tgindex
✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘

Статистика

የጥበብ አፍቃሪ ኖት እንግዲያውስ ትክክለኛውን ቻናል አግኝተዋል። በቻናላችን 👉 በኔና በሌሎች የተፃፉ 👉ግጥሞች🌸 🌹ወጎች 🌸 🌹ልቦለዶች 🌸 አዝናኝ አስተማሪ ታሪኮችና ሌሎች ፅሁፎችን ያገኛሉ... ━━━━━━━━ ✦ ለማንኛውም አስተያየት @itsmetsita Paid Promotion @Tsiyon_awit ይጠቀሙ። Join us @Tsion_liboled

Последний пост
14 авг.
Последнее чтение
15 авг.
Постов за неделю
6
Всего постов
22
Тип
открытый
Язык
am
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
8 119
−4 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
2 111
21 постов
Вовлечённость
26,0%
к подписчикам
Постов в день
0,9
всего 22
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
694
1/48двое суток
795
1/72трое суток
857

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ለ 2 ሳምንት ብቻ የሚቆይ ከ 15% - 18% ልዩ ቅናሽ በዋና ሼልፎች ላይ! የሱቅ ኪራይ እና ግብር አስጨንቆዎታል? መገናኛ Zefmesh Mall በሚገኘው የሴቶች material ሱቃችን ኦሪጅናል ዕቃዎን ብቻ በማምጣት መሸጥ ይጀምሩ! ለኦንላይን ነጋዴዎች ትልቅ ዕድል እኛ የምናሟላቸው አገልግሎቶች፦   ✅ ንግድ ፈቃድ አያስፈልግዎትም   ✅ የሽያጭ ባለሙያ (Salesperson) ከእኛ   ✅ ነፃ ፕሮሞሽን የቦታ ኪራይ በወር (ከቅናሹ በፊት ያሉ ዋጋዎች): * 40x40 ሼልፍ:** 3,000 ብር * 40x60 ሼልፍ:** 3,500 ብር * የዕቃ መረከቢያ (Pick-up): 1,500 - 2,000 ብር (ከ Shein/Amazon ለሚያመጡ የተዘጋጀ) ቦታችን ውስን ስለሆነ ፈጥነው ይመዝገቡ! 📞 0904405974 💬 Telegram: @meronterefe

  • "ልጄ የእኔን ኑሮ አይታ እንደእኔ ኖረች... እኔ ደግሞ አሁን የልጄን ሞት አይቼ እንደልጄ እሞታለሁ..." ወደተንጠለጠለችበት ቦታ ሄድኩ አይገርምም እሷን እንጂ ገመዱን አላወረዱትም ነበር... ለብቻ ይህን ወረቀት መቃብሬ ላይ እንደፎቶ እንዲለጥፉት የሚጠይቅ ፅሁፍ ያፃፍኩትን እንዲያዩት አስቀምጬ ወንበሩን አመጣሁና የልጄን መንገድ ተከተልኩ... ልትሞት አንድ ሐሙስ የቀራት አሮጊት ምን ልሁን ብላ ነው እራሷን የምታጠፋው? እንደሚሉኝ አውቃለሁ ግን አሁንም እነሱ፦ መኖርን እንጂ ሕይወትን አላዩም። ከዚህ በላይ ላወራችሁ አልችልም... ምክንያቱም እግሮቼ የረገጡትን ወንበር ለቀው በመፍጨርጨር ላይ ናቸው! ✍ሌዊ @lewi_derest

  • አሁንም ሲገባኝ ለውሸትም እውቀት ያሻዋል ለካ... ኸተማሪ ቤት ፅሁፍ ብቻ ሳይሆን ነገሮችንም ማንበብ ያስተምሩ ኑሯል ለካ? ልጄን ሳይ ግን ይህ የግል ችሎታ እንጂ ኸተማሪ ቤት የሚሰጥ እውቀት አልነበረም። ከልቤታ ጋር ሦስተኛ ወራችን ላይ ደረስን ግን አንድ ወር እንኳን በቅጡ ቀለም አልተማርኩም... ስነካካው ሲነካካኝ ስሜታችን ከኮከባችን ገጥሞ ከንፈር ተቃመስን... አሳሳሙ ጥበብ ነበረው... ከዚህም አለመማሬ ያጎደለኝ መስሎ ይሰማኝ ነበር... ቀጠሯችን ከቀለም ትምህርት ወደ ፍቅር አርነት አደረሰን... ከቀናችን በአንዱ ቀን... የልቤታ እንዳለኝ ክርስቶስን የሰቀሉት በእለተ አርብ ነው... ፍቅሬንም ይሰቅሉት ዘንድ...ከስስት ተራክቧችን በዓይኖቻቸው አሰናከሉን። ቄስ መሸሻ አውሬ እንዳዩ ሁላ ኡኡ አሉ... "በለተ አርቡ?! አቤቱ መሐረነ!..." የማይገባኝን ግዕዝ እየተረቱ ወደመጡበት ተመልሰው ሮጡ... የኔታ የልቤታ ሆነበት ቀኑ ማታ ሰማይ ከምድሩ ሊጥሉት አበሩ ፍቅሬ ተሰቅሎ ሄደ እኔን ጥሎ ወዴት እንደሆነ አላውቅም... ሲሮጡ የታጠቁትን ተረት በልቤታ አየሁት... እየሮጠ ቢታገለው አልታሰር ብሎት በብስጭት ቀበቶውን መዞ ወዲያ ወርውሮት ሱሪውን በእጁ ጨብጦ እሮጠ... አነሳሁት ቀበቶውን በልብሴ ሸሽጌ ከልብሶቼ መሀል ዶልኩት። ደንግጬ ቤቴ ተሰብስቤ በተቀመጥኩበት ስሜን እየጮኸ ሲጣራ ሰማሁት... ባዶ እግሬን እየሮጥኩ ስወጣ... እየተጣደፈ "እንቺ... እንቺ" እያለ ወረቀት ያውለበልባል እሱጋር ስደርስ... "ይሄንን ደብዳቤ ለምለም ጋር ይዘሽላት ሂጂና...." አውርቶ ሳይጨርስ አባቱ ከማዶ ሽመላቸውን እያወናጨፉ "ና ብዬሀለሁ ዛሬ!" እያሉ ይሮጣሉ... እሱም ሳይጨርስልኝ ትቶኝ እሮጠ... እስካሁን ግን ምን ግራ እንደሚገባኝ ታውቃላችሁ... ቄስ መሸሻ እሱን እንጂ እኔን አለማየቱ... አባቱ ልጁን ማባረሩ እንጂ እኔ ጋር መቆሙን አለማየቱ... ማን ትሆን እያሉ ሲዘብቱ ሰምቻቸው አውቃለሁ! ለነገሩ የሚጥሉትን እንጂ የወደቀውንማ ለምን ብለው ያስተውሉታል... አለመማሬ የጣለኝ እኔ ከዓይናቸው አልገባ ብያቸው! ከለመድናት ዛፍ ልሄድ ልቤ ይሻፍድብኛል... እዛ ቢያገኙኝ ደግሞ ያውቁብኛል ብዬ እየፈራሁ እቀራለሁ። የሰጠኝን ወረቀት አገላብጣታለሁ... ያኔ የተሰማኝ የመሰበር ስሜት ተሰማኝ አሁንም አላነበብኳቸውማ! ለምን ደብዳቤውን ለለምለም ውሰጂላት አለኝ... እኔን ቸው እንኳን ሳይለኝ ለእሷ ደብዳቤ ፃፈላት? ለነገሩ በድንቁርና ካለች ሴት ምን አለው... እወድሻለሁ ብሎ ፅፎላት ይሆን? በእኔ አለመማር እየቀለደላት ይሆን? እንዴት ሲያደርገኝ እንደነበር በጉራ እየነገራት አንቺ ብትኮሪብኝም.. እያላት ይሆን? ለምን ከእኔ ይልቅ ለእሷ ደብዳቤ እስከመፃፍ ቅድሚያ ሰጣት?.... ይህን ሁሉ የሚያስቀባጥረኝ አለመማሬ ነው። ከወራት ብኋላ መታመም ጀመርኩ... ሆዴም ጤነኛ አልመስልሽ አለኝ... እየጠላኋትም ቢሆን ለምለምን አወራኋት... "አንቺ ነበርሽ?" አለችኝ ደንግጣ "ምኑ?"አልኳት ግራ እየተጋባሁ እኔ እኮ እንዴት እንደሚያደርገኝ ነው የነገርኳት "ማነው ይሄ ከዲያቆኑ ጋር ባለገች ምናምን ተብላ እየፈለጓት የነበረችው ሴት" አለችኝ ደነገጥኩ እቺማ ቀለም ብቻ ሳይሆን ጥንቁልናም ተምራለች.... ከእኔ ይልቅ ቅንሀቴና ጥላቻዬ በልጦብኝ "ስሙን አታቂውምና ነው?" አልኳት "ኧረ አቀዋለሁ ቢልልኝ አይደል ድቁናው ከክወናው ጋር አልገጥም ቢለኝ ነው እንጂ" አለችኝ ቅናት ተንገበገብኩ... የሆነ ነገር ባይኖራቸውማ እንዲህ አትናደድበትም ነበር እሷ ቄስ አይደለች እንዴት ዝም ብላ ትናደድበታለች? አሃ አሃ ባለፈው ማዕዱን እንዳበላሁት ነግሯት ነዋ... እንደዛ... ጭስስ ብዬ ትቻት ስሄድ "ለማንኛውም አርግዘሻል!" አለችኝ ስሙልኝ ይመስል እየጮኸች "ምን?" ብዬ ስዞር  "አዎ አርግዘሻል" አችኝ... ሆዴን አየሁት እንደዛ ነው ሲባል ሰምቼ አውቃለሁ ትዝ አለኝ የሚያቅለሸልሸኝ ነገር... ለእኔም ሽመል ሳይመዘዝ ብዬ ወደአዲስ አበባ ጠፍቼ መጣሁ... የማላቀው ቦታ አውቶብዙ አምጥቶ አራገፈኝ... በስተርግዝና ጎዳና ሳድር ያዩኝ የአከባቢው ሰው ተሰባስበው ብር እና እቃ አዋተው ቤት ተከራዩልኝ... "ትውለድና ስትጠነክር እኔቤት እየመጣች ልብስ ትጠብ እከፍላታለሁ..." ትላለች ሌላዋም እንደዛው ያልጠበኳትና ያልፈለኳትን ልጅ ወለድኩ... ግን በቃ ከሆነ አይቀር እሷም የእኔን ድኝቁርና እንዳትኖረው ነፍሴንም ሽጬ ቢሆን አስተምራታለሁ አልኝ ዓይኖቿን ሳይ እሷ ግን በግድ ያንቺን ኑሮ ካልደገምኩ ትለኛለች.... መማር አትፈልግም ምን ጉድ እንደሆነች... ባለመማሬ ሲበሰጨኝ መኖሬ ሳያንስ በእሷ ያለመማር ፍላጎት ሲበሰጨኝ መሞቴ ነው.... ማንበብና መፃፍ እንደቻለችልኝ ሳውቅ... ልጄ ደረሰች አደገችልኝ ስል... ያኔ በነፍሴ እሷን ብቻ አንጠልጥዬ የወጣኋትን ደብዳቤ እንድታነብልኝ ጠርቻት ተቀመጪ ብያት ሳበቃ አባትሽ እንዲህ ባለጌ ነበር የምላት እየመሰለኝ... እኔ ላይ እንዴት እንደቀለደብኝ እየሰማሁ መድማቱ እያስፈራኝ መልሼ ተይው በቃ እላታለሁ... ልጄ የእኔን ተማሪ ማለት አትወደውም ይባስ ብላ የእኔን እኩያ አገባች... እኔ አፈርኩ የአከባቢው ሰው ግን ኮራባት... ትናንቴን ያውቃሉዋ... ብሩን የተሻለውን ቤት እንጂ ሒወቷን አላዩማ! ወለደች ከበደች... መልሳ ቀለለች! የገዛ ልጄ በጥፊ መታኝ ብላ እራሷን ገመድ ላይ አንጠለጠለች... እንግዲህ ምን ቀረኝ ለልጅ ልጄ እንደሆነ.... "አለሁለት!" የሚል ጉረኛ አባት አለው... እናቱ ስለሞተች ከእኛ ጋር ኑሪ ብሎኝ እነሱ ቤት ገባሁ። ግን የልጄ ጠረን አላስተኛ አለኝ በሕልሜ እየመጣች... "ያንቺን ልጅነት የመኖር ግዴታ የለብኝም ነበርኮ!.. ልጅነትሽን ለመኖር መውለድ አይጠበቅብሽም ነበርኮ! ፀፀትሽን ለምን በእኔ  ንስሃ ትገቢያለሽ?  አንቺ ያጣሽውን እኔ የማግኘት ግዴታ ነበረብኝ? ለምን እንደዛ እንድኖር አደረግሽኝ? አንቺ ልጅነትሽን ስትጭኚብኝ... ወላጆችሽ የሆኑብሽን እየሆንሽብኝ ነው!እነሱን እየጠላሻቸው ለምን እነሱን መሰልሽ?" ትለኛለች አቃተኝ መመለስ አቃተኝ... እሷን መስማት አቃተኝ! ያቺን ደብዳቤ አወጣኋት... ከግቢ ወጥቼ አንዱን ወጣት ጠሩሁትና አንብብልኝ አልኩት... ልክ ወሲብ ስንፈፅም እንደሚለኝ "አሉዬ የኔ ዓለም.." ብሎ ነው መፃፍ የጀመረው ገና ካሁኑ ፀፀት አናቴ ላይ ሲወጣ ታወቀኝ... "አሉዬ የኔ ዓለም... ከክብሬ ጎደልኩልሽ... ከምወደው ድቁናዬ ተሰናከልኩልሽ ግን አልከፋኝም... አንቺ አለሽኝ... ሁሉንም ነገር ነገ አውቶብስ ውስጥ እነግርሻለሁ አሁን ግን ቄስ መሸሻ መምህሮቼን ሰብስቦ አባቴ ጋር ሊመጣ ስለሚችል ጊዜ የለኝም... ነገ ሌሊት ሳፏጭልሽ ውጪ አብረን ወደአዲሳበባ እንጠፋለን... እወድሻለሁ አሉዬ!" ይላል አለኝ... አለቀስኩ በስተርጅና አለቀስኩ.... ፉጨትኮ ሰምቼ ነበር... የመን ስራ ፈት ነው በዚህ ለሊት የሚያጮኸው ብዬ ዘነጋሁት እንጂ... አለመማሬ ፍቅሬን ነጠቀኝ... አጉል ቅናቴ እንጂ እንዳለኝ ለምለም ጋር ወስጄው ቢሆን... ፀፀት አንገበገበኝ... "የኔ ልጅ ላስቸግርህ ጣቶቹ የልቤታ ቀለሙን የከተበበት ወረቀት ላይ ቃሌን ከትብልኝ መፃፍያ ከያዝክ ፃፍልኝ ኸመቃብሬ እንደፎቶ ይለጥፉልኛል" አልኩት.. እየተቻኮለ ከሱቅ ገዝቶ መጣና የነገርኩትን ሁሉ በረቀቱ ላይ ካለው ከፍት ቦታ ፃፈልኝ። ወረቀቷን ይዤ እንዲህ አስባለሁ...

  • ያንቺን ልጅነት የመኖር ግዴታ የለብኝም ነበርኮ!.. ልጅነትሽን ለመኖር መውለድ አይጠበቅብሽም ነበርኮ! ፀፀትሽን ለምን በእኔ  ንስሃ ትገቢያለሽ?  አንቺ ያጣሽውን እኔ የማግኘት ግዴታ ነበረብኝ? ለምን እንደዛ እንድኖር አደረግሽኝ? አንቺ ልጅነትሽን ስትጭኚብኝ... ወላጆችሽ የሆኑብሽን እየሆንሽብኝ ነው !  እነሱን እየጠላሻቸው ለምን እነሱን መሰልሽ? አጋጣሚ    ምዕራፍ ፪ ፎቅ ሳይ፦ የቀን ሰራተኞቹ አፈር እንዳልበሉ ሁላ የተማረ ብቻ የገነባው ይመስለኛል.. እዚቹ ጎረቤቴ አስካልዬ  ጋር እንኳን ሁሌ ቡና የሚፈላው በጥቂቱ ማንበብ በጥቂቱ መፃፍ ስለምትችል ይመስለኛል። እነስኳር.. እነሥጋ... ሽሮ እንኳን ባቅሟ ያልተማረ ቤት ላለመግባት ትግሏ ትግል አይደለም። ለዘመናት ያፈቀርኩት ፍቅሬን ያጣሁት ባለመማሬ ነዋ... ማህፀኔ እንኳን ሳይቀር ስህተት የሆነው  ባለመማሬ ነዋ። "ባበይ ተማሪ ቤት አስገባኝ" ስለው "እኔ በሮችን አጠምዳለሁ... ነገ ደግሞ ሀይላቸው ደቦ ጠርቶናል... ከዚያ በስቲያ ደግሞ የታችኛውን መሬት ጉልጓሎ እጀምረዋለሁ... እናትሽን ጠይቂያት" ይለኛል። ባልበሰለ በሕፃን ልቤ ንድድ እላለሁ... እናትሽን ጠይቂያት ለማለት ይሄ ሁሉ ምክንያት... እየተናደድኩ በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ ንዴቴ እንዳይወጣብኝ የተቋጠረ የመሰለኝ ቅንድቤን ፈካ ለማድረግ እየታገልኩ ወደ እናቴ እሄዳለሁ... "ታተይ ባበይ ተማሪ ቤት አስመዝግቢያት አለሽ" ስላት "ተምረሽ የት ልትደርሺ? ሁነኛ የቤት መዝጊያ የምታገኚው የቤቷን ስራ ጠበቅ አርገሽ ስትይዢ ነው ልጄ... እኔ እንዲህ አፈር የምበላ ሞያቢስ ለባላባቶች አቶንም ተብዬጂ...." ወደ አባቴ ታጉረጠርጣለች "ወድጄህ እያልሽ እንደአህያ ማሰሮ አዝለሽ አስሬ ወንዝ ስትመላለሺ የነበርሽ አንቺ" ይላል እንደጉራ እያረገው ትከሻውን ሰበቅ እያረገና ትከሻውን አስደግፎ በእግሮቹ መሀል ያሳለፋት በትሩን አንዴ ብቻ በደግ አርጉ መልሶ ከትከሻው እያኖራት። "ኸወንዙ ስትቦጫረቅ ላይህ? ቱ እቴ! (ወደእኔ እያየች) አያትሽ እንዴት ያለች ጠላ ጠማቂ እንደነበረች ብታይ! ለእሷ ውሃ ሳመላልስ ነውኮ እንዲህ የሚለው... ይልቁስ ውሃ ብቻ ስቀዳ በመኖሬ ነው ወጣወጤ አልጥምልሽ ብሎኝ አባትሽ ላይ የጣለኝ... (መልሳ ዓይኖቿን ወደ ባበይ አንከራታ ፈጥና እየመለሰቻቸውና በስሱ ፈገግ እያለች) ሦስት ጣሳ በቅጡ የማትጠጣ ሰውዬ ሠላሳ ጊዜ ቤታችን ስትመላለስ የኖርከው አንተ ምን እኔን ትላለህ!" ትለዋለች። አንድ ሁለት እያሉ ፍቅር በፍቅር ሁነው ይውሉና ሌቱን ሙሉ የባላገር ወሲብ ችብቻቦ ስሰማ እንቅልፍ አጥቼ አድራለሁ። የምበላው ምግብ ከጥርሴ በቀር የሚፈጨው ጨጓራ ያለኝ አይመስለኝም... ሌቱን ሁሉ አስባለሁ... በእኔ ጥያቄ እነሱ ፍቅር ይሰሩብኛል ወይ? እያልኩ ስብከነከን... ስናደድ አድራለሁ። ቆይቼ ቆይቼ ደግሞ "ባበይ የእገሌ ልጅኮ ተማሪ ቤት ገባች" ስለው። "እቺ ኤናትሽ ሌላ አልወልድም አለይ.. እነሱኮ አራት ልጆች አሏቸው... አንቺን ተማሪ ቤት ሰደን... ከማሳው ማን ማዕድ ሊያቅብለን ነው? እናትሽም ደክማለች እኳን ማሳ ልትወርድ የቤቱን እንኳን ካላንቺ በቅጡ አትከውነውም..." እናቴ ትደረባለች.." ሴትን አርባ ከሞላት ቢድሯት እሷም ትዳሯም ከንቱ ይሆናል ኸተማሪ ቤት መስደዱም እንዲሁ ነው... ሴት የቤት የቤቷን እንጂ የምን ውጭ ውጭ ማለት ነው?" ትለኛለች። ታዝዤ ከላይኛው ታችኛው ቤት ከተገሊት ቤት ብረት ምጣድ ሳመጣ ከገሌ ቤት የደቦና የጠበል ቅመሱ መልዕክት ሳደርስ በየመንገዱ ለብቻዬ እብሰለሰላለሁ... የሆነ ቀን ውሃ ልቀዳ ማሰሮዬን አዝዬ ወንዝ ደርሼ ስመለስ ደክሞኝ ከጥላው ከዛፊቷ ስር አረፍ ብል... የተረገመ ንፋስ ወረቀቷን እያንከባለለ አምጥቶ እንስራዬ ስር ለጠፋት... አንስቼ አየኋት ወርቅ እንዳገኘሁ ሁላ አገላብጬ አየኋት.. የሚያምር ጥሁፍ አለው... ምን እንደሚል ማወቅ ፈለግሁ... ስለምን ይሆን የተፃፈው? አልሁ። አፈጠጥኩ.. አፈጠጥኩ.. አፈጠጥኩ... ዋይ.... ብዬ መጮህ አማረኝ... ፊደሎቹን ምን ብዬ ልጥራቸው... እኔ ደ ነኝ... እኔ ቀ ነኝ... እያሉ ቢያወሩኝ...ጓደኞቼ ቢሆኑ.. ለእነሱ ያለኝን ፍቅር ቢያውቁ ብዬ ተመኘሁ... ለመጨረሻ ጊዜ ባለ በሌለ ሀይሌ ለማንበብ ፈለግሁ በሆነ አስማት ባነባቸው አልኩኝ... ግን አቃተኝ ከየት ይመጣል ታዲያ ፍላጎት ብቻ ነበር እንጂ... የዛን ቀን የተሰበርኩት መሰበር በዛፍ አይድረስ! አለቀስኩ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ... ለመጀመሪያ ጊዜ ባበይንና ታተይን የመጥላት ስሜት ተሰማኝ... እነሱ የኖሩበትን እውነት እንጂ እኔ የደረስኩበትን ፍላጎት ባለመረዳታቸው ጣላቶቼ መስለው ታዩኝ.. ይህም እኮ የእነሱ አለመማር ነበር ግን በቃ... ቀለቅሶዎቼ መሀል... አንድ መልከመልካም ጉብል ብቅ አለ... "እንዴ እንዴ አለሚቱ ለምን ታለቅሻለሽ?" አለኝ ከቤተስኪያን እንደመጣ የሚያሳብቅ ነጠላውን ወደላይ ወርወር እያደረገ... እንደዛ ሲለኝ ለቅሶዬ ለቅሶ ብቻ አልሆን አለ.. እግዜሩ ሲቆጣ አይነት መብረቅ ስቅታዬ የማያቋርጥ ሆነ... "በወላዲቷ... ተይ ነውር ነው" እያለ እንባዎቼን አድርቋቸው እንኳን ስቅታዬ አላባራ አለ... "እኔ አባ ካስተማሩኝ የማቃትን ቀለም አስቆጥርሻለሁ እሮብና አርብ ከዚህ ጠብቂኝ" ሲለኝ... ፈገግኩኝ... "አንቺዬ የእውነትም ከፍቶሽ ኑሯል እየሳቅሽም ስቅታው አይወጣልሽ?" ይለኛል.. እሱ አልገባውም አለመማሬ ምን አይነት አለም እንደሰራልኝ... ባገኘሁት ቁጥር የቤተስኪያኑ እጣን ከነጠላው እየቀረ ሽታው ያውደኛል። አለመማሬ እንዲህ ያስመኘኛል.. እኔም ማንበብና መፃፍ ችዬ ከቤተስኪያኑ እጣን በተጣድኩ እላለሁ... ከፆም ውሎ መቶ ቀለም ላስይዝሽ ሲለኝ ያሳዝነኝ ገባ.. የሆነኛው እሮብ ላይ ለባበይ ይዘሽ ሂጂ የተባልኩትን ማዕድ ቀለም ለሚያስይዘኝ ለየኔታ.. አሁን ሲገባኝ ለልቤታ ይዤው ሄድኩኝ.. እናቴ "ወጣወጥሽ ይጣፍጥጂ ከደህናው..." ምናምን እንደምትለኝ.. በማዕዱ ጣዕም ላማልለው ሲዳዳኝ እንደነበር ሁላ ሳስብ እስካሁን እሽኮረመማለሁ። በላይ በላዩ አጉርሼ የልቤንታ አጥግቤ ሳበቃ.. ስንለያይ ሳቅፈው ሲያቅፈኝ.. ጡቶቼ ከደረቱ ሲላተሙ ጭኖቼ ምን አድርጊ እንደሚሉኝ አይገባኝም አጉል ይቆላቸዋል... "ታተይ ማዕዱኮ ተደፋብኝ ውሻ ሲያባርረኝ..." እንባዬ መጣ እንደፈራ ሰው አለቀስኩ... "እና ነከሱሽ? ወይ ልጄን ውይ ልጄን..." ደረቷን ልትደቃ አምስት ጉዳይ ሲቀራት... "አመለጥኳቸው ስሮት ግን አገልግሎ ወድቆ ማዕዱ ተደፋ" አልኳት "ይደፋ በልተንውስ ወደአፈር አይደል የሚሄደው... ውይ ለምለምዬ ሞት ይርሳኝ እቺኮ ቀልቤን ሰርቃው... ምን ስጪኝ ነበር ያልሺኝ?" "ምጣዴ አልሰማ ብላኝ ነው ለማሰሻ የተፈጨ አጉሎ ካለሽ ብላሻለች እናቴ.." አለቻት ለምለም። ለምለም የምቀናባት ጎረቤታችን ናት እሩቅ ሂዳ ቀለም የምትማር.. ሕልሜን የምትኖር እንስት ናታ... ልሸኛት አብሪያት ሰወጣ... "ማን በልቶብሽ ነው ማዕዱን?" አለችኝ እየሳቀች "ኧረ ተደፍቶብኝ ነው!" አልኳት ደንገጥ ብዬ "ኧረ አትደንግጪ እኔኮ ለምለም ነኝ" "አል.. ደነገጥኩም ግን እንዴት እንደሱ አልሺኝ?" አልኳት "አይ ዝም ብዬ ነው ኸላስቲኩኮ ጥርግ ተደርጎ እንደተበላ የሚያሳብቅ መስመር መስመር ሳይ አልተደፋብሽ እንደሁ ብዬ ነው" አለችኝ

