tgindex
Ethio Radar|ኢትዮ ራዳር

Ethio Radar|ኢትዮ ራዳር

Статистика
@ethioradarinfoанглийский

Welcome to Ethio Radar, a professional news analysis platform brought to you by a dedicated team of experienced journalist. stay informed,stay on radar! እንኳን ወደ ኢትዮ ራዳር ቻናል መጡ,ሀሳብ፣አስተያየት፣ መረጃ ለማጋራት ማስታወቂያ ለማሰራት በ @Ethioradarr01 ያናግሩን

Последний пост
12:50
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
3
Всего постов
30
Тип
открытый
Язык
английский
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
54 530
−493 за 4 дн.
Сутки
−115
−0,21%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
817
27 постов
Вовлечённость
1,5%
к подписчикам
Постов в день
0,4
всего 30
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
711
1/48двое суток
814
1/72трое суток
878

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • 12:5030111

    የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ❗️❗️ ​የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለሥራው ዓለም የሚያዘጋጅ አዲስ የአተገባበር ማንዋል ይፋ ማድረጉን አስታወቀ። ​ይህ አዲስ መመሪያ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ የራሳቸውን ሥራ መፍጠር እንዲችሉና የ21ኛ ክፍለ ዘመን ክህሎት እንዲጨብጡ ለማስቻል ያለመ ሲሆን፤ በውስጡ የያዛቸው ዋና ዋና ነጥቦች እንደሚከተለው ተብራርተዋል፦ ​📌 11 አዳዲስ የሙያ ዓይነቶች፦ በግንባታ፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ቢዝነስ፣ IT፣ ግብርና እና ጤና ሳይንስ ዘርፎች ተዘጋጅተው ለተማሪዎች እንዲቀርቡ ተደርጓል። ​📌 የተማሪዎች ምርጫ፦ ማንኛውም ተማሪ ከአቅሙና ከፍላጎቱ ጋር የሚሄድ አንድ የሙያ ዓይነት ብቻ መርጦ የሚማር ይሆናል። ​📌 የትምህርት ቤቶች አተገባበር፦ ትምህርት ቤቶች ሁሉንም 11 ሙያዎች በአንድ ጊዜ እንዲያስተምሩ አይገደዱም፤ ይልቁንም እንደ አቅማቸውና እንደ አካባቢው ሁኔታ ተስማሚ የሆኑትን መርጠው እንዲተገብሩ ተፈቅዶላቸዋል። @ethioradarinfo

  • 12:123091

    በአደጋው የሰዎች ሕይወት ሊያልፍ ችሏል በማዕከላዊ ሲዳማ ዞን ዳሌ ወረዳ አካባቢ ነሐሴ 9 ቀን ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ገደማ በደረሰ ከባድ የትራፊክ አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፣ በ4 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል። አደጋው ከሐዋሳ ወደ ዓለታ ወንዶ በሚጓዝ የዶልፊን ተሽከርካሪ እና በተቃራኒ አቅጣጫ በሚጓዝ የኤፍኤስአር መኪና መካከል በተፈጠረ መጋጨት የተነሳ መንገድ ዘግተው በቆሙ ሌሎች ተሽከርካሪዎች ላይ አንድ የሲኖትራክ መኪና ተደርቦ በመጋጨቱ የተከሰተ ሲሆን፣ በአጠቃላይ በ11 ተሽከርካሪዎች ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል። @ethioradarinfo

  • 10:2734411

    4 ኪሎ ወርቅ ተያዘ❗️ ከዱባይ ወደ አዲስ አበባ የተጓዘ አንድ ግለሰብ በህገ-ወጥ መንገድ ሊያሳልፈው የነበረ 4 ኪሎ ግራም ጥፍጥፍ ወርቅ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ። ተጠርጣሪው ከፍተኛ ዋጋ ያለውን ይህን ወርቅ በለበሰው ውስጥ ሱሪ ውስጥ በመሸሸግ ለማሳለፍ ሲሞክር በኤርፖርቱ ጉምሩክ ሰራተኞች በተደረገበት ጥብቅ አካላዊ ፍተሻ እጅ ከፍንጅ ሊያዝ ችሏል። በአሁኑ ወቅት ግለሰቡ በህግ ጥላ ስር ውሎ የምርመራ ስራዎች እየተከናወኑበት የሚገኝ ሲሆን፣ የጉምሩክ ኮሚሽን ኮንትሮባንድን በመግታት ረገድ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ለኤርፖርቱ ሰራተኞች እና አመራሮች ምስጋና ማቅረቡን ሀገሬ ቲቪ ዘግቧል። @ethioradarinfo

  • 💵የገንዘብ የመግዛት አቅም 21.05% በየአመቱ እየቀነሰ ገንዘቦትን ባንክ ማስቀመጥ ኪሳራ ነው።💵 ታዲያ ‼️6 ሳይቶችን ሰርተን አስረክበን አሁን ደግሞ (ያለምንም ወለድ እና inflation ) በተዋዋሉበት ብቻ የሚከፍሉትን ሳይት ይዘንሎ መተናል‼️ ከቤተመንግስት አቅራቢያ 📍(አዋሬ) ባለ 3 መኝታ (ከ121ካሬ -157 ካሬ) ከ121ካሬ ጀምሮ ሙሉ ለሚከፍሉ 8,415,000ብር ረጋ ብለው ለሚከፍሉ-12,947,000 ቅድመ ክፍያ-2,589,400(20%)              እስከ 157 ካሬ ሙሉ ለሚከፍሉ-10,919,000 ረጋ ብለው ለሚከፍሉ  -16,799,000 ቅድመ ክፍያ-3,359,000 ብር     📍በቡልጋሪያ (68ካሬ -142ካሬ)       ባለ 1መኝታ ከ68 ካሬ ጀምሮ ሙሉ ለሚከፍል-5,474,000ብር ረጋብለው ለሚከፍሉ-7,820,000 ቅድመ ክፍያ-1,564,000 ብር ባለ 2 መኝታ ከ87 ካሬ ጀምሮ ሙሉ ለሚከፍሉ-7,003,500ብር ረጋ ብለው ለሚከፍሉ-10,350,000 ቅድመ ክፍያ-2,000,000 ብር ባለ3 መኝታ ከ121 ካሬ ጀምሮ ሙሉለሚከፍሉ-9,740,000ብር ረጋ ብለው-13,915,000ብር ቅድመ ክፍያ-2,783,000ብር 📍በሀያት 49 ባለ 3 መኝታ 146&180 ካሬ 📍በፒያሳ ባለ3 መኝታ 136&142 ካሬ ✂️የንግድ ሱቅ 📍በፒያሳ አጠቃላይ ክፍያ-4,800,000 በቅድመ ክፍያ-1,400,000 📍በቡልጋሪያ አጠቃላይ ክፍያ-3,900,000 ቅድመ ክፍያ-900,000 📍በገላን ሙሉ ክፍያ-2,500,000 ቅድመ ክፍያ-500,000 ለበለጠ መረጃ            ☎️ +251938049922                Telegram @yovma

  • без подписи

  • ወጣቱ ቲክቶክር አዶናይ ታዋቂውን የ«ቢኪላ አዋርድ» አሸነፈ! በዲጂታል ሚዲያና በማህበራዊ ዘርፍ በወጣቶች ዘንድ አዎንታዊ ተፅዕኖ ሲፈጥር የቆየው አዶናይ በርሃነ ሀይለሚካኤል፣ በካናዳ በሚዘጋጀው ስመ-ጥር ዓለም አቀፍ የ2026 «ቢኪላ አዋርድ» (Bikila Award) የዓመቱ «Youth Impact Award» አሸናፊ በመሆን ስሙ ይፋ ተደርጓል። ​ከዚህ ቀደም እንደ አርቲስት ቴዲ አፍሮ ያሉ ግዙፍ የሀገራችን ባለሙያዎች የተቀበሉትን ይህንን የክብር ሽልማት አዶናይ መረከቡ፣ በዲጂታል ሚዲያው ዘርፍ ላሳየው የላቀ እንቅስቃሴ የተሰጠው ትልቅ ዕውቅና ተደርጎ ተወስዷል። ​በዘንድሮው የቢኪላ አዋርድ ዙሪያ የወጡ ዋና ዋና መረጃዎች፦ ​📌 የስነ-ስርዓቱ ዝርዝር፦ የሽልማት ስነ-ስርዓቱ በቶሮንቶ ካናዳ «Daniels Spectrum» አዳራሽ፣ ቅዳሜ Sep 26, 2026 ከምሽቱ 12:00 ጀምሮ ይካሄዳል። የካናዳ ፓርላማ አባል ክብርት ዶሊ Begum በዋና ተናጋሪነት እንዲሁም አንጋፋው የቴክኖሎጂ ባለሙያ ሳምሶን ደሚሴ ተፈራ በዋና አቅራቢነት ይመሩታል። ​📌 ሌሎች የክብር ተሸላሚዎች፦ ​ሎሬት አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ (ከሞት በኋላ)፦ ለአፍሪካ ጥበብና ባህል ላበረከቱት አስተዋጽኦ ​አቶ ሳሙኤል ታፈሰ (የሳንሻይን ኢንቨስትመንት ግሩፕ መሥራች)፦ የሕይወት ዘመን ዕውቅና ​አና ጌታነህ (የ African Mosaique መሥራች)፦ የሙያ ብቃት ዕውቅና ​ዶክተር ምህረት ደበበ፣ ገዛሁ በቀለ፣ አብነት ታደለ እና በ GTA የሚኖሩ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ በተለያዩ ዘርፎች የላቀ ዕውቅና አግኝተዋል። ​📌 የትምህርት ብቃት አሸናፊዎች፦ ቢኤምነት አስፋው፣ ኦሊያድ ሩንዳሳ፣ ናትናኤል ተሾመ፣ ኤደን በላይ እና ዮምኒ መኮንን የዘንድሮው የትምህርት ብቃት አሸናፊዎች ሆነዋል። @ethioradarinfo

