- Последний пост
- 15 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 234
- 1/48двое суток
- 268
- 1/72трое суток
- 289
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የፍቅርን ጌታ ማፍቀር አፍቃሪው መቼም የማይደክምበትና እድለቢስ የማይሆንበት ፍቅር ነው 🩶🤎; Te » @Yetsfa_Gexoch1
ለይል መነሳት ከበደኝ ብሎ የኳስ ጨዋታው ግን ከሌሊቱ 7/8 ሰአት ላይ ነው ሲባል ግን አይኑም አካሉም ሀይ ሆኖ ስትመለከተው ጉዳዩ የቀልብ(የኢማን) መሞት እንጂ ድካም እንዳልሆነ ትረዳለህ_|والعياذ بالله|_ ቻናል:-@Lebenfelega
без подписи
በአላህ ይሁንብኝ! ሰዎች የውስጤን መጥፎነት (ድብቅ ጥፋቴን/ወንጀሌን) ቢያውቁ ኖሮ፣ የሚያገኘኝ ሁሉ በእኔ ላይ ሰላምታ መስጠትን እምቢ ይል ነበር። ከእኔም ፊታቸውን ያዞሩ፣ አብሮነቴንም ይሰለቹ ነበር፤ ነገር ግን የላቀው የአላህ ደባቂነት (ሲትር) ጥፋቴንና አመፄን ሸፈነልኝ። Abul_atahiya🤍❤️🩹: ቻናል:-@Lebenfelega
ሰላም ለዛች ቀልብ: ተስፋና ምኞትዋን በሙሉ ምንም በማያቅተው ጌታዋ الله ላይ ላንጠለጠለች. 🤎 ሰላምሽ ይብዛልኝ 🩶🤎: ቻናልl:-@Lebenfelega:
ما هو اليقين؟¿? "እርግጠኝነት ብሎ ማለት:አንተ ልታውቅ ነው ጌታህ الله በሁሉም ነገር ላይ ቻይ መሆኑ በል እንደውም በዙርያህ ያለው ሁሉ ለነገርህ አለመሳካት ሰበብ እንኳን ቢሆን እና ነገራቶች ቢዘጋጉ ጌታህ ምንም እንደማያቅተውና ሁሉንም ነገር ማድረግ እንደሚችል ልታረጋግጥ እርግጠኛ ልትሆን ነው ከብዙ መልካም ስራዎችህ ጋር_! لأنه هو الله_فهذا هو اليقين🩶🤎:
እንዴት ትጨነቃለህ በጌታህ መስተዳድር ውስጥ ሆነህ አንተ ብቻ ወደ ጌታህ ተመለስ ሁሉም ነገር ወዳንተ ሲመለስና፣ሲስተካከል ታየዋለህ! 🩷:عندما يكتمل الأمر بإذن الله، سيعود كل شيء كما شاء
⚡️ጣዉስ እንዲህ ብለዋል፦ «ከሰዎች ሁሉ ቁርአን አቀራሩ የላቀው (በጣም ያማረው)፣ ሲቀራ በሰማኸው ጊዜ አላህን የሚፈራ መስሎ የተሰማህ ሰው ነው።» (ተህዚቡል ከማል፣ 13/452)
ابن عساكر في تاريخه بسنده قال صلى الله عليه وآله وسلم «በዕለተ ቂያማ (በተውላደ መቃብር/በትንሣኤ ቀን) ከሰው ሁሉ ይበልጥ በጽኑ ቊጭትና ጸጸት የሚቃጠለው፦ በዱንያ (በምድራዊ ሕይወቱ) እውቀትን የመቅሰም ሰፊ ዕድልና አቅም ኖሮት ሳይማር የቀረና ዕድሉ ያመለጠው ሰው ነው።
አሁን በ28 ዓመቱ ካገባ ምነው ቸኮልክሳ በሰላም ነው? ይባላል። ታላቅህን አስቀምጠህ ወዴት ነው? ካፒታሊዝሙ ይህን ታላቅ ዒባዳ እያራቆተን ነው። ጋብቻ እየተመናመነ ...በኑሮ ውጣውረድ የደካከመ ጎልማሳ ብቻ ነው ወደ ጋብቻ ብቅ እያለ ያለው።
"አንድ ሰው ለወንድሙ እንዲህ ሲል ጻፈለት፦ ከዚህ በመቀጠል፤ «ዱንያ (የዚህች ዓለም ሕይወት) እንደ ሕልም ናት፣ አኺራ (የመጨረሻው ዓለም) ደግሞ የንቃት ዓለም ነው፤ ሞት ደግሞ በሁለቱ መካከል ያለ ድልድይ ነው። እኛ ያለነው ግን በተደበላለቁ ሕልሞች ውስጥ ነው። ወስሰላም (ሰላም ላንተ ይሁን)።'" — ምንጭ፦ ኢግቲናሙል አውቃት (59) 📱https://t.me/abdurezaq27
➖ይበልጥ ሊያሳስብና ሊያስለቅስ የሚገባው የወንጀል መደራረብና የስህተት መበራከት ሳይሆን፣ ጥፋትን ተላምዶ በቸልተኝነት መሳቅና የልብ መደንዘዝ ነው። ደጋግ ቀደምቶች በተቅዋና በንጽህና ማማ ላይ ሆነውም እንኳ ከፈጣሪ ፍርሃትና ክብር የተነሳ እንባቸው ይፈስ ነበር፤ ዛሬ ግን በወንጀል ባህር ውስጥ እየዋኙ በፈገግታ መኖር እራሱ በትልቅ የጸጸት እንባ ሊታጠብ የሚገባው የመንፈስ መክሰም ነው። 🎯ከኢብኑ ረጀብ ብዕር ➖صباح الخير ➖ 📱https://t.me/abdurezaq27
የሆነ ቀን ትሞታለህ❗️ ከዚያም እንዳልነበርክ ተደርገህ ትረሳለህና: ምናልባት ካስታወሱህ መልካም ሰው ነበር الله ይዘንለትና ብለው ዱዓእ እንዲያደርጉልህ ብሎም ደግሞ ጌታህ መቼም እንዳይረሳህና አንተ እንኳን ረስተከው ጌታህ አስታውሶ የሚከፍልህን ስራ ሰርተህ እለፍ። ትርጉምም ለዛም የሌለውን ህይወት አትኑር ጌታህን በመፍራት በዒባዳህ ያሸበረቀ ህይወትን ኑር🤎🩶:
ለሱ ብቻ🫀🤍:
የዱንያ ፍቅር በልብ ውስጥ ቦታ ካገኘ: የትኛውም የገንዘብ ክምችት የትዳር ጥማትን አያረካውም። ⚠️❗️
"من عيَّر أخاه بذنبٍ لم يمت حتى يعمله." "ወንድሙን በኃጢአት የሚያዋርድ ሰው ራሱ ያንን ኃጢአት ሳይሠራ አይሞትም።" ❤️🔥🔥 imamu malik🤍:
ረቂብ(ተከታታይ): የሆነ ጌታ የሌለን ይመስል . . .❗️
Over thinking kill ur happiness. 🔥❤️🔥:
ለእህታችን .... ከንፈር ከመምጠጥና "እምፅ" ከሚል የስሜት ማስታገሻ ባለፈ፣ የዚህ ትውልዳዊ ሰቆቃ ህያው መፍትሔ እንድትሆኚ ..... ትዳርን ቀለል አድርጊው። እስኪ ከልብሽ እውነተኛ ሁኚ፤ ያ የገዛ ወንድምሽ በኑሮ አዘቅት ውስጥ እየዳከረ፣ የራሱን ጎጆ ለመቀለስ ሲያልብ፣ ሲደክምና ህልሙ ሲጨነግፍ አንጀትን እንደሚበላው ሁሉ፤ ያንቺም ደጅ ላይ በፍቅርና በተስፋ የቆመው፣ በኑሮ ጦርነት እየደማ የሚፈጨረጨረው የሌላው ምስኪን ወንድም ነው። ለገዛ ወንድምሽ የምትመኚውን ርህራሄና ቅንነት ለዚህኛውም አትንፈጊው። አፓርታማ ካልተከራየ፣ ዘመናዊ መኪና ካላቆመ፣ ከተማውን የሚያናውጥ ሰርግና የወርቅ ጌጥ ካልደገሰ እያልሽ በማይጨበጥ የቁሳቁስ ምናብ ራስሽን አትሰሪ። "ሁሉን ያሟላ፣ ያለቀለትና የተንደላቀቀ ህይወት ይዞ ካልመጣ አልገባም" ብለሽ ስትቆዝሚ፣ ርህራሄ የሌለው የጊዜ ባቡር ውድ የሆነውን የመውለድ፣ የመክበድና የማፍራት የተፈጥሮ ፀጋሽን ይዞብሽ ይነጉዳል። ትዳር የነፍሳት ውህደት እንጂ የባንክ ሂሳብ ስምምነት አይደለም። የኢኮኖሚው ገበያ መመሰቃቀል፣ የወጣቱ አቅም መነጠቅና የኑሮው አረመኔነት እያስታወቀሽ፣ በተንደላቀቀ ዝግጁ ህይወት ላይ ለመውጣት ብቻሽን አትባክኚ። ገንዘብ ያለውን መጠጥ ያለ ጎልማሳ በመፈለግ በየቦታው መሽቀርቀርና መሰቃየት ይብቃሽ። ቤተሰቤን የሚረዳ፣ ፋይናንሻሊ ስቴብል የሆነ .....ቅብርጥሴ እያልሽ የትዳር አጋር ሳይሆን ያለ ኮላተራል የባንክ ብድር የሚፈልግ የተወዛገ ነጋዴ ይመስል የገንዘብ ጥማትሽን ለብፁሃን መዘባበቻ አታድርጊው። የተዘጋጀ ድግስ ላይ ከመታደም፣ አብሮ በማብሰል ውስጥ ታላቅ የህይወት ትርጉም አለ። ጉልበትና ጊዜ ባለሽ አፍላ ዕድሜሽ፣ ጥፍርሽን ከጥፍሩ አጋምደሽ አብረሽው ለመስራት ተፍጨርጨሪ። ላብና ወዛችሁ ያልፈሰሰበት የተንደላቀቀ ቪላ ውስጥ ገብቶ የባለቤትነት ስሜት ከማጣት፣ አብራችሁ አፈር ፈጭታችሁ በምትገነቡት ህይወት ውስጥ የማይናወጥ የፍቅር ምሽግ አለ። ተባበሩ፣ ተጋገዙ፣ የህይወትን መራራ ፅዋ አብራችሁ ተጋቱ! እውነተኛ፣ ጠንካራና ጣፋጭ ህይወት በላብና በወዝ ከባዶ ተነስቶ፣ ከትንሽ ወደ ትልቅ የሚያድግ የሁለት ፅኑ ነፍሳት የጋራ ፍሬ ነውና። ትዳርን በማቅለል፣ የዚህን ትውልድ ሸክም አብረሽ አቅልዪ!
የከተማው ቅን ሙስሊም ወጣት ሰቆቃ! በዚህች የጭስና የጭንቀት ከተማ፣ ገና በሃያ አምስት አፍላ የዕድሜ ዘመን አናት ላይ የኑሮ አረመኔነት ፀጉርን በነጭ ቀለም ሲያረክሰው፣ የአዲስ አበባ ወጣትነት ሞትን በቁም የመጠባበቅ ያህል የሚከብድ መፍትሔ አልባ የህልውና ሰቆቃ ሆኖ እናገኘዋለን። አባትና እናትን ከድህነት አዘቅት ጎትቶ የማውጣትና የራስን ጎጆ በጊዜ የመቀለስ የልጅነት ህልም፣ በየዕለቱ በሚያሻቅበው የኑሮ ውድነት ገደል ውስጥ ገብቶ ተቀብሯል። የነገን ራዕይ ሰንቆ ቤት የመከራየት ጉዳይ ቀርቶ፣ የዕለት የታክሲ ሳንቲም ስሌት የነፍስ ጣር በሆነበት እውነታ ውስጥ ወጣቱ በብርቱ ይዳክራል። ከሁሉ በላይ የሚያሳምመው ደግሞ የሞራሉ መላሸቅና የማህበራዊው እውነታ ፅልመት ነው፤ ዝሙትና ልቅነት እንደ ርካሽ ሸቀጥ በየመንገዱ ሲታደልና ስሜትን የሚያቀጣጥል የነውር መንፈስ በየአቅጣጫው ሲነፍስ፣ በአንፃሩ ክቡር የሆነው ትዳር ግን እንደ ሰማይ ኮከብ የራቀውና እንደ ፅኑ ተራራ የከበደው ሆኖበታል። በጊዜ ማግባት የሚባለው ፅንሰ-ሀሳብ ከእውነታው ዓለም ተፋቶ፣ ጥሪት ባጣው ወጣት ህይወት ውስጥ የምናብ ብቻ ቅንጦት ሆኖ ቀርቷል። በአንድ በኩል የማህበራዊ ትስስር ገፆች በሚያዘንቡበት አስመሳይ የድሎት ዶፍ የስነ-ልቦና ጦርነት ሲረታ፣ በሌላ በኩል ደግሞ "ጥብቅ ነኝ" በሚለው ሃይማኖታዊ እምነቱና በሚያሸንፈው የሥጋ ፈተና መካከል ተሰንጥቆ የህሊና ደም ይፈሰዋል። "ሙናፊቅ ነኝ እንዴ?" የሚለው የድብቅ ፀፀት፣ እንዲሁም በድብቅ ወንጀልና በንሰሃ መሃል የሚደረገው ግብግብ እንደ ቋያ እሳት ከውስጥ እየበላው ይንገዳገዳል። ይህ ሁሉ መራራ የህልውና ሸክም ትውልዱን በቁም ያኮሰመነ፣ ትዳርን አርቆ ዝሙትን ያቀረበበት፣ ጉልበት ሳለ አቅም ያሳጣበትና ያላወቀውን እርጅና በግድ ያሸከመው ታላቅ የዘመናችን ሰቆቃ ነው። ከዚህ ሁሉ የነፍስና የስጋ ምስቅልቅል አውጭው መንገድም፣ በፈጣሪ እጅ ካለው የሰብር፣ የኢማን፣ የዱዓና የተወኩል ፅናት ውጭ ሌላ አንዳች አለመሆኑን አምኖ በዝምታ መጓዝ ብቻ ሆኗል። አይዞን ጀግናው እጅ እዳትሰጥ! ይህን አንብበህ እንዳታለቃቅስ! ለይል ሰላት ላይ በርታ! 📱https://t.me/abdurezaq27