አል-ዓፊያ ስፔሽያላይዝድ የህክምና ማዕከል / Al-Afia Specialized Medical Center
Статистикаofficial channel for Al-Afia Medical Center
- Последний пост
- 10 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 21
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 83
- 1/48двое суток
- 95
- 1/72трое суток
- 102
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ከፍተኛ ኮሌስትሮል ምልክት ላያሳይ ይችላል፤ ጉዳቱ ግን ከባድ ነው። 🫀 ልብዎን ለመጠበቅ፦ ✅ የደም ቅባትዎን ይመርምሩ ✅ ጤናማና በፋይበር የበለጸገ ምግብ ይመገቡ ✅ የአካል እንቅስቃሴ ያድርጉ ✅ ሲጋራ አያጨሱ ✅ የታዘዘልዎን መድኃኒት በአግባቡ ይውሰዱ የደም ቅባትዎን ይወቁ፤ ልብዎን ይጠብቁ! #የደም_ቅባት #ኮሌስትሮል #የልብ_ጤና #ጤናማ_አኗኗር #ጤና_ትምህርት #DrOumerAbdu
без подписи
መልካም የጤና ሳምንት💧
ኮሶ ጠፍጣፋ ልጥ መሳይ ነው! ወስፋት ደግም ፓስታ መሳይ ነው። ኮሶ በጥሬ ስጋ አማካኝነት ይመጣል።
без подписи
የጉበት ጤና ምክር 🌟 የጉበትዎን ጤና ይጠብቁ፣ ሕይወትዎን ይጠብቁ! 🌟 ጉበትዎ የሰውነትዎ ተፈጥሯዊ መርዛማ ንጥረ ነገሮችን ማጥፊያ ነው። በሚከተሉት ምክሮች ጤናማ ያድርጉት፦ 🍏 የተመጣጠነ ምግብ ይመገቡ 💧 በቂ ውሃ ይጠጡ 🚫 የአልኮል መጠጥን ይገድቡ 🏃 አዘውትረው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያድርጉ 🚬 ማጨስን ያስወግዱ 💊 መድኃኒቶችን በጥበብ ይጠቀሙ 🩺 አዘውትረው ምርመራ ያድርጉ የባለሙያ ምክር ይፈልጋሉ? የአል-አፊያ ስፔሻላይዝድ ሜዲካል ሴንተርን ያነጋግሩ 📞 0970969696
без подписи
ከአል-ዓፊያ ስፔዛላይዝድ የህክምና ማዕከል የተሰጠ የእለቱ የጤና ምክር ———————————————- 👉በቀን 8 ብርጭቆ ውሃ ይጠጡ! ለምን; - ከሰውነታችን አላስፈላጊ ንጥረ ነገሮችን ያስወግዳል - የአዕምሮ ብቃትን ያሻሽላል - የምግብ ፍጭትን ያሳልጣል - ቆዳን ያለሰልሳል፣ ያጠራል 👉በቂ ውሃ ይጠጡ፣ ጤናዎን ይጠብቁ! -ይህንን መረጃ ለወዳጅዎ ያጋሩ! 👉የጤና እርዳታ ከፈለጉ ይጎብኙን! ስልክ ቁጥር ፡ 0970-96-96-96 011-369-6689 👉https://t.me/alafiamedicalcenter
без подписи
без подписи
без подписи
