጭንቀት ውስጥ እስካልከተታቸው፣ህልማቸውን መኖር እስከተፈቀደላቸው ድረስ ብቻ !! እኔ የአባቴ ልጅ ነኝ፣በወንድ እጅ ያደግኩ ! ለአዳማዊያን በሙሉ ክብር ና ፍቅር አለኝ ።ግን እውነት እውነት ነው ማሽሞንሞን አያስፈልገውም ።ጥፋቱ የእነርሱ ነው ።ለመታረም ቢስማሙ ደቂቃ የማይቆይ ጸብ ነው ፤ በግትርነታቸው እየተፋፋመ ያለው ። ይቅርታ ጠይቀው፣ለሴቶች የተሻለ ዓለም ለመፍጠር እርምጃ መውሰድ ቢጀምሩ ጥሉ ቀርቶ ፍቅራችን በደራ ነበር ። ቆይ ለሔዋን ከእግዛሩ በታች ያለ አዳም ማን ነበራት ??! ✍ሜሮን አለማየሁ ኪቲላ @JALSMyF

  • እስቲ ልሸልም ! Scroll ማድረግ በአማርኛ አቻ ፍቺውን እስከ ነገ ጠዋት 2:00 ሰዓት ድረስ ቀድሞ ለሚነግረን ሰው የ100 ብር ካርድ እሸልማለሁ ። ✍ሜሮን አለማየሁ ኪቲላ @JALSMyF

  • እስቲ ኑሮ ኑሮዋን ፤አዎ አትከልሉኝ እርሷን አሳዩኝ ። ወንድ የሆነ ሰው እስቲ መሬት ላይ አውርዶ ኖሮ ያሳየን ፤Period! አቤት ምላስ፣አቤት ልፍለፋ፣አቤት ቀላሉን ነገር ቆልሎ ታዕምር እየተናገሩ ማስመሰል፥ለፉሩሽካ ሀሳብ ፊሽካ ማስነፋት... ዛሬም፣ነገም ፣ሁሌም እላለው simplicity is the ultimate sophistication !! የተወሳሰበ ነገር ብዙ ግዜ ግልብነት ና ገለባነት አይጠፋውም ። ትንሽ ወሬ ብዙ ስራ!! ✍️ሜሮን አለማየሁ ኪቲላ @JALSMyF

  • ‎how beautiful is that ;having a long and longer break, ‎ ‎ቤት ውስጥ መክረም(መዋል ማደር) ባዘወተራችሁ ቁጥር ውጭ መውጣት እንዴት ነው የሚከብደው ፤ሲብስ ደግሞ ከመኝታ ክፍል ወደ ሳሎን ለመሄድ ራሱ(ምግብ ደርሷል ፣እንግዳ መጥቷል ..)ወዘተ የሚሉ ብዙ motivational contents መስማት ያስፈልጋችኋል ። ‎ ‎ሁሌም ጥንክርክር ብሎ መስራት ፣ላይ ታች ማለት ideal አይደለም ።አንዳንዴ ለድካማችን እድል ና ግዜ እየሰጠን ከዚህ አለም ድካም ከሞት በፊት ማረፍ ጥሩ ነው 😊 ‎ ‎✍️ሜሮን አለማየሁ ኪቲላ ‎ ‎@JALSMyF ‎

  • ‎ከሰው ጋር በመኖር ውስጥ የሚገኙት በረከቶች ሁሉ መልካም ቢሆኑም ከውስጥ ሰላም ጋር ግን አይወዳደሩም ። ‎ ‎ብቸኝነት ምን ቢከብድም ፥ከራስ ዝቅ ብሎ ፣ከህሊና ጎድሎ ከመኖር ግን አይብስም ። ‎ ‎የህይወት መርህ በምን ይሸጣል ??? በድምጽ ና በህዝብ ብዛትስ ይለወጣል እንዴዴ?? ዝንተ ዓለም ለብቻ መቅረት ክብር አይደለም ወይ ራስን ለማይረባ ረብ፣አንቱታ፣ተድላ፣ተቀባይነት፣ሆይሆይታ እየሸራረፉ ከመሸጥ?!! ‎ ‎ብዙውን እየሸኘን ፣ጥቂቱን እያቆየን ከብዙው ደግሞ እየሸሸን እንኖራለን እስካለን !! ‎ ‎በዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ለሄዱትም ለቆዩትም ብርቱ ፍቅር በልባችን አለን ! ‎ ‎✍️ሜሮን አለማየሁ ኪቲላ @JALSMyF

  • ጨዋነት የሚጎድለው ጥበባዊ አገላለጽ ያስጠላኛል ። አዎ ስነ-ጽሑፍ ነፃነት ይፈልጋል ፣ ነፃ ያልሆነ አዕምሮ ሀሳብ መፍጠር ፣መፈላሰፍ መቻሉን አብዝቼ እጠራጠራለሁ ።ነገር ግን ጨዋነት የሚጎድለው ብዕር ያስጠላኛል ። "ጥበብህን እዛው ቀቅለህ.... " በይው በይው ያሰኘኛል ።ታዲያ እኔ አሁን እንዲህ ያለውን ዓ.ነ ጨርሼ ብፅፈው ራሱ አይደብርም ?? ሺ ግዜ አንባቢ ባያነብ ፤አድማጭም ባያዳምጥ ይሻላል ። ጥበብ ጨዋ ነው ፤አታባልጉት !!! ✍ሜሮን አለማየሁ ኪቲላ @JALSMyF

  • ፍቅር ቁጥር አይችልም 💙 !! ‎ ‎በደልንም ፣ ውለታንም አይቆጥርም ። ለዛ ነው መስጠትም ፥መቀበልም የሚያውቅበት ፤ ማይተናነቀው ። ‎ ‎✍️ሜሮን አለማየሁ ኪቲላ @JALSMyF

  • Maybe I have not told you this because I have so much respect for you... or maybe because I thought we both have our own religion, and I assumed it was a way of respecting boundaries... or maybe I was treating this truth as just one part of life rather than the source of life... or maybe I was trying to act like a cool person... or whatever other reason I might have had for not telling you that JESUS IS THE ONLY SAVIOR. To be honest, I am only saying this because I truly love you and want you to have peace of mind, eternal life, and God Himself with you. If you have been a friend, someone close to me, or anyone with whom I have shared any kind of relationship, and I have never said to you, word for word, "Your soul desperately needs JESUS to find true rest," I sincerely apologize. It is so shameful of me. I promise to remind you of this every now and then, throughout all the remaining days we spend together, because I truly want you to know that you're loved by JESUS if you are going to stay around me. But better late than NEVER. So here is my gentle reminder: "JESUS LOVES YOU, AND HE IS THE ONLY SAVIOR." ✍Meron Alemayehu Kitila @JALSMyF

  • አልረሳኋችሁም !! አዎ እየጠፋሁ ነው ግን የአዲስ ተመራቂ ነገር እንደምታውቁት ነው ..ሀሳቡ ብዙ ነው ። ስራውስ አልጠፋም ነበር የከበደን ራስን ና ፍላጎትን ፈልጎ ማግኘት ነው ፤ለብሩ ተብሎ የሚጀመር ስራ እኔነትን ይዞ ሊጠፋ ይችል ይሆናል ና ምንም እንኳ ገንዘቡን ብንሻውም መጀመሪያ ግን ህሊናችንን በvalue ና standard ማሰልጠን ያስፈልጋል ። የቱ ጋ ብንሆን ደስ እንደሚለን ና ሌሎችንም መጥቀም እንደምንችል በጌታ እርዳታ ለማግኘት በመሞከር ላይ ነን ። If you truly love me and you want me to coninue doing the plans I have in mind with you Guys keep me in your prayers ,specially for Good time managemnt and more clearer vision. በለሲቷን ጥቂት ታገሷት 🙏 😂😂እኔ ያሉ ማውራት ትንሽ ሼም ስለሚያስይዝ ብለን እኛ ብለን አወራን እንጂ እኛ የተባልኩትስ እኔ ነኝ ። much respect as always ✍️Meron Alemayehu Kitila @JALSMyF

