የመጻህፍት ዓለም
Статистикаምርጥ ምርጥ የአማርኛ መፅሀፍቶችን ከዌብሣይታችን ላይ በpdf Download በማድረግ ያንብቡ። ይደሰቱ 👇https://typicalethiopian.com/ethiopian-books/ አስተያየት ካሎት @Ethbookworld_00
- Последний пост
- 14 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 2
- Всего постов
- 27
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- Категория
- Книги
- В каталоге с
- 14 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 230
- 1/48двое суток
- 263
- 1/72трое суток
- 284
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
📚📚📚📚 በቅርብ ቀን 📚📚📚📚
ትንሽ ፍሳሽ ትልቅ መርከብ ታሰጥማለች [ቤንጃሚን ፍራንክሊን] በዚህ ዓለም ቀንቶኣቸው ሊኖሩ የሚችሉት... በገጠማቸው ዕድል ያለ ምንም ማመንታት ና ማወላወል ለመጠቀም ወደ ሁዋላ የማይሉት ብርቱዎች ብቻ ናቸው ፣ የተቀረው የህይወት አጫፋሪዎች ነን! 🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅 እንዴት እንደምናበራው ብናውቅበት 'ብርሃን' በእንያንዳንዳችን ልብ ዉስጥ ነዉ 🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅🔅 ሀዲስ ⬇️⬇️⬇️ Download PDF⬇️⬇️⬇️
#New_BOOK 💣💣💣💣💣 📕ፍቅር እኮ ነው !!! ደራሲ - ሰለሞን ሳህለ ከዚህ ቀደም በ ያማል እና የአፍቃሪ ሰው ትንፋሽ በተባሉት ተወዳጅ የግጥም መፅሐፍቶቹ የምንወደው ሰለሞን ሳህለ በአዲስ መፅሐፍ መጥቶልናል። ፍቅር እኮ ነው !!! አዲስ መፅሐፍ 📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚📚
видео или голосовое, без подписи
видео или голосовое, без подписи
#New_Book 📖📖📖📖📖 “የአምባው ላይ ልዑላን ዩንቨርሲቲ" ======================== የተወዳጁ ደራሲ የፍቅረማርቆስ ደስታ የንስር ዓይን የተሰኝውን መፅሐፍ የተለያዩ አዳዲስ ሐሳቦችን በመጨመር በድጋሚ "የአምባው ላይ ልዑላን ዩንቨርሲቲ" በሚል አዲስ ርዕስ አሳትሞ ለንባብ በቅቷል። በሁሉም የመፅሐፍ መደብሮች ያገኙታል። https://t.me/ethiopian_amharic_pdf_books
#Book_News የ8ኛው “ንባብ ለሕይወት!” ዓመታዊ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ የኢትዮጵያ ቤተ-መዛግብትና ቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት እና ንባብ ለህይወት ኢትዮጵያ ፕሮጀክት በጋር የንባብ ሳምንት እና ዓመታዊ የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ከሐምሌ 23 እስከ ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ሊያካሒዱ ነው። “ንባብ ለሕይወት!” የመጻሕፍት አውደ ርዕይ ዘንድሮ ለ8ተኛ ጊዜ የተሰናዳና አውደ ርዕዩ ከሐሙስ ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ እሁድ ሐምሌ 26 ቀን 2018 ዓ.ም ለአራት ተከታታይ ቀናት በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በደመቀ ሁኔታ ይካሔዳል። በዘንድሮው የ“ንባብ ለሕይወት” አውደ ርዕይ ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደራሲያን፣ የመጻሕፍት አታሚዎች፣ አሳታሚዎችና አከፋፋዮች በስፋት እንደሚሳተፉ እና ለዝግጅቱ ልዩ ትኩረት በመስጠት የሚሳተፉ ስመጥር ተቋማት እንዳሉም አመላክተዋል፡፡ በአውደ ርዕዩ ላይ አንጋፋና ወጣት ደራሲያን በየዕለቱ ከአንባቢያን ጋር የሚገናኙበት የፊርማ እና የፎቶ ፕሮግራም ይኖራል፡፡ የተመረጡ የውይይት ርዕሶች ንባብ በዘመነ ሰውሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence)፤ንባብና ቱሪዝም፤የሙሉ ጊዜ ፀሀፊነትና እናትነት፤ የሙሉ ጊዜ ፀሀፊነትና እናትነት፤ ንባብ በማረሚያ ቤቶች እና ንባብና ክረምት በሚሉ ርዕሰ ጉዳዩች ውይይት የሚደረግበት ሲሆን በተጨማሪም በታዋቂው ደራሲ አዳም ረታ የሥነ-ጽሑፍ አበርክቶና ሁለንተናዊ ሥራዎች ላይ የሚያተኩር ልዩ ጥናታዊ ጽሑፍ ለታዳሚው የሚቀርብበት እንደሆነም ጠቁሟል። ዝግጅቱ ህጻናትንም ያካተተ እንደሆነ ከሐምሌ 24 እስከ 26/2018 ዓ.ም በተለይ በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ በልጆች ሥነ-ጽሑፍ እና ንባብ ላይ የሚያተኩሩ ማራኪ መርሐ ግብሮች መዘጋጀታቸውንና መግቢያው በነጻ እንደሆነና መጻሕፍትን በቅናሽ ዋጋ መግዛት የሚያስችሉ የመጻሕፍት የቅናሽ ኩፖኖች መዘጋጀታቸውም ጠቁመዋል። https://t.me/ethiopian_amharic_pdf_books
እስቲ ዛሬ ደግሞ ለለውጥ ያክል አለቃ ክንፌ የላኩልኝን ግጥም መሳይ ምክር ልጋብዛችሁ! 🖋ከ በዕውቀቱ ስዩም (ለለጅ ምክር የአባት መታዘቢያ) ልዠ ሆይ! ሙቫይልህን አስቀምጥ ምክሬን አድምጥ ! ጦርነትን የሚጠምቀው እድሜውን ብትጠይቀው የማቱሳላ ገራዥ የአብርሀም ዣንጥላ ያዥ በጎሽ ያረሰ አዳምና ሄዋን ገምጠው የተፉትን በለስ አንስቶ የጎረሰ የሎጥን ሚስት ሀውልት የላሰ ሆኖ ታገኘዋለህ ፤ ልዠ ሆይ! ጦርነትን የሚያውጀው ያረጀው ነው የጃጀው ግና ጦርሜዳ ላይ የሚዋጋው ያንተ ብጤ ነው ለጋው፤ ሜሲ አንደመታት ኩዋስ ወደ መቃብር የሚልለጋው፤ ልዠዋ! በጀግኖች ዘመን እንኩዋ-“ከመሞት መሰነበት” ይባላል የሰማእት ሀውልት ሆኖ ተመቆም ህያው ሆኖ መተኛት ይሻላል ልዠ ሆይ! በሀያላን እንዳትታፈስ ሁንባቸው መንፈስ መንፈስ መሆን ቢሳንህ ; ሁንባቸው የጎመን ፈስ ቀን እስኪያልፍ ድረስ ወደ ጎረቤት አገር ንፈስ፤ ልዠ ሆይ ! ጦርነት ማለት አንድ ሀሙስ የቀራቸው ሸባዎች፣ አንድ ሀሙስ ብቻ የኖሩትን አበባዎች የሚያስቀጥፉበት አዝመራ ነውና በሰማእትነት ስም ምትክ አልባ ሕይወትህ ሳይከስም እሸት አካልህን ሳይለውጡት ወደ ፍግ ተግተህ አፈግፍግ፤ ልጄ ሆይ! ለማንም ኩስለመናም ነፍስ ይማር ለማለት አንኩዋ ጊዜ ለሌለው የሙቫይልህን ካሜራ አንጂ ጠመንጃህን አትወልውለው፤ አለቃ ክነፌ በተሳትፎዎ ይቀጥሉበት! ✍ በዕውቀቱ ስዩም
📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖📖 ምርጥ ምርጥ መጻህፍቶችን በ pdf በአንድ የቴሌግራም ቻናል ያግኙ 📱ቴሌግራም ➡️ የመጻህፍት ዓለም ✈️ዌብሳይት ➡️ typical ethiopian ➡️ለአንባቢ ወዳጅዎ SHARE ያድርጉ።
"ማንንም እንዳትጠሉ‼️" ዛሬ ተወዳጁ ከያኒ ቴዲ አፍሮ 50ኛ አመቱን የሚያከብርበት ዕለት ነዉ። ከ15 አመታት በፊት ቴዲ አፍሮ በአዲስአበባ ስታዲየም ባዘጋጀው እና ከ40ሺ በላይ ህዝብ በተገኘበት ኮንሰርት ላይ "ትወዱኛላችሁ...❓" የሚል ጥያቄ ለታዳሚዎቹ አንስቶ "አዎ...‼️"የሚል ምላሽ ካገኘ በኋላ ቴዲ አፍሮም በድጋሚ "ማንንም እንዳትጠሉ...‼️" የሚል ምላሽ ነበር የሰጠዉ። መልካም ቀን‼️
መልካም ልደት ወንድም ጋሻ!! የአገር አድባር የትውልድ ድምጽ የዜማ አባት የፍቅር ገጽ "ስምምነ" ይሁንልነ!! ቴዲ አፍሮ 🖋️ ያሬድ ሹመቴ ሐምሌ 07
ስለ ሰሞንኛው ሲኒማ አምፒር መፍረስ መዓዛ ወርቁ በ Facebook ገጿ ካጋራችው ሬዲዮ ላይ እያወሩ እኮ ነው ስለአምፒር መፍረስ "አምፒር ኢምፓየር ነው አይደል?ኢምፓየር አይደለም። አምፒር አማርኛ ነው።" "ፒያሳ በሲኒማ ቤት ተዳልቶለታል።ወረድ ብሎም ዋፋ ነበር ፈርሷል" እትትት በማለት ደከሙ ቃላት ነው ያጠረኝ መቼስ ማይክራፎን በጨበጡ ሰዎች ድፍንነት። የሆነው ሆኖ እስካለን ታሪክ እያስታወስን ልናስተምራችሁ ግድ ይለናል። ሲኒማ አምፒር ጣሊያን የሰራው ነው። ጣሊያን ሲጠራው ኢምፔሮ ነው የሚለው ፤ሀበሻ በመጥራት ብዛት አምፒር አለው።እንግሊዝኛው እንዳሉት ኢምፓየር ነው። ጣሊያን ሀገር ሲወር የሮማ ኢምፓየር መገንባት ነበር አላማው። ቺኔማ ኢምፔሮን አካባቢውን ፒያሳ ሲለው የከተማ ግንባታው አካል ነበር። ፒያሳ መኪና እና ሳይክል የማያልፍበት ሰው በእግሩ የሚንሸራሸርበት መሀል ከተማ እንደማለት ነው። መኪና የማያልፍበት ፒያሳ በ5ቱ አመት የጣሊያን ወረራ ጊዜ ለጉልበት ስራ የተቀጠረ ካልሆነ በስተቀር ጥቁር ድርሽ አይልበትም ነበር። በዚያው መንገድ በሀገር ፍቅር ጊቢ ውስጥ ጣሊያን ሀበሻን የሚያስርበት ቤት ነበረው። ፈርሷል። ሆኖም ታሪካችን ነው። የሲኒማ አዳራሽን የተመለከ ከአምፒር ጋር ተያይዞ ስቴሪዮ የተባለ የፊልም ማሳያም ነበር። ፈርሷል። ስቴሪዮ በራስ ቲያትር ይዞታ ስር ነበር። ለኪነጥበብም ኪሳራ ነው ይሄ። ዋፋ ሲኒማ የነበረበት ማለት ሰይጣን ቤት ተብሎ ይጠራ የነበረው የመጀመሪያ ሲኒማ ቤት ነው። አለ ። አሁን ኤንቢሲ ቴሌቪዥን ስቱዲዮ አድርጎ ይገለገልበታል። ቦታውም ቴዎድሮስ አደባባይ አጠገብ ነው። እንዲህ ታሪክ እያስጠናን ብንመጣ ኖሮኮ ቅርስ እና ማንነት ዋጋ ይኖራቸው ነበር። ኧረ ኤዲያ!
видео или голосовое, без подписи
የታዋቂው ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ ተወዳጅ የራዲዮ ዝግጅት “መቆያ” በመጽሐፍ ታትሞ ለገበያ ቀረበ ዘወትር ቅዳሜ ከሰዓት እና እሁድ ምሽት በሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ራዲዮ ጣቢያ ለበርካታ ዓመታት ሲያስተላልፍ የቆየውና በአድማጮች ልብ ውስጥ ትልቅ ስፍራ ያለው “እነሆ መቆያ” ፕሮግራም በመጽሐፍ መልክ ታትሞ ለገበያ መቅረቡ ተገለጠ። በአንጋፋው ጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ የሚዘጋጀውና የበርካታ ግለሰቦች፣ አገራት እንዲሁም የተለያዩ ክስተቶች እውነተኛ ታሪኮችን በልዩ የአቀራረብ ስልቱ ሲያስደምጥ የነበረው ይህ ዝግጅት፣ አሁን ላይ ከአድማጮች አልፎ ለአንባቢያን እንዲደርስ ተደርጓል። ይህ ስሜት የሚነኩ ታሪኮችን፣ የሕይወት ትምህርቶችንና የሰው ልጅ ተሞክሮዎችን አቅፎ የያዘው ልዩ የራዲዮ ትውስታ፣ ከድምፅ ዓለም ወደ ጽሑፍ ዓለም በመሸጋገር ለአንባቢያን የተለየ የስሜት ጉዞን እንደሚያበረክት ታውቋል። በጉጉት ሲጠበቅ የነበረውና በብዙዎች ዘንድ ከፍተኛ አክብሮት የተቸረው የጋዜጠኛ እሸቴ አሰፋ “መቆያ” መጽሐፍ በአሁኑ ወቅት በጃፋር መጻሕፍት መደብር ውስጥ ለሽያጭ መቅረቡ ተረጋግጧል።
የባሕርን ምስጢር ያገኘሁት በጤዛ ላይ በማተኮሬ ነው -ካህሊል ጂብራን - #one_quote_for_the_day @ethiopian_amharic_pdf_books
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መፃህፍት ዐውደ ርዕይ አርብ ሰኔ 5 2018 የደራሲያን ልምድ ማካፈል መርሐ ግብር #AAUBOOKFAIR2026
ይቅርታ (በድሉ ዋቅጅራ) ባልንጀሬን በጩቤ ወግቼ፣ አዝኜ ይቅርታ ብለው፤ ከሚፈሰው ደሙ ቀድሞ፣ ሳቅ አፍኖ ገደለው፡፡ ------------------
18ኛው ዓመታዊ የመጻሕፍት ዓውደ ርዕይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በይፋ ተከፈተ፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ የሚያዘጋጀው 18ኛው ዓመታዊ የመጻሕፍት ዓውደ ርዕይ በስድስት ኪሎ ዋናው ግቢ በድምቀት ተከፍቷል። ከዛሬ ሰኔ 1 እስከ ሰኔ 7 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ለሰባት ተከታታይ ቀናት ይቆያል ይምጡና ይታደሙ፤ መጻሕፍቶችን ይሸምቱ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ
18ኛው የአዲስ አበባ ዩንቨርሲቲ የመፅሐፍ ዓውደ ርዕይ ዛሬ ሰኞ ከጠዋቱ 4:00 በይፋ ይከፈታል ============================== አስራ ስምንተኛው የአዲስ አበባ ዩንበርስቲፕሬስ የመፅሐፍ ዓውደ ርዕይ እና ሽያጭ ዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም በይፋ መከፈቱ ይታወቃል:: በዚህ የመፅሐፍ ዓውደ ርዕይ እና ሽያጭ ላይ የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፕሬስ ከአዳዲስ መፅሐፎቹን ይዞ አውደ ርዕዩ ላይ ይገኛል:: እንዲሁም ከ40 በላይ አሳታሚዎችና አከፋዮች በቅርቡ የታተሙ መፅሐፍቶችን ይዘው በዓውደ ርዕዩ ላይ እስከ እሁድ ሰኔ 7ቀን ድረስ ይጠብቋችኃል:: በዚህ የመፅሐፍ ዓውደ ርዕይ ላይ ከገበያ የጠፉ እና በርካታ መፅሐፎች : የህፃናት መፅሐፎች: የሐይማኖት መፅሃፎችን ያገኛሉ:: 🗓️ ከ ሰኔ 1 - 7 2018ዓ.ም 📍 AAU Main Campus, 6Kilo ሁላችሁም እንድትገኙ ተጋብዛችኃል!!
18ኛው የመጽሐፍት ዓውደ ርዕይ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 🗓️ ከ ሰኔ 1 - 7 2018ዓ.ም 📍 AAU Main Campus, 6Kilo አይቀርም👌