- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 52
- 1/48двое суток
- 59
- 1/72трое суток
- 64
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
https://youtube.com/shorts/DZ5g_9Ms_CQ?feature=share
https://youtube.com/shorts/4zRVBN89uA0?feature=share
ከፍተኛ ኮሌስትሮል ምልክት ላያሳይ ይችላል፤ ጉዳቱ ግን ከባድ ነው። 🫀 ልብዎን ለመጠበቅ፦ ✅ የደም ቅባትዎን ይመርምሩ ✅ ጤናማና በፋይበር የበለጸገ ምግብ ይመገቡ ✅ የአካል እንቅስቃሴ ያድርጉ ✅ ሲጋራ አያጨሱ ✅ የታዘዘልዎን መድኃኒት በአግባቡ ይውሰዱ የደም ቅባትዎን ይወቁ፤ ልብዎን ይጠብቁ! #የደም_ቅባት #ኮሌስትሮል #የልብ_ጤና #ጤናማ_አኗኗር #ጤና_ትምህርት #DrOumerAbdu
https://youtube.com/shorts/PNGF7B_lXiE?feature=share
https://youtube.com/shorts/OIt1O2pWVaE?feature=share
https://youtube.com/shorts/0egRbN8rc8o?feature=share
https://youtube.com/shorts/D3sF7PODl6E?feature=share
https://youtu.be/OlY7hTrHGa0
t.me/wanawtena2013
https://www.facebook.com/share/r/1FyfcJHReJ/
https://youtu.be/DGFGD-D6ORo
https://youtu.be/xe4cDG4SyqU?si=v6QkDRjdbZckrbbP
©ሆድ ድርቀት መቼ ነው አሳሳቢ የሚሆነው? 👉ሆድ ድርቀት (Constipation) ማለት ሰገራ በሳምንት ከ3 ጊዜ በታች መውጣት፣ ወይም ጠንካራ ሰገራ(hard Stool) በግፊት መውጣት ነው። 👉ምክንያቶቹ ብዙ ሊሆኑ ይችላሉ። 1. የአኗኗር ምክንያቶች:በጣም የተለመዱ መንስኤዎች፡ •በቂ ውሃ አለመጠጣት •የፋይበር እጥረት ( በቂ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ሙሉ እህል ዘሮች አለመውሰድ) •የአካላዊ እንቅስቃሴ ማነስ •ተፈጥሯዊ የመፅዳዳት ፍላጎትን ማዘግየት 2. መድሃኒቶች •የብረት (Iron) ክኒኖች •ኦፒዮይድ የህመም ማስታገሻዎች •አንዳንድ የደም ግፊት መድሃኒቶች (ለምሳሌ calcium Chanel Blockers) •አንዳንድ ፀረ-ድብርት እና ፀረ-አለርጂ መድሃኒቶች 3. የህክምና ሁኔታዎች • የእንቅርት ሆርሞን ችግር (Hypothyroidism) •የስኳር ህመም (Diabetes mellitus) •ከፍተኛ የደም ካልሲየም (hypercalcemia) •የነርቭ በሽታዎች (ለምሳሌ Parkinson disease) •እርግዝና 4. የአንጀት ችግሮች •የአንጀት መታወክ(Irritable bowel syndrome (IBS-C)) •የአንጀት መዘጋት(Bowel Obstruction) •የትልቅ አንጀት ካንሰር (በተለይ አዲስ የጀመረ ድርቀት ከሆነ) 5. ሌሎች •ዕድሜ መጨመር •የጭንቀት እና የጭንቀት ስሜት °ከረጅም ጊዜ የlaxative መድሃኒት መጠቀም 👉*መቼ ወዲያውኑ ሐኪም ማየት ያስፈልጋል?* •በሰገራ ውስጥ ደም ካለ •ከባድ የሆድ ህመም ወይም ሆድ መነፋት •ማስታወክ ካለ •ያልተጠበቀ ክብደት መቀነስ •ከ50 ዓመት በኋላ በድንገት የጀመረ የሆድ ድርቀት •ሰገራ ወይም ጋዝ ፈጽሞ ካልወጣ ©Dr.Kifle Alamirew, Internist
የደም ግፊት Hypertension (HTN) ____ 👉የደም ግፊት (Hypertension) ምንድን ነው? የደም ግፊት (Hypertension) ማለት ደም በደም ሥሮች ግድግዳ ላይ የሚፈጥረው ግፊት ለረጅም ጊዜ ከመደበኛው በላይ ሆኖ ሲቆይ ነው። በዓለም ላይ ከ3 አዋቂዎች 1ዱ የደም ግፊት አለበት፤ ብዙዎች እንዳለባቸው እንኳን አያውቁም። 👉ለደም ግፊት አጋላጭ ሁኔታዎች ▪ከመጠን በላይ ጨው መመገብ ▪የፍራፍሬና አትክልት አመጋገብ ዝቅተኛ መሆን ▪የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማነስ ▪ከመጠን ያለፈ ውፍረት ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ተጋላጭ ሲሆኑ ወንድ ዕድሜ ከ55 በላይ፣ ሴት ዕድሜ ከ65 በከፍተኛ ተጋላጭ ናቸው። 👉የደም ግፊት ምልክቶች ብዙ ሰዎች በመጀመሪያ ደረጃ ምልክቶችን ላያስተውሉ ይችላሉ። ስለዚህ “ዝምተኛ ገዳይ” ተብሎ ይጠራል። ▪የተለመዱ ምልክቶች፦ ራስ ምታት፣ ማዞር፣ የዓይን ብዥታ፣ የትንፋሽ ማጠር፣ የደረት ህመም፣ የልብ ምት መጨመር፣ ድካም፣ አንዳንድ ጊዜ ከአፍንጫ ደም መፍሰስ፤ ▪ከፍተኛ የደም ግፊት ምልክቶች፦ ከባድ ራስ ምታት፣ ግራ መጋባት፣ ለመተንፈስ መቸገር፣ ከባድ የደረት ህመም፤ 👉የደም ግፊት ምርመራ የደም ግፊት በዋናነት ምርመራ የሚደረገው የደም ግፊት በመለካት ነው። ▪መደበኛ፦ ከ120/80 mmHg በታች ▪ከፍ ያለ፦ 120–139 / 80-89 ▪ደረጃ 1 የደም ግፊት፦ 140–159 / 90–99 ▪ደረጃ 2 የደም ግፊት፦>160/>100 mmHg ▪ሌሎች ምርመራዎች፦ የደም ምርመራ፣ የሽንት ምርመራ፣ ECG/EKG፣ የኩላሊት ሥራ ምርመራ፣ የዓይን ምርመራ፤ 👉የደም ግፊት የሚያስከትለው ጉዳት በጊዜ ያልታከመ የደም ግፊት ብዙ የሰውነት አካላትን ሊጎዳና ውስብስብ የጤና እክሎችን ያስከትላል። የልብ ችግር፣ የልብ ድካም፣ የልብ ድንገተኛ ህመም፣ የልብ መጠን መጨመር፣ የአንጎል ችግሮች፣ ስትሮክ፣ የኩላሊት ሥራ መቋረጥ፣ የእይታ ችግር፣ አኑሪዝም (Aneurysm)። 👉መከላከያ መንገድ ▪የጨው መጠን መቀነስ ▪መደበኛ የአካል እንቅስቃሴ ማድረግ ▪ጤናማ ክብደት መጠበቅ ▪ሲጋራ ማቆም፣ አልኮል መቀነስ ▪ውጥረት/ጭንቀት መቀነስ ▪መድሀኒቶችን በሐኪም ትዕዛዝ መሠረት ብቻ መውሰድ 👉ከመድሀኒት ወጪ መቆጣጠሪያ መንገዶች 1. አመጋገብ (Diet) ጤናማ አመጋገብ የደም ግፊትን ለመቆጣጠር ይረዳል። የሚመከሩ ምግቦች፦ ▪ፍራፍሬና አትክልቶች (ሙዝ፣ ፖም፣ ብርቱካን፣ ማንጎ) ▪ያልተፈተጉ እህሎች (Whole grains) ▪ለውዝ፣ ዝቅተኛ ስብ ያላቸው የወተት ተዋጽኦዎች፣ ዓሳና ዶሮ ▪ጤናማ ዘይቶች (የወይራ ዘይት፣ የአኩሪ አተር ዘይት፣ የበቆሎ ዘይት፣ የሱፍ አበባ ዘይት) በትንሽ መጠን (በቀን ከ2 ማንኪያ በታች) 2. በፖታስየም የበለፀገ ምግብ ፖታስየም ያላቸው ምግቦች የደም ግፊትን ለመቀነስ ይረዳሉ። ፖታስየም የጨው (sodium) ተጽእኖን ይቀንሳል። ፖታስየም ያላቸው ምግቦች፦ ሙዝ፣ አቮካዶ፣ ስፒናች፣ ባቄላ፣ ብርቱካን፣ ድንች 3. ውጥረት/ጭንቀት መቀነስ (Stress Reduction) ረጅም ጊዜ የሚቆይ ውጥረት/ጭንቀት መቆጣጠር የደም ግፊትን ለመቀነስ ያግዛል፣ እንዲሁም ጤናማ የአኗኗር ለውጦችንና መድሀኒቶችን በትክክል መከተልን ያነሳሳል። ውጥረትን/ጭንቀትን ለመቀነስ የሚረዱ መንገዶች፦ በቂ እንቅልፍ ማግኘት (በሌሊት 7–9 ሰዓት)፣ ራስን ማረጋጋት፤ እነዚህ የአኗኗር ለውጦች እንደ ስትሮክ፣ የልብ ድካም፣ የኩላሊት በሽታ እና የዓይን ችግሮች ያሉ ውስብስቦችን ለመከላከል ጠቃሚ ናቸው። ምንጭ: የጤና ሚኒስቴር ገፅ
ፊስቱላ ምንድን ነው? ፊስቱላ ማለት የሁለት የተለያዩ ቱቦዎች ወይም የሁለት የተለያዩ የአካል ክፍሎች ከትክክለኛው ተፈጥሮ ውጭ መገናኘት ነው፡፡ ምሳሌ፡ -የምግብ መውረጃ ጉሮሮ እና የአየር መተንፈሻ ቱቦ መገናኘት (Tracheo-esophageal fistula) -የሽንት ቱቦና የማህፀን መገናኘት (Urogenital fistula) -የአንጀትና የቆዳ መገናኘት (Entero-cutaneous fistula) -የፊንጢጣና የቆዳ መገናኘት (Perianal fistula) -እና ወዘተርፈ እነዚህ ፊስቱላዎች በአፈጣጠር ችግር አብረው የሚፈጠሩ ወይም ከውልደት በኋላ በተለያዩ ምክንያቶች የሚከሰቱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ አብረው ከሚፈጠሩት መካከል የምግብ መውረጃ ጉሮሮና የአየር መተንፈሻ ቱቦ መገናኘትየተለመደ ሲሆን በፊንጢጣና በሽንት ቱቦ አከባቢም ሊከሰት ይችላል፡፡ ከውልደት በኋላ ከሚከሰቱ ፊስቱላዎች በብዙዎች ዘንድ የሚታየው የፊንጢጣ አከባቢ ፊስቱላ ነው፡፡ ይህ ፊስቱላ አብዛኛውን ጊዜ በኢንፌክሽን ምክንያት የሚመጣ ሲሆን ፊንጢጣ ዙሪያው ካለው ቆዳ ጋር የሚያገናኝ መስመር በመፍጠር ይከሰታል፡፡ ምልክቶች፡ - ፈሳሽ (ጠረን ያለው) - ህመም - እብጠት (መጠነኛ) - በእጅ የሚዳሰስ መስመር ዓይነቶች፡ የፊንጢጣ ዙሪያ ፊስቱላ በብዙ መንገድ ሊከፋፈል የሚችል ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ - ከፍ ያለ (high fistula) - ዝቅ ያለ (low fistula) ተብሎ በሁለት ይከፈላል፡፡ ምርመራ፡ አብዛኛውን ጊዜ በአካላዊ ምርመራ ሊለይ ይችላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ግን (በተለይ ከፍ ያለ ዓይነት ሲሆን) ኤምአርአይ (MRI) ምርመራ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ህክምና፡ ፊስቱላ በቀዶ ህክምና የሚታከምና የሚድን ሲሆን የቀዶ ህክምና ዓይነቱ እንደፊስቱላው ዓይነት ይለያያል፡፡ ስለነዚህና የመሳሰሉ ችግሮች ህክምናና የምክር አገልግሎት በሰንላይት ክሊኒክ ያገኛሉ፡፡ አድራሻ፡ እንጅባራ ቅዱስ ሚካኤል ህንፃ 0937044711 በማበራዊ ሚድያ አማራጮች Facebook Telegram_channel Tiktok ያግኙን፡፡
እነዚህ የደም ግፊት (Hypertension) ላለባቸው ታካሚዎች አምስት ዋና ዋና ምክሮች ናቸው፦ 1. የጨው አጠቃቀምን መቀነስ በምግብ ውስጥ ያለውን የጨው መጠን በቀን ከአንድ የሻይ ማንኪያ በታች ማድረግ። የታሸጉ እና የተቀነባበሩ ምግቦችን ማስወገድ። 2. የDASH አመጋገብን መከተል ፍራፍሬዎችን፣ አትክልቶችን፣ ጥራጥሬዎችን እና ዝቅተኛ ቅባት ያላቸውን የወተት ተዋጽኦዎችን በብዛት መመገብ። 3. የማያቋርጥ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሳምንት ቢያንስ ለአምስት ቀናት በቀን ለ30 ደቂቃ ያህል የልብ ምትን የሚጨምሩ እንቅስቃሴዎችን (እንደ ፈጣን እርምጃ) ማድረግ። 4. ክብደትን መቆጣጠር ከመጠን ያለፈ ውፍረትን መቀነስ የደም ግፊትን በከፍተኛ ሁኔታ ዝቅ ለማድረግ ይረዳል። 5. መድሃኒትን በአግባቡ መውሰድ ምንም አይነት የህመም ስሜት ባይኖርዎትም እንኳን፣ የታዘዙልዎትን መድሃኒቶች ሳይዘነጉ በየቀኑ በሰዓቱ መውሰድ። ማሳሰቢያ: እነዚህን ምክሮች ከተከታታይ የጤና ባለሙያ ክትትል ጋር ማጣመር ይገባል። t.me/wanawtena2013
🖐️ ALLEN’S TEST 🔍 Purpose Assess blood flow to the hand via radial & ulnar arteries --- ⚙️ Procedure 1. Patient clenches fist 2. Occlude both arteries 3. Patient opens hand (pale) 4. Release one artery 5. Observe color return --- ✅ Interpretation - Normal: Color returns ≤ 5–7 sec - Abnormal: Delayed / no color return --- 📌 Indications - Before radial artery puncture (ABG) - Before arterial line insertion - Before radial artery harvesting (CABG) - Assess hand circulation / ischemia --- 💡 Note Simple bedside test; confirm with Doppler if needed t.me/wanawtena2013
https://t.me/DrOumarOnlineBot 👨⚕️ *Dr. Oumar Online* — 24/7 ነፃ የጤና ምክር! ✅ ያልተወሰነ ጥያቄ በአማርኛ / English / Oromifaa / Tigrinya ✅ የምስል ትንታኔ (Lab, X-ray, ቆዳ, መድኃኒት ፎቶ) ✅ ሙሉ የመድኃኒት ሕክምና 👇 ጀምር፦ @DrOumarOnlineBot
የወንድ ልጆች የዘር ፍሬ በሆዳቸው ውስጥ ሊቀር እንደሚችል ያውቃሉ? አዎ ይህ የወንድ የዘር ፍሬ አለመውረድ (Undescended Testes ) ይባላል፡፡ የወንድ ልጆች የዘር ፍሬ አፈጣጠሩ የሚጀምረው ከፍ ብሎ ከኩላሊት አከባቢ ሲሆን በፅንስ እድገት ወቅት ወደ ታች እየወረደ ልጆች ሲወለዱ በትክክለኛ ቦታው ይደርሳል፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ የዘር ፍሬ ሳይወርድ በማንኛውም ቦታ ላይ ሊቀር ይችላል፡፡ ይህም ሁኔታ ልጆች ከተወለዱ እስከ 3 ወራቸው ድረስ የዘር ፍሬያቸው በትክክለኛ ቦታው ባለመገኘት ይለያል፡፡ በተለይ ልጆች ከ3 ወር እድሜያቸው በኋላ የዘር ፍሬያቸውን በመዳሰስ መለየት ይቻላል፡፡ ይህ ችግር በሁለቱም ወይም ባንዱ የዘር ፍሬ ላይ ሊከሰት ይችላል፡፡ ምን ችግር ያመጣል? 1. መካንነት፡ የወንድ የዘር ፍሬ ከሰውነታች ሙቀት 2ዲግሪ ባነሰ አከባቢ ላይ ይኖራል፡፡ በሆድ ውስጥ ወይም በመንገድ ላይ ሲቀር ደግሞ በሰውነታችን ሙቀት ጉዳት ይደርስበታል፡፡ በዚህም የተነሳ ለመካንነት ያጋልጣል፡፡ 2. የዘር ፍሬ ካንሰር፡ ወደ ታች ያልወረደ የዘር ፍሬ ከወረደ ፍሬ የበለጠ ለካንሰር ተጋላጭ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ችግሩ ሲከሰት በፍጥነት ስለማይለይ ለበለጠ ጉዳት ሊዳርግ ይችላል፡፡ ህክምና፡ ይህ ችግር በቀዶ ህክምና ሊስተካከል የሚችል ነው፡፡ መቼ? ይህ ችግር ሲከሰት ልጆች ከተወለዱ ከ6ወር እስከ 1 ዓመታቸው ሊስተካከል ይገባል፡፡ በቆየ ቁጥር የዘር ፍሬው ጉዳት ከፍ ስለሚል ተሰርቶም ጉዳቱ ላይመለስ ስለሚች ቶሎ ማሰራት ይመከራል፡፡ ምንጭ- ሰንላይት ክሊኒክ አድራሻ፡ እንጅባራ ቅዱስ ሚካኤል ህንፃ//0937044711 t.me/wanawtena2013
