- Последний пост
- 5 мая
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 23
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ሚያዝያ 27 ቀን 2018 ዓ.ም. 85ኛውን የአርበኞች ድል በዓል አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የተሰጠ መግለጫ ሚያዝያ 27 ቀን 1928 ዓ.ም ኢትዮጵያን የወረረው የጣሊያን ፋሽስታዊ አገዛዝ ከአምስት ዓመታት ተጋድሎ በኋላ በተመሳሳይ ቀን ተሸንፎ የወጣበት ዕለት በመሆኑ በሀገራችን የነፃነት ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ ያለው ዕለት ነው። ይህ እለት ፋሽዝም የተሸነፈበት ብቻ ሳይሆን በተመሳሳይ ቀን የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት የተረጋገጠበት ታሪካዊ ቀንም ነው። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለአርበኞች ቀን አደረሳችሁ ይላል። የብልፅግና አገዛዝ የሀገሩን የፖሊሲ ሉዓላዊነት ከማከራዬት አልፎ አዬር ኃይሉን እና መሰል ተቋማትን ለውጭ ኃይሎች መፈንጫ በማድረግ በአርበኞች መስዋዕትነት የተገኘውን የሀገር ነፃነት ለርካሽ ስልጣን ሲል አሳልፎ በመስጠቱ ሀገራችን ያልተነገረ ቅኝ ግዛት ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል። የብልፅግና አረመኔ አገዛዝ በአምስቱ የአርበኝነት ዘመን ጣሊያን ኢትዮጵያዊያን ላይ ከፈፀመው ግብ በብዙ እጥፍ የራቁ የዘር ማጥፋት እና ሰብአዊነት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን በአማራ ህዝብ ላይ እየፈፀመ ነው። የአባቶቹን ታሪክ የወረሰው ሰራዊታችን የአማራን ህዝብ ህልዉና ለማስከበር እና የኢትዮጵያን አንድነት ለማስጠበቅ ከዘመኑ ጥቁር ፋሽስቶች ጋር በመተናነቅ ላይ ይገኛል። ዘር አጥፊዉን አገዛዝ ታግለን በማሸነፍ የተነጠቅነዉን ሀገር ማስመለስ ግባችን እንደመሆኑ መጠን ንቅናቄው አሁን ላይ እያደረገ ያለው ትግል የቀድሞ አርበኞች ካደረጉት የነፃነት ተጋድሎ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው። ፅናትን፣ አይበገሬነትን፣ ቁርጠኝነትን በሚጠይቀው ተጋድሎ ውስጥ በመስዋዕትነት ድል እያስመዘገበ ያለው ሰራዊታችን በአማራ ህዝብ ጠላቶች ላይ የጀመረውን የህልውና ትግል አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እናረጋግጣለን። የባርነት ቀንበር የተሰበረበት የአርበኞችን ቀን ስናከብር የአማራ ህዝብ የተጋረጠበትን የህልዉና አደጋ ለማስወገድ የሚከፈለዉን ማንኛዉንም መስዋዕትነት በመክፈል ትግሉን በድል ለማጠናቀቅ ቃል በመግባትም ጭምር ነው።
እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ____ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ____ የስቅለት በዓል የሚያስተምረን ጽናትና ለዓላማ መሞት ያለውን ትልቅ ትርጉም ነው። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እውነትና ስለ ሰው ልጆች ፍቅር ሲል እስከ ቀራንዮ እንደተጓዘ ሁሉ፣ የአማራን ህዝብ ክብርና ህልውና ለማስጠበቅ የተጀመረው ጉዞ የተፀነሰው በመንገዳችን በድንገት በተቀላቀሉ እና እየወረዱ ባሉት ይሁዳዎች ሳይሆን ውድ ህይወታቸውን ለመክፈል በማይሰስቱ በቁርጠኛ ልጆቹ ልብ ያለ እስከ ቀራንዮ ለመጓዝ የተቆረጠ የማያወላውል ጉዞ ነው። ስቃይና መከራ ለክብር፣ ሞት ደግሞ ለትንሳኤ መንገድ እንደሆኑ ሁሉ፤ ዛሬ የምናልፍበት መከራና የምንከፍለው መሥዋዕትነትም ለታላቅ ድልና ለሕዝባችን ሰላም መሠረት መሆኑ አይቀሬ መሆኑን በመተማን ነው። የአፋብን አመራሮችና መላው የሰራዊት አባላትም ይህ ጉዞ የሕዝባችንን ነጻነትና ደህንነት እስኪያረጋግጥ ድረስ በፅናት እና በሙሉ ልብነት ለማስቀጠል በዚህ ለመላው የሰው ልጆች ሲባል ዋጋ በተከፈለበት ቀን በድጋሜ ቃል እንገባለን። በዓሉን ስናከብር ለአማራ ሕዝብ ህልውና ሲሉ ውድ ሕይወታቸውን የገበሩ ጀግኖቻችንን እና በየበረሃው ደማቸውን ያፈሰሱ ልጆቻችንን ቤተሰቦች በመጠየቅና በመደገፍ፣ በማንነታቸው ምክንያት ከቀያቸው ተፈናቅለው በችግርና በስደት የሚገኙ ወገኖቻችንን በማሰብ፣ "አማራነት ወንጀል" ተደርጎባቸውና በፖለቲካ አመለካከታቸው ምክንያት በየእስር ቤቱ የሚማቅቁ የሕዝብ ልጆችንና ቤተሰቦቻቸውን በማስታወስ፣ ድምፅ በመሆንና በመጠየቅ ከጎናቸው መሆናችንን በማሳየት እንዲሆን ጥሪ እናቀርባለን። በድጋሜ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል አደረሳችሁ! ሚያዝያ ፪ ቀን ፪፼፩፰ ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን)
без подписи
መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር የህክምና ባለሞያዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል። የምኒልክ ዕዝ ህክምና መምሪያን ጨምሮ በየ እዞቹ ባሉ ጤና መምሪያወች የህክምና አገልግሎት እየሰጡ ያሉ ታጋይ ሃኪሞችን ከትግሉ ጋር የሚያዋህዱ ሁለንተናዊ ስልጠናዎች ይሰጣሉ። እንዲሁም ከመጀመሪያ ህክምና እርዳታ እስከ ሌሎች ቀላልና መካከለኛ ቀዶ ጥገና ድረስ በሞያው ዘርፍ የካበተ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች የህክምና ሙያ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል:: በዚህም መሰረት የምኒልክ እዝ 101ኛ ኮር በቀድሞ ሰማዕቱ የ11ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ሻለቃ አርበኛ ሃኪም አድኖ ስጦታው በተሰየመ የስልጠና ፕሮግራም ታጋይ ሐኪሞችን አሰልጥኖ አስመርቋል። አስረስ ማረ ዳምጤ
በክብር የተሰው ጓዶችን አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ “ክብርና ሞገስ ለቅዱስ ዓላማ ለወደቁ ጀግኖቻችን!” አፋብን ደቡብ አማራ ቀጠና በአሳምነው ዕዝ፣ በአፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኮር ነጎድጓድ ክፍለ ጦር ውስጥ ትግላችን ዛሬ ላይ እንዲደርስ ለህዝባችሁ ህልውና መከበር በጀግንነት ከህዝባችሁ ጎን ተሰልፋችሁ ህይወታችሁን ለሰጣችሁ ውድ ጀግና ሰማዕቶች ለአርበኛ ይገረም ከበደ ፣ለአርበኛ ሱራፌል ገብረሃና እና ለአርበኛ ሙሴ እሸቴ ለህዝባቸው የከፈሉት መስዕዋትነት ጥልቅ መሆኑን እንገልጻለን። ትግሉ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ በማደራጀት እና በማሰልጠን እንድሁም ከፊት ሆኖ በመምራት በሸዋ ተራሮችና ሸጦች የጠላትን ሀይል መውጫ መግቢያ በማሳጣት ሲፈፅሙት የነበረው አኩሪ ስራ ህያው ምስክር ሆኖ በታሪክ መፅሃፍት ሲከተብ ይኖራል። ጀግኖቻችን፤ እናንተ የታሪክ አደራን ተሸክማችሁ፣ በቆራጥነትና በፅናት ዋጋ የከፈላችሁት ለነገው ብሩህ ተስፋና ለህዝባችን ህልውና በማፅናት ሰላም ማስፈን ነው። የእናንተ መስዋዕትነት በታሪክ መዝገብ ላይ በወርቅ ቀለም ተጽፎ የሚኖር ሲሆን፣ የጀመራችሁት የትግል ጉዞ (ዓላማ) በሁላችንም ልብ ውስጥ ሲዘከር ይኖራል። በቀን 21 /07/2018 ዓ.ም ከጠላት ሀይል ጋር በነበረ ከባድ ትንቅንቅ ብዙ የአገዛዙን ሀይል ሲተናነቁ አርፍደው የሚተማመኑት እና ቃል የተገባቡት ጀግኖች ታሪክ ማህደር ውስጥ ደምቀው የሚታዩት ገጾች በብዕር ብቻ ሳይሆን፣ በቆራጥ ልጆች ደምና አጥንት የተጻፉ ናቸው እና የህልውና ትግል አማራጭ የሌለው፣ "ለመኖር መዋጋት" የሚሰኝ የሞትና የሽረት ፍልሚያ በመሆኑ ይህን መርጠው ጀግኖቹ የአገዛዙን ሰራዊት አርግፈውት የመጨረሻውን ምርጫ የአባታችንን አፄ ቴወድሮስን የጀግንነት መንገድ ተከትለዋል ። በዚህ ፍልሚያ ውስጥ የተፈጸሙ ጀብዱዎች ደግሞ ተራ ድርጊቶች ሳይሆኑ፣ ከራስ በላይ ለሆነ ዓላማ (ለህዝብ ፣ ለትውልድና ለህልውና) በመታመን የተከፈሉ የክብር ዋጋዎች ናቸው። የተከፈለውም መስዋዕትነት ከራስ በላይ ለጓዶች ለሌሎች ህይወት ሲባል የራስን ህይወት አሳልፎ መስጠት እና ለህዝብ ቅድሚያ በመስጠት ከፍተኛው የፍቅር ማሳያ ሆኖ ተመዝግቧል ። በዚህ ህልውና ትግል ውስጥ የወደቁት ጀግኖች "እኔ ባልኖርም ህዝቤ መኖር አለባት" የሚል ጥልቅ እምነት ያላቸው ጀግኖቹ የነበራቸው ዕምነት ለህዝብ መሰዋት ሞት ሳይሆን፣በታሪክ ውስጥ ዘላለም መኖር ነው የሚሉ ተሰውተው ያሳዩ ናቸው። የእነሱ ድፍረት እኛን ያነሳል፤ የእነሱ ተስፋ ወደፊት እንድንመራ ይረዳናል፤ የእነሱ መስዋዕት ደግሞ በእርምጃ እንድንመልስ ያደርገናል። ጀግኖች ቢሰዉም፣ የከፈሉት መስዋዕትነት ግን የነፃነት ችቦ ሆኖ ይበራል። የእነርሱ ደም የነፃነትን ምድር ያጠጣል። የሚቀጥለው ትውልድ በሰላም እንዲኖርና አንገቱን ቀና አድርጎ እንዲሄድ መሰረት የሚጥሉት እነዚህ ታላላቅ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው። ለተሰውት ጀግኖች ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶችና ለመላው የኮሩ እና የክፍለ ጦሩ አመራርና አባላት መጽናናትን እንመኛለን። ''ክብር ለተሰውት '' አፋብን ደአቀ (አሳምነው ዕዝ) ቀን 22/07/ 2018 ዓ.ም
без подписи
መብረቅ ክፍለ ጦር ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ምልምል ፋኖዎች አስመረቀ! ምኒልክ ዕዝ ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር ለወራቶች ያሰለጠናቸውን ምልምል ፋኖዎች አስመረቀ:: ከአፋብን ምኒልክ ዕዝ ስልጠና መምሪያ በወረደላቸው አቅጣጫ መሰረት ኮርና ክፍለ ጦሮች ምልመላ በማካሄድና ስልጠና በመስጠት ራሳቸውን በሰው ሃይል በማደራጀትና በማጠናከር ላይ ይገኛሉ:: በዚህም ንጉስ ሚካኤል አሊ ኮር መብረቅ ክፍለ ጦር የመለመላቸውን ወጣቶች ለወራቶች ስልጠና በመስጠት አስመርቋል:: በቀጣይም ስልጠናው ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አመራሮች ገልፀዋል:: መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ መጋቢት 11/2018 ዓ.ም
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለኢድ አልፈጥር አደረሳችሁ !! መልካም በዓል !!
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ መጋቢት 10 ቀን 2018 ዓ.ም የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች እንኳን ለኢድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል። በተለይም ስለ ሕዝባችሁ ነፃነት ስትሉ ለነፍሳችሁ ሳትሳሱ በዱር በገደሉ እየተዋደቃችሁ ከምትከፍሉት መራር ዋጋ ጎን ለጎን ይህን ታላቁን የረመዳን ወር በፆምና በጸሎት ያሳለፋችሁ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ አመራሮች እና አባላት እንዲሁም ደጋፊዎቻችን ከፈጣሪ ዘንድ እዝነትና በረከት ለሚታደልበት የኢድ አልፈጥር በዓል እንኳን አደረሳችሁ። የአማራ ሕዝብ ላለፉት በርካታ አሥርት ዓመታት ከደረሰበትና አሁንም እየተፈጸመበት ካለው መንግሥት-መር የጅምላ እልቂትና ጭፍጨፋ እንዲሁም የሀብትና ንብረት ውድመት ውስጥ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዩ ወገናችን ከፊት ተሰላፊ ነው። ወገኖቻችን በክልሉ ውስጥና ከክልሉ ውጭ አማራ-ጠል እሳቤ ባነገቡ ቡድኖችና የጸረ-አማራነት ትርክትን ሥጋ አልብሶ በሚንቀሳቀሰው አገዛዝ በሚፈጸምባቸው ጭፍጨፋ በርካቶች ሕይወታቸው ተቀጥፏል፣ ሀብትና ንብረታቸው ወድሞ ለከባድ ማኅበራዊ ምስቅልቅል ተዳርገዋል። በዚህ ጸረ-አማራ እሳቤ በሚመራው ሥርዓት የሚፈጸመው ሁሉን አቀፍ ጥቃት ተባብሶ በመቀጠሉ ዛሬም በሞት አፋፍ የሚገኙ ወገኖቻችን እልፍ ናቸው። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች ከተፈጸመባቸው ጭፍጨፋ እንደ እድል ተርፈው፡ ሀብትና ንብረታቸው ወድሞ ከቀያቸው ተፈናቅለው በመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ፡ ከሞት ያልተናነሰ ኑሮን እያሳለፉ ይገኛሉ። ወገናችን በዚህ መከራ ውስጥ ሆኖም ታላቁን የረመዳን ወር በፆምና በዱዓ በማሳለፍ የጽናት ተምሳሌትነቱን እያሳየ ነው። በመከራ ውስጥ ሆኖም ለፈጣሪው መገዛትን፣ ጽናትን፣ አሸናፊነትን፣ ትዕግሥትንና ጥበበኝነትን ከወለደው ሕዝብ የወረሰው የአማራ ፋኖ፡ በአማራ ሕዝብ ላይ የተጫነውን የመከራ ቀንበር ይሰብር ዘንድ ሐቅን ከነፍጥ ጋር አንግቦ በድሉ ዋዜማ ላይ ይገኛል። የአማራ ፋኖ እያደረገ ባለው ትግል ሞታቸውን በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ ወገኖቻችንን ታድጎ ሕልውናቸውን ማስከበር፣ ለተፈፀመው እልቂትና በደል ፍትሕና ርትዕ ማስፈን፣ እንዲሁም ወገኖቻችን በገዛ አገራቸው በነፃነት ተንቀሳቅሰው ሀብትና ንብረት ማፍራት የሚችሉበትን ሥርዓት ማንበር፡ የትግላችን ቀዳሚ ዓላማና ከምንም በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ግባችን ነው። ለዚህ ታላቅ ዓላማ ስኬት ሕዝባችን፡ በተለይም ሕዝበ ሙስሊሙ፡ ትግሉን በባለቤትነት ከመምራት፣ ከመታገል ጀምሮ ስንቅና ትጥቅ በማቅረብ፣ የሐሳብና የመረጃ እገዛ በማድረግ እንዲሁም በዱዓ በመርዳት ረገድ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል። ቅዱስ ቁርኣን "እናንተ ያመናችሁ ሆይ፡ በትዕግሥትና በሶላት ታገዙ፡ አላህ በእርግጥ ከታጋሾች ጋር ነውና" ("ያ አዩሀለዚነ አመኑ ስተዒኑ ቢሷብሪ ወሷላህ፣ ኢን-አላሀ መዐ-ሷቢሪን") ሲል ያስተምራል። በእርግጥም ሐቅን ከነፍጥ ጋር ያነገበው የሕልውና ትግላችን፣ በሙስሊሙ ማኅበረሰብ ንቁ ተሳትፎ ዛሬ በድሉ አጥቢያ ላይ ደርሷል። ነገ የህልውናን ትግላችን በነፃነታችን ሲረጋገጥ በዓሉን በሚመጥን ሁኔታ በአደባባዮቻችን እስከምናከብር በዚህ መከራ ውስጥ ሁናችሁ እያከበራችሁ ያላችሁ ህዝባችን እና ሰራዊታችን ድርጅታችን አፋብን መልካም በዓል እንዲሆንላችሁ ይመኛል። በድጋሚ እንኳን ለ1447ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ኢድ-ሙባረክ! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ!
"በዚህ ወቅት በምርጫ የሚፈታ የኢትዮጵያ ሕዝብ ችግር የለም። አጠቃላይ ሁሉን አቀፍ የሽግግር ሂደት ያስፈልጋል!" "ለውጥ ያመጣል ብለው በምርጫ የሚሳተፉትን አልቃወምም። ራሳቸውን ለመከላከል በትጥቅ ትግል ውስጥ ያሉትንም አልቃወምም። ነገር ግን አገዛዙ ምን ያህል በሕዝብ እንደተጠላ በተጨባጭ የሰልፍ ተቃውሞ ማሳየት ከተቻለ፣ ዓለም ከጎናችን እንደሚቆም እርግጠኛ ሆኜ እናገራለሁ። ሁሉም ያግዘናል። ቁጭ ብለን ማውራት ብቻ ከሆነ ሁሉም ይንቀናል። በሠላማዊ ተቃውሞ በአጭር ጊዜ አገዛዙን ለማንበርከክ ዝግጁ ሆነን መጠባበቅ አለብን!" "ሰሜኖች እና ደቡቦች ብሎ የኢትዮጵያን ሕዝብ በአቅጣጫ መከፋፈል የጀመሩት ራሳቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ናቸው። በሐይማኖት፣ በዘርና በፖለቲካ ሕዝብን መከፋፈሉ አልሠራ ሲላቸው፣ አሁን ደሞ በአቅጣጫ ለመከፋፈል ተነሱ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህንን ተንኮል አውቆ አቅጣጫ ሳይገድበው በአንድነት ተነስቶ አገዛዙን ሊታገል ይገባል!" — አቶ ልደቱ አያሌው፣ የሚዲያ መግለጫ
ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምስ/አማራ ቀጠና - ምኒልክ ዕዝ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ የተሰጠ ጥብቅ ማስጠንቀቂያ በማንነትና ወሰን ጥያቄያችን ሽፋን የብልፅግናን ስርዓት ለመጠበቅ በራያ ቆቦ ለተሰበሰባችሁ ለራያ አላማጣ: ባላና ኮረም-ወፍላ የስርዓቱ ታጣቂዎችና ምልምል ሰልጣኞችን በሙሉ! የአማራ ህዝብ ከሩብ ክፍለ ዘመን በላይ አጀንዳ አድርጎ የታገለባቸው የማንነትና የርስት ጥያቄ ዛሬም ግንባር ቀደም ጥያቄና የመታገያ አጀንዳችን መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን 2010 ዓ.ም በለውጥ ስም ከመጣው አብይ አህመድና የብልፅግና አገዛዝ ማግስት ጀምሮ ግን የአማራ ህዝብ ጥያቄ ከማንነትና ከርስት ተሻግሮ የህልውና መሆኑን አደጋው ላይ ያለው ህዝባችንና በርካታ ኢትዮጵያውያን የተስማሙበት ጉዳይ ነው:: ለአማራ ህዝብ የአገራችን ኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታና ሐቁ ይህ ሆኖ እያለ በተጠቀሱት የራያ አካባቢዎች ተወላጅ የሆናችሁ የአማራ ልጆች ከአብይ አህመድና ፓርቲው ብልፅግና ጋር ሆናችሁ የምታመጡት አንዳች ውጤት እንደሌለና ወቅቱን የዋጀ ትግል አድርጋችሁ ዘላለማዊ ነፃነት የምትጎናፀፉት በፋኖ ትግልና መንገድ ብቻ እንደሆነ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን! አብይ አህመድ የራያን ህዝብ ጥያቄ "ካርድ" ዛሬም አንድና ያው በሆነው በአማራ እና በትግራይ ህዝብ መካከል ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዲካሄድና እንዲቀጥል በሂደቱም ስልጣኑን ማራዘም ከቻለም ማፅናት እንጂ ሌላ ዘላቂ መፍትሔ እንዲመጣ እንደማይፈልግ ተደጋጋሚ በተግባር የታየ ሲሆን እኛም እንደ ፋኖ ከአብይ አህመድ የምንጠብቀው መፍትሔ የሚወስንልን እጣ ፈንታም እንደሌለ ልናሳውቃችሁ እንወዳለን! ስለሆነም ይህንን ሐቅና እውነታ ወደ ጎን በመተው ከብልፅግና ጎን ተሰልፈው በራያ ህዝብ ስም በሚነግዱ የደም ነጋዴ አመራሮች እየተመራችሁ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ተታላችሁ በብልፅግና ተደራጅታችሁና ታጥቃችሁ ለውጥ እናመጣለን በሚል ከጨፍጫፊው አገዛዝ ጎን ተሰልፋችሁ ፋኖን ለመውጋት ያሰባችሁ የአካባቢው ተወላጆች ከአድማ ብተናና ሚሊሻ ለይተን እንደማናያችሁ አውቃችሁና የያዛችሁት መንገድ የተሳሳተ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ ስንል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መልክታችንን እናስተላልፋለን! በመጨረሻም በገዳዩ የብልፅግና አገዛዝ ላይ ሰይፍ ማንሳት ሲገባችሁ ሠላሳ ዓመት የተሻገረ ሰልፍን መርጣችሁ በተለያዩ ሰብአዊነት በማይከበርባቸው የመጠለያ ጣቢያዎች እና ከተሞች የተቀመጣችሁ የአካባቢው ተወላጅ ወጣቶች የአማራ ፋኖን በመቀላቀል ትግላችሁን እንድትታገሉ: ነፃነታችሁን በትግላችሁ እንድትጎናፀፉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!!! መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልዉና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን! አፋብን ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የካቲት 30/2018 ዓ.ም
ይሄው ነው!! አባት ሃገር ሸዋ!!
ሰበር የድምሰሳ ዜና !! የካቲት 27/06/18! ዓ.ም አፋብን ቴ/ዕዝ 102ኛ ኮር 11ኛ ክ/ጦር እና 22ኛ ክ/ጦር በጥምረት በመልሶ-ማጥቃት በሜጫ ቀጠና በተለያዩ ግንባሮች ኮሩ ድል ተቀዳጅቷል!! ጠላት ከተለያዩ አጎራባች ወረዳዎች ጭምር ከትናት ምሽት ጀምሮ ያለዉን ሐይል እና ትጥቅ በማቀናጀት ወደ ሜጫ ቀጠና በማንቀሳቀስ የማጥቃት ዘመቻ በዛሬዉ ዕለት አድርጎል። በቀጠናዉን ላይ ያለዉን የወገን ሐይል ሙሉ ለሙሉ ለመደምሰስ እልህ አስጨራሽ ፍልሚያ በተለይም አማሪት ቀጠና ላይ ያደረገ ሲሆን ዉጊያን እንደ ቼዝ የሚጨዋቱት የአበረ ይማም ልጆች በጠላት የዉጊያ ዕቅድ ዉስጥ ገብተዉ እንደ ሰደድ እሳት ጠላት ለብልበዉታል። ጠላት እንደ ፈረስ እየጋለበ ቢገባም እንደ ኤሊ እያዘገመ በእጀ እየተጨበጠ ተማርኮል። በዕለቱ የተገኙ ምርኮዎች:-. 1/ የተደመሰ ጠላት---97 2/ የተማረከ ጠላት----35 3/ 52 ክላሽንኮቭ 4/ ብሬን----01 5/ አይኮም ሬዲዮን---02 6/ የክላሽ ተተኳሽ----2510 7/ የብሬን ተተኳሽ----520 ኮሩ በዕለቱ የተመዘገበዉ ድል በአማራ ህዝብ የትግል ታሪክ ዉስጥ በፊት ዓዉራሪነት ለሚወሳዉ ለአርበኛ መዝገቡ ዋለልኝ መታዋሻ ይሁልኝ ብሏል። ክፋት ለማንም፣በጎነት ለሁሉም!! አዲስ ትዉልድ፣አዲስ አስተሳሰብ፣አዲስ ተስፋ!! የአፋብን ቴዎድሮስ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት
ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለ ጦር [ የካቲት 17/2018ዓ.ም] የአቢይ አሕመድ ጥምር አራዊት ሰራዊትን ከደብረ ታቦር ከተማ በቅርብ ርቀት ከፀጉር ኪዳነ ምሕረት እሥከ ኮካ፣ ከቆለይ እሥከ ዓለም ሳጋ፣ ከእንቁርቁባ እሥከ ተንሸራታች ድረሥ በደምብ ገርፈውታል። ውጊያው ከመጀመሩ ጠላት የዓምሐራ ፋኖን ክንድ መቋቋም ተሥኖት አድማ ብተናዎች ተደምሥሠዋል፣ ተማርከዋል፣ ትራፊክ ፖሊሥ እሥከ ወድያኛው ተሸኝቷል፣ ሚሊሺያ ተሸኝቷል፣ የአቢይ መከላከያ ተማርኳል ተደምስሷል። ጠላት የመዋጋት ሞራሉ ደቅቆ እየተንጠባጠበ ወደ ደብረ ታቦር ከተማ እየፈረጠጠ ይገኛል። ብርቱ ምት ከዓምሐራ ፋኖ የገጠመው አራዊት ሰራዊትም በበቀልና በአጥፊነት ግብሩ 03 ንጹሐን የከተማው ነዋሪዎችን በጭካኔ በጥይት መትቷቸዋል። የተመቱት ንጹሐን 02ቱ ሴቶች ሲሆኑ 01ዱ ደግሞ ወንድ ነው። ተሥፋ የቆረጠ አገዛዝ ከዚህ የበለጠ ጭካኔውን በንጹሐን ላይ እንደሚያሳርፍ ሕዝቡ አውቆ አውሬውን አገዛዝ ወግድ ማለት ምርጫው ሳይሆን ግዴታው ነው። ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን🔑✊ ዝንተዓለም ዓምሐራ Forever AMHARA🔑✊ ፩ ዓምሐራ🔑 አፋብን ሰ/አ/ቀ በላይ ዕዝ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ፩ኛ ኮር ሕ/ግ ክፍል ፋኖ ኃቅ-ዓለው ፀጋ አለባቸው ቋሚ ምሥል፦ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክ/ጦር ሥራ አሥፈጻሚ በከፊል
ጥር 10 ቀን 2018 ዓ.ም የከተራ እና ጥምቀት በዓልን አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እንኳን ለ2018 የከተራ እና ጥምቀት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ይላል። የድርጅታችንን መመስረት ተከትሎ ሰራዊታችን፣ መላው የአማራ ህዝብ፣ የዳያስፖራው ማህበረሰብ እና የትግሉ ደጋፊወች በከፍተኛ ስሜት እና ደስታ መቀበላቸውን ስናረጋግጥ ከፍተኛ ኩራት ይሰማናል። በአንድነታችን ከፍተኛ ልባዊ ደስታን የተጎናፀፈው ሰራዊት እና ህዝብ የድሉን ፅዋ ያነሳ ዘንድ የጠላትን አከርካሪ መስበር የሚችል ስልታዊ አመራር ለመስጠት መዘጋጅታችንን በዚህ አጋጣሚ እናረጋግጣለን። የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የሀገራችን ባህል እና ትውፊት እንዲጠበቅ እና ሁሉም ኢትዮጵያዊ ባህሉን እና እምነቱን በነፃነት የሚያራምድበት ሀገር እንዲኖረን የጀመረውን ፀረ አገዛዝ ተጋድሎ በአዲስ መንፈስ አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም በዚህ አጋጣሚ እንገልፃለን። መላው ሰራዊታችን እና አመራሩ በተቆጣጠርናቸው አካባቢዎች ሁሉ በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከህብረተሰቡ ጋር በትብብር እንድትሰሩ እናሳስባለን። በድጋሚ መልካም የከተራ እና የጥምቀት በዓል! የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи