tgindex
አማራ/ፋኖ

አማራ/ፋኖ

Статистика

እንኳን ወደ አማራ/ፋኖ ቻናል መጡ! ይህ የአማራን ተጋድሎ ለማጠናከር እና አንድነታችንን ለማጎልበት የህዝባችንን ሰላም ለማስጠበቅ ነፃነትን ለማወጅ ወቅታዊ መረጃዎችን የምናቀርብበት የአማራ/ፋኖ ቻናል ነው። አማራ የሆንክ ሁሉ join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በፍጥነት ማግኘት ይቻላሉ። ድል ለአማራ! አማራነት ወይም ሞት!

Последний пост
1 авг.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
20
Тип
открытый
Язык
ti
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
765
0 за 2 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 918
20 постов
Вовлечённость
250,7%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 20
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
204
1/48двое суток
233
1/72трое суток
252

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • የጠላት ሀይል ከባሽ ተነስተው ወደ ይፋት አቅጣጫ በሦስት መስመር የመውረር ሙከራ ያደረገ ሲሆን፦ ➛ከባሽ በንፋስ አምባ በኩል ወደ ዘከሬ ተራራ፣ ➛ከባሽ ቀጥታ ወደ ቀወት መስመር፣ ➛ከባሽ ወደ ቆሎማያ አቅጣጫ በሦስቱም አቅጣጫዎች የተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ወደፊት ለመግፋትም ሆነ ወደኋላ ለመመለስ በማይችልበት ደረጃ በአፋብን ሸ/ጠ/ግ/አ/ዕዝ መሀመድ ቢሆነኝ ኮር ደጃዝማች ተሰማ እርገጤ እና አስቻለው ደሴ ክፋለጦር ከበባ ውስጥ ይገኛል። ተጨማሪ ኃይል (ከሸዋሮቢት፣ ከሞላሌ እና ከመሐል ሜዳ)  ቢጠይቅም፣ በወገን ሀይል ከበባ ውስጥ የሚገኘትን ደፈጣዎችና ከበባዎች ለማለፋ የተቸገረው ሀይል የደገፈውና የመጣለት ኃይል እደሌለ ተረጋግጧል። የባሽ ከተማ ሙሉ በሙሉ በደጃዝማች ተሰማ እርገጤ በክፍለ ጦሩ ቁጥጥር ስር የዋለች ሲሆን፤ በዚህ ውጊያ ላይ የባሽ ክላስተር እና የተሬ ክላስተር አባት አርበኞች ጦር ከፍተኛ ታሪክ እየሠሩ ይገኛሉ ሁለት የጠላት ኃይልን እስከወዲያኛው እዳሰናበቱ ተረጋግጧል። በሌላ እቅጣጫ ከመዘዞ አቅጣጫ የተቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ከመዘዞ ተነስቶ በአያበር ቀበሌ በኩል ወደ መንግስት ለመሸጋገር ሲንቀሳቀስ  በአካባቢው በሚገኘው አስቻለው ደሴ ክፍለ ጦር ቅጽበታዊ እርምጃ ተወስዶበት ከበባ ውስጥ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት መሶቢት በተባለ ቦታ ተራራ ላይ ተሰቅሎ የሚገኝ ሲሆን፣ ተጨማሪ ደጋፊ ኃይል ቢጠይቅም የሚደርስለት በማጣቱ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ ይገኛል። በተያያዘ ዜና ከአጣዬና አላላ ተነስቶ በሁለት አቅጣጫ ማለትም የአጣየው በከሰያት ወደ ደረትማ እዲሁም የአላላው በብርቂቶ ወደ ደረትማ  የተንቀሳቀሰውን ዘራፊ ጥምር ቡድን ጀግናው 7/ለ70 ክፍለጦር እዳመጣጡ እያሳደዱት ሲሆን መሸሽ ያልቻለው በየጉረኖው ተደፍቶ ቀርቷል። በዚሕም ጠላት የሞቱትን ትቶ የቆሰሉት ወደ አጣዬ ወስዶ በማሳከም ላይ ይገኛል። ክብር ለትግሉ ሠማዕታት ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ©የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!!

  • 11 апр.1 0233

    እንኳን ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት መታሰቢያ በዓል በሰላም አደረሰን። ፍቅር አሸንፎ የተሰቀለበት፣ ሞት ተሸንፎ ሕይወት የተገኘበት ይህ ዕለት፤ በቤታችሁ ሠላምን፣ በልባችሁ ፍቅርን፣ በኑሯችሁ ደግሞ የተትረፈረፈ በረከትን ይክፈታችሁ።በረከቱ ከሁላችን ጋር ይሁን። ‎ ‎..... ቃሉ ተፈፀመ ... ከጥል ሊያወጣን፤ ካለንበት ኀጢያት፤ ከሲኦል ጎዳና፣ የአዳም ፍቅር ስቦት፤ ከሰማይ ወረደ፤ መጣ በደመና፣ የምስጢር ባለቤት፤ ጥበብ አስተማሪ፣ የአለም ሁሉ ጌታ፣ በገመድ ጎተቱት፤ በጂራፍ ገረፉት፣ በችንካር ተመታ፣ መከራ አፀኑበት፤ ጉኑን በጦር ወግተው፤ አፈሰሱት ደሙን፤ ቃሉም ተፈፀመ፤ ለአዳም የገበለት፤ የሰጠው ቃል ኪዳን፣ ሲፈረድባቸው፤ ከገነት ሲወጡ፤ አዳም እና ሔዋን። መልካም በዓል!

  • 🔥ወጣቱ ሁለት የአገዛዙ ወታደሮችን አንገት አንቆ ባህር ውስጥ በመስጠም የአጥፍቶ ጠፊ እርምጃ ወሰደ‼️ ዮናስ ክንፈ ይባላል። ገና የ24 አመት ወጣት ነበር። ተወልዶ ያደገው አንጎት ወረዳ 01 ቀበሌ ውስጥ ነው። በዚህ ወረዳ ከዚህ ቀደም የወረዳው የሚኒሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊ በፋኖ መገደሉ ይታወቃል። ከሚኒሻው ግድያ ጋር ተያይዞ ዮናስ ክንፈን የአገዛዙ ወታደሮች ከቤቱ አፍነው በመውሰድ ያሰቃዩታል። ለአንድ ወር ሲያሰቃዩት ከርመው ምንም አይነት የወንጀል ፍንጭ ሲያጡበት ከአንድ ወር እገታ በኋላ ተለቆ ወደ ትውልድ ቀየው ተመለሰ። ፀረ አማራው ኃይል፡ ዮናስን"መልክህ አላማረንም" በሚል ሰበብ እንደገና የክፋትና የስቃይ መረቡን ያጠምድበታል። ዮናስ የአረመኔዎችን እንቅስቃሴ ተመልክቶ አካባቢውን ለቆ ተሰወረ። ሌላ ቦታም የቀን ስራም ቢሆን እየሰራ ለመኖር የትውልድ ቀየውን ለቆ ተሰደደ። ዮናስ ሀገር ለቆ መሰደዱን የሰማው የብልፅግና ኃይል፡ የዮናስን አባት ከመኖሪያ ቤታቸው ሂዶ በማፈን ለእስር ይዳርጓቸዋል። ዮናስ የአባቱን በአረመኔዎች እጅ መውደቃቸውን ሲሰማ እራሱን በአባቱ የስቃይ ቦታ ላይ ለማድረግ ወስኖ ወደ አረመኔው የአገዛዙ ሰራዊት መጥቶ እጅ ሰጠ። የፋሽስቱ ዐብይ አህመድ ገዳይ ወታደሮች ዮናስን እደተራበ ጅብ እያፋሸጉ ተቀበሉት። ዮናስን ልብሱን አስወልቀው እርቃኑን አቁመው ለመስማት የሚሰቀጥጥ፡ ለማየት የሚዘገንን ግፍ ፈፀሙበት። እጆቹን የፍጥኝ ወደኋላ አመሰቃቅለው 8 ቁጥር እስር ካሰሩት በኋላ በገላው ላይ በእሳት የሚነድ ላስቲክ  አንጠባጠቡበት። በላስቲኩ የእሳት ጠብታ ተቃጥሎ ስጋው ቀልጦ አጥንቶቹ ጠቁረው እስኪታይ ድረስ እጅግ ከባድ ግፍ ፈፀሙበት። በመጨረሻም ዮናስ፡ ከዚህ ስቃይ ይገላገል ዘንድ ጨፍጫፊዎቹን "የደበቅኩት መሣሪያ አለኝ እሱን ልስጣችሁ ወደ ደበቅኩበት ቦታ ውሰዱኝ" ይላቸዋል። ደብዳቢዎቹም ለአለቃቸው ሂደው ይነግሩታል። "ጥሩ መሳሪያውን አምጡት ይሄማ ጥሩ ብር ነው። ሽጠን ወደ ኪሳችን እናደርጋለን። ከዚህ ጦርነትኮ ያለን ትርፍ ገንዘብ ነው።ሰለዚህ ከደበቀበት ቦታ ያሳያችሁና መሣሪያውን አምጡ" የሚል መልክት ሲሰጣቸው ዮናስን በላስቲክ የተቃጠለ አካላቱን ልብስ አልብሰውና ሸፍነው መሳሪያውን ከቀበረበት ቦታ እንዲወስዳቸው አደረጉት። ዮናስ አንድ ውሳኔ በልቡ ወስኗል። በጋዞ ከሚገኝ እግድ ባህር ከሚባል ቦታ ላይ እንደደረሱ መንገዳቸው በባህሩ ዳርቻ ነበር። ዮናስ፡ ከተከተሉት ሶስት የመከላከያ ሰራዊት አባላት መካከል የሁለቱን ወታደሮች አንገት አንቆ በመያዝ ወደ ጥልቁ ባህር ይዟቸው ሰጠመ። ዮናስ ገዳዮቹን ገሎ ራሱን ከስቃይ ታድጎ የፀጋ፣ የክብር፣ የጀግና ሞትን ሞተ። ሦስተኛው የመከላከያ ሰራዊት አባል፡ ዮናስ ሁለቱ ጓዶችህን ባህር ገፍትሯቸው እሱም ሲገባ አንተ ምን አየሰራህ ነበር በሚል ትጥቅ እንዲያወርድ ተደርጎ ተረሽኗል። የሁለቱ መከላከያ ሰራዊት አባላት አስከሬን እና የዮናስ ክንፍ አስከሬን ከሰጠሙበት ባህር በስምንተኛው ቀን ተንሳፎ ታየ። የአገዛዙ ወታደሮች የራሳቸውን አስከሬን ከባህሩ አውጥተው ከቀበሩ በኋላ የዮናስን አስከሬን አናስወጣም በሚል የከለከሉ ቢሆንም፡ የአከባቢው ማሕበረሰብ "ከዚህ በላይ ምን ልታደርጉት ነው?" በሚል ቁጣና እቢተኝነት የዮናስን አ*ስ*ከ*ሬን ከባህሩ አውጥተው  ተወልዶ ባደገባት መንደር የጀግና ስርዓተ ቀብር ፈፀሙለት። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል! ©በአፋብኃ ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ የደጋው መብረቅ ኮር ሕዝብ ግንኙነት ክፍል! #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 21/ዐ3/2018 ዓ.ም

  • ከራስ አርበኛ ዘመነ ካሴ የተላለፈ የትግል ጥሪ ‼️ ⛔️ጤና ይስጥልኝ!!! ሰውም ኢትዮጵያዊም ያልሆነውን ጭራቅ ከህዝባችንና ከሀገራችን አናት ላይ አንስተን ማንነታችንን አክብረን እና አስከብረን የምንኖርበትን ስርአት ለመገንባት በጋራ እንነሳ!!!! የአማራ ህዘብ በተፈፀመበት እና አሁንም እየተፈፀመበት ባለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ምክንያት እራሱን ለማዳን እያደረገ ባለው ተጋድሎ አኩሪ ድሎችን ተጎናፅፏል። ሊያጠፉት እስከ አፍንጫቸው ታጥቀው የመጡትን ጠላቶቹን በታላቅ ወኔ እና ጀግንነት እየተፋለመ በያሉበት እየደመሰሰ፣ እራሱን እያደራጀ፣ ከጠላት የማረከውን እየታጠቀ ህልውናውን ለማስከበርና የወዲፊቱን የኢትዮጵያ ሁኔታ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ ጋር በመተባበር በጋራ ለመወሰን ትግሉን አጠናክሮ ቀጥሏል። እኛ አማራዎች በእያንዳንዱ ቀን ከምናደርገው የጦር ሜዳ ፍልሚያ ጎን ለጎን እራሳችንን የማሰልጠን፣የማስታጠቅ እና የማደራጀት ስራችንን ያለአንዳች መዘናጋት አጠናክረን እንቀጥላለን። አደረጃጀቶቻችንም የተናበበና የተቀነባበረ አመራር ለመስጠት በሚያስችለን መልኩ ለማሰባሰብ የምናደርገውን ጥረት በጥሩ መንገድ በትጋት እየሰራን ነው። ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ሀይሎች ጋር የምናደርገውን የትግል አጋርነት እና ቅርርብ መልክ ለማስያዝ የአማራ ፋኖ በከፍተኛ ትጋት እየሰራ ነው። አማራ እራሱን እየተከላከለ በትጥቅ እና በአደረጃጀት ሀይሉን እያጠናከረ ከሌሎች ኢትዮጵያን ሀይሎች ጋር ትግሉን አስተባብሮ በድል ለመቋጨት የሚያደርገው ትንቅንቅ እንደተጠበቀ ሆኖ በከተሞች የሚኖረው ህዝብ ግን የአረመኔው የአብይ አገዛዝ ዋና ገፈት ቀማሽ ሆኖ እያለ በእጁ ብዙ ሊጠቀምበት የሚችል የትግል ግብአት እና ሀይል ቢኖረውም እስካሁን በተደረገው ትግል ላይ የትጥቅ ትግሉን በመጠኑ ከመደገፍ ባለፈ በተገቢው ሁኔታ የትግሉን ጊዜ እና መስዕዋትነት ለማሳጠር በተቀናጀ መንገድ አልተነቃነቀም። በዛሬዋ የአብይ አህመድ አረመኔያዊ አገዛዝ ኢትዮጵያ በከተሞች ለሚኖረው ህዝብ በሰላም ወጥቶ መግባት ብርቅ ነው። ያለ ጉቦ ጉዳይ ማስፈፀም የማይታሰብ ሆኗል። ልጆቹን ለሚገድልበት ገንዘብ ለማሰባሰብ ህዝባችንን አጥንቱን እየጋጠው ነው። በኑሮ ውድነት ሰቅዞ እያሰቃየው ነው። ከትግል መነሻችን ጀምሮ በተደጋጋሚ እንደገለፅነው የአማራ ህዝብ ህልውና የሚጠበቀውና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ የተጫነውን አገዛዝ ከነግሳንግሱ መቅበር የሚቻለው ሁሉንም የትግል ስልቶች በተገቢው ቦታ እና ጊዜ በተጠና እና በታቀደ መንገድ አቀናጅቶ እና አዋህዶ በመምራት እንደሆነ ላፍታም መዘንጋት የለበትም። የኢትዮጵያ ከተሞች አዲስ አበባን ጨምሮ አረመኔው አብይ አህመድ በትጥቅ የሚፋለሙትን ጀግኖች ለማጥፋት ሴራ የሚጎነጉንበት፣ስንቅና ትጥቅ የሚያገኝበት፣የወንበዴ እና የዘር አጥፊ መደበቂያ ዋሻ መሆኑ በአፋጣኝ ማክተም አለበት። በመሆኑም በከተሞች የሚኖረው ህዝባችን ነባራዊ ሁኔታው በሚፈቅደው የትግል አይነት ሁሉ እምቢተኝነትን በማፋፋም አረመኔውን ስርአት ለመንቀል በቆራጥነት እንዲነሳ ጥሪዬን እያስተላለፍኩ የከተማ ትግላችንን በልዩ ሁኔታ የሚከታተል እና የሚያስተባብር የስራ ግብረ ሀይል ተቋቁሞ ተገቢውን አመራር እንደሚሰጥ እናሳውቃለን። ድል ለአማራ ህዝብ ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ አዲስ ትውልድ አዲስ አስሳሰብ አዲስ ተስፋ ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን ህዳር 6_2018 አም አርበኛ ዘመነ ካሴ

  • 🔥የአገዛዙ ብልፅግና ሰራዊት ንፁሃንና እንስሳትን በከባድ መሳሪያ ጨፈጨፈ‼️         ህዳር 05/2018ዓ.ም የአገዛዙ ብልፅግና ወንበር አስጠባቂ ጨፍጫፊ ሰራዊት በሰሜን ወሎ አስተዳደር ዞን ላስታ ወረዳ 04 ቀበሌ ሳርዝና ልዩ ስሟ ወምበርኮ ማርያም ከምትባል ደብር እህል በመዉቃት ላይ ያሉ ንፁሃንን ላሊበላ ከተማ ልዩ ስሙ ሁለት ቁጥር ከሚባለው ቦታ በመሆን በዘፈቀደ ሞርተር 120 ወደ ንፁሃን በመተኮስ የአንድ ቤተሰብ ልጆች    1. ህፃን ወርቅየ ጌታቸውዕድሜ=15 ወዲያውኑ አውድማው ላይ ሲሞት    2. ህፃን ደባሽ ጌታቸው ዕድሜ=8 ቀኝ እጁ የተቆረጠ እንዲሁም    3. የልጆቹ አባት አቶ ጌታቸው መለሰ    ዕድሜ=46 በከባድ ሁኔታ የቆሰለ    4.  ሰባት ከብቶች ወዲያውኑ ሲሞቱ    5. አውድማው ላይና በዙሪያው የነበረ ሦስት ክምር እህል ከ30 ኩንታል በላይ የሚገመት እህል ወድሟል። የብልፅግና ወራሪ ሰራዊት ግብረ ሰዶም የሚፈፅም፣ህፃናትን የሚያርድ፣ንፁሃንን የሚረሽን በመድፍ አረር የሚቆላ፣አራጅ፣ደፋሪ ፀረ አማራ በመሆኑ በህዝባዊ ማዕበልና እምቢተኝነት ለአንዴና ለመጨረሻ ተባብረን እናስወግደው ሲሉ የጄኔራል ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ አርበኛ ሃምሳ አለቃ ጌታየ ተፈሪ ጥሪ አስተላልፈዋል። መዳረሻው ድልና ነፃነት የሆነው የአማራ ህዝብ የህልውና ተጋድሎ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲል የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ግዙፉ ላስታ ጄኔራል አሳምነው ፅጌ ኮር ጄ/ተፈራ ማሞ ክፍለ ጦር  ቃል አቀባይ አርበኛ ፋኖ ሽፈራው አለልኝ መረጃውን አድርሷል። ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!! ©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ምስራቅ አማራ ቀጠና ምኒልክ ዕዝ #ዐንድ_አማራ‼️ #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 05/ዐ3/2018 ዓ.ም

  • ለወደመው ስልጣኔያችን ፣ ለተወረረው ለም መሬታችን ፣ ለተዘረፈው ቅርሳችን ፣ አደጋ ውስጥ ለገባው ማንነታችን ፣ ለተገፋው ህዝባችን ፣ ለተገፈፈው ክብራችን ፣ ለተቀማው ሐብታችን ፣ ለጠፋው ስማችን ፣ ለተዳፈነው ታሪካችን ስንል ያስነሳነው የጠብ መንጃ አብዮት በድል መንገድ ላይ ነው ። ትውልዱ የተንሻፈፈውን የኢትዮጵያን ፖለቲካ ምህዋር ያስተካክላል ፤ ዘረኝነትን ከእነ አካቴው ያጠፋል ፣ የተዛባውን የፖለቲካ አስተሳሰብ ያርማል ፣ ብሔራዊነትን እና ሉዓላዊነትን ያሰፍናል ፤ ህዝባችን የሰው ሐብቱን ፣ የተፈጥሮ ሐብቱን ፣ ጊዜውን ፣ ጉልበቱን ይጠቀማል ። ይህ ትግል ስርዓት በመቀየር ፣ መንግሥት በመገልበጥ ፣ አብይን በመለወጥ ብቻ አይቆምም ። የዚህን ትግል ዳር መድረስ የሚጠብቁ ፣ ለመለወጥ እና ለመቀየር የተዘጋጁ ፣ የፋኖን አሸናፊነት የሚዋጁ ብዙ ጉዳዮች ከፊታችን እየጠበቁን ነው ። አዲስ ትውልድ አዲስ አስተሳሰብ አዲስ ተስፋ !!

  • ደስታህን በኑሮህ ከሚገጥሙህ ሁኔታዎች ጋር አታገናኘው፤ ደስታ ማለት የችግር አለመኖር አይደለም፤ በችግር ውስጥ እያለፍክ መሳቅ ነው። ነገሮች ምርጥ ሲሆኑማ ሁሉም ይደሰታል እኮ፤ አንተ ግን በአምላክህ እና አጠገብህ ባሉ መልካም ነገሮች ሁሌም ደስተኛ ሁን። ውስጥህ ሲደሰት ውጪህ ላይ ይገለጣል፤ ከዛ አንተ ደስተኛ ስለሆንክ አለም አብራህ ትስቃለች፤ ከባድ የመሰለህ ነገር ተራ ሲሆን ታየዋለህ፤ ሰዎች የደስታህን ምንጭ ለማወቅ ሲሉ አክብረው ያደምጡሀል፤ አንተ ጋር ማውራት ወይ አብሮህ መሆን የማይፈልግ የለም፤ ያንተ ስራ መገረም ብቻ ይሆናል። ወዳጄ መቼም የማይተው አምላክ እንዳለህ ማሰቡ ራሱ የደስታ ጥግ ነው።

  • 🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻 🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼 🌻2018🌻መልካም🌻አዲስ አመት🌻             🌻🌻🌻      መልካም🌻አዲስዓ መት   መልካም🌻     አ🌻ዲ🌻ስ መልካም 🌻        ዓ🌻መ🌻ት ለወዳጄ 🌻          ዓ🌻መ🌻ት 🌻🌻🌻🌻        አ🌻ዲ🌻ስ                          ዓ🌻መ🌻ት                        አ🌻ዲ🌻ስ                      አ🌻ዲ🌻ስ                    ዓ🌻መ🌻ት                  አ🌻ዲ🌻ስ             ዓ🌻መ🌻ት         አ🌻ዲ🌻ስ       ዓ🌻መ🌻ት    አ🌻ዲ🌻ስ ዓ🌻መ🌻ት               🌻🌻🌻🌻 🌻መ🌻ል 🌻ካ🌻ም🌻🌻🌻🌻 🌻አ🌻ዲ🌻ስ🌻ዓ🌻መ🌻ት 🌻             🌻   🌻   🌻       🌻መል🌻🌻🌻ካም🌻   አ🌻ዲ🌻ስ          ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ            ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ            ዓ🌻መ🌻ት   አ🌻ዲ🌻ስ          ዓ🌻መ🌻ት        🌻መ🌻ል🌻ካ🌻ም🌻              🌻  🌻  🌻                                       🌻🌻አዲስ            🌻🌻🌻አመት         🌻🌻መ🌻ልካም    🌻🌻አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት             አዲስ🌻ዓመት   🌻መልካም  🌻 አዲስዓመት   🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻    አዲስዓመት🌻ለወዳጄ🌻🌻   🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻               🌻   🌻   🌻       🌻መ🌻ል🌻ካ🌻ም🌻   አ🌻ዲ🌻ስ          ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ            ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ            ዓ🌻መ🌻ት   አ🌻ዲ🌻ስ          ዓ🌻መ🌻ት        🌻መ🌻ል🌻ካ🌻ም🌻       🌻መል🌻🌻🌻ካም🌻   አ🌻ዲ🌻ስ          ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ            ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ              ዓ🌻መ🌻ት አ🌻ዲ🌻ስ            ዓ🌻መ🌻ት   አ🌻ዲ🌻ስ          ዓ🌻መ🌻ት        🌻መ🌻ል🌻ካ🌻ም🌻                🌻   🌻   🌻 🇪🇹ሀገራችን ሰላም የምትሆንበት🌻🌻 🌻🌻🌻ያሰብነው የሚሳካበት  🌻🌻 🌻️🌻🌻                                         🌻🌻 🌻የካሳ🌻የሰላም🌻የጤና🌻የበረከት🌻️ 🌻🌹⁣🌾ዓመት 💐🌷ይሁንልን።🌻🕊🌻

  • 1/ ቅቤ ገደል! ትናንት ምሽቱን በአንጀኔ አድርጎ ወደ ፈረስ ቤት እየተጓዘ የነበረውን የአረመኔውን ወራሪ ሠራዊት ጀግኖቹ የኢንጅነር ክበር ተመስገን ብርጌድ ፋኖዎቻችን ቅቤ ገደል ላይ ደፈጣ በመጣል  የጨበጣ ውጊያ አድርገው በርካታ ቁጥር ያለው የጠላትን ኃይል መደምሰስ የቻሉ ሲሆን አረመኔው ሠራዊትም አስከሬኑንና ቁስለኛውን እየጎተተ ወደ አንጀኔ ተመልሷል። 2/ አረመኔዉ ስርዓት ከሱርታ መገንጠያ በመነሳት ወደ ጁጋ ተራራ የተንጠለጠለ ሲሆን ንስሮቹ የግጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ጥምር ጦር በሞርተር ከተራራዉ በማዉረድ  ቀጥቅጦታል። በዚህም ጥቃት ጠላት ሬሳዉን ማንሳት ያልቻለ ሲሆን የጠላት ሃይል በመናድ ወደ ቆንጆዎቹ ተቀላቅሏል በዚህም መሰረት -1 ብሬን _1ስናይፐር _5 ክላሽ  በመያዝ የጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦርን ተቀላቅለዋል ። አዲስ ትውልድ  አዲስ አስተሳሰብ  አዲስ ተስፋ የአማራ ፋኖ በጎጃም ‎ ሐምሌ 09/2017ዓ.ም

