Wolkite University Law Students Association
Статистикаይህ የወልቂጤ ዩንቨርስቲ የህግ ተማሪዎች ማህበር ቻናል ነው ስለ ማህበሩ አጠቃላይ ሁኔታ እንዲሁም ስለተለያዩ የህግ ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ከታች👇 ባለው መስፈንጠሪያ ተቀላቀሉ
- Последний пост
- 4 авг.
- Последнее чтение
- 13 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 29
- Тип
- открытый
- Язык
- am
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 580
- 1/48двое суток
- 664
- 1/72трое суток
- 716
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የክፍት ሥራ ቦታ ማስታወቂያ ማስተካከያ የፍትህ ሚኒስቴር በሀምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው ክፍት የሥራ ማስታወቂያ ላይ የተቀመጠው አጠቃላይ የትምህርት ውጤት (CGPA) መስፈርት ማስተካከያ ተደርጎበታል። በዚሁ መሠረት የሚፈለገው ውጤት፦ * ለወንድ አመልካቾች: 3.6 እና ከዚያ በላይ * ለሴት አመልካቾች: 3.25 እና ከዚያ በላይ ተደርጎ የተሻሻለ መሆኑን እየገለጽን፤ ተወዳዳሪዎች ይህንኑ አውቃችሁ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ የኢፌዲሪ የፍትሕ ሚኒስቴር በሕግ የተጣለበትን ኃላፊነት በላቀ ለመወጣት ይችል ዘንድ የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በማውጣት የአሰራር እና የአደረጃጀት ማሻሻያዎችን አድርጓል። በአዲሱ አደረጃጀት መሠረት ባሉ የተለያዩ ማስተባበሪያዎች፣ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች፣ ዳይሬክቶሬቶች ተመድበው ለመስራት ፍላጎቱ እና ተነሳሽነቱ ያላቸው እና ከዚህ በታች የተመላከቱ መስፈርቶችን የሚያሟሉ የሕግ ባለሙያዎችን በዐቃቤ ሕግነት ለመቅጠር ይህ ማስታወቂያ ወጥቷል። በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 30 ቀናት ውስጥ በተወዳዳሪነት መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን። አስፈላጊ የሆኑ መስፈርቶች፡ ኢትዮጵያዊ የሆነ/የሆነች እና በኢትዮጵያ የሚኖር /የምትኖር ፤ ለሕገ መንግስቱ እና ለሕግ የበላይነት ተገዢ የሆነ/የሆነች ፤ የየትኛውም የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነ/ያልሆነች ፤ በታታሪነቱ/ቷ ፣ በታማኝነቱ/ቷ ፣ በሥነ-ምግባሩ/ሯ መልካም ስም ያተረፈ/ች መሆኑን/ኗን ይማርበት/ ትማርበት ከነበረበት ዩኒቨርሲቲ ወይም ከሚኖሩበት አካባቢ ካለ የመንግስት ተቋም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል /የምትችል ፤ የወንጀል ቅጣት ሪከርድ የሌለበት/ባት ፤ የፌዴራል መንግስቱን የሥራ ቋንቋ የሚችል/የምትችል ፤ እንደ አስፈላጊነቱ የሚሰጠውን የጽሁፍም ይሁን የቃል ወይም ሁለቱንም ፈተና መውሰድ እና ማለፍ የሚችል /የምትችል፤ የሥራ መደብ፡ (ዐቃቤ ሕግ) ዐቃቤ ሕግ ደረጃ ሦስት ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፡ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋም በሕግ ትምህርት በመጀመሪያ ዲግሪ በ2018 ዓ.ም የተመረቀ /የተመረቀች፤ የመመረቂያ ነጥብ (Cumulative GPA) 3.6 ከዚያ በላይ ያለው/ ያላት፣ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት 85 ፐርሰንታይል እና ከዛ በላይ በማምጣት ፈተናውን ያለፈ/ያለፈች፤ ብዝሃነት፣ ሴት እና አካል ጉዳተኛ ተወዳዳሪዎችን እናበረታታለን፤ የሥራ ልምድ - 0 አመት ብዛት -25 የምዝገባ ሁኔታ፡- http://www.justice.gov.et በሚለው የተቋሙ ዌብሳይት ክፍት የሥራ ቦታ በሚለው ሥራ ባለው ማስፈንጠሪያ ወይም https://forms.gle/rWi1n6wi8HYYZubc7 በመጠቀም የሚጠይቀውን መረጃ በመሙላት እና ማስረጃዎችን በማያያዝ መመዝገብ ይቻላል። የምዝገባ ቀን፡- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ፤ ማስታወሻ፡- ተወዳዳሪዎች ሲመዘገቡ ሊያሟሏቸው የሚገባቸው ሰነዶች፡- 1. ኢትዮጵያዊ መሆናችሁን የሚገልጽ መታወቂያ/ፓስፖርት እና ብሔራዊ መታወቂያ በpdf scan የተደረገ፤ 2. ዋና የትምህርት ማስረጃ (student copy) ጨምሮ በpdf scan የተደረገ ፤ አጠቃላይ የመመረቂያ አማካይ ውጤት CGPA እና የመውጫ ፈተና ውጤትን Exit Exam የሚገልጽ የትምህርት ማስረጃ፣ 3. ከሚኖሩበት አካባቢ ካለ የመንግስት ተቋም ወይም ከተመረቁበት የትምህርት ተቋም የመልካም ሥነ ምግባር ማስረጃ፣ ለበለጠ መረጃ ፡- በስራ ሠዓት በስልክ ቁጥር ፡- +251-15-15-7432 በመደወል፤ እንዲሁም በኢሜል አድረራሻ፡- mojprosecutorsadministration@justice.gov.et ወይም mojpublicprosecutorsa@gmail.com ላይ በመፃፍ ማግኘት ይችላሉ። የኢፌዲሪ ፍትሕ ሚኒስቴር
🏆 Congratulations 🎉 The Wolkite University Law Students Association extends its heartfelt congratulations to Ephrem Hailemariam, a student of Wolkite University School of Law, for securing 🥈Second Place in the 3rd National ELSA Essay Competition on the topic: “The Role of Youth in Advancing Transitional Justice in Ethiopia.” This remarkable achievement demonstrates excellence in legal research, writing, and a strong commitment to contributing to the development of justice and the legal profession. Your success brings pride to Wolkite University School of Law and serves as an inspiration to fellow law students. 👏 Congratulations once again, Ephrem! We wish you continued success in all your future endeavors. ⚖️ Wolkite University Law Students Association (WULSA)
без подписи
Judicial training ማስታወቂያ ለጉራጌ ዞን የህግ ተመራቂዎች
#Judicial_Training ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ፍትህ መምሪያው በመምጣት እንድትመዘገቡ ጊዜ ካለፈ በኃላ የሚመጣ ተመዝጋቢ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን ። ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምስራቅ ጉራጌ ዞን ፍትሕ መምሪያ Thank you @unstoppableO2 for sharing with us🙏 የሕግ መረጃ @legal_infoo
