Book for all Ethiopia
Статистика- Последний пост
- 11 июн. 2025 г.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги
- В каталоге с
- 15 авг.
- 1/24сутки в ленте
- —
- 1/48двое суток
- —
- 1/72трое суток
- —
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
видео или голосовое, без подписи
አብርሆት ቤተ-መጻሕፍት የአባልነት ምዝገባ ተጀምሯል። ለመመዝገብ ይህን ቅደም ተከተል ይከተሉ :- 1. በ www.abrehot.org.et/register/ በመግባት የምዝገባ ፎርሙን ይሙሉ 2. ፎርሙን እንደጨረሱ ወደ ክፍያ ገፅ ይወስዳቹሀል ፣ አመታዊ የአባልነት ክፍያ በቴሌብር ወይም በንግድ ባንክ በኩል በቀላሉ መክፈል ይችላሉ። 3. ቅድመ ተከተሉን እንደጨረሱ አባልነቶ አፕሩቭ ይሆናል። ቅድመ ተከተሉን ከጨረሱ ቡሀላ በ15 ቀን ውስጥ ዲጂታል የአባልነት መታወቂያ በኢሜይል ይደርሶታል። አባል ሲሆኑ የሚከተለውን ጥቅሞች ያገኛሉ :- 1. መፃህፍትን በነፃ መዋስ። 2.ለ12 ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል ሙሉ ወጪ በመሸፈን። 3. የጋራ የውይይት ክፍሎችን በኦንላይን ማግኘት።. 4. ከ 1.5 ሚልየን በላይ ጆርናሎች እና የመመረቂያ ፅሁፎች በቀላሉ በኦንላይን ማግኘት። 5.በቶሞካ ትኩስ መጠጦች ላይ 35% ቅናሽ። ብርሀን ለኢትዮጵያ 🇪🇹
видео или голосовое, без подписи
የሽንታችን መልክ ስለጤናችን ምን ያመላክታል? ↔️ ⚪️🟡 🖌 ንፁህ ዉሀማ ወይም ፈዛዛ ቢጫ - በቂ ዉሃ ሰዉነታችን ሲያገኝ, ጤናማ መልክ ነዉ!! 🟧 🖌 ደማቅ ቢጫ - በቀን ዉስጥ የምንጣዉ ዉሃ ሲያንስ!! 🔴 🖌 ቀይ - ደም ሽንት ዉስጥ ሲቀላቀል ፣ የተመገብነው ምግብ (እንደ ቀይ ስር፣ ወይን ፍሬ)፣ የወሰድነዉ መድሀኒት (እንደ ቲቢ መድሀኒት)!! 🟠 🖌 ብርቱካናማ - የጉበት ህመም ሊኖር አንደሚችል ያመላክታል!! 🟢🟣 🖌 አረንጓዴ ወይም ወይነጠጅ - የሽንት ኢንፌክሽን ያመላክታል!! ✒️ የደፈረሰ ሽንት እና ያልተለመደ ሽታ የኢንፌክሽን ምልክቶች ናቸዉ!! ዶ/ር ፍጹም ሰለሞን የቴሌግራም ቻነል: https://t.me/drfitsumsolomon
видео или голосовое, без подписи