ሃይፖስፓዲያ Hypospadia ሃይፖስፓዲያ (Hypospadia) - ማለት የወንድ ልጆች የሽንት መሽኛ ጫፍ (urethral meatus) ከተለመደው ቦታ ማለትም ከብልት ጫፍ ወረድ ብሎ በታች በኩል ሲገኝ የሚሰጥ ስያሜ ነው፡፡ ይህም የሽንት ቱቦ (urethra) በሚመጣበት መንገድ ሁሉ ሊከሰት ይችላል፡፡ የወንድ ልጅ ብልት አፈጣጠር ችግሮች መካከል አንዱ የሆነው ሃይፖስፓዲያ (Hypospadia) ከ300 ወንድ ልጆች ባንዱ ሊከሰት የሚችል የአፈጣጠር ችግር ነው፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ሊከሰት የሚችል ሲሆን ከእነዚህም መካከል በእርግዝና ጊዜ የሚወሰዱ መድሃኒቶችና በዘር የሚተላለፉ ችግሮች ዋናዎቹ ናቸው፡፡ ዓይነቶች፡ ታችኛው (Distal)- ወደብልት ጫፍ የተጠጉ ክፍተቶችን የሚያላክት ሲሆን ላይኛው (Proximal) - ደግሞ ከብልት ጫፍ ከፍ ብለው የሚከሰቱ እና ከባድ ተብለው የተለዩ የሃይፖስፓዲያ አይነት ናቸው፡፡ ምልክቶች፡ 1. የሽንት ቱቦ ጫፍ በቦታው አለመገኘት 2. የብልት ወደፊት መጣመም (በተለይ ሲቆም) 3. የሸለፈት መደራራብ አንዳንዴም የተገረዘ መምሰል 4. ሽንት ሲሸኑ እዛው በቅርበት መፍሰስ (ቀጥ ብሎ አለመሸናት) ባይታከም ምን ሊያስከትል ይችላል? 1. ሽንት ሲሸና በቅርበት በማፍሰስ ለንፅህናና ለራስ መተማመን ችግር መፍጠር 2. በግብረ ስጋ ግንኙነት ላይ ችር መፍጠር 3. የመካንነት ችግር ህክምና ሃይፖስፓዲያ በህክምና መስተካከል የሚችል የተፈጥሮ ችግር ሲሆን እንደየዓይነቱ በአንድ ወይም በሁለት ዙር በሚደረግ ቀዶ ህክምና ይስተካከላል፡፡ እንዲህ ዓይነት ምልክት ያላቸው ህፃናት ቀዶ ህክምናው ሳይሰራ መገረዝ የለባቸውም፡፡ ገጠመኝ፡ ከአመታት በፊት ነበር አንድ 40ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የሚገኝ ጎልማሳ ወደ ቢሮዬ መጥቶ ችግሩን ያወራኝ፡፡ ችግሩ የአፈጣጠር ችግር ሲሆን ታችኛው ሃይፖስፓዲያ ( Distal Hypospadia) ሲሆን ልጆችን ወልዶ በትዳር የሚኖር ቢሆንም ሽንት ሲሸና በቅርበት በመፍሰሱ ምክንያት ከማህበረሰቡ ጋር ለመኖር እንቅፋት እደሆነበት በተለይ ደግሞ ሰብሰብ ተብሎ በማህበር በሚጠጣበት ቦታ ላይ እንደሚቸገር ገልፆ መፍትሄ እንዳለው ጠየቀን፡፡ እኛም ተደጋጋሚ ቀዶ ህክምና ሊያስፈልግ ስለሚችል ብዙ ገንዘብ ሊጠይቅ ከመቻሉ ውጭ ሊስተካከል እንደሚችል ነገርነው፡፡ እሱም በሬዎች አሉኝ ሽጬ ልምጣ ብቻ ይስተካከልልኝ ብሎን ሄደ፡፡ እንዳለውም ተመልሶ መጣ፡፡ ባንድ ዙር ቀዶ ህክምናም ሊስተካከል ቻለ፡፡ በቀጠሮ ሲመጣ ከደስታው ብዛት የተነሳ በጓሮው የበቀለውን ዓይነት ሁሉ እሸት (በቆሎ ፣ ቃሪያ ፣ ዱባ…..) ይዞልን መጣ፡፡ ስለነዚህና የመሳሰሉ ችግሮች ህክምናና የምክር አገልግሎት በሰንላይት ክሊኒክ ያገኛሉ፡፡ አድራሻ፡ እንጅባራ ቅዱስ ሚካኤል ህንፃ//0937044711 በማበራዊ ሚድያ አማራጮች Facebook Telegram_channel Tiktok ያግኙን፡፡