tgindex
መዝሙር ግጥሞች ቤት🛎EOC🔔✝️

መዝሙር ግጥሞች ቤት🛎EOC🔔✝️

Статистика

ይህ_የኢ_ኦ_ተ_ቤ_ክ_አስተምህሮና_ሥርዓትን_የምንማማርበት_Channel_ነው ! #ወደ_ቻናላችን_በመቀላቀል 👇 #➲የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መፅሐፍትን በPDF #➲ስንክሳር ትምህርቶች #➲መዝሙራትን በግጥሞች #➲ኪነ-ጥበብ #➲ጥያቄዎችን በሐይማኖት ብትኖሩ እራሳችሁን መርምሩ"2ኛቆሮ-13 ፥ 5 Group ገጽ👇 https://t.me/Orthodoxs_Tewahdo_menfeswi_group 👆👆👆👆👆👆

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
23
Всего постов
80
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
43 970
−90 за 3 дн.
Сутки
−40
−0,09%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
252
40 постов
Вовлечённость
0,6%
к подписчикам
Постов в день
3,3
всего 80
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
228
1/48двое суток
261
1/72трое суток
281

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 13 авг.16удалён 13 авг.

    🎯 ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይፈልጋሉ? ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ዘማሪ አቤል መክብብ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎤 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 🎤 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ ┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓ 🎚 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 🎚 ┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛ 🎤 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇 🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧

  • ንባባት፡ --- ፩ኛቆሮ. ም፫ ቊ.፲—፳፪ (ወከመ ጸጋሁ ለእግዚአብሔር) ፩ኛ ጴጥ. ም.፫ ቊ. ፯ (ወከማሁ አንትንሂ አንስት ተኰነና፤) ግብ.ሐዋ. ም.፲፮ ቊ.፲፫—፲፱ (ወወፃዕነ በዕለተ ሰንበት እምአንቀጸ ሀገር) ምስባክ ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ፤ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን፡፡ ወንጌል -- ወንጌለ ማርቆስ ም. ፲፮ ቊ. ፱—፲፱ (ወተንሢኦ በጽባሕ በእሁድ ሰንበት) ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ አው ግሩም ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 5 መታሰቢያ፡ አብርሃም ካልእ ወዮሐንስ ሐራ ወአባ ፊልጶስ ዘደብረ ቢዘን ንባባት፡ --- ፪ኛቆሮ. ም፲፪ ቊ.፲—፲፯ፍጻሜ ም. (ወበእንተዝ ሠመርኩ በሕማምየ) ፩ኛ ዮሐ. ም.፭ ቊ. ፲፬—ፍጻሜ ም. (ወዛቲ ይእቲ እንተ ብነ ገጽ ኀቤሁ) ግብ.ሐዋ. ም.፲፭ ቊ.፩—፲፫ (ወቦ እለ ወረዱ እምብሔረ ይሁዳ) ምስባክ ወትሰይመኒ ውስተ ርእሰ ሕዝብ፤ ሕዝብ ዘኢየአምር ተቀንየ ሊተ፤ ውስተ ምስማዐ ዕዝን ተሠጥዉኒ፤ ወንጌል -- ወንጌለ ሉቃስ ም. ፲፭ ቊ. ፩—፲፩ (ወሀለዉ ይቀርብዎ መጸብሐውያን) ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ አው ግሩም ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 4 መታሰቢያ፡ ሕዝቅያስ ንጉሥ ወፊልጶስ ወአኃዊሁ ወማቴዎስ ንባባት፡ --- ሮሜ. ም፲፪ ቊ.፲፰—ፍጻሜ ም. (ወከመዝ ሐልዩ ምስለ ቢጽክሙ) ፩ኛ ጴጥ. ም.፭ ቊ. ፲፪ (አትሕቱ እንከ ርእሰክሙ) ግብ.ሐዋ. ም.፲፯ ቊ.፳፫—፳፰ (ወቢጺሕየ ዝየ ርኢኩ ጣዖተክሙ) ምስባክ እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሣሕ ንጉሥ፤ ወብዙኃ ይትሐሠይ በአድኅኖትከ፤ ፍትወተ ነፍሱ ወሀብኮ፡፡ ወንጌል -- ወንጌለ ሉቃስ ም. ፲፬ ቊ. ፴፩—ፍጻሜ ም. ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ አው ዘቄርሎስ ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 3 መታሰቢያ፡ ስምዖን ዘዓምድ ወቅድስት ሶፍያ ንባባት፡ --- ፩ኛተሰ. ም፩ ቊ.፩—ፍጻሜ ም. (ወሥዒነነ ተዐግሦ አብደርነ ንንበር አቴና) ፩ኛ ጴጥ. ም.፫ ቊ. ፲—፲፭ (ወዘሰ ያፈቅራ ለሕይወት ወይፈቱ ይርአይ) ግብ.ሐዋ. ም.፲፬ ቊ.