tgindex
Min Addis?

I blog about marketing and sales, and also provide Infotainment news. Want to place ads? Click here: https://telega.io/c/min_ddis ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ሚዛናዊ ፣ አዝናኝ እና አስተማሪ የሆኑ ወሬዎች የሚለቀቁበት የኢንፎቴይንመንት ቻናል ነው

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
4
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Маркетинг
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
10 491
−22 за 3 дн.
Сутки
−14
−0,13%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 692
21 постов
Вовлечённость
25,7%
к подписчикам
Постов в день
0,6
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 765
1/48двое суток
2 022
1/72трое суток
2 181

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 13 авг.1 567161

    “ዓላማዬ ሐብታም መሆን እንጂ የሀብታም ሚስት መሆን አይደለም”:- ድምፃዊት ቬሮኒካ አዳነ አርቲስት ቬሮኒካ አዳነ በቅርቡ የሰጠችው አስተያየት አነጋጋሪ ሆኖ ቀጥሏል። “ዓላማዬ ሀብታም መሆን እንጂ የሀብታም ሚስት መሆን አይደለም” ያለችው አርቲስቷ፣ ግቧ በራሷ ጥረትና ልፋት የፋይናንስ ነፃነትን ማሳካት መሆኑን ገልጻለች። ከሀብታም ሰው ጋር በመጠጋት ወይም በመጋባት ሀብት ማፍራት እንደማትፈልግ የገለጸችው ቬሮኒካ፣ በሙያዋ በመስራት ሀብት መፍጠር እንደምትፈልግ ተናግራለች። “በራሴ ጥረትና ልፋት የፋይናንስ ነፃነት ማሳካት ነው ግቤ” ስትልም አቋሟን አስረድታለች። አስተያየቷ በማኅበራዊ ሚዲያ ውይይት እያስነሳ ሲሆን፣ የሴቶች የፋይናንስ ነፃነት፣ የራስ ጥረት እና ትዳር ከሀብት ጋር ስላለው ግንኙነት የተለያዩ ሀሳቦች እየተሰነዘሩ ነው። የአርቲስቷን አስተያየት እንዴት ተመለከታችሁት? አስተያየታችሁን በጨዋነት አስቀምጡ። Via-:-ኢትዮ ታይምስ @min_ddis

  • 12 авг.1 9141711

    “የኢየሱስ ስቅላት ሕገ-ወጥ ነው!” — ጉዳዩን ወደ ዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ሊወስዱ የሞከሩት ኬንያዊ ጠበቃ! አንድ ኬንያዊ ጠበቃ የኢየሱስ ክርስቶስን መታሰርና መሰቀል ሕጋዊነት ለመሞገት ወደ ፍርድ ቤት አምርተው እንደነበር ሲሰሙ ሊገረሙ ይችላሉ። የቀድሞው የኬንያ ፍርድ ቤት ቃል አቀባይ ዶላ ኢንዲዲስ፣ ኢየሱስ ፍትሐዊ የፍርድ እድል አልተሰጠውም በማለት ያልተለመደ ክስ አቅርበው ነበር። ጠበቃው ለስቅላቱ ምክንያት የሆኑት ሂደቶች በሙሉ አድሏዊና መሠረታዊ የሰብአዊ መብቶችን የጣሱ ናቸው ሲሉ ተከራክረዋል። እኚህ ጠበቃ ለተፈጸመው ፍርድ  ጲላጦስን፣ ንጉሥ ሄሮድስንና የአይሁድ ሽማግሌዎችን ተጠያቂ ለማድረግ ሞክረዋል። "የኢየሱስ ወዳጆች" የተባለው የእሳቸው ስብስብ፣ የጥንቱ የፍርድ ሂደት ውድቅ እንዲደረግ ይፈልጉ ነበር። ነገር ግን ጥረታቸው ስኬታማ ሊሆን አልቻለም። ክሱ በኬንያ ፍርድ ቤት ውድቅ ከተደረገ በኋላ፣ የዓለም አቀፍ ፍርድ ቤት ደግሞ የኔ ሥልጣን በሀገራት መካከል ያለውን አለመግባባት መዳኘት እንጂ ከ2,000 ዓመታት በፊት የተከሰተን ነገር ማየት አይደለም ሲል አቤቱታውን ሳይቀበለው ቀርቷል። (መረጃው የአዲስ አድማስ ነው) @min_ddis