  • መምሰል ከፈለጋችሁ ወይ ክርስቶስን አልያም ቅዱስ ጳውሎስን ምሰሉ!!እነርሱን መምሰል ከከበዳችሁ..ካቃታችሁ ካቃታችሁ ግን በቃ ራሳችሁን ምሰሉ እንጂ ሌላን ሰው ለመምሰል አትድከሙ ።(የመጨረሻ አላማችሁ አድርጋችሁ ማለቴ ነው እንጂ በእድገት ሂደት ውስጥ የአንዳንድ ሰዎች ተፅዕኖ ሊያርፍ እንደሚችል አይዘነጋም!!) ✍ሜሮን አለማየሁ ኪቲላ @JALSMyF

  • እንደተባባልነው I have no plan to continue sharing my thoughts over here ,we would rather start taking steps very soon tho the day is not not decided yet,Till then ግን በጣም አጥር ምጥን ያሉ ቁም ነገሮችን ልንገራችሁ ። 1)over dramatic በመሆን ውስጥ I mean ነገሮችን አወሳስቦ(over sophisticate) በማድረግ ሂደት ውስጥ ብዙ superficiality እንዳለ ጠርጥሩ! 2)እንደኛ ድህነት ጥግርር ባደረገው ማህበረሰብ ውስጥ ለfresh graduate ወይም ለማንኛውም ስራ ፈላጊ ፣ስራ ከማግኘት በላይ አስቸጋሪው ና ከባዱ ነገር ራስን ና ፍላጎትን ፈልጎ ማግኘት ነው ።ሁላችንም እንደምናውቀው ድህነት ባለጌ ነው ፣ጠርሰቅ ያለ ብር ያለው ስራ ሁሉ regardless of our passion and value ዋጋ አለው ብለን እንድናስብ ያስገድደናል ። 3)ofc አርግዘናል!ልጃችን ምናልባት ሶስት ወር ሆኖታል ፤የሰው ቅርፅ ይዟል ፥ነገር ግን ያልጨረሰው የእድገት ሂደት አለ ።ምንም እንኳ ራሳችንን በመስታውት እያየን ልጃችን እንደኛው ቆንጆ እንደሚሆን እያሰብን ቶሎ ለመውለድ ብንቋምጥም ፣ጤናማ ልጅ ከፈለግን we have to wait till the right time comes. 4)The last but not the least is...I honestly don't get it why we insist on choosing not to trust God despite all odds!I think we have to pray everytime "አለማመኔን እርዳው" የሚለውን የትሁት ሰው ጸሎት። አራት የTiktok video content በአንድ ግዜ ነው ያገኛችሁት😂you deserve! ✍Meron Alemayehu Kitila @JALSMyF

  • ሰላም ለሀገራችን ! ከምስራቅ እስከ ምዕራብ። ከሰሜን እስከ ደቡብ። ትምህርት ቤት መሄድ እየፈለገ ጦር ሜዳ የሚሰደድ ወንድም እስከማይኖር ፣ልጇን አጥታ በሀዘን ሲቃ የምትማቅቅ እናት እስከማትኖር ፣ አባት ቤተሰቡን ከሞት፣ከረሀብ፣ከፍርሀት መከላከል አቅቶት እርባና ቢስነት እንዳይሰማው እስክናደርግ ድረስ ፣የምትደፈር ሴት እስከማትኖር ድረስ ፣ የሰው ነፍስ ዋጋ እስከሚያገኝ ድረስ እባካችሁ እባካችሁ Let's start to do something!! show me you really care ,This has nothing to do with politics This is Genuinly a call to humanity! Let's say NO to war ! በቃ ጦርነት በቃ መጠላላት በቃ መገዳደል በቃ መጠላለፍ ሰላም ለሰው ልጆች ፣ለአምላክ ፍጥረቶች በሙሉ!ያለ ጎሳ፣ያለ ነገድ፣ያለ ኃይማኖት፣ያለ ፆታ ፣ያለ ዕድሜ ልዮነት !!! peaceforall #NoMoreWar #EnoughisEnough #MoP #NEYLPD #JFA-PF #ENG #Tigray #Amhara #Afar #Oromia #Ethiopia NEYLPD (Network of Ethiopiam Youth LeGeneration)aders for Peace and Democracy) JFA-PF (Justice For All-Prison Fellowship) ENG (Empowering Next Generation) ✍Meron Alemayehu Kitila @JALSMyF

