tgindex
🎤ቦርፎሪኮን🎸

🎤ቦርፎሪኮን🎸

Статистика

♦️ #የዚህ_የቴሌግራም_ቻናል_አላማ ♦️ ለራሱ ለቤተሰቡ እና ለሀገሩ የሚጠቅም ፤ በመልካም ስነ ምግባር የታነፀ ፤ ራሱን በፅድቅ እቃ ጦር ያስታጠቀ ፤ በቅድስና የተያዘ ፤ ራሱን የሚገዛ እንዲሁም ፍቅርን የሚኖር ትውልድን ማፍራት ነው። ቦርፎሪኮን ቻናል , ኢትዮጵያ ለአስተያየት, @john11 ይጠቀሙ። We have weekly #maranata program in Sunday at 3:00 pm

Последний пост
13 авг.
Последнее чтение
14 авг.
Постов за неделю
1
Всего постов
23
Тип
открытый
Язык
ti
Категория
Криптовалюты (по похожим)
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
1 563
−3 за 5 дн.
Сутки
0
0,00%
Неделя
—
 
Месяц
—
 
Просмотров на пост
237
23 постов
Вовлечённость
15,2%
к подписчикам
Постов в день
0,1
всогО 23
УпОПинаниК
0
канаНОв
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
25
1/48двое суток
28
1/72трое суток
30

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 13 авг.29иС yekal_sink

    йоС пОдписи

  • 11 авг.41иС yekal_sink

    ራእይ 5 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ በዙፋኑ ላይም በተቀመጠው በቀኝ እጁ ላይ በውስጥና በኋላ የተጻፈበት በሰባትም ማኅተም የተዘጋ መጽሐፍን አየሁ። ² ብርቱም መልአክ፦ መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ማኅተሞቹንም ይፈታ ዘንድ የሚገባው ማን ነው? ብሎ በታላቅ ድምፅ ሲያውጅ አየሁ። … ⁴ መጽሐፉን ሊዘረጋ ወይም ሊመለከተው የሚገባው ማንም ስላልተገኘ እጅግ አለቀስሁ። ⁵ ከሽማግሌዎቹም አንዱ፦ አታልቅስ፤ እነሆ፥ ከይሁዳ ነገድ የሆነው አንበሳ እርሱም የዳዊት ሥር መጽሐፉን ይዘረጋ ዘንድ ሰባቱንም ማኅተም ይፈታ ዘንድ ድል ነሥቶአል አለኝ።

  • 13 июл.107иС LivingGodchurch

    " እንደ ልጆችም ከእናንተ ጋር። ልጄ ሆይ፥ የጌታን ቅጣት አታቅልል፥ በሚገሥጽህም ጊዜ አትድከም፤ ጌታ የሚወደውን ይቀጣዋልና፥ የሚቀበለውንም ልጅ ሁሉ ይገርፈዋል ብሎ የሚነጋገረውን ምክር ረስታችኋል። ለመቀጣት ታገሡ፤ እግዚአብሔር እንደ ልጆች ያደርግላችኋልና፤ አባቱ የማይቀጣው ልጅ ማን ነው? ነገር ግን ሁሉ የቅጣት ተካፋይ ሆኖአልና ያለ ቅጣት ብትኖሩ ዲቃላዎች እንጂ ልጆች አይደላችሁም። ከዚህም በላይ የቀጡን የሥጋችን አባቶች ነበሩን እናፍራቸውም ነበር፤ እንዴትስ ይልቅ ለመናፍስት አባት አብልጠን ልንገዛና በሕይወት ልንኖር በተገባን? እነርሱ መልካም ሆኖ እንደ ታያቸው ለጥቂት ቀን ይቀጡን ነበርና፥ እርሱ ግን ከቅድስናው እንድንካፈል ለጥቅማችን ይቀጣናል። ቅጣት ሁሉ ለጊዜው የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፥ ዳሩ ግን በኋላ ለለመዱት የሰላምን ፍሬ እርሱም ጽድቅን ያፈራላቸዋል። ስለዚህ የላሉትን እጆች የሰለሉትንም ጉልበቶች አቅኑ፤ ያነከሰውም እንዲፈወስ እንጂ እንዳይናጋ፥ ለእግራችሁ ቅን መንገድ አድርጉ።" (ዕብ 12+5-13) ሐምሌ 06/2018 ዓም

  • 27 июн.13611иС yekal_sink

    https://youtu.be/uacCc22VIWk?si=lnl5p9C76Jo3d5AT 🎥

  • 1 мая229иС yekal_sink

    የአንተ መልእክት ነው ላንቺም ይሆናል !

