"ወደ ጌታህም ብቻ ከጅል"{وإلى ربك فارغب}✍🏻𝐬𝐮𝐦𝐞𝐲𝐚
Статистика«ይህች መንገዴ ናት።ወደ አላህ እጠራለሁ።እኔም የተከተለኝም ሰው በግልፅ ማስረጃ ላይ ነን።ጥራትም ለአላህ ይገባው።እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም»በል። ሱረቱ ዩሱፍ 108 ~~~~~~~~~~~~~~ ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያዬት 👇👇👇👇👇👇👇👇👇 @Hamden_Lilah
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 5
- Всего постов
- 25
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 38
- 1/48двое суток
- 43
- 1/72трое суток
- 46
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ፈጥኖ ማን ይመልስ ! ✈️✈️ ትክክለኛውን መልስ ያገኝ ሰው add የሚለውን በመጫን ስጦታ ያገኛል። 📝 ጥያቄ ጂብሪል ዐለይሂ ሰላም ስንት ክንፎች አሉት ?
ዒልም ሁለት ነው ዒልመ ሰጠር ወዒልመ ሰደር! ዒልመ ሰጠር በግርድፉ ሲተረጎም ከወረቀት፣ ከኪታብ የሚገኘው ነው። ይህ አስፈላጊ ዒልም ሲኾን በስፋት ሰዎች ለፍተው ለማግኘት የሚጥሩበት ነው። ሌላው «ሚን ዱኒይ» የሚባለውና እጅግም የረቀቀው የዒልም ዓይነት ዒልመ ሰደር (የልብ ዕውቀት) የሚባለው ነው። ይህ የዒልም ዐይነት ረቂቅ ነው። አላህ ለባሮቹ በተለያየ መንገድ የሚለግሳቸው ነው። ዘውቅም፣ ኢማንም ያለበት ነው። ኸድርና ሙሳን አስታውሱ። የኸድር ዒልም ዒልመ ሰደር ነው። ይህ በቁርኣን የተላቀው አገላለጽ ነው። የቁርኣንና የሐዲሶች ትምህርቶች፣ የተለያዩ ንባቦች ዓላማው ወደዚህ ረቂቅ ዐለም መሻገር ነው። ይህ መንገድ ግልጹ የሸሪዓ መንገድ ነው። የትኛውም ዒልም በመንፈሳዊነት በሰለዋት፣ በዚክር፣ በቁርኣን ቲላዋ ካልተገራ ዕውቀት በራሱ ብቻውን ድርቀትንና ጥመትን ይፈጥራል። ዒልም ስንጨምር በአምልኮና በመንፈሳዊነት ተግባራት ላይ መጨመርን ካላሳየን በጣም ከባድ የኾነ አውቆ የማጥፋት ስሜት ውስጥ እንዘልቃለን። ለዚህም ነው ዑለሞች በሰለዋትና በዚክር ዊርድ ላይ መቆየት የዒልመ ሰደር በረካን በሕይወት እንደምናገኝ የሚመክሩን።
𝐆𝐀𝐀𝐅𝐅𝐈𝐈 𝐇𝐈𝐑𝐌𝐀𝐀𝐂𝐇𝐈𝐒𝐀𝐀! 💡 𝐄𝐫𝐠𝐚𝐦𝐚𝐚𝐧 𝐑𝐚𝐛𝐛𝐢𝐢 (𝐒.𝐀.𝐖) 𝐥𝐚𝐛𝐬𝐚 "𝐁𝐚𝐫𝐚 𝐤𝐚𝐧𝐚 𝐛𝐨𝐨𝐝𝐚 𝐦𝐮𝐬𝐡𝐫𝐢𝐤𝐧𝐢 𝐇𝐚𝐣𝐣𝐢𝐢 𝐡𝐢𝐧 𝐠𝐨𝐝𝐡𝐮, 𝐊𝐚'𝐚𝐛𝐚𝐚𝐬 𝐪𝐮𝐥𝐥𝐚𝐚𝐧 𝐡𝐢𝐧 𝐭𝐚𝐰𝐰𝐚𝐟𝐮" 𝐣𝐞𝐝𝐡𝐮 𝐮𝐮𝐦𝐦𝐚𝐭𝐚 𝐝𝐮𝐫𝐚𝐭𝐭𝐢 𝐚𝐤𝐤𝐚 𝐥𝐚𝐛𝐬𝐮𝐮𝐟 𝐞𝐞𝐧𝐲𝐮𝐮𝐧 𝐠𝐚𝐫𝐚 𝐌𝐚𝐤𝐤𝐚𝐚𝐭𝐭𝐢 𝐞𝐫𝐠𝐚𝐧? Add My Channel👇 @Rafiiqul_Islaam @Rafiiqul_Islaam
𝙲𝙷𝙰𝙽𝙽𝙴𝙻 𝙱𝙰𝚁𝚂𝙸𝙸𝚂𝙾𝙾 𝙵𝙸 𝙱𝙰𝚂𝙷𝙰𝙽𝙽𝙰𝙽𝚂𝙸𝙸𝚂𝙾𝙾 𝚃𝙰'𝙰𝙽 𝙰𝚁𝙶𝙰𝙲𝙷𝚄𝚄𝙵 𝙼𝙰𝙻𝙻𝙰𝚃𝚃𝙾𝙾 𝙼𝙰𝙶𝙰𝚁𝙸𝙸𝚂𝙰𝙰 𝙲𝚄𝚀𝙰𝙰𝚂𝚄𝚄𝙳𝙷𝙰𝙰𝙽 𝚂𝙴𝙴𝙽𝙰𝙰! 🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩 🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩 🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩 🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩 🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩🟩 𝑻𝑯𝑰𝑺 𝑰𝑺 𝑯𝑶𝑷𝑬 𝑷𝑹𝑶𝑴𝑶𝑻𝑰𝑶𝑵 𝑨𝑫𝑽𝑬𝑹𝑻𝑰𝑺𝑰𝑵𝑮 𝑻𝑬𝑳𝑬𝑮𝑹𝑨𝑴 𝑪𝑯𝑨𝑵𝑵𝑬𝑳𝑺/𝑮𝑹𝑶𝑼𝑷𝑺 Add: 👇👇 @Rafiiqul_Islaam @Rafiqul_Islam_Promotion ➕ @Rafiqul_Islaam ➕
ማን ቀድሞ ይመልስ ! 🚀🚀 ትክክለኛውን መልስ የመለሰ add የሚለውን በመጫን ጠቃሚ ነገር ያገኛል ! ጥያቄ 👉 በቁርኣን ውስጥ ረጅሙ ሱራ (ምዕራፍ) ማን ይባላል?
𝑪𝑯𝑨𝑵𝑵𝑬𝑳 𝑨𝑲𝑲𝑨𝑴𝑰𝑰 𝑩𝑨𝑹𝑩𝑨𝑨𝑫𝑫𝑼⁉️ 𝑾𝑯𝑨𝑻 𝑪𝑯𝑨𝑵𝑵𝑬𝑳 𝑫𝑶 𝑻𝑯𝑬𝒀 𝑾𝑨𝑵𝑻⁉️ Channel/Group 20K+ 𝐒𝐮𝐛𝐬𝐜𝐫𝐢𝐛𝐞𝐫𝐬 𝐅𝐫𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐨𝐦𝐨𝐭𝐞𝒓: @Rafiqul_Islaam Adds:👇👇👇 My Channel @Rafiiqul_Islaam HP: @Rafiqul_Islam_Promotion
"ከሰው ሁሉ ይበልጥ ጀግናው ማነው?" — የአሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ ምስክርነት ታላቁ ሰሐባ አሊይ ኢብኑ አቢ ጣሊብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በአንድ ወቅት አብረዋቸው ለነበሩ ሰዎች ጥያቄ አቀረቡ፦ "ከሰው ሁሉ ይበልጥ ጀግናው ማነው?" አሏቸው። ሰዎቹም፦ "ጀግናውማ አንተ ነህ!" ብለው መለሱለት። አሊይም እንዲህ አሉ፦ "እኔማ ከማንም ጋር ለፍልሚያ (ሜዳ ላይ) ወጥቼ እኩል ሳልካካስ የቀረሁበት (ያላሸነፍኩበት) ጊዜ የለም። ነገር ግን እውነተኛውን ጀግና ንገሩኝ?" አሏቸው። ሰዎቹም፦ "አናውቅም፣ ማነው?" ሲሉ ጠየቁ። አሊይ እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ "እሱማ አቡ በክር ነው አሉ!" ቀጥለውም ምክንያቱን እንዲህ አስረዱ፦ "በበድር ጦርነት