tgindex
Amen Charitable Organization አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት

Amen Charitable Organization አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት

Статистика

~💢አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት#ንግድ ባንክ፦ 1000427953967 በጎነት ለራስ ነው! ~💢 በቴሌብር ለበጎአድራጎት ሚለውን ተጭነው በቀን 1ብር ይለግሱ እናመሰግናለን🙏 ~💢 'no child left behind,every child matters' ~💢 Address : Addis Ababa, Figa mebrat ~💢 አሜን ዳቦና ኬክ አድራሻ: ፊጋ መብራት ~💢 for more info📱0965940498

Последний пост
26 мая
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
28
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Новости и СМИ (по похожим)
В каталоге с
14 авг.
Подписчики
2 982
+6 за 1 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
1 376
28 постов
Вовлечённость
46,1%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 28
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
1/48двое суток
1/72трое суток

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ውድ የአሜን ቤተሰቦች ሊንኩን ተጭነው አሜን በጎ አድራጎት ለሚያሳድጋቸው ህፃናት 1 ብር በቴሌብር ይለግሱ እናመሰግናለን። ኢትዮቴሌኮምን ከልብ እናመሰግናለን። 👇👇👇👇👇👇👇 https://www.superapp.ethiomobilemoney.et:38443/static/mIndex.html?executeUrl=macle%3A%2F%2Fa8db9bb622cd44e48369eb5697411379%2FadvPage%2Fdetail.html%3Fid%3Dc0Gu000001W3fj2rtZxI&appType=customer

  • ውድ የአሜን ቤተሰቦች ሊንኩን ተጭነው አሜን በጎ አድራጎት ለሚያሳድጋቸው ህፃናት 1 ብር በቴሌብር ይለግሱ እናመሰግናለን። 👇👇👇👇👇👇👇 https://www.superapp.ethiomobilemoney.et:38443/static/mIndex.html?executeUrl=macle%3A%2F%2Fa8db9bb622cd44e48369eb5697411379%2FadvPage%2Fdetail.html%3Fid%3Dc0Gu000001W3fj2rtZxI&appType=customer

  • 12 апр.1 500132

    እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ​ይህ የትንሳኤ በዓል ጨለማው አልፎ ብርሃን የወጣበት፣ ሞት ድል ተነስቶ ሕይወት የታወጀበት ታላቅ ዕለት ነው። እኛም በአሜን በጎ አድራጎት ድርጅት ስም የምናከናውናቸው የበጎ አድራጎት ተግባራት ለእልፎች ተስፋና ብርሃን እንዲሆን የምናደርገውን ጥረት አጠናክረን እንቀጥላለን። ​በዓሉ የፍቅር፣ የሰላም፣ የመረዳዳትና የአንድነት እንዲሆንላችሁ ከልብ እንመኛለን። በተለይም በዚህ ቅዱስ ዕለት ከሞት ወደህይወት መሻገራችንን በማሰብ እና ከተሰጠን ላይ ደግሞ ለሌላቸው በማካፈል የበዓሉን ትርጉም በተግባር እንድንገልጸው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። ​መልካም የፋሲካ በዓል! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ! ​አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት "ፍቅር በተግባር!" ሚያዚያ 4 ቀን 2018 ዓ.ም