  • 27 апр.2132иС yekal_sink

    ዛሬ ሰኞ 19/8/18 እግዚአብሔር ስለአንተ ፣ ስለአንቺ በታላቅ ቅናት ይወርዳል! 🙏✨ ዘካርያስ 8 📖 ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ² የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ስለ ጽዮን ታላቅ ቅንዓት ቀንቻለሁ፥ በታላቅም ቍጣ ስለ እርስዋ ቀንቻለሁ🔥። ³ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ ጽዮን ተመልሻለሁ፥ በኢየሩሳሌምም መካከል እኖራለሁ🏙️፤ ኢየሩሳሌምም የእውነት ከተማ ትባላለች🌟፤ የሠራዊትም ጌታ የእግዚአብሔር ተራራ የተቀደሰ ተራራ ይባላል⛰️። የማይሆን የሚመስሉ ነገሮች ይሆናሉ አይዞህ ፣ አይዞሽ መከራን እንዳለፈውሃ ትረሰዋለህ

  • 25 апр.189иС yekal_sink

    Revival(#ተሀድሶ )***ክፍል 3                                 በፓስተር ጆን የሀገራችን ቤተክርስቲያን አሁን ያለችበት ሁኔታ  ብዙ ጥናቶች  እንደሚያሳዩት ፡- • ሀገራችን ውስጥ ዘረኝነቱ ፣ኢፍትሓዊነቱ፣ ሙስናው፣ የሰዎች በገፍ እና በግፍ መገደል ፣ ሀገራዊ አንድነት መላላት…ወዘተ መገለጫ ሆነዋል ፡፡ ቤተክርስቲያን በትልቅየሞራል፣ የአመራር፣ የጸጋ ስጦታዎች አጠቃቀም፣ በአስተምህሮ፣ በአገልግሎት፣ …ትልቅ መበላሸትና መፍረስ ውስጥ  ገብታለች ፡፡ ምዕመኑ ለስህተት ትምህርት ተዳርጓል፤ መዝሙር እንጂ ደቀመዝሙርነት መርዶአል ፡፡ የነህምያ ወንድም አናኒ “ሰውም  ቅጥሩም ፈርሷል”  የኢየሩሳሌም ቅጥር ፈርሶአል ›› ነበር ያለው፡፡   ራእ 2፡  4-5 በኤፌሶን ወዳለው ወደ ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ! ⁴ ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና። ⁵ እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ። የእግዚአብሔር ዝምታ ያለማየት ያለመመልከት ያለመፍርድ ችግር ሳይሆን የምህረቱ ታላቅነትን ያሳያል ። ሌላው:-...........ይቀጥላል ..... t.me/borforiconn

  • 20 апр.1731иС yekal_sink

    Online አሁን ላላችሁ 📡 ትንቢተ ዳንኤል 2:21 📖 --- ²¹ ጊዜያትንና ዘመናትን ይለውጣል፤ ነገሥታትን ያፈልሳል፥ ነገሥታትንም ያስነሣል፤ ጥበብን ለጠቢባን እውቀትንም ለአስተዋዮች ይሰጣል። ✨👑

  • йоС пОдписи

  • 6 апр.261иС yekal_sink

    መጋቢት 28/07/18 ክፍል (2)         * * *ለሪቫይቫል (ተሀድሶ )***                                  በፓስተር ጆን ምን አድርጌአለሁ ብሎ ራሱን የሚጠይቅ የለም የነቢዩ የኤርምያስ ጩኸት !                  8:6-12 << አደመጥሁ ሰማሁም፤ ቅንን ነገር አልተናገሩም፤ ማናቸውም፦ ምን አድርጌአለሁ? ብሎ ከክፋቱ ንስሐ የገባ የለም፤ ወደ ሰልፍም እንደሚሮጥ ፈረስ እያንዳንዱ በየመንገዱ ይሄዳል። ⁷ ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም የመምጣታቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የእግዚአብሔርን ፍርድ አላወቁም። ⁸ እናንተስ፦ ጥበበኞች ነን የእግዚአብሔርም ሕግ ከእኛ ጋር ነው እንዴት ትላላችሁ? እነሆ፥ የጸሐፊ ብርዕ ሐሰተኛ ነው በሐሰትም አድርጎአል። ⁹ ጥበበኞች አፍረዋል ደንግጠውማል ተማርከውማል፤ እነሆ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ጥለዋል፤ ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው? ¹⁰ ከታናሹ ጀምሮ እስከ ታላቁ ድረስ ሁሉ ስስትን ያስባሉና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉ በተንኰል ያደርጋሉና ስለዚህ ሚስቶቻቸውን ለሌሎች፥ እርሻቸውንም ለሚወርሱባቸው እሰጣለሁ። ¹¹ የሕዝቤንም ሴት ልጅ ስብራት በጥቂቱ ይፈውሳሉ፤ ሰላም ሳይሆን፦ ስላም ሰላም ይላሉ። ¹² አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል እግዚአብሔር። ይሁዳ ከመማረኳ በፈት የተነገረ የነቢዩ ትንቢት ነው ። በጉልህ አሁን ያለንበት ዘመናችን ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ የእግዚአብሔር ቃል ነው።           ✅ የነቢያት አገልግሎት           ✅ የሀሰተኛ አስተማሪዎች          ✅  የእረኛ ሳይሆን የሙያተኛ ፓስተሮች            ✅የሳይሆኑ ሐዋርያት ነኝ ባዮች ወዘተ...   በምድራችን የእግዚአብሔር እንዳይሰራ እና በውጭ ላሉት ማሰብን ትተን በውስጥ ላሉት በጎች መስጋትና መጨነቀ የእለት ተለት ስራ ሆነዋል ።        አሁን ነው አትመጣም ወይ ማለትን ማዘውተር............ይቀጥላል ።            t.me/yekal_sink     share 🙏