ወቅት ለአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መጠለያ ሰራንና፦ 'ከአጋሪዎች (ሙሽሪኮች) ጥቃት እንዲከላከልላቸውና ማንም እንዳይደፍራቸው ከመልእክተኛው ጋር የሚቆየው ማነው?' አልን። በአላህ እምላለሁ! ማንም ወደ እሳቸው ሳይቀርብ አቡ በክር ሰይፉን መዝዞ በመልእክተኛው ራስ ላይ ዘብ ቆመ። ሊጠጋቸው የሞከረውን ሁሉ እየተከላከለ ማንም እንዳይቀርባቸው አደረገ። ስለዚህ እሱ ከሁሉ በላይ ጀግና ነው።" አሊይ ንግግራቸውን በመቀጠል ሌላም ታሪክ አወሱ፦ "የአላህ መልእክተኛን (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ቁረይሾች ሲያዳፏቸው፣ ሲያጎሳቁሏቸውና 'አማልክትን ሁሉ አንድ አምላክ ያደረግከው አንተ ነህ?' እያሉ ሲያዋክቧቸው አየሁ። በአላህ እምላለሁ! በዚያ አስፈሪ ሰዓት አቡ በክር ብቻ ነው ወደ መካከላቸው ዘልቆ በመግባት ይህንንም ሲመታ፣ ያንንም ሲገፋና ሲያባርር ያየሁት፦ 'ወዮላችሁ! ጌታዬ አላህ ነው ስላለ ብቻ ሰውን ትገድላላችሁ?' እያለ የተከላከለላቸው።" ከዚህ በኋላ አሊይ የለበሱትን ካባ ከፍ አደረጉና ፂማቸው በዕንባ እስኪረስ ድረስ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ። በመቀጠልም በዚያ ለነበሩት ሰዎች እንዲህ የሚል ጥያቄ ሰነዘሩ፦ "በአላህ ይሁንባችሁ ንገሩኝ፤ በቁርአን የተወደሰው የፈርዖን ቤተሰብ የሆነው አማኝ (ሙእሚን ) ይበልጣል ወይስ አቡ በክር?" ሰዎቹ ሁሉ ዝም አሉ። አሊይም፦ "አትመልሱልኝም?" አሉና ራሳቸው እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ "በአላህ እምላለሁ! ከአቡ በክር አንዲት ሰዓት ከፈርዖን ቤተሰብ አማኝ ሺህ ሰዓታት ትበልጣለች። ምክንያቱም ያኛው ሰው (የፈርዖን ዘመድ) እምነቱን ይደብቅ ነበር፤ አቡ በክር ግን (ህይወቱን ለሰይፍ አሳልፎ በመስጠት) እምነቱን ለዓለም ይፋ ያደረገ ጀግና ነው።"በማለት የአቡ በክርን ጀግንነት መሰከሩ። ምንጭ፦ *ሙስነድ አል-በዛር / ታሪኽ አል-ኹለፋእ (ለኢማም አስ-ሱዩጢ)*
ነብዩ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፡- “የፈለግከውን ያክል ብትኖር ትሞታለህ! የፈለግከውን ብትወድ ትለየዋለህ! የፈለግከውን ስራ ዋጋውን ታገኛለህ! እወቅ! የሙእሚን ክብሩ የሌሊት ሰላት መስገዱ፣ የበላይነቱም ከሰዎች መብቃቃቱ ነው፡፡” (ሐኪም ዘግበውታል፡፡ አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል)
መዲና እንደ ወናፍ ናት! አንድ ሰው ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) ዘንድ መጣና እስልምናን በመቀበል ላይ ቃል ገባላቸው፡፡ በነጋታው ደግሞ ተመልሶ መጣ። ወባ ይዞት እየተንዘፈዘፈ ነበር። ለነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ.) “ለርስዎ በገባሁት ቃል የተነሣ ነውና የታመምኩት ቃልኪዳኔን ይመልሱልኝና በፊት እንደነበርኩት ልሁን፡፡” አላቸው። ነቢዩም (ሰ.ዐ.ወ.) ሀሳቡን አልተቀበሉትም። ሰውዬውም መዲናን ለቆ ሄደ። ከዚያም ነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ.) እንዲህ አሉ፦ “መዲና እንደ ወናፍ ናት መጥፎነቷን ሁሉ ገፍትራ ታወጣለች፣ ጥሩነቷ ይቀራል።” (መዲና ከነቢዩ ዱዓ በኋላ ወባ ከውስጧ ተጠርጎ ወጣ።) አንዳንድ ሰው እንዲህ ነው፡፡ ... አላህን የሚያመልከው ቋፍ ላይ ሆኖ ነው። ችግር ሲያገኘው ይንሸራተታል፡፡ መልካም ሲገጥመው ይፀናል፡፡ እንደነርሱ አትሁን፡፡ አንዳንዶች በአምልኮ ላይ እያሉ ጭምር መፈተን መኖሩን አያውቁም። ከፍጥረቱ አንፃር የአላህን ፈለግ አይረዱም፡፡ አንዳንዶች አላህን የሚወዱት በሠጣቸው ልክ ነው። እነርሱ በሚጠሉት ነገር የፈተናቸው እንደሆነ ይርቁታል። አንዳንዶች ገንዘብ የተሠጣቸው እንደሆነ አብዝተው ያመሰግናሉ፤ ካጡ ደግሞ አምርረው ይጠላሉ፣ ይነጫነጫሉ፡፡ አንዳንዱ ሰው በወዳጆች መከበብ ደስ ይለዋል፣ በጣም ከሚወዳቸው መካከል አንዳቸውን በሞት ያጣ እንደሆነ ክፉኛ ይራገማል፣ ራሱንም ሆነ አምላኩንም ይጠላል፡፡ አንዳንዶች እኛ የሰው ልጆች የአላህ ባሮች መሆናችንን አይገነዘቡም፣ አገልጋይ ባሮቹ እንደሆንን አያስታውሱም፡፡ ባሮች ጌታቸው እንዳረጋቸው ነው የሚሆኑት፣ ለጌታ መልስ አይሠጠውም፣ ከአለቃ ጋር ክርክር አይገጠምም፡፡ የዱንያ ፈተና እንደሆነ ለአላህ ነቢያት ጭምር አልቀረም፡፡ ነቢዩ ዕቁብ በልጃቸው መጥፋት ምክንያት ለረጅም ዘመን ተክዘዋል፣ ነቢዩ ዩሱፍ ታስረዋል፣ ነቢዩ ዒሳ ደህይተዋል፣ ነቢዩ አዩብ ለዓመታት ታመው ከርመዋል፣ ነቢዩ ዩኑስ ተጨንቀዋል፣ ግራ ተጋብተዋል…. በሁሉም ላይ የአላህ እዝነትና ሰላም ይስፈን፡፡ ይህች ዓለም የፈተና ናት። በአላህ ፈቃድ - መገናኛችን ጀነት ነው
እዚህ ዱንያ ላይ ሁሉም ነገር ይተውሀል ወይ ደግሞ አንተ ትተወዋለህ ... ከ الله በስተቀር ...ወደሱ ከተቃረብክ ያብቃቃሃል ፤ ትተኸው ከሸሸህ ደግሞ ይጠራሃል.... Subhanelah
ብዙ ሴቶች በ ገንዘብ ምክንያት የተሳሳተ ትዳር ውስጥ ሲሆኑ፣ ብዙ ወንዶች ደግሞ በ ውበት ምክንያት የተሳሳተ ትዳር ውስጥ ናቸው!!!
