tgindex
✞︎ቤተ ቅዱስ ሚካኤል ✞︎ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ✞︎⛪️

✞︎ቤተ ቅዱስ ሚካኤል ✞︎ኦርቶዶክሳዊ አስተምህሮ ✞︎⛪️

Статистика

በዚህ Channel ውስጥ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ዶግማ ፤ ቀኖና እና ትውፊት የጠበቁ ትምህርቶች ይተላለፉበታ ✞︎የተለያዩ_ተከታታይ ትምህርት ✞︎ስበከት ✞︎ስንክሳር _የቅዱሳን _ገድል _ በየዕየለቱ አለ ✞︎መንፈሳዊ ጥያቄዎች በዕየለቱ አለ ✞︎የተለያዩ ሌሎች መንፈሳዊ ጽሑፎ ለአስተያየት: ጥቆማና ጥያቄ በዚህ ያግኙን ☞ @Kidus_Michaelabate_12_bot

Последний пост
15 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
14
Всего постов
545
Тип
открытый
Язык
und
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
37 153
+32 за 5 дн.
Сутки
+15
+0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 465
40 постов
Вовлечённость
3,9%
к подписчикам
Постов в день
2,0
всего 545
Упоминаний
2
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1 196
1/48двое суток
1 370
1/72трое суток
1 478

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • без подписи

  • без подписи

  • ​📖📖 ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፱/9 🤩በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ​📌በዚች ቀን ከስጥኑፍ አገር የሆነው፣ በሥጋውም በነፍሱም ንጹሕ የነበረውና አምላካዊ ራእይን ያይ የነበረው የከበረው ቄስ አባ ኦሪ በሰማዕትነት አረፈ። ​📌ይህ ቅዱስ እጅግ ርኅሩኅና ንጹሕ በመሆኑ፣ የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመሠዊያው ላይ ታይቶ ብዙ ምሥጢራትን ይገልጥለት ነበር። ​📌ዜናው በኒቅዮስ አገር መኰንን ዘንድ በተሰማ ጊዜ አስቀርቦ "ለአማልክት ዕጣን አቅርብ" አለው፤ ቅዱስ ኦሪ ግን ለተሠሩና ለረከሱ አማልክት አልሠዋም ብሎ እምቢ አለ። መኰንኑም በብዙ ሥቃይ አሠቃይቶ ወደ እስክንድርያ ላከው። ​📌በዚያም በጽኑዕ ሥቃይ አሠቃይተው በእስር ቤት ጣሉት፤ ቅዱስ ኦሪ ግን በእስር ቤት ሳለ ድንቆችና ተአምራትን በማድረግ ደዌ ያለባቸውን ሰዎች ሁሉ ፈወሳቸው። ​📌መኰንኑም ይህን ሰምቶ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡት አዘዘ፤ እርሱም ተጋድሎውን ፈጽሞ የሰማዕትነትን አክሊል ተቀበለ። ​📌ከዚህ በኋላ የከበረው ዮልዮስ ሥጋውን አንሥቶ በግንዘት ወደ አገሩ ወደ ስጥኑፍ ላከው። የመከራውም ወራት ካለፈ በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ሠርተው ሥጋውን በውስጧ አኖሩት፤ ከቅዱስ ሥጋውም ታላላቅ ተአምራትና ፈውስ ተገለጠ። ​"ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን፤ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።" ምንጭ፦📖📖#መጽሐፈ_ስንክሳር ​"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" (የቅዱሳንን ዜና/ታሪክ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል) ✍️አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር📖)  📱ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄🌐 ╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮    @Kidus_Michaelabate_12 ╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯ ​📌በንጽሕናው አምላካዊ ምሥጢር የተገለጠለትንና በእስር ቤት ሆኖ ድውያንን የፈወሰውን የታላቁን ሰማዕት የቄስ አባ ኦሪን ገድል Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ❕

  • 14 авг.1 29654

    "ኑ ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ" (ብፁእ አቡነ ሺኖዳ) ኑ ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ ፤ ኑ በፀሎት ወደአምላክ ቅረቡ ፤ በፀሎት ማለት እንዴትነው? ይህስ የልባችሁን ምስጢር ሁሉ ሳትደብቁ እርሱ እግዚአብሄር እንደሚያስፈልጋችሁ መናገር ማለት ነው ፤ እንዲህም በሉ ፦ “ጌታ ሆይ ወደ አንተ መምጣት እፈልጋለሁ ፡ ጌታ ሆይ ካንተ ተለይቼ እኔ ምንም ነኝ ፡ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ህይወቴን አጣሁ ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ደስታየን ሁሉ አጣሁ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ህይወቴ ትርጉም አልባ ሆነ ፤ ጌታ ሆይ እኔ አንተን ያጣሁ እለት ህይወቴ ጣእም አልባ ሆነ” በሉ ፤ ዳግምም ከእግዚአብሄር እግር ስር ተደፍታችሁ እንዲህ በሉት፦ “ አምላኬ ሆይ ፦ ወደ አንተ መመለስ እፈልጋለሁ ፤ ነገር ግን ጠላቶቼ ከእኔ በእጅጉ የሚበልጡ ናቸው ፤ ነፍሴንም አምላክሽ አያድኑሽም የሚሏት ብዙ ናቸው” ፡፡ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ ፤ “ ጌታ ሆይ ታደገኝ ወደ አንተ የምመለስበትን መንገድ ምራኝ” በሉት ፤ ለአምላካችሁ ንገሩት ፦ “ካንተ ከተለየሁ ወዲህ አቅሜ ሁሉ ተዳክሟልና ጌታ ሆይ ልዩ ሃይልህን ላክልኝ ፡ ወዳንተ የምመለስበትን ልዩ ርዳታህን ስጠኝ ፤” በማለት፡፡ ብዙ ሰወች በመደጋገም “ወደ እግዚአብሄር የምመለሰው እንዴት ነው ?” ይላሉ፡፡ ከእግዚአብሄር እግር በታች ራሳችሁን ጣሉ ፡ እንዲህም በሉት ፦ “ ጌታ ሆይ ሳትባርከኝ አልለቅህም ፡ ወዳንተ አቅርበኝ ፡ ከልጆችህ እንደአንዱ አድርገኝ ፡ ሃጢአቴን ብቻ ይቅር እንድትልልኝ አልሻም ፡ ይልቁንም ከሃጢአት ፍቅር ትለየኝ ዘንድ ጭምር እንጂ ፡”በሉት ፦ ዳግምም “ ጌታ ሆይ የሃጢአት ፍቅር ልቤን ተቆጣጥሮታልና ይህን ካላስወገድኩ ወዳንተ መቅረብ አይቻለኝም ፡ ጌታ ሆይ የሃጢአትን ፍቅር ከልቤ ላይ ንቀል ፡” በሉት ዳግምም እንዲህ በሉት ፦ ”ጌታ ሆይ ከሃጢአቴ ነፅቼ ወዳንተ መምጣት እንደምን ይቻለኛል? ይልቁንስ መጀመሪያ አንተ ናልኝ ሃጢአቴንም ደምስስ እንጂ “ እንዲህም በሉት ፦ “ በራሴማ ሃጢአትን ማስወገድ ብችል ወዳንተ መቼ መመለስ ያቅተኝ ነበር? እኔ ግን አንተ ከሃጢአቴ እንድታርቀኝ እወዳለሁ ፡ ጌታ ሆይ ፦ ሃይልህን እንድትሰጠኝ እፈልጋለሁ”በሉት፡፡ እመኑኝ የምወዳችሁ ልጆቼ ፦ ትክክለኛዋን ፀሎት ያወቃት እርሱ ትክክለኛዋንም ንስሃን የሚያውቅ እርሱ ነው ፤ ማር ይስሃቅ እንደተናገረው “ንስሃ ከፀሎት ውጭ እንደሚገኝ የሚያስብ ሰው እርሱ በዲያቢሎስ የተታለለ ነው” ምክንያቱም በፀሎት ወደ እግዚአብሄር የምትመለሱበትን ሃይልን ታገኛላችሁና፡፡ ስለሆነም ከየትኛውም ስራ ይልቅ ራሳችሁን ለፀሎት አስገድዱ ፤ ምክንያቱም በፀሎት አማካኝነት በእናንተና በእግዚአብሄር መካከል ያለውን ግድግዳ አስወግዳችሁ እንደገና ወደእርሱ ትመለሱ ዘንድ ይቻላችኅልና ፤ በጣም ብዙ ሰወች ከፀሎት ይልቅ ለአገልግሎት መትጋታቸው የሚገርም ነው ወይንም ከፀሎት ይልቅ በንባብ የሚተጉትም እንደዚያው ወይንም ከፀሎት ይልቅ በተመስጦ የሚተጉትም እንደዚያው ወይንም ከፀሎት ይልቅ በመንፈሳዊ ስብሰባወች ለመታደም የሚተጉትም እንደዚያው ፤ ለዚህ እኮ ነው ከእግዚአብሄር ጋር ባላቸው ግንኙነት የማይሳካላቸው ፤ ይፀልያሉ ያነባሉ ደግሞም ስብሰባወችን ይታደማሉ በዚህ ሁሉ ሰአት ከእግዚአብሄር ጋር ምንም ግንኙነት የላቸውም ፤ ምንም አይነት ግንኙነት ፡፡ ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ ፤ ወደእግዚአብሄር ተመለሱና ከእርሱ ውሰዱ  ስለዚህ ልጆቼ  ወደ እግዚአብሔር ተመለሱ" join👇 ╔═════════════╗ @Kidus_Michaelabate_12 ╚═════════════╝    ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ ✨💫#sʜᴀʀᴇ & #ʟɪᴋᴇ💫

  • 14 авг.1 40263

    🛐🛐 🛐🛐ዓለም ዓቀፍ የቤተክርስቲያን ታሪክ 📖📖                     ክፍል ፲፰ [18] ⛪ የቤተክርስቲያን ታሪክ በዘመነ ሐዋርያት ➡️ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ ቅዱስ ጴጥሮስ በገሊላ ባሕር ዳር በምትገኘው በቤተሳይዳ ተወለደ። የአባቱ ስም ዮና ይባላል። ከአምስት ዓመቱ ጀምሮ ያደገው በቅፍርናሆም ከተማ ሲሆን በጐልማሳነቱ ከወንድሙ ከእንድርያስ ጋር በገሊላ ባሕር ዓሣ ማሥገር ጀመረ። ለደቀመዝሙርነት…

  • 14 авг.1 16972

    እርሱ ያልበደለ ሳለ የኛን በደል ተሸክሞ ሲሞት እኛ ግን የገዛ ጥፋታችንን ማመን ተስኖናል። እርሱ ለጠላቶቹ ይቅርታ ሲለምን እኛ ግን ወዳጆቻችንን መውደድ አቅቶናል። የእኛ ፍቅር እንደ ጠዋት ጤዛ ሲረግፍ የእርሱ ፍቅር ግን እንደ ጸኑ ተራሮች ዛሬም ቀና ሲባል የሚታይ ነው። ብዙ ወዳጆች ቀየርን፤ እግዚአብሔርን ግን የሚተካ አላገኘንም። ብዙ ደጆች ደርስን ስንመለስ ተዘጉ፤ እግዚአብሔር ግን በእኛ ላይ በሩን አልዘጋም። በብዕር ፍቅሩን የሚገልጥልን ወዳጅ አጥተናል፣ በደም ነጠብጣብ እወዳችኃለሁ የሚለንን ውድ ግን አግኝተናል። <<ጌታ ሆይ ምን ያህል ትወደኛለህ?>> ብንለው። የእሾህ አክሊል የደፋውን ራስ፣ ችንካር የነደላቸውን እጆች፣ በጦር የታመሰውን ጎኑን፣ ያሳየናል። እኛስ እንወደዋለን? መልሱ ለእናንተው ይሁን      join👇 ╔═════════════╗ @Kidus_Michaelabate_12 ╚═════════════╝    ♡ ㅤ    ❍ㅤ     ⎙ㅤ   ⌲               ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ   ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ ✨💫#sʜᴀʀᴇ & #ʟɪᴋᴇ💫

  • 14 авг.1 225106

    ​📖📖 ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፰/8 🤩በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ​📌በዚች ቀን ከመምህራነ ኦሪትና ከሊቃነ ካህናት አንዱ የሆነው አረጋዊው አልዓዛር፣ ሚስቱ ሰሎሜ እና ፯ቱ (7) ልጆቻቸው (አንኤም፣ አንጦኒኃስ፣ ዖዝያ፣ አልዓዛር፣ አስዮና፣ ስሙና፣ መርካሎስ) በሰማዕትነት አረፉ። ​📌አረጋዊው አልዓዛር ሕዝቡን በፈሪሃ እግዚአብሔር ያስተዳድር ነበር። ነገር ግን ከዘመዶቹ ወገን የሆኑ ፫ (3) ካህናት (ስምዖን፣ አልፍሞስ፣ መባልስ) በሹመቱ ቀንተው በሙሴና አሮን ላይ እንደተነሱት ዳታንና አቤሮን ተነሱበት። ሕዝቡ ግን የአልዓዛር ሹመት ከእግዚአብሔር እንጂ ከሰው አይደለም ብለው ከለከሏቸው። ​📌እነዚህም ቀናተኞች ወደ ግሪክ ንጉሥ ወደ አንጥያኮስ ሄደው አነሳሱት፤ መጥቶም የኢየሩሳሌምን መንግሥት እንዲወስድ በተንኮል አገሩን አስረከቡት። ​📌ንጉሥ አንጥያኮስም በገባ ጊዜ ሊቀ ካህናቱን አልዓዛርን ይዞ የእሪያ (የእርያ) መስዋዕት እንዲሰውር አዘዘው፤ ቅዱስ አልዓዛር እምቢ ባለው ጊዜ ፯ቱን (7) ልጆቹን ገደላቸው። እርሱንና ባለቤቱ ሰሎሜንም በእሳት ባጋሉት የብረት ምጣድ ላይ አስተኝተው ገደሏቸው፤ በዚህም ሰማዕትነታቸውን ፈጸሙ። ​"ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የእነዚህ ቅዱሳን በረከታቸው ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።" ​ ምንጭ፦📖📖#መጽሐፈ_ስንክሳር ​"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" (የቅዱሳንን ዜና/ታሪክ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል) ✍️አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር📖)  📱ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄🌐 ╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮    @Kidus_Michaelabate_12 ╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯ ​📌ስመ እግዚአብሔርንና የኦሪትን ህግ ላለማፈር ከነቤተሰባቸው ለሰማዕትነት የበቁትን የአረጋዊው አልዓዛርንና የቅድስት ሰሎሜን ገድል Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ❕