  • ያንቺን ልጅነት የመኖር ግዴታ የለብኝም ነበርኮ!.. ልጅነትሽን ለመኖር መውለድ አይጠበቅብሽም ነበርኮ! ፀፀትሽን ለምን በእኔ  ንስሃ ትገቢያለሽ?  አንቺ ያጣሽውን እኔ የማግኘት ግዴታ ነበረብኝ? ለምን እንደዛ እንድኖር አደረግሽኝ? አንቺ ልጅነትሽን ስትጭኚብኝ... ወላጆችሽ የሆኑብሽን እየሆንሽብኝ ነው !  እነሱን እየጠላሻቸው ለምን እነሱን መሰልሽ? ....More

  • 10 авг.1 2349

    እናቴ እና አባቴ ለመውለድ ሳይማከሩ ነው ባጋጣሚ የተወለድኩት። ነገውን አውቆ የሚኖር ሰው የለም። ነገ አጋጣሚ ነው! በቃ በአጋጣሚዎች የተገነባ ብቻ! የነገ መልኩ ግን ትናንትን ይመስላል ልበል? በአጋጣሚ "ዞር በይ ከፊቴ አንቺ መናጢ!" "እህ እማ ደሞ... አስተማሪውኮ..." "ዞር በይ ብዬሻለሁ ዛሬ... ውዳቂ! እንደእኔ የማንንም እከክ ስታራግፊ ትኖሪያታለሽ ምን ገዶች ኋላ!" "ለምንድነው ሁሌ…

  • 3 авг.2 204378

    "ልጁን ጠፍጥፌ ሆዴ ውስጥ አልከተው እኔ.. የነሳህን ፈጣሪ ሂድና ተጨቃጨቀው እኔን ተወኝ" ትለኛለች ከልላ መውለድ ያቃተኝ መስሏት... ፈጣሪ ሰጠ ፈጣሪ ነሣ... ሃሃሃሃሃሃ እያለ ሲሟዘዝ  ለሦስተኛ ጊዜ ማሰብ ቻልኩ... ይሄንን ሰው አጥብቄ ያዝኩት... እሱም አላሳፈረኝም ቶሎ ቶሎ ያገኘኝ ጀመር... ችግሩ ከእሱ እንዳይሆን ፈርቼ ነበር... አሁንም ግን ፍርሃቴ አላሳፈረኝም። አንዳንድ ጓደኞቼ እንዳሉኝ የእርግዝና ምልክት እየታየብኝ ገው... ሰውዬው ጋር ደውዬ እንዳመመኝና አብሮኝ ሐኪም ቤት ይዞኝ እንዲሄድ ጠየኩት... እንዴት እንደሚያደርገኝ ስነግረው... መኪናዋን እንዴት ነድቷት እንደሆነ አላውቅም ስልኩን ሳልዘጋው ቤት ደርሶ ክላክስ አደረገልኝ... ማርገዜን ሲያረጋግጥ ደስ አለው አሁኑኑ ከዚህ ልጣፊ ቤት ካልወጣሽ አለ... ለእናት ሌላ ቆንጆ ኮንደሚኒየም ተከራየላትና እቃዎችን አሟላላት... እኔም ምን የመሠለ ቪላ ቤት ውስጥ በስተርግዝናዬ መንጎማለል ጀመርኩ... የሆነ ቀን እናቴ ልጠይቀኝ እቤት መታ... "እማ ግን ያኔ ሰፈር ስንለቅ ጎረበረቶችሽ ምን እንዳሉ ሰማሽ?" አልኳት "ምን አሉ? ምን ሲሉ ሰማሽ?" "ሴት መውለድ ደጉ... ያወቀችበት እንዲህ እናቷን ከቆርቆሮ ታወጣለች የኔዋ እዚህ ዲዛይን ፋሽን እያለች መርፌ ስትጠቀጥቅ ትውላለች... እያሉ ሲቀኑብኝ ነበር" አልኳት "ሰው አግኝተው ቀኑብሽ? ቱ! እቴ... የተማረውን አግኝተሽ እንጂ ተምረሽ መሠለሽ..." ከመማር ጋር ያላት ፍቅር እንዴት ነው ጎበዝ... ተምሬም ይሁን ሳልማር ሀብት ካገኘሁ ምን ትፈልጋለች? አሁን አሁን እናቴ እያበሳጨችኝ ነው አጉል ካልተማሩ ብሎ ፍልስፍና ምን ሰባተኛ ሰማይ ልትወጣበት ነው? ሆ እንዲሁ ከእናቴ ጋር እየተነታረኩ ዘጠኝ ወሬን ፉት አድርጌ ሀብት ንብረቴን ወለድኩ... የደግነቱ ጥግ ቁጭ አባቱን የሚመስል ከነቃጭሉ ዱብ አደረኩ። ልጁን ያየ ጊዜ ተንሰፍስፎ ሊሞት... ጉድ እኮ ነው ሰው በአራት ሰራተኛ ይታረሳል? አራስነቴ ለዘላለም በሆነ ብዬ ተመኘሁ... እነሱ አልበቃ ብለውት "ሌላ ሰራተኛ እንጨምር እንዴ?" ይለኛል.. ይታያችሁ ከዚህ መቅበጥና መንበላጠጥ ብኋላ የእናቴን ህይወት መድገም የሚባል ነገር ሲታሰብ... ልጃችን ሦስት አመት ሲሞላው... ነገሮች ቀስ በቀስ መቀየር ጀመሩ... በጊዜ ጊደት ልጄን በመንገዴ የማሳደግ መብቴን ተነጠኩ... በእራሱ ማህፀን የወለደው እስኪመስል ድረስ.. ልጄን አትቆጪው ይላል... ብቻውን የወለደው ይመስል... ቢቀብጥስ እኔ አባቱ እያለሁለት ምን ቤት ነሽ ይለኛል... ጭራሽ ይባስ ብሎ... "ልጄን ይህንን አረክ ያንን አድርግ እያልሽ የምትከታተይው ስራ ፈት ስለሆንሽ ነዋ?" ብሎ አንድ የቀረችውን ሰራተኛ አባረራትና የቤቱ ስራ እኔ ላይ ወደቀ... አልከፋኝም የተሻለ ኑሮ እየኖርኩ ነዋ እናቴም እየኖረች ነዋ... የቀፋችው ቀን.. ያልተሻለችው ኑሮ የምትመጣበት ቀን ደረሰች... ቁርስ እየበላን... ደግሞኮ እየነገርኩት ነው ነጭ ልብስ ነው እያየህ ብላ ብዬውነበር... ሲዝረከረክ በእጁ የያዘው ጉርሻ ልብሱ ላይ ወደቀ.. ተናደድኩ እንዴት አድርጌ እንደማጥበው እኔ ነኝ የማውቀው... "ቅያሬ እንኳን የለህም ምን ሸሚዝ ለብሰህ ልትሄድ ነው?" ብዬ ሪሞቱን ቀምቼ ቴሌቪዥኑን አጠፋሁበት... ልጄ! አዎ የገዛ ልጄ ምናገባሽ ብሎ በጥፊ መታኝ... ይሄ ሁሉ ያባቱ ስራ ነው... ደንግጬ ወደ አባቱ አፈጠጥኩ.. "ምን ታይኛለሽ እውነቱን እኮ ነው እኔ አባቱ አዲስ ሸሚዝ እገዛለታለሁ.." አይለኝም... ትዳር መስርቼ ልጅ ወልጄ ለ26 አመት የኖርኩባት ዓለም ለሁለተኛ ጊዜ እንግዳዋ እንደሆንኩ ተሰማኝ.. በአሁኑ ግን መንቃት አይደለም ይልቁኑ ማንቀላፋትን መረጥኩ። ቁጭ ብዬ አሰብኩ... ቀድሞ ነገር ብር እንጂ ልጁን ፈልጌ አልወለድኩትም... እንደ እናት አይደለም እንደ ሰራተኛ እንኳን ሳያከብሩኝ የሚበሉትን ሳበስል... የሚለብሱትን ሳጥብ... መኖሪያቸውን ሳፀዳ.. እንዴ?!.. እንዴ?!.. ለአራተኛ ጊዜ አሰብኩ.. የእናቴን ኑሮ እየኖርኩ ነው! እናቴ እና አባቴ ለመውለድ ሳይማከሩ ነው ባጋጣሚ የተወለድኩት... ነገውን አውቆ የሚኖር ሰው የለም። ነገ አጋጣሚ ነው! በቃ በአጋጣሚዎች የተገነባ ብቻ! የነገ መልኩ ግን ትናንትን ይመስላል ልበል?... ትናቴን የሚመስል ነገ ላይ ደረስኩ እኮ! የእናቴ ፍልስፍና አሸነፈኝ.. ባለመማር ውስጥ አለመኖር ብቻ ነው ያለው.. ባለመማር ውስጥ የተሻለ ሕይወት ሳይሆን የተሻሀ አለመኖር ነው ያለው...  ስለዚህ ለምን እኖራለሁ? ከዚህ በላይ ላወራችሁ አልችልም ምክንያቱም አንገቴ ላይ ገመድ አጥልቄ የረገጥኩትን ወንበር ለቅቄ በመንጠልጠል ላይ ነኝ.... ✍ሌዊ @lewi_derest

  • 3 авг.2 012176

    እናቴ እና አባቴ ለመውለድ ሳይማከሩ ነው ባጋጣሚ የተወለድኩት። ነገውን አውቆ የሚኖር ሰው የለም። ነገ አጋጣሚ ነው! በቃ በአጋጣሚዎች የተገነባ ብቻ! የነገ መልኩ ግን ትናንትን ይመስላል ልበል? በአጋጣሚ "ዞር በይ ከፊቴ አንቺ መናጢ!" "እህ እማ ደሞ... አስተማሪውኮ..." "ዞር በይ ብዬሻለሁ ዛሬ... ውዳቂ! እንደእኔ የማንንም እከክ ስታራግፊ ትኖሪያታለሽ ምን ገዶች ኋላ!" "ለምንድነው ሁሌ እንደዚህ የምትናገሪኝ? እህ... ይከፋኛልኮ! እኔ ውለዱኝ ብያችኋለሁ እንዴ እንደዚህ የምታሰቃዬኝ!" "እኛስ ተወለጂ ብለንሻል? ክፉ ቀን ላይ ጥሎኝ ባጋጣሚ ተረገዝሽ እንጂ..." አን..ድ በሉልኝ! በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ስቅስቅ ብዬ ያለቀስኩበት ቀን ይሄ ቀን ነው። ከትምህር ቤት የውጤት ካርድ ከእናቴ ጋር ተቀብለን ስንመጣ ሰባተኛ ክፍልን ለሦስተኛ ጊዜ መውደቄን ስታውቅ ነበር እንደዚህ የተናገረችኝ። እሺ ቆይ እኔ ምን ላድርግላቸው?... ስድስተኛ ክፍል እያለሁ አልፍ አልፎ የምሰማት x ሰባተኛ ክፍል ከመግባቴ በአስተማሪ አስጠመደችኝ... ይሄው እየተከታተለ እኔ ያለሁበት ክፍል ስም ጠሪ እየሆነ ያስወድቀኛል። ኬሚስትሪ ገብታ በስሱ ነካክታት ስትወጣ ፊዚክስ ይገባል... ምኑንም ሳልጨብጠው x,x,x እንዳለ ይወጣል ከዛ ማትስ ከመግባቱ በቅጡ እንኳን ሰላም ሳይለን... "2x +...."ምናምን ብሎ ይጀምረኛል ሆ...እኔ የx ነገር ግራ ግብት ብሎኝ ስተክዝ ስተክዝ... አስተማሪው "የxን ዋጋ ፈልጋችሁ ኑ.. የቤት ስራ ነው.. ደግሞ አምስት ማርክ አለው" ይላል አምስት ጣቱን እያሳየ... ወይ ጉድ x የቤት ስራም ትሆናለች? እሺ አሁን ምን ብዬ ነው የምፈልጋት? እቃ እያጠብኩ? ቤት እያፀዳሁ? ለነገሩ ምን አለፋኝ እማዬ ከእኛ አልፎ የሰው ቤት ውስጥ እራሱ ትሰራ የለ.. ከምፈልግ xን የት እንዳየቻት እጠይቃታለሁ...  ወይ ደግሞ እነ አብርሽ ቤት ለቡና ስለምትሄድ.. አብርሽ የክፍላችን ሰቃይ ተማሪ ነው... እሱ xን የት እንደሚፈልጋት እይልኝ እላታለሁ... ብዬ እንዳልኩት ስጠይቃት... "የምን x አመጣሽብኝ ደግሞ?" ትለኛለች "አስተማሪው ነዋ የxን ዋጋ ፈልጋችሁ ኑ.. የቤት ስራ ነች አምስት ማርክ አላት ብሎን" የኔ ምስኪን እናት "እኔ አላቅልሽም ብቻ ቅድም በእቃ ማስቀመጫው ስር የሆነ ነገር ሲወድቅ ሰምቼ ነበር እሱ ከሆነ ሂጂ እስኪ እይው..." ስትለኝ እኔ የእናንተ ሞኝ ሂጄ መፈለግ... ምን አገኘሁ? ጣራና ግድግዳዋን በቆርቆሮ ካዘመመች ቤታችን የተነቀለ ሚስማር... እሱን ይዤ መሄድ... ደግሞኮ በኩራት ደስ ብሎኝ... ገና ከመግባቱ "ቲቸርዬ xን እኮ ፈልጌ አገኘኋት" አልኩት... "ሌሎቻችሁስ ሰራችሁ?" ብሎ ጠየቀ የእኔን እንዳልሰማ ሁሉ.. ሲመስለኝ ግን ለካ ጎበዝ ተማሪ መስዬው ነው። አንድ ሁለት ተማሪዎችን ጠየቀ... የማይገባኝን መደመርና መቀነስ... የሌሉ ቁጥሮችን ከየት እንዳመጧቸው አላውቅም መደርደር ጀመሩ... አስተማሪው ልክ አይደላችሁም ሲላቸው ደስ አለኝ... እነዚህ ሞኝ ናቸው እንዴ የቤት ስራ ነው ብሏቸው እዚህ በቁጥር ይፈልጋሉ እንዴ? ነበር ያልኩት ጉዴን አላወኩ። "አንቺ ነበርሽ መልሱን አግኝቼዋለሁ ያልሺኝ?" አለኝ ተስገብግቤ አዎ አልኩት... "እሺ የx ዋጋ ምንድነው ተነሺና አሳይን" ብሎ ቾክ የያዘ እጁን ዘረጋልኝ... ቾኩን ለምን እንደሰጠን እኔም ለምን እንደተቀበልኩት አላቅም ብቻ በክፍሉ ውስጥ ሞቅ ያለ ጭብጨባ ሲጨበጨብልኝ እያሰብኩ ደስ ብሎኝ ጥርስ በጥርስ ሁኜ በእጄ እያፍተለተልኩ ጨብጬ የያዝኩትን ሚስማር ወደላይ ከፍ አድርጌ... "ይሄው ቲቸርዬ xን ስፈልግ ያገኘሁት መልስ" አልኩኝ ሞቅ ያለ የተማሪዎች ሳቅ ሞቅ ካለ ጥፊ ጋር... ሠማይ ከምድሩ ተደበላለቀብኝ... እኔኮ ልቀልድበት አልነበረም... አስተማሪው ግን "እንኳን አንቺን ስንት ጎረምሳ አስተምረናል... እንደቀለድሽብኝ በዕድሜሽ እቀልድብሻለሁ!" አለኝ ኧረ እኔኮ... ብል የሚሰማኝ ጠፋ... እንደዱርዬ ታየሁ... ተቆጠርኩ... ስመ ዱርዬ በሴት ሲሆን ይብሳል... ሱሪ እንኳን በቅጡ አርጌ የማላቅ ሴትዮ መንደር ለመንደር ከሚያጨሱት እኩል ተሰደብኩ....