  • 11 авг.2 066382

    ፎቷቸውን ትኩር ብዬ ተመለከትኩት፣ ህይወታቸው ገና ከፊታቸው የሚጠብቃቸው ወጣቶች እንደሆኑ ያስታውቃሉ። መሀል ላይ ያለው ወጣት ድንጋጤው ይጋባል፣ ሰው ባላጠፋው ጥፋት ሲከሰስ የሚሰማው ስሜት። ሁሉም 'ፋኖ ናችሁ' ተብለው ተረሸኑ፣ አስከሬናቸው እንኳን እንዳይነሳ ለቀናት ተከለከለ። ተመስገን ጌታቸው፣ ይታገሱ አሰግደው፣ ግዛው ግርማዬ! ነፍስ ይማር🙏 (Via-:-ጋዜጠኛ ኤልያስ መሠረት) @min_ddis

  • 10 авг.2 52716

    ቤተሰብ ለመጠየቅ የሄደችውን ባለትዳር  አስገድዶ መድፈር የፈፀመው አጓቷ እና ሌላኛው ተከሳሽ በእስራት ተቀጡ በካምባ ዙሪያ ወረዳ ኦቶሎ ቀበሌ ከርሼ በተባለ አካባቢ ነው የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው። ፖሊስ እንዳታወቀው ተበዳይ 22 ዓመቷ ሲሆ   ባለትዳር ናት  ቤተሰቦቿን ለመጠየቅ በመንገድ  ላይ እየተጓዘች ባለችበት ወቅት ተከሳሾቹ እንዳገኟት ተገልጿል። በዚህም ከተከሳሾቹ መካከል አንደኛው የተበዳይዋ አጎት ሲሆን ይህንን የቤተሰብ ቅርበት በመጠቀም ተበዳይዋ ሌሊቱን በሌላኛው ተከሳሽ ቤት አድራ በማግስቱ እንድትጓዝ በማሳመን ይዟት ይሄዳል። ሆኖም በጫካ ውስጥ ከደረሱ በኋላ ተከሳሾቹ ተበዳይዋን በዱላ በመምታት ራሷን መከላከል እንዳትችል ካደረጉ በኋላ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል መፈፀማቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። በደረሰው ወንጀል ተበዳይዋ ያቀረበችውን አቤቱታ ተከትሎ ፖሊስ ምርመራ በማካሄድ  የተበዳይዋን ቃል ጨምሮ በሰውና በሰነድ ማስረጃዎች የተደገፈ መሆኑን በመግለጽ የምርመራ መዝገቡ ለዐቃቤ ህግ ይልካል። ዐቃቤ ህግም ክስ መስርቶ ጉዳዩን ለካምባ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ያቀርባል።ፍርድ ቤቱም በጉዳዩ ላይ የቀረቡትን ማስረጃዎችና የተከራካሪ ወገኖችን አቋም ከመረመረ በኋላ፣ የዋና ወንጀል አድራጊው ከተበዳይዋ ጋር የቅርብ የስጋ ዝምድና ያለው በመሆኑ  ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም በዋለው የወንጀል ችሎት 1ኛ ተከሳሽ አየለ ባርጋደ በ14 ዓመት ፅኑ እስራት፣ 2ኛ ተከሳሽ  ጹንዖ ገርሻ ደግሞ በ13 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ መወሰኑን ምክትል ኮማንደር አሸናፊ ኃይሌ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል። (ዳጉ ጆርናል) @min_ddis