#ፕሮስቴት 📌 ከሽንት ፊኛ በታች የሚገኝ እጢ ነዉ!! 📌 ወንድ አጥቢ እንስሳት ላይ ብቻ ይገኛል!! 📌 ስራዉም የዘር ፈሳሽ ማመንጨት፣ በግንኙነት ጊዜ የዘር ፈሳሽ ወደ ዉጪ እንዲወጣ መርዳት ነዉ!! 📌 ፕሮስቴት ላይ ሊያጋጥም የሚችል ህመም ኢንፌክሽን፣ መጠኑ መጨመር ወይም ካንሰር ነዉ!! 📌 ምልክቶቹም የሽንት ጉልበት መቀነስ ፣ የሽንት መቆራረጥ፣ ለሊት ከእንቅልፍ ደጋግሞ ለሽንት መነሳት፣ ቀንም የሽንት ቶሎ ቶሎ መምጣት ናቸዉ!! 📌 እነዚህ ምልክቶች ካሎት ሐኪም ያማክሩ!! 📌 ህክምናዉም በሚዋጥ መድሀኒት ወይም ቀዶ ህክምና ነዉ! ስለፕሮስቴት ተጨማሪ መረጃ ወደፊት ይቀጥላል!! ➡️➡️➡️➡️ https://t.me/drfitsumsolomon ዶ/ር ፍጹም ሰሎሞን
*ስለምንታይ አብዚ ዝረከብካኒ ይመስለካ?- ለምን እዚህ ያገኘኸኝ ይመስልሃል? ----------------------------------------- ማስታዎሻ: "የሰው የነፍስ ዋጋው ስንት ነው?" ለማለት ማስታዎሻ ትሁንልኝ፡፡ ዛሬ ላይ ቁጥር የሆነብን የአንድ ሰው ሞት በጀርባው የብዙ ሰዎችን የነፍስ ኩርፊያ ተሸክሟል፡፡ ከእናንተ አንደኛችሁን ባስቀይም ቢያንስ እናታችሁ/አባታችሁ እንደማሳዝናቸው እርግጥ ነው፡፡ ከአንድ ሰው ጋር ለማውራት ጊዜ ከተገኘ ብዙ ነገሮችን እንሰማለን፡፡ ዮሐንስ በላይ
ሺ ሰማኒያ [1080] አንድ ቅዳሜ ቀን ጫማዬን ለማስጠረግ የሆነ ቦታ ቆሜ ሳለሁ አንድ መበለት እኔ ወዳለሁበት መጥተው ስባሪ ሣንቲም እንድጥልላቸው እጃቸውን ዘረጉልኝ፡፡ "ይቅርታዎትን? እዛች ቤት ይግቡና ቁርስ ይዘዙ፤ አብረን እንበላለን" አልኳቸው፡፡ እጃቸውን አየር ላይ እንደዘረጉ ዝም ብለው አዩኝ፡፡ "ጫማዬን አስጠርጌ እስክጨርስ የሚፈልጉትን አዘው ይጠብቁኝ" አልኳቸው፡፡ "ኧረ ብሩ ይበቃኛል" አሉ የሆነ አይነት ሳቅ እና መሽኮርመም እያሳዩኝ፡፡ ብሩን ብቻ የፈለጉ አይመስልም፡፡ ሳይጠራጠሩ፤ ምናልባት እረስቶት ባይመጣ ብለው የፈሩ ይመስለኛል፡፡ ለመሄድ ከተስማሙ በኋላ ዘወር እያሉ አንድ ሁለት ጊዜ ተመለከቱኝ፡፡ "ይቅርታ ትንሽ አፍጥንልኝ" አልኩ ጎንበስ ብዬ፡፡ ቀይር ብሎ ቆርቆረውን ከመምታቱ በፊት ጫማዬን ለመቀየር እግሬን ወደ ላይ ብድግ አደረግሁለት፡፡ "እሺ" አለና ቆርቆሮውን ኳ! አደረገው፡፡ ቁርስ የምበላበት ቤት እንደገባሁ ወደዚህ የላኳቸውን እናት በዐይኔ ፈለኳቸው፡፡ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን ጥቁር ፌስታል ጭናቸው ላይ እንዳደረጉ በሩ አጠገብ ጭብጭ ብለው አየኋቸው፡፡ "ለምን ይሸከማሉ?" አንደኛውን ወንበር ወደእሳቸው ሳብ አደረኩና፤ "እዚህ ላይ ማስቀመጥ ይችላሉ" አልኳቸው፡፡ እቃውን እስቀምጠው ወደኔ ለማየት እንዲመቻቸው ትንሽ ዘወር አሉ፡፡ "ምን አዘዙ?" "ምንም" አንገታቸውን አቀረቀሩ፡፡ "እሺ፡፡ . . . ፍርፍር ነገር ይሁን ወይንስ ቂጣ ነገር? ጨጨብሳ፣ ቅንጬም ከፈለጉ አለ" "ቅንጬ ይሸጣል?" ገረማቸው፡፡ "አዎ አለ" አሁንም ትንሽ ተሽኮረመሙ፡፡ "ቅንጬ ይሁንለዎት?" "እሺ!" አስቸናጋጁን ጠርቼ ቅንጬ እና ጨጨብሳ እንዲያመጣልን ነገርኩት፡፡ "የፈጠነ! አንድ ሌላ ጨጨብሳ እና አንድ ቅንጬ" አለ አስተናጋጁ ድምጹን ከፍ አድርጎ፡፡ ከንግግሩ ጋር አብሮ የተበላባቸውን እቃዎች ለማንሳት ወደጠረጴዛዎቹ ይበራል፡፡ ምን ብዬ ወሬ እንደምጀምር ስለጠፋብኝ፡፡ "ልጅ አለዎት?" በጊዜው የመጣልኝን ጥያቄ አቀረብኩ፡፡ "የለኝም" ጎንበስ ብለው ያደፈ ነጠላቸውን ማፍተልተል ያዙ፡፡ የማይሆን ርዕስ የመረጥኩ ስለመሰለኝ ቀጥዬ የምጠይቀው ነገር ሁሉ ነውር ሆነብኝ፡፡ "የሚጠጣ ምን ይምጣላችሁ?" አለ አስተናጋጁ አጠገባችን ቆሞ ቁልቁል እያየን፡፡ "ማዘር! የሚጠጣ ምን ይፈልጋሉ?" "ምንም አልፈልግ፡፡ በልቼ ስጨርስ ቡና ልጠጣና አንድኛዬን በደንብ አድርጌ ልመርቅህ?" ንግግራቸው ውስጥ "እሺ በለኝ?" የሚል ልመና ነበረው፡፡ "አሺ፡፡ . . . ትንሽ ቆይተን ትኩስ ነገር እንጣለን" አልኩኝ፡፡ መጀመሪያ እሳቸውን ቀጥዬ እሱን እየተመለከትኩ፡፡ ወይዘሮ መብራት ርዕሶም ይባላሉ፡፡ ዕድሜአቸው ሰባዎቹ ውስጥ ይገመታል፡፡ ተወልደው ያደጉት ከአሥመራ ወጣ ብላ ያለች ትንሽ መንደር ውስጥ ነው፡፡ በቀይ ኮከብ ዘመቻ አስመራ ያለ አንድ ቡና ቤት ውስጥ ጽዳት ሠራተኛ ሆነው ይሠሩ ነበሩ፡፡ ቤቱ ብዙ የደርግ ወታደሮች ከሚያዘወትሩት እንደነበር በታሪክ ጭምር ይታወቃል፡፡ *** ልክ እንደዛሬው ቅዳሜ እረፋድ ላይ፤ ቤቱን አጽድቼ ቁርሴን ልበላ ቀጭ እንዳልኩ፤ አንድ የደርግ ወታደር በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ገባ፡፡ ጥግ ላይ ሁለት መኮንኖችን ስለነበሩ ትንሽ ደንገጥ አለ፡፡ ለእነሱ ሰላምታ ካቀረበ በኋላ እጄን ይዞ ወደ ጓዳ ወሰደኝ፡፡ * አስተናጋጁ አንድ የጀበና ቡና እና አንድ ሻይ ይዞልን መጣ፡፡ * ወደ ውስጥ እንደገባን፤ "ሻለቃ ባሕሩ ተመቶ ሆስፒታል ገብቷል" አለኝ፡፡ "*ብህይወት አሎ ድዩ ሞይቱ?" አልኩት፡፡ "ደህና ነው፡፡ ወደ አዲስ አበባ ሊሄድ ስለሆነ ሊያገኝሽ ይፈልጋል" አለኝ፡፡ ተያይዘን አሥመራ ሆስፒታል ሄድን፡፡ የሚታከምበት ክፍል ስገባ፤ ገና በር ላይ እንዳለሁ አልጋው ላይ ቁጭ ብሎ አየሁት፡፡ በጣም ደስ አለኝ፡፡ እቅፍ አድርጎ ሳመኝና አልጋው ጠርዝ ላይ አስቀምጦ፡፡ "ቦርድ የምወጣ ይመስለኛል፡፡ አዲስ አበባ አብረን እንሂድ?" አለኝ፡፡ "አዲስ አበባ?!" በጣም ደነገጥኩ፡፡ እሱ ግን ፈገግ እያለ፤ "ከዚህ በኋላ ሚስቴ አድርጌሻለሁ" አለኝ፡፡ * "አሁን እዚህ ያገኘኸኝ ለምን ይመስልሃል? ታናሽ እኅቴን ይዤ ከእሱ ጋር አዲስ አበባ መጣሁ " * ትንሽ ፈገግ ማለት ስጀምር ፊታቸው ጭፍግግ ሲል አየሁት፡፡ የህይወታቸው አሳዛኝ ክፍል ሊጀምር እንደሆነ ስለገባኝ ትንሽ ሰብሰብ ለማለት ሞከርኩ፡፡ "*ዕድል ወድ ሰብ ይገርምዩ" አሉ ጨርሰው ያስቀመጡትን ስኒ እንደገና ፉት እያሉ፡፡ "ይደግማሉ?" አልኳቸው፡፡ በጭንቅላታቸው ብቻ መለሱልኝ፡፡ *** አዲስ አበባ መኖር ከጀመሩ ሠላሳ አንድ ዓመት ሆኗቸዋል፡፡ ባለቤታቸው ከዛሬ አሥራ ሁለት ዓመት በፊት ሲሞቱ ያስቀመጡላቸው ምንም አይነት ጥሪት አልነበረም፡፡ ይባስ ብሎ ይኖሩበት የነበረው ቤት ከባለቤታቸው ወንድም ጋር የፍርድ ቤት ክርክር ገጠመው፡፡ * ይረዳኛል ብዬ ስላሰብኩ ለባለቤቴ ጓደኛ ነገሩን በዝርዝር አጫወትኩት፡፡ የጠበቃ ብር እንዳይበዛብኝ የቤቱን ዋጋ ዝቅ አድርገሽ ተከራከሪ ብሎ ነገረኝ፡፡ ሰውየው ከባለቤቴ በላይ የወንድምዬው ወዳጅ ነበር፡፡ ተንኮል እንደነገረኝ የገባኝ ነገሩ ካለፈ በኋላ፣ ቆይቶ ነው፡፡ ወንድምዬው ይህንን መሠረት አድርጎ፤ ለዳኞቹ ጉቦ ሰጠና የተባለውን ብር ለእኔ ከፍሎ ቤቱን እንድለቅ ለፍርድ ቤቱ አመለከተ፡፡ * ትኩሱን ቡና ከሦስት ጊዜ በላይ ፉት አላሉትም፡፡ * ብሩን ወስጄ ቤቱን እንድለቅ ተፈረደ፡፡ ቤቱ ግን ሚሊዮን ያወጣ ነበር፡፡ ሁለት መቶ ሃምሳ ሺ ብር እና የታመመች እኅቴን ይዤ ከቤት ወጣሁ፡፡ ሦስት ዓመት በትክክል መኖራችንን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡ ለህክምና፣ ለኑሮ እያልን ብሩን ጨረስነው፡፡ ለረጅም ጊዜ ዝም ብለው መሬት መሬቱን ሲመለከቱ ቆይተው፤ "*ስለምንታይ አብዚ ዝረከብካኒ ይመስለካ?" አሉኝ፡፡ ዝም አልኳቸው፤ "ልመና ወጣን፡፡ አሁን እስጢፋኖስ በተክርስቲያን የላስቲክ ቤት ሠርተን ነው የምንኖረው" የማይሠራ የሬድዮ ድምጽና የተበላሸ የቴሌቪዥን ምስል፤ መስማትና ማየት ጀመርኩ፡፡ *** ----------------------------------------- * ብህይወት አሎ ድዩ ሞይቱ? - በህይወት አለ ወይንስ ሞቷል? * ዕድል ወድ ሰብ ይገርምዩ - የሰው ልጅ ዕድል በጣም ይገርማል፡፡
የመፅሐፍ ሎተሪ ይህ የመፃህፍት ወዳጆች፣ የንባብ አፍቃሪዎች ቡድን ነው። ይህ ቡድን ከ461,000 በላይ አባላት አሉት። ባለፈው በሰበሰብነው poll ከ2000 በላይ ፍቃደኞች አሉ። ከዚህ ውስጥ ቢያንስ 400 ተሳታፊዎች ብናገኝ እቅዳችን ግብ ይመታል። ይህንኑ እንደሚከተለው አስረዳለሁ፦ 400 አባላት እያንዳንዳቸው 50 ብር ቢያዋጡ 20,000 ብር ይኖረናል። በዚህ 20,000 ብር እጣ እያወጣን ለ20 አንባቢዎች ለእያንዳንዳቸው ከ5—8 መፃህፍት እንገዛለን። መርሃግብሩ በየሳምንቱ የሚካሄድ ይሆናል። ለተጨማሪ ማብራሪያ እኔን ወይም Fantahun Abie ፋንታሁን አቤን ያነጋግሩ። በሎተሪው ለመሳተፍ ከዛሬ ጀምሮ ወደዚህ አካውንት 50 ብር እያስገባችሁ ያስገባችሁበትን ስክሪንሻት እያደረጋችሁ በኢንቦክስ ላኩልን። Tewodros Shewangizaw የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000429953611
видео или голосовое, без подписи
የምስራች ለውድ አንባቢያን! ሀሁ መጽሐፍት መደብር ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ እንኳን ለታላቁ ዓብይ ጾም በሰላም አደረሳችሁ እያልን። የፊታችን ሐሙስ በጉጉት የሚጠበቀውን የዲያቆን ሄኖክ ሃይሌን "የብርሃን እናት" መጽሐፍ ቅድሚያ ከፍለው ለሚገዙ 500 አንባቢያን በ260ብር ከፍተኛ ቅናሽ ያደረግን መሆኑን እያሳወቅን ይህ ቅናሽ የሚቆየው እስከ የካቲት 23/06/2014ዓ.ም ብቻ ነው።በዚህ የባንክ አካውንት1000171387808 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፈንታሁን አቤ ብላችሁ ካስገባችሁ በኋላ የሳገባችሁበትን ደረሰኝ +251924408461/@books_of_hahu በዚህ የቴሌግራም አድራሻ ማስቀመጥዎን አይርሱ። "ነፍሴ ሆይ! የምትድኝበትን እኔ እነግርሻለሁ፥ ከዚህ ሁሉ ይልቅ ወደ ቅድስት ድንግል ጩኺ፣ እንዲህም በይ #የብርሃን_እናት ሆይ! በልጅሽ ፊት በደልሁ ኃጢአቴን አስተስርይልኝ፡፡" አባ ጊዮርጊስ ዘጋሥጫ ሀሁ መጽሐፍት መደብር አድራሻ፦ ቁ.1. ስታድየም ናሽናል ታወር ግራውንድ ፍሎር ቁ.2 ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ሕንጻ ስ.ቁ 0911006705
Channel photo updated
Channel photo removed
https://www.linkedin.com/posts/henoke-seyuome-%E1%89%B0%E1%8C%93%E1%8B%A1-%E1%8C%8B%E1%8B%9C%E1%8C%A0%E1%8A%9B-2512b95b_blhblibnz-bqvbkrbpp-blxblhbpmbpcbnz-activity-6862286540635160576-QZtJ
видео или голосовое, без подписи
Surra's Classic Colls እንኳ ደህና መጡ! ዘመን የማይሽራቸው ሙዚቃዎች በዚህ አሉ። https://t.me/SuClassicColls
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
Eid Mubarak
видео или голосовое, без подписи