፳—ፍጻሜ ም. (ወበሳኒታ ሖረ ምስለ በርናባስ) ምስባክ ወይሰግዳ ሎቱ አዋልደ ጢሮስ በአምኃ፤ ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኵሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ ኵሉ ክብራ ለወለተ ንጉሠ ሐሴቦን፤ ወንጌል -- ወንጌለ ሉቃስ ም. ፲፰ ቊ. ፱—፲፰ ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ፡፡) ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 2 መታሰቢያ፡ አትናስያ ቅድስት ወድሚና ሰማዕት ወአኃዊሁ ወኢዮጰራቅስያ ብፅዕት ንባባት፡ --- ፩ኛጢሞ. ም.፪ ቊ.፰—ፍጻሜ ም. (ወእፈቅድ ለኵሉ ሰብእ ይጸልዩ በኵሉ ገጸ መካን) ፩ኛ ጴጥ. ም.፫ ቊ. ፩—፮ (ወከማሁ አንትንሂ አንስት ተኰነና ለኣምታቲክን) ግብ.ሐዋ. ም.፲፮ ቊ.፲፫—፲፱ (ወወፃእነ በእለተ ሰንበት እንአንቀጸ ሀገር) ምስባክ ወይወስዱ ለንጉሥ ደናግለ ድኅሬሃ፤ ወቢጻሂ ይወስዱ ለከ፤ ወይወስድዎን በትፍሥሕት ወበሐሤት፤ ወንጌል -- ወንጌለ ዮሐንስ ም. ፰ ቊ. ፱—፲፪ ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ፡፡) ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 1 መባቻ፡ጾመ ፍልሰታ፡ መታሰቢያ፡ አመ ዐሚሩ ለነሐሴ አቦሊ ሰማዕት ወተዝካረ ሐና እመ እግዝእትነ ወዮሴፍ ወኒቆዲሞስ እለ ገነዝዎ ለእግዚእነ ንባባት፡ --- ፩ኛጢሞ. ም.፭ ቊ.—፲፩ (ሊቃናተ ኢታመጒጽ) ፩ኛ ዮሐ. ም.፭ ቊ. ፩—፮ (ኲሉ ዘየአምን ከመ ኢየሱስ ውእቱ መሢሕ) ግብ.ሐዋ. ም.፭ ቊ.፳፯—፴፬ (ወእምዝ ሖረ መጋቤ ምኵራብ) ምስባክ ወእነግር ስምዐከ በቅድመ ነገሥት ወኢትይኀፈር፤ ወአነብብ ትእዛዘከ ዘአፍቀርኩ ጥቀ፤ ወአነሥእ እደውየ ኀበ ትእዛዝከ ዘአፈቅር ወንጌል -- ወንጌለ ዮሐንስ ም. ፲፱ ቊ. ፴፰—ፍጻሜ ም. ቅዳሴ --- ዘዮሐንስ አፈወርቅ አው ዘእግዝእትነ ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! እመቤታችን የጾመ ፍልሰታ የእለታት ታዋቂ ልጥፎች ምስል መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ገድላት ሰዋስዋዊና ምሥጢራዊ ፍች ገድል የሚለው ቃል ገደለ - አቈሰለ፣ አረደ፣ አነቀ፣ እገደል ጣለ ከሚለው የግእዝ ቋንቋ ቀዳማይ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ዕብራይስጥ ጋድል ይለዋል፡፡ “ወገደለ ንጉሥ እምጥሪተ ዚኣሁ፣ ወመላእክትኒ ገደሉ ለሕዝብ” ከሚለው ይህ ይታወቃል ፪ዜና. ፴፭፥፯፡፡ ትርጕሙም በቀጥታ ትግል፣ ፈተና፣ ውጊያ፣ ሰልፍ፣ ድልና አክሊል እስኪገኝ ድረስ የሚደክሙት ድካም፣ የሚሠሩት ሥራ፣ የሚቀበሉት መከራ ማለት ይኾናል፡፡ መጻሕፍተ ገድል (ቅዱሳት ገድላት) የሚባሉት በሕይወታቸው እግዚአብሔርን ያከበሩ ቅዱሳን/ት  ሰዎች ያለፉበትን የመከራ ሕይወትና በክርስትናቸው ምክንያት ያገኛቸውን ፈተና ያለፉበትን ወንጌላዊ ጥበብ የሚተርክ፤ ለአማኒያን መማሪያ ለቅዱሳን መዘከሪያ ኾነው የሚቀርቡ ቅዱሳት መጻሕፍት አዋልድ ናቸው ምሳ. ፲፥፯፡፡ ስለዚህ ገድላት ሦስት ዐበይት ጠቀሜታዎች/ዓላማዎች አሏቸው፡፡ አንደኛውና ዋናው የክርስቶስን ክብር መግለጥ ነው፡፡ ሁለተኛው ለምእመናን ትምህርት ነው፡፡ ሦስተኛው ደግሞ ለቅዱሳኑ ተዝካር/መታሰቢያ ይኾን ዘንድ ነው፡፡ ክርስቶስን ለመግለጥ በአጭር ቋንቋ በገድላት የክርስቶስ ክብር ይገለጥባቸዋል እንጂ ገድሉ የተነገረለት ቅዱስ ብቻ ክብር አይደለም፡፡ “አመ ይመጽእ ይሴባሕ በቅዱሳኒሁ ወይትአኰት በእለ የአምኑ ቦቱ” ፪ተሰ. ፩፥፲ በቅዱሳኑ ይገለጽ ዘንድ በሚያምኑበትም ይመሰገን ዘንድ በመጣ ጊዜ ምስል የጌታ ወንድሞችና እኅቶች፡ (ማቴ.13፣55) ያዕቆብ፣ ዮሳ፣ ስምዖንና ይሁዳ በማቴዎስ ወንጌል ውስጥ ጌታችን በትውልድ አገሩ ሲሰብክ ሳለ በናዝራውያን ወገኖች “ ወንድሞቹ ” ተብለው እንደተጠሩ እናነባለን፡፡ ( ማቴ . 13 ፣ 55) ኹሉም ባይኾኑም አንዳንድ ፕሮቴስታንት ወንድሞች ይህን ገጸ ንባብ በመያዝ፣ ከዚሁም ጋር በሌላ ቦታ ዮሴፍ እመቤታችንን “ እስከምትወልድ ድረስ አላወቃትም ” ( ማቴ .1 ፣ 25) ከሚለው ንባብ ጋር በማናበብ ከወለደች በኋላ ግን ዐወቃት ወደሚል እኩይ አገባብ ጠምዝዘው እመቤታችን ከጌታ በተጨማሪ ከዮሴፍ የወለደቻቸው የሥጋ ወንድሞቹና እኅቶቹ አሉ ብለው ስሕተት ይናገራሉ፡፡ ትምህርቱ ልክ ከማይኾንባቸው ምክንያቶች መካከል የተወሰኑት፡ 1. ሌላ እናት ? … ያዕቆብና ዮሳ በድጋሚ በማቴ .27 ፣ 55 ላይ ተጠቅሰዋል፤ ያኔ በጌታችን በስቅለቱ ጊዜ “ እናታቸው ” ተጠቅሳለች፤ እመቤታችን ግን አልነበረችም፡፡ ምክንያቱም የያዕቆብና የዮሳ እናት ይህችኛዋ ማርያም ከኾነች አባታቸው ደግሞ ሉቃ .6 ፣ 15 እልፍዮስ እንደኾነ ይናገራል፡፡ ይህ ማለት ደግሞ እነዚህን ገጸ ንባቦች ይዘው ዐራቱ የእመቤታችንና የዮሴፍ ልዦች ናቸው የሚሉ ሰዎች አባታቸው እልፍዮስ ኹኖ መገኘቱ እንዴት እንደኾነ የማስረዳት ሸክምም አለባቸው ማለት ነው፡፡ ያዕቆብ የተባለው በገላትያ መልእክት ላይ ( ገላ .1 ፣ 19) ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ጳውሎስ ወደኢየሩሳሌም በሄደ ጊዜ ከ 12 ቱ ወገን ያገኘው ብቸኛው እርሱ እንደኾነ የጠቀሰው ሐዋርያው ቅዱስ ያዕቆብ ሲኾን እርሱንም “ ...

