Abu Salih Asselefy
Статистика- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 19
- Всего постов
- 33
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 109
- 1/48двое суток
- 124
- 1/72трое суток
- 134
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ምርጫው የእናንተ ነው የተመቻቹን ንኩት👇👇👇
🪴🪴ያሰላም🪴🪴 👉ደማቁ ፕሮግራማችን በ ሙሀመድ ከድር ከዶቦ ባማረ ሁኔታ ቀጥሏል Live በ IMO Group መርከዝ አት-ተቅዋ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://s.imoim.net/jcK8Ju?from=copy_link ገባ ገባ በሉ እንዳያመልጣችሁ በጣም ወሳኝ እና አንገብጋቢ ትምህርት እየተሰጠ ነው ለጓደኞቻችሁ ሼር ሼር አድርጉላቸው https://s.imoim.net/jcK8Ju?from=copy_link
🪴🪴ያሰላም🪴🪴 👉ደማቁ ፕሮግራማችን ሊጀመር ትንሽ ሰዓት ብቻ ቀረው ሼር ሼር ሼር ሼር እያደረጋችሁ ጠብቁ ጀዛኩሙሏሁ ኸይረን Live በ IMO Group መርከዝ አት-ተቅዋ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 https://s.imoim.net/jcK8Ju?from=copy_link ገባ ገባ እያላችሁ እንዳያመልጣችሁ በጣም ወሳኝ እና አንገብጋቢ ትምህርት ነው ሚሰጠው በአሏህ ፍቃድ ለጓደኞቻችሁ ሼር ሼር አድርጉላቸው
🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴 🪴አሰላሙ ዐለይኩም ወረህመቱላሒ ወበረካቱሁ 🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴🪴 👉እነሆ የፊታችን ጁመዓ ታላቅ የሙሓደራ ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ይጠብቃችኋል ። 🌹🌹🌹🌹 🌹በዚህ ውብና ድንቅ ፕሮግራም የሚገኙ ውድ ተጋባዥ እንግዶቻችን ።🌹 🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹 1,ኡስታዝ አቡ ማሂር ሙሀመድ ኸድር ከዶቦ 2,ኡስታዝ ኸይረዲን ብን ጀማል አሏህ ይጠብቀው 3,ኡስታዝ ሙሀመድ አህመድ ከቡታጅራ 4,ኡስታዝ አቡ ኢንቲሷር ከቡታጅራ አሏህ ይጠብቀው እና ሌሎችም ኡስታዞች ይኖራሉ ኢንሻአላህ 🔰ፕሮግራሙ የሚካሄደው በ imo room መርከዝ አት-ተቅዋ ላይ! 🔰ፕሮግራሙ የሚካሄድበት ሰዓት በኢትዮ ከምሽቱ 02:30 ጀምሮ__? 🔰የፕሮግራሙ አዘጋጅ ወንድም አቡ ፈሪሃት ከወራቤ 🔰ፕሮግራም የሚተላለፍበት ቻናል በኢሞ https://s.imoim.net/jcK8Ju?from=copy_link 🔰የቴሌግራም ቻናላችን ለመቀላቀል ጆይን ብለው ይግቡ ቡዙ ጠቃሚ መረጃዎችን ያገኛሉ !! https://t.me/abusalih1234 https://t.me/abusalih1234