መምህሩም በዛች አለማወቄ ቂም ይዞ ለሦስተኛ ጊዜ ስም ጠሪዬ ሁኖ ጣለኝ.. እንዳለው በእድሜዬ ቀለደብኝ... እናቴ በአጋጣሚ ነው የወለድኩሽ ማለቷ ግን ውስጥ ውስጡን በላኝ... ያ ደነዝ ጭንቅላቴ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓይኖቼ የዕንባ ፀበል ተጠምቆ ማሰብ ጀመረ... ትምህር እንደዛ እንዳልነበር ገባኝ.. እራሴን ሳስበው ሌላ ዓለም ውስጥ ነበርኩ እንዴ? እላለሁ.. እንዴት በዛ ልክ የማላገናዝብ ደደብ ሆንኩ እላለሁ... እናቴስ እሺ ከነጭራሹኑ አልተማረችም እኔ ግን... ያስለቀሰኝ በአጋጣሚ መወለዴን ማወቅ አልነበረም... 17 አመት ሙሉ የኖርኩባት ዓለም ላይ እንደ ጨቅላ ሕፃን አሁንም እንግዳ መሆኔ ሲገባኝ እንጂ... እናቴ መከራ እንኳን የታየኝ አሁን ነው... ይሄ ለእኔ ከባድ ነገር ነው... አሁን ምን አይነት ስሜት እንደሚሰማኝ ታቃላችሁ? አለ አይደል የሆነ በጣም የሚያስፈራ ህልም እያያችሁ ደንግጣችሁ ስትነቁ የሚሰማችሁ... እንደሱ አይነት ስሜት ይሰማኛል... አላውቅም ብቻ እንደዚሁ እንዳለሁ ትልቅ ሁኜ የተወለድኩ... ድንገት ነገሮች ባንዴ የተገለጡልኝ መስሎ ነው የሚሰማኝ... ለእናቴ የተቀየረ ነገር የለም... እንደድሮው ታመናጭቀኛለች... "እናቴ ትምህርት ለእኔ አልተፈቀደም ስራ ልጀምር እያሰብኩ ነው" አልኳት... ይሄኮ ማሰብ ስጀምር ያሰብኩት የመጀመሪያ ሀሳቤ ነበር! እሷ ግን... "ወፍ እንደዘራው እህል ካለጊዜሽ ተወልደሽ የእኔን ሕይወት ያመሳቀልሽው አይበቃም? የእናትሽን ኑሮ መኖር ነው የምትፈልጊው?" ትለኛለች። የእናቴ ኑሮ ምን አይነት ነው? ለመታዘብ እሞክራለሁ... ከእማውራነት ጎድላ የአባውራውን ቤት የምታፀዳ ልብስ የምታጥብ ምስኪን የቀን ሰራተኛ ናት... አእናስ! ቦለኬት መሸከም ወይም ጉድጓድ መቆፈር ብቻ ነው እንድ ታዲያ የቀን ሰራተኛነት... የእናቴን ህይወት መድገም አስፈራኝ... በድንገት ሀብታም የምሆንበትን ነገር ፈለኩ... በቃ እናቴን ከዚህ ሕይወቷ ጎትቼ የማወጣበት አንድ የማርያም መንገድ ማግኘት ተመኘሁ... እንደወንዱ ጥሬ ግሬ እንዳልል አልሆንሽ አለኝ.. በሴት አቅም ልሰራ የምችለው የእናቴን መሰል ስራ ነው... አልተማርኩማ! ከመማር አይቆጠርም መቼስ... ማሰብ ከጀመርኩ ሁለተኛ ሀሳቤን አሰብኩ.. ለእናቴ ግን አልነገርኳትም... እሷ ስላልተማረች ሸው ሁሉ የበለጣት ሰለተማሩ ይመስላታል.. እኔም እንድማር ብቻ ነው የምትፈልገው.... በሁለተኛው ሀሳቤ መሠረት.. ሀብታም ወንዶችን መፈለግና ማጥመድ ከዛ አንዱን አግብቼ እናቴን ማሳረፍ... ያለመማር ፍልስፍናዋን ማረምና ባለመማር ውስጥም የተሻለ ኑሮ እንዳለ ማሳየት... ትግሌ ከኑሮ ጋር ብቻ ሳይሆን ከእናቴ አስተሳሰብ ጋርም ጭምር ነዋ። አንዱ ይመጣል ይሄዳል.. ደግሞ ሌላኛው.. በቃ ባለሀብቱ ሁሉ አግብቶኝ ሕይወቴን የሚቀይር ሳይሆን ለቀን ደስታው ብቻ የምገኝለት ሴት እንድሆንለት ይፈልጋል። ለጊዜው ሕይወት ባይቀይርም ግን የተሻለ ብር ስለሚሰጡኝ ከቀን ደስታቸው አላጎድላቸውም ነበር... የሆነ ቀን አንዱ ባለሀብት ጥብዝ ብሎ ሰክሮ... "ለምን ሚስቴ ላይ እንደምማግጥባት ልንገርሽ አይደለም... ልጅ ስላልወለደችልኝ ነው... ፈጣሪ የረገማት ሴት...ስለሆነች ነው.. እኔ በልጅ ናፍቆት ተቃጠልኩኩ እሷ ግን...

  • 2 авг.1 56811

    እናት እና አባት ለመውለድ ሳይማከሩ ነው ባጋጣሚ የተወለድኩት። ነገውን አውቆ የሚኖር ሰው የለም። ነገ አጋጣሚ ነው! በቃ በአጋጣሚዎች የተገነባ ብቻ! የነገ መልኩ ግን ትናንትን ይመስላል ልበል? ....loading

  • 27 июл.2 43341

    ጋሽ ስብሀትን የምወዳቸው በአንድ ነገር ብቻ ነው.. ከእራሳቸው የሚደብቁት ቃል የላቸውም.. ሁሉንም ቃል ለስነ-ፅሁፋቸው ይጠቀሙበታል! ማስረጃ ከፈለጋችሁ፦ ትኩሳት ገፅ 153 @lewi_derest

  • 26 июл.2 807102

    ፖድካስቶች ላይ "Egoን ስለ መግደል" እንደትክክል ነገር በኩራት ይሰብኩታል። Ego! መዳን ነው ያለበት እንጂ መሞት የለበትም! ትክክለኛው ሳይኮሎጂ የሚያስተምረው ይሄንን ነው! ምክንያቱም የትኛዋም "እኔ" የምንላት ጥቃቅን ነገር ሳትቀር Ego ናት... Ego ማለትኮ እኔ ማለት ነው.. የቃሉም ትርጉም እኔ ማለት ነው! Egoን የመግደል ሂደት በራሱ የunconscious መጋዘናችሁን በshadow ማጨቅ ነው የባሰ የስነ-ልቦና ቀውስ ውስጥ ይገታል! Ego ይታመማል የታመመን Ego ማከምና ማዳን ነው እንጂ Egoን መግደል የሚል ሀሳብ በጣም የተሳሳተ ሀሳብ ነው! Egoን መግደል እኮ ማንነትን (እኔነትን!) መግደል ማለት ነው! ይሄ ደግም ማንነት የለሽ! ሰዋዊነታችንን ትርጉም የሚያሳጣና የትርጉም ቀውስ ውስጥ የሚከተን ነው ! እና እባካችሁ ኢጎን መግደል በሚል ሀሳብ እንዳትያዙ! @lewi_derest

  • 25 июл.2 7133

    ፖድካስቶችን የማየት ልማድ አለኝና ምን ታዘብኩ መሰላችሁ... ብዙ ፖድካስቶች ላይ Egoን ስለመግደል በስሱም በጨረፍታም ይነካኩታል... እናንተ ምን ታስባላችሁ? ኢጎአችንን መግደል አለብን በሚለው ትስማማላችሁ? ለምን? @lewi_derest

  • 17 июл.3 844306

    "ማሂን የደፈራት ማን ማን ነው? የነገረኝ ሰው ቢያንስ ቅጣት ይቀየርለታል የሰረቀበት ጣቱን ብቻ ነው የምቆርጥለት... መቼስ ከመሞት ይሻላል አይደል?" አልኩኝና መናገር የሚፈልግ ካለ ተመለከትኳቸው... ከሦስቱ በስተቀር ሌሎቹ ሁሉም መናገር ፈልገው ነበር.. ገባኝ "አንተ... አንተና አንተ ናቸውሁ አይደል የደፈራችኋት? ተሳሳትኩ እንዴ?" ብዬ የቀሩትን አራቱን ተመለከትኳቸው... አራቱም እነሱ እንደሆነ በጭንቅላታቸው ንቅናቄ ገለፁልኝ... "ይቅርታ አድርጉልኝ የሚቀየረው ቅጣቱ ሳይሆን ኤሌክትሪኩን የማስርባችሁ ቦታ ነው... ከዛ በተረፈ ማናችሁም በሕይወት አትተርፉም..." ብዬ በቀሌን ጀመርኩ... የሁሉንም ሱሪ እንዲያወልቁልኝ ለሰዎቼ ነገርኳቸው... ማሂን የደፈሯትን ሦስቱን ሰዎች ቀጥታ ኤሌክትሪኩን ቆለጣቸው ላይ ቋጠርኩት... የተቀሩት ላይ ደግሞ እግራቸው ላይ... ከዛ መቆጣጠሪያውን አበራሁት... እንደዛ ቀን ደስታዬ እረ....ጅም ሁኖ አያውቅም በዛ ከተባለ አምስት ደቂቃ ነበር አሁን ግን ያለማቋረጥ ከአንድ ስአት በላይ ደስተኛ ሁኜ ነበር ምክንያቱም እንደዛ አጥንቴ ድረስ የተሰማኝ ሀዘኔታ ለረጅም ደቂቃዎች ሲካስ ነበር... ፊታቸው በላብ ተጠምቆ... ደም ስራቸው ተገታትሮ ሲታገሉ ከማየት በላይ ምን ቀረኝ... ኧረ ደግሞ የገረመኝንና በጣም ያሳቀኝን ልንገራችሁማ ሰው ሲናደድ.. ሲደነግጥ.. ሲያለቅስ ምናምን ፊቱ ቀይ ይሆናል...ከመካከላቸው ሁለቱ ጥቁር ናቸው.. የእነሱ ፉት ሳይቀር ከመሰቃየታቸው የተነሳ የቀላው.." ታሳሪው ሁላ በዚህች ንግግሬ አሽካካ.. እኔም አብሪያቸው እስቃለሁ... በቃ እስር ቤት ለእኔ ገነቴ ነው.. ማሂ ሁሌም እየመጣች ትጠይቀኛለች... በመጣች ቁጥር በኩራት የምታወራልኝ... "ያኔ በቴሌቪዥን እነዛ ውሾች እንደቋንጣ አንጠልጥለሀቸው ሲታዩ የተሰማኝ ደስታ...." ትላለች... "ምን ስትል ኤሌክትሪኩን አሰብከው ግን አንተን ይንሳኝ ማርዬ ጭንቅላት አለህ..." ትለኛለች... ትስቃለች ትጫወታለች.. ግን ሳቅና ጨዋታዋ ውስጥ ትልቅ የጎዳት ሀዘን እንዳለ ያስታውቅባታል። አንድ ቀን ተፈትቼ አብረን እንኖር ይሆናል.. ማን ያውቃል ማርገዝ የምትችልበት እድሜዋ ላይም ሊሆን ይችላል የምፈታው! ✍ሌዊ https://t.me/lewi_derest