  • መንፈሳዊ ጥያቄ እና መልስ ማህበር📥EOC🛎: ሰላም ለኪ የጾመ ፍልሰታ የእለታት ምስባክ፣ቅዳሴ፣ምንባባት፣ወንጌልና ሌሎችም ነሐሴ 01, 2018ዓ.ም ነሐሴ 16 መታሰቢያ፡        ፍልሰተ ሥጋሃ ለእግዝእትነ ወፍልሰተ ሥጋሁ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ወጊጋር መስፍነ ሶርያ፡፡ ምንባባት፡         ሮሜ. ፰ ቊ. ፴፰—ፍጻሜ ም.  ዮሐ. ፪ ቊ. ፩—፯  የሐዋ. ፩ ቊ. ፲፪—፲፭ ማቴ. ፳፮  ቊ. ፳፮—፴፩ ምስባክ፡   ቀደሰ ማኅደሮ ልዑል፤                እግዚአብሔር ውስተ ማዕከላ ኢትትሐወክ፤                  ወይረድኣ እግዚአብሔር ፍጽመ፡፡                  ወዓዲ                  ወተዚያነዉ ዳኅናሃ ለኢየሩሳሌም፤                  ወፍሥሐሆሙ ለእለ ያፈቅሩ ስመከ፤                  ይኩን ሰላም በኃይልከ፡፡                             ቅዳሴ፡      ዘእግዚእነ (ነአኵተከ) ነሐሴ 15 መታሰቢያ፡        ክርስጢና ሰማዕት፫፼፲ወ፪ ማኅበራኒሃ ወዕንባምሬና ቅድስት፣ ሐዋርያት ለግንዘተ እሙ ለእግዚእነ ወለውረንዮስ ሰማዕት፡፡ ምንባባት፡         ቆሮ. ፩ ም. ፲፪ ቊ. ፲፰—ፍጻሜ ም.  ይሁዳ. ፩ ቊ. ፲፯—ፍጻሜ ም. የሐዋ. ፩ ቊ. ፩—፲፪ ማቴ. ፲ ቊ. ፩—፲፭ ምስባክ፡   ውስተ ኵሉ ምድር ወፅአ ነገሮሙ፤                            ቅዳሴ፡      ዘሐዋርያት (ዘበደኃሪ) ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 14 መታሰቢያ፡ በዓለ መስቀል ወባስሊቆስ ሰማዕት ወድምጥያ ሰማዕት ገባሬ ተአምር ወዮሐንስ ወስምዖን አኃው፡፡ ንባባት፡ --- ፩ ቆሮ. ም.፩ ቊ.፲—፲፪ (አስተበቊዐክሙ አኃዊነ በስሙ ለእግዚእነ) ያዕቆብ. ም.፩ ቊ. ፲፪ (ወብፁዕ ብእሲ ዘይትዔገሣ ለእኪት) ግብ.ሐዋ. ም.፲ ቊ.፴—፵፬ (ወይቤሎ ቆርኔሌዎስ ረቡዐ ዮም) ምስባክ ዘአዘዝከ መድኃኒቶ ለያዕቆብ፤ ብከ ንወግዖሙ ለኵሎሙ ፀርነ፤ ወበስምከ ናኃሥሮሙ ለእለ ቆሞ ላዕሌነ፡፡ ወንጌል -- ወንጌለ ማቴዎስ ም. ፲፯ ቊ. ፲፬—፳፬ (ወበጺሖሙ ኀበ አሕዛብ ቀርበ ኀቤሁ) ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ አው ዘዮሐንስ አፈወርቅ፡፡ ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 13 መታሰቢያ፡ በዓለ ደብረ ታቦር ወልደቱ ለሙሴ ወብንያም ወጋልዮን መስተጋድል ንባባት፡ --- ዕብ. ም፲፩ ቊ.፳፫—፴ (በተአምኖ ተወሊዶ ሙሴ) ፪ኛ ጴጥ. ም.፩ ቊ. ፲፩ (ወዓዲ እጔጕዕ ከመ ተሀሉ ኀቤክሙ) ግብ.ሐዋ. ም.፯ ቊ.፵፬—ፍጻሜ ም. (ወደብተራ ስምዕ እንተ ነበረት ኀበ አበዊነ) ምስባክ ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሑ፤ ወይሴብሑ ለስምከ፤ መዝራዕትከ ምስለ ኃይል፡፡ ወንጌል -- ወንጌለ ሉቃስ ም. ፱ ቊ. ፳፰—፴፰ (ወእምድኅረ ዝንቱ ነገር አመ ሳምንት ነሥኦሙ) ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ አው ዘዲዮስቆሮስ፡፡ ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 12 መታሰቢያ፡ ቅዱስ ሚካኤል አስተርአዮ ለቈስጠንጢኖስ ወነግሠ ቈስጠንጢኖስ በሮሜ ወ፳፻ ሰማዕታት ማኅበራነ ፋሲለደስ ንባባት፡ --- ፩ ቆሮ. ም፱ ቊ.፲፯—ፍጻሜ ም. (ወእመሰ ዘእምፈቃድየ ገበርክዎ ለዝንቱ) ይሁዳ. ም.፩ ቊ. ፳ (ወከማሁ እሉኒ እለ በሕልሞሙ ይጌምኑ) ግብ.ሐዋ. ም.፳፬ ቊ.፩—፳፪ (ወአመ ኀሙስ ዕለት ወረደ ሐናንያ) ምስባክ እግዚኦ ኩነኔከ ሀቦ ለንጉሥ፤ ወጽድቀከኒ ለወልደ ንጉሥ፤ ከመ ይኰንኖሙ ለሕዝብከ በጽድቅ፡፡ ወንጌል -- ወንጌለ ማቴዎስ ም. ፳፪ ቊ. ፩—፲፭ (ወአውሥአ ኢየሱስ ዳግመ ወነገረ በምሳሌ) ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ አው ዘዮሐንስ አፈወርቅ ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 11 መታሰቢያ፡ ኮኑ ፫፻ ነፍስ ምስለ ቅዱስ ፋሲለደስ ወአባ ሞይስስ ኤጲስ ቆጶስ ወእብጥልማዎስ ንባባት፡ --- ፩ ቆሮ. ም፳ ቊ.፲፩—ፍጻሜ ም. (ወይእዜኒ ጸሐፍኩ ለክሙ ከመ ኢትደመሩ) ፩ኛ ዮሐ. ም.፪ ቊ. ፲፬—፳ (ጸሐፍኩ ለክሙ አበው እስመ አእመርክዎ) ግብ.ሐዋ. ም.፲፪ ቊ.፲፰—፳ (ወጸቢሖ ተሀውኩ ሠገራት) ምስባክ ህየንተ አበውኪ ተወልዱ ለኪ ደቂቅ፤ ወትሠይሚዮሙ መላእክተ ለኵሉ ምድር፤ ወይዘክሩ ስመኪ በኵሉ ትውልደ ትውልድ፡፡ ወንጌል -- ወንጌለ ሉቃስ ም. ፮ ቊ. ፳—፳፬ (ወውእቱሰ አንሥአ አዕይንቲሁ) ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ) ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ❤️❤️ ነሐሴ 10 መታሰቢያ፡ ማኅበረ በኵር ወመጥራ ሰማዕት ወሐርስጥፎሮስ ወቢካቦስ ወዮሐንስ ንባባት፡ --- ዕብ. ም፩ ቊ.፩—፳፪ (ወአንትሙሰ በጻሕክሙ ኀበ ጽዮን) ፩ኛ ጴጥ. ም.፩ ቊ. ፯—፲፫ (ወባሕቱ ኅዳጠ ይእዜ ሀለወክሙ) ግብ.ሐዋ. ም.፬ ቊ.፴፩—፳፭ (ወእንዘ ይጼልዩ አድለቅለቀ ውእቱ መካን) ምስባክ ተዘከር ማኅበረከ በትረ ርስትከ፤ ወአድኀንከ በትረ ርስትከ፤ ደብረ ጽዮን ዘኀደርከ ውስቴታ፡፡ ወንጌል -- ወንጌለ ሉቃስ ም. ፲፮ ቊ. ፱—፲፱ (ወአነሂ እብለክሙ ግበሩ ለክሙ አዕርክተ) ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ) ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 9 መታሰቢያ፡ አባ ኦሪ ሰማዕት ወጲላጦስ ሊቀ ጳጳሳት ንባባት፡ --- ፊልጵስ.. ም፩ ቊ.፲፪—፳፬ (እፈቅድ አኃዊነ ታእምሩ ዜናየ) ፪ኛ ዮሐ. ም.፩ ቊ. ፯—ፍጻሜ ም. (ወዛቲ ይእቲ ተፋቅሮትነ) ግብ.ሐዋ. ም.፲፭ ቊ.፲፱—፳፭ (ወይእዜኒ እብለክሙ ኢታክብዱ) ምስባክ ወትቀውም ንግሥት በየማንከ፤ በአልባሰ ወርቅ ዑፅፍት ወሑብርት፤ ስምዒ ወለትየ ወአጽምኢ እዝነኪ፡፡ ወንጌል -- ወንጌለ ዮሐንስ ም. ፲ ቊ. ፩—፳፪ (አማን አማን እብለክሙ) ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ አው ዘባስልዮስ ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 8 መታሰቢያ፡ አልአዛር ወሰሎሜ ብእሲቱ ወውሉዱ ፯ቱ ወአሞን ንባባት፡ --- ሮሜ. ም፫ ቊ.፱—፳፬ (ወንሕነ እሙንቱ እለ ጸውዐነ ውስተ ክብሩ) ፩ኛ ጴጥ. ም.፬ ቊ. ፲፪—ፍጻሜ ም. (አኃዊነ ኢታንክርዋ ለእንተ ትመጽአክሙ፤) ግብ.ሐዋ. ም.፲፯ ቊ.፴፩—ፍጻሜ ም. (ወጸቢሖ ለእኩ መኳንንት) ምስባክ ወድቀት እሳት ወኢርኢክዋ ለፀሐይ፤ ዘእንበለ ይትዐወቅ ሦክክሙ ሕለተ ኮነ፤ ከመ ሕያዋን በመዓቱ ይውኅጠክሙ፡፡ ወንጌል -- ወንጌለ ማቴዎስ ም. ፯ ቊ. ፲፪—፳፮ (ኵሎኬ ዘትፈቅዱ ይገብሩ ለክሙ ሰብእ) ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ) ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 7 መታሰቢያ፡ ፅንሰታ ለእግዝእትነ ወተስእሎተ ቂሣርያ ወጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት ወልደቱ ለዮሴፍ ወልደ ራሄል ወናዖድ ንጉሠ ኢትዮጵያ ንባባት፡ --- ዕብ. ም፩ ቊ.፩—፲፯ (ወለቀዳሚትነ ደብተራ) ፩ኛ ጴጥ. ም.፪ ቊ. ፯—፲፰ (እስመ ከመዝ ጽሑፍ ናሁ እሠይም፤) ግብ.ሐዋ. ም.፲ ቊ.፩—፴ (ወሀሎ ፩ዱ ብእሲ በሀገረ ቂሣርያ) ምስባክ ብፁዕ ብእሲ ዘአንተ ገሠጽኮ እግዚኦ፤ ወዘመሀርኮ ሕገከ፤ ከመ ይትገኀሥ እመዋዕለ እኩያት፡፡ ወንጌል -- ወንጌለ ማቴዎስ ም. ፲፮ ቊ. ፲፫—፳፬ (ወበጺሖ ኢየሱስ ብሔረ ቂሣርያ) ቅዳሴ --- ዘእግዝእትነ (ጐሥዓ) ጾሙን የሰላም የፍቅር የበረከት የድኅነት ያድርግልን! ነሐሴ 6 መታሰቢያ፡ ኢየሉጣ ወማርያም መግደላዊት ወአባ ዊፃ