📌 እድሜ ጊዜ ነው። ሰው ሞተ የሚባለውኮ ጊዜው ሲያልቅ ነው። ጊዜ ሲረዝም እድሜ ሲያልቅ ደግሞ ሞት ነው። ሞት መራራ ከሆነ ምነው የጊዜ መባከን ቢያንስ ሕመም አይሆንብንም? ሰው ቀጥሮህ ሲቀር ከእድሜህ እየቀነሰብህ ነው። 👉 የሆነ ሰው ያለ አግባብ የወሰደብህን ገንዘብ አንድ ቀን ሊመልስልህ ይችላል፤ የወሰደብህን ጊዜ ግን መቼም አይመልስልህም። አንድ ሊቅ እንዳለው "ለሰው የምትሰጠው ትልቁ ስጦታህ ጊዜ ነው።" እንዴት? ካልከኝ የሰጠኸው ጊዜ ከእድሜህ ላይ የተቀነሰ ነውና። ©
🫀 ቀልቡን ሰሊም 🕊 ግርግርና ጫጫታ በበዛበት ዓለም ውስጥ ትልቁ ስኬት የገንዘብ ክምችት ሳይሆን "የረጋ ልብ" ባለቤት መሆን ነው። ጌታችን አላህ (ﷻ) እንዲህ ይላል፦ يَوْمَ لَا يَنفَعُ مَالٌ وَلَا بَنُونَ إِلَّا مَنْ أَتَى اللَّهَ بِقَلْبٍ سَلِيمٍ "ገንዘብም ልጆችም በማይጠቅሙበት ቀን፤ ወደ አላህ በንጹህ (ጤናማ) ልብ የመጣ ሰው ቢሆን እንጂ። ተገላባባጭ ልባችንን ወደ ፀጥታ የምንመልሰው በምድራዊ ጫጫታ ሳይሆን አሏህን በመዘከር ነው። ልብ ልክ እንደ መስታወት ናት በወንጀል ትቆሽሻለች በዚክር ደግሞ ትወለወላለች። أَلَا بِذِكْرِ اللَّهِ تَطْمَئِنُّ الْقُلُوبُ "ንቁ! አላህን በማውሳት ልቦች ይረጋጋሉ።" ልብህ ከደከመች ወደ ጌታህ ዙር። እርሱ የተሰበረውን ልብ ይጠግናልና !!!
без подписи
2 ተኩላዎች አሉብኝ ይሽቀዳደሙብኛል‼️ 💡አንድ ወጣት ወደ አንድ ነገር አዋቂ ሽማግሌ ዘንድ ይሄድና እንዲህ ይላቸዋል፦ "ነፍሴ ውስጥ ሁለት ተኩላዎች አሉብኝ። ይሽቀዳደሙብኛል ፤ አንደኛው መልካም ነገር እንድሰራ ሲጎትተኝ ፤ ሌላኛው ደግሞ መጥፎ ነገር እንድሰራ ይጎትተኛል። ምን ተሻለኝ" ሲላቸው 👉"ይበልጥ የምትመግበው ተኩላ ነው ሊያሸንፍ የሚችለው። ስለዚህ መርጠህ ተንከባከብ።" አሉት 👉 እናማ መርጠን እንንከባከብ ለኢማን ግልፅ ቀመር አለ ፤ ኢማን በመልካም ስራ ይጨምራል በመወንጀል ደግሞ ይቀንሳል። 👉 በቃ ኢማንህ እንደቀነሰ ሲሰማህ ውዱዕ አድርግ ፣ የውዱዕ ሱና ስገድ ፣ የፈርድ ሰላት ሱናዎችን ቀጥል ፣ ከቁርዐን የገራልህን ያህል አንብብ ፣ ምላስህን በዚክር ሙላው ይህ ነው ኢማንን ከፍ የሚያደርገው ✨ አላህን በስንዝር ብትቀርብ እርሱ በክርን ይመጣሀልና ከቀለለህ ጀምረህ ኢማንህን አጠንክር ፤ ዒባዳ የሚከብደን ወንጀል ማብዛታችን ስለሆነ በቻልነው አቅም ከወንጀል እየተቆጠብን እስቲግፋርንም አንዘንጋ የሆነ ቀን ይህ አብዝተን የመገብነው ተኩላ ሀያል ሆኖ ማየታችን የማይቀር ነው
📌 ቀብር ውስጥ የምንመለከተው ስልክ ፤ አብሮን የሚገባ ቤተሰብ ፣ አሊያም የሚከተለን ጓደኛ የለም "ያኔ በጓደኛቸው ዘውትር የሚጎበኙትና የሚዘየሩት የቁርአን ጓደኞች ብቻ ናቸው ፤ ቁርአን ጓደኛውን አይረሳም! ቀብር ውስጥም ሆነ የቂያም ቀን ወዳጁን ለብቻውም አይተውም " ወላሂ በህይወት እያለ ቁርአንን ወዳጁ አድርጎ ለያዘ ሰው መልካም ይገባው! እሱ እድለኛ ነው
🔖 ኢብኑል ቀይም (ረሒመሁላህ) እንዲህ ይላሉ፦ "የሙእሚን ኃይሉ ከልቡ ይመነጫል።ልቡ በተጠናከረ መጠን ሰውነቱም ይጠነክራል። ፈጅር (አላህን የማይታዘዝ ሰው) ግን ምንም እንኳን በአካል ጠንካራ ቢሆንም፣ በችግርና በፈተና ጊዜ ከሁሉ ይልቅ ደካማ ይሆናል፤ በጣም በሚያስፈልገው ጊዜ የአካሉ ኃይል ይተወዋል። የፋርስና የሮም ንጉሣዊ ኃይሎችን አስተንትን፤ እጅግ ብርቱ ሠራዊትና አካላዊ ኃይል ነበራቸው፣ነገር ግን በጣም በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ያ ኃይል አልጠቀማቸውም። አላህም የኢማን ሰዎችን በልባቸው ጽናትና በአካላቸው ብርታት አጠንክሮ በእነርሱ ላይ ድል አጎናጸፋቸው።" • ابن القيم | الداء والدواء صـ (١٣٦).📚 =
ከህይወት ተስፋ የምንቀርጥበት ቀን ይመጣል ... ከዛም .. ሞት መጥቶ ልብሳችንን ሌላ ሰው ከኛ ላይ አውልቆት እርቃናችንን ያጥበናል ... ከዛም ጨለማው ቀብር አለ ..... ባለንበት ሁኔታ አሏህን መገናኘት አሳፋሪ ነውና ወደሱ እንመለስ ! https://t.me/MerkezulimamiAhmed
👉አጋጣሚ ረፍዶበት ለሱብሂ ሶላት መስጂድ ሳይደርስ ተሰግዶ ስላመለጠው ያለቀሰ..... እና 👉 የሚደግፈው የኳስ ቡድን ስለተሸነፈ የሚያለቅስ ወንድ፡- አይስተካከሉም፣እኩል አይሆኑም... ልዩነት ۗ قُلْ هَلْ يَسْتَوِي الَّذِينَ يَعْلَمُونَ وَالَّذِينَ لَا يَعْلَمُونَ ۗ إِنَّمَا يَتَذَكَّرُ أُولُو الْأَلْبَابِ سورة الزمر ٩ «እነዚያ የሚያውቁና እነዚያ የማያውቁ ይስተካከላሉን?» በላቸው፡፡ የሚገነዘቡት ባለ አእምሮዎቹ ብቻ ናቸው.
#የኔ እይታ ትናንት ሰወችን ከሀራም ሲከለክል እና ወደ ኸይር ሲ'ያመላክት የነበረ ሰው ዛሬ ወንጀል ላይ ወድቆ ስናየው ለምንድነው የምንደሰተው? ያኔ እየሰራን የነበረውን ወንጀል እንድናቆም ሲያስጠነቅቀን ከኛ የተሻለ እንደሆነ ተሰሞቶን ስለነበር እና አሁን ከፍታውን እኛ ለመውሰድ ስለምንፈልግ ይሆን? ወይስ ኢማን ቋሚ ነገር ስለሚመስለን? ልባችን ውስጥ ያለው ኢማን አንድ ቦታ ላይ ለደቂቃም ቢሆን ያለበት አይቆይም! ከፍ ወይ ዝቅ ይላል። ትናንት በጥሩ የኢማን ከፍታ ላይ ሁኖ ሰወችን ከመጥፎ ሲከለክል እና በኸይር ሲያዝ የነበረ ሰው ዛሬ ከነበረበት ከፍታ ተንሸራቶ ያንኑ አልያም ሌላ ወንጀል ሲሰራ ልታየው ትችላለህ። ያኔ ግን እኔን ሲመክር እንዳልነበረ ዛሬ እሱ ተገኘበት እያልን ከመጠቋቆም ይልቅ ወደነበረበት የኢማን ከፍታ እንዲመለስ ዱአ ማድረግ ግድ ይለናል። አስታውስ እስኪ.. ከአመታት በፊት ይቀፍህ የነበረ እና ዛሬ እንደቀላል የምትሰራው ሀጢያት የለም? ከዚህ በፊት ስትሰራው የነበረ እና ዛሬ በአላህ እገዛ ተውበት አድርገህ የተመለስክበት እና አሁን ስታስበው የሚያንገሸግሽህ ወንጀልስ የለም? ሰወች ከከፍታቸው ተንሸራተው ስናይ አላሁመ ያ ሙቀሊበል ቁሉብ ሰቢት ቀልቢ አላዲኒክ ከማለት ይልቅ መጠቋቆም የቀለለን እንዴት ይሆን?