  • 17 июл.2 745266

    አሳዘነችኝ ማዘኔ አጥንቴ ድረስ ዘለቀ... ስላፈቀርኳት አይደለም... ግን ይሄ አሁን እሷ ላይ ያየሁት መልክ የእኔም የሆነኛው ሕይወቴ ውስጥ የነበረ መልክ ነው! በቀል..! ሁሉም ሰው "እንዴት ለሴት ብሎ እንዲህ ያደርጋል!" ይሉኛል... እነሱ የማይገባቸው ነገር ግን አለ!... ሴት ብዬ ወይም ለእሷ ብዬ አልነበረም ያደረኩት። አልክድም ማሂን አፈቅራታለሁ.. አውቃለሁ ወደድኩህ ወደድኩሽ ተባብለን አብረን ከሆንን... ከንፈሮቻችን መቃመስ ከጀመሩ ገና ሳምንታችን ነው! ግን እነሱ እንደሚሉት ትኩስ ፍቅር አውሮኝ አልነበረም... ማሂ አቤል የሚባል የአስራ አንድ አመት ወንድም አላት... ቤተሰቦቿን ስራዬ ብላ ቤቷ ወስዳ ነው ያስተዋወቀችኝ። ቤተሰቦቿ ሀብታም ቢሆኑም ግን ሰዋዊነታቸው አልተፋቀም... ማነህ? ምንድነህ? አላሉኝም ነበር.. ልጃችን ወዳሀለች ውደዳት ብቻ ነበር ያሉኝ... ከአቤልም ጋር በጣም ተግባብተን ነበር...  እሱም እንደእኩያው እኔም እንደእኩያዬ እስከመተያየት ነበር ቅርርባችን። ይቅርታ ቆይ አንዴ ማሂ ደወለች ላውራትና ታሪኩን እቀጥልላችኋለሁ... "ሄሎ ማሂ..." "ማ.. ማርቆስ..." እያለቀሰ ነበር "አቤልዬ ምን ሆንክ? ማሂ ምን ሁና ነው?" "ቶሎ.. ቶሎ እቤት ና" በቃ እሄን ብቻ ነበር የተናገረው ስልኩ ተዘጋ... ወደቤት ሄድኩኝ... ቤታቸውን ሰው አጥለቅልቆት ነበር... ተደናገጥኩ.. ሰዎቹን ሁሉ ገፈታትሬ ወደሳሎን ስገባ ሦስት እሬሳዎች... ተጠቅልለው ተደርድረዋል... ማሂን ነርሶቹ ወደ አንቦላንሱ እንድትገባ ይለምኗታል... "ለምን እታከማለሁ? ለምን? ለመዳን? ቤተሴቤ ሙቶ ለምን እድናለሁ? አልሄድም!" ትጮሀለች... ደርቄ ቀረሁ.. ፖሊሱ ፖሊስነቱ ትዝ ሳይለኝ ገፍትሬው እሬሳዎቹን ከተጠቀለሉበት ጥቁር ነገር ዚፑን ከፍቼ አየኋቸው... የኔ ትንሽ አቤልዬም ዓይኖቹን ጨፍኗል... አለቀስኩ... የሚወዱትን ሰው ሲያጡ ማንኛውም ሰው እንደሚያለቅሰው እየጮኹክ አለቀስኩ... ወደማሂ ስመለከትና ማሂም በለቅሶዬ ጩኸት ወደእኔ ስታይ ተገጣጠምን.. ፊቷ ላይ አለመቻል አየሁ... ብችል ኑሮ! የሚል ቁጭት... ተንደፋድፋ መታ አቀፈችኝ... "ገደሉብኝኮ! ማርዬ ቤተሶቼን ገደሉብኝ!" ድምጿ ኡፍፍፍ አልገባችሁም አጥንቶቼን ሳይቀር ሰነጣጠቃቸው... አሳዘነችኝ ማዘኔ አጥንቴ ድረስ ዘለቀ... ስላፈቀርኳት አይደለም... ግን ይሄ አሁን እሷ ላይ ያየሁት መልክ የእኔም የሆነኛው ሕይወቴ ውስጥ የነበረ መልክ ነው! የትኛው ሕይወትህ ላይ ብትሉኝ አላውቅም ግን ይሄንን መልክ የሆንኩት ያክል ተሰምቶኛል.. የሆነ ጊዜዬ ላይ እንዲህ የነበርኩ ያክል ነው ውስጤ የራደብኝ... "እነማን ናቸው?" አልኳት ያ ያለቅስ የነበረው እኔ ጠፋ ዕንባዬ ከዓይኖቼ አይደለም ከጉንጮቼ እራሱ የደረቁበት ፍጥነት ለእኔም አልገባኝም... እረጋ ብዬ ፖሊሱን ስለሁኔታው ጠየኩት... ቅድም እንደዛ በለቅሶ ሳብድ ያየኝ አልመስልህ አለው! "በቅድሚያ ግን ማህሌት ወደሆስፒታል እንድትሄድ አግባባት" "ማሂ ምን ሁናለች?" "ደፍረዋታል ተገቢውን ሕክምና ማግኘት አለባት...." አላልኳችሁም ባሂን ስለማፈቅራት አልነበረም ለበቀል የተነሳሁት.... ይታያችሁ የማፈቅራትን ሴት እንደደፈሩብኝ ስሰማ ውስጤ የጨመረም የቀነሰም ነገር አልነበረም... እንደዛ የበቀል እሳት ውስጤ የነደደው ማሂ ውስጥ ያየሁት የሆነኛው መልኬን ስለነበር ነው! ማሂ እንድትታከም አሳምኛት ወደአንቦላንሱ ገባች... ፖሊሱ ስለተፈጠረው ነገር ሲነግረኝ.. ሰፈራቸው ማሂን ወደድኩሽ እያለ የሚያስቸግራት ልጅ ነበር.. በርግጥ ለእኔም ነግሳኛለች ግን ፍቅረኛ እንደያዘች ሲያውቅና ሰፈር ውስጥም በተደጋጋሚ ከእኔ ጋር ስለሚያያት... ማስቸገሩን ትቶ ነበር.. ለካ እሱ እየተዘጋጀ ነበር... የሰፈር ጓደኞቹን ሰብስቦ... በነሱ ቤት አልታወቁም ጭንብል አድርገው የነማሂ ቤት በማታ ይገባሉ... ከዛ እናትና አባቷን ብርና ጌጣጌጥ እንዲሰጧቸው ካደረጉ ብኋላ ያ ወደድኩሽ ምናምን የሚለው ልጅ ማሂን ሊደፍራት ሲል.. እናትና አባቷ ከተንበረከኩበት ተነስተው ከሌቦቹ ጋር ግብግብ ሲጀምሩ በጩቤ ደጋግመው የወጓቸው... አቤልዬም የኔ ትንሽ ተደብቆ ለእኔ ደውሎ ሲያወራኝ አይቶት አንዱ ደንግጦ እንዳመጣለት አንገቱን ይወጋዋል... ማሂንም ደፍረው የያዙትን ይዘው ይወጣሉ... ደደብ ደደብ ናቸው! ጭንብል ያደረጉት ለጌጥ ነው እንዴ? እንዴት ዛቻቸውን አያስተካክሉም! "በሰፈራችን ሌላ መቶ ሲበላሽ እያየንማ ዝም አንልም!" ቀሽሞች ፖሊሱን ትቼው ወጣሁ... በዚህ ልክ ደደብ ከሆኑ ቢያንስ አንዲቸው ሰፈር ውስጥ ይኖራሉ ብዬ መፈለግ ስጀምር... ሁለቱ የሆነን ሰው በችኮላ አዋርተውት.. ክንብንባቸውን አስሬዬ እያስተካከሉ ወደሚቅሙበት ቤት ገቡ... ያዋሩትን ሰው ተከትዬ ሄጄ አወራሁት... "ሰላም የቅድሞቹን ልጆች የት ነው የምታውቃቸው?" አልኩት "እነቾቤ የሰፈር ልጆች እኮ ናቸው!" "አንተም የእነሱ ጀማ ነሀ?" አጠያየቄ አስደነገጠው ፋወለኛ እንደሆኑ ያውቃል እኔም ተጠያቂ መሆን እንደማይፈልግ ስለማውቅ ነው አውቄ ከእነሱ አንዱ እንደሆነ እንዳሰብኩ ያስመሠልኩት "ኧረ አይደለሁም! እኔ ደላላ ነኝ ዛሬ እስከማታ ከሰፈር ወጣ ያለና ሰው የማይበዛበት አከባቢ ቤት እንድፈልግላቸው እየነገሩኝ ነበር እዚሁ ሰፈር ስለማያቸው እንጂ ሌላ ጉዳይ የለንም" አለኝ... "እኔ እንደዛ አይነት ቤት አውቃለሁ.." ብዬው ወደቤቱ ይዤው ሄድኩኝ.. እኔ የምኖርበት አከባቢ ሰው የማይኖርበት አንድ ባዶ ግቢ ነበር... ለምን እንደሆነ እኔጃ ሰው ከገባባት እረጅም ጊዜ የሆነው ግቢ ነው... "እንደነገሩኝ ከሆነ የሚሆናቸው ይመስለኛል"አለኝና ፎቶ አንስቶ ላከላቸው... ተስገብግበው ብር ላኩለት.. ሰደላላው ለእኔ የቤቱን ኪራይ ላከልኝና እንደሚያመጣቸው ነግሮኝ ሄደ... እስኪመጡ ተደብቄ ጠበኳቸው... ጫታቸውንና ውሃ ተሸክመው መጡ... እኔም የተወሰኑ ሰዎችን አዘጋጅቼ ሌሊት ላይ ገባንና ሁሉንም አሰርናቸው... ከዚህኛው ጥግ እስከዛኛው ጥግ ሁለቱ ግድግዳዎች ላይ ተጠንካራ ብረት አሰርንና ሁሉንም አንጠለጠልናቸው ልክ እንደቋንጣ... አሁን በቀል ተጀመረ.. "እናንተ ጉልበተኞች ናችሁ አይደል በቃ ከእናንተ በላይ ማንም የለም? የሰውን ነፍስ በከንቱ የምታደክሙት ይሄንን የዱርዬ ደደብ ጭንቅላታችሁን ተማምናችሁ ነው አይደል?" ደካማ የሆነ የኤሌክትሪክ ፍሰት ያለውን ገመድ ቀድሜ አዘጋጅቼ ነበር... "እኔ ስለኤሌክትሪክ ብዙም እውቀት የለኝም ግን እነዚህ ገመዶች ከ5 እስከ 10 አፔር የሚደርሱ የኤሌክትሪክ ፍሰት አላቸው ይህ ማለት ሰውነታችሁ ላይ ተጣብቀው ከአንድ እስከ ሁለት ስአት ቢቆዩ ምን የሚፈጠር ይመስላችል?" ተራ በተራ አየኋቸው... "መጀመሪያ ንዝረቱ በማሽን ማሳጅ እየተደረጋችሁ ያክል ለስለስ ያለ ነው... እየቆየ ሲሄድ ግን ደማችሁን እየመጠጠው መላ ሰውነታችሁ እየተቃጠለ... ንዝረቲ ጭንቅላታችሁን ሰላም የሚነሳ.... መላ ሰውነታችሁ በዚህ ንዝረት ሲኦል ይገባል... ደግሞ ደስ የሚለው በአንዴ አይገድላችሁም..... ቢያን ከአንድ ስአት በላይ ያሰቃያችኋል... በተለይ ጭንቅላት መረበሹ እንዴት ደስ ይላል መሠላችሁ... ሃሃሃሃሃሃ" ሁሉም በፍርሃት ከተንጠለጠሉበት ተወራጩ... በከንቱ ይደክማሉ ቢወርዱምኮ መልሼ እሰቅላቸዋለሁ ይሄንን እንዴት አያስቡም? ለነገሩ...

  • 17 июл.2 1022

    አሳዘነችኝ ማዘኔ አጥንቴ ድረስ ዘለቀ... ስላፈቀርኳት አይደለም... ግን ይሄ አሁን እሷ ላይ ያየሁት መልክ የእኔም የሆነኛው ሕይወቴ ውስጥ የነበረ መልክ ነው!....Loading

  • 15 июл.2 75643

    ወረቀቱ ከኔ ፃፊው ሳይቸግረኝ.. ነገር ወዲያ ወዲህ ሆነና ቸገረኝ! ምን ያደርጋል ፖስታ ነጋዴ ቢያመጣው.. መገናኘት ነበር ናፍቆት የሚያወጣው! 🔥 @lewi_derest

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

  • видео или голосовое, без подписи

✍ ልብ ወለድ በፅዮን ✍ fiction ❤️😘 — tgindex