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 🕊 † እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የጽንሰት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ! † † 🕊 ቁጽረታ [ጽንሰታ] ለማርያም 🕊 † ይህችን ዕለት አበው ሊቃውንት "ጥንተ መድኃኒት፤ የድኅነት መነሻ ቀን" ሲሉ ይጠሯታል:: ስለ ምን ነው ቢሉ:- ለዓለም ድኅነት ምክንያት የሆነች የአምላክ እናቱ የተጸነሰችበት ዕለት በመሆኑ ነው:: አንድም ከአዳም ስሕተት በኋላ ያለ ጥንተ አብሶ የተጸነሰች የመጀመሪያ ሰው እርሷ ናትና እንዲህ ይላሉ:: "ለጽንሰትኪ በከርሥ: እንበለ አበሳ ወርኩስ: ወለልደትኪ እማኅጸን ቅዱስ::" "ድንግል ሆይ! መጸነስሽ ያለ በደል ነው: የተወለድሽበት ማኅጸንም ቅዱስ ነው::" [መጽሐፈ ሰዓታት, ኢሳ.፩፥፱ ፣ መኃ.፬] ይሕች ዕለት ለኢያቄምና ለሐና ብቻ ሳይሆን ለፍጥረት ሁሉ የተስፋ ድኅነት ቀን ናትና ሐሴትን ልናደርግ ይገባል:: የእመቤታችን መጸነስስ እንደ ምን ነው ቢሉ:- ከነገደ ይሁዳ የሚወለድ ቅዱስ ኢያቄም የሚባል ደግ ሰው ከነገደ ሌዊ [አሮን] የተወለደች ሐና የምትባል ደግ ሴት አግብቶ: በሕጉ ጸንተው: በሥርዓቱ ተጠብቀው ይኖሩ ነበር:: ነገር ግን በዘመኑ ሰዎች "ልጅ የላችሁም" በሚል ይናቁ ነበር:: ኦሪታውያን ልጅ የሌለውን "ኅጡአ በረከት-ከጸጋ እግዚአብሔር የራቀ" ነው ብለው ያምኑ ነበር:: ኢያቄምና ሐና ልጅ እንዲሰጣቸው ሲያዝኑ: ሲጸልዩ ዘመናቸው አልፎ አረጁ:: እነሱ ግን የሚያመልኩት የአብርሃምና ሣራን አምላክ ነውና ተስፋ አልቆረጡም:: የለመኑትን የማይነሳ ጌታ በስተእርጅናቸው ድንቅ ነገርን አደረገላቸው:: አንድ ቀን ርግቦች ከጫጩቶቻቸው ጋር ሲጫወቱ የተመለከተች ቅድስት ሐና ፈጽማ አለቀሰች:: "እንስሳትና አራዊትን: እጽዋትን በተፈጥሯቸው እንዲያፈሩ የምታደርግ አምላክ ምነው ሐናን ድንጋይ አድርገህ ፈጥረሃታልን?" ብላ አዘነች:: ይህን የተመለከተ ቅዱስ ኢያቄም ወደ ተራራ ወጥቶ ሱባኤ ያዘ:: ለአርባ ቀናትም ሲጸልይና ሲማለል ቆየ:: በአርባኛው ቀን ሁለቱም ሕልምን ያልማሉ:: እርሱ:- ነጭ ርግብ ሰማያትን ሰንጥቃ ወርዳ: በሐና ቀኝ ጆሮ ገብታ: በማኅጸኗ ስትደርስ አየ:: እርሷ ደግሞ :- የኢያቄም በትር አብቦ: አፍርቶ: ጣፋጭ ፍሬውን ሰው ሁሉ ሲመገበው ታያለች:: ቅዱስ ኢያቄም ከሱባኤ እንደ ተመለሰ ያዩትን ተጨዋውተው "ፈቃደ እግዚአብሔር ይሁን" አሉ:: ለሰባት ቀናትም በጋራ እግዚአብሔርን ሲለምኑ ሰነበቱ:: በሰባተኛው ቀን [ማለትም ነሐሴ ፯] መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ክንፉን እያማታ ወደ እነርሱ ወረደ:: "ዓለም የሚድንባት: የፍጥረት ሁሉ መመኪያ የሆነች ልጅ ትወልዳላችሁ" ብሏቸው ተሠወራቸው:: እነርሱም ደስ ብሏቸው እግዚአብሔርን አመሰገኑ:: እንደ ሥርዓቱም በዚህች ቀን አብረው አድረው እመ ብርሃን ተጸነሰች:: "ኦ ድንግል አኮ በፍትወተ ደነስ ዘተጸነስኪ" "ድንግል ሆይ! ኃጢአት ባለበት ሥጋዊ ፍትወት የተጸነስሽ አይደለም" እንዳለ ሊቁ:: [ቅዳሴ ማርያም] † 🕊 ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት 🕊 † ዳግመኛ ይህች ዕለት የቅዱስ ጴጥሮስ መታሰቢያ ናት:: ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ስብከቱ በዚህች ቀን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ቂሣርያ ፊልጶስ ይዟቸው ሔደ:: በዚያም ጌታ ከእነሱ ራቅ ብሎ ተቀምጦ ነበርና የማይሰማቸው መስሏቸው እርስ በእርስ ይከራከሩ ገቡ:: የክርክራቸው መነሻ ደግሞ ጌታችን ነበር:: የዋሃን [ገና ምሥጢርን ያልተረዱ] ነበሩና አንዱ ተነስቶ "ኤልያስ ነው": ሌላኛው "ሙሴ": ሦስተኛው "ኤርምያስ ነው" በሚል ተከራከሩ:: ቅዱስ ጴጥሮስ ለብቻው ቆሞ ነበርና ጠርተው "ሃሳባችንን አስታርቅልን:: ለአንተስ ማን ይመስልሃል?" አሉት:: አረጋዊው ሐዋርያም ተቆጣቸው:: "እናንተ እንደምታስቡት እርሱ ከነቢያት አንዱ ሳይሆን "እግዚአ ነቢያት-የነቢያት ፈጣሪ ነው" አላቸው:: ወዲያውም ጌታ ጠርቷቸው ወደ እርሱ ቀረቡ:: ቸር አምላክ "ለምን ተጠራጠራችሁኝ" ብሎ መገሰጽ ሲችል እንዳይደነግጡ ጥያቄውን በፈሊጥ አደረገ:: "የሰውን ልጅ ሰዎች ማን ይሉታል?" አላቸው:: እነርሱም በልባቸው ያለውን የሌላ አስመስለው ተናገሩ:: ጌታችን "እናንተስ ማን ትሉኛላችሁ?" ቢላቸው ጸጥ አሉ:: ገና ሃይማኖታቸው አልጸናም ነበርና:: በዚያን ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ ተነስቶ "አንተ ውእቱ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው-አንተ የሕያው እግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ክርስቶስ ነህ" አለው:: [ማቴ.፲፮፥፲፮] ይህች ቃል የክርስትና ሃይማኖት መሠረት ናትና ጌታችን "አንተ ዓለት ነህ" ብሎ የቤተ ክርስቲያንን በዚህ እምነት ላይ መመስረት ተናገረ:: ለቅዱስ ጴጥሮስም "መራሑተ መንግስት-የመንግስተ ሰማያት መክፈቻ ቁልፍ [ሥልጣን]" ተሰጠው:: ሊቀ ሐዋርያትነትንም ደረበ:: ዛሬ ለበርካቶቹ የጸነነባቸው ይሔው እምነት ነው:: ኢየሱስ ክርስቶስን "አምላክ ወልደ አምላክ: ወልደ ማርያም: አካላዊ ቃል: ሥግው ቃል: ገባሬ ኩሉ: የሁሉ ፈጣሪ"ብለው ካላመኑ እንኳን ጽድቅ ክርስትናም የለም:: † 🕊 አፄ ናዖድ ጻድቅ 🕊 † ሃገራችን ኢትዮጵያ ምስፍና ከክህነት: ንግሥናን ከጽድቅ ያጣመሩ ብዙ መሪዎች ነበሯት:: ከእነዚህ አንዱ ደግሞ አፄ ናዖድ ናቸው:: ጻድቁ ንጉሥ የነገሡት ከ1487 እስከ 1499 ዓ/ም ሲሆን ለእመቤታችን በነበራቸው ልዩ ፍቅር ይታወቃሉ:: ካህን እንደ ነበሩም ይነገራል:: ዛሬ ሁላችን የምንወዳትን ጸሎት [ሰላም ለኪ: እንዘ ንሰግድ ንብለኪ . . .] የደረሷት እርሳቸው ናቸው:: ትልቁን መልክአ ማርያምም ደርሰዋል:: ይህ መልክእ ጣዕሙ ልዩ ነው:: የጻድቁ ንጉሥ ሚስት [ማርያም ክብራ] : ልጆቻቸው [አፄ ልብነ ድንግልና ቡርክት ሮማነ ወርቅ] እጅግ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩ:: ንጉሡ አፄ ናዖድ ከባለሟልነት የተነሳ ድንግል ማርያምን "እመቤቴ ስምንተኛው ሺ መቼ ይገባል? ጊዜውስ እንዴት ያለ ነው?" አሏት:: እመ ብርሃንም በአካል ተገልጻ የዘመኑንና የሰውን ክፋት ነገረቻቸው:: ንጉሡም አዝነው "እመቤቴ! ከዛ ዘመን አታድርሺኝ" አሏት:: በዚህ ምክንያት የስምንተኛው ሺህ ዘመን መስከረም 1 በ1500 ዓ/ም ሊገባ እርሳቸው ነሐሴ 7 ቀን በ1499 ዓ/ም ዐርፈዋል:: ጌታችን መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የድንግል እናቱን ጣዕም: ፍቅር: የቅዱስ ጴጥሮስን ሃይማኖትና የአፄ ናዖድን በረከት ያሳድርብን:: 🕊  † ነሐሴ ፯ [ 7 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ፩.በዓለ ጽንሰታ ለእግዝእትነ ማርያም ፪.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና ፫.ቅዱስ ገብርኤል መበሥር ፬.ቅዱስ ጴጥሮስ ሊቀ ሐዋርያት ፭.አፄ ናዖድ ጻድቅ [ንጉሠ ኢትዮጵያ] ፮.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ ፯.አባ ጢሞቴዎስ ሊቀ ጳጳሳት † ወርኀዊ በዓላት ፩.ሥሉስ ቅዱስ ፪.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ፫.አባ ሲኖዳ [የባሕታውያን አለቃ] ፬.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት ፭.አባ ባውላ ገዳማዊ ፮.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ፯.ቅዱስ አግናጥዮስ † "መሠረቶቿ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው:: ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ እግዚአብሔር የጽዮንን ደጆች ይወዳቸዋል:: የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ! በአንቺ የተደረገው ድንቅ ነው . . . ሰው እናታችን ጽዮን ይላል::" † [መዝ.