Join the IFA Summer Camp 2026 Apply for Institute of Foreign Affairs(IFA) Summer Camp 2026 & gain valuable knowledge, practical experience & networking opportunities with future leaders. Who Can Apply: 🔸2026 Bachelor's degree graduates 🔸Current Master's students 🔸Applicants in Diplomacy, International Relations, Political Science or related social science fields 🔸Minimum CGPA, Female: 3.3 & above, Male: 3.5 & above 🔗Apply: here 📩Email: summer.camp@ifa.gov.et ✍Note: Both Email & forms are Mandatory to fill. Deadline: July 10, 2026 የሕግ መረጃ @legal_infoo
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሰብዓዊ መብቶች ሳምንታዊ መርሐ-ግብር ተጀመሯል ! ሰላም ውድ የክለባችን አባላት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እንዲሁም የግቢያችን ተማሪዎች በሙሉ በየሳምንቱ ረቡዕ የሚቀርበው የክረምት ልዩ ዝግጅታችን ዛሬ በአይነቱ ልዩ በሆነው የመክፈቻ ዝግጅታችን፣ የሰብዓዊ መብቶችን መሰረታዊ ምንነት በአጭሩ እንደሚከተለው በመቃኘት ይጀምራል። ⚖️ ሰብዓዊ መብቶች ምንድናቸው? ሰብዓዊ መብት ማለት ማንኛውም ሰው ሰው በመሆኑ ብቻ ፣ በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ሊያገኛቸው የሚገቡ መሠረታዊ መብቶች ናቸው። እነዚህ መብቶች በዘር፣ በፆታ፣ በሃይማኖት ወይም በማንኛውም ሌላ መመዘኛ ሳይለዩ ለሁሉም የሰው ልጆች በእኩልነት የሚሰጡ ናቸው። 📜 ሰብዓዊ መብቶች በአራት ዋና ዋና ባህሪያት ይታወቃሉ፦ ✨1 ፡(inheritable by nature) በተፈጥሮ የሚገኙ ናቸው ከአንድ ሰው የማይነጠሉ እና የማይወረሱ ናቸው 🌍2 (universal) አለማቀፋዊ ናቸው፡ በዓለም ዙሪያ ላሉ ሰዎች ሁሉ በዘር በፆታ በቀለም በሀይማኖት በፖለቲካ አስተሳሰብ ሳይለይ እኩል ተፈጻሚነት አላቸው 🔗 3 inseparable የማይነጣጠሉ፡ ሁሉም መብቶች እርስ በርስ የተያያዙ ናቸው፤ አንዱን መብት ማክበር ሌላውን ለማረጋገጥ ይረዳል። 4🏖 inalienable (የማይገረሰሱ) ሊገረሰሱ ወይም ሊቀነሉ አይችሉም። በሕግ በተደነገገ ከባድ የወንጀል ቅጣት ካልሆነ በስተቀር አየገረሰሱም። 📊 ክፍሎችስ አሉት? አዎን! ሰብዓዊ መብቶች በጊዜ ሂደት ባዳበሩት ይዘት በሶስት ትውልዶች ይከፈላሉ፦ 1)st gen (ሲቪል እና ፖለቲካዊ) ዓላማው :የዜጎች ነፃነትን ሚያረጋጥ። በህይወት የመኖር መብት፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት 2nd gen (ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ባህላዊ)፦ ዓላማው : እኩልነትን ሚያረጋገጥ ነው። የትምህርት መብት፤ የጤና አገልግሎት መብት ሀብት፣የማፍራት መብት 3rd gen የጋራ/የአብሮነት መብት:- ዓላማው: አንድነት እና አብሮነትን ማጠንከር የሰላም መብት ፤ ንፁህ አካባቢ የማግኘት መብት። ለቀጣይ ሳምንት በምን ርዕስ እንዘጋጅሎ ? ሀሳቦን አሰተያየት መስጫው ላይ (comment) ያስፍሩ እናመሰግናለን ። ✍ Natnael.A 💡 የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሰብዓዊ መብቶች ክለብ
ለመላው የህግ ትምህርት ቤት ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ ዛሬ የደረሳችሁበት የምርቃት ቀን በአጋጣሚ የመጣ ሳይሆን የብዙ አመታት ጥረት፣ፅናት እና እንቅልፍ አልባ ለሊቶች ውጤት ነው። እስከዛሬ ድረስ ስታልፏቸው የነበሩ ፈተናዎች እና እያንዳንዱ መሰናክሎች ለዛሬ ቀን አድርሰዋችኋል። ይህ የምርቃት ቀን የአንዱ ምእራፍ መዝጊያ ቢሆንም ለሌላ ጉዞ ደሞ መጀመሪያ ነው። የነገው ጉዞአችሁ የተቃና እና በደስታ የተሞላ እንዲሆንላቹ ልባዊ ምኞቴ ነው በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ ። ✍️ ብሩክ ገዛኸኝ የቀድሞ የWulsa ፀሀፊ የአሁን የፌደራል አ/ህግ።
100% Pass Rate! Congrats all!
Dear 2026 graduates of Wolkite University School of Law(Home), Congratulations on reaching this important milestone. As a proud former student of this very school and now a lecturer who had the privilege of teaching your cohort—the first class I taught in my role as an instructor—I feel a deep sense of pride and connection to each of you. Your graduation reflects years of hard work, late nights, thoughtful debate, and steady commitment to justice and learning. You have not only mastered legal doctrine and reasoning but also shown the character and perseverance that the legal profession demands. Watching you grow from learners into thoughtful advocates has been one of the most rewarding experiences of my career. As you step into the next chapter—whether further study, legal practice, public service, or other paths—carry with you the values this school instilled: integrity, compassion, rigorous analysis, and service to your community. Remember that law is not only a profession but a responsibility to those who rely on fair and honest representation. I am immensely proud to have been part of your journey in two roles: as an alumnus who once walked the same halls and as the first cohort I taught as a lecturer. Your success is a shared achievement for you, your families, and our law school. Go forward with confidence, continue to learn, and make a positive impact wherever you serve. Congratulations once again, Class of (2026). May your careers be fulfilling, your judgments wise, and your commitment to justice unwavering. We love you! Best, Remedan Nürgeta
Congratulations, Wolkite University School of Law Class of 2026! A remarkable milestone has been achieved. Congratulations to all graduates who successfully passed the Exit Examination and completed this important chapter of their legal journey. As you prepare to take the oath of your profession, remember that the law is more than a career. It is a commitment to justice, integrity, and service to society. Soon, you will wear your graduation gowns, walk across the stage with pride, and step into a future filled with responsibility and opportunity. The world needs principled advocates, courageous leaders, and dedicated defenders of justice. May your knowledge serve humanity, and may your voices contribute to a more just society. Congratulations, Future Lawyers! 🎓 Wolkite University School of Law Class of 2026 Ephrem Hailemariam
You can check your exit exam result through the below link https://result.ethernet.edu.et/result
📢 የ2018 የትምህርተ ዘመን ተመራቂዎች እንኳን ደስ አላችሁ!
ነገሮች ሁሉ ከመሳካታቸው በፊት ከባድ መምሰላቸው ተፈጥሯዊ ቢሆንም እናንተ ግን ባለፉት ዓመታት እጅግ አድካሚ የሆኑትን የሕግ መጻሕፍትና በርካታ ፈተናዎችን በጽናት አልፋችሁ እዚህ የደረሳችሁ ጠንካራ ተማሪዎች ናችሁ። እያነበባችሁ ያደራችሁበት ሌሊት፣ የደከማችሁበት ልፋትና ያነበባችሁት እያንዳንዱ የሕግ አንቀጽ ነገ ፍሬ የሚያፈራበት ትልቅ ቀን በመሆኑ በራሳችሁ ሙሉ እምነት ሊኖራችሁ ይገባል። ጭንቀትን አስወግዳችሁ በተረጋጋ መንፈስ ጥያቄዎችን በጥንቃቄ እያነበባችሁ ጊዜያችሁን በአግባቡ ከተጠቀማችሁ የተረጋጋው አእምሯችሁ ያጠናችሁትን በቀላሉ እንደሚያስታውሰው ጥርጥር የለውም። ይህ የመውጫ ፈተና የድላችሁና ወደ ቀጣዩ ትልቅ የሕይወት ምዕራፍ መሸጋገሪያ ማብሰሪያ እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ:: መልካም ዕድል! አቃቤህግ እንዳልካቸው ተስፋዬ የቀድሞ የWULSA አባል !
Candidate_placement_and_Schedule_by_Exam_Round_with_Session_1.pdf
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2018 በጀት አመት መጨረሻ የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና መስጫ ጊዜ ሰሌዳ
Interested applicants should submit their CV and cover letter to kiya.fule@csrc-et.org, copying contact@csrc-et.org, by no later than June 12, 2026. The selected fellow will be assigned at Central Ethiopia region, Hosaena.
Law Wednesday (10/10/18) Morning session 5:00-7:30
#Notice_Exit_Exam ለሰኔ ወር exit-exam ተፈታኝ ተማሪዎች በሙሉ:- የሃገር አቀፍ Exit exam ፈተና ከሰኔ 4/2018 ዓ/ም መሆኑን አውቃችሁ በብሔራዊ መታወቂያ (National ID) በመጠቀም የራሳችሁን መለያ ማረጋገጫ (Self-Identity Verification) ከዛሬ ጀምሮ ማጠናቀቅ ይኖርባችኋል። ይህ ማረጋገጫ በምዝገባ ጊዜ በሰጣችሁት የFAN ቁጥር እና የግል መረጃ (Biographic Data) መሠረት ይፈጸማል። ይህን ሂደት ለማጠናቀቅ ከ2–3 ደቂቃ ብቻ ይወስዳል። ለፈተናው መቀመጥ አስፈላጊ የሆነ ግዴታ ስለሆነ፣ የመለያ ማረጋገጫውን በተቻለ ፍጥነት በሚከተለው መግቢያ በመጠቀም ማጠናቀቅ ይጠበቅባችኋል። https://verify.ethernet.edu.et. On the verification page, candidates will find everything they need to complete the process, including a video guide.