የሕይወት ቃል
Статистика፯ ቁጥር ሰው የመሆን ሚስጥር መፍቻ ✔በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ 7 ቁጥር 735 ጊዜ የተጠቀሰ ሲሆን በዚህም ቻናል ጠቅለል ተደርጎ የሚዳሰስ እንዲሁም ኢትዮጵያና ሰባት ቁጥርን ከቀደምት አባቶቻችን እውቀት በመጨለፍ ምን እንደሚያገናኛቸው በስፋት የሚዳሰስበት በተጨማሪም ስለ አውሬው ቁጥር፣ስለ መናፍስቶች ድብቅ ሴራ የሚቀርብበት ቻናል በመሆኑ ይህን ቻናል በመቀላቀል በቂ ግንዛቤን ይያዙ !
- Последний пост
- 5 июн.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://youtu.be/k6KE-_OqIjo?si=_fQeSPdIP23S6mKc
ክፍል ስድስት በጸሎት ሰዓት ማዛጋት /ማዛጋት የአየር አጋንንት ብቻ ሳይሆን የጠቋርም ምልክት ነው/ share)በቀሲስ ሄኖክ ወ/ማርያም(share telegram link join t.me/abizeeotc ተወዳጆች ሆይ በክፍል አምስት በጸሎት ሰዓት በእንቅልፍ እና በመደበት እንዴት እንደሚፈትነን አይተናል፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ ስለ ማሳጋት ስናነሳ ማዛጋት ከመሰልቸት እና ከድካም እንደሚመጣ እና በተለይም የማይግሪን ቅድመ ማስጠንቀቂያ ምልክት እንደሆነ የሥጋ ጠቢባቡ ይናገራሉ፡፡ እኛ ግን ሲደክመን በነገሮች ስንሰላች የምናሳየው ማዛጋት ሳይሆን በጸሎት ሰዓት በልዩ ሁኔታ ስለምናዛጋው ነው፡፡ ወዳጆቼ ማዛጋት በጸሎት እና በቅዳሴ ሰዓት ላይ ጎልቶ ይታይብናል፡፡ በተለይ በጸሎት ሰዓት ደግሞ ይብስብናል፡፡ አንዳንዶች በግል፣ በቤተሰብ እና በማሕበር ጸሎት መካከል ያዛጋቸወዋል፡፡ ሌሎት በቅዳሴ መሐል ያዛጋቸዋል፡፡ በጸሎት ሰዓት የምናዛጋው ወይም የምናፋሽገው ውስጣችን ያለው አጋንንት ጸሎቱ ሲከብደው፣ በስውር ሲጨንቀው፣ አለሁ ሲለን የሚያሳየው ባሕርይ ነው፡፡ አንዳንዶች ማዛጋትን የርኩስ መንፈስ ውስጣችን የመኖሩ ምልክት አድርገው ላይቀበሉት ይችላሉ፡፡ ምክንያቱም ከላይ እንዳየነው ማዛጋት ከድካም፣ ከመሰልቸትና እንዲሁም ከለመድነው ሱስ መቋረጥ ጋር ስለሚገናኙት ነው፡፡ ለምሳሌ ቡና መጠጣት ያስለመድንበት ሰዓት ሲያልፍ ልናዛጋ ወይም ልናፋሽግ እንችላለን፡፡ ግን በጸሎት መሃል የምናዛጋው በፍጹም ከልማድና ከሱስ ጋር ይገናኝም፡፡ በነገራችን ላይ የቡና፣የጫት እና የሌሎችም ነገሮች ሱሰኞች ሆንን የሱስ ሰዓታችን ሲያልፍ የምናዛገው አምሮን ሳይሆን ያስለመደን አጋንንት ‹‹ሰዓቴ አልፏል ምሴን አምጣ›› እያለ እያዛጋ እየጠየቀን ነው፡፡ አንድም ሰዓቴ አልፏል እያለ እያስታወሰን ነው፡፡ እስኪ ልብ በሉ አንድ የጫት ሱሰኛ ለአንድ ሳምንት ጫት መቃሙን ቢተው በየሰዓቱ ነው የሚያዛገው፡፡ ግን አንድ ሰው ለአንድ ሳንምት እንጀራ ትቶ ሌላ ነገር ቢበላ እንጀራ ባለመብላቱ አያዛጋውም፡፡ ምናልባት ሊያምረው ይችላል፡፡ ማዛጋት ቢኖርብን ከጊዜ በኋላ የለመድነው ጫት ሳይሆን ከሕፃንነት ጀምሮ ስንበላ ያደግነውን እንጀራ ስንተው ነበር፡፡ ስለዚህ በሱስ ማጣት ማዛጋት እና በጸሎት ሰዓት ማዛጋት ቅሉ ቢለያይም የአጋንንት ነው፡፡ አንዳንዴ ከማዛጋታችን ወይም ከማፋሸጋችን የተነሳ እራሳችንን መቆጣጠር አንችልም፡፡ ማዛጋቱ ወይ ማፋሸጉ እየባሰ ሲሄድ ሳናለቅስ እንባችን ከዓይናችን ላይ ይንጠባጠባል፡፡ ከማዛጋታችን የተነሳ አገጫችን የሚላቀቅ፣ አፋችን የሚሰነጠቅ እስኪመስለን ልንደርስ እንችላለን፡፡ አንዳንዶች ጸሎታቸውን በማዛጋት ጀምረው በማዛጋት የሚጨርሱ አሉ፡፡ ግን ይህ በሚሆንበት ሰዓት በፍጹም አትሳቀቁ ይልቁንም በጸሎት በርቱ፡፡ የሚፈትናችሁን መናጢ በጸሎታችሁ ኃይል አይታችኃልና፡፡ በጸሎት ሰዓት ማዛጋት አጋንንት እንደሚፈትነን ምልክት ነው፡፡ በተለይ ዓይነ ጥላ፣ ዛር በተለይም ጠቋር፣ መተት፣ እጀ ሰብዕ፣ የዛር ብዳ ወዘተ ካለብን መንፈሱ በውስጣችን ሲጨናነቅ እናዛጋለን፡፡ ወዳጆቼ ጠቋር የተሰኘ ከእናት አባት ከአያት ቅድመ አያት ሲዋረሰን፣ ሲያድርብን መንፈሱ በውስጣችን ይደበቃል፡፡ ከዛ ብርቱ ጸሎት ስንጀምር መንፈሱ እራሱን ከማጋለጡ በፊት በማዛጋት ይገለጣል፡፡ በሚገርም ሁኔታ ማቆም እና መቆጣጠር እና ሰውን እስክናፍር ድረስ ያዛጋናል፡፡ በማዛጋት መካከል ሰውነታችን ይወጣጠራል፣ ከትከሻችን ወደ ኃላ እየሳበ ያንጠራራናል፣ ድምጽ ማውጣት እንጂ የሚቀረን ከመጮህ ባልተናነሰ መልኩ ሃሃሃሃ… እያልን በከፍተኛ ሁኔታ እናፋሽጋለን፡፡ ይህ ከአየር አጋንንት ለሌላ የዛር መንፈስ የሆነው የጠቋር ምልክት ነው፡፡ ተወዳጆች ሆይ እስኪ ወደ ኃላ ሂዱና በእናት በአባታችሁ እና በአያቶቻችሁ በልኩል የነበረውን በየዋህነት ከባዕድ አምልኮ ጋር የተገናኘ ነገር ጠይቋቸው፡፡ በእርግጠኝነት ‹‹አዎ በፊት ነበረ አሁን ትተውታል፤አያታችሁ ታመልክ ነበር ግን ትታ ንስሐ ገብታ ሞታለች፣ በፊት ሲወራ እሰማለሁ ግን እኔ አልደረስኩበትም ወዘተ ….›› እያሉ ይነግሯችኃል፡፡ እኛም ትተው ንስሐ ገብተው መቁረባቸውን፣ መሞታቸውን ስናስብ መንፈሱ እኛ ጋር ያለ አይመስለንም፡፡ ወዳጆቼ የሚያመልኩት ቤተሰቦቻችን ንስሐ ገቡ እንጂ አጋንንትቱ ንስሐ አልገባም፡፡ በተሰቦቻችን ቆርበው ሞቱ እንጂ ያመልኩት የነበረው አጋንንት አይሞትም፡፡ የዘር ሐረጋችንን እየተከተለ፣ ዕድላቸውን እየከለለ፣ በቁማቸው እየገደለ ባዶ ያደርገናል፡፡ የማዛጋት ምልክት ስናይ በጸሎት ከበረታን በማዛጋቱ መንፈሱ ወደ መጋለጡ ይሄዳል። አጋንንቱ ሊለፈልፍ ይችላል፡፡ ስለዚህ በጸሎታችን ሰዓት እንዳንዴ ቤተሰቦቻችንና የሚያውቁን ሰዎች ፊት ልናዛጋ እንችላለን፡፡ ይሄ ሊያስጨንቀን አይገባም፡፡ ወዳጆቼ መቼም አጋንንት እንደ ነፋስ አይደል? በጸሎት ሰዓት በማዛጋት የሚፈትነን አጋንንት በጸሎት እየበረታን ከሄድን እንደ ጢስ እየተነነ፣ እንደ ጉም እየበነነ በመሄድ ከላያችን፣ ከዙርያችን ይርቃል፡፡ ያኔ ማዛጋት እና መወጣጠር፣ መንጠራራቱ ከእኛ ይወገዳል፡፡ ስለዚህ ማዛጋት በውስጣችን አንዳች የማናውቀው ክፉ መንፈስ የመኖሩ ምልክት ነው፡፡ ‹‹ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል›› ት.ኢሳ 53÷8 ክፍል ሰባት በጸሎት ሰዓት የሆድ ቁርጠት ይቀጥላል። @delilamedia
без подписи
ክፍል አምስት የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት በእንቅልፍ እና በመደበት ይፈትነናል በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ ተወዳጆች ሆይ በክፍል አራት የአየር አጋንንት በጸሎት ጊዜ ሐሳባችንን በመበተን እንዴት እንደሚፈትነን አይተናል፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ ከላይ በርዕሱ የተጻፈውን እንመለከታለን፡፡ የቅዱሳን አምላክ ምስጢሩን ይግለጽልን፡፡ ወዳጆቼ የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት በእንቅልፍ እና በመደበት፣ እንዴት እንሚፈትነን እናያለን፡፡ የአየር አጋንንት በሁለት መልኩ ነው በእንቅልፍ እና በመደበት የሚፈትነን፡፡ አንደኛው ለጸሎት እንዳንነሳ እንደ ጸራሞ እና ደራሞ እንቅልፍ እየጣለብን ዱካክ እንዲጫነን በማድረግ ሲሆን፤ ሁለተኛው ሌሊት አልያም ጠዋት ወይም ማታ ለጸሎት ስንቆም ያላሰብነውን የእንቅልፍ መዓት እያመጣ ሕሊናችን እንዲዝል፣ ዓይናችን በክቡድ እንቅልፍ እንዲገላጀጅ በዚህም መቆም እንዳንችል በማድረግ ነው፡፡ ለጸሎት ሌሊት ልንነሳ ስንል አንድ የማናውቀው ግን የምናስተውለው ኃይል ይጫጫነናል፡፡ ታድያ በዛን ቅጽበት የአየር አጋንንት ‹‹ደክሞሃል፣ ትንሽ ተኝተህ ትነሳለህ፣ ጠዋት ሲነጋ ትጸልያለህ›› በማለት ሹክ ይለናል፡፡ እኛም ሐሳቡ የራሳችን ስለሚመስን ተቀብለን፣ ተስማምተን ተመልሰን እንተኛለን፡፡ ሁላችንም ላይ የሚስተዋለው ደግሞ ሌሊት በተኛንበት አልያም ለጸሎት ለመነሳት ባሰብንበት ሰዓት የሆነ ኃይል አልጋው ላይ አጣብቆን፣ ሰውነታችንን አደንዝዞን፣ እጃችንን እንኳን እንዳናማትብ አዝሎን፣ እንዳንጮህ አፍኖን፣ የጮህን እንኳን ቢመስለንም ሰሚ አልባ ጯሂ አድርጎን ይደብተናል፡፡ ወዳጆቼ ይህ ሁሉ የሚሆነው የአየር አጋንንት ሲቀርበን በላያችን ሲያንዣብብና ሲፈትነን የሚሰማን ስሜት ሳይሆን አጋንንታዊ ክስተት ነው፡፡ ሌላው ውስጣችን ተደብቆ፣ አሸምቆ የኖረው ዓይነ ጥላው፣ ዛሩ ለጸሎት ልንነሳ ስንል ውግያውን በገሀድ ስለሚጀምር ነው፡፡ እነዚህን ሁሉ ተቋቁመን ለጸሎት ብንነሳ እንኳን የአየር አጋንንቱ በአቅራብያችን ስላለ በመነሳታችን ተበሳጭቶ ልክ ለጸሎት መቆም ስንጀምር በአልጋ የተውነውን እንቅልፍ በቁማችን በመከመር እንቅልፍ እንቅል ይለናል፡፡ እኛም እንቅልፉ መልሶ ሲጫነን ቅድም ያቋረጥነው ያልጨረስነው እንቅልፍ እንጂ የአየር አጋንንት እንደሚያንገላጅጀን አናስተውልም፡፡ በዚህ ችግር ስንቴ ጸሎታችንን ሳንጨርስ ተመልሰን ተኝተናል? የጸሎት መጽሐፍችንን መያዝ እስኪያቅተን፤ብንይዝም እጃችን መያዝ አቅቶት እስክንጥለው ድረስ ይፈትነናል፡፡ ይህ በሚሆንበት ሰዓት ከፍተኛ የመደበት ክስተት ውስጥ ስለምንገባ ሐሳባችንን ሰብስበን በተመስጦ ሆነን ለመጸለይ እንቸገራለን፡፡ ምክያቱም በአየር አጋንንቱ ተጽዕኖ የመደንንዘዝ እና የመፍዘዝ ስሜት ውስት ስምንገባ፡፡ በርታ ያሉት ደግሞ በስንት ውግያ እንቅልፋቸውን አሸንፈው ለሊት ጸሎታቸውን ካደረሱ የአየር አጋንንቱ በሌሊት እንቅልፍ በመበሳጨት ቀን ከፍተኛ የእንቅልፍ መዓት በማምጣት ያንገላጅጀናል፡፡ ምናልባት የሌሊት እንቅልፉን በተለያየ ሥራ ብንቋቋምም ጥስቅ ያለ የራስ ምታት በማምጣት ይፈትነናል፡፡ በዚህም የመደንዘዝ ክስተት ውስጥ ይከተናል፡፡ የአየር አጋንንቱ ይህን ሁሉ የሚያደርገው በቀጣዩ ቀን በማዳከም ከዛም ለማስተኛት እንዲመቸው ነው፡፡ እድሜ ለሳይንስ የተማርነው ደግሞ ‹‹ሳይንሱ ለስምንት ሰዓት መተኛት አለባችሁ ያለበለዝያ ለጤና ጥሩ አይደለም›› በሚለው ፈሊጥ፣ አጋንንቱ የስንፍና ፍልጥ ያሸክመናል በመተኛት ያሳምነናል፡፡ በዚህ እሳቤ እኛም ጸሎት እና ተጋድሎን መለማመድ አንችልም፡፡ እኛም በቀጣዩ ቀን ሌሊት አልያም ሊነጋጋ ሲል እንቅልፍ ሲጥለን የተኛነው በድካም እንጂ በአየር አጋንንት ተጽእኖ ሳይሆን የትላንቱ እንቅልፍ ተደራርቦብን ስለሚመስለን የጸሎት ሰዓታችንን እናሳልፋለን አልያም ጸሎቱን እናስታጉላለን፡፡ የእንቅልፍ ማጣት አልያም በአግባቡ አለመተኛት ጸሎታችንን ተረጋግተንና በአግባቡ እንዳንጸልይ ያደረገን እንጂ የአየር አጋንንት የፈተነን አይመስለንም፡፡ የሚገርመው ለጸሎት ስንቆም ወይም ስንጀምር የቀን ሥራ ከሠራ፣ድንጋይ ሲሸከም ከዋለ ሰው ይልቅ ከፍተኛ የድካምና የመዛል ስሜት ይታይብናል፡፡ ቆመን የእለት ወዳሴ ማርያም ለማድረስ እንንቀጠቀጣለን፡፡ ለረጅም ሰዓት ቆመን ወሬ ስንሰልቅ ሰው ስንቦጭቅ ማይደክመን ለግማሽ ሰዓት ለመጸለይ ስናስብ ይደክመናል፡፡ ይህ የሚሆነው የአየር አጋንንቱ በአቅራብያችን ስለሚሆን ነው የመጫጫን ስሜት የሚሰማን፡፡ ታድያ በዚህ ሁሉ ግብግብ ውስጥ እኛም በስጨት ብለን ‹‹ጸሎቴ ልክ አይደለም፣ለምን እንደዚህ እሆናለው›› በማለት ጸሎታችን ምስጋና ሳይሆን ጭቅጭቅ ይሆንብናል፡፡ ግን ፈተናውን መቻል ግድ ይለናል፡፡ ዛሬ በጸሎታችን፣ በሕይወታችንና በተለያየ ነገር ሲፈትነን የከረመው የአየር አጋንንት እኛ በጸሎት እየበረታን ስንሄድ እርሱ እየተዳከመ ይሄዳል፡፡ እኛ በመንፈሳዊ ኃይል እየጎለመስን ስለምንሄድ በመጨረሻ ፈተናችንን እስክንረሳ ድረስ አጋንንቱ ከእኛ ይርቃል፡፡ ጌታም ከፈተናችን በኋላ በተፈተንባቸው በአየር አጋንንት ፈንታ ጠባቂ፣አነቃቂ የሆኑ ቅዱሳን መላእክቶቹን ያዝልናል፡፡ ከፈተናችን በኋላ እኛም የተራጋጋ ሕይወት ይኖረናል፣ ጸሎታችንም የተመስጦ ይሆናል፡፡ ሲረብሹን የነበሩ ርኩሳን መናፍስት ስለሚርቁን ምናልባት የራሳችን የሥጋ ባሕርይ ካልሆነ በቀር የአጋንንት ፈተናው ጋብ ይላል፡፡ ጌታችን በገዳመ ቆርንጦስ ከተፈተነ በኋላ ነው ‹‹መላእክት ቀርበው ያገለግሉት ነበር›› የተባለው፡፡ ይህ ለእኛ ትልቅ ትምህርት ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ሰው የመላእክትን አገልግሎት፣ተራዳኢነት የሚያገኘው ከፈተና በኋላና ፈተናውን ከተወጣ በኋላ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ /ማቴ 4÷11/ የአጋንንት ፈተና ከራቀን በኋላ ሁሌም አንፈተንም አይባልም፡፡ በራሳችን ስንፍናና በጸሎት ከደከምን ከእኛ የራቀው አጋንንት ‹‹ዕረፍት…አያገኝም›› ስለተባለ ማረፍያ ፍለጋ ወደ እኛ ይመጣል፡፡ /ማቴ 12÷43/ ትላንት በስንት ትግልና መከራ የራቀን አጋንንት ዛሬ ኃጢአት ስንሠራ ካገኘን፣ ጸሎታችንን መተዋችንን ካወቀ ወንጌሉ እንዳለው ‹‹ወደ ወጣሁበት ቤት እመለሳለሁ…ቢመጣም ባዶ ሆኖ ተጠርጎና አጊጦ ያገኘዋል፡፡ ከዚያም ወዲያ ይሄድና ከእርሱ የከፉትን ሰባት ሌሎች አጋንንት ከእርሱ ጋር ይወስዳል፣ ገብተውም በዚያ ይኖራሉ›› ያለው ይደርስብናል፡፡ /ማቴ 12÷44-45/ ልብ በሉ አጋንንት ምን ያህል የእኛን ድክመት እየተጠቀመ እንደ ባዶ ቤት ሆነን በራችንን ከፍተን ካገኘን፤ ጸጋችን በኃጢአት ተጠርጎ ከውስጣችን ሲወጣ ቀድሞ ይፈትነን የነበረው አጋንንት በፈተና ስልት እና በብዛት እጥፍ ሆኖ ለስቃይ እንደሚዳርገን ማወቅ አለብን፡፡ ‹‹ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል›› ት.ሆሴ 4÷6 ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ት.ኢሳ 53÷8 ክፍል ስድስት በጸሎት ሰዓት ማዛጋት ይቀጥላል …… @delilamedia
без подписи
@delilamedia
ክፍል አራት በጸሎት ሰዓት ሐሳባችን ለምን ይበተናል? በተመስጦ መጸለይ ለምን አቃተን? /ልብና ሕሊና በክፉ ሐሳብ ተተብትቧል፣አንደበት ደግሞ ይጸልያል/ በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም ሼር በማድረፍ ለወዳጆ አዳርሱ ተወዳጆች ሆይ በክፍል ሦስት ‹‹የአየር አጋንንት በሳኦል ሕይወት›› በሚል የአየር አጋንንት በሳኦል ሕይወት በክፉ ጭንቀት፣በቅናት እና በምቀኝነት ብሎ እስከ ውድቀት እና ሞት እንዴት እንዳደረሰው ተመልክተናል፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ የአየር አጋንንት በጸሎት ጊዜ እንዴት እንደሚፈትነን እናያለን፡፡ ብዙዎቻችን በጸሎት ሰዓት ሰውነታችን ባለበት ልባችን የለም፡፡ ጸሎታችን ባለበት ተመስጦአችን የለም፡፡ በተቃራኒው የማንፈልጋቸው ሐሳቦች ናቸው ያሉት፡፡ የዚህ ሁሉ ነገር ችግሩ የአየር አጋንንት ስለሆነ እንዴት ባለ ግልጽ እና ስውር የፈተና ስልት እንደሚዋጋን በዝርዝር እናያለን፡፡ በጸሎት ጊዜ የአየር አጋንንት ፈተና የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት ከሌሎቹ አጋንንት በተሻለ መልኩ የሚፈትኑን በአየር ላይ ስለሚያንዣብቡ በቀላሉ ለእነሱ የተጋለጥን ስለሆነ ነው፡፡ ጸሎታችንን ልክ እንደ ጀመርን በቅጽበት እኛ በማናውቀው ምናልባትም እራሳችን በሚመስለን መልኩ አንድ ሐሳብ ልባችን ውስጥ በማስገባት ወይም የረሳነውን በማስታወስ ይፈትኑናል፡፡ ለምሳሌ የተጣላነው ሰው፣ ያስቀየመን ሰው፣ ለሰው ያበደርነው ገንዘን፣ የጠፋብን /የረሳነው/ ዕቃ ወዘተ ትዝ የሚለን ጸሎት ላይ ስንሆን ነው፡፡ ይህን የሚያደርጉት የአየር አጋንንት ናቸው፡፡ በዚህም ያልፈለግነውን ሐሳብ ከኛ ለማራቅ በምንገጥመው ውስጣዊ ግብግብ ጸሎቱ ይዘነጋናል፣ በጸሎት መጽሐፍ የምናደረሰው ምስጋና ይረሳናል፡፡ ምን እንደጸለይን እንኳ ላናስታውስ እንችላለን፡፡ አንዳንዶቻችን ጸሎቱን መጀመራችንን እንጂ መጨረሳችንን አናውቅም፡፡ ጸሎቱን መጨረሳችንን እንጂ በጸሎቱ ውስጥ ያለውን ምስጋና ተማጽኖ ልመና አናስታውስም፡፡ የአየር አጋንንቱ ሐሳቡን ለእኛ ሰጥቶ እሱ ከእኛ ይርቃል እኛም በማንፈልገው ሐሳብ ተጠምደን ጸሎታችንን እናደርሳለናል፡፡ የምንፈልገውን ሳይሆን የማንፈልገውን ሐሳብ እናስተናግዳለን፡፡ ይዘን የቆምነውን የጸሎት ዓላማ በሌላ ይለወጥብናል፡፡ ይህ ታላቅ የአጋንንት ፈተናን ቅዱስ ጳውሎስ ስለተሰቃየበት ‹‹የማልወደውን ክፉ ነገር አደርጋለሁና ዳሩ ግን የምወደውን በጎውን ነገር አላደርገውም፡፡ የማልወደውን የማደርግ ከሆንሁ ግን ያን የማደርገው አሁን እኔ አይደለሁም፣ በእኔ የሚኖር ኃጢአት ነው እንጂ›› በማለት አጋንንት ምን ያህል ይፈትነው እንደነበር ከልምዱ እንድንማር ነግሮናል፡፡ /ሮሜ 7÷19-20/ ቅዱስ ጳውሎስ የሚፈትነውን አጋንንት ‹‹ኃጢአት›› በማለት ነው የገለጠው፡፡ የአየር አጋንንቱ በጸሎታችን ተስፋ መቁረጥ እንዲሰማን ‹‹እንዲህ እያሰብኩ ከምጸልይ ቢቀርብኝ ይሻላል›› እንድንል ያደርገናል፡፡ የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት እኛን መፈተኑ ሁለት ነገር ያስጠቅመዋል፡፡ አንደኛው በጸሎታችን መሐል እየገባ እንዳንመሰጥ፣ ተመስጦን እንዳንለማመድ ሲያደርገን ሁለተኛውና ዋነኛው በጸሎታችን ተስፋ ቢስ እንድንሆን ወይም ተስፋ እንድንቆርጥ ያደርገናል፡፡ የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት አንድ ሐሳብ በስውር ሹክ ብሎን ይሄዳል በሐሳቡ እኛ እንሰቃያለን፡፡ ወዳጆቼ ምንም በጸሎታችሁ ሰዓት ሐሳባችሁ ባይሰበሰብም ተመስጦ ባይኖራችሁም መጸለይ ማቋረጥ የለባችሁም፡፡ ጸሎታችሁን ተስፋ በመቁረጥ ከተዋችሁ ያኔ ለአጋንንቱ እጅ እንደሰጣችሁ፣ እንደ ተማረካችሁ ቁጠሩት፡፡ ዓላማው ጸሎታችሁን በፈተና ማስተው ነውና ከተዋችሁ ደግሞ አጋንንታዊው ደስታ እንዲኖረው አደረጋችሁት ማለት ነው፡፡ ሊቁ ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ ‹‹በመንፈሳዊ ሕይወትህ ተስፋ ከቆረጥክ ለሰይጣን እጅ እደሰጠህ ቁጠር›› ብሏል፡፡ አንዳንዴ ከንፈር ጸሎትን ቢነዳም፣ ልብ ነገር ቢያሰናዳም ከመጸለይ ወደ ኋላ ማለት አይገባም፡፡ ለዚህም እንድትጽናኑ ሳይሆን እውነቱን በአስረጂ ምሳሌ ልንገራችሁ፡፡ ለምሳሌ አንድ ዓይነ ስውር በበትሩ እየተመራ ውሻ ባለበት መንደር ቢሄድ ውሻው ዝም አይልም፡፡ ይልቁንም እኔን ሊመታኝ ነው በማለት ምንም ያልተነካው ውሻ በዓይነ ስውሩ ላይ ይጮኋል፡፡ ዓይነ ስውሩም ውሻ መከላከያ ሳይሆን መንገድ መምሪያ ትሆነው ዘንድ የያዛት በትር ከውሻ ንክሻ ትታደገዋለች፡፡ ውሻውም ዓይነ ስውሩ የያዛት በትር መምሪያ ሳትሆን እሱን መምቻው ስለምትመስለው ዓይነ ስውሩን ከመንከስ ይልቅ በትርዋን እየፈራ ይጮህበታል፡፡ ዓይነ ስውሩ መንገድ መምሪያው ትሆነው ዘንድ የያዛት በትር ሳያውቀው ከውሻ ንክሻ ትታደገዋለች፡፡ ጸሎታችንም ልክ እንደዚህ ነው፡፡ እኛ ወደ እግዚአብሔር ይመራናል፣ ጥያቄያችንን ይመልሳል፣ ችግራችንን ያቃልላል ብለን የያዝነው ጸሎት ለአጋንንት እንደ ዱላ ምት ስለሚሆንበት ይረበሻል፣ እንደ ፍላጻ ስለሚወጋው ከእኛ ይርቃል፡፡ እኛ ወደ እግዚአብሔር ያቀረብነው ጸሎት ለአጋንንት እሳት ስለ ሚሆን በላያችን ላይና በአቅራብያችን ላለው ርኩስ መንፈስ እሳት በመሆን ያቅጥለዋል፡፡ ስለዚህ በየትኛውም የሐሳብ መበተን ውስጥ ብንሆንም በፊቱ ለክፋት ሳይሆን ለጸሎት እንደቆምን የሚያውቀው እግዚአብሔር ጸሎታችንን ይሰማናል፡፡ አንድ ሰው በጸሎቱ ሰዓት የአየር አጋንን እየፈተነው እንደ ሆነ በምን ያውቃል? ካልን ግልጽ ምልክቶች አሉት፡፡ ምልክቶቹም በጸሎት ሰዓት የሐሳብ መሰረቅ፣ የልቦና መዘበራረቅ፣ ተረጋግቶ አለመጸለይ፣ እንቅልፍ እንቅልፍ ማለት፣ መደበት፣ መሰልቸት፣ አትጸልይ የሚል ስሜት መሰማት፣ ለምን እንደምንጸልይ ግራ መጋባት፣ መቁነጥነጥ፣ ወገብ አከባቢ ሕመም መሰማት፣ እጅና በተለይ ሙሉ ሰውነት መዛል፣ በውስጣችን መነጫነጭ፣ ማኩረፍ፣ መፍዘዝ፣ መደንዘዝ፣ ትንፋሽ ማጠር፣ ማፋሸግ፣ እያዛጉ እንባ ማንጠባጠብ፣ ድንገተኛ እራስ ምታት፣ ምላስ መተሳሰር፣ የፍርሃት ስሜት መሰማት፣ ጭው የሚል ነገር ውስጥ መግባት፣ የልብ ምት መጨመር ወይም መቀነስ፣ መንቀጥቀጥ፣ ድንገተኛ ሆድ መነፋት፣ በፈስ መወጠር ወዘተ ናቸው፡፡ እነዚህ የአየር አጋንንቶች በጸሎት ሰዓታችን ሲፈትኑን የምናያቸው ምልክቶች ስለሆኑ መደናገጥ አያስፈልግም፡፡ እነዚህ ምልክቶች የዓይነ ጥላ፣ዛር፣መተት እና ድግምት ወዘተ ያለበት ሰውም ላይ ጎልተው ይታያሉ፡፡ ወዳጆቼ በጸሎት ሰዓት ሕሊናችን ልቦናችን ተበትኖ ብንጸልይም ከአንድበታችን የሚወጣው ቃለ እግዚአብሔር ለአጋንንት እሳት መሆኑን አንርሳ፡፡ ምክንያቱም ጸሎት በምቾት ውስጥ ሆኖ ሳይሆን በፈተና ውስጥ ሆኖ ሲጸልዩት ነው በረከትና ጸጋን የሚያሰጠው፡፡ ጸሎታችን ምንም እንኳን ተመስጦ ባይኖረውም ከልብ ፍላጎት የሚወጣ ስለሚሆን ተሰሚነቱ አያጠራጥርም፡፡ ጸሎት እግዚአብሔርን ከመሻት፣ ለማግኘት ከመጣር የሚመጣ ስለሆነ ይሰማል፡፡ ይልቁንም ልንጠነቀቅበት የሚገባው ‹‹እግዚአብሔር ጸሎቴን አይሰማኝም›› ማለት እግዚአብሔር እንደሌለ እንደማይሰማ መቁጠር ነው፡፡ ይህ ደግሞ እራሱን የቻለ ኃጢአት ነው፡፡ እንኳን እግዚአብሔር እኛም እንዳቅማችን የሰውን ችግር እንሰማለን፡፡ ስለዚህ በጸሎታችን መሐል የሚገጥሙን የሐሳብ ፈተናዎች ከአጋንንት መሆኑን አውቀን፣ እግዚአብሔር ጸሎቴን አይሰማኝም ከሚል ከስንፍና ሐሳብ ተላቀን ልንጸልይ ይገባናል፡፡ ‹‹ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል›› ት.ሆሴ 4÷6 ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ት.ኢሳ 53÷8 ክፍል አምስት የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት በእንቅልፍ እና በመደብት ይፈትነናል /የአየር አጋንንት በእንቅልፍ በፈስና በሌሎች/ ይቀጥላል ……
без подписи
በሳኦል ላይ አድሮ ዳዊትን እስከ ሞት የተገዳደረ አጋንንት እኛንም በሰው እያደረ ሕይወታችንን ለማበላሸት፣ ባስ ሲልም እስከ ሞት ይፈልገናል፡፡ እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ዳዊት ለምን የአጋንንቱ ሰለባ አልሆነም? እንዴትስ አልገደለውም? ብንል ዳዊት አጋንንቱ እሱን ከመዋጋቱ በፊት በእግዚአብሔር ተቀብቶ ነበር፡፡ ይህንንም ‹‹ሳሙኤልም የዘይቱን ቀንድ ወስዶ በወንድሞቹ መካከል ቀባው፡፡ የእግዚአብሔርም መንፈስ ከዚያን ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ›› በማለት የዳዊት መቀባትንና ኃይለ እግዚአብሔርን መላበሱን ይነግረናል፡፡ ለዚህም ነው አጋንንቱ በዳዊት ሕይወት ላይ ሥልጣን ያጣው፡፡ /1ኛ ሳሙ 16÷13/ ይህ ማለት ዳዊት ሳኦል ላይ ባደረ አጋንንት አልተፈተነም ማለት አንችልም፡፡ ይልቁንም አጋንንቱ ሳኦልን የሞት መሣርያ በማድረግ ሊገድለው ዱር ለዱር ተራራ ለተራራ ዳዊትን እጅጉን አሳዶታል፡፡ /1ኛ ሳሙ 23÷19 …./ እኛም እንደ ዳዊት የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ እና የአግዚአብሔርን ኃይል በጾም፣ በጸሎት፣ በስግደት፣ በቅዱስ ቁርባን ከተላበስን አጋንንቱ በእኛ ላይ ኃይል አይኖረውም፡፡ ግን እንደ ዳዊት በራሳችን ሰው፣ በጓደኛ፣ በቤተሰብ አድሮ ሊያሳድደን ይችላል፡፡ በመጨረሻ ሳኦልን ያልተላቀቀው አጋንንት በራሱ ሰይፍ እራሱን እዲያጠፋ አደረገው፡፡ አጋንንቱ የሳኦልን አንገት አስቆርጦ ላጣዖት መቅደስ መብዓ አደረገው፡፡ አስከሬኑም በአጥር ላይ ተንጠለጠለ፡፡ የሳኦልን ሞት የሰሙት ሰዎች አስከሬኑን ወስደው አቃጠሉት፡፡ ሳኦል በእግዚአብሔርና በእስራኤላውያን ዘንድ ጥሩ ስምና መልካም መቃብር ሳይኖረው ቀረ፡፡ /1ኛ ሳሙ 31÷1-13/ እኛም ለእግዚአብሔር መታዘዝን እንቢኝ ብለን፣ሕጉን አፍርሰን የምንኖር ከሆነ በሳኦል የንግሥና ሕይወት የገባው አጋንንት በእኛም ሕይወት ጣልቃ በመግባት ከውርደት እስከ ሞት ያደርሰናል፡፡ ስለዚህ የሳኦልን ዓይነት የውድቀት እና የሞት ታሪክ የተጻፈልን ከእሱ እንድንማርና ከአጋንንት ሕብረት በማራቅ፣ ለእግዚአብሔር ሕግ በመጠንቀቅ መኖርን እንድናተርፍ ነው፡፡ ዛሬ በዘመናችን ብዙዎቻችን የሳኦልን የውድቀት እና የቁም ሞት እየኖርን ነው፡፡ ስለዚህ ከዚህ አስከፊ የአጋንንት የፈተና ሕይወት እንድንላቀቅ ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር መጣበቅ አለብን፡፡ ‹‹ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል›› ት.ሆሴ 4÷6 ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ት.ኢሳ 53÷8 በቀጣይ ክፍል አራት በጸሎት ሰዓት ሐሳባችን ለምን ይበተናል? በተመስጦ መጸለይ ለምን አቃተን? /ልብና ህሊና በክፉ ሐሳብ ተተብትቧል፣ አንደበት ደግሞ ይጸልያል/ ይቀጥላል …… @delilamedia
ክፍል ሦስት የአየር አጋንንት፣ በሳኦል ሕይወት! share)በቀሲስ ሄኖክ ወ/ማርያም (share ተወዳጆች ሆይ በክፍል ሁለት የአየር አጋንንት የሚባሉት የትኞቹ ናቸው? የሚለውን በሰፊው ተመልክተናል፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ የአየር አጋንንት በሳኦል ሕይወት ውስጥ እንዴት እንደሚመስል እናያለን፡፡ የቅዱሳን አምላክ ምስጢሩን ይግለጽልን፡፡ ወዳጆቼ በብሉይ ኪዳን ክፉ መንፈስ በግልጽ ሰውን እንዴት እንደሚፈትን ከታየበት ክስተት አንዱ በእስራኤሉ ንጉሥ በሳኦል ሕይወት ነው፡፡ ሳኦል እግዚአብሔር ከመሬት አንስቶ፣ ከእስራኤላውን በላይ አጉልቶ ያየው የመረጠውና ያነገሠው ሰው ነበር፡፡ እስራኤላውያን ነብዩ ሳሙኤል በሸመገለ ጊዜ ንጉሥ ስጠን ብለው አስጨነቁት፡፡ ይህ ሐሳባቸው ግን መልካም አልነበረም፡፡ እግዚአብሔርም የሳኦልን ፍጻሜ ያውቅ ስለነበር ሳሙኤል ‹‹በዚያን ቀን ለእናንተ ከመረጣችሁት ከንጉሣችሁ የተነሳ ትጮኻላችሁ፤ በዚያን ቀን እግዚአብሔር አልሰማችሁም›› ብሎ ነገራቸው፡፡ ሳሙኤልም የሚቀባው ንጉሥ ፍጻሜው መልካም እንዳልሆነ ቢነግራቸውም ሕዝቡ እንቢ አለው፡፡ እንደ ፍላጎታቸው ንጉሠ መዓት ሳኦልን አነገሠላቸው፡፡ /1ሳሙ 8÷18-22/ በዚህ መንገድ የነገሠው ሳኦል አሞናውያንን ድል በመንሳት ሕዝቡን ደስ አሰኘ፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር በመታዘዝ አልጸናም፡፡ በመጀመርያ ፍልስጤማውያንን ፈርቶ የሳሙኤልን መምጣት ሳይጠብቅ መሥዋዕትን በማቅረብ እግዚአብሔርን በደለ፡፡ በዚህም ያልታዘዘውን መስዋዕት በማቅረቡ ከሳሙኤል ዘንድ መንግስቱ ተነጥቆ ለዳዊት እንደተሰጠ መርዶ ሰማ፡፡ /1ሳሙ 13÷9-14/ ሁለተኛ በአማሌቅ ላይ በታዘዘ ጊዜ ለእግዚአብሔር በሙሉ ልቡ አልታዘዘም፡፡ እስራኤላውያን ከግብጽ የባርነት ሕይወት ወጥተው ወደ አገራቸው ሲመለሱ አማሌቃውያን በመንገድ እያሸመቁ አደጋ እየጣሉ ያሰቃይዋቸውና የመከራን መንገዳቸውን ያስረዝሙባቸው ስለነበር አማሌቃውያንንና የአማሌቅን ንጉሥ አጋግን እንዲገድላቸው፣ እንስሳቶቹንም እንዲያጠፋ ቢያዘውም የተባለውን ሳይፈጽም አጋግን ከመግደል ይልቅ በመማረክ፣ ከእንስሶችም የሰቡትን በመተው ለእግዚአብሔር ያለመታዘዙን አሳየ፡፡ ሳሙኤልም ‹‹ለምርኮ ሳስተህ ለምን የእግዚአብሔርን ቃል አልሰማህም? ለምንስ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረግህ?›› አለው፡፡ ሳኦልም ሽምጥጥ አደርጎ ‹‹የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቻለሁ እግዚአብሔርም በላከኝ መንገድ ሄጃለሁ›› ብሎ በገሀድ ሳሙኤል ሳይሆን እግዚአብሔርን ዋሸ፡፡ /1ሳሙ 15÷19-20/ የሚገርመው ሳኦል እግዚአብሔር ያዘዘውን ሳይፈጽም እንደፈጸመ ቆጥሮ እግዚአብሔርን በምክንያት ለማስረዳት ሞከረ፡፡ ሳኦል አጋግን አስቀምጦ፣ የሰቡትን እንስሶች ከጓሮ አኑሯቸው የታዘዝኩትን ፈጽምያለሁ ግደል የተባልኩትን ገድያለሁ አለ፡፡ ሳሙኤልም ሳኦል የደበቃቸውን እንስሶች ግሳት እና ጩኸት ሰምቶ ‹‹መታዘዝ ከመሥዋዕት፣ ማዳመጥም የአውራ በግ ስብ ከማቅረብ ይመረጣል›› ብሎት ባለመታዘዙ ወቅሶት ንቆት ሄዷል፡፡ /1ሳሙ 15÷22/ በመጨረሻም እግዚአብሔር ሳኦልን በማንገሡ ተጸጸተ፡፡ ከዚህ በኃላ ነው እንግዲህ አጋንንት የሳኦልን ሕይወት በጭንቀት መጎብኘት የጀመረው፡፡ በሳኦል ሕይወት የአየር አጋንንት እንዴት ያሰቃየውና ያስጨንቀው እንደ ነበር ተጽፏል፡፡ ሳኦልን የሚስጨንቀው የአየር አጋንንት በራሱ ፈቃድ ለፈተና የመጣ ሳይሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ የታዘዘ ነበር፡፡ በሳኦል ሕይወት ጣልቃ በመግባት ያሰቃየው የነበረው የአየር አጋንንት ምቹ ጊዜ አግኝቶ ነው፡፡ ከሳኦል ላይ የእግዚብሔር ቅዱስ መንፈስ መነሳት፣ ለአየር አጋንንቱ ምቾት ሰጥቶታል፡፡ የእግዚአብሔር መንፈስ ከሳኦል ሲርቅ የአየር አጋንንቱ ቦታ አገኘ፣ ሳኦልንም በጭንቀት ጎበኘ፡፡ በሳኦል ላይ የነበረው የንግሥና ጸጋና ሞገስ ከሳኦል ተነስቶ ለዳዊት ሲሰጥ ሳኦል ለአጋንንቱ ባዶና በር የሌለው ቤት ሆነለት፣ መጥቶም ሰፈረበት፡፡ የእግዚአብሔር ቅያሜ መንግሥቱን ጸጋውን አሳጥቶት ለአጋንንት አሳልፎ ሰጠው፡፡ አሁን ሳኦል ሞገሰ ቢስ፣ ጸጋ ቢስ ሆኗል፡፡ ይጠብቀው፣ ይመራው የነበረው ቅዱስ መንፈስ አሁን የለም፡፡ ሳኦል ነፍሱ ከጸጋ ተራቁታ እርቃንዋን ሆናለች፡፡ በዚህን ጊዜ ነው ሳኦል የአጋንንቱ የጥቃት ሰለባ የሆነው፡፡ ወደ ኢዮብ የመጣው ሰይጣን፣ ንብረት አጥፊ፣ ልጆችን በሞት ገፊ ሆኖ ነው ለፈተና የመጣው፡፡ በኢዮብ ላይ ግላዊና ቤተሰባዊ ውድመትን ያደረሰው ሰይጣን በቅዱስ ኢዮብ የቅድስናና የጽድቅ ሕይወት መጠን የታዘዘ ነበር፡፡ ኢዮብን የፈተነው ሰይጣን እግዚአብሔርን ‹‹ልፈትነው›› ብሎ ጠይቆ ነው፡፡ ሳኦልን ያሰቃየው የነበረው የአየር አጋንንት ‹‹ልፈትነው›› ብሎ ጠይቆ ሳይሆን ሂድ ተብሎ የታዘዘ አጋንንት ነበር፡፡ ኢዮብ በጽድቁ፣ በእግዚአብሔር ወዳጅነት ነው የተፈተነው፡፡ ሳኦል ግን ለእግዚአብሔር አልታዘዝም፣ የታዘዝኩትን አልፈጽምም ከማለት ከሥጋዊ እብሪት የመጣበት ፈተና ነበር፡፡ እዚህ ላይ ልብ ልንለው የሚገባው ሰይጣን ምን ያህል በሕይወታችን በቅናት ጣልቃ በመግባት፤ ከማሰቃየት እስከ ሞት ድረስ እንደሚገዳደረን ነው፡፡ ወደ ሳኦል ስንመለስ ሳኦልን እጅጉን ያሰቃየው የነበረው አጋንንት የአየር አጋንንት ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡ ምክንያቱም የአየር አጋንንት አንዱና ዋናው መገለጫው የማይያዝና ሄድ መጣ እያለ፣ቀን እየጠበቀ፣ አድፍጦ ሕይወታችንን በጥብጦ የሚሄድ ክፉ መንፈስ በመሆኑ በሳኦል ላይም ይህን መገለጫውን ይዞ ነው ሲያሰቃየው የነበረው፡፡ አሁን ሳኦል በአየር አጋንንት ተይዟል ግራ ገብቶታል፡፡ በጭንቀት ሕመም ክፉኛ የሚሰቃየው ሳኦል ችግሩን እንኳ በአግባቡ አላወቀም፡፡ የአጋንንቱ ሰለባ እሱ ሆኖ ሳለ በሚገርም ሁኔታ የራሱ ችግር ለባርያዎቹ ተገልጦላቸው ‹‹እነሆ ክፉ መንፈስ ከእግዚአብሔር ዘንድ ያሰቃይሃል›› ብለው መፍትሔውንም ነገሩት፡፡ /1ኛ ሳሙ 16÷15/ እኛም እንደ ሳኦል እየተጋረደብን ጸጋችን ተገፎ፣ አጋንንት በሕይወታችን መንገድ ላይ ተሰልፎ ሲያሰቃየን አይታወቀንም፡፡ እንደ ሳኦል በባርያዎች ካልተነገረን አንረዳም፤ ተነግሮንም አንሰማም፡፡ ይህ ብቻ አይደለም በሳኦል ላይ ያደረው የአየር አጋንንት ዳዊትን አልፍቶታል፡፡ ዳዊት በገና እየደረደረ ሲዘምር ሳኦል ላይ ያደረው አጋንንት ይርቃል፡፡ ዳዊት ሲሄድ አጋንንቱ ይመጣል፡፡ ሳኦልን ያስጨንቀው ያሰቃየው የነበረው አጋንንት ዳዊት ደግሞ በዝማሬና በበገና ያስጨንቀው ነበር፡፡ በዚህ ያቄመው አጋንንቱ ዳዊት ጎልያድን በመግደሉ የእስራኤል ሴቶች ‹‹ሳኦል ሺህ፣ ዳዊትም እልፍ ደገለ›› ብለው ሲዘፍኑ ጦር በመወርወር ከግርግዳ አጣብቆ በክፉ ሞት ሊገድለው ሞክሮ ነበር፡፡ ሳኦልን ሄድ መጣ እያለ ያሰቃየው አጋንንት ዳዊት ጎልያድን በገደለ ግዜ የቅናት መንፈስ በመሆን እጅጉን ተፈታትኖታል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሳኦል ላይ ያደረው የአየር አጋንንት ‹‹ከዚያን ቀን ጀምሮ ሳኦል ዳዊትን ተመቅኝቶ ተመለከተው›› የሚለው አገላለጥ አጋንንቱ ዳዊትን ምን ያህል ለክፉ ተግባር እንደፈለገው ያሳየናል፡፡ /1ኛ ሳሙ 18÷9/ አጋንንት መንፈሳዊ ሕይወት ከጀመርንበት፣ በጎ ምግባር መሥራት ከተያያዝንበት ጊዜ አንስቶ እኛንም በምቀኝነት እንደሚመለከተን፤ እንደ ዳዊት የጾሩን ፍላጻ እንደሚወረውርብን ማስተዋል አለብን፡፡
без подписи