  • йоС пОдписи

  • የካቲት 23/6/18 ❤የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት 🔥 የእግዚአብሔር ድምፅ ለሁለንተናዊ ለህይወት መንገዶች ወሳኝ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ግደታችን ነው። ለህይወቴ፣ለመንገዴ፣ለስራዬ፣ለአገልግሎቴ በአጠቃላይ ለሁሉም ነገር እግዚአብሔር ምን ይላል ማለት የህይወት መርህ ማድርግ ተገብህ ነው ። ይህ ለምንድነው ለምንለው ጥያቄ ሳንሰማ ወጥተን እንዳንከስር እንዳንባዝን፣እንዳንቀብዝብዝ :-ሉቃስ 15 ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ š² ከእነርሱም ታናሹ አባቱን፦ አባቴ ሆይ፥ ከገንዘብህ የሚደርሰኝን ክፍል ስጠኝ አለው። ገንዘቡንም አካፈላቸው። š³ ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሹ ልጅ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፥ ከዚያም እያባከነ ገንዘቡን በተነ። 2ኛ) መልካም የሚመስሉ ሁሉ ለጊዜው እና ታይተው የሚጠፉ በመሆናቸው የእግዚአብሔር ፊቃድ አለበት የለበትም ድምፁን በመስማት መንቀሳቀስ :-ሉቃስ 15 ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ š⁴ ሁሉንም ከከሰረ በኋላ በዚያች አገር ጽኑ ራብ ሆነ፥ እርሱም ይጨነቅ ጀመር። š⁾ ሄዶም ከዚያች አገር ሰዎች ከአንዱ ጋር ተዳበለ፥ እርሱም እሪያ ሊያሰማራ ወደ ሜዳ ሰደደው። 3ኛው )ቶሎ የእግዚአብሔርን ድምፅ ሰምተን መወሰን ኃጢአታችን ቶሎ መናዘዝና መመለሾ ሉቃስ 15 ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ š⁡ ወደ ልቡም ተመልሶ እንዲህ አለ፦ እንጀራ የሚተርፋቸው የአባቴ ሞያተኞች ስንት ናቸው? እኔ ግን ከዚህ በራብ እጠፋለሁ። š⁸ ተነሥቼም ወደ አባቴ እሄዳለሁና፦ አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥ 4ኛው ) ምንም እንኳን ብንቆሽሽ ብንበድል ጌታ ምህረቱ የበዛው አምላክ መሆኑን ተርድተን በእግሩ ሾር መውደቅ ዳግም የዛ ባርያ አለመሆን እና የእግዚአብሔር እጅ ሰፊ መሆኑን መረዳት ሉቃስ 15 ÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻÂŻ ²š ልጁም፦ አባቴ ሆይ፥ በሰማይና በፊትህ በደልሁ፥ ወደ ፊትም ልጅህ ልባል አይገባኝም አለው። ²² አባቱ ግን ባሪያዎቹን አለ፦ ፈጥናችሁ ከሁሉ የተሻለ ልብስ አምጡና አልብሱት፥ ለእጁ ቀለበት ለእግሩም ጫማ ስጡ፤ 5ኛ) የእግዚአብሔር ድምፅ ሰምተን ስንመለስ በሰማይ ደስታ እንደሆነ ታውቃላችሁ? “ይህ ልጄ ሞቶ ነበርና ደግሞም ሕያው ሆኖአል፤ ጠፍቶም ነበር ተገኝቶአልም። ደስም ይላቸው ጀመር።” — ሉቃስ 15፥24 ..........P/john............... t.me/borforiconn t.me/yekal_sink

  • 26 февр.2572иС yekal_sink

    የካቲት 19/06/2018 እግዚአብሔር በአንተ የጀመረውን በአንተ/ቺ ይጨርሳል 🔥🔥🔥🔥🔥 ይህ ለምን እንዲህ ሆነ አትበል አትበይ በእናንተ የጀመረውን መልካሙን ስራ ያስጀመረው እግዚአብሔር ነዉ እርሱ ያስጨርሳልም ያደርገዋል። ተቀደምኩኝ አትበሉ ኃጢአት እንደምቀድሙ ነው የሚራመዱት ነገር ግን ድጥ ላይ ነው የቆሙት የተሳካላቸው የሆነላቸው ቢመስልም ነገራቸው ድንገት እስክታዩ ነው ያለ እርሱ ፊቃድ የተጓዙ ሁሉ የበሉ ሁሉ ድንገት ይተፋሉ! እግዚአብሔር ከአንተ ጋር መሆኑን ያላወቁ ሰዎች እግዚአብሔር የለም ብሉም በአንተ የጀመረውን በአንተ በመጨርስ አብሮነቱን ይገልጻል ማዳኑን ትታያላችሁ አሜን ❤❤❤ “የዘሩባቤል እጆች ይህን ቤት መሠረቱ፥ የእርሱም እጆች ይፈጽሙታል፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርም ወደ እናንተ እንደ ላከኝ ታውቃላችሁ።” — ዘካርያስ 4፥9 ................P/john.............. t.me/yekal_sink

  • 23 янв.31711иС yekal_sink

    ✅በእምነት ምሰሉአቸው✅ “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።” (ዕብ.13፥7)           🎯የሙሴ ወላጆች እምነት🎯 “ሙሴ ከተወለደ በኋላ፣ ወላጆቹ መልከ መልካም ሕፃን መሆኑን ስላዩ በእምነት ሦስት ወር ሸሸጉት፤ የንጉሡንም ዐዋጅ አልፈሩም።” (ዕብ. 11፡ 23) የግብጽ ንጉስ በእስራኤል ሰፈር የሚወለዱ ወንድ ልጆች ሁሉ ወደ አባይ ወንዝ ውስጥ እንዲጣሉ አዋጅ አውጥቶ በነበረበት ዘመን ነበር ሙሴ የተወለደው። ወላጆቹ ሙሴ ወንድ መሆኑን ባዩ ጊዜ ከባድ ፈተና ውስጥ መውደቃቸው እንደተሰማቸው ጥርጥር የለውም። አዎ፣ በእርግጥም የፈርኦንን ትእዛዝ አለማክበር ልጃቸውን ከማጣትም ባሻገር እነርሱንም አደጋ ላይ እንደሚጨምራቸው ያውቃሉ። ምናልባት በሰፈር በጎረቤቶቻቸው ብዙዎች አዲስ የተወለዱ ወንድ ልጆቻቸውን አዋጁን በማክበር ወደ አባይ ወንዝ ጥለዋል። ታዲያ እነርሱ የተለየ ነገር ማድረግ የሚችሉበት ምን አቅም አላቸው ? የእግዚአብሔር ቃል ግን ሲነግረን የሙሴ ወላጆች የንጉሡን አዋጅ ባለመፍራት ሕፃኑን ወደ አባይ ወንዝ ለመወርወር አሻፈረኝ አሉ። ይህንን ያደረጉት ደግሞ በምን ኃይል እንደሆነ ቅዱስ ቃሉ ሲነግረን እንዲህ ይለናል፦ “ሙሴ ከተወለደ በኋላ፣ ወላጆቹ መልከ መልካም ሕፃን መሆኑን ስላዩ በእምነት ሦስት ወር ሸሸጉት፤ የንጉሡንም ዐዋጅ አልፈሩም።” (ዕብ. 11፡ 23) በእርግጥም የነገስታት ንጉስ በሆነው በእግዚአብሔር በመታመን የግብጽን ንጉሥ ዐዋጅ ባለመፍራት ሕጻኑን ሸሸጉት። በአምላካቸው ስልጣን ላይ የነበራቸው እምነት የትኛውንም ምድራዊ ስልጣን እንዳይፈሩ አደረጋቸው? እኛስ የነገስታት ንጉስ የጌቶች ጌታ በሆነው አምላክ ላይ እኛም እምነታችንን ስናደርግ የትኛውም ምድራዊ ኃይል አያስፈራንም። በእውነተኛው አምላክ በመታመን ትክክለኛውን ነገር ለማድረግ ሁልጊዜ ድፍረት ልናገኝ እንችላለን።         *P/john* t.me/yekal_sink

  • 19 янв.2531иС yekal_sink

    ✅በእምነት ምሰሉአቸው✅           *11/05/2018** “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።” (ዕብ.13፥7) 🔥🔥🔥የዮሴፍ እምነት🔥🔥🔥 "ዮሴፍ ሊሞት በተቃረበ ጊዜ፣ ስለ እስራኤል ሕዝብ ከግብጽ መውጣት በእምነት ተናገረ፤ ስለ ዐፅሙም ትእዛዝ ሰጠ።" (ዕብ. 11:22) ✅ዮሴፍ ገና በለጋ እድሜው ብዙ መከራን የተቀበለ ሲሆን በእምነት ከጥልቅ ሸለቆ ወደ ከፍታ መሻገርን ከታሪኩ እንማራለን። ገና በልጅነቱ የተቀበለው ሕልም (ራእይ )የተስፋው መልሕቅ ሆኖለት በተቃራኒ አቅጣጫ ይሄድ የነበረው የሕይወቱ አቅጣጫ ተስፋ አላስቆረጠውም። ✅ይልቁንም በወንድሞቹ ተሽጦ ወደ ግብጽ ሲወርድ፣ በሐሰት ተወንጅሎ እስርቤት ሲወረወር በገባበት ቦታ ሁሉ በተስፋ የተሞላን ሕይወት ኖረ። ለ13 አመታት በምሬት እና በሽንፈት መንፈስ ሳይሆን በትጋትና በጥበብ ኑሮውን ይመራ ነበር። በዚያ ሁሉ ውስጥ ደግሞ አምላኩ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር እንደነበረ ቃሉ ደጋግሞ ይነግረናል። (ዘፍ 39፣1-2) ✅የአምላኩ ጊዜ ደርሶ ከእስር ቤት ወደ ቤተመንግስት በአስደናቂ ፍጥነት ከፍ በተደረገ ጊዜ ዮሴፍ ለዚያ ያበቃውን አምላኩን አልረሳም። የጥበቡ ሁሉ ምንጭ እርሱ መሆኑን በግብጹ ፈርኦን ፊት መሰከረ። ከባድ በደል ያደረሱበት ወንድሞቹ በልጅነቱ ባየው ሕልም መሰረት በእጁ ላይ በወደቁ ጊዜ የበቀል እርምጃን ከመውሰድ ይልቅ በአምላኩ በመታመን ይቅር አላቸው። 🤔በመጨረሻም ለሞት በተቃረበ ጊዜ ዮሴፍ ለቀደሙት አባቶች የተሰጠውን ተስፋ በማመንና በማስታወስ ከግብጽ እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደሚያወጣ ተናገረ። ✅ ያን ጊዜም የእርሱን ዐጽም በዚያ እንዳይተዉት ይልቁንም ወደ ተስፋይቱ ምድር ከእነርሱ ጋር ይዘውት እንዲሄድ ትእዛዝ ሰጠ። በዚህም ዮሴፍ ከምድራዊ ስኬት ይልቅ ለእግዚአብሔርን ዘላለማዊ ርስት ትልቅ ዋጋ እንደሰጠ እንረዳለን። ይህን ያደረገው ደግሞ በእምነት ነበር። እኛም እንደ ዮሴፍ በተለያየ የሕይወት መከራ ውስጥ የምናልፍ ቢሆን በእምነት አምላካችን እንጠብቀው። እርሱ ቃሉን ይፈጽማል። ከምንም በላይ ደግሞ የምድሩን ሳይሆን የሰማዩን ርስት በእእምነት እንጨብጥ። ከዮሴፍ እምነት በመነሳት እግዚአብሔርን ስለ እምነት በጸሎት ምን ትጠይቁታላችሁ ? እግዚአብሔር መጎብኘትን ይጎበኛችኃል ። *P/john* t.me/borforiconn t.me/yekal_sink share ,sha

  • 18 янв.18111иС yekal_sink

    🎯በእምነት ምሰሉአቸው🎯 “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።” (ዕብ.13፥7)            🔥የያዕቆብ እምነት🔥 “ያዕቆብ በሚሞትበት ጊዜ እያንዳንዳቸውን የዮሴፍን ልጆች በእምነት ባረካቸው፤ በበትሩም ጫፍ ዘንበል ብሎ ሰገደ።” (ዕብ. 11፡ 21) ያዕቆብ በእግዚአብሔር ላይ ሙሉ በሙሉ ለመታመን ረዥም መንገድን የተጓዘ ሰው ነበር። ምንም እንኳን የብኩርና በረከት የእርሱ እንደሚሆን ቀድሞ ቢነገርም እናቱና እርሱ አጭበርብረው በረከቱን ለመውሰድ የሄዱበት መንገድ ብዙ ዋጋ አስከፈለው። ማታለልን ብቻ ሳይሆን መታለልንም በሕይወቱ ተጋፈጠ። ታዲያ በዚያ ሁሉ ውስጥ ሲያልፍ ያዕቆብ በአምላኩ ላይ መደገፍን ለመማር እድል አገኘ። በተለይም ስሙ የያዕቆብ ወደ እስራኤል በተለወጠበት በዚያ ሌሊት፣ የእግዚአብሔር መልአክ የጭኑን ሽሉዳ በመንካት ባረከው። ያዕቆብም እያነከሰ በረከቱን ተቀበለ። በሕይወቱ መጨረሻ ላይም “የዮሴፍን ልጆች በእምነት ባረካቸው። በበትሩም ጫፍ ዘንበል ብሎ ሰገደ።” (ዕብ.11:21) ይህ ያዕቆብ ለመስገድ የተጠቀመበት በትር የእምነት ጉዞውን የሚያስታውስ ነበር። ከአባቱ ቤት ሸሽቶ ሲሄድ ይህችን በትር ብቻ ይዞ ነበር የተሻገረው። ወደ አባቱ ቤት ሲመለስ ግን ሁለት ሰራዊት ሆኖ ነበር የመጣው። እንዲህ ብሎ እንደ ተናገረው፦ “እኔ ባሪያህ እስካሁን ላደረግህልኝ ቸርነትና ታማኝነት ብቁ አይደለሁም፤ ዮርዳኖስን ስሻገር በእጄ ላይ ከነበረው በትር በቀር ምንም አልነበረኝም፤ አሁን ግን ይኸው ሁለት ሰራዊት ሆኛለሁ።” (ዘፍ. 32፡10) ያን በትር ተደግፎ ባነከሰ ቁጥር በእግዚአብሔር ላይ መደገፍን፣ ዝቅ ብሎ ለእግዚአብሔር መስገድን፣ በእምነት የአምላኩን ፈቃድ መቀበልን ያስታውስ ነበር። ታዲያ አሁን በሕይወቱ መጨረሻ ላይ እምነቱን በጣለበት ጌታ ተደግፎ የዮሴፍን ልጆች ባረከ። እርሱም ለመጨረሻ ጊዜ በበትሩ ጫፍ ዘንበል ብሎ ሰገደ። ከያዕቆብ ስለ እውነተኛ እምነት የምንማረው በራሳችን ማስተዋልና መንገድ ከመደገፍ ይልቅ በእግዚአብሔር ላይ መደገፍ የእውነተኛ እምነት ትክክለኛ መገለጫ እንደሆነ ነው። እኛም እንደ ያዕቆብ በእግዚአብሔር ላይ እንደገፍ። እርሱም በእውነተኛው በረከት ይባርከናል። ከያዕቆብ እምነት በመነሳት እግዚአብሔርን ስለ እምነት በጸሎት ምን ትጠይቁታላችሁ ? የፀሎት ርዕሳችሁን ከዚህ በታች ዘርዝሩና ቀኑን ሙሉ በልመና መንፈስ ይዋሉ።                                ......P/john.. t.me/yekal_sink

  • 17 янв.1921иС yekal_sink

    🎯በእምነት ምሰሉአቸው🎯 “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።” (ዕብ.13፥7)             🇪🇹የይሥሐቅ እምነት🇪🇷 "ይሥሐቅ ወደ ፊት የሚሆነውን ዐስቦ ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው።" (ዕብ. 11፡ 20) ይሥሐቅ ልክ እንደ ወላጆቹ ከሚስቱ ከርብቃ ልጅ ለመውለድ ባለመቻል ለአመታት ቆይተው ነበር። እግዚአብሔርም ተመሳሳዩን ተአምር በመድገም ለይስሐቅ ጸሎት መልስ በመስጠት ልጅ ሰጣቸው። እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈው፦ “ይሥሐቅ፣ ርብቃ መካን ስለ ነበረች ስለ እርሷ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰማ፤ ርብቃም ፀነሰች።” (ዘፍ. 25፡ 21) ይሁንና ይህ የርብቃ እርግዝና ከተለመደው ውጪ ነበር። ሁኔታውን ልዩ ያደረገው መንታ ማርገዟ ብቻ ሳይሆን ልጆቹ በማሕጸኗ ውስጥ ይጋፉ የነበረ መሆኑ ነው። ይህ ለምን እንደሚሆን እግዚአብሔርን በጠየቀች ጊዜም ስለምትወልዳቸው ልጆች የወደፊት ሁኔታ ተነገራት። ታዲያ ይስሐቅ በእምነት ልጆቹን ከእግዚአብሔር የተቀበለ ብቻ ሳይሆን፣ እግዚአብሔር በልጆቹ በኩል ሊያደርግ የወደደውን እንደሚፈጽምም አምኖ ነበር። ከዚህ እምነቱም የተነሳ “ይሥሐቅ ወደ ፊት የሚሆነውን ዐስቦ ያዕቆብንና ዔሳውን በእምነት ባረካቸው።” (ዕብ. 11፡ 20) በእርግጥም እግዚአብሔር የሰጠውን የተስፋ ቃል የማያጥፍ፣ እቅዱም ከቶ በማንም የማይሰናከል አምላክ ነውና የታመኑበት ፈጽሞ አያፍሩም። ስሐቅ እምነት እግዚአብሔር የተናገረውን እንደሚያደርግ በመታመን የወደፊቱን ሁሉ ለእርሱ በእምነት ማስረከብ እንደምንችል እንማራለን። እኛም በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብንሆን እግዚአብሔር ሊያደርግልን ቃል የገባልንን በማሰብ፣ ለእኛም ሆነ የእኛ በሆኑት ሁሉ ላይ በረከቱን በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ ሊሰጠን የሚወድ አባት እንዳለን እንመን። በእምነትም የበረከትን ቃል ከአፋችን እናውጣ። ከይስሐቅ እምነት በመነሳት እግዚአብሔርን ስለ እምነት በጸሎት ምን ትጠይቁታላችሁ ? የፀሎት ርዕሳችሁን ከዚህ በታች ዘርዝሩና ቀኑን ሙሉ በልመና መንፈስ ይዋሉ። ............p/john............. t.me/yekal_sink t.me/borforiconn

  • 9 янв.240иС yekal_sink

    йоС пОдписи

  • 3 янв.2712иС yekal_sink

    🎯እምነት ምሰሉአቸው🎯 “የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ በእምነታቸው ምሰሉአቸው።” (ዕብ.13፥7) .........✝️የሣራ እምነት✝️....... “ሣራም ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደሆነ ስለ ቈጠረች፥ ምንም እንኳን መካን ብትሆን፥ ዕድሜዋ እንኳ ካለፈ በኋላ ዘርን ለመፅነስ ኃይልን በእምነት አገኘች።” (ዕብ. 11፡ 11) 1.) አብርሃም “ዘርህ እንደ ሰማይ ከዋክብት እንዲሁም እንደምድር አሸዋ ይበዛል” የሚለው ተስፋ በተሰጠው ጊዜ ሚስቱ ሣራ መካን ነበረች። ነገሩን የበለጠ ከባድ ያደረገው ደግሞ ተስፋው ለመፈጸም ጊዜ ሲወስድ የመውለጃዋ እድሜ እያለፈ መሆኑ ነበር። እናም ሣራ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ተስፋ በተጠራጠረች ጊዜ ከአገልጋይዋ ከአጋር አብርሃም እንዲወለድ ሁኔታዎችን አመቻቸች። 2.) እግዚአብሔር ግን የራሱን ዕቅድ የሚተገብርበት ጊዜ ነበረው። ታዲያ ልጅ የመውለጃዋ ጊዜ ደርሶ ከመለኮት የዛሬ አመት ልጅ እንደምትወልድ መልዕክት ሲመጣ ሣራ “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል” ብላ ሳቀች። ለማመን ከበዳት። “አብርሃምና ሣራም በዕድሜአቸው ሸምግለው ፈጽመው አርጅተው ነበር፥ በሴቶች የሚሆነውም ልማድ ከሣራ ተቋርጦ ነበር። ሣራም በልብዋ እንዲህ ስትል ሳቀች፦ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ ፍትወት ይሆንልኛልን? ጌታዬም ፈጽሞ ሸምግሎአል።” 3.) እግዚአብሔርም አብርሃምን አለው፦ “ካረጀሁ በኋላ በውኑ እወልዳለሁን? ስትል ሣራ ለምን ሳቀች? በውኑ ለጌታ የሚሳነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመለሳለሁ፥ ሣራም ልጅን ታገኛለች።” ሣራም ስለ ፈራች፦ “አልሳቅሁም” ስትል ካደች። እርሱም፦ “አይደለም፥ ሳቅሽ እንጂ” አላት።” (ዘፍ. 18፡ 11-15) ይገርማል! ምንም እንኳን ሣራ በመጀመሪያ በጥርጣሬ የሳቀች ቢሆንም “በውኑ ለጌታ የሚሳነው ነገር አለን?” የሚለው ቃል ምነት ሆናት። ተስፋ የሰጠው የታመነ እንደሆነ ስለ ቆጠረች፣ ለመፀነስ ኃይልን በእምነት አገኘች። እኛም እንደ ሣራ እግዚአብሔርን በመጠራጠር ለብዙ ኪሳራ ተዳርገን ቢሆን እርሱ ትላንት እንዲህ ነበራችሁ በማለት ተስፋ አይቆርጥብንም፤ ድካማችንንም በማስተዋል እምነታችንን የሚያበረታን ቃል ይሰጠናል። በእርሱም ብንታመን እኛም እንደ ሣራ በእምነት ኃይልን እናገኛለን። ከሣራ እምነት በመነሳት እግዚአብሔርን ስለ እምነት በጸሎት ምን ትጠይቁታላችሁ ? የፀሎት ርዕሳችሁን ከዚህ🛐 በታች ዘርዝሩና ቀኑን ሙሉ በልመና መንፈስ ይዋሉ። ........P/john............ t.me/borforiconn t.me/yekal_sink

  • 2 янв.2081иС yekal_sink

    .......✝️የአብርሃም እምነት✝️..........                 ዕብ 13:7 “አብርሃም እግዚአብሔር በፈተነው ጊዜ፣ ይሥሐቅን መሥዋዕት አድርጎ በእምነት አቀረበ፤” (ዕብ.11:17) በዕብራውያን ምእራፍ አስራ አንድ ላይ ስማቸው ከተዘረዘሩት የእምነት አርአያዎች መካከል በሰፊው የተነገረለት አብርሃም እንደሆነ እናያለን። በእርግጥም አብርሃም የእምነት አባት ተብሎ የሚታወቅም ሲሆን ስለ እምነት የተጻፈው እንዲህ ይነበባል፦ 1. አብርሃም ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም እሺ ብሎ በእምነት ታዞ ሄደ "አብርሃም ርስት አድርጎ ወደሚቀበለው ስፍራ እንዲሄድ በተጠራ ጊዜ በእምነት ታዘዘ፤ ወዴት እንደሚሄድ ባያውቅም፣ ዕሺ ብሎ ሄደ። በባዕድ አገር እንዳለ መጻተኛ በተስፋዪቱ ምድር በእምነት ተቀመጠ፤ የተስፋውን ቃል ዐብረውት እንደሚወርሱት እንደ ይሥሐቅና እንደ ያዕቆብ በድንኳን ኖረ፤ ምክንያቱም መሠረት ያላትን፣ እግዚአብሔር የሠራትንና የፈጠራትን ከተማ ይጠባበቅ ነበር።" (ቁ. 8-9) 2. አብርሃም ምንም እንኳ ዕድሜው ቢገፋ ሚስቱም መካን ብትሆንም በእምነት የልጅ አባት ለመሆን በቃ። ✅“አብርሃም ምንም እንኳ ዕድሜው ቢገፋም፣ ሣራም ራሷ መካን ብትሆንም፣ ተስፋን የሰጠውን ታማኝ አድርጎ ስለ ቈጠረ በእምነት የልጅ አባት ለመሆን በቃ። ስለዚህ እንደ ሞተ ሰው ከሚቈጠር ከዚህ ከአንድ ሰው፣ እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛና እንደ ባሕር ዳር አሸዋ ተቈጥሮ የማያልቅ ዘር ተገኘ።” (ቁ. 11-12) ✅. አብርሃም ልጁን ይስሐቅን አምላኩን በመታዘዝ በእምነት አቀረበ። አብርሃም እግዚአብሔር በፈተነው ጊዜ፣ ይሥሐቅን መሥዋዕት አድርጎ በእምነት አቀረበ፤ የተስፋን ቃል የተቀበለው እርሱ፣ አንድ ልጁን ሊሠዋ ዝግጁ ነበር፤ ይህም እግዚአብሔር፣ ✅“ዘርህ በይሥሐቅ ይጠራል” ያለለት ነበር። አብርሃም እግዚአብሔር ሙታንን ሊያስነሣ እንደሚችል ተገንዝቦ ነበር፤ ይሥሐቅንም ከሞት የመነሣት አምሳያ ሆኖ አገኘው። (ቁ. 17-19) አዎ፣ ከአብርሃም እውነተኛ እምነት በእግዚአብሔር ላይ በመደገፍ እርሱ አድርጉ የሚለንን በመታዘዝ የምንኖረው ሕይወት እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል።             ጥያቄ ? 🎯ከአብርሃም እምነት በመነሳት እግዚአብሔርን ስለ እምነት በጸሎት ምን ትጠይቁታላችሁ ? የፀሎት ርዕሳችሁን🛐 ከዚህ በታች ዘርዝሩና ቀኑን ሙሉ በልመና መንፈስ ይዋሉ።   ...........P/john........... t.me/yekal_sink t.me/borforiconn