  • 9 авг.2 34581

    የሊዮኔል ሜሲ አባት ሆርሄ ሜሲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ:: የዓለማችን ታላቁ እግር ኳስ ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ አባት እና ዋና ወኪል የሆኑት ሆርሄ ሜሲ (Jorge Messi) በ68 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት መለየታቸው ይፋ ሆኗል። የልጁን ስኬታማ የእግር ኳስ ህይወት እና የንግድ እንቅስቃሴዎች በቅርበት ሲመሩ የቆዩት አባት ሆርሄ ሜሲ፣ በትውልድ ከተማቸው ሮዛሪዮ በሚገኝ ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ሲረዱ ቆይተው አርብ ነሐሴ 01 (August 7) ምሽት 4:00 ገደማ ሕይወታቸው ማለፉን የሜሲ ቤተሰቦች እና የአርጀንቲና መገናኛ ብዙኃን አረጋግጠዋል። እንደ ዴይሊ ሜይል (Daily Mail) እና ዘ ሰን (The Sun Football) ዘገባዎች ከሆነ፣ ይህ መረጃ በቤተሰቦቹ በኩል ይፋ የተደረገ እና ተረጋገጠ ነው። ሆርሄ ሜሲ ላለፉት በርካታ ወራት ከልብ እና ከነርቭ ህመም ጋር ተያይዞ በጽኑ ሲታመሙ የቆዩ ሲሆን፣ ቤተሰቦቻቸው የህክምና ሁኔታቸውን ከሚዲያ እይታ ውጪ ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። በዓለም ዋንጫ ጨዋታ ወቅት ሜሲ በሜዳ ላይ ያሳየው የተለየ የሐዘን ስሜት እና እንባ፣ ከአባቱ የጤና ሁኔታ ጋር የተያያዘ እንደነበር ይታወቃል። ሆርሄ ሜሲ ለአልቢሴሌስቴው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ የአባትነት ሚናቸውን ከመወጣት ባለፈ፣ ገና በወጣትነቱ ከሮዛሪዮ እስከ ባርሴሎና እና ባሻገር ላስመዘገባቸው ድንቅ ስኬቶች እና ግዙፍ የቢዝነስ ግዛቶች ዋና መሃንዲስ በመሆን የማይተካ ሚና ተጫውተዋል። ይህ ወቅት ለሜሲ ቤተሰቦች እና ለመላው የእግር ኳስ ቤተሰብ እጅግ ከባድ አጋጣሚ በመሆኑ፣ ለሊዮኔል ሜሲ፣ ለእናቱ ሴሊያ ኩቺቲኒ እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው በሙሉ ፈጣሪ መጽናናቱን እንዲሰጣቸው እንመኛለን። @min_ddis

  • 8 авг.2 239211

    የረፈደ ይቅርታ ማነው ያረፈደ አራዳ ¡ ማይኮ ሚኪ ይቅርታ ከጠየክ ተጸፅተህ ይቅርታ ጠይቅ ! የደከመ ማህበረሰብ ብለህ በጅምላ ተሳድበሃል። ማብራሪያህ ሚዛን አይደፋም። ጠያቂው ደግሞ መሞገት አልቻልክም! ጭራሽ ማይኮ ሚኪን ደግፈኸው ምንም እንዳላጠፋ ሰው ነው የምታወራው። ብዙ ሰዎች እኔን ኢንተርቪው ለማድረግ ይፈራሉ አላለም 😂😂😂😂😂😂 ማይኮ ሚኪ በግልፅነትና በሥነ- ስርዓት መካከል ሰፊ ልዩነት እንዳለ መረዳት አለብህ። ማይኮ ሶሻል ሚዲያ ላይ ከማንም በፊት እንደጥንቸል ፈጣን ነበርክ። ባልሆነ ድርጊትህ ግን ብዙ ኤሊዎች ቀድመውሃል ! በትክክል ከተጸፀትክ አሁንም ፈጣኑ ጥንቸል አንተ ነህ ! Via:-ዘሪሁን ተዝናኑ @min_ddis

  • 7 авг.2 4878

    видео или голосовое, без подписи

  • 7 авг.3 1368

    видео или голосовое, без подписи

  • 7 авг.2 511219

    ከላይ በምስሉ የምትመለከቷቸው ወንዶች በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ መስረተው  በመገኘታቸው በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባምባሲ ከተማ ፓሊስ በቁጥጥር ስር ዋሉ !    ከማህበረሰቡ ወግና ባህል እንዲሁም እምነት ያፈነገጡ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ ። ባምባሲ ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም| ከማህበረሰቡ ወግና ባህል እንዲሁም እምነት ያፈነገጡ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ ። በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል በባንቢስ ከተማበፎቶ የተመላከቱት እኒሁ ታደለ እናውጋውና በፀሎት እንየው የተባሉ ተጠርጣሪዎች በተመሳሳይ ፆታ ጋብቻ በመመስረታቸው... በማህበረሰቡ ጥቆማና ተጠርጣሪዎቹም የእምነት ቃላቸውን በሰጡት መሰረት ፖሊስ ተገቢውን የምርመራ ስራ መጀመሩንና በቀጣይ ውጤቱን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን ። ይሄንን መሰል አፀያፊ ተግባር እንዳይከሰት መፍትሔ ግን ምን ይሆን ? በጣም አስደንጋጭ ነው ። (ምንጭ፦ የባንቢስ ከተማ አስተዳደር ኮምኒኬሽን) @min_ddis

  • 6 авг.3 107

    видео или голосовое, без подписи

  • 6 авг.3 28312

    ቴሌቲቪ አዳዲስ ሀገርኛ ፊልሞችን ይዞ መጣ! ቴሌቲቪ ተመርቆ ወደ ሥራ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ በርካታ ድንቅ እና የተመረጡ የሀገራችንን የአማርኛ ፊልሞች ለተመልካች ሲያቀርብ መቆየቱ ይታወቃል። አሁንም በተመሳሳይ አዳዲስ እና አዝናኝ ፊልሞችን በመተግበሪያው (App) ላይ ይዞላችሁ መጥቷል። በዚህም መሠረት «ዲያስፖራው» እና «ሹምሽረት» የተሰኙት አዳዲስ ፊልሞች ሐሙስ መጋቢት 30 ቀን ከምሽቱ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ በቴሌቲቪ መተግበሪያ ላይ መታየት ይጀምራሉ። ዲያስፋራው የሮማንቲክ ኮሜዲ ዘውግ ያለው «ዲያስፖራው» ፊልም፣ ተወዳጁ ተዋናይ አለምሰገድ ተስፋዬ ከ6 ዓመታት ቆይታ በኋላ የተወነበት ድንቅ ሥራ ነው። በተጨማሪም በበርካታ ፊልሞቿ የምናደንቃት ተዋናይት ማክዳ አፈወርቅ ከ10 ዓመታት በኋላ ወደ ፊልም ኢንዱስትሪው የተመለሰችበት ሲሆን፤ ታዋቂዋ ቲክቶከር ባምቢ ሀበሻ (ሐና ግደይ) ለመጀመሪያ ጊዜ የሠራችበት እንዲሁም ተሻለ ወርቁ እና ሌሎችም ተዋንያን የተሳተፉበት አዝናኝ ፊልም ነው። በተጨማሪም በሲኒማ ቆይታውም ከ6 ወር በላይ በመታየት ሪከርድ መስበር የቻለ ተወዳጅ ፊልም ነው። ሹምሽረት በወንዶች ጉዳይና በሌሎች በርካታ ፊልሞች ተወዳጅነትን ያተረፈው ተዋናይ አድማሱ ከበደ ፈታኝና ጥሩ የታሪክ ፍሰት ያለው ስክሪፕት በማጣቱ ምክንያት ከሲኒማው ለረጅም ጊዜ ርቆ ከቆየ በኋላ፣ በቅርቡ በዩልያን ተክለማርያም ተደርሶ በተዘጋጀው “ሹም ሽረት” በተሰኘው አዲስ ፊልም ወደ ፊልም ተመልሷል። በዚህ ፊልም ላይ አንጋፋዋ ተዋናይት ፍቅርተ ደሳለኝ በተለየ ገጸ-ባህሪ የተሳተፈች ሲሆን፣ በተጨማሪም ማስተዋል ወንደሰን እና ሌሎችም ባለሙያዎች  ተሳትፈውበታል። እነዚህን  2 ፊልሞች ሐሙስ ዕለት በቴሌቲቪ መተግበሪያ ጠብቋቸው! ቴሌቲቪን ለማውረድ https://teletv.et/download

  • 6 авг.2 514121

    ዳናይት መክብብ ከቀረበባተ ክስ በነፃ ተሰናበተች የቲቪ ፕሮግራም አቅራቢዌ ዳናይት መክብብ ቀርቦባት የነበረው ክስ ውድቅ ተደርጎ በነፃ የተሰናበተች ሲሆን፣ ከእሷ ጋር በተመሳሳይ መዝገብ የተከሰሱ ሌሎች አራት ተከሳሾች ግን ጥፋተኛ ተብለው ገንዘብ እንዲከፍሉ ተወስኖባቸዋል። የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ አራተኛ ፍትሐብሔር ችሎት ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለው ችሎት በሰጠው ውሳኔ፣ አምስተኛ ተከሳሽ ሆና የቀረበችው ዳናዊት መክብብ የንግድ ፈቃድ አይታ የማስታወቂያ ሥራ የሰራች በመሆኗ በጉዳዩ ላይ ልትጠየቅ አይገባም በሚል ከክሱ በነፃ አሰናብቷታል። ጉዳዩ የተጀመረው 13 ከሳሾች «ወደ ውጭ ሀገር እንልካችኋለን» በሚል ከእያንዳንዳቸው 437 ሺህ ብር የተቀበላቸው የኤቢኤል ኮንሰልታንሲ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ የቤተልሔም ታደሰ፣ ገሊላ በለጠ፣ አቤል ተስፋዬ እና የዳናዊት መክብብ ክስ በመስረታቸው ነው። ከሳሾቹ የተወሰደብን ገንዘብ እንዲመለስልን በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ተከሳሾቹ ሊመልሱልን አልቻሉም ሲሉ ለፍርድ ቤቱ አብራርተው ነበር። እንደ ኢትዮጲካሊንክ ዘገባ ለወራት ክሱን ሲመለከት የቆየው ፍርድ ቤቱ፣ አራቱ ተከሳሾች ጥፋተኛ ሆነው በመገኘታቸው በነጠላና በአንድነት የተወሰደውን ገንዘብ ለከሳሾቹ እንዲከፍሉ ሲወሰን፣ ዳናዊት መክብብ ግን በነፃ ተሰናብታለች። (ዘገባውን የሰራው ኢትዮፒካሊንክ ነው) @min_ddis

