Ethio-Chamber
СтатистикаThe Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations (ECCSA) is an apex organization of Chambers & Sectoral Associations in Ethiopia. It has 21 members including 12 Regional Chambers of Commerce and Sectoral Associations, two City Chambers
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 12:45
- Постов за неделю
- 43
- Всего постов
- 49
- Тип
- открытый
- Язык
- английский
- Категория
- Новости и СМИ (по похожим)
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 956
- 1/48двое суток
- 1 095
- 1/72трое суток
- 1 181
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ስምምነት (AfCFTA) ትግበራ ዙሪያ በሀዋሳ ከተማ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል። ................... በምክር ቤቱ፣ GIZ AU እና በሲዳማ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ትብብር በተዘጋጀው ስልጠና በሲዳማ ክልልና በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ላኪዎች፣ አስመጪዎች፣ አምራቾች እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰማሩ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮችን ተሳትፈዋል። የስልጠናው ዋና ዓላማም የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የAfCFTA ስምምነት ፕሮቶኮሎችን፣ የንግድ ሂደቶችንና የአተገባበር መስፈርቶችን በተሻለ ሁኔታ እንዲረዱ በማድረግ፣ በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማብቃት ነው። የስልጠናው ተሳታፊዎችም ስለ ስምምነቱ መሠረታዊ ሂደቶችና ሊሟሉ ስለሚገባቸው መስፈርቶች የተሻለ ግንዛቤ እንዳገኙና በቀጣይም በየሚሰማሩባቸው የንግድ ዘርፎች ላይ በትኩረት በመስራት በአፍሪካ ገበያ ያላቸውን ድርሻ ለማሳደግ እንደሚጥሩ አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ በAfCFTA ስምምነት በመጠቀም ምርቶችን ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት በመላክ አወንታዊ ውጤቶችን እያስመዘገበች ሲሆን፣ የአፍሪካን ሰፊ ገበያ በበለጠ ለመጠቀም የግሉን ዘርፍ አቅም ማሳደግ እንደሚገባ ተጠቁሟል። የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የኢትዮጵያን የግሉ ዘርፍ በአፍሪካ ገበያ ተወዳዳሪና ተጠቃሚ ለማድረግ ተከታታይ የግንዛቤ ማሳደጊያና የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን እየሠጠ ይገኛል። ❇️❇️❇️❇️ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የአገራችን ባንኮች፤ አምራች ኢንዱስትሪዎችን እንዲሁም የተቀናጀ ግብርናን በፋይናንስ በመደገፍ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በመተካት፣ የወጪ ንግድን በማሳደግና ሰፊ የሥራ ዕድሎችን በመፍጠር ሚናቸውን በሚጠበቅባቸው ደረጃ እና ኃላፊነት እንዲወጡ ቢያግዙ የሚያስመሰግን ተግባር ነው። ከዚህ አንፃር የስንቄ ባንክ በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ዋስትና ፤ የተሻለ የስራ ዕድል የመፍጠርና የመለወጥ አቅም ያላቸው ዜጎችን በፋይናንስ በመደገፍ፤ በክልሉ የሥራ እንቅስቃሴና የሥራ ዕድል ፈጠራ ላይ አበረታች ሚና እንዲጫወቱ የማድረግ ሚናውን እየተወጣ ይገኛል። ሌሎች ክልሎችና የአገራችን ባንኮችም የኦሮሚያ ክልልንና የስንቄ ባንክን ተሞክሮ በመከተል ወጣቶችን፣ አምራቾችንና ኢንተርፕራይዞችን በፋይናንስ በመደገፍና በተሻለ ሁኔታ በመሥራት ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ ብሎም አይተኬ ሚናቸውን እንዲያበረክቱ ምክረ-ሀሳቤን አቀርባለሁ። ❇️❇️❇️❇️ Baankiin Siinqee dargaggoota Oromiyaa rakkoo diinagdeef Saaxilamaniif qabatamaan Wabii ta'u isaa mirkanneesaa jira. Baankiin Siinqee, Mootummaa Naannoo Oromiyaa irraa wabii argateen, Dargaggoota carraa hojii uumuu, kalaquu fi jijjiirama fiduu danda’an maallaqaan deeggaruun, sochii dinagdee fi carraa hojii uumuu Naannichaa keessatti gahee jajjabeessaa taphachaa jira. Baankonni biyyattii biroonis industirii oomishaa fi qonna walitti hidhamiinsa qabu maallaqaan deeggaruu, oomishaalee alaa galan Omisha biyya keessaan bakka buusuu, al-ergii guddisuu fi carraa hojii bal’aa uumuu keessatti gahee isaan irraa eegamu sadarkaa irraa eegamun sirnaan yoo bahatan, dinagdee biyya keenyaa keessatti hojii galataa fi fakkeenyummaa qabu raawwatu. Kanaaf, Naannoleen biroo fi baankonni biyyattii muuxannoo garii Naannoo Oromiyaa fi Baankii Siinqee irraa barachuun, dargaggoota, oomishtoota fi dhaabbilee hojii uumuu keessattj bobba'aaniif maallaqaan deeggaruun, caalaalmaatti hojjechuudhaan guddina dinagdee biyya keenyaa keessatti gahee isaanii isa murteessaa fi bakka hin bu’amne akka bahatan yaadaa fi gorsa koo nan dhiyeessa. ሰብስብ አባፊራ አባጆቢር የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ፕሬዚደንት ❇️❇️❇️❇️❇️ Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in
የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የሲንቄ ባንክን የ2025/26 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም እጅግ ከፍተኛ ነው ሲሉ አደነቁ፡፡ የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የሲንቄ ባንክ የ2025/26 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ ባደረጉት ንግግር የባንኩን ከፍተኛ አፈጻጸም አድንቀዋል። ክቡር ፕሬዝዳንቱ ይህንን የተናገሩት በአዲስ አበባ ስካይላይት ሆቴል በተካሄደው የባንኩ ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር ሲሆን፣ ለባንኩ ማኔጅመንት እና ለአመራሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ክቡር አቶ ሽመልስ አብዲሳ አክለው እንደተናገሩት ባንኩ የፋይናንስ አካታችነትን በማረጋገጥና የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ተሳትፎ በማሳደግ በማህበራዊ-ኢኮኖሚ እና በልማት ድጋፍ ላይ እያደረገ ያለውን ተግባራት አርአያነት ያለው መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ባንኩ እስካሁን ለኢኮኖሚው ያቀረበው ጠቅላላ የብድር የማህበረሰቡን ሕይወት በቀጥታ በመለወጥና የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ያለው ትርጉም እጅግ ከፍተኛ መሆኑን የሚያመላክት ነው ብለዋል፡፡ “ባንኩ የጀመረውን ሁለንተናዊ የዕድገት ጉዞ አጠናክሮ እንዲቀጥል የክልሉ መንግሥት ድጋፍ አይለየውም” ሲሉም ተናግረዋል፡፡ ክቡር ፕሬዝዳንቱ ለባንኩ ማኔጅመንት እና የሥራ ኃላፊዎች ባስተላለፉት የማጠቃለያ መልዕክት፦“የእናንተ ስኬታማነት የሚረጋገጠው፣ በቅርንጫፍ ባንኮቻችሁ አካባቢ የሚኖር ደሃ ሰው ኑሮ ሲለወጥ ነው” ሲሉ ባንኩ በማህበረሰብ ደረጃ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ ❇️❇️❇️❇️❇️ Ethiopian Chamber of Commerce and Sectoral Associations ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት የቢዝነስ አመራር አካዳሚ በአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጣና ዉስጥ ሊተገበር በሚገባ የኤክስፖርት መመሪያ፣ በታክስ ኮምፕሊያንስና በሴቶች የቢዝነስ አመራር ላይ ያዘጋጀዉን ስልጠና ለመዉሰድ የምትፈልጉ ከላይ በተለጠፈዉ ማስታወቂያ ላይ ባለዉ ጊዜና ቦታ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እናሳዉቃለን። ❇️❇️❇️❇️ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in
በአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጣና ሥምምነት ትግበራ ላይ ያተኮረ ስልጠና በሀዋሳ እየተሠጠ ነው። ........................... ስልጠናው የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት (ECCSA) ከGIZ AU እና ከሲዳማ ንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር በአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጣና ሥምምነት (AfCFTA) ትግበራ ዙሪያ ያተኮረ ነው። በሲዳማ ክልልና በሀዋሳ ከተማ የሚገኙ ላኪዎች፣ አስመጪዎች እና በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰማሩ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮችን የስልጠናው ተሣታፊዎች ናቸው። የኢትዮጵያ የንግድንል ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት ምክትል ዋና ጸሐፊ ወ/ሮ ሔለን ረታ ስልጠናው የኢትዮጵያ ነጋዴዎች በአፍሪካ ገበያ የበለጠ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ጉልህ ሚና እንዳለው ገልጸዋል። የነጋዴው ማኅበረሰብ የAfCFTA ስምምነት ፕሮቶኮሎች፣ የንግድ ሂደቶችና የሥምምነቱን የመተግበሪያ ሂደቶች በአግባቡ እንዲረዳ ማድረግ የስልጠናው ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ወይዘሮ ሔለን አብራርተዋል። የሲዳማ ክልል የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የቦርድ አባል ዶ/ር መላኩ አበራ በበኩላቸው፣ ስልጠናው የክልሉ ነጋዴዎች ስለAfCFTA በቂ ዕውቀት እንዲያገኙና በአፍሪካ ገበያ ውስጥ ተሳታፊ እና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ገልጸዋል። ስልጠናውን የሚሰጡት ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና ከሌሎች ተቋማት የተውጣጡ በዘርፉ ሰፊ ሙያዊ እውቀትና ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች ናቸው። ነጋዴዎች የAfCFTA የንግድ ሥርዓትን፣ የንግድ ሂደቶችን፣ የጉምሩክ አሠራሮችን እና በሥምምነቱ የተፈጠሩ የአፍሪካ ገበያ ዕድሎችን በአግባቡ መረዳት እንዳለባቸው ይታመናል። ኢትዮጵያ በቀጣናዊ የንግድ ሥምምነቱ አማካኝነት የንግድ ተሳትፎዋን በማስፋት ምርቶች ወደ ተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተላኩ ሲሆን በተካሄዱ የንግድ ልውውጦችም አወንታዊ ውጤቶች መገኘታቸው ይታወቃል። የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኀበራት ምክር ቤት የግሉን ዘርፍ አቅም ለማሣደግና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆን ከልማት አጋሮች ጋር በመተባበር ቀጣይነት ያላቸውን ሥልጠናዎች እየሠጠ ነው። ❇️❇️❇️❇️ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ስልክ፡ +251115514005 ፋክስ፡ + 251115517699 P. O. Box 517, ኢ.ሜይል: info@ethiopianchamber.com ድረ ገጽ: www.ethiopianchamber.com ቴሌግራም t.me/ethiopiachamber X- https://x.com/EthiopiaChamber ፌስ ቡክ፡ https://www.facebook.com/EthiopianChamber Youtube:https://www.youtube.com/@ethiopianchamber Linkedin(ሊንክዲን):https://www.linkedin.com/company/ethiopianchamber/in
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи