Tewhid || توحيد
Статистикаይህ ቻናል ሀዲሶች ፣ ቁርአኖች ፣ ጠቃሚ ምክሮች ፣ መልዕክቶች የሚለቀቁበት ነው። https://t.me/Tawhid_100
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 16
- Всего постов
- 28
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 7
- 1/48двое суток
- 8
- 1/72трое суток
- 8
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
без подписи
🌀 ለቻነል ባለቤቶች በሙሉ👇 👉ኑ በነፃ 💯 ቻነል እናሳድጋለን ፈጥነው ያስመዝግቡ 📥 ለ ተወሰኑ ቻነሎች ብቻ ቦታ አለን 🏃♂➡️ 🧩Folder 1👇 🎯Above 300+ subscribers✅ 🧩Folder 2👇 🎯 Above 500+ subscribers✅ 🧩Folder 3👇 🎯Above 1k+ subscribers✅ 🌀 ቻናል ለማስመዝገብ አናግሩኝ ... ........ 👇👇........... ...... @selluhi ለሽያጭ የቀረቡ ኢስላማዊ ቻናሎችም አሉ
ጥያቄ 🤔❓ በሱረቱ አል-ከህፍ ውስጥ የተጠቀሰዉ የአስሃቡል ከህፍ ታሪክ ብቻ ነው ? Wave👉 @selluhi
без подписи
ከበረዓ ቢን ዐዚብ ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦ ﴿كنّا معَ رسولِ اللَّهِ في جِنازةٍ، فجلسَ على شَفيرِ القبرِ، فبَكى، حتّى بلَّ الثَّرى، ثمَّ قالَ: يا إِخواني لمثلِ هذا فأعِدُّوا﴾ ❝ከእለታት አንድ ቀን ከረሱል ጋር በአንድ ጀናዛ ላይ ነበርንና ቀብሩ ጫፍ ላይ ተቀምጠው አፈሩ እስኪርስ ድረስ አለቀሱ። ከዛ እንዲህ አሉ፦ ‘ወንድሞቼ ሆይ! ለእንዲህ ዓይነት ቀን ተዘጋጁ።❞ 📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል፡ 3402 ➥https://t.me/sunah_channel
ከፊሉ ልጅ የለኝም ብሎ ያለቅሳል። ሌላውን ልጁ ያስለቅሰዋል። ከፊሉ እህት ወንድም የለኝም ብሎ ይከፋዋል። ሌላው በእህት በወንድሞቹ ውስጡ ቆስሏል። ዱንያ አጃዒቧ አያልቅም። ግማሹ በመከራ፣ ሌላው በጥጋብ ያለቅሳል። "እናቱ የሞተችበትና፣ ገበያ የሄደችበት እኩል ያለቅሳል" በሚለው አገርኛ ብሂል ውስጥ ህመም አለ። መከራ ሁሉ አንድ አይደለም። ከባሰም በላይ ብዙ የባሰ እንዳለ በማስተዋል "አልሐምዱ ሊላህ" እንበል። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
°ውዱን ቀናችሁን የተዋበና የፈካ ለማድረግ የማለዳ ስንቅ 🎧 ለቀልባችሁ እንዲሆን አጫጭር የ ቁርአን ቲላዋዎችን የምንለቅበት ቻነል👇
ጥያቄ 🤔❓ በሱረቱ አል-ከህፍ ውስጥ የተጠቀሰዉ የአስሃቡል ከህፍ ታሪክ ብቻ ነው ? Wave👉 @selluhi
ዑመር ብኑል ኸጧብ ረዲየላ፞ሁ ዐንሁ እንዲህ ብለዋል:– (إنّ لهذه القلوب إقبالًا وإدبارًا، فإذا أقبلت فخذوها بالنوافل، وإن أدبرت فألزموها الفرائض). "ልቦች መነቃቃትና መቀዛቀዝ አላቸው። ሲነቃቁ በትርፍ ዒባዳዎች ያዟቸው። ሲቀዛቀዙ ደግሞ በግዴታዎቹ አስገድዷቸው።" [መዳሪጁ ሳ፞ሊኪን: 2/318]
📌ለደረቀችው ልቤ! 🎙በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የቀጥታ ስርጭት ተጀመረ! 👇👇 https://t.me/Sle_qelbachn1?livestream=4b7952a17ac57f8cf5
መውሊድ ለምን አላማ እንደተጀመረ ያውቃሉ? ~ መውሊድ በሺዐዎች እንደተጀመረ ቀደም ብየ ገልጬ ነበር። አሁን ደግሞ ለምን አላማ ጀመሩት የሚለውን ባጭሩ እዳስሳለሁ። በግብፅ የአስዩጥ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት የነበሩት ዶክተር ሐሰን ኢብራሂም ሐሰን እና በሃገሪቱ የትምህርት ሚኒስቴር የማህበራዊ ትምህርቶች ገምጋሚ የነበሩት ጦሀ አሕመድ ሸረፍ በጋራ በመሆን “አልሙዒዝ ሊዲኒላህ” በሚል ርእስ ስለ“ፋጢሚያዎቹ” ንጉስ ጥልቅ ጥናት በማድረግ አንድ መፅሐፍ አዘጋጅተዋል፡፡ በዚህ መፅሐፍ ውስጥ “አውደ - አመታት እና በዓላት” በሚል ርእስ ስር ያሰፈሩት ሃሳብ “መውሊድ ለምን አላማ ታስቦ ነው የተጀመረው?” ለሚለው ጥያቄ ጥሩ ምላሽ ይሰጣል፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት፡- “(ንጉሱ) አልሙዒዝ በሂጅራ አቆጣጠር የመጀመሪያው ቀን፣ በነብዩ ﷺ መውሊድ ቀን፣ በረጀብ መጀመሪያና አጋማሽ ላይ፣ በሸዕባን መጀመሪያና አጋማሽ ላይ፣ በረመዷን መጀመሪያ ቀን ከሚያስተዳድራቸው ህዝቦች ጋር ይካፈል ነበር፡፡ ይህን የሚያደርገው * የሱኒ፞ዮቹን ልብ ለማረጋጋት፣ * እንዲሁም በሱኒ፞ዮች መርሆዎችና በሺዐዎች እምነቶች መካከል ያለውን ርቀት ለማጥበብ በማሰብ ነው፡፡ * በተጨማሪም ይሄ አልሙኢዝ ሊዲኒላ፞ህ የንግስና ዘመኑን ያሸበረቀባቸውን እነዚህን በዓላት የኢስማዒሊያ ሺዐ መዝሀብ እምነቶችን ለማሰራጨት ይጠቀምባቸው ነበር፡፡ ለዚህም ነበር የሑሰይንን ዝክር ህያው ለማድረግ የዓሹራእ ቀንን ያከብር የነበረው፡፡ ልክ እንዲሁ የበርካታ አኢማዎችን መውሊድና ስልጣን ላይ ያለውን ገዢ መውሊድ በሚልም (የራሱን ልደት) ያከብር ነበር፡፡ * ልክ በዚህ መልኩ የህዝቦቹን ትኩረት ወደሱ ለመሳብና የኢስማዒሊያ ሺዐ መዝሀብ መሰረታዊ እምነቶችን ለማሰራጨት እነዚህን በዓላት እንደ መዳረሻ ይጠቀምባቸው ነበር፡፡” [አልሙዒዝ ሊዲኒ'ላህ፡ 284] ስለዚህ መውሊድ የተጀመረው ለፖለቲካዊ ትርፍና የሺዐን እምነት ለማስፋፋት ዓላማ ነው ማለት ነው፡፡ የክርስቲያኖቹ ገና፞፣ ሁዳዴ፣ …፣ የሺዐዎቹ የዓሹራእ በዓል፣ ገዲር ኹም፣ …፣ የእሳት አምላኪ መጁሳዎቹ ነይሩዝ ይከበሩ ከነበሩት በዓላት ውስጥ ነበሩ፡፡ የህዝብን ትኩረት ለመሳብ፣ ቅሬታ ውስጥ ያሉ ሱኒ፞ዮችን ልብ ለማረጋጋት በሂደትም ወደራሱ የሺዐ እምነት ሰዎችን ለማስገባት በማለም ነው፡፡ ቀስ እያለ በጉልበት ወደ ሺዐ እምነት መጣራት እንደተጀመረ ይታወስ፡፡ ስለዚህ አላማቸው ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡትን የህዝብ ግፊቶች በማርገብ ይከተሉት የነበሩትን የኢስማዒሊያ ሺዐ እምነት ማስፋፋት ነበር፡፡ ይሄ ደግሞ ዛሬ ሱፍዮች እንደሚያስቡት “የወሃብዮች” ፕሮፓጋንዳ ሳይሆን ከላይ እንዳየነው የታሪክ አጥኚዎች ድምዳሜ ነው፡፡ የመውሊድ ስርኣቱ ለእኩይ አላማ የታለመ ስለነበርም ነው ሶላሑዲን አልአዩቢይ ሺ0ዎችን አስወግዶ ግብፅን ሲቆጣጠር አስቁሞት የነበረው፡፡ መቼም እሱንም “ወሃቢ ነው” እንደማትሉ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ ዳግም የተጀመረው ኋላ በመምሉካውያን ጊዜ ነው፡፡ የመውሊድ ተግባር እንደገና ሲመለስ ሌሎቹ በአላት የሌላ እምነት መሰረት ያላቸው ወይም ሺዐ-ዘመም ስለነበሩ በሱኒ፞ው አለም ገበያ አላገኙም፡፡ ዛሬም የሙስሊሞችን መብት የሚጨፈልቁ የፖለቲካ ኃይሎች አጉል ተቆርቋሪ ሊመስሉ ለመውሊድ የተለየ ሸፋንና ድጋፍ ሲሰጡ ማየት የተለመደ ነው። ብልጥ የሆነ ሰው ሊያስተውል ይገባል። አላህ ማስተዋሉን ይስጠን። = የቴሌግራም ቻናል፦ https://t.me/IbnuMunewor https://t.me/IbnuMunewor
“ሁኔታህን ብታስተውልማ … አላህ አንዳንድ ነገሮችን ሳትፈልጋቸው ሰጥቶሀልኮ። የፈለግከውን ጉዳይ ሲከለክልህ ደግሞ… በዚያ መከልከል ውስጥ አንተ ያላወቅከው መልካም ነገር ስለመኖሩ እርግጠኛ ሁን።” ኢብኑል ቀይዪም
በሁሉም ነገር ላይ ዘበኛ አትሁን… ሁሉንም በተጠንቀቅ አትከታተል…አንዳንድ ነገሮች ይሂዱ ተዋቸው… ሌሎቹም ይለቁ አታቋርጣቸው… በነገሮች መለዋወጥ ውስጥ ተደሰት… ምናልባት ሰዎች የማይገነዘቡት ታላቅ የአላህ ጥበብ ይኖረዋል…