Deborah School
СтатистикаShaping the Next Generation with Wisdom and Character!
- Последний пост
- 2 авг.
- Последнее чтение
- 14 авг.
- Постов за неделю
- 0
- Всего постов
- 20
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 1 769
- 1/48двое суток
- 2 027
- 1/72трое суток
- 2 186
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
Document from Gemechis Ashuri
For grade 11 and 12 summer class phase 2
без подписи
For grade 12 summer English practice questions
Summer special con curriculum, Phase 1 all.zip
For grade 11 and 12 summer class
ውድ ወላጆች/አሳዳጊዎች የ2019 ዓ.ም. የነባር ተማሪዎች ምዝገባ በይፋ የተጠናቀቀ ቢሆንም፣ በቀደመው ማስታወቂያችን እንደገለጽነው ለተማሪዎቻችን የመጨረሻና የማይደገም የምዝገባ ዕድል ለመስጠት ወስነናል። በመሆኑም፣ ዛሬ ቅዳሜ ሐምሌ 25 እና ሰኞ ሐምሌ 27 ፣ 2018 ዓ ም ትምህርት ቤት በአካል በመገኘት የልጅዎን ምዝገባ እንዲያጠናቅቁ በአክብሮት እንጠይቃለን። 📣ጥብቅ ማሳሰቢያ 📢 በተሰጠው ቀንና ሰዓት በአካል ቀርበው የልጃቸውን ምዝገባ የማያጠናቅቁ ወላጆች/አሳዳጊዎች የልጃቸውን የመማሪያ ቦታ በፈቃዳቸው እንደተዉ ይቆጠራሉ። በመሆኑም የሚኖሩንን ክፍት ቦታዎች አዲስ ተመዝጋቢ ተማሪዎች የምንቀበልበት ይሆናል። ት/ቤቱ Dear Parents/Guardians, Although the registration for returning students for the 2026/27 (2019 E.C.) academic year has officially ended, as stated in our previous notice, we have decided to give our students a final, non-repeatable registration opportunity. Therefore, we respectfully request that you come to the school in person today, Saturday, August 1 (Hamle 25), and Monday, August 3 (Hamle 27), to complete your child's registration. 📣 STRICT NOTICE 📢 Parents/Guardians who do not appear in person to complete their child's registration on the designated dates and times will be considered to have voluntarily forfeited their child's seat. Consequently, we will accept new applicant students for any remaining open spots. The School
Dear Parents / Guardians, As you are aware, registration for the 2019 E.C. (Ethiopian Calendar) academic year is currently underway for both returning and new students from Kindergarten (KG) to Grade 12. First and foremost, we would like to express our gratitude to the many parents who have already come to the school and registered their children. To those parents who have not yet registered your children: Because a large number of new students are choosing our school and our available spaces are limited, we strongly urge you to register your children as soon as possible according to the set schedule. This will help avoid any inconveniences that may arise from missing the deadline. Important Notice for Grade 6 and Grade 8 Students Please be informed that summer remedial/reinforcement classes are mandatory for all Grade 6 and Grade 8 students for the upcoming 2019 E.C. academic year. Start Date: Wednesday, Hamle 15, 2018 E.C. Time: All students must report to school starting from 8:00 AM (2:00 local time). ⚠️ Urgent Reminder For parents or guardians who have not yet registered your children for the 2019 E.C. academic year, please note that the school will be open tomorrow, Friday, Hamle 10, 2018 E.C., as well as Saturday, Hamle 11, 2018 E.C., until **4:30 PM (10:30 local time). We strongly urge you to come and complete the registration. Best regards, The School Administration
ውድ ወላጆች/ አሳዳጊዎች ከመዋዕለ ህፃናት አንስቶ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ለ2019ዓ.ም የትምህርት ዘመን የነባር ተማሪዎች እንዲሁም የአዲስ ተማሪ ምዝገባ እየተካሄደ እንዳለ ይታወቃል። በቅድሚያ በርካታ ወላጆች ትምህርት ቤት ተገኝታችሁ ልጆቻችሁን ስላዝመዘገባችሁ እናመሰገናለን። በመቀጠል እስካሁን ልጆቻችሁን ላላስመዘገባቸሁ ወላጆች : - አዳዲስ ተማሪዎች በብዛት ት/ቤቱን መርጠው እየመጡ በመሆኑ እንዲሁም ያሉን ቦታዎች ውስን በመሆኑ ፣ እናንተ ደግሞ በተባለው የጊዜ ሰሌዳ ባለማስምዝገባችሁ ሊፈጠር የሚችለውን ችግር ለመቀነስ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ ቀድማችሁ እንድታስመዘገቡ እናሳስባለን። በተጨማሪ በ2019ዓ.ም. የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በክረምቱ የማጠናከርያ ትምህርት መማር ግዴታ መሆኑን ተገንዝባችሁ፣ ትምህርቱ የሚጀምረው እሮብ ሐምሌ 15: 2018 ዓም ስለሆነ ከተጠቀሰው እለት አንስቶ ሁሉም ተማሪዎች ከጠዋቱ 2 ሰዐት ጀምሮ ትምህርት ቤት እንድትገኙ ትምህርት ቤቱ ያሳስባል። ማሳሰብያ:- ለ2019ዓም የትምህርት ዘመን ልጆቻችሁን ላላስመዘገባችሁ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ነገ አርብ ሐምሌ 10:2018 ዓም እንዲሁም ቅዳሜ ሐምሌ 11 ትምህርት ቤቱ እስከ 10:30 ድረስ እንደሚሰራ ተገንዝባችሁ ምዝገባውን እንድትጨርሱ እናሳስባለን። ትምህርት ቤቱ
ጥብቅ ማሳሰቢያ ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ይሄ የክረምት ተማሪዎች የምስክር ወረቀት የሚሰጠው በየእለቱ በሚያዘው አቴንዳንስ መሰረት እንዲሁም የምስክር ወረቀቱ ከቶፕ-30 ውጪ ሆነው የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርቱን ለሚከታተሉ ተማሪዎችም መሆኑን ተገንዝባችሁ ትምህርታችሁን የለምንም ቀሪ መከታተል እንደሚኖርባችሁ በድጋሜ ለማሳሰብ እንወዳለን። ከትምህርት ቢሮ በደረሰን ማሳሰቢያ ይሄንን ሰርተፍኬት ያልያዘ ተማሪ በ 2019 ዓ.ም የማናስተናግድ እንደሆነ ለመግለፅ እንወዳለን።