የአየር አጋንንት በሦስቱ መጽሐፈ መነኮሳት በማር ይስሐቅ፣ በፊልክስዮስ እና በአረጋዊ መንፈሳዊ በተባሉት መጻሕፍት ላይ እንዴት ባለ የፈተና ስልት/ከሐሳብ ፈተና እስከ ተግባር ፈተና/ አባቶችን፣ ወጣኒ መናኞችን እንደሚፈትኗቸው በሰፊው ተጽፏል፡፡ የተለያዩ ገድለ ቅዱሳንም አጋንንቱ በገዳማቸው በሚኖሩት መነኮሳት ላይ በተለያየ ስልት እና ጥቃት ይፈትናቸው እንደነበር ይነግረናል፡፡ ስለዚህ የአየር አጋንንት ፈተና መነኮስ፣ ቄስ፣ ምዕመናን ሳይል ባለንበት መንፈሳዊ ደረጃ ይፈትነናል፡፡ ስለዚህ መገለጫቸው ማሰቃየት፣ ጥርጥር፣ ክርክር፣ ክፉ ሐሳብን በሰዎች ሕሊናና ልቦና ማስረጽ፤ አላስፈላጊ ሐሳቦችን በሰዎች ልቦና ውስጥ በማስገባት በራሳቸው ሐሳብ ማመጽ፤ የማያባራና መግቻ የሌለውን፣ በድርጊት የማንገልጸውን መጥፎ ሐሳቦች በማሳሰብ፤ በውስጣችን ሆነው እግዚአብሔርን፣ እመቤታችንን፣ ቅዱሳንን መሳደብ፣የእኛ ባልሆነ ሐሳብ በመጥመድ ከራሳችን ጋር እድንጣላ ማድረግ፣በሕይወታችን ብቻ ሳይሆን በሞታችን ጣልቃ መግባት ወዘተ ቋሚ እና ተቀዳሚ ሥራቸው ነው፡፡ ወዳጆቼ ደጋሚዎች እነዚህን የአየር አጋንንት በድግምት፣ በአስማት እየሳቡዋቸው፣ከአየር ላይ እያወረድዋቸው ሰዎችን ያቆራኛሉ፡፡ የአየር አጋንንት በማቆራኘት ሰዎችን በትንታ፣ በሚበሉት እዲታነቁ፣ እራሳቸውን እዲያጠፉ፣በልብ ሕመምና በውጋት ብሎም በሌላ ሕመም በተመሰለ ክስተት ሰዎችን ለመግደል ይጠቀሙባቸውል፡፡ የአየር አጋንንትን ደጋሚዎች ለክፋ ተግባራቸው ፈጣኖችና አደገኛ ስለሆነ በቅጽበት ሰዎችን ስለሚቆራኙላቸው በስፋት ይጠቀሙባቸዋል፡፡ የአየር አጋንንት በተለያየ ምክንያት ከተቆራኘን ለመላቀቅ ትንሽ ይከብደናል፡፡ ምክንያቱ መንፈሱ በአየር ላይ ስለሚኖር እግዚአብሔር፣ ጠባቂ መልአካችን ወይም የሚራዳን መልአክ ከእኛ ካላራቀልን፣ ካላሰረል ውግያውና ጥቃቱ ቀላል አይደለም፡፡ ይህን አጋንንት በጽኑ ለመዋጋት ጸሎት እና ትጋት ብርታትን ብሎም ትእግስትን ይጠይቃል፡፡ ወደ ኋላ በሰፊው እናያለን፡፡ ወዳጆቼ አጋንንት ብዛታቸው በሰው ልጅ የሚቆጠሩ አይደሉም፡፡ በክረምት የሚዘንበው የዝናብ ነጠብጣብ ብዛት የአጋንንትን ብዛት አያህልም፡፡ ምክንያቱም አጋንንንት የሚቆጠሩ የሚሰፈሩ ስላልሆኑ፡፡ እንግዲህ እነዚህ ናቸው ለሕይወታችን እንቅፋት በመሆን የሚፈትኑን፡፡ ሰውም ላይ ሲሰፍሩ በብዙ ሺ ሆነው ነው፡፡ /ማር 5÷9‚ ሉቃ 8÷30/ የዚህን የጸሎት ጠላታችንን የአየር አጋንንት ስውር እና ግልጽ የተቀነባበረ የሐሳብ ክፋት እና ስውር ጥቃት በዝርዝር እንመለከታለን፡፡ የቅዱሳን አምላክ ይርዳን፡፡ ‹‹ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሳ ጠፍቶአል›› ት.ሆሴ 4÷6 ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ት.ኢሳ 53÷8 በቀጣይ ክፍል ሦስት የአየር አጋንንት፣ በሳኦል ሕይወት! ይቀጥላል …… @delilamidia
ክፍል ሁለት የአየር አጋንንት የሚባሉትን እንመልከት። share)በቀሲስ ሄኖክ ወ/ማርያም(share ተወዳጆች ሆይ በክፍል አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዲያብሎስ፣ ሰይጣን እና አጋንንት ምን ይላል የሚለውን በሰፊው አይተናል፡፡ በዚህ ክፍል ደግሞ ከአጋንንት የአየር አጋንንት የሚባሉት የትኞቹ ናቸው? የሚለውን በሰፊው እንመለከታለን፡፡ የቅዱሳን አምላክ ምስጢሩን ይግለጽልን፡፡ ወዳጆቼ ስለ አየር አጋንንት በወንጌል ላይ ስሙ በግልጽ ባይጻፍም ሰዎችን ይፈትን እንደ ነበር በግብሩ ተጠቅሷል፡፡ በጨረቃ የሚነሳ የተባለው ጨረቃ በሰማይ ላይ ስላለች የአየር አጋንንቱን ለመጥቀስ ነው፡፡ የአየር አጋንንት እንደ ሌሎቹ ሳይሆን ድንገት ነው የሚፈትነን፡፡ ለዛም ነው በወንጌል የተጠቀሱት ሰዎች በጨረቃ ድንገት እየተነሳ ይጥላቸው ያሰቃያቸው የነበረ፡፡ /ማቴ 4÷24፣ ማቴ 17÷14/ ቅዱስ ጳውሎስ የአየር አጋንንትን ‹‹በአየር ላይ ስልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ›› ያለው የአየር አጋንንትን ነው፡፡ /ኤፌ 2÷1-2/ የአየር አጋንንት የሚባሉት በጸሎት ሰዓት የሰውን ሐሳብ በመበተን በተለይም የማንፈልጋቸውን ምናልባትም ጸያፍ ነገሮችን በማሳሰብ ከፊልም ባልተናነሰ መልኩ በማሳየት በመፈተን የሚታወቁት ናቸው፡፡ የአየር አጋንንት ከሌሎቹ አጋንንት ልዩ የሚያደርጋቸው ሰዎችን በጸሎት ሰዓት እና በግላዊ ሕይወታቸው በስውር በመፈተኑ ነው፡፡ መንፈሱን የሚያከፋው እንደ ስሙ በአየር ላይ ስለሚያንዣብብ፣ ሕይወታችንን በክፉ ሐሳቦች ስለሚተበትብ በቀላሉ ልናርቀው አለመቻልችን ነው፡፡ ብቅ ጥልቅ፣ ሄድ መጣ እያለ እያደባ ብሎም የክፋት ሐሳቡን ሹክ ብሎን ስለሚሄድ ፈተናው ለማንኛችንም ከባድ ነው፡፡ የአየር አጋንንት እንደ ሌሎቹ በጸበል የመለፍለፍ ወይም የመጋለጥ እድሉ አናሳ ነው፡፡ ምክንያቱም በአየር ላይ ሆኖ ስለሚዋጋን በቀላሉ የጥቃቱ ሰለባ ሊያደርገን ይችላል፡፡ የአየር አጋንንት ቅዱሳንን በሐሳብ ኃጢአት በመፈተን፣ መነኮሳትን በገዳማቸው ተረጋግተው እንዳይቀመጡ፣ ምዕመናንን በክፉ ሐሳብ እንዲዋጡ የሚያደርግ ክፉ መንፈስ ነው፡፡ የዚህ ክፉ መንፈስ ውግያ በቅዱሳን ላይ እጅጉን ይጸናል፡፡ ቅዱሳንን መንፈሳዊ አለመረጋጋት እና ውጣ ውጣ፣ ሂድ ሂድ የሚል ፈተና ውስጥ በመክተት ጾር ያጸናባቸዋል፡፡ ብዙዎቻችን የዚህ መንፈስ ሰለባ ስንሆን የምናስባቸው ክፉ ሐሳቦች፣ የምንተገብራቸው መጥፎ ድርጊቶች የእኛ ስለሚመስሉን የመንፈሱን ጥቃት በቀላሉ ለማወቅና ለመረዳት እንቸገራለን፡፡ ይህ የአየር አጋንንት እንኳን እኛን ቅዱስ ጳውሎስን የሚፈልገውን ሳይሆን የማይፈልገውን ሲያሳስበው፣ የማይወደውን ሲያስደርገው እንደ ነበር ‹‹በእኔ የሚያድር ኃጢአት ነው›› በማለት ገልጾታል፡፡ /ሮሜ 7÷15-17/ ይህ የአየር አጋንንት እንኳን ለመተግበር ለሰው ለመናገር የምናፍርበትን ክፉና ጸያፍ ሐሳብ በማመንጨት፣ ክፉ ሐሳቡን በልባችንና በሕሊናችን በመርጨት፣ የራሳችን ሐሳብ እስኪመስለን ድረስ የሚያደርሰን ያልታወቀበት ጥንተ ጠላታችን ነው፡፡ የአየር አጋንንት የክፉ ሐሳብ ችግር ስለሌለበት ከበቁት አባቶች ታች እስካለነው ምዕመናን ድረስ፣ የራሱን ሐሳብ በማዋረስ ይፈትነናል፡፡ በሚሊዮን የምንቆጠረው ክርስትያኖች የፈተና ሁኔታችን ይቀል ይከብድ ካልሆነ በቀር የዚህ መንፈስ ተጠቂ ነን፡፡ የአየር አጋንንት የሰውነታችን ማዕከላዊ መዝገብ በሆኑት በልቦናና በሕሊና ላይ በመቀመጥ፣ በጆሮ ሹክ በማለት ይፈትናል፡፡ ብዙዎቻችንን እንደ ሌሎች አጋንንት ፊት ለፊት እና በውስጥ ሳይሆን በርቀት የሚዋጋ በመሆኑ ለብዙዎቻችን ሁኔታው ግራ ይገባናል፡፡ ፈተናው ስለሚቀያየር አልያዝ አልጨበጥ ይለናል፣ ሕይወታችንን ግን በፈተና ይዞራል፡፡ ከዲያቢሎስ ወገን የሆነው የአየር አጋንንትን ቅዱስ ጴጥሮስ ‹‹ባለጋራችሁ ዲያቢሎስ የሚውጠውን ፈልጎ እንደሚያገሳ አንበሳ ይዞራልና›› ያለው የአየር አጋንንት አንድ ቦታ በመቀመጥ ሳይሆን እያንዣበበ፣ እየዞረ በፈተና ማዕበል ሊውጠን መዘጋጀቱን ያሳየናል፡፡ /1ኛ ጴጥ 5÷8/ ጌታችን በጸሎተ ሐሙስ ከሐዋርያት ጋር በነበረበት ምሽት ቅዱስ ጴጥሮስን ‹‹ስምዖን ስምዖን ሆይ፣ እነሆ ሰይጣን እንደ ስንዴ ሊያበጥራችሁ ለመነ›› በማለት አጋንንት ምን ያህል ሐዋርያትን ለመፈተን እንደተዘጋጀ ያሳያል፡፡ ጌታችን የሰይጣንን ፈተና በሚበጠር ስንዴ መስሎ የነገራቸው የውግያውን ረቂቅነት እና ስውር ስልት ሊያሳውቃቸው ፈልጎ ነው፡፡ ዛሬም እኛ በአጋንንት ፈተና እንደ ስንዴ ተበጥረን መንፈሳዊ ፍሬያችን ጠፍቶ፣ ባክኖ ገለባችን ብቻ ቀርቷል፡፡ /ሉቃ 22÷31/ ኤጲፋንዮስ በመጽሐፈ አክሲማሮስ እንደሚነግረን የአየር አጋንንት የሚባሉት በቀደመው ወራት ሳጥናኤል ቅዱሳን መላእክትን ‹‹እኔ ነኝ የፈጠርኃችሁ›› በማለት ሰማያዊ ሽብር ሲፈጥርባቸው መላእክት ለሦስት ተከፍለው ነበር፡፡ የመጀመርያዎቹ የብርሃን መላእክት የሆኑት በቅዱስ ገብርኤል ቃል በመጽናናት ‹‹የፈጠረንን እግዚአብሔርን እንስክናውቅ እስክናይ ባለንበት እንጽና›› በሚለው ቃል የጸኑ ናቸው፡፡ እነዚህ ቁጥራቸው ከቅዱሳንና ከብርሃን መላእክት ጋር የሆኑ ናቸው፡፡ ሁለተኛው ምድብ በሳጥናኤል ቃል በማመን ‹‹አዎ ሳጥናኤል ነው የፈጠረን›› በማለት ፈጣሪን የከዱ፣ ከሳጥናኤል ጋር በክህደተ እግዚአብሔር የተዛመዱ ናቸው፡፡ እነዚህ ናቸው ሰይጣናት አጋንንት ተብለው የጨለማ ሠራዊት የሆኑት፡፡ ሦስተኞቹ የጸሎት እና የእምነት ጠንቅ የሆኑት ‹‹እግዚአብሔር ነው ወይስ ሰይጣን ነው የፈጠረን?›› ብለው ሳይለዩ፣ በጥርጥር የታዩ ናቸው፡፡ በቅዱስ ገብርኤል ቃል የጸኑት እግዚአብሔር ነው የፈጠረን ያሉት ብርሃናውያን መላእክት ክብርን ተጎናጽፈው ከእግዚአብሔር ጋር በሰማይ ሲቀሩ፤የካዱት ተዋርደው ከሳጥናኤል ጋር ወደ ሲኦል ወርደዋል፡፡ ሦስተኛቹ ተጠራጣሪዎቹ ግን ከእግዚአብሔርም ከሳጥናኤልም/ከሰማይም ከሲኦልም/ ሳይሆኑ በአየር ላይ ቀርተዋል፡፡ ግን ተጠሪነታቸው ለሳጥናኤል መሆኑን ልብ በሉ፡፡ ምክንያቱም ሳያምኑ መጠራጠር፣ ከሳጥናኤል ጋር የሚያስደምር ስለሆነ ከእሱ ጋር ተቆጥረዋል፡፡ እነሱም ‹‹የአየር አጋንንት›› ተብለዋል፡፡ መጽሐፈ አክሲማሮስ ‹‹የተጠራጠሩት በአየር ላይ ቀርተው ዛሬ ነፍስ ከሥጋ ተለይታ ስትወጣ የጻድቃንን ነፍስ እያስደነገጡ፣ የኃጥአንን ነፍስ እየቀጠቀጡ የሚኖሩ የዓየር አጋንንት የሚባሉ ናቸው›› በማለት የአየር አጋንንት በጸሎት ሰዓት ሐሳብን መበተን እና በተለያየ ነገር መፈተን ብቻ ሳይሆን ነፍስ ከሥጋ ስትለይ ነፍሳችንን በማስፈራራት በማሰቃየት የሚያስጨንቁን ናቸው፡፡ /መ.አክሲ ዘረቡዕ ገጽ 136÷46/ በድርሳነ ቅዱስ ሚካኤል ላይ የአየር አጋንንት በደመና/በአየር ላይ ሆነው እንደሚፈትኑን ‹‹የሳጥናኤል ሠራዊት አጋንንት፣ ሰይጣናት ረቂቅነት ያላቸው ከደመና በላይ የሚኖሩ ሰውን የሚያስቱ ርጉማን የተረገሙ በሰው ልቦና ውስጥ ገብተው ተንኮልን የሚያስተምሩ፣ ኃጢአትን የሚያሠሩ እሊህ የሰይጣን ሠራዊት ነፍስና ሥጋ ያላቸው እንዳይመስላችሁ›› በማለት የአየር አጋንንትን ከነ ሥራቸው በሚገባ ተጽፎልናል፡፡ /ድርሳነ ሚካኤል ዘጥር ይመልከቱ/ እንዲሁም ‹‹ሰውን ከማሳት በስተቀር ምንም ስልጣን የላቸውም›› በማለት ሰውን በማሳት የሰለጠኑ፣ የተካኑ መሆናቸውን ይኸው ድርሳን ይነግረናል፡፡
без подписи
ዲያቢሎስ በታላቅ ቁጣ ወደ ምደር ስለመውረዱ በዓለማችን ላይ ስለሚደረጉት ግፍና ኃጢአት፣ በእኛም ላይ የሚደርሱት ፈተናና መከራ ምስክር ናቸው፡፡ ይህን ካልን ሰይጣን፣ አጋንንት፣ ዲያቢሎስ ምን ያህል ለሰው ልጅ የመንፈሳዊ፣ የግላዊና የማህበራዊ ሕይወት መሰናክልና ደንቃራ እንደሚሆኑ ካወቅን፤ ብዙዎቹም የእነዚህ ሰለባ በመሆናቸው ቤተሰባቸውን፣ ትዳራቸውን፣ ሥራቸውን ትምህርታቸው ትተው ያወቁት የነቁት በጸበልና በገዳማት፣ ያላወቁት እና ያልነቁት በሐኪም ቤት ሲንከራተቱ ሲብስም በአልጋ ሲውሉ ስናይ አጋንንት ተፈቶ የተለቀቀበት ዘመን ለመሆኑ ምስክር አያሻም፡፡ ደግሞስ ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱ ‹‹ዓለም በሞላው በክፉው መንፈስ እንደተያዘ እናውቃለን›› ብሎን የለ፡፡ /1ኛ ዮሐ 5÷19/ ወዳጆቼ መጽሐፍ ቅዱስ ትልቅ እና ሰፊ ሽፋን ሰጥቶት ጌታም ሐዋርያትም ከሰዎች ያስወጡት አጋንንት ‹‹የለም፣እኔን አይፈትነኝም›› ብሎ በራስ ከመመካት የፈተናችን ዙርያ ገብ መቃኘት እና የአጋንንቱን ፈተና በጸሎት ኃይል ለመግታት መታገሉ የተሻለ ነው፡፡ ‹‹ከትውልዱ ማን አስተዋለ?›› ት.ኢሳ 53÷8 በቀጣይ ክፍል ሁለት የአየር አጋንንት የሚባሉት የትኞቹ ናቸው? ይቀጥላል …… @delilamedia
የአየር አጋንንት ውጊያ በጸሎት ጊዜ ክፍል 1 መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዲያቢሎስ፣ ሰይጣንና አጋንንት ምን ይላል? በቀሲስ ሄኖክ ወ/ማርያም (share ተወዳጆች ሆይ ያለመታደል ሆኖ በሥጋ ተማርን አወቅን የሚሉት ምሁራን፣ ፈላስፎች ስለ ሰይጣን ያላቸው ግንዛቤ እጅጉን ያሳዝናል፡፡ እነዚህ ሰዎች የሰው ልጅ ጠላት የሆነውን ሰይጣንን ‹‹ሰይጣን የለም፣ ቤተ እምነቶች በምዕመናኑ ላይ የፈጠሩበት ምናባዊ ምስል ነው፣ ከእምነት ተቋማቸው እንዳይወጡ፣ በፍርሃት እንደ ተዋጡ እንዲኖሩ የሚያደርጉት ማስፈራሪያ እና ማሠሪያ ነው›› እያሉ በገሃድ ሲናገሩ፣ በመጽሐፎቻቸው ሲጽፉ ይታያል፡፡ እጅጉን የሚገርመው ነገር በዓለም ላይ ስለ ቅዱሳን መላእክት እና ስለ ሰይጣናት የተጻፉትን መጻሕፍት ብንመዝናቸው ‹‹የሉም፣ ምናብ ናቸው›› ስለሚሉት ስለ ሰይጣን የተጻፈው መጽሐፍ እጅጉን ይበልጣል፡፡ ለማነጻጸር እንኳን አይቻልም፡፡ ምዕራባውያን ትላንት ምናብ ነው የሚሉትን አጋንንት ዛሬ ዛሬ ማምለኪያ ቤት ሠርተውለት በፊልሞቻቸውም ሰፊ ሽፋን ሰጥተውት በሰይጣንኛ ይተውናሉ፡፡ ስለ መናፍስት የሚሠሩትም ፊልሞች ከፍተኛ ተመልካችና ገቢ የሚያስገኙ ናቸው፡፡ የእኛም አገር ወጣቶች አጋንንታዊ፣ አስማታዊ ዘውግ ያላቸውን ፊልሞች በተመስጦና በጉጉት ያያሉ፡፡ እንግዲህ ለሰይጣን እንዲህ እየሆኑለት ‹‹የለም፣ ምናብ ነው›› ይሉታል፡፡ እሱ ግን አለ ሲሉት በገሃድ፣የለም ሲሉት ተመችቶት በስውር የሰው ልጆችን ለአሳር መዳረጉ አልቀረም፡፡ ደግሞም የሰይጣን ትልቁ ጥበቡ አለሁ አለማለቱ ነው፡፡ ሰዎች አለ ሳይሆን የለም ሲሉት ነው እሱ ግን መኖሩን ልክ ነፋስ ሳይታይ ዛፍን እንደሚያንቀሳቅስ እሱም ሕይወታችንን በፈተና በመከራ በማቃወስ ይገለጣል፡፡ ወዳጆቼ እስኪ በመጀመርያ ስለ አጋንንት፣ስለ ሰይጣን፣ስለ ጋኔንና ስለ ዲያብሎስ በብሉይ ኪዳን እና በሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ላይ ያላቸውን ገጽታ ዘርዘር አድርገን እንመልከተው፡፡ በብሉይ ኪዳን ላይ ‹‹አጋንንት›› 6 ጊዜ ‹‹ሰይጣን›› 16 ጊዜ ‹‹ጋኔን›› 1 ጊዜ ስማቸው ሲጠቀስ ዲያብሎስ እስከነ ጭራሹ ስሙ የለም/አልተጠቀሰም፡፡ በሐዲስ ኪዳን ላይ ‹‹አጋንንት›› 50 ጊዜ ‹‹ሰይጣን›› 34 ጊዜ ‹‹ጋኔን›› 22 ጊዜ ‹‹ዲያቢሎስ›› 33 ጊዜ ስማቸው ተጠቅሷል፡፡ እነዚህ ሁሉ ስማቸው ቢለያይም ሥራቸው ተንኮላቸው አንድ ነው፡፡ የሚለያቸው ደረጃቸው፣ የመፈተን አቅማቸውና በሲኦል ባላቸው እሳታዊ ስልጣን ነው፡፡ የሚገርመው በብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ላይ አጋንንትን ጋኔንን ሰይጣንን፣ ዲያቢሎስን ከሰዎች ላይ ስለማውጣት የሚናገር የለም፡፡ እንደ ሐዋርያት አጋንንትን ከሰው ላይ አውጥቶ የፈወሰ ነብይ አልተጻፈም፡፡ በመጽሐፈ ጦቢትና በድርሳነ ሩፋኤል ላይ የምናገኘው ታሪክ ቅዱስ ሩፋኤል አስማንድዮስ የተባለ ገዳይ ጋኔን ከወለተ ራጉኤል/ሳራ/ ጭን ላይ በጦብያ አማካኝነት እንደወጣ ተጽፏል፡፡ ጋኔኑ ወጣ የተባለበት መንገድ ጋኔኑ በባሕሪው ይጠላው በነበረው፣ በመልአኩ የተባረከው የዓሳ ጉበት፣ ልብ ከዕጣን ጋር ተደባልቆ ቢጤስበት ነው የለቀቀው፡፡ ይህ አሠራር ደግሞ አሁን የሚተገበር ሳይሆን የሚሞከር አይደለም፡፡ እንዲሁም ብላቴናው ዳዊት ሳኦልን ያስጨንቀው የነበረውን ‹‹ክፉ መንፈስ›› ተብሎ የተገለጸውን የጭንቀት መንፈስ በገና እየደረደረ እየዘመረ ሳኦልን ደስ ያሰኘውና ያሳርፈውም ነበር፡፡ በዚህ በዳዊት የዝማሬ ጸጋና የበገና ጥዑም ድምጽ ሳኦልን ይረብሸው የነበረው ክፉ መንፈስ እየበረገገ ከሳኦል ይርቅ እንደ ነበር ተጽፏል፡፡ /1ኛ ሳሙ 16÷23/ እዚህ ላይ የቅዱስ ዳዊት አገልግሎት እንደ ሐዋርያት አጋንንቱን በማናዘዝ፣በማውገዝ እና በማዘዝ ‹‹ውጣ›› በማለት ሳይሆን በዝማሬው ሞገስ ነው ያርቀው የነበረው፡፡ ዳዊት በበገና ጥዑም ዝማሬ ያርቀው የነበረው በጭንቀት የተመሰለው የአየር አጋንንት በተደጋጋሚ እየመጣ ሳኦልን ያስቸግረውና ዳዊትን ያለፋው ነበር፡፡ በመጨረሻም ዳዊት ከሳኦል ላይ ያርቀው የነበረው ክፉ መንፈስ ዳዊት ላይ አቂሞ በሳኦል አድሮ በጦር ወግቶ ለመግደል ጦር እስከ መወርወር ደርሶ ነበር፡፡ አቅሙን ያወቀው ዳዊትም በሳኦል ላይ ያደረውን አጋንንት ከመዋጋት ይልቅ ከፊቱ ዞር በማለት አምልጦታል፡፡ /1ኛ ሳሙ 19÷-9-10/ በሐዲስ ከዳን ላይ ግን ጌታችን ነው ለመጀመሪያ ጊዜ አጋንንትን፣ ሰይጣንን፣ ጋኔንን ከሰው ማውጣት የጀመረው፡፡ ሐዋርያትም ጌታቸውን ተከትለው አሱን አብነት አደርገው ነው አጋንንተን ሰይጣናትን ማውጣት የጀመሩት፡፡ በእርግጥ በብሊይ ኪዳን ላይ ሰይጣን ኢዮብን እንደ ከሰሰው በመጽሐፈ ኢዮብ 2÷3-7 ላይ ተጽፏል፡፡ እንዲሁም ኢያሱን በእግዚአብሔር ፊት ሰይጣን ሊከሰው እንደመጣ በት.ዘካርያስ 3÷1-2 ላይ ተጽፏል፡፡ ከዚህ ውጪ ሰይጣን በእስራኤል ላይ እንደተነሳ ተጽፋል፡፡ ስለዚህ ሰይጣን ሕዝባዊ ጠላት እና ጥፋት አምጪ ሆኖ እንጂ ግለሰብን የሚያሰቃይ ሆኖ ብዙም አልተገለጠም ነበር፡፡ በሐዲስ ኪዳን ላይ ግን ሰይጣን ፍጹም መንገዱን በመለወጥ በብሉይ ኪዳን ዘመን የነበረውን የተንኮል ገጽታውን በመቀየር ብሶበት፣ በረቀቀ የፈተና ስልት መጥቷል፡፡ ሰይጣን በሐዲስ ኪዳን ዘመን ጌታችንን ፈታኝ ሆኖ ታይቷል፡፡ ማቴ 4÷1-10 ተወዳጆች ሆይ ጌታችን ለደቀ መዛሙርቱ ከካህናት አለቆችና ከጻፎች ከሽማግሎች ብዙ መከራ ተቀብሎ እንደሚሞትና በሦስተኛው ቀን እንደሚነሳ ሲነግራቸው የዋሁና ከቅንነቱ የተነሳ የሚቸኩለው ቅዱስ ጴጥሮስ ጌታችንን ወደ እራሱ አስጠግቶት ‹‹ጌታ ሆይ ይህ ከቶ አይደርስብህም›› ሲለው ጌታችንም ‹‹ወደ ኋላዬ ሂድ አንተ ሰይጣን፤ የሰውን እንጂ የእግዚአብሔርን አታስብምና እንቅፋት ትሆንብኛለህ›› ተብሎ በግልጽ ላየው ቅዱስ ጴጥሮስን በስውር ላየው ደግሞ ቅዱስ ጴጥሮስ አንደበት ላይ ሆኖ አዛኝ አንጓች የሆነው ሰይጣን ተሰድቧል፡፡ /ማቴ 16÷21-23/ ሰይጣን ከተንኮለኝነቱ አንጻር ደግሞ የቃለ እግዚአብሔር ሌባ እንደሆነ በማር.4÷14 ላይ ሰይጣን በሰው ልብ በመግባት የራሳችን ሐሳብ በመሰለ ሐሳብ እራሱ ለሚፈልገው አላማ ምን ያህን እንደሚጠቀምበን በሉቃስ 22÷3 ላይ ቅዱስ ጳውሎስን በሕመም ይጎስመው እንደነበር በ1ኛ ቆሮ 12÷7 ላይ የብርሃን መልአክ መስሎ ሰዎችን እንደሚያስት 2ኛ ቆሮ 11÷14 ላይ ለማገልገልና በጎ ነገር ለመሥራት እንደሚያዘገይ እና እንኳን እኛን ቅዱስ ጳውሎስን እንዳዘገየ በ1ኛ ተሰሎ 2÷18 ላይ ዓለሙን ሁሉ የሚያስተው እርሱ እንደሆነ በዮሐንስ ራዕይ 12÷9 ላይ ሐሰተኝነት፣ በዓመጽም ማታለል፣ ሐሰተኛ ምልክቶችን ማሳየት የሰይጣን ሠራር እንደሆነ በ2ኛ ተሰሎ 2÷9-10 ላይ ሃይማኖታችንን ትተን መልካም ምግባር ሳንሠራ ከቀረን ለሰይጣን ከተዘጋጀው የእሳት መኖርያ ውስጥ አብረን እንደምንኖር በማቴዎስ 25÷41 ላይ ተጽፏል፡፡ ወዳጆቼ አጋንንት ሰዎች ላይ የተለያየ ደዌና ሕመም በመሆን ያሰቃዩ ስለነበር ጌታችንም ሐዋርያትም በሰፊው ከሰዎች እንዳስወጧቸው ቅዱስ መጽሐፍ መዝግቦልና፡፡ አጋንንት በሚገርም ሁኔታ ሰዎችን እንደ ቤታቸው ማደርያ አደርገዋቸው ምን ያህል ያሰቃይዋቸው እንደ ነበር ሐዲስ ኪዳን ላይ በሰፊውና በዝርዝር ተቀምጧል፡፡ ዲያቢሎስም በሐዲስ ኪዳን ላይ ክፋቱና ተንኮሉ ተዘርዝሯል፡፡ የሚገርመው ደግሞ የዘመኑ ፍጻሜ እየቀረበ ስለሆነ ዲያቢሎስም ዘመኑ እያለቀበት ስለሆነ ቅዱስ ዮሐንስ ‹‹ዲያቢሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቁጣ ወደ እናንተ ወርዷል›› በማለት ጽፎልናል፡፡ /ራዕ 12÷12/
без подписи
без подписи
без подписи
📌 ርዕስ፡ የእመቤታችን ተአምራት በሕይወታችሁ... ✨ ሰላም ለእናንተ ይሁን የደሊላ ሚዲያ ቤተሰቦች! የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትና ረድኤት የማይነገር፣ ቸርነቷም የማይታክተው ነው። በቃና ዘገሊላ የጎደለውን እንደሞላች ሁሉ፣ ዛሬም በልጇ ፊት ሆና ለሁላችንም ትለምናለች። በመሆኑም ዛሬ አንድ ጥያቄ ልንጠይቃችሁ ወደድን፡ ❓ በሕይወታችሁ የእመቤታችንን ረድኤት፣ ልዩ ጥበቃና አማላጅነት በተጨባጭ ያያችሁበትና ፈተናችሁ ወደ ደስታ የተቀየረበት አጋጣሚ አለ? የእመቤታችንን ክብር ለመመስከርና ለሌሎች ተስፋ ለቆረጡ ወንድሞችና እህቶች ትምህርት እንዲሆን፣ ያያችሁትን በረከት በኮሜንት (Comment) ስር አጋሩን። 👇 📺 የበለጠ መንፈሳዊ ትምህርቶችንና የቅዱሳን ታሪኮችን ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናላችንን ይጎብኙ፦ 👉 [https://youtube.com/@delilamedia?si=30u55Sm0lZq_Ntkt] ✅ ይህ መልእክት ለብዙዎች እንዲደርስ Like እና Share ማድረጋችሁን አትርሱ። #DelilaMedia #ድንግልማርያም #ተአምር #አማላጅነት #ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ #ኢትዮጵያ