  • 13 авг.33удалён 14 авг.

    ዉዳሴ ማርያም ትርጓሜ እና ቅዳሴ ማርያም  ትርጓሜ ተጀምሯል ቮይስ ቻት ግቡ🙏 ሼርርር እያደረጋችሁ የእመቤታችን የበረከቷ ተካፋይ ይሁኑ❕😍🙏 ተጀምሯል ቮይስ ቻት ከታች ባለው ሊንክ ግቡ👇👇👇 https://t.me/Kidus_Michaelabate_12?livestream=734416c83093913917 https://t.me/Bete_kidus_Michael_12

  • 13 авг.2 21038

    🛐🛐 🛐🛐ዓለም ዓቀፍ የቤተክርስቲያን ታሪክ 📖📖                     ክፍል ፲፯ [17] ⛪የቤተክርስቲያን ታሪክ በዘመነ ሐዋርያት ዘመነ ሐዋርያት ብለን የምንጠራው ዘመን በበዓለ ሃምሳ መንፈስ ቅዱስ ለመቶ ሀያው (120) ቤተሰብ ከወረደ ጀምሮ -100 ዓ.ም ያለው ጊዜ ነው። ሐዋርያት በሁሉም አቅጣጫ ወንጌልን በመስበክ ጨለማው ዓለም ብርሃን የሆነበት፣ አልጫው የጣፈጠበት ፣የክርስቶስ አምላክነት…

  • 13 авг.1 620811

    🤩ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን የቀጠለ...❕     🤩ቤተክርስቲያን ከመሠረቷ እስከ ጉልላቷ ትርጉሟና ምሳሌዋ🤩                  ክፍል ፲፫ (13) ✍️አዕማድ /የምሰሶዎች/ ➡️ቤተክርስቲያን ሲሰራ ትላልቅና ትናንሽ ምሰሶዎች ይኖሩታል ትላልቆቹ የሐዋርያት ትንንሾቹ ደግሞ የአርድዕት ምሳሌ ናቸው፡፡ የምዕመናንን ልቦና በወንጌል ላይ በመመስረታቸው ነው። ➡️አዕማድ በወንጌል ይመሰላሉ፡፡ አማናዊቷ ቤተክርስቲያን…

  • 13 авг.2 0052110

    ​📖📖 ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፯/7 🤩በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ​📌 በዚች ቀን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ወደ ጻድቁ ኢያቄም ተልኮ የእመቤታችን የድንግል ማርያምን ፅንስ ያበሠረበትና ቅድስት ሐና የፀነሰችበት ቀን ነው። እንዲሁም የሐዋርያት አለቃ ቅዱስ ጴጥሮስ "አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ" ብሎ የመሰከረበት መታሰቢያ በዓል ነው። ​📌ጻድቁ ኢያቄምና ባለቤቱ ቅድስት ሐና ልጅ አጥተው በስደትና በጽኑ ጸሎት ይኖሩ ነበር፤ ልጅ ቢሰጣቸውም ለእግዚአብሔር ቤት አገልጋይ ሊያደርጉ ተሳሉ። ቅዱስ ገብርኤልም ለኢያቄም ተገልጦ የዓለም ሁሉ መመኪያ የምትሆን፣ ለዓለም ድኅነትን የምታመጣ ሴት ልጅ እንደሚያገኙ አበሠረው። ቅድስት ሐናም በዚች ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችንን ፀነሰች። ​📌በዚችም ቀን ጌታችን በፊልጶስ ቂሣርያ ደቀ መዛሙርቱን "ሰዎች የሰውን ልጅ ማን ይሉታል?" ብሎ በጠየቃቸው ጊዜ፣ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ "አንተ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ክርስቶስ ነህ" ብሎ መሰከረ። ​📌ጌታችንም የቅዱስ ጴጥሮስን ሃይማኖት አድንቆ የመንግሥተ ሰማያትን ቁልፍ ሰጠው፤ የሐዋርያት ሁሉ አለቃና የቤተ ክርስቲያን መሠረት አደረገው። ከእርሱም የክህነትና የሹመት ሁሉ መሠረት ተተከለ። ​"ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በከበሩ ኢያቄምና ሐና፣ በሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስም ጸሎት ይማረን፤ በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።" ​ ምንጭ፦📖📖#መጽሐፈ_ስንክሳር ​"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" (የቅዱሳንን ዜና/ታሪክ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል) ✍️አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር📖)  📱ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄🌐 ╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮    @Kidus_Michaelabate_12 ╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯ ​📌የእመቤታችንን የፅንሷን ብስራትና የታላቁን ሐዋርያ የቅዱስ ጴጥሮስን የእምነት ምስክርነት ታሪክ Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ❕

  • 12 авг.1 638910

    🛐🛐 🛐🛐ዓለም ዓቀፍ የቤተክርስቲያን ታሪክ 📖                     ክፍል ፲፮ [16] 🛐 🛐የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ስደትና ውጤቱ ባለፈው ክፍል እንደተመለከትነው በሐዋርያት ትምህርት ባመኑት ምዕመናን መካከል የተፈጠረውን ክፍተት ለማስተካከል ሰባት ዲያቆናት እንደተመረጡና ከእነርሱም መካከል አንዱ ቅዱስ እስጢፋኖስ እንደሆነ ተመልክተናል። ቅዱስ እስጢፋኖስ በፍጹም እምነት የጠነከረና…

  • 12 авг.1 511155

    እናታችን ቅድስት አርሴማ ናት 👰"ውበት ሐሰት ነው፤ ደም ግባትም ከንቱ ነው እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርሷ ትመሰገናለች" ምሳሌ📖 30፥31። "ቅድስት አርሴማ" እግዚአብሔርን የምትፈራ በቅዱሳን ሰማዕታት ማህበርና በገነት በሮች የሕይወት ፍሬ ያፈራች ሰማዕት ናት። 🛐የምድር ሀብት ጌጥ ብሎም የንጉሥ ሚስት ንግሥት መባልን ሁሉ እንቢ ብላ ለምድርም ለሰማይም ንጉሡ ለሆነው ለ ክርስቶስ የተሞሸረች ስለ እርሱም በነፍሷ መከራን የተቀበለች ብፅዕት ሰማዕት ናት "በብዙ መከራና ስቃይ የእግዚአብሔርን መንግሥት ልንገባ ይገባናል" እንዳለ መጽሐፍ.ቅዱስ ዮሐ.ሥራ.📖 14፥22) ቅድስት አርሴማም የመከራውን ሸክም የእሳቱን ዋዕይ ታገሠች። ስለዚህም መንግሥተ ሰማያትን ወረሰች። እርሷ ከ ድንግል ማርያም በታች ከሴቶች ልጆች ትበልጣለችና በዚህች ቅድስት ሰማዕት አርሴማ ጸሎት የሚታመን ብፁዕ ነው። መታሰቢያዋንም በዕጣንና በመሥዋዕት የሚያደርግ ብፁዕ ነው። ስለ ቅድስት አርሴማ እንጀራንና ጽዋ ውኅ ለድሃ የሚሰጥ ብፁዕ ነው። በዚህ ዓለም በሥጋው መዳንን ዕጥፍ ድርብ ያገኛል። በሚመጣው ዓለም መልካም ዋጋንና የማያልፍ ሕይወትን ፈጽሞ ያገኛል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በወንጌል ቃል=> "በነቢይ ስም ነቢይን የሚቀበል የነቢይን ዋጋ ያገኛል በጻድቅ ስም ጻድቅን የሚቀበል የጻዲቁን ዋጋ ያገኛል፤ በስሜና በደቀመዝሙሬ ስም ከታናናሾች ለአንዱ ቀዝቃዛ ጽዋ ውኅ ያጠጣ እውነት እላችኃለሁ በሰማያት ዋጋውን አያጣም" ብሏልና። (ማቴ 📖10፥40-42)። የእናታችን ቅድስት አርሴማ ባረከቷ ይደርብን ። አሜን።3 ☦️አርሴማ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት ሞገስ አግኝተሻል በክርስቶስ🛐☦️      ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄 ╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮    @Kidus_Michaelabate_12 ╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯

  • 12 авг.1 592114

    ​📖📖 ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፮/6 🤩በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ​📌በዚች ቀን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፯ (7) አጋንንትን ያወጣላትና ከሐዋርያት ጋር ወንጌልን የሰበከችው የከበረች ቅድስት መግደላዊት ማርያም አረፈች። ​📌ይህች ቅድስት ጌታችንን ተከትላ ያገለገለችው ሲሆን፣ በመከራውም ጊዜ እስከ መቃብሩ ድረስ አልተለየችውም። በእሑድ ሰንበት ማለዳ ገና ጨለማ ሳለ ወደ መቃብሩ በመገሥገሥ የጌታችንን ትንሣኤ የመጀመሪያ አበሣሪ ለመሆን በቅታለች። ​📌ጌታችንም ከተነሣ በኋላ ለእርሷ ተገልጾ "ሄደሽ ለወንድሞቼ 'ወደ አባቴና ወደ አባታችሁ፡ ወደ አምላኬና ወደ አምላካችሁ አርጋለሁ' ብለሽ ንገሪያቸው" ብሎ አዘዛት፤ እርሷም ወደ ሐዋርያት ሄዳ ትንሣኤውን አበሠረች። ​📌ከጌታችን ዕርገት በኋላ ሐዋርያትን እያገለገለች ኖረች፤ በ፭ኛው (50) ቀን መንፈስ ቅዱስ በወረደ ጊዜም ከሐዋርያት ጋር ተቀበለችው። ​📌ከዚህ በኋላ ከሐዋርያት ጋር ወንጌልን እየሰበከች ብዙዎችን ወደ ክርስቶስ ሃይማኖት መለሰች፤ ሐዋርያትም ሴቶችን እንድታስተምር ዲያቆናዊት አድርገው ሾሟት። ከአይሁድም ብዙ መከራ፣ ግራፍና እንግልት ቢደርስባትም ተጋድሎዋን ፈጽማ በሰላም አረፈች። ​"ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም የክርስቲያን ወገኖችን ሁሉ በጸሎቷ ይማረን ለዘላለሙ አሜን።" ​ ምንጭ፦📖📖#መጽሐፈ_ስንክሳር ​"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" (የቅዱሳንን ዜና/ታሪክ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል) ✍️አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር📖)  📱ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄🌐 ╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮    @Kidus_Michaelabate_12 ╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯ ​📌የጌታችንን ትንሣኤ ለመጀመሪያ ጊዜ ያበሠረችውንና ከሐዋርያት ጋር ወንጌልን ያስተማረችውን የቅድስት መግደላዊት ማርያምን ታሪክ Share በማድረግ የበረከቷ ተካፋይ ይሁኑ❕

  • 🛐የቤተክርስቲያን ከመሠረቷ እስከ ጉልላቷ ያለው  ትርጉምና ምሳሌ                  ክፍል ፲፪(12) በቀጣዩ ክፍል ቤተ ክርስቲያን ከመሠረቷ እስከ ጉልላቷ ያላትን ትርጉምና ምሳሌ እንመለከታለን። ➡️በመጀመሪያ ሕንፃ ቤተክርስቲያን በአዳም ትመሰላለች ይኸውም አዳም የሰው ዘር ሁሉ መጀመሪያ አስገኝ እንደሆነ ቤተክርስቲያንም የድኅነት ሥጢራት ሁሉ መገኛ ናትና፡፡ ➡️በመንግስተ ሰማያት ትመስላለች…

  • 11 авг.1 91253

    🛐🛐 🛐🛐ዓለም ዓቀፍ የቤተክርስቲያን ታሪክ 📖                     ክፍል ፲፮ [16] 🛐 🛐የመጀመሪያው የቤተክርስቲያን ስደትና ውጤቱ ባለፈው ክፍል እንደተመለከትነው በሐዋርያት ትምህርት ባመኑት ምዕመናን መካከል የተፈጠረውን ክፍተት ለማስተካከል ሰባት ዲያቆናት እንደተመረጡና ከእነርሱም መካከል አንዱ ቅዱስ እስጢፋኖስ እንደሆነ ተመልክተናል። ቅዱስ እስጢፋኖስ በፍጹም እምነት የጠነከረና ታምር የማድረግ ጸጋ የነበረው ነው። ከተሰጠው ሥራም በተጨማሪ ጊዜ ባጋጠመው ቍጥር በየምኵራቡ እየዞረ ለአይሁድ ዓለምን ለማዳን ስለመጣው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ከብሉይ ኪዳን እየጠቀሰ ያስተምራቸው ነበር ። እሱም የሚናገረው በመንፈስ ቅዱስ እየተመራ ስለ ነበር በመቃወም ይከራከሩት የነበሩትን መልስ ስላሳጣቸው በቅናት መንፈስ በመመራት እሱን ለማጥፋት “ይህ ሰው ኦሪትንና ቤተ መቅደስን ይነቅፋል ፤ በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም ፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ቤተመቅደስ ያፈርሰዋል ፤ ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋል” ብለው የሚመሰክሩ የሐሰት ምስክሮች አስነሥተው ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ይዘው ወደሸንጎ አቀረቡት።  (የሐዋ. 6፡13-14)   በዚያን ጊዜ የእስጢፋኖስ ፊት እንደ መልአክ ፊት ያበራ ነቀር። የካህናት አለቃው መልስ እንዲሰጥ ቢጠይቀው ስለተከሰሰበት በመመለስ ፈንታ አይሁድ ከጥንት ጀምረው እግዚአብሔርን በመቃወም ስለሚያደርጉት መጥፎ ሥራ የተሰማውን ኃዘን በመግለጽ ከአብርሃም ዘመን ጀምሮ እስከ መድኃኒታችን ኢየሱስ ድረስ ያለውን የቅዱሳት መጻሕፍትን ጽሑፍ በሚገባ ተረከላቸው። አይሁድ በእግዚአብሔር የሰጣቸውን ሕገ ኦሪትን ትተው ሞሎክ የተባለውን ጣዖት ማምለካቸውንና ጌታንም በግፍ እንደሰቀሉ ገልጾ ነገራቸው። አይሁድ ግን የእስጢፋኖስን ንግግር ከሰሙ በኋላ  እነዚህን ንግግሮች በእግዚአብሔር ላይ እንደተሰነዘሩ ስድቦች በመቍጠር ያለፍርድ ቤት ውሳኔ ዘለው ያዙት ። ከከተማም አውጥተው በድንጋይ ወግረው ገደሉት። ደጋግ የሆኑ ክርስቲያኖች በድኑን ወስደው እንባ በእንባ እየተራጩ ቀብረውታል። ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም በስሙ ቤተ ክርስቲያን አሳንፃ በዓሉን ጥር 1 ቀን ታከብራለች " በዚያን ጊዜ አይሁድ ክርስትናን እናጠፋለን ብለው ባነሡት ስደት ምክንያት ከሐዋርያት በስተቀር ወደ ሰማርያ ፣ ፊኒቅያ ፣ ቆጵሮስና ሶርያ (አንጾኪያ)ና ሌሎች ሀገራት ተሰደዱ። የተሰደዱት ክርስቲያኖችም ሁሉ በየሄዱበት ሀገር ስላስተማሩ ይህ ስደት ክርስቲያኖችን በማጥፋት ፈንታ ለክርስትና መስፋፋት በጣም ጠቃሚ ሆነ። ይቀጥላል...❕   ​📱ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄🌐 ╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮    @Kidus_Michaelabate_12 ╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯

  • 11 авг.2 01455

    ☦️የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታሪክ ባጭሩ አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች፡፡ በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ፡፡ ☦️አባታችን ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል። በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ፡፡ አባታችን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል፡፡ መላእክት በአክናፈ እሳት ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል፡፡ ለፅንሰትከ ፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በብሥራተ መልአክ ለተፀነስነከው መፀነስና በወርኃ ታኀሣሥ ለተወለድከው ልደትህ ሰላም እላለሁ። ክቡሩ አባት ሆይ ስለ ዓለሙ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጌትነቱ ልደት ተርሴስ ግብር እንደገበረ፤እኔም ፍጹም ልባዊ የእጅ መንሻ ወርቅ አቀርብልሃለሁ። ለተኃፅኖትከ፥ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የቤተ ክርስቲያን መብራት የምትሆን የተመረጠች የክብርት እናትህን ጡት ባለመጥባት በመንፈስ ቅዱስ እንክብካቤ ስለ አደግኸው አስተዳደግህ ሰላም እላለሁ።

  • 11 авг.1 56784

    ​📖📖 ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፭/5 🤩በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ​📌በዚች ቀን በከሀዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ዘመን በሠራዊት ውስጥ እያለ በምሥጢር ክርስቲያኖችን ይረዳ የነበረው ታላቁ ተጋዳይ ቅዱስ ዮሐንስ ወታደር አረፈ። ​📌የዚህ ቅዱስ ወላጆቹ ክርስቲያኖች ነበሩ፤ እርሱም በከሀዲው ንጉሥ ዑልያኖስ ሠራዊት ውስጥ ወታደር ሆኖ ያገለግል ነበር። ንጉሡም ክርስቲያኖችን ያሠቃዩ ዘንድ ከባልንጀሮቹ ወታደሮች ጋር በላከው ጊዜ፣ እርሱ ለባልንጀሮቹ ክርስቲያኖችን የሚጠላ ይመስል ነበር። ​📌ነገር ግን በምሥጢር (በስውር) ወደ ክርስቲያኖቹ ገብቶ የሚያስፈልጋቸውን በጎ ነገር ሁሉ ይሰጣቸው፣ በመከራቸውም ያጽናናቸው ነበር። ​📌ሁልጊዜም በጸሎት፣ በጾምና በመጽዋት ተጠምዶ የቅዱሳንን አኗኗር ሲኖር ቆይቶ፣ ምስጉን አምላኩን እግዚአብሔርን በቅንነት አገልግሎ በሰላም አረፈ። ​"ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱሱ ጸሎት ይማረን፤ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።" ​ ምንጭ፦📖📖#መጽሐፈ_ስንክሳር ​"ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን" (የቅዱሳንን ዜና/ታሪክ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል) ✍️አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (መጽሐፈ ምሥጢር📖)    ​📱ሼር // 𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄🌐 ╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮    @Kidus_Michaelabate_12 ╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯ ​📌በወታደርነት አገልግሎቱ ውስጥ ሆኖ በምሥጢር ምዕመናንን ያጽናና የነበረውን የታላቁን ተጋዳይ የቅዱስ ዮሐንስን ታሪክ Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ❕