  • Check out Meron Alemayehu Kitila's video! #TikTok https://vm.tiktok.com/ZSCXMsUPb/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite

  • Check out Meron Alemayehu Kitila's video! #TikTok https://vm.tiktok.com/ZSCXMsUPb/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite

  • ከድግስ ግርግሩ ሳንወጣ ፤ ደስታ ሙሉ የሚሆነው ከወዳጅ ዘመድ ጎረቤት ጋር ሲጋሩት ነው ና ከመሀል ከተማ ራቅ ብለው የሚገኙ የሀገራችን ክፍሎች በተለይ በትግራይ እንዲሁም በአማራ ና ኦሮሚያ ያሉ ወንድም እህቶቻችን አንዳንዶቻችን ደግሞ የስጋ ዘመዶቻችን ጭምር እንደኛው በአንፃሩም ቢሆን በሰላም ወጥተው መግባት እንዲችሉ ስለ ሰላም በሰላማዊ መንገድ መስበክ ና ማድረግ የምንችለው ነገር ካለ ማሰብ ና መመካከር ይኖርብናል። ፀሎት ያለው ሚና ቀላል እንዳልሆነ ሳላስታውሳችሁ አላልፍም ። ከሰሞኑ እንመለስበታለን ። @JALSMyF ✍ሜሮን አለማየሁ ኪቲላ

