ከራድዮን🕊🕊
Статистика╱◥██████◣ │∩│🌄▤│▤▤│ -✅እንኳን ደህና መጡ ከራድዮን — የጥበብ ድምፅ! በልጅ ስሉጥ እና በሌሎች ገጣሚዎች የሚቀርቡ፡ 👉ልብ የሚነኩ ትረካዎች 👉የማይረሱ ግጥሞች 👉የሕይወት ፍልስፍናዎች 👉 የውሎ ገጠመኞች ይቀላቀሉን፣ በጥበብ ይርኩ! የብዕር ጠብታ የሀሳብ ጋሪ ከራድዮን ነው የጥበብ አዝማሪ ኑ አብረን እንደግ
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 7
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 37
- 1/48двое суток
- 42
- 1/72трое суток
- 45
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ፥ ያሳያል። — 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6:15-16 Amharic Bible Bot
አንዳንድ ፍቅር... አንዳንድ ፍቅር አለ ላለመጥፋት እየታገለ፤ የመውደድ ልኬት የፍቅር ስሌት፤ ሳይኖራቸው የተፋቀሩ — ስንት አሉ... ፍቅር እየተሰጣጡ፣ ነፍስ እየተለዋወጡ፤ ለዘላለም የሚኖሩ። ስንት አሉ..... @Rufaylen13 💫 ✍️ ህላዌ💕
ክፍል ሰላሳ ሶስት ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ … ራሴን ሳትሁ… (ጨለማ ውስጥ ነበርኩ… ነገር ግን እንደ ብርሃን የሚያበራ ህልም ውስጥ ሆኜ…) ከሩቅ… አንድ ነጭ ነገር… ቀስ ብሎ ግልፅ ሆነልኝ… እሷ…ናት አብሱዬ… ነጭ በነጭ ልብስ ለብሳ… እንደ አበባ ተውባ … ንፁህ እርጥበት ሳይነካት… ወደ እኔ እየሮጠች መጣች… “አቤኒ…” ብላ በስሜ ጠራችኝ… ድምፅዋ… በልቤ አቃጨለ… እኔም እጄን ላቅፋት አየዘረጋሁ… “አብሱ…” ብዬ ወደ እሷ መሮጥ ጀመርኩ… ርቀቱ አጭር ነበር… ግን እንደ ዘመን ረዥም ሆነብኝ… እሷ እየቀረበች… እኔም እየቀረብኩ… ልንገናኝ ልንተቃቀፍ ተቃርበን— በድንገት… እግሯ ተንሸራተተ… በመካከል ወደቀች… “አብሱ!!!” ብዬ ጮኽኩ… ልደርስባት ፈለግሁ… ግን እግሬ አልንቀሳቀስም አለኝ… እጄ አልደረሰባትም… እሷ በመሬት ላይ… እኔ ግን በርቀት… ሆነን ዓለም ቆመ… … “አብሱ!” ጮህኩ ብድግ አልኩ ነቃሁ… ሰውነቴ በላብ ተሞልቶዋል … ዓይኖቼ ፈጠዋል… ህልም እንደነበር አስተዋልኩ… ዙሪያዬ ተመለከትኩ… ነጭ ግድግዳ… የመድሀኒት ሽታ… ዝምታ… ሀኪም ቤት ነኝ… ልነሳ ሞከርኩ… እጄ ከላይ በተንጠለጠለ ጉልኮስ ቁስሌን ጎተተ… በዚያው ቅፅበት— “እንዴ! አቶ ኢብራሂም!” የሚል ድምፅ ተሰማኝ… ነርሷ በፍጥነት ወደኔ መጣች… “እንኳን በሰላም ነቃህ… አትነሳ… እባክህ…” አለች (ረጋ ባለ ድምፅ)… እኔ ግን ሁሉም ጥያቄ ሆነብኝ— “የት ነኝ? ምን ሆንኩ? ማን አመጣኝ?” አልኳት በቀጥታ… እሷ ትንሽ ፈገግ እያለች — “መጀመሪያ አረፍ በል… እነግርሃለሁ…” አለችኝ… ከዚያ ቀስ ብላ ማስረዳት ጀመረች— “መንገድ ላይ ወድቀህ ነበር… ራስህን ስተህ…” “ጓደኞችህ አመጡህ…” “ምን ሆኜ ነው?” “ደምህ ወርዶ ነበር… ምግብ ስላልበላህ… ደክሞሀል…” ቃላትዋ እንደ ሩቅ ድምፅ ይመስሉኝ ነበር… “ስንት ቀን…?” አልኳት… “አንድ ቀን…” አለች… ከዚያን ወጣች… እንደነቃሁ በር ላይ ወታ ለሰዎች ነገረቻቸው… በትንሽ ጊዜ— ልዩነት በሩ በፍጥነት ተከፈተ… አብዱና የሱፍ…ናቸው “ኢብሮ!” ብለው ሁለቱም ወደ እኔ መጡ… የሱፍ ትከሻዬን አጠናክሮ አየያዘ… “በርታ በል…” አለኝ… አብዱ በስስት አይኖቹ እያየኝ … “አልሃምዱሊላህ…” ደጋግሞ አመሰገነ… ሀኪሞቹ መድሀኒት...ምግብ መብላት እንዳለብኝ...ምክር ሰተውኝ ከዚያን ወደ ቤት ገባሁ… ለሶስት ቀን ሙሉ… ከእኔ አልተለዩም… ቤቴ ሆኑ… አብረውኝ ተኙ… አብረውኝ ተቀመጡ… ዱአ አደረጉልኝ… ምግብ ሰሩልኝ.... መከሩኝ… “አብሱን እርሳት…” “አላህን ቅርብ አድርግ…” “ይሄ ይሻልሀል …” ከአንደበታቸው ሁሌም አይጠፋም እኔ ግን… ልቤ አልተስማማበትም… ያ ቅዠት… በህልሜ ያየሁት… እሷ በመካከል ስትወድቅ… ሀሳቤ አላረፈም… ቀን ሆነ ከሌሊት… እሷን ብቻ አስባለሁ … ናፈቀችኝ… አራተኛ ቀን ላይ… “ሁለቱም እየመጣን እንጠይቅሀለን…” ብለውኝ ወደየ ቤታቸው ሄዱ… ቤቱ ብቻውን ሆነ… እኔ ግን… በሩ እስኪዘጋ ድረስ ጠብቄ… ቀስ ብዬ ከአልጋዬ ተነሳሁ… “ላገኛት…” እግሬ ብዙም እየተንቀሳቀሰ አልነበረም ስወድቅ የሆነ ነገር መቶኛል… ግን ልቤ እየገፋኝ… ወደ አብሱ ቤት መንገድ መራመድ ጀመርኩ… በእግሬ እያዘገምኩ… ስለሷ እያሰብኩ… ቀስ ቀስ እያልኩ— “እንዴት ሆና ይሆን…?” “አገኛታለኋ…?” “ወይስ…?” አላገኛትም አያይይይይ ህልም የእውን ተቃራኒ ነው (ከራሴ አየተሟገትኩ....) በመጨረሻ… በራቸው አጠገብ ደረስኩ… እጄን ወደ በሩ… ላንኳኳ—ስል ግን… ከሩቅ… ያልጠበቅሁት ነገር ታየኝ… እጄ መልሶ ተጨበጠ… እግሬ ባለበት ቆመ… ልቤ ተወገረ… ባለሁበት ደርቄ አፍጥጬ ቀረሁ… ይሄ ፅሁፍ 35❤️ ካገኘ🤗 .........ይቀጥላል......... @Rufaylen13 💫 ✍️ ህላዌ💕
እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። — የማቴዎስ ወንጌል 11:28 Amharic Bible Bot
የፊተኛውን ነገር አታስተውሉ፥ የጥንቱንም ነገር አታስቡ። — ትንቢተ ኢሳይያስ 43:18-19 Amharic Bible Bot
ያልታመመው ሞተ🙂↕️
ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። — ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:6 Amharic Bible Bot