  • 10 авг.1 85351

    🛐🛐 🛐🛐ዓለም ዓቀፍ የቤተክርስቲያን ታሪክ📖📖                     ክፍል ፲፬ [14] ⛪የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች የአንድነት ኑሮ በኢየሩሳሌምና በአካባቢዋ ይኖሩ የነበሩት የመጀመሪያዎቹ የክርስቶስ አማኞች በመጀመሪያ ጊዜ ከአይሁድ ኅብረተሰብ በአምልኮም ሆነ በማኅበራዊ ኑሮ ጨርሰውም አልተለዩም ነበር፡፡ በአምልኮ ሰዓት ጊዜ ግን ወስነው በኢየሩሳሌሙ ኤጲስቆጶስ በያዕቆብ በማርቆስ እናት በማርያም…

  • 10 авг.1 84099

    በኢየሩሳሌም ራቁቴን ሰቀሉኝ፣ አሁን ደግሞ አንተ ድጋሚ በሮም ራቁቴን ትሰቅለኝን?›› ብሎ ተናገረው፡፡ ዮሐንስም እጅግ ደንግጦ ‹‹እንዴት አድርጌ ልሳልህ?›› ብሎ የሳለውን ሥዕል ቢጠይቀው ሥዕሉም ‹‹ከለሜዳ አልብሰህ ሳለኝ›› አለው፡፡ ዮሐንስም እንዳለው ከለሜዳ አልብሶ ከሳለው በኋላ ሥዕሉን ትኩር ብሎ ተመልክቶ ቢስመው ከንፈሩ አንድ ቀን ተኩል ያህል ተጣብቆ ቆይቷል፡፡ ዛሬም ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የምትጠቀምባቸውን የጌታችንን ስነ ስቅለት የሚያሳዩ ሥዕሎች መገኛቸው ይህ ወንጌላዊው ዮሐንስ የሳለው ሥዕል ነው፡፡ ✨ቅዱስ ዮሐንስ በተለያዩ ስሞች ይጠራል፡፡ በሕይወቱና በኑሮው ሁሉ ጌታችንን ለመምሰል ይጥር ነበርና ጌታችንም እጅግ ይወደው ስለነበር ‹‹ፍቁረ እግዚእ›› ተባለ፡፡ የታላቁ ያዕቆብ ታናሽ ወንድም ስለሆነና አባቱም ዘብድዮስ ስለሚባል ‹‹ዮሐንስ ወልደ ዘብድዮስ›› ተባለ፡፡ ለጌታችን ባለው ቅናትና ከወንድሙ ጋር ሆነው ባሳዩት የኃይል ሥራ እንዲሁም የጌታችንን አምላክነት በመግለጡ ‹‹ወልደ ነጎድጓድ›› ተብሏል፡፡ ነገረ መለኮትን ከሌሎቹ በበለጠ ሁኔታ አስፍቶና አምልቶ በማስተማሩ ‹‹ነባቤ መነኮት ወይም ታኦሎጎስ›› ተብሏል፡፡ ኃላፊውንና መጻዒውን ጊዜ በራእዩ ስለገለጠ ‹‹አቡቀለምሲስ›› ተባለ፣ ይህም በግሪክኛ ባለራእይ ማለት ነው፡፡ የጌታችንን መከራ መስቀሉን እያስታወሰ 70 ዘመን ሙሉ እያለቀሰ ስለኖረና ፊቱም በሀዘን ስለተቋጠረ ‹‹ቁዱረ ገጽ›› ተብሏል፡፡ ረድኤት በረከቱ ይደርብን፣ በጸሎቱ ይማረን፡፡ (ምንጭ፡- ስንክሳር ዘወርሃ ጥር፣ ቤተ ክርስቲያንህን ዕወቅ፣ የቅዱሳን ታሪክ-30) ሼር //𝐒𝐇𝐀𝐑𝐄 ╭══✧•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ✧══╮     @Kidus_Michaelabate_12 ╰══✧•ೋ•✧๑♡๑✧• ✧══╯          #pray🙏#share