  • 🔥የአፋብኃ በጎጃም ቀጠና የ24 ሰአት አበይት ሁነቶች‼️      ሰኔ17/2017ዓ.ም ሀ. በቀን 16/10/2017 ዓ/ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት አባ ኮስትር ብርጌድ የረዝ ቀበሌ ላይ የደፈጣ ጥቃት በመፈፀም በጠላት ላይ ጉዳት ማድረስ ተችሏል። በዚህ ደፈጣ በቁጥር ያልታወቀ የጠላት ኃይል ሙትና እና ቁስለኛ ተደርጓል። ለ. አፋብኃ ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር ቢትወደድ አያሌዉ መኮነን ብርጌድ ጠላት ላይ ታላቅ ድል ተቀናጅቷል። ጎጃም አገዉ ምድር ክ/ጦር፣ ቢትወደድ አያሌዉ መኮነን ብርጌድ ሰዓታት በፈጀው አዉደ ዉጊያ የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በጎንደር ቀጠና አድዋ ክፍለ ጦር የንጋት ጮራ ብርጌድ በጋራ ከቁንዝላ ከተማ በቅርብ ርቀት ከምትገኘዋ ዳርፉር ዝችር ላይ መሽጎ ያለዉን የጠላት ሀይል ላይ ዶፍ አውርደውበታል። አሸባሪዉ የብልፅግና ጦር የሞቱበትን አስከሬን ለመለቃቀም ሳንክራ ባርከንታ ላይ ያለዉን ሀይል በማሰባሰብ ዳግሞኛ ለማጥቃት ቢሞክርም ከሽፎበት ውጊያው በፋኖ አሸናፊነት ተጠናቋል። በዚህም ዉግያ፦ ➣ 9 የመከላከያ አባላት እስከ ወዲያኛዉ ሲሸኙ፣ ➣ 11 አባላትም ቁስለኛ ሁነዋል። ሐ. በዛሬው ዕለት በሰከላ ወረዳ ግሽ አባይ ከተማ ዙሪያ ባሉ ቀበሌዎች በወራሪው ኃይል የታፈኑ ኗሪዎችን የግዮን ብርጌድ አስለቅቋል። በግዴታ ሰልፍ ትወጣላችሁ በማለት ከኮለል ቀበሌ 34፣ ሳውሳ 50፣ ጎደር 64 ኗሪዎችን ከቤተክርስቲያን አፍኖ ወደ ሰከላ ግሽ አባይ ከተማ ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረውን ሀይል የግዮን ብርጌድ አናብስቶቹ አባግስ ሻለቃ፣ ግትም ሻለቃና ሀይሌ አድማሱ ሻለቃ በአንድ ላይ ጥምረት በመፍጠር ጠላት ላይ መብረቃዊ ጥቃት በመሰንዘር ከታፈኑት ሰዎች መካከል 144 ንጹሀንን አስለቅቀዋል። ሰከላ ወረዳ ግሽ አባይ ከተማ የመሸገው አሸባሪው ሀይል 22 ንጹሀንን አፍኖ የወሰደ ሲሆን ፋኖን ታወግዛላችሁ፤ ፋኖን ማታወግዙ ከሆነ እናንተም ፋኖናችሁ ትረሸናላችሁ በማለት ሲያስፈራራቸውና ስልጠና ሲሰጥ እንደዋለ ግዮን ብርጌድ መረጃ ደርሶታል። መ. ከየጁቤ በመውጣት በቀን 17/10/2017 ዓ.ም የአፋብኃ በጎጃም የሐዲስ ዓለማየሁ 7ኛ ክፍለ ጦር አብራጂት ብርጌድን ከነሙሉ ትጥቁ የተቀላቀለው ምሊሻ አሽከርነት ሰለቸኝ ከህዝቤ ጎን ለመቆም ብልፅግናን ትቼ ወጥቻለሁ ብሏል። ሠ. የበረኸኛው ቀስተ ደመና ብርጌድ በጫጎ ደረባና  በገነት ቀበሌዎች ሕዝብን በመሰብሰብ የጨፍጫፊው የብልጽግና አገዛዝ በሕዝባችን ላይ እያደረሰ ያለውን መጠነ ሰፊ ጥፋትና የንጹሐንን ጭፍጨፋ በተመለከተ፤ ለማሕበረሰባችን መልካም አስተዳደርን ለማሳለጥ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ማሕበረሰቡን በሰፊው ያወያየ ሲሆን ማህበረሰቡን የሚያውኩ ሁነቶች ካሉ ከፋኖ ጋር በመረባረብ የአካባቢን ሰላም ማስከበር እንደሚገባ በሰፊው ውይይት ተደርጓል። አዲስ ትውልድ ፣አዲስ አስተሳሰብ ፣አዲስ ተስፋ!    © አፋብኃ በጎጃም ቀጠና #ላንጨርስ_አልጀመርንም‼️ #ምረር_አማራ💪 #ድል_ለአማራ_ፋኖ💪 #ድል_ለአማራ_ህዝብ💪 17/10/2017 ዓ.ም

  • የአማራን ሕዝብ ሕልዉና ለማስጠበቅ ለወጣቶች ወታደራዊስልጠናና የፖለቲካ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራው ወሳኝ ነው።

  • ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል (አፋብኃ) ጎንደር  ቀጠና  ዳግማዊ ቴዎድሮስ (5ኛ) ኮር ምስረታን አስመልክቶ የተሠጠ መግለጫ! የአማራ ህዝብ የገጠመውን የህልውና አደጋ እስከ ወዲያኛው ለመቀልበስ የፋኖ ትግል በሁለንተናዊ የትግል ስትራቴጂ በስርዓቱ ላይ የበላይነቱን አስጠብቆ አሁን ካለበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ስለሆነም በአማራ ህዝብ ተሳትፎና ድጋፍ በሰው ሃይል፣ በትጥቅና ስንቅ እንዲሁም በአደረጃጀት እየጠነከረ መጥቷል። ሆኖም በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው ግዙፉ ኮር  እነሆ ዛሬ ማለትም ግንቦት 26 ቀን 2017ዓ.ም             ከበለሳ እስከ ደንቢያ ሳንኪሳ፣ ከፎገራ እስከ ወገራ፣ ከዞዝ አምባ እስከ አይንባ፣ ከእብናት እስከ ዳባት እንዲሁም ከፎገራ እስከ ጃናሞራ ቀጠናን የሚሸፍን ስያሜው “ዳግማዊ ቴዎድሮስ  (5ኛ) ኮር የተባለ ኮርን መስርተናል። መስራች ክ/ጦሮችም የሚከተሉት ናቸው።    1- መብረቅ ክፍለ ጦር    2- ጎንደሬ በጋሻው ክፍለ ጦር    3- ንስር በለሳ ቅ/እጅጉ ክፍለ ጦር    4- ጥቁር አንበሳ       ""    5-ዞዝ አምባ ንጉሱ      ""    6- ታድሎ ብርሃን        ""    7- ፋናየ ውቤ ክፍለ ጦር ናቸው።       የዳግማዊ ቴዎድሮስ (5ኛ) ኮር የስራ አስፈፃሚ አባላት የሚከተሉት ናቸው:- 1. አርበኛ የሻምበል ሙሉሰው      የኮር  ዋና ሰብሳቢ 2. አርበኛ መኮነን አስፋው          "    ምክ/ሰብሳቢ 3. አርበኛ አንተነህ ብርሃኔ          "     ወታ/አዛዥ 4. አርበኛ ጌታቸው አያልቅበት       "    ምክ/ወ/አዛዥ 5. አርበኛ አየልኝ ውዴ             "     ዘመቻ መምሪያ 6. አርበኛ ሱራፌል ኢልያስ            "     ምክ/ዘመቻ መምሪያ 7. አርበኛ ሰሎሞን ደሴ             "      ፅ/ቤት ሃላፊ 8. አርበኛ ኤርሚያስ ንጉሴ           "     ፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊ 9. አርበኛ አብነት ሞላ              "     ህ/ግንኙነት ሃላፊ 10. አርበኛ ናትናኤል ሙሉዓለም        "      አስተዳደር ሃላፊ 11. አርበኛ ሲራክ ጥሩነህ            "      አደረጃጀት ሃላፊ 12. አርበኛ ደምወዝ ጀግናው          "     ሕዝብ አስተዳደር ሃላፊ 13. አርበኛ አምባቸው ወንዴ           "   ህግና ስነ-ምግባር ሃላፊ 14. አርበኛ ገዛኸኝ ያለው             "   ሎጀስቲክስ ሃላፊ 15. አርበኛ ደምወዝ ጀምበር           "    ምክ/ሎጀስቲክስ ሃላፊ 16. አርበኛ አለሜ ባየ                "     ት/ት እና ስልጠና ሃላፊ 17. አርበኛ ባብል ብርቁ              "     ፋይናንስ አስተዳደር  18. አርበኛ አበበ ደስታው             "     ግዥ ክፍል  ተጠሪ 19. አርበኛ አማኑኤል ምትኩ           "      የሰው ሃይል አስተዳደር  20.        *                       "     መረጃና ደህንነት መሆናቸውን እየገለፅን ለተመረጡት የስራ አስፈፃሚ አባላት በሙሉ መልካም የስራ ጊዜን እየተመኘን በተመደባችሁበት የስራ መደብ ከሙሉ መተማመን ጋር አደራ እንላለን።              ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!!            ግንቦት 26 ቀን 2017 ዓ/ም             ጎንደር-አማራ-ኢትዮጵያ

  • https://www.facebook.com/profile.php?id=100063492799485

  • ይህን ግቡና Follow አድርጉት👇https://www.facebook.com/profile.php?id=61576923506720

  • በመጨረሻም የፋኖን የማያወላውል አለም አቀፍ የሰብአዊ እና የሰብአዊ መብቶች ህግጋትን እናረጋግጣለን። ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የእኛ ኃይሎች የጦር እስረኞችን አያያዝ ጨምሮ ዋስትናን ለመቀነስ በከፍተኛ ዲሲፕሊን እና እግድ ሠርተዋል። ለአማራ ህዝብ ደህንነት እና ክብር የምናደርገው ትግል በመሰረታዊ የህግ እና የሞራል መርሆዎች ላይ የተመሰረተ ነው እና ከአሜሪካ መንግስት እና ከሌሎች አለም አቀፍ አጋሮች ጋር ገንቢ ግንኙነት ለማድረግ ክፍት እንሆናለን። የ AFNF የፖሊሲ ቁርጠኝነት እና አሁን ካለችበት ችግር ባሻገር ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊት የሰፈነባት ኢትዮጵያ ራዕይን ጨምሮ ቀጣይ የውይይት እድሎችን በደስታ እንቀበላለን። በአክብሮት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል

  • ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል የተሰጠ መግለጫ! የአሜሪካው አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ለሰጠው መግለጫ ምላሽ ከአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል ይፋዊ ግንኙነት --[የአማርኛ ትርጉም] የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ሃይል አመራር በቅርቡ በአዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኢምባሲ ያወጣውን መግለጫ በአክብሮት ተቀብሎ በኢትዮጵያ እየታየ ባለው አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ላደረጉት ተሳትፎ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋን አድናቆቱን ያቀርባል። በአማራ ላይ ለሚደረገው ጦርነት ለመላው የኢትዮጵያ ዜጎች ደህንነት፣ ክብር እና ደህንነት ቅድሚያ የሚሰጠውን ዘላቂ መፍትሄ እንደሚያስፈልግ ኤምባሲው በድጋሚ ማረጋገጡን እናደንቃለን። የትምህርት እና የጤና አጠባበቅ ተደራሽነትን ወደነበረበት መመለስን ጨምሮ ለአገሪቱ አሳሳቢ የሰብአዊ ቀውስ ምላሽ ለመስጠት የሰጠውን መግለጫ እናደንቃለን። እነዚህ ለቁጥር የሚታክቱ ሰላማዊ ዜጎች በተለይም በአማራ ክልል የሚኖሩትን እውነታ ስለሚያንፀባርቁ AFNF በጥልቅ የሚጋራው ስጋቶች ናቸው። በዚህ ረገድ የአየር ላይ ጥቃቶችን እና ሌሎች የዜጎችን ህይወት አደጋ ላይ የሚጥሉ ጥቃቶችን ማቆም አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተናል። በአብይ አህመድ መንግስት ሃይሎች የተፈፀመ የአውሮፕላን እና የአየር ድብደባ በአማራ ክልል እና አካባቢው በሺዎች የሚቆጠሩ ንፁሀን ዜጎች ያለ አግባብ ጥቅም ላይ ውለዋል። እነዚህ ጥቃቶች በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ጣቢያዎች፣ በገበያ ቦታዎች፣ በሃይማኖታዊ ቦታዎች እና በመኖሪያ አካባቢዎች በመምታቱ በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ውድመት አድርሰዋል። ስለሆነም አምባሳደሩ አፋጣኝ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፣ በገዥው አካል ላይ እንዲህ ያለውን አድሏዊና የዘር ማጥፋት ተግባር ለማስቆም እና ለሚያደርሱት አስከፊ መዘዞች ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ጫና ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበናል። AFNF በመግለጫው ውስጥ ከተገለጹት ዋና የሰብአዊ ጉዳዮች ጋር በማጣጣም እና በመላው አገሪቱ እየተባባሰ ባለው የሰብአዊ መብት ሁኔታ የኤምባሲውን ማንቂያ ይጋራል። የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም አማሮች ስልታዊ የዘር ማጥፋት፣ የዘር ማጽዳት፣ መፈናቀል፣ የጦር መሳሪያ ጥቃት፣ ሰው ሰራሽ ረሃብ እና ጭቆና ተሸክመዋል። ይሁንና መግለጫው ምናልባት በአማራው ላይ እየደረሰ ያለውን ግፍና በደል ምን አይነት ባህሪ እና አስከፊነት በማንሳት ሊሆን እንደሚችል በአክብሮት እናስተውላለን። በዚህ አጋጣሚ የአብይ መንግስት በአማራ ክልል እና በሌሎች የአማራ ተወላጆች እየፈፀመ ያለው ድርጊት የጦር ወንጀል እና በሰው ልጆች ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ብቻ ሳይሆን የዘመናት የዘር ማጥፋት ሂደት አካል ነው የሚለውን ግምት ውስጥ አስገብተናል። ይህ አካሄድ በተነጣጠሩ ጥቃቶች፣ በግዳጅ መፈናቀል እና በስርአት ቸልተኝነት የሚንፀባረቀው ከ1990ዎቹ ጀምሮ በተለይም በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ (ጎንደር)፣ በራያ (ወሎ)፣ በደራ (ሸዋ)፣ በመተከል (ጎጃም) እና በ"ኦሮሚያ" ክልል ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ነው። AFNF ወደ ትጥቅ ተቃውሞ የተመለሰው ከብዙ አሥርተ ዓመታት ሰላማዊ ትግል በኋላ ነው። በአማራው ላይ እየተካሄደ ባለው የዘር ማጥፋት ዘመቻ የነዚህ አመታት ኢ-አመጽ ጥረቶች ያልተሳካላቸው ሲሆን በመጨረሻም በጠላቶቻችን ዘንድ የድክመት ምልክት እና የዘር ማጥፋት ዘመቻውን ለማስቀጠል ፍቃድ ተደርገዋል። በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ ፋኖ ግልጽ ወይም ተጨባጭ ዓላማዎች የሉትም የሚለው ሀሳብ በተዘዋዋሪም ይሁን ባልታሰበበት ሁኔታ በጣም ያሳስበናል።የተከበሩ አምባሳደር፣ ከትልቅ አክብሮት ጋር፡ ከመጥፋት ስጋት ውስጥ ካለ ህዝብ ህልውና የበለጠ ህጋዊ ወይም የበለጠ ምን አላማ ሊሆን ይችላል? አላማችን ከህልውና ስጋት አንጻር ህይወትን መጠበቅ መሆኑን መልሰን ልንገልጽ እንወዳለን። ፋኖ ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል የተውጣጡ አርሶ አደሮች፣ መምህራን፣ የህክምና ባለሙያዎች፣ የዩኒቨርስቲ መምህራን እና ጋዜጠኞች የተቃውሞ ሸክሙን በምርጫ ሳይሆን በግዴታ የተሸከሙ ግለሰቦችን ያቀፈ ነው። ህብረተሰባቸውን ከዘር ማጥፋት ጥቃት የመታደግ የሞራል ግዴታ ስላለባቸው ተገድደዋል።ይህም በእኛ እምነት መንግስት መከላከል ብቻ ሳይሆን ቀዳሚ ፈጻሚ ነው። እነዚህ ስጋቶች ቢኖሩም፣ የ AFNF ለሰላም ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ለማረጋገጥ በዚህ አጋጣሚ እንጠቀማለን። በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም የሽግግር ፖለቲካ ማዕቀፍ እና ተዓማኒነት ያለው ሁሉን አቀፍ ብሄራዊ ውይይት መጀመርን ይጠይቃል ብለን በፅኑ እናምናለን። ይህ አይነቱ ሂደት ግልጽ እና የኢትዮጵያን ልዩ ልዩ ህዝቦች እና ድምጽ የሚወክል መሆን አለበት። ዩናይትድ ስቴትስ እንደ ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ አጋር እና ዓለም አቀፋዊ የዴሞክራሲ እሴቶች ደጋፊ በመሆን ይህንን ዓላማ እንድትደግፍ በአክብሮት እንጠይቃለን። በዚህ ረገድ የዩኤስ መንግስት ወደ አካታች አስተዳደር እና ፍትህ የሚደረግ ሽግግርን ለማመቻቸት የታለሙ ማዕቀቦችን ጨምሮ ሁሉንም ተገቢ የዲፕሎማሲ መሳሪያዎችን እንዲያሰማራ እናሳስባለን። በዚህ አጋጣሚ ሰላምን ለማስፈን ፍቃደኛ መሆናችንን ደግመን እንገልፃለን ነገርግን በአብይ አህመድ መንግስት በኩል ያለው መልካም ፍላጎት እና ታማኝነት የጎደላቸው የፖለቲካ አላማዎችን በማጥበብ አገዛዙ ካለው የማታለል ታሪክ አንጻር ነው። ይህ እንዳለ ሆኖ AFNF የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ያቀርባል ይህም መተማመንን የሚያበረታታ እና ለተለመደ ውይይቶች ምቹ ሁኔታዎችን ይፈጥራል። እነዚህ ቅድመ ሁኔታዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ ነገር ግን አይወሰኑም፦ • ጦሩ ባስቸኳይ ማቆም እና የፌደራል አጋር ሃይሎች የሀገር መከላከያ ሰራዊትን ከአማራ ክልል መልቀቅ እና የብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤቶችን በሙሉ መፍረስ እና የአማራ ክልል የፖለቲካ እና አመራሮችን ከስልጣን ማባረር እና በፋኖ አደራዳሪነት ስልጣን ወደ ሽግግር አስተዳደር በሰላም እንዲሸጋገሩ፤ • በአለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች - በተባበሩት መንግስታት የታዘዘ የምርመራ ቡድንን ጨምሮ - በክልሉ ውስጥ የተፈጸሙትን ጭካኔዎች በተመለከተ ጥልቅ እና ገለልተኛ ምርመራ ለማድረግ ፈጣን እና ያልተቋረጠ መዳረሻ። እነዚህ ምርመራዎች አጥፊዎችን ለፍርድ ለማቅረብ ተጨባጭ የተጠያቂነት እርምጃዎችን መከተል አለባቸው • በማንነታቸው እና/ወይም በፖለቲካ እምነታቸው የታሰሩትን የአማራ የፖለቲካ እስረኞች፣እንዲሁም በገዥው አካል ታግተው የሚገኙ የፋኖ አባላትን ቤተሰብ አባላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈታሉ። • በሁሉም የአማራ ክልል አካባቢዎች የቴሌኮሙኒኬሽን እና የኢንተርኔት፣ የመብራት፣ የውሃ እና የባንክ አገልግሎቶችን እንደገና መጀመር፤ • በመላው የአማራ ክልል እና የተፈናቀሉ (ከዘር ማጥፋት የተረፉ) ሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ማህበረሰቦች እንደገና እንዲቀጥል እና ያለማቋረጥ እንዲተላለፍ ማድረግ; • በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ (ጎንደር)፣ ራያ (ወሎ)፣ መተከል (ጎጃም) እና ደራ (ሸዋ)፣ የተፈናቀሉ ማህበረሰቦችን ወደ አጎራባች ክልሎች ጨምሮ በአማራ-ብዙ ወረዳዎች ለመደበኛ የማንነት እና የድንበር አስተዳደር እውቅና መስጠት። • የአማራ ማህበረሰቦች ጥበቃ - ንብረቶቻቸውን ጨምሮ - በመላው ኢትዮጵያ በተለይም በታሪክ ጠላት በሆኑ ወረዳዎች።

  • መልካም ዜና የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል ሸዋ ቀጠና ትግሉ የደረሰበት ደረጃና ቀጣይ ለሚደረጉ ስምሪቶች የሚመጥን የአመራር ስምሪት በድርጅቱ መመሪያ እና ደንብ መሰረት ሰጥቷል። በዚህም መሰረት 1ኛ.አርበኛ ኢሳያስ ደመቀ የአፋብኃ ሸዋ ቀጠና ም/መሪ 2ኛ. አርበኛ ንጉስ ይመሩ የአፋብኃ ሸዋ ቀጠና ትምህርት እና ስልጠና መምሪያ 3ኛ. አርበኛ ኤፍሬም ባዩ የአፋብኃ ሸዋ ቀጠና ምክትል ፖለቲካ ዘርፍ መምሪያ ኃላፊ 4ኛ. አርበኛ ተፈሪ ወንዶሰን የአፋብኃ ሸዋ ቀጠና ምክትል የሰው ሀይል መምሪያ ኃላፊ 5ኛ. አርበኛ አበራ ምንጉዴ የአፋብኃ ሸዋ ቀጠና ምክትል ጥናት እና እስትራቴጂ መምሪያ ኃላፊ 6ኛ. አርበኛ ስለሽ አበረ የአፋብኃ ሸዋ ቀጠና ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ 7ኛ.አርበኛ ሽመልስ ንጉሴ የአፋብኃ ሸዋ ቀጠና የሰው ኃብት አስተዳደር መምሪያ ኃላፊ 8ኛ. አርበኛ ሽፈራው ኢያሱ የአፋብኃ ሸዋ ቀጠና ም/ሀብት አሰባሰብ መምሪያ ኃላፊ 9ኛ. አርበኛ አለባቸው እምሩ የአፋብኃ ሸዋ ቀጠና ም/ቀጣዊ ትስስር መምሪያ ኃላፊ 10ኛ. አርበኛ አሰፋ ነበበ የአፋብኃ ሸዋ ቀጠና ም/ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ከላይ በስም የተጠቀሱት የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይል በሸዋ ኃላፊዎች በተመደቡበት ቀጠና ድርጅቱ የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እና ግዴታ በቅንነት እና በታማኝነት ይወጡ ዘንድ ኃላፊነት ተሰጥቷቸዋል። ክብር ለተሰውት ሰማዕታት! ግንቦት 15/2017 ዓ/ም አፋብኃ ሸዋ ቀጠና የህዝብ ግንኙነት ክፍል ሸዋ አማራ ኢትዮጵያ