بسم الله الرحمان الرحيم الحمد لله رب العالمين، والصلاة والسلام على نبينا محمد، وعلى آله وصحبه أجمعين. أما بعد: 👉ውድ የአላህ ባሮች ሆይ! ዛሬ ላስታውሳችሁ የፈለግኩት ጉዳይ በእጅጉ ከባድና አስፈላጊ ጉዳይ ነው። 👉እሱም በሐቅ ላይ የተሰባሰብን ወንድሞች እና እህቶች እርስ በርሳችን መዋደድ፣ መተዛዘን፣ መደጋገፍና አንድነታችንን መጠበቅ እንዳለብን ነው። ዛሬ ባለንበት ግዜ በአብዛኛው የምናየው(የምንመለከተው)ነገር በጣም የሚያሳዝን ነው። እውነተኛ ሱናን እና የሰለፎችን መንገድ እንከተላለን የምንል ሰዎች በመካከላችን ፍቅርና መተዛዘን መዋደድ መከባበር ልንጨምር ሲገባ፣በመሀከላችን -መጠላላት መመቀኛኘትን ፣ መቃቃር፣ መተቻቸት፣መናናቅ ፣ወዘተ ይታያል። ይህ ተግባራችን ግን የሰለፎች መንገድ አይደለም። 👉አላህ سبحانه وتعالى እንዲህ ብሏል፦ ﴿وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا وَلَا تَفَرَّقُوا﴾ «ሁላችሁም በአላህ የእምነት ገመድ ተያያዙ(ተሰባሰቡ)በጥብቅ ያዙ፤ አትለያዩም።» ውድ ወንድሞቼ ሆይ! አላህ የእኛን አንድነት እንድንጠብቅ አዞናል። 👉 ይህ አንድነት መጠበቅ ማለት ስህተትን አይተን ችላ ማለት ወይም ሐቅን መተው አይደለም። ነገር ግን ሐቅን በጥብቅ እየጠበቅን በሀቅ እየተመካከርን እና ሀቅን በሀቅነቱ እየገለፅን የወንድማችንን ልብ፣ ክብርና ክብረ ባሕርይ መጠበቅ ነው። 👉አላህ እንዲህ ይላል፦ ﴿إِنَّمَا الْمُؤْمِنُونَ إِخْوَةٌ فَأَصْلِحُوا بَيْنَ أَخَوَيْكُمْ﴾ «ምእመናን(ሙእሚኖች) በእርግጥ ወንድማማቾች ናቸው፤ ስለዚህ በሁለቱ ወንድሞቻችሁ መካከል አስተካክሉ(አስታርቁ)።» 👉እንግዲህ ሙእሚኖች ወንድማማቾች ከሆኑ፣ ወንድማችን ሲወድቅ እንዲወድቅ መግፋት ሳይሆን እጁን ይዘን ማንሳት ይገባናል። ሲሳሳት ማዋረድ ሳይሆን በርህራሄ መምከር ይገባናል። 👉ምቀኝነት የወንድማማችነት ጠላት ነው ውድ የአላህ ባሮች ሆይ! አንድ ወንድማችን በእውቀት ከፍ ሲል፣ ብዙ ሰዎች ሲጠቀሙበት፣ ዳዕዋው ሲስፋፋ፣ አላህ በሥራው በረከት ሲሰጠው፤ እኛ መቅናት(መመቃኘት) ሳይሆን ለእርሱ መደሰት አለብን። የወንድማችን ስኬት የእኛ ውድቀት አይደለም። አንድ የሱና ወንድም ሲጠነክር የሱና ዳዕዋ ነው የሚጠነክረው። 👉ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «لا تَحَاسَدُوا، ولا تَبَاغَضُوا، ولا تَدَابَرُوا، وكونوا عبادَ الله إخوانًا» «አትቀናኑ(አትመቀኛኙ)፣ አትጠላሉ፣ ጀርባችሁንም አትሰጣጡ፤ የአላህ ባሮች ሆናችሁ ወንድማማቾች ሁኑ።» 👉ወንድምህ ለአንተ ግንብ ነው ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦ «المؤمن للمؤمن كالبنيان يشد بعضه بعضًا» «አማኝ የሆነ አካል ለሌላኛው አማኝ እንደ ሕንፃ(ግንብ) ነው፤ አንዱ ክፍል ሌላውን ያጠናክራል።» አንድ ግንብ ጡቦቹ እርስ በርሳቸው ከተለያዩ ግንቡ ይፈርሳል። እኛም እንዲሁ ነን። አንዱ ሌላውን ካልደገፈ፣ ካልተዛዘነ፣ ካልመከረና ካልጠበቀ የጠላት ሥራ ይቀላል።