  • ‎ለካ እስካሁን መሬት እየተሽከረከረች ነው🤭🤭 ??! ‎ ‎ሰኔ 20 2018 እ.ኢ.አ ጅማ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት ዘርፍ ለአመታት ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ሲያስመርቅ እኔም በጌታ እርዳታ ከሺዎቹ መሀል አንዷ ነበርኩ ። ‎ ‎እምብዛም ግርግር የምወድ ዓይነት ሰው ባለመሆኔ ምንም እንኳን የአመታት ልፋት በመልካም መደምደሚያ ሲገባደድ ያለው ስሜት ቢሰማኝም ከceremony ጋር ተያይዞ የሚመጣው መዋከብ ግን ላያስደስተኝ ና ቶሎ ሊታክተኝ እንደሚችል በማሰብ የሰጋሁት እኔ ብቻ አልነበርኩም ቤተሰቦቼ ና በቅርበት የሚያውቁኝ ወዳጆቼ ጭምር እንጂ ። ‎ ‎እንደ ሴት ተመራቂ ተማሪ ሽርጉዱን ቀደም ብሎ ለመጀመር የሚያስችል ተነሳሽነት እንደሌለኝ ያወቁት ወላጆቼና ጓደኞቼ አንዳንዱን ነገር ራሳቸው አንዳንዱን ደግሞ በብዙ ግፊት ያስደርጉኝ ነበር ።(ፀጉሬን ምን ላድርገው የሚለውን መወሰን ራሱ ከExit በላይ ከብዶኝ ለመመረቅ ሰዓታት ሲቀረኝ የወሰንኩት ውሳኔ ነበር😁) ‎ ‎ከሁሉ በላይ አሳስቦኝ የነበረው ግን ጅማ በነበረኝ ቆይታ እግዚአብሔር በጎነቱን ለማሳየት የሰጠኝን መልካም ሰዎች(ባለውለታዎቼ) ን ና ወላጅ ቤተሰቦቼን ምን ባደርግ ማመስገን በምፈልግበት ልክ ማመስገን እችላለሁ ።እንዴት ግርግር ያልበዛበት የተረጋጋ ዝግጅት ማዘጋጀት እችላለሁ የሚለው ነበር ። ‎ ‎እና I said to God, "እንግዲህ ጌታ ሆይ እኔ የምወደውን አይነት ድግስ ልትረዳም ልትደግስም የምትችለው አንተ ነህ,I will be waiting for you" አልኩት ።And HE DID IT MORE AMAZINGLY THAN I COULD HAVE EVER IMAGINED!አባቴም አይደል! I was truly showered with so much love. ‎ ‎አይደርሱ የለ ወላጆቼ ከያሉበት ወደ ጅማ መጡ ፣የምርቃቱም ቀን ደረሰ ፤ እግዚአብሔር ከጠበቅኩት በላይ እኔንም፣ቤተሰቦቼንም፣ወዳጆቼንም አስደሰተን!!ግርግር ና ሁከት ያልበዛበት፣ዝም ያለ ና የተረጋጋ ፥energy drain የማያደርግ የምስጋና ግዜ በእውነት ደስታዬ ደስታቸው ከሆነው ወዳጆቼ ጋር አሳለፍኩ ። ‎ ‎ይህ ሁሉ ሲሆን ሁሉም ነገር ባለበት የቆመ እስኪመስለኝ ነበር ነፍሴ በሀሴት የተሞላው ፣ ለካስ ቅዳሜ ምርቃቱ አልፎ እሁድ አመሻሽ ላይ ቸርች ስሄድ ፕሮግራም አልቆመም Dave እያስተማረ ነው፣ሰኞ ወደ ግቢ ለጉዳይ ስሄድ ተማሪዎች እየተማሩ ፣ሰራተኞችም እየሰሩ ነው ፥ለካ ነገር ሁሉ በነበረበት እየቀጠለ ነው ፣መሬትም እየተሽከረከረች ነው 🤣🤣። ‎ ‎ሁሉ ነገር የቆመ እስኪመስለኝ ድረስ ነበር አምላኬ ያስደሰተኝ!!ስለዚህ ነገር ከማመስገን በቀር ከቶ ምን እመልሳለሁ ! ‎ ‎ሙሉ ቤተሰቦቼ(እህቶቼ ና ወንድሜ በተለይ አባቴ እንኳን ተመረቅን) ፣ ሽምዬ ና ትጌ እንዲሁም ሙሉ ቤተሰቦቹ ፣ዴቭዬ ና ንጉዬ እንዲሁም መላው ቤተሰቦቹ ፣ጌርዬ ና ኩምዬ እንዲሁም መላው ቤተሰቦቹ ፣አዚዬ ና አማ እንዲሁም መላው ቤተሰቦቿ ፣አክሊሉ ና ሮሚ እንዲሁም መላ ቤተሰቦቹ ፣ዳኙዬ ና መላው የቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች በሙሉ ፣ቃልዬ ና ሀኒዬ(ሀና ኡስማን) እንዲሁም ጓደኞቼ በሙሉ  የግቢ ቆይታዬን ስላስዋባችሁት ና ስለ እውነተኛው መውደዳችሁ ጌታ ኢየሱስ አብዝቶ አብዝቶ ይባርካችሁ ።እጅግ በጣም አመሰግናለሁ ።እግዚአብሔር ያክብራችሁ ። ‎ ‎ደህና አድርጎ አስጨረሰኝ። ‎ ‎በተለያየ መንገድ እንኳን ደስ አለሽ ላላችሁኝ በቅርብም በሩቅም ያላችሁ ስለ መልካም ምኞታችሁ አመስጋኝ ነኝ ። ‎ ‎And a special thanks to God, who uses everyone and everything for my good. Thank You for being with me through every high and every low, for holding my destiny in Your hands, and for being my true Provider, faithful Father, and Protector. Glory be to God the Father, the Son, and the Holy Spirit. I know it is You, dear God! ‎ ‎ጌታ ይሄ ምንድነው የምትሉትን ፥ቁም ነገር እንኳን የማይመስል ነገራችሁን እየሰራ ያስገርማችሁ!! ✍ሜሮን አለማየሁ ኪቲላ @JALSMyF

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

Meron's school of thoughts😊 — tgindex