Tesfaab Teshome
Статистикаለአስተያየት @jtesfaab ላይ ይፃፋልኝ ለመቀላቀል @tfanos ይጫኑ። ቤተሰብ ስለሆንን አመሰግናለሁ ❤❤😍
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 6
- Всего постов
- 24
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 596
- 1/48двое суток
- 683
- 1/72трое суток
- 736
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
ፍቅር በአንድ ጀምበር አይሞትም። እንደ ሻማ እየቀለጠ በዝግታ ይደክማል፤ እሳቱ እያለ ብርሃኑ ይደበዝዛል። ሳራ ከባሏ ጋር ከተጋቡ ሰባት ዓመታት አልፈዋል። የመጀመሪያዎቹ ዓመታት እንደ ጸደይ ነበሩ፤ ትንሽ ቤታቸው በሳቅ፣ በህልምና በተስፋ የተሞላ ነበር። ዛሬ ግን ልባቸው ተራርቋል። ለእራት ሲቀመጡ ውይይታቸው ከሁለት አሊያም ሦስት ሐረጎች አያልፍም። "ውሃ አቀብዪኝ" "እሺ።" "ማታ አመሻለሁ።" "እሺ።" ከዚያ ዝምታ። ሳራ ሙዚቃን ትወዳለች። ሙዚቃ የልቧ ቋንቋ ነው። ስትደሰት ትዘፍናለች፣ ስታዝን ዘፈን ታዳምጣለች። ባሏ ሙዚቃ አይወድም። "ይህ ጫጫታ ምንድነው?" ይላል ሙዚቃ ሲሰማ መጀመሪያ ሳራ ተቆጣች፤ ከዚያ ለመልመድ ሞከረች። በመጨረሻ ግን ሙዚቃዋን በጆሮ ማዳመጫ ብቻ መስማት ጀመረች። እንደ ሌሎች ስሜቶቿ ሁሉ ሙዚቃንም በድብቅ.... ከቅዳሜዎች በአንዱ ከሥራ ባልደረባዋ ጋር ወደ ሙዚቃ ዝግጅት ሄደች። መካከለኛ ሬስቶራንት ነበር። የቡና ሽታ፣ የፒያኖ ድምፅ እና ዝቅተኛ ብርሃን የተቀላቀሉበት። በዚያ ሳሚን አየችው። ሳሚ በመድረኩ ላይ አልነበረም፤ ጠረጴዛ ተደግፎ ዓይኑን ጨፍኖ ሙዚቃውን ያጣጥማል። ዘፈኑ ሲያልቅ ከሁሉም ዘግይቶ በቀስታ አጨበጨበ። የሳሚ ተግባር የተለየ ምክንያት አልነበረውም፤ ነገር ግን ሳራ አስተዋለችው። ከዝግጅቱ በኋላ በቡና ማዘዣው ፊት ተገናኙ። "ይህን ዘፈን ትወጂዋለሽ?" ሳሚ ጠየቃት። "በጣም።" "እኔም። ግጥሙ ከዜማው ይልቅ ይመስጠኛል።" ሳራ በፈገግታ ተመለከተችው። ሳሚ ሳቀ። ሳራ ልቧ ደነሰ። ከረጅም ጊዜ በኋላ በጥልቀት የምታወራውን ሰው እንዳገኘች ታውቋታል። ከዚያ ምሽት በኋላ ሳሚና ሳራ አልተለያዩም፤ ይሁን እንጂ በየቀኑ የሚገናኙ ጓደኞችም አልሆኑም። የሚያገናኛቸው መንገድ ያልታሰበ ነበር። አንድ ዘፈን፣ አንድ ዘፈኑን የሚመለከት የጽሑፍ መልዕክት። "ይህን ግጥም ስሰማው አንቺን አስታወሰኝ" ሳራ መልእክቱን አነበበች። ከዚያም ዘፈኑን አዳመጠች። በግጥሙ ውስጥ ራሷን አገኘች። ... መጀመሪያ ስለ ሙዚቃ፣ ቀጥሎ ስለ መጻሕፍት፣ ከዚያ ስለ ልጅነታቸው፣ በመጨረሻም ስለ ልባቸው አወሩ.... "ምን እያነበብሽ ነው?" ባሏ ጠየቀ። "የሥራ ጉዳይ ነው።" ቃሉ ከአፏ አፈተለከ፤ ልቧ ደነገጠ። ያ የመጀመሪያዋ ውሸት ነበር። ትንሽ ውሸት። የምታነበው የሳሚን የጽሑፍ መልክት ነበር። "እንገናኝ?" ሳሚ አጭር የጽሁፍ መልዕክት ላከለት። ልቧ "አዎ" ይላል፤ ሕሊናዋ "አይ" ይላል።.... ጣቶቿ ልቧን መረጡ። "እሺ" ብላ ፃፈች። ተገናኙ! ሰው የማይበዛበት መናፈሻ መርጠው ተገናኙ! "ለምን ፈራሽ?" እንደተገናኙ ሳሚ ጠየቃት። ሳራ ሳቀች፤ ዓይኖቿ ግን አልሳቁም። ከንፈሯ ሲስቅ አይኗ ተከዘ። "ሳራ...ባለትዳር መሆንሽን አልረሳሁም።" "እኔም አልረሳሁትም።" "ታዲያ ለምን መጣሽ?" ሳራ መልስ አላገኘችም። የሳራ ሕይወት በሁለት ተከፍሏል። አንደኛው የቤቷ ሕይወት ነበር፤ ዝምታ፣ የተለመደ ኑሮ ፣ የተለመደ ግዴታ። ሁለተኛው የሳሚ ዓለም ነበር፤ ሙዚቃ፣ ውይይት፣ ሳቅ፣ እና ያልተነገረ ፍቅር። መሽቷል ፤ እየዘነበ ነበር። "ዛሬ አትሂጂ..." አለ ሳሚ በቀስታ። ሳራ ፊቱን ተመለከተች። በዓይኖቹ ውስጥ የታፈነ ስሜት ነበር። ያንኑ ስሜት እሷም ተሰማት። ቀስ ብሎ እጇን ያዘ። ሳራ እጇን አልሰበሰበችም።... ጥሳው የምትሻገረው መስመር ምን እንደሆነ ታውቃለች። ነገር ግን ከአንዳንድ መስመሮች በፊት ልብ ይራመዳል፤ አእምሮ ደግሞ ከኋላ ይከተላል። ያቺ ምሽት የሕይወታቸውን አቅጣጫ ቀየረች። ውጭ አላደሩም፥ ነገር ግን በሳሚ መኪና ውስጥ ከንፈር ለከንፈር ተጎራረሱ። ቀሚሷን ገለበ፥ ቀበቶውን ፈታችለት። ጡት ማስያዣዋን ሲያላላው አገዘችው... ከዚያ ምሽት በኋላ ሳራ እንቅልፍ ማግኘት አቃታት። የሳሚ እጅ አሁንም በመዳፏ ላይ ያለ ይመስላት ነበር። "ምን እያደረግሁ ነው?" ብላ ራሷን ትጠይቃለች። ቀናት መደበኛ ጉዟቸውን ቀጠሉ። ከሳሚ ጋር ሲሆን የምትስቀው ሳራ ፥ ከባሏ ጋር ሲሆን ግን የምታወራው ቃል እያነሰ ሄደ። በባሏ ፊት ጭምት በሳሚ ፊት ተጫዋች ሆነች። "ሳራ… ደስተኛ ነሽ?" ባሏ ድንገት ጠየቃት። ጥያቄው እንደ መብረቅ መታት። "ለምን ጠየቅከኝ?" "አካልሽ ከእኔጋ ነው፤ ልብሽ ግን ሌላ ቦታ ይመስላል" ሳራ ዓይኖቿን ዝቅ አደረገች። ለመጀመሪያ ጊዜ ባሏ የልቧን ርቀት አስተውሎ ነበር። በሳምንቱ መጨረሻ ሳሚን አገኘችው። "አንቺ ተለዋዋጭ ነሽ" አለ ሳሚ "ምን ማለትህ ነው?" "ከእኔ ደስታን ታገኛለሽ፤ ከዚያ ደግሞ ጥፋተኝነት ይሰማሻል። ይህ ለሁለታችንም ከባድ ነው።" "አንተን ማጣት አልፈልግም።" ሳሚ ፈገግ አለ፤ ግን በፈገግታው ውስጥ ሀዘን ነበር። "እኔም አንቺን ማጣት አልፈልግም። ግን እራስሽን እያጣሽ እኔን እንድታገኚ አልፈልግም።" መሽቶ ባሏ ወደ ቤት ሲመጣ ትንሽ የሙዚቃ ማጫወቻ አመጣላት። "ይህ ለአንቺ ነው።" "አንተ… ሙዚቃ አትወድም እኮ።" "አንቺ እንደምትወጂ አውቃለሁ" የሳራ ጉሮሮ ደረቀ። የሳራ ልብ በሁለት አቅጣጫዎች ይጎተት ጀመር። Via ተስፋአብ ተሾመ https://t.me/Tfanos
ጎዳና አዳሪ ነበርኩ። አስፓልት ጥግ ከቦይ አጠገብ ማዳበሪያ ለብሼ ተኝቻለሁ፤ መንገድ ዳር ኖሬያለሁ። ብድግ ብዬ ከቤት ወጣሁ። እግሬ እንደ መራኝ በዘፈቀደ ሄድኩ። በ14 አመቴ የቤተሰቦቼን ቤት ትቼ ተሰደድኩ። ከቤት የወጣሁባት የመጀመሪያ ቀን የዘላለም ያህል ረጅም ነበረች። ከተማውን ሳካልል ዋልኩ። ሲመሽ አስፓልት ጥግ ተቀመጥኩ። የለበስኳት ነጭ ትሽረት በአንድ ቀን ነተበች። ብርዱ አጥንቴን ሰረሰረው። ጥርሶቼ ተፏጩ ፥ ሰውነቴ ተንቀጠቀጠ። "ያዝ" አለኝ አስፈሪ ገፅ ያለው ጎረምሳ። ቀና ብዬ አየሁት። ማዳበሪያ አቀበለኝ። ማዳበሪያውን ይዤ ፈዘዝኩ። "ልበሰው" አለኝ። ልታዘዘው ሞከርኩ። ነገር ግን አቃተኝ። ማዳበሪያ እንዴት እንደሚለበስ ግራ ገባኝ። እየሳቀ አስተካክሎ አለበሰኝ። "ምግብ በልተሃል?" "አይ" ትራፊ ሰጠኝ። ምግቡን ብፀየፍም ረሃቡ በለጠብኝ። እየፈራሁ ጥቂት ቀመስኩ፣ ሲያቅለሸልሸኝ ተውኩት። ሲጃራ አቀበለኝ "አልፈልግም" አልኩ። ማስቲሽ ሰጠኝ እሱንም አልፈልግም አልኩ። "ትለምደዋለህ። ከሳምንት በኋላ ሱሰኛ መሆንህ አይቀርም" አለኝ እየሳቀ። ማዳበሪያው ብርዱን አላሸነፈውም። ሰውነቴ ወባ እንደያዘው ሰው ይንቀጠቀጣል። "ከቤት ተጣልተህ ነው?" አለኝ እየሳቀ። እንባዬ ገነፈለ። ተንሰቅስቄ አለቀስኩ። ያለቀስኩት በረሃብና ብርዱ ምክኒያት ነበረ። "ምን ሆነሃል?" አለኝ ቤተሰቦቼ እንዴት እንደበደሉኝ ነገርኩት። ጨካኝ አባትና እናት እንዳለኝ ተረኩለት። ሲሰማኝ ከቆየ በኋላ "አይዞህ፥ አሁን ተኛ" ብሎኝ ሄደ። የሚከረፋ ቦይ አጠገብ ማዳበሪያ ለብሼ ተኛሁ። "ወላጆቼ ክፉ ናቸው" ብዬው ነበር። 15 ቀናት በጎዳና ስኖር ላገኘኋቸው የጎዳና ጓደኞቼ ቤተሰብ ያደረሰብኝ በደል ተረኩላቸው... እያስተዛዘንኩ ነገርኳቸው። ከንፈር መጠጡልኝ። እውነታው ሌላ ነበር። ከቤት ያስወጣኝ ልጅነት ነበር። ያስኮበለለኝ ጥጋብ ነበር። የሸፈትኩት በእብሪት ነበር። ነገር ግን ጥፋቴን ማመን ከበደኝ። የገዛ ጥፋቴን ከምቀበል ውሸት መፍጠሩ ቀለለኝ። ጥፋት የሌለባቸውን ወላጆቼን በሀሰት ወነጀልኩ። ሃላፊነት መውሰድ ከባድ ነው። "አጥፍቻለሁ" ማለት ቀላል አይደለም። "ብስለት ጎድሎኝ የተሳሳተ ውሳኔ ወሰንኩ" ብሎ መናገር ይተናነቃል። ሌላውን መወንጀል ቀላል ነው። ተበድያለሁ ማለት ቀላል ነው። ሃላፊነትን ማሸሽ ቀላል ነው። እንዲያ ነው... አንዳንዴ የገዛ ስህተታችንን ላለመቀበል ሌሎችን እንወነጅላለን። የውሳኔ ስህተት መስራታችንን ላለማመን ሌሎች ሰዎችን እናጠለሻለን። አንዳንዴ እንዲያ ነው..... Via ተስፋአብ ተሾመ https://t.me/Tfanos