ትልቅ ክፍተት ይፈጠራል 👉ወንድሞቼ ሆይ! ሰዎች በሁሉም ነገር አንድ አይሆኑም። የእውቀት ልዩነት ሊኖር ይችላል፤ አስተያየት(አስተሳሰብ )ሊለያይ ይችላል። ነገር ግን ልዩነት ወደ ጥላቻ፣ ምቀኝነት፣ መሰዳደብና መበታተን መቀየር የለበትም። ስህተት ካየን እንመክራለን። ግን የምክር ዓላማችን ወንድማችንን ማዋረድ ሳይሆን ማስተካከል ይሁን። ዓላማችን እኛ እንደበለጥን ማሳየት ሳይሆን ሐቅ እንዲገለጥ ይሁን። ይህንን ዱዓ በብዛት እንበል፦ ﴿رَبَّنَا لَا تَجْعَلْ فِي قُلُوبِنَا غِلًّا لِلَّذِينَ آمَنُوا رَبَّنَا إِنَّكَ رَءُوفٌ رَحِيمٌ﴾ «ጌታችን ሆይ! በልባችን በአመኑት ሰዎች ላይ ቂም አታድርግብን፤ ጌታችን ሆይ! አንተ በጣም ሩህሩህና አዛኝ ነህ።» [الحشر: 10] ይህ የሙእሚኖች ዱዓ ነው። ስለዚህ ልባችንን ከምቀኝነት፣ ከጥላቻ፣ ከትዕቢትና ከቂም እናጽዳ። የአላህ ባሮች ሆይ! እስኪ ዛሬ እያንዳንዳችን ራሳችንን እንጠይቅ፦ 👉ወንድሜ ሲሳካ እደሰታለሁን? 👉ወንድሜ ሲሳሳት በርህራሄ እመክረዋለሁን? 👉ወንድሜ በችግር ሲወድቅ እረዳዋለሁን? 👉በሌለበት ክብሩን እጠብቃለሁን? 👉ለእርሱ በሌሊት ዱዓ አደርጋለሁን? እያንዳንዳችን ከራሳችን እንጀምር። ሰለፊያ በምላስ ብቻ የምንጠራው ስም አይደለም፤ በእምነት፣ በአክላቅ፣ በርህራሄ፣ በእውነትና በአዳብ የምንኖረው መንገድ ነው። አንዱ ወንድሙን ካጠናከረ፣ ሁላችንም እንጠነክራለን። አንዱ ወንድሙን ካፈረሰ ግን ሁላችንም እንዳንወድቅ እንጠንቀቅ። اللهم أصلح ذات بيننا، وألِّف بين قلوبنا، واهدنا سبل السلام. اللهم انزع من قلوبنا الحسد والبغضاء والغل والكِبر، واجعل قلوبنا سليمةً لإخواننا المسلمين. اللهم ألِّف بين قلوب أهل السنة، واجمع كلمتهم على الحق، وأصلح علماءهم ودعاتهم وشبابهم، واجعلهم متعاونين على البر والتقوى. اللهم من كان منا مخطئًا فاهده، ومن كان مصيبًا فثبته، واجعلنا جميعًا مفاتيح للخير مغاليق للشر. اللهم اجعلنا متحابين فيك، متراحمين فيما بيننا، ناصحين مشفقين، متعاونين على الحق. ربنا لا تجعل في قلوبنا غلًّا للذين آمنوا، ربنا إنك رؤوف رحيم. اللهم آمين يا رب العالمين. 🪴በዚህ ፅሁፍ ላይ ማነኛውም ስህተት ካያችሁ እርምት ስጡኝ በአሏህ ፍቃድ ለማስተካከል ዝግጁ ነኝ። ✍ወንድማችሁ አቡ ፈርሃት አስ-ሰለፊይ https://t.me/abusalih1234