  • 5 авг.2 8652

    видео или голосовое, без подписи

  • 5 авг.3 1432

    видео или голосовое, без подписи

  • 5 авг.2 66082

    ተወዳጇ ድምፃዊት ገነት ማስረሻ የህይወት አጋሯን በሞት ተነጠቀች ሞት የሰው ልጅ የጋራ እጣ ፈንታ ቢሆንም፣ የህይወት አጋርን እና የልብ ወዳጅን ማጣት የሚያሳድረው ሀዘን እጅግ ጥልቅ እና ከባድ ነው። በኢትዮጵያ የሙዚቃ መድረክ ላይ ለረጅም ዓመታት በጣፋጭ ድምጿ እና በማይጠገቡ ስራዎቿ የብዙዎችን ልብ ስታስደስት የኖረችው ተወዳጇ ድምፃዊት ገነት ማስረሻ፣ የህይወት አጋሯን እና የልጆቿን አባት አቶ አዱኛ ይስማቸውን በሞት ተነጥቃለች። አቶ አዱኛ ይስማቸው የልጅነት አየራቸውን በተነፈሱባት እና በተወለዱባት ታሪካዊቷ የጎንደር ምድር፣ ልዩ ስሟ እንፍራዝ በተባለችው ውብ ከተማ በ1948 ዓ.ም ነበር ወደዚህ ዓለም የመጡት። በምድራዊ የህይወት ጉዟቸውም በውጣ ውረድ ውስጥ አልፈው 70 የተከበሩ ዓመታትን አስቆጥረዋል። ድምፃዊት ገነት እና አቶ አዱኛ በፍቅር እና በመከባበር የታነፀ ፅኑ ትዳርን መስርተው፣ የትዳራቸው የፍቅር ማሳያ የሆኑ ሁለት ወንድ እና ሁለት ሴት ልጆችን አፍርተዋል። አቶ አዱኛ ለድምፃዊቷ የትዳር አጋር ብቻ ሳይሆኑ፣ በህይወት ጉዟዋ ሁሉ ከጎኗ የቆሙ ፅኑ ደጋፊዋ፣ የደስታዋ ተካፋይ እና የልብ ወዳጇ ነበሩ። ገነት ሆይ! የሰው ልጅ ውጫዊ አካሉ ቢያልፍም፣ አብራችሁ ያሳለፋችሁት መልካም ጊዜ፣ የተካፈላችሁት ጥልቅ ፍቅር፣ እና ያፈራችኋቸው አራት ውድ ልጆች ሁሌም ከጎንሽ ሆነው የህያውነቱ ማረጋገጫ ይሆናሉና በርቺ... ፅኚ! ሀዘንሽን እንጋራለን፤ ፈጣሪ ልብሽን ያፅናው። የዚህ የተከበሩ የቤተሰብ አባት እና ውድ የትዳር አጋር የቀብር ስነስርዓት፣ ሐምሌ 29 ቀን 2018 ዓ.ም በቦሌ አራብሳ ደብረ ገነት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ የጥበብ ቤተሰቦች እና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት ተፈፅሟል። ነፍሳቸውን ፈጣሪ በገነት ያኑርልን🙏🙏 (ዘሃበሻ) @min_ddis

  • 4 авг.3 6432

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 авг.3 6932

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 авг.3 1462

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 авг.2 4692

    видео или голосовое, без подписи

  • 4 авг.2 5322

    видео или голосовое, без подписи

Min Addis? — tgindex