የሰው ልጅ የተፈጠረው ለመልፋት ይመስለኛል። ሁለት እግር እና ሁለት እጅ የተደረገልንም ለዚያው ይመስለኛል። #WHO መቀመጥ ሲጋራ እንደማጨስ ነው ብሏል‼ t.me/wanawtena2013
#የማህፀን_ጫፋ_ካንሰር_ምልክቶች ====== ✅ያልተለመደ የሴት ብልት ደም መፍሰስ፣ ለምሳሌ ከግብረ-ስጋ ግንኙነት በኋላ ወይም ከማረጥ በኋላ ደም መፍሰስ። ✅ ያልተለመደ ከሴት ብልት የሚወጣ ፈሳሽ ውሃ, ወፍራም ወይም መጥፎ ጠረን ሊሆን ይችላል. ✅ በግብረ ሥጋ ግንኙነት ወቅት የሆድ ህመም ✅ የሽንት ድግግሞሽ ወይም አጣዳፊነት መጨመር. ✅ በሽንት ጊዜ የመሽናት ችግር ወይም ህመም. ✅ በእግር ላይ ህመም ወይም እብጠት 🔷መከላከል ይቻላል? አዎ ✅. የ HPV ክትባት ይውሰዱ፡ የ HPV ክትባት ከማህፀን በር ካንሰር ለመከላከል ምርጡ መንገድ ነው። ዕድሜያቸው ከ11-12 ለሆኑ ልጃገረዶች እና ወንዶች የሚመከር ቢሆንም እስከ 26 ዓመት ድረስ ሊሰጥ ይችላል. ✅ መደበኛ የፔፕ ምርመራዎችን ያድርጉ፡- የፔፕ ምርመራዎች በማህፀን በር ጫፍ ውስጥ ካንሰር ከመያዛቸው በፊት የቅድመ ካንሰር ሕዋሳትን መለየት ይችላሉ። ሴቶች በ 21 ዓመታቸው መደበኛ የፔፕ ምርመራ ማድረግ መጀመር አለባቸው እና በየሶስት ዓመቱ እስከ 65 ዓመት እድሜ ድረስ ማግኘታቸውን መቀጠል አለባቸው። ✅ ደህንነቱ የተጠበቀ የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ተለማመዱ፡- የኢንፌክሽን አደጋን ለመቀነስ ኮንዶም ይጠቀሙ ✅ ማጨስን አቁሚ፡- ሲጋራ ማጨስ የማኅፀን ካንሰርን የመጋለጥ እድልን ይጨምራል ስለዚህ ማጨስን ማቆም ለመከላከል ጠቃሚ እርምጃ ነው ምንጭ- ጤናዎ በእጅዎ t.me/tena_amakari
#የኤች_አይ_ቪ(HIV/AIDS) #ከእናት_ወደ_ልጅ_መተላለፍን_መከላከያ_መንገዶች (PMTCT) ===== ☑️ #ሊደረጉ_የሚገባ_ዋና_ዋና_እርምጃዎች ======= ☑️ለሁሉም እርግዝና ያላቸው ሴቶች የHIV ምርመራ ማድረግ አለባቸው 🖊ውጤቱ ፖዘቲቭ(+) ከሆነ፣ በፍጥነት የፀረ_ቫይረስ ሕክምና (ART) መጀመር አለባቸው። 🖋ይህ የቫይረሱን መጠን (viral load) ዝቅ በማድረግ እና ወደ ህጻኑ እንዳይተላለፍ ይረዳል። ☑️ #ደህንነቱ_የተጠበቀ_ወሊድ_ማድረግ ====== 🖊በጤና ተቋም በሕክምና ባለሙያዎች ቁጥጥር ስር መውለድ። 🖊አንዳንድ ሁኔታዎች ላይ ቀዶ ህክምና(CS) ሊያስፈልግ ይችላል። ☑️ #የሕጻን_አመጋገብ_አማራጮቾንመወሰን ====== 1. #የእናቱ_ጡት_ብቻ ==== የእናት ጡት ብቻ ለ6ወር ከዛም እንደማንኛውም ህፃን ተጨማሪ ምግብ ማስጀመር እና ጡት ማጥባቷን እስከ 2 ዓመት መቀጠል። 🖋ይህን ለማድረግ እናቲቱ የፀረ HIV መድሀኒት እየወሰደች መሆን አለበት። 2. #በፎርሙላ_መጠቀም ====== ከመጀመሪያው ጀምሮ በፎርሙላ ምግብ ብቻ መቀጠል። ይህም ከወሊድ በኋላ በጡት ማጥባት የሚተላለፈውን የቫይረስ መጠን ያስወግዳል። 3. #የተለገሰ_የጡት_ወተት(Donor milk) መጠቀም። ==== ይህ ብዙ ጊዜ ተግባራዊ የሚሆነው ባደጉት ሀገሮች ላይ ነው። ☑️ #ለህጻኑ_የፀረ_ቫይረስ_ሕክምና (Prophylaxis) #መስጠት ===== - HIV ያለች እናት የወለደችው ህጻን ለተወሰነ ጊዜ (4-6 ሳምንት) የፀረ_HIV መድሃኒት እንድወስድ ማድረግ። ከ6ሳምንት በኋላ ለህፃኑ የHIV ምርመራ ማድረግ እና ነፃ ሁኖ ከተገኘ የቫይረስ ህክምናውን ማቋረጥ። ☑️ #ውጤታማነት ====== - በትክክል ከተከተለ፣ የHIV ከእናት ወደ ልጅ የመተላለፍ አደጋ ከ2% በታች ሊሆን ይችላል። - ያለ ምንም እርዳታ ግን ፣ አደጋው የከፋ ነው፣የመተላለፍ እድሉም ከ30-45% በላይ ሊሆን ይችላል። ☑️ #ተጨማሪ_ጠቃሚ_ምክሮች ======= ✔ የእርግዝና ወቅት የደም የHIV ምርመራዎችን በጊዜ ማድረግ። ✔ የHIV + ከሆኑ፣ በጊዜ ሕክም መጀመር እና መከታተል። ✔ የልጅዎ ስለሚደረገው ጥንቃቄ ከሕክምና ባለሙያዎች ጋር መወያየት። ☑️ #ምንጭ ጤናዎ በእጅዎ t.me/wanawtena2013
#ተከታታይ_የጽንስ_መጨንገፍ(#ውርጃ)/Recurrent pregnancy loss/ ====== 👉ከስድስት ከሚፈጠሩ ጽንሶች አንዱ(15%) በራሱ ጊዜ እንደሚጨናገፍ ያውቃሉ? 👉ሁለትና ከዛ በላይ ጊዜ ፅንስ በራሱ ጊዜ ከተጨናገፈ ሙሉ የሀኪም ምርመራ ማድረግ ያስፈልጋል። ይህ የሚያስፈለገበት ምክንያት መንስኤውን ለማወቅና ቀጣዩ እርግዝና እንዳይጨናገፍ ለመከላከል በማሰብ ነው :: 👉ብዙ ጊዜ ፅንስ በራሱ የሚጨናገፈው እርግዝና በተፈጠረ በመጀመሪያው ሦስት ወራት ውስጥ ሲሆን አንድ አንድ ጊዜ ከወር አበባ ጋር በመመሳሰል ከትንሽ ስጋ መሰል ነገር ጋር ሊወጣ ይችላል። 👉ጥናቶች እንደሚያሳዩት የዚህ ችግር መንስኤ እስከ 60% በህክምና ምርመራ ሲታወቅ 40% በሚሆኑት ሴቶች ላይ ግን መንስኤው በምርመራም ቢሆን አይታወቅም። 👉 በተከታታይ ለሁለትና ከዚያ በላይ ጊዜ ጽንስ በራሱ ጊዜ መቋረጥ ተከታታይ የፅንስ መጨንገፍ ወይም recurrent pregnancy loss ይባላል። 👉 መንስኤዎቹም ከሚከተሉት አንዱ ሊሆን ይችላል :: 1) የዘረመል ችግር(chromosome abnormalities) ለአብዛኛው የጽንስ መጨናገፍ መንስኤ የፅንሱ የዘረመል ችግር ነው። ይህም እንደበጎ የሚታይ ሲሆን ማለትም እንደዚህ የክሮሞዞም ችግር ያለባቸው ልጆች ቢወለዱ በጣም አስቸጋሪ እና ለህይወታቸውም አዳጋች ስለሚሆን ተፈጥሮ በራሱ ጊዜ ችግር መኖሩን ሲያረጋግጥ እንዲወገድ ስለሚያደርግ ነው። 2)የሆርሞን ችግሮች ለምሳሌ ስኳር እና የእንቅርት ችግር(thyroid hormone disorders) 3) የማህፀን ችግሮች ለምሳሌ የማህፀን ዕጢ( myoma) 4)የማህፀን ኢንፌክሽን 5) የወንድ ዘር (sperm)ችግሮች 6) የሴቶች ለሲጋራ አልኮል እንዲሁም ለሌሎች መርዛማ ኬሚካሎች መጋለጥ 👉#ምርመራዎቹስ #ምንድን #ናቸው? ====== የተደጋጋሚ የጽንስ ማቋረጥ ያጋጠማቸው ጥንዶች መንስኤውን ለማወቅ የተለያዩ ምርመራዎችን ማድረግ ያስፈልጋቸዋል ከነዚህ መካከል 1) ሙሉ የሀኪም የአካል ምርመራ (physical examination) 2) የማህፀን ምርመራ :- ብዙ ግዜ የማህፀን ችግሮች በአልትራሳውንድ ይታያሉ፡ 3) የሆርሞን ምርመራዎች ለምሳሌ የስኳር እንዲሁም የዕንቅርት ሆርሞን ምርመራዎች 4) እንዲሁም የፓቶሎጂ ምርመራ ከተጨናገፈው የጽንስ ክፍል ላይ ወይም የእንግዴ ልጅ ላይ ተወስዶ ሚመረመር የጽንስ ምርመራ /ፓቶሎጂ ያስፈልግ ይችላል።በዚህም ምርመራ አብዛኛውን የመጨንገፍ ምክንያት ማወቅ ይቻላል። በተለይም የዘረመል ችግር ካለ በዚህ ምርመራ በቀላሉ ማወቅ ይቻላል። 👉 #የህክምና #አማራጮቹስ ? ====== የህክምና አማራጮቹ እንደየመንስዔው ይለያያሉ። 1) ጤናማ ውፍረት መጠን እንዲኖር ማድረግ፤ ጤናማ አመጋገብ ፤ ሱሶችን ማስወገድ 2) የስኳር ፣ የታይሮይድ ሆርሞን እንዲሁም የፕሮላክቲን ሆርሞን ችግሮች ካሉ እነሱን በመድሃኒት ማስተካከል። 3) የማህፀን ችግር ካለ ለምሳሌ የማህፀን እጢ(myoma) ወይም polyp ካለ በቀዶ ህክምና ማስተካከል ወይም ማውጣት። 👉እንዲሁም ሌሎች የተለያዩ የህክምና አማራጮች ሲኖሩት መንስኤውን ማወቅና ለችግሩ መፍትሄ መፈለግ የጽንስ መቋረጡ እንዳይቀጥል ለማድረግ ያግዛል ። ምንጭ- ጤናዎ በእጅዎ t.me/wanawtena2013
📢 #ስቲች ( Episiotomy ) ======= ✅️በተለምዶ ስቲች የምንለው ፣የብልትን የውጨኛውን ክፍል በመቀስ በመቁረጥ ማስፋት ነው። ✅️ከውጨኛው የብልት ከንፈር ላይ ፣ቀላል ማደንዘዣ በመርፌ በመውጋት ፣ ከፍ ያለ ቁርጠት፣እና መግፋት ሲኖር መቁረጥ ነው። #ለምን #አስፈለገ? 👉በምጥ ሰዐት ለማዋለድ መሳሪያ መጠቀም ሲኖርብን 👉 ፅንስ ኪሎው ከፍ ያለ ሆኖ የበለጠ ጉዳት (tear )ያመጣል ተብሎ ከተገመተ። 👉የፅንስ ልብ ምት ጥሩ ሳይሆን ቀርቶ ቶሎ ለማዋለድ ሲያስፈልግ፣ 👉በመቀመጫው ያለ ፅንስ ፣ 🚫ለሁሉም ሴት አይደረግም ፣ #ከስቲች #ጋር #ተያይዘው #የሚመጡ #ችግሮች #ምንድናቸው? 👉ህመም ፣(pain) ቁጭ ብሎ ማጥባትእስኪያቅትሽ ድረስ ህመም ሊኖርሽ ይችላል። 👉የቁስሉ መብገን(ኢንፌክሽን) 👉በግብረስጋ ግኑኝነት ጊዜ ህመም ፣(Dyspareunia) 👉ሽንትን መቆጣጠር አለመቻል ፣ 👉ሰገራን መቆጣጠር አለመቻል ፣ 👉ቶሎ ላይድን ይችላል። 👉ከ ታቀደው ከፍ ያለ መጠን ያለው ስቲች ( ይህ ሲሆን የፊንጢጣ ጡንቻ ጉዳት በተለያየ መጠን ይከሰታል ) #ስቲች #እንዴት #ይድናል? 👉ስቲች ለመዳን ከ ስድስት እስከ ስምንት ሳምንት ይፈልጋል (6-8 ሳምንት ) ✳️አሁን በብዛት ለመስፋት የምንጠቀመው ክር በራሱ ከሰውነት ጋር ይዋኻዳል ፣ 👉ማስታገሻ መድኃኒት መውሰድ ። 👉በመጀምሪያዎቹ ቀናት እብጠቱን ለመቀነስ በረዶ ማድረግ (perineal cold pack ): 👉የሰገራ ድርቀት እንዳይኖር መጠንቀቅ ( ይህ አንድ በ እርግዝና ጊዜ ይባባሳል ፣ከወሊድ በኻላምይቀጥላል )እንዳይኖር 👉አመጋገብን ማስተካከል ፣ 👉ውሃ መጠጣት፣ 👉አንዳንድ የ ሰገራ ማለስለሻ መድኃኒቶችን መጠቀም ። 👉ቁስሉን በ ቀን አራት ጊዜ በ ንፁህ ውሃ መዘፍዘፍ (መታጠብ አደለም ) #ግኑኝነት #መች #ነው #ማድረግ #የሚቻለው? ❤️ቁስሉ ከዳነ ከወር ካስራአምስት ቀን ጀምሮ ይቻላል:: #ማስተዋል #ያለብሽ!!! ✍ለጥቂት ወራት ህመም ይኖርሻል ፣ ✍በተጨማሪም ስለምታጠቢ የብልት መድረቅ ሊኖርሽ ይችላል ። ይሄንን ከግምት በማስገባት በግኑኝነት ጊዜ ማለስለሻ መጠቀም ጥሩ ነው።❤️❤️ #ከስቲች #ጋር #በተያያዘ #ህክምና #መቼ #መሄድ #አለብኝ? 👉ህመሙ እይባሰ ሲሄድ ፣ 👉መጥፎ ጠረን ያለው ፈሳሽ ከ ቁስሉ ሲወጣ 👉መግል ከቁስሉ ሲወጣ ፣ 👉ቁስሉ ከደማ፣ 👉ቁስሉ እያበጠ ሲመጣ ፣ 👉ትኩሳት ፣ብርድ ብርድ ማለት ሲኖርሽ፣ 👉ሰገራ መቆጣጠር ካቃተሽ 💜💜በስቲች ከወለድሽ ከወራት በኃላም ህመም( በግኑኝነት ጊዜ ፣) ይኖራል ፣ ይህ ከሆነ ሀኪምሽ ጋር መሄድ ፣ እናም በማማከር የተለያዩ መፍትሔዎችን መፈለግ ። #በቅንነት#ሸር #አድርገው #ለሌሎችም #ያድርሱ፡፡ ምንጭ #ጤናዎ በእጅዎ
ይህ ችግር 'ዛንቴላስማ-xanthelasma' ይባላል። የኮሌስትሮል መብዛት ምልክት ነው። 📞09-70-96-96-96
ይህ ጋንግሪን ይባላል። ይህ ችግር የገጠመው በፍጥነት ሀኪም ማማከር ይገበዋል። 09 70 96 96 96 ደውለው ቀጠሮ ማስያዝ ይችላሉ።
без подписи
без подписи