✅ የጁምዓ ቀን ሱናዎች ❶ኛ ገላን መታጠብ። ➋ኛ ሽቶን መቀባባት እና መዋብ። ❸ኛ ሲዋክን መጠቀም። ❹ኛ የክት ልብስ መልበስ። ❺ኛ በጊዜ መስጂድ መጓዝ። ❻ኛ በእግር እየተጓዙ ወደ መስጅድ መሄድ። ❼ኛ መስጂድ ከደረሱ በኋላ የሰዎችን ትከሻ በመረማመድ ሰዉን አለማስቸገር። ❽ኛ ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ቢሆንም ተህየቱ መስጂድ መስገድ። ❾ኛ ኹጥባ ወደ የሚያደርገው ኢማም መዞርና እሱን እያዩ ኹጥባ ማድመጥ። ❿ኛ ኹጥባ በሚደረግበት ሰዓት ፀጥታን መላበስ። ⓫ኛ ሰደቃን ማብዛት። ⓬ኛ ከሀሙስ ማታ ጀምሮ እሰከ ጁምዓ ዐስር ድረስ ሱረቱ ከሕፍ መቅራት። ⓭ኛ ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሰዓትን መጠባበቅ። ⓮ኛ በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን በብዛት ማውረድ። https://t.me/abusalih1234
شرح كتاب "سبيل الرشاد " للأستاذ الفاضل إلياس أول _حفظه الله _. وفيه نصائح طيبة في التآخي في الله والحث على المودة والألفة والبعد عن الغيبة والنميمة والحسد.
قال الشيخ عبد الحميد اللتمي - حفظه الله تعالى وكل ما ورد في القرآن من قصص الأنبياء ** وما أعطاهم من الآيات ومدحهم عليه من المجهودات ، والصبر على البليات ، والشكر على الانعامات ، وما خلد ذكرهم في الأجيال على مر السنوات ، وما يعطيهم في الآخرة من الزلفة والرفعة في الدرجات والقرب عنده في أعلى المقامات ، ولا سيما لأشرف المخلوقات وأفضل البريات ، ومقدم ذي الرسالات محمد بن عبد الله رسول الله - صلى الله عليه وسلم - بعد المخلوقات كل حين وساعات وكذلك أصحابه الكرام من المهاجرين والأنصار الذين سعوا إلى إعلاء هذه الكلمة المباركة من غير قصور ولا فتور حتى بذلوا النفيس والنفوس الغاليات وكل من تبعهم بإحسان من مؤمن ومؤمنات إلى أن يأتي يوم لا تنفع هذه الكلمة ''لا إله إلا الله محمد رسول الله'' فيه ولا غيرها من الطاعات والعبادات والقربات ، فكل ذلك بتحقيق هذه الكلمة لفظا ومعنا وقلبا وقالبا ظاهرا وباطنا ، مقتضيات وموجبات ومستلزمات وثبات عليها وموت على ذلك ءالآء الله في مكانة لا إله إلا الله ، صفحة ( ١٣٣ ) 👉ሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ አል-ለተሚ — አላህ ይጠብቀው — እንዲህ አሉ፦ «በቁርአን ውስጥ ከነቢያት ታሪኮች የተወሳው ሁሉ፣ አላህም ለእነርሱ ከሰጣቸው ተአምራትና ምልክቶች፣ እንዲሁም በእነዚያ አላህ ያመሰገናቸው ጥረቶችና ተጋድሎዎች፣ በመከራዎች ላይ ያደረጉት ትዕግሥት፣ አላህ በሰጣቸው نعمة (በረከቶችና ጸጋዎች) ላይ ያደረጉት ምስጋና፣ እንዲሁም ስማቸውንና ዝክራቸውን በዘመናት ሁሉ በትውልዶች መካከል ዘላቂ እንዲሆን ያደረገው፤ እንዲሁም በመጨረሻይቱ ዓለም ከአላህ ዘንድ የሚያገኙት ቅርበት፣ ከፍተኛ ደረጃና ክብር፤ በተለይም ከፍጡራን ሁሉ ክቡር ለሆነው፣ ከሰዎች ሁሉ በላጭ ለሆነው፣ የመልእክተኞች መሪ ለሆነው ሙሐመድ ኢብኑ ዐብደላህ — የአላህ መልእክተኛ ﷺ፤ እንዲሁም ከእርሳቸው በኋላ በየዘመኑና በየሰዓቱ ይህንን ቃል ለማስፋፋትና ከፍ ለማድረግ ያለምንም ድካምና መታከት የተጋደሉት የተከበሩ ሰሐቦች፣ ከሙሐጂሮችና ከአንሷሮች፤ ይህንን የተባረከ ቃል ከፍ ለማድረግ በመጣር ውድ የሆኑ ንብረቶቻቸውንም ሆነ የተከበሩ ነፍሳቸውን እስከመስጠት ደርሰዋል። እንዲሁም እስከ የትንሣኤው ቀን ድረስ በመልካም ሁኔታ እነርሱን የተከተሉ እምነተኛ ወንዶችና ሴቶች ሁሉ። በዚያ ቀን ግን «ላ ኢላሃ ኢለላህ፣ ሙሐመዱር ረሱሉላህ» የሚለው ቃልም ሆነ ሌሎች የአምልኮ ሥራዎች፣ ታዛዥነቶችና ወደ አላህ የሚያቀርቡ መልካም ሥራዎች ምንም ጥቅም የማያስገኙበት ጊዜ ይመጣል። ስለዚህ ይህ ሁሉ ይህንን ቃል በንግግር፣ በትርጉሙ፣ በልብና በውጫዊ ተግባር፣ በውስጣዊና በውጫዊ መልኩ፣ ከሚያስፈልጉት መስፈርቶችና ግዴታዎች ጋር፣ እንዲሁም በእርሷ ላይ ጸንቶ በእርሷ ላይ መሞትን በማረጋገጥ የሚገኝ ነው። **እነዚህ ሁሉ የአላህ ጸጋዎች በ«ላ ኢላሃ ኢለላህ» የሚገኘውን ቦታና ዋጋ ያሳያሉ።» 👉የንግግሩ ዋና መልእክት ሸይኹ የሚያስረዱት፣ «ላ ኢላሃ ኢለላህ» በአፍ ብቻ መናገር እንዳልሆነ ነው። ትርጉሟን ማወቅ፣ በልብ ማመን፣ በተግባር መፈጸም፣ የምታስገድደውን መታዘዝ፣ በእርሷ ላይ መጽናትና በእርሷ ላይ መሞት ያስፈልጋል። በአጭሩ፦ የነቢያት፣ የሰሐቦችና የእነርሱን መንገድ የተከተሉ ሰዎች ጥረት ሁሉ ይህንን የተወደደ የተውሒድ ቃል በእውነተኛ መልኩ ለመፈጸም ነው። ✍በወንድም አቡ ፈሪሃት አስ-ሰለፊይ https://t.me/abusalih1234
مناظرة الإمام الشافعي لأحد المرجئة قال الإمام الشافعي : ومن أين قلت ، إن العمل لا يدخل في اﻹيمان ؟ قال المرجئ : من قوله تعالى : { إن الذين ءامنوا وعملو الصالحات } البقرة (٢٧٧) فصار الواو فصلا بين الإيمان والعمل ، فالإيمان : قول ، والأعمال شرائع . فقال الشافعي : وعندك الواو فصل ؟ قال المرجئ نعم . فقال الشافعي : فإذا كنت تعبد إلهين : إله في المشرق ، وإله في المغرب ، لأن الله تعالى يقول : {رب المشرقين ورب المغربين} . فغضب الرجل ، وقال : سبحان الله ! أجعلتني وثنياً ؟ فقال الشافعي : بل أنت جعلت نفسك كذلك . قال : كيف ؟ قال : بزعمك أن الواو فصل . فقال الرجل : فإني أستغفر الله مما قلت ، بل لا أعبد إلا رباً واحداً ، ولا أقول بعد اليوم : إن الواو فصل ، بل أقول : أن الإيمان قول وعمل ، ويزيد وينقص . 📚 حلية الأولياء وطبقات الأصفياء ، لأبي نعيم الأصبهاني (١١٠/٩) t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk https://t.me/abusalih1234
🟢የፈትዋ ቁጥር 1⃣3⃣ እድር መመስረት ወይም አባል መሆን⁉️ መልስ 🔊በሸይኽ ዐብዱልሀሚድ አለተሚይ https://t.me/abusalih1234
➖ከቢድዓ ባለቤቶች ጋር ፈጽሞ መተባበር አይቻልም ➖ሙመይዓዎች እነማን ናቸው? 🎙ኸድር አህመድ አል ኬሚሴ (በሀቅ ላይ በነበረበት አቋሙ የተናገረው) https://t.me/abusalih1234
መውልድን የማናከብርበት ዋና 4 ምክንያቶች የነቢዩ እና የሰሃባዎች አርአያነት ማጣት፦ ነቢዩ ሙሐመድ፣ የቅርብ ባልደረቦቻቸው (ሰሃባዎች) እና ታላላቅ የጥንት ምሁራን (ታቢዒዮች) ይህንን ቀን በዓል አድርገው አላከበሩም። የቢድዓ (የባዕድ አምልኮ/ፈጠራ) ስጋት፦ በሃይማኖት ውስጥ ነቢዩ ያላዘዙትን ወይም ያላደረጉትን አዲስ የአምልኮ ሥርዓት መጨመር በጥብቅ የተከለከለ (ቢድዓ) ነው። የሃይማኖት መሟላት፦ እስልምና ነቢዩ ከመሞታቸው በፊት ሙሉ በሙሉ ተሟልቶ አብቅቷል። አዲስ በዓል መፍጠር ዲኑ አልተሟላም እንደማለት ይቆጠራል። ውዴታን በሱና መግለጽ፦ ለነቢዩ ያለንን ፍቅር መግለጽ ያለብን በዓመት አንድ ቀን በመሰብሰብ ሳይሆን፣ በየቀኑ ትዕዛዛቸውን እና ሱናቸውን በመተግበር ነው። https://t.me/abusalih1234
👑✍ ለትዳር የሚመረጥ ወንድ!👑 ⇨ ለጌታው ታዛዥ የሆነ ⇨ የቀደምቶችን መንገድ የሚከተል ⇨ የሚስቱን ሀቅ ሊጠብቅ የሚችል ⇨ ለሀቅ ልቡ ክፍት የሆነ ⇨ ስነምግባሩ እና ዲኑ ያማረ ⇨ ከጥሩ ቤተሰብ የተወለደ ⇨ ሚስጥር ጠባቂ የሆነ ⇨ ለመከሰብ ዝግጆነት ያለው ⇨ የሸሪአዊ እውቀት የሚማር https://t.me/abusalih1234
🌺✍ ለትዳር የምትመረጥ ሴት፦🌺 ⇨ ሲያያት የምታስደስተው ⇨ ሲያዛት እሺ የምትለው ⇨ በነፍሷም በንብረቱም የማትቃረነው ⇨ ለጌታዋ ታዛዥ የሆነች ⇨ ከጥሩ ቤተሰብ የተወለደች ⇨ ሚስጥር ጠባቂ የሆነች ⇨ ውስጧም ውጪዋም ቆንጆ የሆነች ⇨ ወላድ እና አፍቃሪ የሆነችዋ 👆 በቃ አግባ አትልፈስፈስ! https://t.me/abusalih1234
አሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ እህት ወንድሞች አንድ ነገር ላስቸግራቹ ነው ለአላህ ብላቹ ተባበሩኝ አንዲት እህት ስደት ከመጣች ሁለት አመት ሆኗታል ግን በጣም እሚያሳዝነው አሰሪዋ ጠንቋይ ናትና ልጅታን ምንም ነገር እንዳታቅ አድርጋ አፍዝዛታለች እናም ይችህ እህት አላህ ዳኚ ሲላት ዝምብላ ከቤቱ ትወጣለች ከዛም ሲደክማት መንገድ ላይ ቁጭ ትላለች ከዛም አንድ ሱዳናዊ ግለሰብ ያያታል ሲያያት ግን…