  • "በቂሊንጦ እስር ቤት ውስጥ ፣ የተደቀነብንን አደጋ መላው ህዝባችን እንዲያውቅልን እንፈልጋለን!" በቂሊንጦ የፌዴራል እስር ቤት የምንገኝ የአማራ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንገኛለን። የማረሚያ ቤቱ ከሚፈፅምብን በርካታና የተለመዱ አስተዳደራዊ ፣ አካላዊና ሥነልቦናዊ ጥቃት በተጨማሪ የፌዴራል ፖሊስ የኮማንዶ ፣ የአዲስ አበባ ልዩ ኃይል ፣ የመከላከያ ኮማንዶ ከፌዴራል ፖሊስ  የወንጀል ምርመራና አቃቤ ህግ ጋር በመቀናጀት ተከታታይ የህልውና ስጋት የሚደቅኑ ግፎችና የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እየፈፀሙብን ይገኛሉ። በትናንትናው እለት የፌዴራልና የመከላከያ ኮማንዶ ወታደሮች ከማረሚያ ቤቱ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ላይ ''ዞን አምስት'' ተብሎ በሚጠራውና እነ አቶ ዮሀንስ ቧያለው ፣ ክርስቲያን ታደለ ፣ አብዱራህማን አሊ ፣ ዶ/ር ሲሳይ አውግቸውና ሌሎችም  የአማራ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች የሚገኙበትን ዞን በመውረር ፣ እስረኞችን በብርድ ከዞን ቅጥር ውጭ በማስወጣት ፣  አካላዊ ጥቃት በማድረስና በማንገላታት ከፍተኛ ግፍ ፈፅመዋል። ውድ ወገኖቻችን! ''በህዝባችን ላይ የሚፈፀመው ሥርዓታዊ ጥቃትና የህልውና አደጋ መቆም'' አለበት ብለን በመታገላችን ምክንያት እስከ ሁለት ዓመት ድረስ ያለምንም ፍትህ ፥ ከሰመራና አዋሽ አርባ የማሰቃያ ካምፖች ፣ ሜክሲኮ ከሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ፣ በገላንና ማዕከላዊ ማጎሪያዎች ከተፈፀመብን የግፍ መዓት ተርፈን እስከአሁኑ ሰአት ድረስ በፍትህ ማጣት  እየተሰቃየን እንደምንገኝ ይታወቃል። በአሁኑ ሰዓት በብልፅግና ሥርዓት ተስፋ የቆረጠ አካሄድ ምክንያት ፣ በቂሊንጦ የምንገኝ  የአማራ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች የህልውና አደጋ እንደተደቀነብንና በማናቸውም ሰዓት ወደከፉ የማሰቃያ ስፍራዎች ድጋሚ ልንጋዝና በህይወታችን ላይ አደጋ የሚጥል ጥቃት ሊፈፀምብን እንደሚችል መላው ህዝባችን እንዲያውቅልን እንሻለን!        ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን!

  • ሰበር ዜና - 15ኛው ኮሎኔል ተቀነደሸ! ኮሎኔል ተስፋዬ የተባለ የፋሽስቱ ስርዓት የምዕራብ እዝ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ የአፋብኃ ባህርዳር ብርጌድ በፈፀሙት የተጠና የደፈጣ ጥቃት መቀንደሹ ተረጋግጧል። ጥቃቱ ከዚህ የግለሰብ አገልጋይ ኮሎኔል በተጨማሪም ሌሎች አመራርና ተራ የአገዛዙ ወታደሮችንም የበላ እንደነበር ተነግሯል። ይህንን ድል ተከትሎም በጎጃም ቀጠና ብቻ ፉት ተደርገው የተሸኙ ኮሎኔሎች ቁጥር 15 የደረሰ ሲሆን የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ኃይልም የአገዛዙን ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን መንደል አንድ ብሎ መጀመሩ በዚህ ድንቅ ጥቃት ተበስሯል።

  • ውድ የአማራ/ፋኖ ግሩፕ አባለት ከሁሉም አቅጣጫ በፍጥነት መረጃ ለማግኘት add member እናደርግ! የግሩቡን ተከታይ ቁጥር በፍጥነት ወደ 2000 እና ከዛም በላይ ከፍ እናድረገው። _መጀመሪያ አማራ/ፋኖ የሚለውን ፕሮፋይል ንኩ ከዚያም 1ኛ፡ ከዚያ add member የሚለውን ንኩ 2ኛ፡ ቀጥላችሁ የጓደኞቻችሁ ዝርዝር ሲመጣ አማራ የሆኑትን ብቻ በመንካት ምረጡ። 3ኛ፡ በቀኝ በኩል ታች ያለችዋን ሰማያዊ የራይት✅ ምልክት ንኩ። 4ኛ፡ በመጨረሻም Add የሚለውን ንኩና  አማራ የሆኑትን ብቻ የጉርፕ  አባል አድርጉ። #መስፈርት👇 በዚህ ግሩፕ ውስት አባል መሆን የሚችል ሰው፡ 1 አማራ የሆነ ብቻ ያውም ቁርጠኛ አማራ 2 ፋኖን የሚደግፍ እና የሚያበረታታ 3 በአማራነቱ የማይደራደር 4 ለህዝቡ የሚታገል የሚቆረቆር 5 የብልፅግና ደጋፊ ያልሆነ የሚጠላ እና የሚታገል 6 ትክክለኛ መረጃ የሚሰጥ እና ሸር በማድርግ ለሌሎች የሚያዳርስ 7 ከፋፋይ አጀንዳን የሚጠላ ለአንድነት እና ለሰላም የሚያስብ 8 መሳደብ ፍፈፅሞ የተከለከለ ነው 9. ግሩፑን የማይመጥን አላስፈላጊ ፀያፍ ነገር መለጠፍ ከግሩፑ remove ይደረጋል 10... 11.......ጨምሩበት ከዚህ ውጭ የሚሳደብ የአማራን አንድነት ለመከፋፈል የሚያስብ እና እርስ በርስ ለማከራከር እና ለማጋጨት የሚፈልግ አናሰተናግድም። ይህን አይነት ድርጊት የሚፈፅም ሰው ካለ ይወገዳል እናተም ጠቁሙኝ 👇 https://t.me/+Ex2b2aAQgQI2ZTc0