"ለምን አትፈቺውም? የተሻለ ወንድ አጥተሽ ነው?" አለችኝ። ያበጠ ከንፈሬን እያየች ከንፈር መጠጠችልኝ። "እስኪገድልሽ ነው የምትጠብቂው? ለምን አትለዪውም?" ትለኛለች አይኔን እያየች። ምንድነው የሚያስለቅሰኝ? ትንፋሽ እስኪያጥረኝ አለቀስኩ። ዱላ እንግዳዬ አይደለም፤ ዱላው አያስለቅሰኝም። ጥፊና እርግጫውን በዝምታ መቀበል አውቄበታለሁ፤ ጥፊና እርግጫው አያስለቅሰኝም። ከመች ወዲህ እንደተለወጥኩ አላውቅም። ኩራቴን ገዝግዞታል። ክብሬን በዝግታ ገፎታል። ሲሰድበኝ አልገረምም። ዱላውን ተላምጃለሁ። ተለውጫለሁ። ኩራቴን አጥቼ መዋረድን እስክለብስ ድረስ ተለውጫለሁ። ሁሉም ነገር የተቀየረው በዝግታ ነበር። መጀመሪያ ላይ ስሳሳት ብቻ ይሰድበኝ ጀመር። ስድቡ ለስህተቴ የተሰጠ ቅጣት ነበር። ቀጥሎ ስድቡ ወደ አስፈሪ ቁጣ አደገ። ድንፋታው እንደ አደገኛ መብረቅ ነበር። ስድቡን የለመደ ልቤ ድንፋታውን ለመደ። የመጀመሪያ ጥፊውን የተቀበልኩት የዛሬ አምስት አመት ነው። ሲመታኝ ተገረምኩ እንጂ አልተናደድኩም። ደነገጥኩ እንጂ አልተበሳጨኹም። "እንዴት መታኝ? በኔ ላይ እጁን አነሳ?" አልኩ በመደነቅ። የመታኝ ቀን ፣ ሲመሽ ጠብቆ "በሌላ ነገር ተበሳጭቼ ነበር" አለኝ። በሌላ ነገር ባይበሳጭማ አይመታኝም ነበር። ይወደኝ አይደል? ጨክኖ አይመታኝም። ሌላ ነገር ስላበሳጨው ነው የመታኝ አልኩ... አሁን ያለሁበት እንዴት እንደደረስኩ አላውቅም። መጀመሪያ ሰሞን "እንዴት ይመታኛል" ብዬ እገረም ነበር። ቀጥሎ "ዛሬ ይመታኝ ይሆን?" ብዬ መስጋት ጀመርኩ። አሁን ደግሞ ዱላውን ለመድኩ። "ከንፈርሽ ምን ሆነ?" አለችኝ። የጠየቀችኝ እያወቀች ነው። ከንፈሬ የተረነጠቀው በእሱ ቡጢ እንደሆነ ታውቃለች "መትቶኝ ነው" አልኳት እንደዋዛ።... ሰልችቶኛል። መመታቱ ሳይሆን "ዛሬም ተተመታሁኝ" ብሎ መናገር ሰልችቶኛል። "እስከመች ነው የምትታገሺው ለምን አትለዪውም?" "ልለየው አልችልም" "ትወጂዋለሽ?" "አልወደውም" "ለምን አትለየውም" አለቀስኩ። ምንድነው ያስለቀሰኝ? ዱላው አያስለቅሰኝም። አምስት አመት ተደበደብኩኝኮ። የመለየት ስጋት አያስለቅሰኝም። አብሬው እየኖኩ ተለይቼዋለሁ። እፈራለሁ። ልለየው እፈራለሁ። ከተለየሁት ይርበኛል። "ለምን አትለዪውም?" "ከተለየሁት ምን እበላለሁ? ማን ያኖረኛል?" Via ተስፋአብ ተሾመ https://t.me/Tfanos
Tesfaab Teshome pinned a photo
የዙፋን ልፊያ ለዓመቱ ምርጥ የልብወለድ መጽሐፍ እጩ ሆኗል። ይህን ፖስት ሼር አደርጉት ሕንፀት የመጽሐፍ እውቅና ስነስርዓት በየአመቱ በተለያዩ ዘርፎች መጽሐፍትን ይሸልማሉ። በዚህ ዓመትም በተለያዩ ዘርፎች መጽሐፍት ይሸለማሉ። በልብወለድ ዘርፍ ለመጨረሻው ዙር እጩ የሆኑ 3 መጽሐፍት ታውቀዋል። ከሦስቱ አንዱ የኔ መጽሐፍ ነው። ከናንተ ምን ይጠበቃል? አንደኛ ከታች ባለው ሊንክ የናንተን ድምጽ ስጡ ሁለተኛ ለሌሎች አገሩ (የዙፋን ልፊያን ያነበባችሁና ሽልማት ይገባዋል ብላችሁ የምታስቡ ድምፃችሁን ስጡ) ሊንክ 👇 https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSeZMqmGgXJMRGUIvi6ZrTucv_j4H8vTTTe1vt-hpvod4AHvnQ/viewform
አገራዊ ሰርግ ተዘጋጅቷል። ሞት የሚወለድበት ድግስ ተደግሷል። ድንቁርናና መንበር ተጋብተው ሞትን ወለዱ። አሁንም አላዋቂነትና ስልጣን ተጋብተው በላይ በላዩ ሞትን ይወልዳሉ። ዛሬም ብሔራዊ ድግስ አለ፥ መንበርና ድንቁርና ዳግመኛ ይጣመራሉ። ከሰርጉ በኋላ ሞት ይወለዳል። "እናት አባት ሲሞት በአገር ይለቀሳል እህት ወንድም ሲሞት በአገር ይለቀሳል አገር የሞተ ቀን ወዴት ይደረሳል" ማልቀስ እፈልጋለሁ። ትውልዴን የሚወክል እንባ ማፈሰስ እመኛለሁ። አንች ከፈቀድሽልኝ ማቅ እለብሳለሁ ፥ ደረት እደቃለሁ፥ ፀጉር እነጫለሁ፥አመድ በላዬ ነስንሼ "ወየው" እላለሁ። ማልቀስ ፍቀጂልኝ። በእኔ ላይ ያለሽን ስልጣን ተጠቅመሽ እንዳለቅስ እዘዢ። "እየፈረሰች ስላለች አገርህ አልቅስ ፥ ስለዘመመው ብሔራዊ ጎጆ እንባህን አፍስሰ" በዪኝ። ተመልከች አገሩን ስካር ከጠመንጃ ተባበሩ። መንበርና ጥላቻ ተዳመሩ። ተጣምሪዎቹ በእጃቸው ያለውን ስል ሰይፍ ለሞት አዳይ መልዓክ አቀበሉ። የሞት መልዓክ ለማንም አልራራም። ሰይፉን ከሰገባው መዘዘ። አሰላሳይ አንጎል የተሸከሙ አንገቶች ተቀሉ። ሰው ረከሰ፥ ሰውነት ፈረሰ። በየሜዳው ሬሳ ተከመረ። ተመልከች አገሩን። በኛና በፖለቲከኞቻችን መካከል ያለው ግኑኝነት የዲዳና የእውር ነው። ችግራችንን እንዳናስረዳቸው መናገር የተሳነን ነን። ሁኔታችንን አይተው እንዳይገነዘቡ ማየት የማይችሉ ናቸው። ዝናብ አልነበረም፥ ሰፈራችን ግን ጨቅይቷል። መሬታችንን ያጨቀየው የሰው ደም ነው። የደም ኩሬ ሲፈጠር ፥ ሬሳ እንደ ቆሻሻ ሲከመር ፥ ሰው ከቁስ በታች ሲሆን ማልቀስ የለብኝም? ማልቀስ እፈልጋለሁ። ደረት እየደቃሁ ፥ ፀጉር እየነጨሁ ፥ ልብሴን እየቀደድኹ ማልቀስ እፈልጋለሁ። ብዕሬን ያነሳሁት ናፍቀሽኛል ልልሽ ነበር። አይንሽን ካየሁት ስንት ዘላለም ሆነኝ? ጡትሽን አይቼ ከተገረምኩ ስንት ዘላለሞች ነጎዱ? በደቂቃ ሽራፊና በዘላለም መካከል ያለሽው ልዩነት አንቺ ነሽ። ካንቺጋ ስሆን ዘላለም ጥቂት ነው። ያላንቺ የማሳልፈው አንድ ቀን ከዘላለም ክምር ትኬሻ ይለካካል። ድምፅሽን ከሰማሁት ስንት ዘላለም አለፈ? አይንሽን ካየሁት ስንት ዘላለም ተቆጠረ? በጡትሽ ከተገረምኩ ስንት ዘላለም ነጎደ? በፀጉርሽ ከተደነቅኹ ስንት ዘላለም ሆነ? "ናፍቀሽኛል" ልልሽ ብዕር ባነሳም ናፍቆቴን ልነግርሽ አቅም አጣሁ። በየሜዳው የወደቁ ታናናሾቼ አጥንት መንፈሴን ወጋ። ሀዘን ሸነታተረኝ። ስለ ውብ ጡቶችሽ እያሰብኩ ፈገግ ባልኩበት አፍታ ፥ ደመ ከልብ የሆኑ እኩዮቼ በአይኔ ተሳሉ። ፈገግታዬ ከሰመ፥ አይኔን እንባ ጋረደው። እውድሽ አይደል? ዘመን ነው ጠላታችን። እንዲህ ባለ ደም አፍቃሪ ዘመን መፈጠር አልነበረብኝም። ዘመኔ ሌላ ቢሆን ኖሮ ሰማይ በሚያክል ብራና መወድስ እፅፍልሽ ነበር። ያለነው ሰው በረከሰበት ዘመን ባይሆን፥ ለሰማይ አዕፋት ስላንቺ እተርካለሁ። "የውዴን ድምፅ ስሰማ እታደሳለሁ፥ ድምጿ መድሃኒቴ ነው" ብዬ እናገር ነበር። በዛፎች መካከል ተገኝቼ ስለ ፀጉርሽ እተርክ ነበር። ነበር... ዘመን ነው ጠላቴ። ፍቅሬን ልነግርሽ ብዕር ባነሳሁበት አፍታ፥ በየሜዳ የወደቁ ታናናሾቼን እያሰብኩ እንዳለቅስ ያደረገኝ ዘመን ጠላቴ ነው። ለከንፈርሽ መወድስ ላቀርብ ስዘጋጅ ፥ በየሜዳ የፈሰሰ ደም አስባለሁ። ተመልከች አገሩን ጎበዙ እንደዘበት በወጣበት ቀርቷል። ወላጅ ጧሪ ልጁን በዋዛ ቀብሯል። የሀዘን ስል ካራ እናትን ገደለ። የመሞትን ተራ አባት ተከተለ። ተመልከች አገሩን በአገሩ ድግስ አለ። ብሔራዊ ሰርግ ነው። ስልጣን ከድንቁርና ተጋብተዋል። የሞት መልዓክ ከሙሽሮቹ መግደያ ፍቃድ አግኝቷል። ገዳዩ ሰይፍን ከአፎቱ መዟል። ብርቱ ይቀጠፋል፥ አዛውንት ይወድቃል፥ ጎበዙ ይረግፋል ፥አዳጊ ይቀጫል። እባክሽ አለሜ ፥ ከዚህ ሁሉ መዓት አድኚኝ። መሄጃ የለኝም። መሸሸጊያዬ አንቺ ነሽ። በእቅፍሽ ስሆን እድናለሁ። እቅፍሽ የሀዘኔን ተራራ ይንደዋል።የፍርሄቴን አለት ይሰብረዋል። ከመከራ ይከልለኛል። ፍልሚያ እና መቀጠፍ ፥ በበዛበት ሐገር መሸሸጊያ ሁኚኝ ፥ በእቅፍሽ ልሰወር አለሜዋ፥ እንደማህተም በልብሽ እንደማህተም በክንድሽ አኑሪኝ። ፍቅር ከሞት የበረታች ናት Via ተስፋአብ ተሾመ https://t.me/Tfanos
ለቅዳሜ ምሽት ቀጠሮ እንያዝ... በርዕዮት ኪን ልዩ ፕሮግራም ተዘጋጅቷል። አራት መጽሐፍትን በኢንተርኔት እንመርቃለንተ ህይወት ተፈራ ፥ ይፍቱስራ ምትኩ ፥ አድህኖም ምትኩ እና እኔ አለን። ደጋሹ Tewodros Tsegaye ነው። ቴዲና የርዕዮት ቡድን ስለ ሚያዘጋጀው ድግስ ማብራሪያ ያስፈልግ ይሆን? ጥሩ ድግስ እንደሚሆን ሁላችንም እናውቃለን። ቅዳሜ ሐምሌ 18 ከምሽቱ 12 ፡30 ጀምሮ እንገናኛለን!