፹፮፥፩-፮] † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • 🕊 †  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡  † [ †  እንኩዋን ለቅድስት እናታችን ማርያም መግደላዊት ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ  † ] †  🕊 ቅድስት ማርያም መግደላዊት  🕊  † ይህችን ቅድስት "ማርያም" ያሏት ወላጆቿ ሲሆኑ "መግደላዊት" እያሉ የጠሯት ደግሞ ሐዋርያት [ወንጌላውያን] ናቸው:: ለምን እንዲህ ብለው ጠሯት ቢሉ :- በዘመኑ "ማርያም" የሚባሉ ብዙ ሴቶች ነበሩና ከእነሱ ለመለየት ነው:: አንድም ሃገሯ ከእሥራኤል አውራጃዎች በአንዱ [በመግደሎን] ተወልዳ ያደገች ናትና:: ማርያም መግደላዊት ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ነበረችና ሰዎች ያደንቁዋት: ወንዶች ይከተሏት ነበር:: በዚህም ፯ [7] አጋንንት ተጠግተው ፯ [7] ዓይነት ኃጢአትን ያሠሯት ነበር:: በተለይ ደግሞ በዝሙት: በትውዝፍት [ምንዝር ጌጥ] እና ትዕቢት በእጅጉ የታወቀች ነበረች:: በእንዲህ ያለ ግብር ጸንታ ለዘመናት ኖረች:: በዚያ ወራት የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንን ተዋሕዶ ያስተምር ነበርና ስለ እርሱ ሰማች:: "ጌታ ኃጥአንን አይጸየፍም [ይቀበላል]: አጋንንትንም ያስወጣል" ብለውም ነገሯት:: ጥሪው የእግዚአብሔር ነውና ማርያም መግደላዊት አልዘገየችም:: ወደ እርሱ ሔዳ ጌታ ባያት ጊዜ ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነውና አቀረባት:: በቸርነቱም ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን ፯ [7] የአጋንንት ነገድ አስወጣላት:: በዚያች ሰዓት ዕለቱኑ እንደተወለደ ሕጻን ከነበረባት ችግር ሁሉ ንጹሕ ሆነች:: ጌታም ከ፴፮ [36]ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ትሆን ዘንድ መርጦ ተከታዩ አደረጋት:: ቅድስት ማርያም ከዚህች ቀን ጀምሮ ፍጹም ተቀየረች:: እርምጃዋ ሁሉ የተባረከና የንጽሕና ሆነ:: ጌታን እስከ ዕለተ ሕማሙ ድረስ በመዓልትም: በሌሊትም በቅን አገለገለችው:: ጌታችን ስለ እኛ መከራን በተቀበለባት በዚያች ዕለተ ዐርብም ከጠዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ከጐኑ ነበረች:: ከግርፋቱ እስከ ስቅላቱ እያለቀሰች ተከትላዋለች:: በእግረ መስቀሉ ያለቅሱ ከነበሩ ቅዱሳት አንስትም አንዷ እርሷ ነበረች:: [ዮሐ.፲፱፥፳፭] (19:25) ቅዱሳኑ ዮሴፍና ኒቆዲሞስ ጌታን ሲቀብሩትም ከእሕቶቿ ጋር አብራ ተከትላ አይታለች:: እሑድ በሌሊት: ገናም ሳይነጋ መቃብሩን ታይ ዘንድ: ሽቱም ልትቀባ ወደ ጐልጐታ ገሠገሠች:: ፍጹም የአምላክ ፍቅር አድሮባታልና ግርማ ሌሊቱንና የአይሁድ ጭፍሮችን አልፈራችም:: ጌታችንም ከእመቤታችን ቀጥሎ ከፍጥረት ወገን ትንሳኤውን ያየች የመጀመሪያዋ ሰው ትሆን ዘንድ አደላት:: በመቃብሩ ራስጌና ግርጌም ፪ [2] መላእክትን [ሚካኤልና ገብርኤልን] ተመለከተች:: ዘወር ስትል ደግሞ የክብርን ባለቤት አየችው:: አላወቀችውምና "ማርያም" አላት:: "ረቡኒ-ቸር መምሕር ሆይ" ብላ ሰገደችለት:: ጌታም "ሑሪ ኀበ አኀውየ ወበሊዮሙ . . . ሒደሽ ለደቀ መዛሙርቴ በያቸው . . . " ብሎ የትንሳኤው ሰባኪ አደረጋት:: "ወሖረት ወነገረቶሙ ለአርዳኢሁ . . . " እንዲል ትንሳኤውን ለደጋጉ ሐዋርያት ሰበከችላቸው:: ቅድስት ማርያም መግደላዊት ከክርስቶስ ትንሳኤ በሁዋላ ለ፵ [40] ቀን መጽሐፈ ኪዳንን ፤ ትምሕርተ ኅቡዓትን ተምራለች:: በዕርገቱ ተባርካ : በበዓለ ሃምሳ ከቅዱስ መንፈሱ ጸጋ ተካፍላለች:: በአዲሲቷ ቤተ ክርስቲያን ውስጥም ልዩ አገልግሎት ነበራት:: ቅዱሱ እስጢፋኖስ ፰ [8] ሺውን ማሕበር ሲመራ ሴቶችን ታስተዳድርለት ነበር:: ከሁሉ በላይ ግን ቅድስቲቱ የቅዱሳን ሐዋርያት መጋቢ ነበረች:: በዘመኑ መንፈስ ቅዱስ የሚባርከውን አጋፔ [የፍቅር ማዕድ] የምታዘጋጀው እርሷ ነበረች:: እንዲያውም አንዴ የሚበላ ጠፍቶ ለሐዋርያት ማዕድ ፍለጋ በሔደችበት እግሯ ቆስሎና ደምቶ መመለሷ ይነገራል:: እንዲህ አድርጋ ያዘጋጀችውን ማዕድ ቅዱስ መልአክ ወርዶ ወደ ሰማይ ወስዶታል:: ለቅዱሳን ሐዋርያትም እያመጣ ይመግባቸው ነበር:: እናታችን ማርያም መግደላዊት በስብከተ ወንጌልም የተመሰከረላት ነበረች:: የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን ዲያቆናዊት ሴት ስትሆን ክርስትናንም ተዟዙራ ሰብካለች:: ስለ ቅዱስ ስሙም ሽሙጥን: ስድብን: መንገላታትን እና ግርፋትን ታግሳለች:: በተለይ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋታል:: ቅድስቷ እናታችን መልካሙን ገድል ተጋድላ በበጐ እድሜ በዚህች ቀን ሔዳለች:: በዓለም የሚገኙ ክርስቲያኖች ሁሉ [ከአንዳንዶቹ በቀር] ያከብሯታል:: †  🕊 ቅድስት ኢየሉጣ ዘቂሣርያ  🕊 † በቀድሞው የግሪክ ግዛት [ቂሣርያ ውስጥ] በዘመነ ሰማዕታት አካባቢ የነበረችው ቅድስት ኢየሉጣ ክርስትናን የወረሰችው ከወላጆቿ ነው:: ገና ወጣት እያለች ወላጆቿ በማረፋቸው የሃብታቸው ወራሽ ሆነች:: ነገር ግን አንድ ክፉ ሰው መጥቶ ሃብቷን ነጠቃት:: በዚህ አዝና "የዳኛ ያለህ" ልትል ወደ ፍርድ ቤት ስትሔድ የጠበቃት ግን የሚገርም ነበር:: የተገፋችው እርሷ ተከሳሽ: ገፊው ደግሞ ከሳሽ ነበር:: የክሱ ጭብጥ ደግሞ "ክርስቲያን ነሽ" የሚል ነበር:: በወቅቱ በመኯንንቱ ፊት ክርስትናዋን ብትክድ በቀጥታ ሃብቷን ማግኘት ትችል ነበር:: እርሷ ግን ለአፍታ አሰበች:: "እንዴት ዘላለማዊ ሃብቴን [ሃይማኖቴን] በኃላፊው ንብረት እለውጣለሁ" ብላ ሁሉም እየሰሙ ጮክ ብላ "ክርስቲያን ነኝ" አለች:: ወዲያውም ሞት ተፈርዶባት ተገደለች:: ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ስለ ሰማዕታት በጻፈው ድርሳን ላይ በስፋት አመስግኗታል:: ለሴቶችም ታላቅ ምሳሌ ናት ብሏታል:: ቅዱሳት እናቶቻችንን ያጸና ቸር አምላካቸው እኛንም በሃይማኖትና በምግባር ያጽናን:: ከበረከታቸውም አብዝቶ ያድለን:: 🕊 [  † ነሐሴ ፮ [ 6 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ] ፩. ቅድስት ማርያም መግደላዊት [ከ፴፮ [36]ቱ ቅዱሳት አንስት] ፪. ቅድስት ኢየሉጣ ሰማዕት [ ዘቂሣርያ ] ፫. አባ ዊጻ [ የታላቁ ሲኖዳ ደቀ መዝሙር ] [   †  ወርሐዊ በዓላት    ] ፩. ቅድስት ደብረ ቁስቁዋም ፪. አባታችን አዳምና እናታችን ሔዋን ፫. አባታችን ኖኅና እናታችን ሐይከል ፬. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ ፭. ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ ፮. ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ ፯. ቅድስት ሰሎሜ ፰. አባ አርከ ሥሉስ ፱. አባ ጽጌ ድንግል ፲. ቅድስት አርሴማ ድንግል " ጌታ ኢየሱስም :- "ማርያም" አላት:: እርሷ ዘወር ብላ በእብራይስጥ :- "ረቡኒ" አለችው:: ትርጉዋሜውም "መምሕር ሆይ!" ማለት ነው:: ጌታ ኢየሱስም :- "ገና ወደ አባቴ አላረግሁምና አትንኪኝ:: ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሔደሽ . . . ዐርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው" አላት:: መግደላዊት ማርያም መጥታ ጌታን እንዳየች ይሕንም እንዳላት ለደቀ መዛሙርቱ ነገረች::" [ዮሐ.፳፥፲፮] (20:16) † ወስብሐት ለእግዚአብሔር † † ወለወላዲቱ ድንግል † † ወለመስቀሉ ክቡር † [ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ  ]          †              †               † ▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬ 💖                   🕊                    💖

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

መዝሙር ግጥሞች ቤት🛎EOC🔔✝️ — tgindex