  • 1 апр.1 5825

    без подписи

  • 1 апр.1 5885

    без подписи

  • 1 апр.1 5684

    без подписи

  • 1 апр.1 1426

    без подписи

  • 1 апр.1 580155

    🌟 🇪🇹 እጅን ከመዘርጋት... እጅን ወደ መስራት! 🇪🇹 🌟 ​"እጅን ለልመና ሳይሆን ለስራ መዘርጋት ክብር ነው!" የሚለው አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት ​በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማእከል አዳራሽ ቁጥር 3 ውስጥ መልካምን ስራ እያከናወነ ይገኛል። አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት "ስራ ያስከብራል!" የሚለውን ታላቅ መርህ አንግቦ፣ ከልመና ተላቆ በራሱ ለመቆም በመቁረጥ እንደሁልጊዜው የጥበብ ስራዎቹን ይዞ ቀርቧል። ​ለምን መምጣት አለብዎት? እርስዎ የሚገዙት እያንዳንዱ ጌጣጌጥ ወይም የአሜን አርት እጅ ጥበብ ውጤት ተራ ሽያጭ አይደለም። እርሱ፦ 📍 የአንድን ወገን ህይወት ከጎዳና የሚያነሳ ድልድይ ነው! 📍 "መስራት ትችላላችሁ" የሚል የክብር ምስክርነት ነው! 📍 የነገ ተስፋን የሚጭር የብርሃን ስንቅ ነው! ​🎨 ምን ይዘን ቀረብን? • ​በልዩ ጥበብ የተሰሩ ውብ ጌጣጌጦች • ​ለፋሲካ በዓል ድምቀት የሚሆኑና ለስጦታ የሚሆኑ በፍቅርና በጽናት የተጠነሰሱ ድንቅ የእደ-ጥበብ ስራዎች ​📍 አድራሻ፦ ኤግዚቢሽን ማእከል (መስቀል አደባባይ) — አዳራሽ ቁጥር 3 📅 ጊዜ፦ ከመጋቢት 17 እስከ ሚያዚያ 3 (የፋሲካ ዋዜማ) ​መፈክራችን፦ "ገዝተው ይርዱ! ስራ ያስከብራል!" የሚል ነው። ​የበዓልዎን ደስታ በበረከት ያጅቡ። መጥተው በመግዛት ከጎናቸው መሆንዎን ያሳዩ። የእርስዎ ጥቂት ድጋፍ አሜን ለሚያሳድጋቸው ውድ ልጆቻችን የሙሉ ህይወት ለውጥ ነው! ለሚቀጥለው ትውልድ ልመናናን አናወርስም! አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት። 🙏🙌🙏

  • 17 мар.1 7673

    без подписи

  • 17 мар.1 6393

    без подписи

  • 17 мар.1 77093

    ልመናን በተግባር መበቀል! አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት 10ዓመት ያስቆጠረ የታሪክ ምዕራፍ እየፃፈ ነው! ✨🇪🇹 ​በሳለፍነው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ላይ አንድ እፁብ ድንቅ ኩነት ተመልክተናል። በኮንቬንሽን ሴንተር ተዘጋጅቶ በነበረው የኤግዚቢሽን መድረክ ላይ ክቡር አቶ ፋሲካው ሞላ (የኢፌዲሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር)፣ ክቡር አቶ አህመድ ሁሴን (የምክር ቤቱ ፕሬዝዳንት)  ክቡር አቶ ጃፋር በድሩ (የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር) እና ክቡር አቶ መሱድ ገበየሁ፦ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር የአሜን በጎ አድራጎት ድርጅትን ራሱን ለመቻል እያደረገ ያለውን ጥረት በጎበኙበት ወቅት በታየው ነገር እጅጉን መደነቃቸው ይታወሳል። ​አሜን ከልመና ወጥቶ ራስን በመቻል ይቻላል የሚለውን የኢትዮጵያዊያን ጽኑ እምነት በተግባር እያሳየ ይገኛል። ​ባለሥልጣናቱ እንደገለጹት፤ "ስራ ያስከብራል" በሚል መሪ ቃል፣ ድርጅቱ ለሚያሳድጋቸው ልጆች የሥራ ክብርን በማስተማር በርካታ ስራዎችን በመፍጠሩ በአሜን ውስጥ ያለው ትውልድ "ብሩህ ኢትዮጵያን የሚያሳይ" እና ነገ ለኢትዮጵያ መልካም ልዩ ፍሬ የሚያፈሩ ልጆች የሚወጡበት ማህፀን እንደሆነ ገልፀዋል። እንዲሁም ሌሎች ከአሜን ትልቅ ትምህርት ሊወስዱ እንደሚገባና ድርጅቱ እየሰራ ያለው ሥራ የመንግሥትን አቅጣጫ የተከተለ መሆኑን ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። ​አዎ! አሜን ልመናን ለመበቀል ተነስቷል። በኢትዮጵያ ላይ አዲስ ታሪክ እንፅፋለን! ልጆቻችንን ሰራተኛ እንጂ ተመጽዋች አያደርጋቸውም። ይህ ለሁላችንም ኩራት ነው! ፈጣሪ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ይባርክ! ​#አሜን_በጎ_አድራጎት #ልመናን_መበቀል #ራስን_መቻል #በጎነት_ለራስ_ነው #ብሩህ_ኢትዮጵያ #AmenCharity

  • 8 мар.1 47022

    "ልመናን በፈጠራ የረታው 'አሜን' በልህቀት ማህተም ታተመ! በቅድሚያ የኢፌዲሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን መስራያቤትን እና የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤትን ከልብ እናመሰግናለን! ተስፋን በተግባር፣ በጎነትን በፈጠራ የቀየረው አሜን "ከአድናቆት እስከ ሽልማት፦ በጎ አድራጎት ድርጅቱ በአዲሱ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ላይ ድምቀት ሆኖ አመሸ!" ድንቅ በጎ ስራዎቹም በሽልማት ታጀቡ!" አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት በ5ኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ላይ የልህቀት አሻራውን አሳረፈ፤ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችንና ሴክተሩን በፈጠራ ሥራዎቹ ለ3ቀናት ሲያስገርም ሰንብቷል። ​ "ራስን መቻል ለዘላቂ ሰላም እና ለአካታች ልማት" በሚል መሪ ቃል በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር ለ3 ተከታታይ ቀናት (የካቲት 26-28 ቀን 2018 ዓ.ም) በደማቅ ሁኔታ በተከበረው 5ኛው የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ላይ፣ አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት የፈጠራ ጥበብን ከሰብዓዊነት ጋር አቆራኝቶ በማቅረብ የጉባኤው ድምቀት ሆኖ ሰንብቷል። ​ድርጅቱ በኤግዚቢሽኑ ላይ ይፋ ያደረጋቸው እጅግ ማራኪ የአርት ሥራዎችና የጌጣጌጥ ጥበቦች፣ "በጎ አድራጎት ከልመና ተላቆ ራስን በመቻል ላይ ሊመሠረት ይገባል" የሚለውን የድርጅቱን ጽኑ ራእይ በተግባር ያሳዩ ነበሩ። ይህ ድንቅ ዝግጅት በሀገር ውስጥና በውጭ በጎ አድራጎት ድርጅቶች፣ በልማት አጋሮችና በከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ዘንድ ከፍተኛ መገረምንና አድናቆትን ፈጥሯል። ​የአሜን በጎ አድራጎት ድርጅትን የሥራ ውጤቶች በግርምት ከጎበኙ ከተመለከቱና በአገልግሎቱ ከተመሰጡ የክብር እንግዶች መካከል፦ • ​ክቡር አቶ አደም ፋራህ፦ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት፣ • ​ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ፦ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር፣ • ​ክብርት ሃና አርዓያሥላሴ፦ የፍትሕ ሚኒስትር፣ • ​ክቡር አቶ ሳምሶን ቢራቱ፦ የኢፌዲሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር፣ • ​ክቡር አቶ ፋሲካው ሞላ፦ የኢፌዲሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ምክትል ዳይሬክተር፣ • ​ክቡር አቶ አህመድ ሁሴን፦ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ፕሬዝደንት፣ • ​ክቡር አቶ ተረፈ ደጌቲ፦ የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር፣ • ​ክቡር አቶ መሱድ ገበየሁ፦ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር፣ • ​ክቡር አቶ ጃፋር በድሩ፦ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር • ክቡር አቶ ግዛቸው አስራት ፦ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት ቺፍ ኦፍ ስታፍና ጄኔራል ዳይሬክተር እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግስት ሚኒስትሮች ይገኙበታል። ​ባለሥልጣናቱ በጉብኝታቸው ወቅት ድርጅቱ በአሁኑ ወቅት በኃላፊነት ከሚያሳድጋቸው 50 ልጆች ጎን ለጎን፣ ማህበረሰቡን ወደ ምርታማነትና ራስን ወደ መቻል የሚያሸጋግሩ የሙያ ስልጠናዎችንና የገቢ ማስገኛ ስራዎችን በትጋት ማከናወኑ "እንደ ሀገር ለተያዘው የብልፅግና ጉዞ ትልቅ ግብዓት ነው" ሲሉ አድናቆታቸውን ገልጸዋል። በተለይም አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ የቆየውን "የእጅ ወደ አፍ" የበጎ አድራጎት ባህል በመቀየር፣ በፈጠራ ሥራዎች ላይ የተመሠረተና ራስን የቻለ ተቋማዊ አሰራርን በማስተዋወቁ ረገድ እያመጣ ያለው በጎ ተፅዕኖ በሚኒስትር ደረጃ ባሉ አመራሮች ዘንድ ታላቅ አክብሮትን አትርፎለታል። የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ሳምንት ዋነኛ አላማ በዘርፉ ያሉ ድርጅቶች በማህበረሰቡ ውስጥ በሚደረጉ ማናቸውም እንቅስቃሴ ያላቸውን ሚና ለህዝብ እና ለባለድርሻ አካላት እንዲያስተዋውቁ ዕድሉን መፍጠር እና የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከመንግስት፣ ከግሉ ዘርፍ እና ከሌሎች የልማት አጋሮች ጋር ተቀራርበው በትስስር የሚሰሩበትን መድረክን ማመቻቸት ነው።  ​በአጠቃላይ፣ አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት በዚህ ታሪካዊ መድረክ ላይ ያሳየው ውጤታማ እንቅስቃሴ፣ ድርጅቱ ከሰብዓዊ አገልግሎት ባለፈ ለሀገር ገጽታ ግንባታና ለኢኮኖሚ ትንሳኤ እያበረከተ ያለውን ሚና በደማቅ ቀለም የጻፈ ክስተት ሆኖ ተመዝግቧል። በዝግጅቱ መጨረሻም በጎ አድራጎት ድርጅቱ በበጎ ስራዎቹ የክብር ማህተም አረፎበታል፤ በባለስልጣን መስሪያቤቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት በኩል የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር በሆኑት ከክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ እጅ የላቀ የተሳትፎ የምስጋናና የእውቅና ሽልማት ተበርክቶለታል። አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት በኢትዮጵያ ውስጥ የቆየውን የበጎ አድራጎት ባህል በመቀየር፣ በፈጠራ ሥራዎች ላይ የተመሠረተና ራስን የቻለ ተቋማዊ አሰራርን በማስተዋወቁ ረገድ እያመጣ ያለው በጎ ተፅዕኖ በዚህ ሽልማት አማካኝነት ዳግም ተረጋግጧል። ይህ እውቅና ለድርጅቱ ቀጣይ ጉዞ ብርታት ከመሆኑም በላይ፣ በሀገራዊ የብልፅግና ጉዞ ውስጥ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ያላቸውን የማይተካ ሚና በጉልህ ያሳየ ሆኗል። ​ሽልማቱ የእናንተም በመሆኑ ለውድ የአሜን ቤተሰቦች እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን። ልመናን ለሚቀጥለው ትውልድ አናወርስም!! በጎነት ለራስ ነው! ስራ ያስከብራል! አሜን በጎ አድራጎት ድርጅት። የካቲት 29 ቀን 2018ዓ.ም

  • 8 мар.1 0971

    без подписи

  • 8 мар.1 2041

    без подписи

  • 8 мар.1 3552

    без подписи

  • 8 мар.1 4081

    без подписи

  • 8 мар.1 3381

    без подписи

  • 8 мар.1 1722

    без подписи

  • 8 мар.1 2772

    без подписи

  • 8 мар.1 1611

    без подписи