ቀጣይ አመት ምግብ ይኖረን ይሆን? አይርበንም ይሆን? እንጃ ብቻ ዛሬ ጠዋት ከቤት ስወጣ ወደ ሰማይ አንጋጠጥኩ። ይህ ሰሞንኛ ልማዴ ነው። በየጠዋቱ ሰማዩን አየዋለሁ። "ዛሬ ይዘንብ ይሆን?" እላለሁ። ድንገት የገበሬ አመል አመጣሁ። መዝነብ አለመዝነቡ የሚያስጨንቀው ሰው ሆንኩ። ልጅ እያለሁ ፥ ቤተሰቦቼ ከዘመድ አዝማድ የሚያደርጉት ውይይት ላይ የማይረሳ ጥያቄ ነበር። "እናንተጋ ይዘንባል?" ይባባላሉ። "እናንተጋ ይዘንባል ወይ?" የሚለው ጥያቄ አይቀሬ ጥያቄ ነው። ከልጅነት ከፍ ባልኩበት እድሜ የጥያቄው ዋጋ አይገባኝም ነበር። ሰዎች ወሬ ለማስቀጠል ብቻ የሚወራወሩት ጥያቄ ይመስለኝ ነበር። "ይዘንባል ወይ?" የሚለው ጥያቄ ግዙፍ ነው። ጥያቄው ስለዘንድሮ ቢመስልም ስለ ዘንድሮ አይደለም። ስለ ቀጣይ አመት እጣፈንታ የሚደረግ ውይይት ነው። "ይዘንባል ወይ?" ማለት "ቀጣይ አመት ምግብ ይኖረናል ወይ?" ማለት ነው። በዚህ አመት ዝናብ ከሌለ በቀጣይ አመት ምግብ የለም! እንደ ሐገር ግብርና ላይ ጥገኛ ነን። ግብርናችን ደግሞ ኋላ ቀር ነው። በምግብ ራሳችንን አልቻልንም። በጎተራችን የአደጋ ግዜ መጠባበቂያ የለም። አንድ ክረምት ዝናብ ከቆመ ሚሊዮኖች ለረሃብ ይጋለጣሉ። ካልዘነበ አይዘራም። ካልተዘራ አይታጨድም። ዘርተን ካላጨድን ምግብ የለም። ክረምት በደረሰ ቁጥር አያቴ "እናንተጋ ይዘንባል?" ይል ነበር። አጎቶቼ "እናተጋ ይዘንባል ወይ?" ይሉ ነበር። እናንተ ያላችሁበት አካባቢ ይዘንባል? ገበሬው በጦርነት እየታመሰ ነው። መታረስ የነበረበት መሬት ለጦርነት ቀጠና ውሏል። በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ የዘንድሮ ክረምት እየዘነበ አይደለም። ላይ ላዩን ስታይ ክረምት ደስ አይልም። ነገር ግን ክረምት መጥላት በኛ አያምርም። መለኮታዊ አቅም እንዲኖረኝ እመኛለሁ። አንዳች ተአምር የማድረግ አቅም ቢኖረኝ ዝናብ አዘንብ ነበረ። ከሰኔ ጀምሮ "ዛሬ ይዘንብ ይሆን?" እያልኩ ነበር። ምናልባት እያረጀሁ ይሆናል። በክረምት ወራት ዝናብ ሲጠፋ ልቤ ይሸበራል። ይዘንብ ይሆን? Via ተስፋአብ ተሾመ https://t.me/Tfanos
ትውልድ አይደናገር ፥ እኛም እንናገር እግር ኳስ ቅሪላ ማልፋት ብቻ አይደለም። የጠገበ ፈረንጅ እርግጫም አይደለም። እግር ኳስ የብዙ ነገሮች ድምር ውጤት ነው። የግለሰቦች ተሰጥኦ ፥ የቡድን ስራ ፥ የአመራር ጥበብ ፥ ስነልቦናዊ ጥንካሬ ፥ የአእምሮ ፍጥነት ፥ የአካል ብቃት ፥ አልሸነፍ ባይነት... ወዘተ ተጣምሮ እግር ኳስን ይፈጥራሉ። ከላይ ከተጠቀሱት ያለ አንዱ ዘመናዊ እግር ኳስ የለም። እግርኳስ እንደ ቡድን ከፍታው ላይ ሲደርስ የጋርዲዮላን ባርሴሎና ይመስላል። እንደ ግሰለሰብ የእግር ኳስ ከፍታ ልዮ ሜሲ ነው። ሊዮኔል ሜሲ ፥ የማይገረሰስ ንጉሥ! ለመጀመሪያ ጊዜ ሜሲን ያየሁት የዛሬ 21 አመት ነበር። እንደሁልጊዜው ከአባቴጋ ኳስ ልናይ ሄደን። እጄን ይዞኝ Dstv ቤት ወሰደኝ። 30 ቁጥር የለበሰ ፥ ፀጉሩ የተደፋ ልጅ እግር ተጫዋች አየሁ። ግራ እግሩ ተአምር ይሰራል። ሮናልዲኒሆን ለማየት ሄጄ 30 ቀጥሩን አየሁ። "ማነው ይሄ ልጅ?" አልኩት አባቴን። "ሜሲ ይባላል" አለኝ። ስሙን ለመሸምደድ ወሰንኩ። ለአመታት እግር ኳስ አይቻለሁ። እግርኳስ የሰጠኝ ደስታ ብዙ ነው። እግር ኳስ በስሜት ከፍ አድርጎኛል። ሜሲ ደግሞ እያንዳንዱ ስሜት እንዲሰማኝ አድርጓል። "ሜሲን ሳየው አለቅሳለሁ" የሚሉ አሉ። እንዲህ የሚሉ ሰዎች እውነታቸውን እንደሆነ አውቃለሁ። እግር ኳስ ላይ እንደ ሜሲ ስሜታዊ የሚያደርገኝ ሰው የለም። ሁሉንም ስሜቶች እንዲሰማኝ አድርጓል። ሜሲን በተመለከተ ስህተት ሰርቼ አውቃለሁ። የ45 ደቂቃ ብቻ ስህተት! 2010 ላይ አርሰናል ከባርሳ ሲጫወት የአርሰናል ደጋፊ ነበርኩ። ሜሲን በተመለከተ የመጀመሪያና የመጨረሻ ስህተት ሰራሁ። ሜሲ ኳስ በያዘ ቁጥር ሰቀቀን ነበር። ከሜሲ ተቃራኒ ቡድን የመደገፍን ሰቀቀን አወቅኩ። ከእረፍት በኋላ ቡድን ቀይሬ ባርሳን ደገፍኩ። በእርግጥ ባርሴሎናን ሳይሆን ሜሲን ነው የደገፍኩት። ሜሲን በምወድበት መጠን የወደድኩት ቡድን እንኳን የለም! ሜሲ ታታሪ መሆኑን የሚረሱ አሉ። ሜሲ ጠንካራ ሰራተኛ እንደሆነ የማያውቁ አሉ። ይህ የለየለት ውሸት ነው! ሊዮ ሜሲ በየጊዜው ይደበደብ ነበር። የግዲያ ሙከራ ሲደረግበት ቆይቷል። (እሱ ላይ የተሰሩ ፋውሎችን ቪዲዮ ፈልጋችሁ ተመልከቱ) በእኒያ ሁሉ ድብደባዎች ያልተጎዳው ለምንድነው? ሜሲ ገና በለጋነቱ በጉዳት መሰናበት ነበረበት። ልክ እንደ አንሱ ፋቲ ፥ ቦያን ክርኪች ፥ ጃክ ዌልሼር... ወዘተ ባክኖ የቀረ ተሰጥኦ መሆን ነበረበት። ነገር ግን ያን ሁሉ ዱላ ተቋቁሞ አለፈ። ምክኒያት... ከጨዋታ በኋላና በፊት በአግባቡ ልምምድ ይሰራል። ሊዮ ቀደም ባለው ዘመን ቅጣት ምት በመምታት አናውቀውም። ከሱ ይልቅ ዴኮ ሱዛ፥ ሮናልዲኒሆ... ወዘተ ነበሩ። አሁን ግን ምርጡ የቅጣት ምት አስቆጣሪ ሆነ። ለምን? ጠንክሮ ስለሰራ ፥ ስለተለማመደ። ሊዮን እንወደዋለን፥ እናደንቀዋለን። በእግርኳስ ማግኘት ያለብንን ሁሉ ሰጥቶናል። ድሪብል ለሚወድ ምርጡ ድሪብለር ነው። ከግብ ክልል ውጭ የሚቆጠር ግብ ለሚወድ ቁጥር አንዱ ሜሲ ነው። ፕሌይ ሜከር ከወደዳችሁ ሜሲ ዋነኛው ነው። ጎል ለሚወድ የጎል ምንጭ ነው። ሜሲ ሮኒልዲኒሆ ፥ ዚዳን እና ሮናልዶ ተቀላቅሎ የተፈጠረ ልዩ ፍጡር ነው። ሜሲን ከወጣትነቱ ጀምሮ ስላየሁት እድለኝነት ይሰማኛል። የወጣቱ ሜሲ ምስል በአይኔ ተስሏል። አሯሯጡ በአይኔ ተስሏል ፥ ኳስ አገፋፉ በአይኔ ተስሏል ፥ አይረሴ ጎሎቹ በአይኔ ተስለዋል። እንኳን ኳስ ወደድኩ። ኳስ ባልወድ ኖሮ ሜሲን አላውቀውም ነበር። እናመሰግናለን ሊዮ! አይኖቻችንን በእንባ ስለሞላኸው እናመሰግናለን አይረሴ ምሽቶችን ስለ ሰጠኸን እናመሰግናለን ስለ ግራ እግርህ ተአምር እናመሰግናለን ስለ ፈጣን አእምሮህ እናመሰግናለን እናመሰግናለን ሊዮ! Via ተስፋኣብ ተሾመ https://t.me/Tfanos
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ዛሬ አትሮኖስ ነበርን። ስለ መጽሐፌ "ዙፋን ልፊያ" አወራን። ጥሩ ውይይት ነበረን። በበጎ አስተያየቶች ልቤ ሞቋል፥ እንዲታረም በተነገሩኝ ነጥቦች ተምሬበታለሁ። እንኳን ተወያየን ፎቶ ፥ ዶክተር ፍርድአወቀ ማሞ (የቀይ ባርህ ሲቀላ መጽሐፍ ደራሲ) ፣ አርቲስት ዘላለም ምፅላል (ሱዳን ምንልታዘዝ ድራማ ላይ)፣ ሊዲያ ተስፋዬ (ደራሲ) ፣ ተስፋዬ አድሃኖም (Phd የነገረመለኮት እና የቋንቋ መምህር) እና ተስፋአብ ተሾመ
видео или голосовое, без подписи
🤔
"የሜሲ ቡድን ተሸነፈ" ብለው ተስፋ ካደረጉ በኋላ አርጀንቲና ማሸነፏ ያረካል። ተስፋቸው ገደል ሲገባ ደስ ይላል። መጀመሪያ የፖርቱጋል ደጋፊ ነበሩ፥ ቀጥለው ፈረንሳይ ፥ ቀጥለው እንግሊዝ... ሜሲን ሊያስቆም ይችላል ብለው ያሰቡትን ሁሉ ደግፈዋል። የሜሲ እግሮች ተስፋቸውን ደጋግሞ ቀምቷል። እየመሩ ተስፋ አድርገው ሲሸነፉ ደስ ይለኛል (በነገራችን ላይ ሜሲ የምንፈልገውን ሁሉ ሰጥቶን ጨርሷል። በዚህ አለም ዋንጫ ሜሲን በመጥላት የነሆለሉ በስኬቱ ሲበሽቁ ማየቱ ነው የሚያስደስተኝ
አርጀንቲና በኢ-ፍትሐዊ መንገድ ብታሸንፍ ደስ ይለኛል። ኦፍ ሳይድ ጎል አግብተው ቢፀድቅ ፥ የማያሰጥ ፔናሊቲ ተሰጥቷቸው ቢያገቡ ፥ እንግሊዝ ንፁህ ጎል ቢሻርባት ደስ ይለኛል። ለምን? ሜሲን የሚጠሉ ሰዎች በደንብ መናደድ አለባቸው። ጨጓራቸው ሲላጥ ማየት እፈልጋለሁ!
ጡቴ መውረድ የጀመረ ይመስለኛል። መቀመጫዬ እንደ ድሮው እንዳልሆነ ይታወቀኛል። ጉንጮቼ ማዲያት ማውጣት ጀምረዋል። ከናፍሮቼን ሲጃራ አጥቁሯቸዋል። እያረጀው ይሆን? የከፋ ቀን ይመጣል። በተፈጥሮዬ ውብ የነበርኩበት ቀን አልፎ በሜካፕ ጉልበት እንኳን ማማር የማልችልበት ቀን ይመጣል። . . . አረጃለሁ። መክሰም አልፈልግም። በፍጹም መክሰም አልፈልግም። ተወልጄ ሳልጨርስ መሞት አልፈልግም። ኑሮዬን ሳላጣጥም ዘመኔ እንዲያከትም አልሻም። በህይወቴ ዛሬ የሚባል ቀን ኖሮኝ አያውቅም። የሆነ ወቅት ላይ ስለ ነገ ሳስብ ዛሬዬ አመለጠኝ። ትላንት ያለ ልክ በተስፋ እና ህልም ውስጥ ገብቼ የአሁን ሃያልነት ተረሳኝ። ነገ ያልኩት ቀን ሲደርስ ደግሞ ተስፋ ካደረግናቸው ህልሞቻችን መካከል ብዙዎቹ እንደ ጉም እንደማይጨበጡ ገባኝ። በለጋነቴ ሁሉም ህልሞች የሚሰምሩ ይመስለኝ ነበር። የሆነኛው የእድሜ ዘመን ላይ ሁሉም ነገር የሚሳካ ይመስላል። ጨረቃን የግላችን ለማድረግ እንመኛለን። አለምን ለመቆጣጠር እናልማለን። ባለጠጎች እንደምንሆን እርግጠኞች ነበርን፡፡ ተዓምራዊ የፍቅር ህይወት እንደሚኖረን፣ ዝናችንም ወደር እንደማይገኝለት እናስባለን። ሃሳባችን እንደሚሳካ አንጠራጠርም። እውነታው ግን ሩቅ የመሰለን ነገ ሩቅ አይደለም። እድሜ እንደምናስበው ረጅም አይሆንም። ልጅ ሳለሁ ፈጥኜ ወጣት እንደምሆን መች ገመትኩ? ከልጅነት ወደ ጉርምስና ከጉርምስናም ወደ ወጣትነት የተሸጋገርኩበትን ፍጥነት አሰላሁት። ሩቅ አይደለም። ልጅ ሳለሁ በጉርምስና እድሜ ላይ በደረሱ ታላቆቼ ቀንቼ ነበር። ስለጎረምሶቹ አስቤ ሳልጨርስ ጎረመስኩ። ወጣቶችን ተመልክቼ የወጣትነት ዘመን ላይ ስለመድረስ መመኘት ከመጀመሬ ወጣት ሆኜ ተገኘሁ። ጉልምስናና ሽምግልናም ሩቅ አይደሉም። በእርግጠኝነት ስለወጣትነቴ አስቤ ሳልጨርስ እጎለምሳለሁ። በመጎልመሴ መደነቅ ስጀምር ደግሞ አረጃለሁ። ፈጥኜ በማርጀቴ ተገርሜ ፣ አይኖቼን ከድኜ ዘመኔን ማሰብ ልጀምር ስል እድሜዬ ያከትማል። ጊዜ ፈጣን ነው። ከ #ክራራዊ_ህይወት መጽሐፍ የተወሰደ ደራሲ ተስፋአብ ተሾመ አሳታሚና አከፋፋይ ጃፈር መጽሐፍት https://t.me/Tfanos
"እናቴ ሦስቴ አግብታ ሦስቴ ፈታለች። ከእህቴ እና ከወንድሜ ጋር አባት እንደማንጋራ ታውቂያለሽ። እናቴ አዲስ ሕይወት በጀመረች ቁጥር በትዳሯ እንደምትፀና የምትወራረድ ቢሆንም፣ አዲሱ ሕይወት ብዙም ሳይቆይ መዝመም ይጀምርና የመጠገን እድልን ሳያገኝ ይፈርሳል።ይህ እንዴት ሆነ?›› ‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል›› ‹‹ወንድሜ ለትዳር ምንም አይነት መጓጓት እንዳልነበረው ታውቂያለሽ... እማማና ዘመዶቿ ወትውተውት ካገባ በኋላ በሦስት ዓመቱ ተፋታ። ከትዳሩ መፍረስ በኋላ ለገዛ ልጁ እንኳን ግድ የለሽ ሆኖ የተገለለ ኑሮ እየገፋ እንደሆነ ታውቂያለሽ።... ይህ እርግማን አይደለም?›› ‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል›› ‹‹እህቴ ቁጥብ እና በራስ መተማመን ያላት ሴት እንደነበረች መመስከር እንደምትችይ አውቃለሁ። ስለ መልኳ ሁሉም ሰው ይናገራል። መብራት ከተማ ውስጥ የእህቴን ያህል ቆንጆ ማግኘት እንደማይቻል እወራረዳለሁ፡፡ ትዳር ከመሠረተች በኋላ ግን ሕይወቷ ተመሳቀለ። የወለደችው ልጅ ጡት ሳይጥል ትዳሯ ፈረሰ። በዚህ የተነሳ ማንንም ማመን የማትችል፣ በራስ መተማመኗን ያጣች ሆናለች። በሃዘኗ ብርታት የተነሳ ውበቷ ከድቷታል። የተሰበረች ሴት ነች... ይህ እርግማን አይደለም?›› ‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል›› ‹‹የእኔን ታሪክ ታውቂዋለሽ። የፍቅር ሕይወቴ በመለየት ይደመደማል። ጀመርኩ ስል ይቋረጣል። የገነባው ሲመስለኝ ይፈርሳል። አንዴ አይደለም። በተደጋጋሚ እንጂ!.... ይህ እርግማን አይደለም?›› ‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል›› ‹‹ስለ አያቴ የትዳር ሕይወት ነግሬሽ አውቃለሁ?›› ‹‹ነግረሽኝ አታውቂም›› ‹‹የእማዬ እናት አራቴ አግብታ አራቴ ፈታለች›› ‹‹ይህን አላውቅም ነበር›› ‹‹የእናቴ ታናሽ እህት ሁለት ጊዜ ትዳር መስርታ ሁለት ጊዜ ትዳሯ ፈርሷል፡፡ ሁለቱ ልጆቿ ከሁለት ባሎች የተገኙ ናቸው፡፡ ይሄ ያለጥርጥር የዘር እርግማን ነው›› ‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል›› ‹‹ከአያቴ ጀምሮ እስከ እኔ ድረስ ታሪካችን ተመሳሳይ የሆነው በአጋጣሚ አይደለም። በእርግጠኝነት ከዘር የሚተላለፍ የቤተሰብ እርግማን አለብን›› ‹‹እርግማን ላይሆን ይችላል›› ‹‹ገደል ግቢ›› ‹‹ንፁህ ሙች እርግማን አይደለም›› ‹‹ገደል ግቢ አልኩኮ›› ከ #የዙፋን_ልፊያ መጽሐፍ የተወሰደ ደራሲ ተስፋአብ ተሾመ አሳታሚና አከፋፋይ ጃፈር መጽሐፍት https://t.me/Tfanos
ጡቴና ዳሌዬን ወደ ገንዘብ ለመመንዘር ተሰለፍኩ። ውበቴን ሸጬ ገንዘብ ለመቀበል ወደ ገበያ ወጣሁ። በገበያ መካከል እርቃኔን ቆምኩ። "ይሄን የመሰለ ውበት ኖሮሽ እንዴት ትቸገሪያለሽ?" አሉኝ። ቆንጆ ሴት ችጋር ሊያገኛት አይገባም ሲሉኝ አመንኳቸው። ውበት እና መከራ ደመኛ እንደሆኑ ሰበኩኝ፥ ስብከታቸው በዝግታ ወደ ልቤ ሰረገ። መሰረታዊ ፍላጎቴ የተሟላ ነበር። መኪና ባይኖረኝም የታክሲ ተቸግሬ አላውቅም። ምግብ ባላማርጥም አልራብም። ቤት ባይኖረኝም የቤት ኪራይ መክፈል አይቸግረኝም። በባንክ የምቆጥበው ባይተርፈኝም እዳ ገብቼ አላውቅም። በፍስሃ ክንዶች ባልንተራስም ሃዘን አይደቁሰኝም። ችጋር እንደሚደቁሰኝ የነገሩኝ ሌሎች ናቸው። ውበቴን ባዳነቁ አፍታ "አንቺን የመሰለች ልጅ ይህ ኑሮ አይገባትም" ይሉኛል። ቆንጆ ሴት ሰርታ መኖር አይገባትም የተባለ ይመስል ከንፈር መጠጡልኝ። አስተያየታቸው ሲደጋገም ለራሴ ማዘን ጀመርኩ። የመከራ ብዛት በቡጢ እንደነረተኝ ተሰማኝ። "ውብ ሆኜ የምቸገረው ለምንድነው?" አልኩ። ስለ ውበቴ ሳስብ ከራሴ ፍቅር ያዘኝ። ስርጉድ ጉንጬን፥ ዞማ ፀጉሬን አፈቀርኩ። ዳሌዬን አፈቀርኩ። ጡቶቼን አፈቀርኩ። "መቸገር አይገባሽም" ይሉኝ ነበር። ያሉኝን ሁሉ አመንኩ። ድህነቴን በፀጋ መቀበል ቸገረኝ። "ኑሮሽ መልክሽን አይመጥነውም" ማለት ምን ማለት እንደሆነ ያወቅኩት ዘግይቼ ነው። ራሴን ለሽያጭ እንዳቀርብ እየተጠየቅኩ እንደሆነ የተረዳሁት ራሴን ለገበያ ካቀረብኩ በኋላ ነበር። አንድ ነገር ገንዘብ እንዲያመጣ ከተፈለገ መሸጥ አለበት። መመንዘር ይኖርበታል። ውበቴም ገንዘብ እንዲያመጣ መመንዘር ነበረበት። ለሽያጭ ያልቀረበ ነገር ገንዘብ አያመጣም። "በዚህ ውበትሽ...." የሚለው ስብከት ካሸነፈኝ በኋላ "በዚህ ውበቴ መድህየት አይገባኝም" አልኩ። ራሴን ለሽያጭ እያቀረብኩ እንደሆነ አልገባኝም ነበር። ገላዬን ቁስ ለማድረግ እንደወሰንኩ አልገባኝም ነበር። ለኢ-መደበኛ ሽርሙ^ጥና እንደታጨሁ አልገባኝም ነበር። አሁን በገበያ መካከል እርቃኗን እንደ ቆመች ወይዘሮ ሆኛለሁ.... Via ተስፋአብ ተሾመ https://t.me/Tfanos
ሜሲ ለወደፊቱ የተዋጣለት አሰልጣኝ የሚሆን ይመስለኛል። ሜሲን ለመጀመሪያ ጊዜ ያየሁት የዛሬ 21 አመት ነበር። ላለፉት አመታት በየአመቱ ተአምር እያሳየን ቀጥሏል። እንደ ተጫዋች ማሳካት ያለበትን ሁሉ አሳክቷል። ኳስ መጫወት ሲያቆም ምን ይሆናል? ጥሩ አሰልጣኝ የሚሆን ይመስለኛል። ጥሩ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ሁሉ ጥሩ አሰልጣኝ ይሆናሉ ማለት አይደለም። ማራዶናን ጨምሮ በርካታ ጥሩ ተጨዋቾች አሰልጣኝ ሲሆኑ ባክነዋል።... የሜሲ ግን ይለያል። ሜሲን ለአመታት ሲጫወት የተመለከተው ሁሉ ጨዋታ የማንበብ ብቃቱን ያውቃል። በዝግታ እየተራመደ ሜዳውን ስካን ያደርጋል። የተጫዋቾችን አቋቋም ያጠናል ፥ የተጋጣሚን ክፍተት ይቃኛል። ሜሲ ሳያቋርጥ ወክ እያደረገ ሜዳውን ያካልላል፥ ጨዋታውን ያነባል።.... ከዚያን በኋላ ምን እንደሚያደርግ ይታወቃል። ሜሲን 30 ቁጥር ከሚለብስበት ዘመን ጀምሮ ሳየው አድጌያለሁ። ያኔ ፈጣን ራጭ ነበረ። በጊዜ ሂደት ፍጥነቱን ቢያጣም አእምሮው ስል ነው። ያ ስልነት በየጊዜው እየጨመረ መጥቷል። ሜዳ ውስጥ ያለው የጨዋታ ንባብ ለወደፊቱ ጥሩ አሰልጣኝ ያደርገው ይሆናል። እንደ ጋርዲዮላ አዳዲስ አስተሳሰቦችን ላያስተዋውቀን ይችላል። ነገር ግን ጥሩ ፕራግማቲክ አሰልጣኝ የሚወጣው ይመስለኛል። (አልዓዛር አስግዶም "ሜሲን ስለምንወደው እንስገበገብለታለን" ብሏል። ከ20 አመት በላይ ሲጫወት አይተነው አልጠገብነውም። ቢሆንም ኳስ ማቆሚያው ደርሷል። ማን ያውቃል አሰልጣኝ ሆኖ ሌላ አይነት ሜሲን ያስተዋውቀን ይሆናል) Via ተስፋአብ ተሾመ https://t.me/Tfanos