اسم الكتاب : البراهين العتيدة في كشف أحوال وتأصيلات علي الحلبي الجديدة المؤلف : الشيخ أبو معاذ رائد آل طاهر قرأه وراجعه : العلامة الشيخ د.ربيع بن هادي المدخلي رحمه الله والعلامة الشيخ د.محمد بن هادي المدخلي حفظه الله https://t.me/abusalih1234
🔖አይይ ሱፊይ አህሉል_አህዋዕ ሰለፊዮችን በመረጃ ማሸነፍ ሲያቅታቸው ልክ ከላይ በቪዲዮ እንደምትመለከቱት ደዕዋቸውን ለማቋረጥ ለማደናቀፍ ከቻሉ በጉልበት እሄ ካልተሳካላቸው ደሞ ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ፀጥታ ቢሮዎች ወይም ፍርድ ቤት ለፍርድቤት ሲርመጠመጡ ታያቸዋለህ! 👌በተለይ በተለይ በዚህ ሰዓት ፍርድ ቤት ለፍርድ ቤት ሲራሮጡ ምታያዋቸው "ሙመይዓዎችን" ነው። ሀዳሁሙላህ!! https://t.me/abusalih1234
🔷በሐቅ ላይ መጽናት ፤ አለመገለባበጥ የአህለሱና መለያ ባህሪ ነው ከአህለሱና ጉልህ መለያዎች : በሐቅ ላይ መጽናት ፣ አለመገለባበጥ ፣ የጥልቅ እውቀት ባለቤትም ይሁን ማንኛውም ደግ የአሏህ ባሪያ መገለባበጥና የአቋም መጣረስ ከእነርሱ ዘንድ አይታወቅም። የአቋም መጣረስ ፣ መገለባበጥ የሚገኘው ውዳቂ፣ ሸረኛና ወራዳ ከሆኑ ሰዎች ዘንድ ነው። ሸይኹል ኢስላም ኢብን ተይሚያ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "የሱናና የሐዲስ ባለቤቶች ከኡለሞቻቸውም ይሁን ከሌሎች ደጋግ የአሏህ ባሮች ከንግግሩ ከአቂዳው የተመለሰ አንድም አይታወቅም ። በተለያየ ፈተና እና መከራ ቢፈተኑ እንኳ ከሰዎች መካከል በትእግስት ከፍተኛውን ደረጃ የያዙ እነርሱ ናቸው። ይህ የነብያትና ቀደምት ተከታዩቻቸው ባህሪ ነው። የጉድጓድ ባለቤቶች እና የመሳሰሉት ፤ ከዚህ ኡመት ቀደምቶች ፣ሶሃቦች ፣ ታብዕዮች እና ሌሎችም አኢማዎች ባህሪ ነው። ኢማም ማሊክ - ረሂመሁሏህ - እንዲህ ብለዋል :- "በዚህ ጉዳይ ፣ ፈተና ባልደረሰበት አንድም አካል አትቅኑ።" አሁንም እንዲህ ብለዋል :- "አሏህ አማኝን መፈተኑ አይቀርም። ከታገሰ ደረጃውን ከፍ ያደርግለታል።" https://t.me/abusalih1234
✅ የሰው ልጅ ጠላቶች ሶስት ናቸው ! قال يحى بن معاذ – رحمه الله تعالى – " أعداء الإنسان ثلاثة. دنياه، وشيطانه، ونفسه. فاحترس من الدنيا بالزهد فيها ومن الشيطان بمخالفته ومن النفس بترك الشهوات ". البصائر والزخائر (8/75) የሕያ ኢብኑ ሙዓዝ የተባለ ዓሊም እንዲህ ይላል : – " የሰው ልጅ ጠላቶች ሶስት ናቸው ። ዱንያ, ሸይጧንና ነፍሱ, ከዱንያ ችላ በማለት, ከሸይጧን እሱን በመኻለፍ (ባለመታዘዝ) ከነፍስህ ደግሞ ስሜትህ የፈለገውን ነገር በመተው ተጠበቅ "። http://t.me/bahruteka
без подписи