ምጥን መረጃ 🎤 📻
Статистикаቻናላችንን ሰብስክራይብ በማድረግ ትኩስና ወቅታዊ መረጃዎችን ከምጥን መረጃ ያግኙ @ምጥን ወቅታዊ @ምጥን ሃገራዊ @ምጥን ዓለም አቀፍ @ምጥን ስፖርት @ምጥን መዝናኛ ፈጣንና ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እንዲሁም ሃሳብ፣ አስተያየት እና የሚዲያ ሽፋን ጥቆማ ለማድረስ👉@Bk12jr ይጠቀሙ
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 8
- Всего постов
- 39
- Тип
- открытый
- Язык
- ti
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 77
- 1/48двое суток
- 88
- 1/72трое суток
- 95
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በአዲስ አበባ የትራፊክ ሕግ ጥሰት ከ1.5 ሚሊዮን ማለፉ ተገለጸ በአዲስ አበባ ከተማ በተያዘው ዓመት ከ1.5 ሚሊዮን በላይ የትራፊክ ሕግ ጥሰቶች መመዝገባቸውን ዋና ኢንስፔክተር ሰለሞን አዳነ በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 በሚተላለፈው ታዲያስ አዲስ የሬዲዮ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልጸዋል። ከተመዘገቡት ጥሰቶች መካከል ከ100 ሺህ በላይ የሚሆኑት የቀይ መብራት ጥሶ ማለፍ ሲሆኑ፣ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ከ900 ሺህ በላይ ተሽከርካሪዎች እንደሚንቀሳቀሱም ተመልክቷል። ዋና ኢንስፔክተሩ የትራፊክ ሕግን አለማክበር ለሕይወትና ንብረት መጥፋት ዋነኛ መንስኤ መሆኑን አሳስበው፤ የቁጥጥርና የቅጣት አፈጻጸሙ መጠናከሩ ግን አደጋዎችን በመቀነስ ረገድ አዎንታዊ ውጤት እያሳየ ይገኛል ብለዋል። በዚሁ መሠረት በ2017 ዓ.ም 4መቶ11 የነበረው የሞት አደጋ በ2018 ዓ.ም ወደ 3መቶ82፤ የከባድ አደጋዎች ቁጥር ደግሞ ከ1 ሺህ9መቶ85 ወደ 1ሺህ8መቶ65 ዝቅ በማለት የ1መቶ20 አደጋዎች ቅናሽ አሳይቷል። በአንጻሩ ቀላል አደጋዎች ከ1መቶ15 ወደ 7መቶ35፣ የንብረት ጉዳቶች ደግሞ ከ34 ሺህ84 ወደ 34 ሺህ7መቶ2 ከፍ ብለዋል። በመጨረሻም አሽከርካሪዎች በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው ሕግን በማክበር ማሽከርከር እንዳለባቸው እና የሰው ሕይወትና ንብረትን ከውድመት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ (CEO) አቶ መስፍን ጣሰው ለተጨማሪ አንድ ዓመት በሥራቸው ላይ እንደሚቆዩ ማረጋገጣቸውን 'አዲስ ፎርቹን' ዘገበ። የአየር መንገዱ የዳይሬክተሮች ቦርድ በሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ሰብሳቢነት የአቶ መስፍን ጣሰውን የሥራ ዘመን ማራዘሙ ተገልጿል። አቶ መስፍን በቅርብ በሰጡት መግለጫ፣ ጡረታ መውጣት የነበረባቸው ከ3 ዓመት በፊት የነበረ ቢሆንም በመንግሥት ፍላጎት መጀመሪያ ለ2 ዓመት ከዚያ ለ1 ዓመት የስራ ውላቸው መራዘሙን ተናግረው ነበር። አሁንም ለተጨማሪ አንድ ዓመት ኃላፊነታቸው መራዘሙን 'አዲስ ፎርቹን' ከእሳቸው ማረጋገጡን ገልጿል።
видео или голосовое, без подписи
መሐሪ ብራዘርስ የወላጅ አባታቸውን የሙዚቃ ሥራዎች ዳግም ለአድማጭ ሊያደርሱ ነው የሀገራችን ተወዳጅ እና እውቅ የሙዚቃ ባንድ የሆነው መሐሪ ብራዘርስ ባንድ አባላት የበርካቶች ህይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ የነበራቸውን የወላጅ አባታቸውን የሙዚቃ ሥራዎች ዳግም ለሙዚቃ አፍቃሪያን ለማድረስ በዝግጅት ላይ እንደሚገኙ አስታወቁ። የባንዱ መሪ ሙዚቀኛ ሔኖክ መሐሪ እንደገለጸው፤ የወላጅ አባታቸውን እና የብሔራዊና ሀገር ፍቅር ቴአትር ድንቅ ሁለገብ ሙዚቀኛ የነበሩትን መሐሪ አብርሃ 12 የተመረጡ የተውጣጡ የሙዚቃ ሥራዎችን እንደገና አዘጋጅተው ለማቅረብ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ይገኛሉ። በዚህ ልዩ ስራ ላይ የቀደሙ ተወዳጅ ዜማዎች በበርካቶች ዘንድ ተደማጭ የነበሩ የአባታቸው ስራዎች በሔኖክ መሐሪ ዋና አዘጋጅነት አዲስ ህይወት ዘርተው ይቀርባሉ። ባንዱ ከተመሰረተ 20 ዓመታት ከማስቆጠሩ ጋር ተያይዞ የታሪካዊ ቤተሰባዊ ምስሎችና የሙዚቃ ስራዎች በድምቀት ይከበራሉ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪዎች አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፍ የምስለ-ችሎት ፍጻሜ አለፉ። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የህግ ተማሪዎች በአህጉራዊው የዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና የግልግል ዳኝነት (arbitration) የምስለ-ችሎት ውድድር (FDI Moot) የዞኑ አሸናፊ በመሆን አፍሪካን ወክለው ለዓለም አቀፉ ፍጻሜ ማለፋቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጹ። ለመጀመሪያ ጊዜ በተሳተፉበት በዚህ ፈታኝ ውድድር ከናይጄሪያ፣ ከኬንያ እና ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ 14 ቡድኖችን በመበለጥ ከሰብ-ሳሃራን አፍሪካ አንደኛ በመውጣት ውድድሩን አጠናቀዋል። በዚህ ውድድር ላይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ወክለው የተሳተፉት ፦ ➡️ ባምላክስራ ፋሲል (የ3ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) ➡️ ቃልኪዳን ሰብስቤ (የ4ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) ➡️ ዲቦራ ታደሰ (የ4ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) እና ➡️ ናሆት ግርማ (የ5ኛ ዓመት የህግ ተማሪ) ናቸው። ለዚህ አህጉራዊ ውጤት ያበቃቸው ዋና ምክንያት ምንድን ነው ? " ለዚህ ውጤት ያበቃን ቀደም ሲል በቪስ ሙት (Vis Moot) የነበረን ልምድ ነው። ከቡድናችን አራት አባላት መካከል ሦስቱ በዓለም አቀፍ የግልግል ዳኝነት ውድድር ላይ ለአንድ አመት ተወዳድረዋል። ይህ ልምድ በጣም ጠቅሞናል። አሁን ላይ የተወዳደርንበት ጉዳይ ከአለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ህግ እና የግልግል ዳኝነት ጋር የተያያዙ ውስብስብ ጥያቄዎችን ያካተተ ነበር። ከዋና ዋናዎቹ የስነ-ስርዓት ክርክሮች መካከል ከሳሹ ቀደም ሲል አቤቱታውን ለሌላ አካል አቅርቦ ስለነበር አሁን እንዳይከለከል የሚለው እና የክስ ማገጃ ትእዛዝ መሰጠት አለበት ወይ ? የሚሉት ይገኙበታል። የፍሬ-ነገር ክርክሩ በበኩሉ ፍትሃዊ እና እኩል እንክብካቤ እንዲሁም ንብረት መውረስን የሚመለከቱ ጥያቄዎችን አካቷል። በውድድሩ ወቅት የገጠመን ትልቁ ፈተና ከዳኞቹ ለሚቀርቡ ዝርዝር እና ያልተጠበቁ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት ነው " ብለዋል። የተወዳዳሪዎቹ መሪ የሆኑትና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞው የህግ ተማሪ፣ የህግ ባለሙያ ቦርጋ ደለሳ፥ ተማሪዎቹ እስካሁን ያለምንም ድጋፍ ለዚህ ድል የበቁ ቢሆንም፣ በመጪው ኦክቶበር (October) ወር በቻይና በሚካሄደው የመጨረሻ ፍጻሜ ላይ ለመሳተፍ ከፍተኛ የገንዘብ እና የተቋማት ድጋፍ ይፈልጋሉ ብለዋል። በተለይም ፦ - ለዓለም አቀፍ ጉዞ፣ - ለእንግዳ ማረፊያ፣ - ለቪዛ፣ - ከምዝገባ ጋር የተያያዙ ወጪዎች እና ለዝግጅት ድጋፍ የሚያስፈልግ በመሆኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት (በተለይም የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን) የሕግ እና የንግዱ ማኅበረሰብ፣ እንዲሁም ሌሎች ድርጅቶች ትብብር እንዲያደርጉላቸውና እውቅና እንዲሰጧቸው ጠይቀዋል። ይህ እድል የነዚህ አራት ተማሪዎች ብቻ ሳይሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን፣ ኢትዮጵያን እና የአፍሪካን የሕግ ትምህርት በዓለም አቀፍ መድረክ ለማስተዋወቅና ለመወከል የሚሰጥ ትልቅ ዕድል መሆኑን ገልጸዋል። ተወዳዳሪዎቹን ማግኘት የምትፈልጉ፣ የቡድኑ መሪ የሆኑትን የህግ ባለሙያ ቦርጋ ደለሳን በስልክ ቁጥር +251925494142 ማግኘት ትችላላችሁ።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
ታሪካዊው ኢትዮጵያ ሆቴል ሊፈርስ ነው በአዲስ አበባ ከተማ ብሔራዊ አካባቢ የሚገኘውና የአገሪቱ አንጋፋ ተቋም የሆነው ታሪካዊው የኢትዮጵያ ሆቴል የማፍረስ ሂደት መጀመሩን ከፎርቹን ጋዜጣ ሰምተናል። ቀደም ብሎ ከሆቴሉ ጀርባ የሚገኘው የስብሰባ አዳራሽ መፍረስ የጀመረ ሲሆን የዋናው ሕንፃ ማፍረስ ሥራም በጥቂት ቀናት ውስጥ ተጠናቆ በቅርብ ጊዜ ሙሉ በሙሉ እንደሚጠናቀቅ ተገልጻል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በሆቴሉ ቅጥር ጊቢ ውስጥ የሚገኙ ሰባት የንግድ ሱቆች አስቀድመው ተነስተዋል። በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በ109 ክፍሎችና በ140 ሠራተኞች አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው ይህ ባለ አምስት ፎቅ ሕንጻ በ2002 ዓ.ም ታዋቂው ባለሃብ አቶ በላይነህ ክንዴ በ94 ሚሊዮን ብር በቢኬ ግሩፕ በኩል የገዙት ሲሆን አሁን ላይ በኢትዮጵያ ሆቴል ምትክ ዘመናዊ ሕንፃ ለመስራት አቅደዋል። ተቋሙ ሠራተኞቹ እንደማይቀነሱና በሥሩ ባሉት 22 ኩባንያዎች ውስጥ እንደሚያዛውራቸው ቃል ገብቷል።
የኤርትራ ወታደራዊ አዛዦች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው መግባታቸውን አምባሳደር ባጫ ደበሌ ገለጹ የኤርትራ መንግሥት ከፍተኛ የጦር አዛዦች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰው ወደ ዛላምበሳ ከተማ በግልጽ መግባታቸው እና የኤርትራን ሰንደቅ ዓላማ መስቀላቸው የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የክልል አንድነት በግልጽ የጣሰ ድርጊት መሆኑን በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ገለጹ። አምባሳደር ባጫ ደበሌ ባሰፈሩት ጽሑፍ እንደገለጹት፣ ይህ ክስተት በተናጥል የተከሰተ ሳይሆን በኤርትራ አገዛዝ እና "ጽምዶ" በተባለው የሕወሓት ቡድን መካከል ሲካሄድ የቆየው ስውርና ግልጽ ቅንጅት ውጤት ነው። አምባሳደሩ አክለውም፣ የኤርትራ ጦር ታንኮችንና ከባድ መሣሪያዎችን ወደ ትግራይ ክልል በማስገባት በኢፌዴሪ መንግሥትና ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓት ላይ ያቀደውን ግልጽና ኃይል የተቀላቀለበት እንቅስቃሴ ማፋጠኑን ጠቁመዋል። የኢትዮጵያ መንግሥት ከፕሬቶሪያው የሰላም ስምምነት በኋላ ላለፉት ሁለት ዓመታት በላይ ለቀጣናው ሰላም ሲል ከፍተኛ ስልታዊ ታጋሽነት ማሳየቱን ያብራሩት አምባሳደር ባጫ፣ የኤርትራ መንግሥት ግን የቀረቡለትን የዲፕሎማሲያዊ ውይይት ጥሪዎች በሙሉ ውድቅ ማድረጉን አስረድተዋል። በተጨማሪም የኤርትራ አገዛዝ የትግራይ ወጣቶችን በግዴታ በመልመልና ለሱዳን ጦርነት በቅጥረኝነት በመሸጥ ለገዛ ፖለቲካዊ ፍላጎቱ መጠቀሚያ እያደረጋቸው እንደሚገኝ አጋልጠዋል። ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በኤርትራ መንግሥት ላይ የጣለው ማዕቀብ አሁናዊ ለውጥ ያላመጣ በመሆኑ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የዜጎቹን ደኅንነትና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ሲባል በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት ራስን የመከላከል ሕጋዊ መብቱን ተጠቅሞ እርምጃ ለመውሰድ ሊገደድ እንደሚችል አምባሳደር ባጫ ደበሌ አስጠንቅቀዋል። የኤርትራ መንግሥት በኢትዮጵያ ግዛት ውስጥ የሚያንቀሳቅሰውን ኃይል በአስቸኳይ ካላወጣና ከጣልቃ ገብነት ካልተቆጠበ፣ የሚፈጠረው ቀጣናዊ አለመረጋጋት በራሷ በኤርትራ ሕልውና፣ በቀይ ባሕር አካባቢና በሙሉ የአፍሪካ ቀንድ ላይ የከፋ ሰብዓዊና ፖለቲካዊ መዘዝ እንደሚያስከትል ማሳሰባቸውን ከሆርን ሪቪው ያገኘነው የአምባሳደሩ መልዕክት ያመላክታል፡፡
видео или голосовое, без подписи
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የ2018 ዓ.ም የጾመ ፍልሰታ የሱባዔ መልእክት አስተላለፉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ለ2018 ዓ.ም ጾመ ማርያም (ፍልሰታ) ባስተላለፉት የቡራኬና የሱባዔ መልእክት፣ ምእመናን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅና ፍቅርን በመተግበር ሱባዔውን እንዲያሳልፉ ጥሪ አቀረቡ። ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው እግዚአብሔርን መውደድ በምናባዊ ነገር ሳይሆን ትእዛዙን በመጠበቅና ባልንጀራን ፤ መላውን የሰው ወገን እንደ ራስ አድርጎ በመውደድ የሚገለጽ መሆኑን ገልጸዋል። ድንግል ማርያም ከአእላፋት መላእክት በላይ የምትበልጥ የአምላክ ማደሪያ በመሆኗ፣ ምእመናን በጾሙ ወቅት የእግዚአብሔርን ትእዛዝ በመጠበቅ እመቤታችንን ሊያከብሯትና በጸሎቷም ሊታመኑ እንደሚገባ አሳስበዋል። በ15ቱ የሱባዔ ወቅት የተራቡትን በመመገብ፣ የታረዙትን በማልበስ፣ የተጣሉትን በማስታረቅ፣ የታመሙትንና የታሰሩትን በመጠየቅ እንዲሁም በንሥሐና በቅዱስ ቁርባን ማለፍ እንደሚገባ አዝዘዋል። በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም ዙሪያ ሥጋት የሆነውንና ፍጥረትን የሚያወድመውን ጦርነት እግዚአብሔር በኃይሉ እንዲያስቆም ምእመናን በሱባዔው ወቅት በትሑት ሰብእናና በቅን ልቦና እንዲጸልዩ አባታዊ አደራቸውን አስተላልፈዋል። ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም
ኤር ኢንዲያ አቶ ተወልደ ገብረማርያም አዲሱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርጎ መሾሙ ተሰማ የታታ ግሩፕ ባለቤት የሆነው ኤር ኢንዲያ ቦርድ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቀድሞ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቪዬሽን ባለሙያ አቶ ተወልደ ገብረማርያምን የአየር መንገዱ አዲስ ዋና ስራ አስፈፃሚና ማኔጅንግ ዳይሬክተር አድርጎ በይፋ መሾሙ ተነግሯል። ይህንን ኃላፊነት ከመረከባቸው በፊት፤ ሐምሌ 2018 መጀመሪያ ላይ አቶ ተወልደ የፓኪስታን አለምአቀፍ አየር መንገድ (PIA) ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆነዉ መመረጣቸው ተዘግቦ ነበር። አዲሱ ዋና ስራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያ አየር መንገድ በቆዩባቸው ዓመታት አየር መንገዱን የአፍሪካ ትልቁና አትራፊው ተቋም እንዲሆን በማድረግ ዓለም አቀፍ እውቅናን ያተረፉ ሲሆን፣ በአስቸጋሪ ጊዜያት ጭምር ያለ መንግስት ድጋፍና የሰራተኛ ቅነሳ ተቋሙን በብቃት መምራታቸው ይነገርላቸዋል።
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የፆታ ውዝግብ( የሆርሞን መብዛት ) ኢትዮጵያዊቷን አትሌት ወደ ወንድ የሚያደላ የሆርሞን መብዛት አለባት በሚል ምክንያት ወደ አሜሪካ ሳትጓዝ ቀረች። በጋና አክራ የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ400ሜ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ያስመዘገበችውና በአሁኑ የአሜሪካ ኦሪገን.... ዩጂን ከ20 አመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ጠንካራ ዝግጅት ስታደርግ የቆየችው እንዲሁም ለአሸናፊነት ቅድመ ግምት የተሰጣት አጃይባ አሊየ ወደ አሜሪካ ሳትጓዝ ቀርታለች። አትሌት አጃይባ በሻምፒዮናው ላይ እንድትወዳደር ስም ዝርዝሯ የገባ እና የአሜሪካ ቪዛ ተሰጥቷት ነበር። ለሲዲ ስፖርት ስማቸው እንዳይገለፅ የፈለጉ ባለሙያ አትሌቷ ከፆታ ውዝግብ ማለትም (ወደ ወንድ የሚያደላ የሆርሞን መብዛት) ጋር በተገናኘ ወደ ስፍራው ሳትሄድ ቀርታለች ማለታቸውን ጋዜጠኛ ሶፎንያስ እና ጋዜጠኛ ግርማቸው ተናግረዋል ። ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያውያኖቹ ፋንቱ ሜጌሶ እና ወርቅ ውሃ ጌታቸው እንዲሁም ደቡብ አፍሪካዊቷ ካስተር ሰሜንያ በተመሳሳይ ጉዳይ ስማቸው ሲነሳ እንደነበር አይዘነጋም ። በሌላ በኩል ደግሞ የአትሌት አጃይባ ስም ውድድሩ ቦታ መለጠፉ ግዮን ማለዳ ተመልክቷል ። የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እና አጋፋሪዎቹ እርስ በእርሱ የሚጣረስ ምክንያት ማቅረብ ሌላ ተጨማሪ ጥፋት ነው ። ጉዳዩ ፈጣንና አስተማሪ እርምጃ ከሚመለከተው አካል ይሻል ትልቅ እድል ነው ያገኘችው በፍጥነት መፍትሔ ማግኘት አለባት ።
ፖለቲከኛ አቶ አበባ አካሉ መታሰራቸው ተሰማ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ትንታኔ በመስጠት እና በፓርቲ ፖለቲካ የሚታወቁት አቶ አበበ በትናንትናው ዕለት መታሰራቸውን የቤተሰብ ምንጮች ለአንዳፍታ ሚዲያ ተናግረዋል፡፡ ፖለቲከኛው በምን ምክንያት እንደታሰሩ ያልታወቀ ሲሆን፤ ባሁኑ ሰአት ሜክሲኮ በሚገኘው የፌዴራል ፖሊስ እንደሚገኙም ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል፡፡
በምዕራብ ትግራይ "አዲስ ግጭት መቀሰቀሱን" የ #ትግራይ ባለሥልጣናት ገለጹ የትግራይ ባለሥልጣናት የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት በምዕራብ ትግራይ “አዲስ ወታደራዊ ጥቃት ከፍቷል” ሲሉ ከሰሱ። ግጭቱ ቅዳሜ ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ማለዳ በምዕራብ ትግራይ ዞን በሸረሪና አቅጣጫ መጀመሩን ገልጸዋል። ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የሚመራው የክልሉ አስተዳደር ዛሬ ባወጣው መግለጫ፥ የፌደራል መንግሥት በምዕራብ ትግራይ ዞን «ግልጽ ጦርነት ከፍቷል» ሲል በመክሰስ ከክልሉ ጋር የቆየውን ፍጥጫ አባብሶታል ብሏል።
• የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የፕሬዚዳንትነት ምርጫ ይፋዊ የእጩዎች ጥቆማ ዛሬ ተጀምሯል” አቶ ኃይሉ ሞላ የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴው ዋና ሰብሳቢ አቶ ኃይሉ ሞላ ዛሬ በጁፒተር ሆቴል መግለጫ ሰጥተዋል። የፌዴሬሽኑ ምርጫ በመጪው መስከረም 5 ቀን 2019 ይካሄዳል። ዘንድሮ ከፊፋ በተሰጣቸው ምክረ ሀሳብ የተሻሻለውን ደንብ መሰረት አድርጎ ምርጫው ፕሬዚዳንታዊ በሆነ መልኩ ብቻ ይካሄዳል። አዲሱ የምርጫ ስርዓት እጩ ፕሬዚዳንቶች የራሳቸውን ካቢኔ ይዘው መወዳደር ይችላሉ። እያንዳንዱ እጩ ፕሬዚዳንት 1 ምክትል ፕሬዚዳንትን ተጠባባቂዎችን ጨምሮ በአጠቃላይ 14 አባላት ያሉት ካቢኔ ይዞ ለውድድር መቅረብ እንደሚጠበቅበት ሰብሳቢው ገልጸዋል። በምርጫው ዕለት ድምጽ የሚሰጠው ለፕሬዚዳንቱ ብቻ ሲሆን አሸናፊው ፕሬዚዳንት ከተመረጠ ያቀረበው ካቢኔ ሙሉ በሙሉ አብሮት ለአራት ዓመታት የሚቆይ ይሆናል። ለፕሬዚዳንትነት የሚወዳደሩ እጩዎች ኢትዮጵያዊ መሆን፣ የመጀመሪያ ዲግሪ እንዲሁም በስፖርቱ ቢያንስ 5 ዓመት እና ከዚያ በላይ ያገለገለ መሆን እንደሚኖርበትም ገልጸዋል። የእጩዎች ጥቆማ ሰነድ ከሐምሌ 24 እስከ ነሐሴ 4 ቀን ድረስ ተሰብስቦ ለፌዴሬሽኑ ጽሕፈት ቤት ገቢ ይደረጋል። ነሐሴ 4 ቀን ታሽጎ የምርጫ አስፈጻሚ ኮሚቴው ይረከባል። ኮሚቴው ሰነዶቹን መርምሮ መስፈርቱን ላላሟሉ ተወዳዳሪዎች የማስተካከያ 3 ቀናት የሚሰጥ ሲሆን በውሳኔው ላይ ቅሬታ ያላቸው አካላት አቤቱታቸውን ለተቋቋመው የምርጫ ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ማቅረብ ይችላሉ። ለፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባኤ አባላት፣ ለባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣ ለፊፋ እና ካፍ የምርጫው መመሪያ ደንብ እና የጊዜ ሰሌዳ ተልኳል። እጩዎች የራሳቸውን የውድድር ሀሳብ እና ፕሮግራም ለስፖርት አፍቃሪው የሚያስተዋውቁበት የመገናኛ ብዙኃን መድረክ እንደሚመቻች ጠቁመዋል።
መልካም ዜና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከነገ ሐምሌ 25 ቀን 2018 ዓ/ም ጀምሮ ከጎንደር ሁመራ ቋሚ የበረራ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል። የበረራ አገልግሎቱ፣ ዘወትር #ቅዳሜ ከጎንደር ወደ ሁመራ የሚደረግ ሲሆን ዘወትር #ሰኞ ደግሞ ከሁመራ ወደ ጎንደር አገልግሎት እንደሚሰጥ አሚኮ ዘግቧል። @tikvahethiopia
🔶JFm ከስርጭት ታገደ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ጄኤፍኤም (JFM) 106.7 የሬዲዮ ጣቢያ ከሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ታሳቢ በሚደረግ ስልጣን ለቀጣዮቹ ስድስት ወራት ከስርጭት ሙሉ ለሙሉ እንዲታገድ መወሰኑን ኖር ሬድዮ ሰምቷል። ባለሥልጣኑ ውሳኔውን ያሳለፈው በጣቢያው ላይ ባደረገው የይዘት ክትትልና በአካል ተገኝቶ ባከናወነው የኢንስፔክሽን ምልከታ በርካታ የሕግና የፈቃድ ውል ጥሰቶችን…