ክፍል ሰላሳ ሁለት ፍቅር ወይንስ እምነት #በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ በሩን ተደግፌ አለቀስኩ… ድምፄ ተዋጠ … እንባዬ ግን አልቆ ነበር። ለአፍታ እንባዬን ዋጥ ሳደርግ… ከውጪ… የአብሱ የተሰበረ የሲቃ ድምፅ ተሰማኝ። ልቤ በአንድ ጊዜ ተናወጠ… “ክፈት… አቤኒ…” እንደምትል ተሰማኝ… ወደ በሩ እጄ ተዘረጋ… ልከፍትላት ፈለኩ… ላቅፋት ፈለኩ… እንደ ቀድሞ እጄ ውስጥ እንድትሆን ፈለኩ… ግን… አንድ ነገር ውስጤን አጠነከረ… እኔን ከእሷ በኀይል አራቀኝ… አታፈቅረኝም....አይደል እጄን አወረድኩ… በሩን አልከፈትኩም… ከእንባዬ ጋ መልሼ ተነጋገርኩ… “በቃ…” አልኩ ለራሴ… ከዚያ… ሁሉም ነገር ዝም አለ… ስልኬ ጠራ… አየሁት… እሷ ነች… ልቤ እንደገና መታ… ነገር ግን እጄ አልተንቀሳቀሰም… ዘጋሁባት… ደገመች… ደገመች… እኔም ግን… ደጋግሜ ዘጋሁት… ሰላም ማግኘት ፈለግኩ… ልረሳት ሞከርኩ… ከቤት አልወጣሁም… ምግብ መብላት አላሰኘኝም… ልቤ ለብቻው በሀሳብ ይበላኛል… ሳብሰለስል....በመጨረሻ…እንቅልፍ አሸነፈኝ...ጥቅልል ብዬ ተኛሁ… በንጋታው ጠዋት ከመንቃቴ… ስልኬ መጮህ ጀመረ…አስደነገጠኝ ምንጊዜ እንደከፈትኩት ረስቼዋለሁ… ከብዙ ጊዜ ጥሪ በኋላ አነሳሁ… “አሰላሙ አለይኩም…” ድምፅ ተሰማኝ… ሀጂ ነበሩ… እኔም በደካማ ድምፅ “ወዓለይኩም ሰላም…” አልኩ… ትንሽ ጊዜ ዝም አሉ… እያሰቡ እንደሆነ ተሰማኝ-.... ከዚያ በረጅም ትንፋሽ መናገር ጀመሩ— “ልጄ… ድምፅህ ደህና አይመስልም… ልብህ ደክሞአል…” “ነገር ግን አላህ አይጨክንም… ሰው ቢሰበር እርሱ ይጠግናል…” “ያ የምታስበው የሚሰማህ ህመም… ያልፋል…” “ልጄ… ይቅርታ መማር አለብህ… ለራስህንም… ለሌሎችም…” እኔ ዝም ብዬ እየሰማኋቸው… እንባዬ ከየት እንደመጣ ሳላቅ ዳግመኛ መውረድ ጀመረ… “ና… መስጊድ ና…” አሉኝ በረጋ ድምፅ “ቁርአን ትቀራለህ… ልብህ ይረጋጋል …” “ሰላት ታደርጋለህ… ነፍስ ትዘራለህ…” “ና በቃ… ስለእሷ ማሰብ ይብቃህ ልጄ…” “አላህ ያለው ነገር ይሻልሀል…” “አንተ ገና ትኖራለህ…ብዙ ታያለህ” የነገሩኝ ቃላቸው… እንደ አባት እጅ ልቤን አሸሸገው… እኔ ግን ቃል አጣሁ… “ሀጂ… እኔ…” አልኩ በቀስታ ነገር ግን ሌላ ቃል አልቀጠልኩም… “ና… እንጠብቅሃለን…” አሉኝ እኔም… “እሺ… እመጣለሁ…” አልኳቸው…ደስስ እንዲላቸው ብቻ… ......ተሰነባበትን.... ግን… መሄድ አልቻልኩም… ድፍረቱን አጣሁ ተነሳሁ...እንባዬን ጠራረግኩ ሰውነቴ ከባበደኝ… በስንት ቀኔ ገላዬን ታጠብኩ… መስታወት ላይ ራሴን ስመለከት… ራሴን አላወቅሁትም… ፊቴ ላይ ፂም ሞልቶታል… ዓይኖቼ ደክመዋል… “ይሄ እኔ ነኝ…?” ብዬ አስብኩ… ግን… ውስጤ ባዶ ነበር… ቤቴ ተዝረክርኳል… እንደ ልቤ… ከሰዓት በኋላ… ትንሽ የሆነ ነገር የሚበላ ለመግዛት … በኪሴ ያለውን ብር አራግፌ…ከቤቴ ወጣሁ በስንት ጊዜዬ... መንገድ ጀመርኩ… ነገር ግን…ጥቂት እንደሄድኩ እግሬ አልታዘዝም …አለኝ አካሌ ከባበደኝ… ራሴን አዞረኝ… ሰማይ እና ምድር ተቀላቀሉብኝ… የሰዎች ድምፅ እንደሚርቀኝ ተሰማኝ… “አቤኒ…!” የሚል ድምፅ የሰማሁ መሰለኝ… እሷ ነች…? ወይስ በህልሜ ነው…? አላወቅሁም… ዓይኖቼ ጨለሙብኝ… እግሬ ተንሸራተተ… … ከዚያ… ምንም አልተሰማኝም… ራሴን ሳትሁ....ወደቅኩ ይሄ ፅሁፍ 30❤️ ካገኘ🤗 .........ይቀጥላል......... @Rufaylen13 💫 ✍️ ህላዌ💕
አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ። — መዝሙረ ዳዊት 51:1 Amharic Bible Bot
ፈሪ ልብ ላላቸው። እነሆ፥ አምላካችሁ በበቀል በእግዚአብሔርም ብድራት ይመጣልና፥ መጥቶም ያድናችኋልና በርቱ፥ አትፍሩ በሉአቸው። — ትንቢተ ኢሳይያስ 35:4 Amharic Bible Bot
እምነትም ተስፋ ስለምናደርገው ነገር የሚያስረግጥ፥ የማናየውንም ነገር የሚያስረዳ ነው። — ወደ ዕብራውያን 11:1 Amharic Bible Bot
ብዙ ያስታመመ ብዙ አያለቅስም🙌 ምንማለት ነው fam😊
እግዚአብሔርም ለድሆች መጠጊያ ሆናቸው፥ እርሱም በመከራቸው ጊዜ ረዳታቸው ነው። — መዝሙረ ዳዊት 9:9-10 Amharic Bible Bot
ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። — ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:13 Amharic Bible Bot
ምረጪ🥰☹️
አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም፤ በከንቱ የሚገበዙ ያፍራሉ። — መዝሙረ ዳዊት 25:3 Amharic Bible Bot
ያንም መገለጡን በራሱ ጊዜ ብፁዕና ብቻውን የሆነ ገዥ፥ የነገሥታት ንጉሥና የጌቶች ጌታ፥ ያሳያል። — 1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 6:15-16 Amharic Bible Bot
ንገሪኝ አሁን እንደኔ ያለ አለ!? ክንፍ ሳይኖረው ለሰማይ ስንጥብ ሳይኖረው ለባህር ልብ ሳይኖረው ለምድር እንዲሁ የተፈጠረ !? በጨካኝ ዓለም ውስጥ ጥርሱ ሳይሾልለት ጥፍሩ ሳይረዝምለት ቀንድ ሳይቆምለት፤ እንዲሁ እያለቀስክ ተንፍስ የተባለ!? አለ !? ንገሪኝ ሰምተሻል!? ሰው ጭንብሉን ጥሎ ሰው ሲኾን አይተሻል!? ሰው ልቡን ቢያራራ ሰው ትጥቁን ቢፈታ ሰው ፍፁም ይቅር ቢል ይኖር ይመስልሻል!? ይቻላል !? መርዝ የሌለው ዕባብ ጥርስ የሌለው አዞ እሾህ የሌለው ጃርት በደስታ ይኖራል!? እሾህ ቀንድና መርዝ የፈጠረ ጌታ ጦርነት ይጠላል!? ይቻላል!? ሰው ላይሞት ይኖራል !? ቻው ... ባይኖረው ፍቅር ሰው ችሎ ያፈቅራል!? እንጃ ፤ እኔ .. ምንም አላውቅ ፤ ምንም አልናገር ፤ ብቻ እንድታውቂው ነው ፤ ለብቻዬ ስኾን እንደሚያስጨንቀኝ እንዲህ ያለው ነገር። . . https://t.me/Kenako_12
እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት። — 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 5:7 Amharic Bible Bot
#ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ እውነተኛ ታሪክ ነው...ለግለሰቧ ደህንነት ስል ስሞችን ለውጬዋለሁ። -ከገጠመኝ ውስጥ .... *ትሁትና ፍቅረኞችዋ💔 ነገሩ የሚጀምረው የዛሬ 5 አመት ይሆነዋል በክረምቱ ሰበብ እረፍት ስለሆነ የሆነ ገዳም ለሱባኤ በሄድኩበት ጊዜ አንዲት መልከ መልካም አይኖችዋ የሚያማምሩ ስትታይ ውብ የሆነች ነገርግን አለባበሷ ጉስቅል ያለ ፊቷ የገረጣ ሰውነቷ ክስት ብሎ ያለእድሜዋ ስትታይ ትልቅ ትመስላለች ግን አተኩሮ ላያት ስትታይ አፍላ ወጣት ናት...23 አመቷ ነው በሁለት ሳምንት ተግባባን እና በወሬ ወሬ ስለ ፍቅር ታሪኳ ጠየቅኳት ውስጧ ባይደሰትም ቀስ በቀስ.... ነገረችኝ ትህትና እውነትም እንደ ስሟ እሷም ትሁት ናት። ትሁት የመጀመሪያዋን ፍቅረኛዋን ያገኘቹ እሷ 8 እሱ 10 ክፍል በሚማርበት ወቅት ነው....ሁኔታውን ስታጫውተኝ የምትወደው ፍቅረኛዋ አጠገቧ ካለው ግቢ ሲሆን የዛን ጊዜ ሁኔታዋን ስታጫውተኝ አይኖችዋ እንባ እያቀረሩ🥺 እንደነገርኩሽ ጎረቤቴ ነው ሲገባ ሲወጣ አይኖቼ እሱን ለማየት ይንከራተታሉ የአይን ፍቅር ነው የሚባለው እንደዛ ነገር አሰቃኝቶኛል ...በጊዜ ሂደት እሱም እኔን እያየ በአይናችን መግባባት ጀመርን... ከዛን አንድ ቀን የሱና የኛ ግቢ አጥር ፊለፊት ከምንተያይበት አቅጠጫ የሆነ ፅሁፍ ፅፎ ወረቀት አስቀመጠልኝ...እናቴ ስትወጣ ጠብቄ በሆነ ጠባብ ክፍተት ወደ እሱ ግቢ ገባሁ ወረቀቱን አነበብኩ በሰማያዊ ና በቀይ እስኪሪብቶ ያሸበረቀ ልብ ጦር ሲወጋው ውይ እንዴት ደስስ እንዳለኝ የእሱን ሉክ ወስጄ እኔም በአቅሜ ፅጌረዳ🌹 አበባ ስዬ እንደገባሁ በፍጥነት ከግቢው ወጣሁ እናም እንዲህ በስዕል መልክት መላላክ ከጀመርን እንደ ቀልድ 3ወር አለፈን በአካል ተገናኝተን አውርተን አናውቅም ግን በፅሁፍ ተግባብተናል እሱም ፍቅሩን እኔም ፍቅሬን በፅሁፍ ግልጥ አረግን....እንደውም ከፃፈው ውስጥ ግጥምም ባይገጥምም ይፅፍ ነበረ መቼ ነው ማገኝሽ አንቺ የቅርብ ሩቅ የምሰጥሽ አለኝ የያዝኩትን ፍቅር....ብዙ... ...የተፃፃፉት እንዲሁ በፅሁፍ እያወሩ እያጠራቀመች አንድ ቀን ቦርሳዋ ውስጥ ታላቅ እህቷ ታገኝባትና እጅጉን ተገረፈች...ተሰደበች ያልደረሰባት ነገር የለም በርበሬ ራሱ ሳይቀር ታጥናለች...እንደዛም ሆኖ ግን እጅግ በጣም ነበር የምትወደው🤗 ከእለታት ባንዱ ቀን ግቢ ቤተሰቦችዋ በሌሉበት ወቅት እሱ ከጓደኛው ጋ ሁን በአጥር ውስጥ ወረቀት ወረወረላት ...ሰፍ ብላ ስታየው ስልክ ቁጥር ነበር....በስንትንተኛው ቀን ብቻ እሷ ስልክ ስለሌላት በእናቷ ስልክ ተደብቃ ደወለችለት አወራቹ ቀስ በቀስ እያ ወሩ በተግባቡ ቁጥር በነፃነት ልታገኘው በአካል ልታናግረው ፈለገች ተቀጣጠሩ....ተገናኙ....ግን በቀጠሮ ቦታው የነበረው የምትወደው ፍቅረኛዋ ሳይሆን ጓደኛው ነበር😱😢 ተራ ቁጥር 2 ፍቅረኛዋ ይቀጥል ወይ? @Rufaylen13 💫 ✍️ ህላዌ💕