ለ11ኛ እና 12ኛ ክፍል የክላስተር የማጠናከሪያ ትምህርት ተከታታይ ተማሪዎች በሙሉ ዛሬ የሶስተኛ ቀን የክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት በተገኙ ተማሪዎች በጥሩ ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን የትምህርት ቢሮ አቅጣጫ ብሎም የትምህርት ቤቱን ስርዓት አክብረው በበሻሌ ትም/ት ቤት ተገኝተው የተከታተሉ ተማሪዎቻችንን እያመሰገንን የተላለፈውን መልዕክት ችላ በማለት ያለተገኙ ተማሪዎች ላይ ከት/ጽ/ቤት በሚተላለፍልን ህግ መሰረት እርምጃ የምንወስድ መሆናችንን እያሳወቅን ነገ 2:ዐዐ ሰዓት ላይ በበሻሌ ትምህርት ቤት ተገኝታችሁ የማጠናከሪያ ትምህርቱን እንድትከታተሉ በጥብቅ እናሳስባለን። ት/ቤቱ
ለ12ኛ ክፍል 5ኛ ዙር የማሕበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች 1ኛ: ዩኒፎርም :- ሁላችሁም የት/ቤቱን ዩኒፎርም ለብሳችሁ ነገ፡ ሐምሌ 9:2018 ዓ.ም በት/ቤት እንድትገኙ። ጀንስ ቱታ ወይም ሌላ አይነት ሹራብ የመሳሰሉት ተቀባይነት የላቸውም። በድጋሜ ለማሳሰብ የትምህርት ቤቱን የተሟላ ዩኒፎርም (ሹራብ ውሃ ሰማያዊ ሸሚዝ እና ጥቁር ጨርቅ ሱሪ) አድርጋችሁ ጠዋት 1:30 ላይ እንድትገኙ። 2ኛ ፦ ምሳ፡- ማንም ተማሪ ከግቢ መውጣት ስለማይችል የየራሳችሁን ምሳ ይዟችሁ እንድትገኙ። 3ኛ፦ ምንም አይነት የእጅ ሰዓት ማድረግ አይቻልም። ወረቀት ወይም ሶፍት የመሳሰለትን ይዞ መምጣት አይቻልም። ማስቲካም አይቻልም። የማሰቢያ ወረቀት ከዛው ከት/ቤት ይሰጣል። 4ኛ፦ Admission card እና የፋይዳ መታወቂያ መያዝ ይኖርባችኋል 5ኛ፦ መነፅር የምትጠቀሙ ተማሪዎች የሐኪም የማዘዣ ወረቀት ካልያዛችሁ መነፅሩን ይዟችሁ መግባት አትችሉም። 6ኛ፦ በህክምና ምክንያት መድሐኒት የምትወስዱ ተማሪዎች ካላችሁ፡ የሐኪሙን ማዘዣ ወረቀት መያዝ አለባችሁ። 7ኛ፦ ሞባይል :- ሞባይል ይዞ መምጣት የማይቻል ሲሆን ሞባይል ይዞ የሚመጣ ተማሪ ካለ ሞባይሉ በፌዴራል ፖሊስ ይወረስበታል። መልካም ፈተና
ውድ ወላጆች (አሳዳጊዎች) ለ3 ቀናት ሲሰጥ የነበረው አራተኛው ዙር የማሕበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል የበይነ መረብ ፈተና እጅግ አሁንም በተሳካ መልኩ የተጠናቀቀ መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን። ት/ቤቱ ።
የመጨረሻ ማሳሰቢያ ለ2019 ዓ.ም ወደ11ኛ እና ወደ12ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች እና ወላጆች : በዛሬው እለት የክረምት ትምህርት ማላቂያ እንደተጀመረ ይታወቃል። በእለቱ በተወሰደው አቴንዳንስ የመጣውን ተማሪ የተለየ ሲሆን፡በዚህም የተገኘችሁ ተማሪዎችና ወላጆች እያመሰገንን ከነገ ጀምሮ በክረምት ማላቂያው ላይ ተገኝተው አቴንዳንስ ለማያስይዙ ተማሪዎች ምዝገባ የማናስተናግድ ፣ ቀድማችሁ ብትመዘገቡም በማላቂያው ላይ በመገኘት እና አቴንዳንስ በማስያዝ የሚሰጠውን ሰርተፍኬት ካልያዛችሁ በ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የማናስተናግድ እንዲሁም መሸኛ የማንፅፍ መሆኑን አውቃችሁ ለሚያጋጥማችሁ ችግር ትቤቱ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን እናሳውቃለን ። በመሆኑም ዛሬ የተገኛችሁ ነገም እንድትገኙ እያሳሰብን ነገ እና ከነገ ጀምሮ በማትገኙ ተማሪዎች ዙሪያ ት/ቤቱ ከወዲሁ ኃላፊነት የማይወስድ መሆኑን በድጋሜ እናሳስባለን ። ት/ቤቱ
To our graduates: may the fear of God be the foundation of your wisdom, and may faith, character, and courage guide you into a bright future. #DeborahSchool Shaping the Next Generation with Wisdom and Character! https://www.instagram.com/reel/DaqejJspKDZ/?igsh=MWQ4MW8wbWN6aXIybg==
የስብሰባ ጥሪ በ2019 ዓ.ም ወደ11ኛ እና ወደ12ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች ወላጆች : በክረምት ትምህርት ማላቂያ ስትራቴጂ ዙሪያ ውይይት ለማድረግ ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 4 : 2018 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 በት/ቤት ቅጥር ግቢ እንድትገኙ እናሳስባለን ። ት/ቤቱ
ጥብቅ ማሳሰቢያ በ2019 ዓ.ም ወደ11ኛ እና ወደ12ኛ ክፍል ለምትገቡ ተማሪዎች : ዛሬ ከትምህርት ፅ/ቤት በደረሰን መመሪያ መሰረት 1ኛ፦ የትምህርት ማላቂያ cluster ት/ቤት በቦታ ርቀት ምክንያት ከኢትዮ ቻይና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ወደ በሻሌ 1ኛ ደረጃ ክላስተር (ከ one Planet አጠገብ) የተለወጠ መሆኑን እናሳውቃለን። 2ኛ. ትምህርት የሚጀመረው ሰኞ ከሐምሌ 6: 2018 ዓ.ም ስለሆነ ሁሉም ተማሪ በተባለው ቀን አንስቶ በበሻሌ 1ኛ ደረጃ በመሔድ በግማሽ ቀን (ከጠዋት 2 ሰዓት - 6:30 ) የሚሰጠውን የክረምት የትምህርት መማር እንድትጀምሩ። በእለቱ አቴንዳንስ ስለሚያዝ ሁሉም ተማሪ በቦታው እንዲገኝ። 3ኛ፦ ከትምህርት ፅ/ቤት በተሰጠን መመሪያ መሰረት የሚሰጠውን የክረምት ማላቂያ ትምህርት ለሚያጠናቅቅ ተማሪ certeficate የተዘጋጀ ሲሆን ፤ ይህን ያልያዘ ተማሪ በ 2019 ዓ.ም የማይስተናገድ መሆኑን በመመሪያው ላይ ተገልጿል። 4ኛ፦ ከትምህርት ፅ/ቤት በመጣው መመሪያ ላይ ከት/ቤት ለሚለቁ ተማሪዎች ሆነ ከሌላም ት/ቤት የሚመጡ ከሚመጡበት ት/ቤት የክረምት ትምህርት እየተከታተሉ መሆኑን የሚገልፅ መሸኛ ደብዳቤ መያዝ ይኖርባቸዋል የሚል መሆኑን እንገልግለን። ስለሆነም ወደ 11ኛ ወይም ወደ 12ኛ ክፍል የምትገቡ እና ትምህርቱን ከሐምሌ 6 ጀምሮ ላልተከታተላችሁ እና መሸኛ ለምትፈልጉ ተማሪዎች የሚያስፈልገውን የመሸኛ ደብዳቤ የማንፅፍ መሆኑን እንገልፃለን። 5ኛ፦ በዕለቱ ሁሉም ተማሪ ዩኒፎርም አደርጎ በበሻሌ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ጠዋት 2፡00 ሰዓት ላይ እንድትገኙ። በመጨረሻም : ለሁሉም በ2019 ዓ.ም. ወደ 11ኛ እና 12ኛ ክፍል ለሚገቡ ተማሪዎች ወላጆች ፤ በዚህ የክረምት ትምህርት ማላቂያ ስትራቴጂ ዙሪያ ውይይት ለማድረግ ነገ ቅዳሜ ሐምሌ 4 : 2018 ዓ.ም ጠዋት በት/ቤት ቅጥር ግቢ እንድትገኙ እናሳስባለን ። ት/ቤቱ
ጥብቅ ማሳሰቢያ በ2019 ዓ.ም ወደ11ኛ እና ወደ12ኛ ክፍል ለምትገቡ ተማሪዎች : ከዚህ በፊት በተገለፀላችሁ መሰረት የክረምት ትምህርት ማላቂያ የሚጀመረው ከሐምሌ 6: 2018 ዓ.ም ስለሆነ ሁሉም ተማሪ በተባለው ቀን አንስቶ በኢትዮ ቻይና 1ኛ ደረጃ ት/ቤት (ቦታው ሰሚት ኮንደሚኒየም) በመሔድ የክረምት የትምህርት መማር እንድትጀምሩ። ማሳሰቢያ፦ከትምህርት ፅ/ቤት በተገለፀልን ማሳሰቢያ መሰረት በዚህ የክረምት ትምህርት ላይ የማይገኝ (የማይሳተፍ) ተማሪ ለ2019 ዓ.ም ምዝገባም ሆነ ትምህርት ከየትኛውም ት/ቤት ግልጋሎት የማያገኝ ሲሆን ፤ በዚህም እኛም በክረምት ትምህርት ማለቂያ ላይ የማይሳተፍ ማንኛውንም ተማሪ ለማስተናገድ የማንችል መሆኑን ለመግለፅ እንወዳለን። ት/ቤቱ
ለ12ኛ ክፍል የማሕበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ሁሉም (የ4ኛ እና የ 5ኛዙር) የማሕበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ቅዳሜ ፣ ሐምሌ 4: 2018 ዓ.ም ጠዋት አረንቴሽን ስለሚሰጥ ፤ ከጠዋቱ 1:30 ላይ የተሟሏ ዩኒፎርም በማድረግ የፋይዳ መታወቂያ እና አድሚሽን ካርድ በመያዝ በትምህርት ቤት እንድትገኙ። መቅረትም ሆነ ማርፈድ በፍፁም አይቻልም። ት.ቤቱ
Registration for the 2026/27 Academic Year is now open. Give your child the opportunity to learn, grow, and excel at Deborah School! ለ2019 ዓ.ም. የትምህርት ዘመን ምዝገባ ጀምረናል፤ ልጅዎ በላቀ ትምህርት እና በጠንካራ ሥነ-ምግባር በሚገነባበት ዲቦራ ትምህርት ቤት ዛሬውኑ ያስመዝግቡ! #DeborahSchool #ዲቦራ https://www.instagram.com/p/Dah_YqawmP7/?igsh=MWNmNWVvZmVrazlwYg==