  • ፊንቴክ ❗️ በፊንቴክ ኢንቨስትመንት ሽፋን በተፈጸመ ማጭበርበር የተጠረጠሩት አርቲስቶችና ቲክቶከሮች ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረጉ ተሰማ። ​የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት በዋሉት ችሎት የሰጣቸው ውሳኔዎችና ያከናወናቸው አሰራሮች እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፦ ​📌 የመቃወሚያው ውድቅ መደረግ፦ ተከሳሾች "የሠራነው የማስታወቂያ ሥራ እንጂ የኮምፒውተር ማጭበርበር ወንጀል አልፈጸምንም" ሲሉ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ውድቅ አድርጎታል። ​📌 የዐቃቤ ሕግ አቤቱታ፦ ተከሳሾቹ "እግረኛው" በተሰኘ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጽ ላይ መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ፣ ድርጊቱ በፍትሕ ሂደቱ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል በሚል ዐቃቤ ሕግ ባለ 5 ገጽ አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል። ​📌 የችሎቱ ተለዋጭ ቀጠሮ፦ ፍርድ ቤቱ የቀረበውን አቤቱታና ጉዳዩን ለማጣራት ጋዜጠኛ ተክለሃይማኖት አዳነ እና ጠበቃ አበባው አበበ በችሎት ተገኝተው የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ለጥቅምት 02 ቀን 2019 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። @ethioradarinfo

  • ሴኔጋልን ጨምሮ የ30 የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች ለንግድና ለጉብኝት (B1 እና B2) ወደ አሜሪካ ለመጓዝ የቪዛ ማመልከቻ በሚያስገቡበት ወቅት እስከ 20 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የዋስትና ማስያዣ እንዲከፍሉ የሚያስገድድ አዲስ መመሪያ ተጣለ። ​የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ይህ አሰራር የቪዛ ጊዜያቸውን አጠናቀው በህገ-ወጥ መንገድ የሚቀሩ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ ያለመ ነው ሲል የገለጸ ሲሆን፤ በአንጻሩ የስደተኞች እና የጉዞ መብት ተሟጋቾች ውሳኔው ህጋዊ ተጓዦችን በማስደንግጥና ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጫና በመፍጠር ህጋዊ የሆኑ ጉዞዎችን የሚያስቀር ነው ሲሉ ተችተውታል። @ethioradarinfo

  • የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሙሉ የራስ-ገዝነት (Autonomy) መብቱን ተግባራዊ ለማድረግ ባካሄደው አዲስ የመዋቅር ማስተካከያ ምክንያት፣ ከ500 በላይ የሥራ አመራርና አስተዳደር ሠራተኞች እንዲሁም 50 መምህራን ያለ ምደባ መቅረታቸው ተገለጸ። ​ከዚሁ የሪፎርም እርምጃ ጋር ተያይዞ የወጡ ዋና ዋና መረጃዎች፦ ​📌 የምደባው መስፈርት፦ ምደባው ለአስተዳደር ሠራተኞች በፈተና ውጤት፣ ለመምህራን ደግሞ በተማሩት የትምህርት ዘርፍ አግባብነትና ዝግጅት ላይ ብቻ ተመስርቶ የተከናወነ መሆኑ ተጠቅሷል። ​📌 የፕሬዚዳንቱ ማብራሪያ፦ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በጉዳዩ ላይ በሰጡት ምላሽ «ማንም ሠራተኛ አልተባረረም» ያሉት ሲሆን፣ ያለ ምደባ የቀሩት ሠራተኞች በጡረታ፣ በካሳ ክፍያ ወይም ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ በሚጀምራቸው የንግድ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ተካተው መፍትሔ እንደሚሰጣቸው አረጋግጠዋል። ​📌 ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች አቅጣጫ ጠቋሚ፦ በሀገሪቱ ከሚገኙ 46 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል የመጀመሪያው ሞዴል የራስ-ገዝ ተቋም የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሪፎርም እርምጃ፣ ቀጣይ ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ በመዘጋጀት ላይ ለሚገኙት እንደ ጂማ፣ መቐለ፣ ባህር ዳር እና ጎንደር ዩኒቨርሲቲዎች ትልቅ ማሳያ እንደሚሆን ተገልጿል። @ethioradarinfo

  • 2 авг.1 03032

    አማራ ክልል የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ሆኗል ተማሪዎች ውጤታቸውን https://amhara.ministry.et/#/result የሚለውን አድራሻ በመፃፍ ፤ በሚመጣው ቅጽ ላይ  የተማሪ መለያ ቁጥር (Registration Number) እና ስም በአማርኛ በማስገባት ፤ ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡

  • በቀድሞ የህወሓት አመራሮች የተመሰረተው ስምረት ፓርቲ፣ የትግራይ ሕዝብ የማይፈልገውና የማይመኘው አዲስ ወታደራዊ ግጭት መከሰቱን አስመልካች እጅግ ጠንካራ መግለጫ አውጥቷል። ​የፓርቲው መሪ አቶ ጌታቸው ረዳ ባስተላለፉት መልዕክትና በመግለጫው የተካተቱት ዋና ዋና ነጥቦች፦ ​📌 «የሳተላይት ክትትል ውጤቱን ጠብቁ»፦ ግጭቱን ማንና መቼ እንደጀመረው ለማወቅ አስቀድሞ ተዘጋጅቶ የወጣውን የኋላቀሩ ቡድን መግለጫ ከመስማት ይልቅ፣ ገለልተኛ አካላት የሚያደርጉትን የሳተላይት ክትትልና የክትትሉን ውጤት መጠበቅ ተገቢ መሆኑ ተገልጿል። ​📌 የውጭ ኃይሎች እጅና የፕሪቶሪያ ውል ጥሰት፦ አሁን የተከፈተው ጦርነት በውጭ ኃይሎች ፍላጎትና እቅድ የሚመራ መሆኑን በመጥቀስ፤ ቡድኑ የፕሪቶሪያውን የሰላም ውል በመጣስና የጊዜያዊ አስተዳደሩን ሥልጣን በኃይል ገልብጦ ህገ-ወጥ አስተዳደር ከመሠረተ በኋላ አሁን "ግዛታዊ አንድነትን ማስከበር" በሚል ሽፋን አዲስ ጦርነት ደግሷል ሲል ከሷል። ​📌 «ወደ አራት ኪሎ እንመለሳለን የሚለው ቅዠት ይቁም»፦ አቶ ጌታቸው ረዳ ለትግራይ ሠራዊት አመራሮችና አባላት ባስተላለፉት መልዕክት፣ በግዳጅ ወጣቱን በመመልመል "ወደ አራት ኪሎ እንመለሳለን" የሚለውን ቅዠት በአስቸኳይ ማቆም እንደሚገባ አሳስበዋል። ​📌 «ለወንጀለኞች ህልውና አትሙቱ»፦ አቶ ጌታቸው አክለውም፣ ለሠራዊቱ አባላት ሊያሳስባቸው የሚገባው በጣት የሚቆጠሩ ወንጀለኞች ህልውና ሳይሆን የትግራይ ሕዝብ ሰላምና ህልውና በመሆኑ በሕይወታቸውና በአካላቸው ላይ የሚጫወቱ አካላትን "ይበቃል" ሊሏቸው እንደሚገባ ጥሪ አቅርበዋል። ​ፓርቲው አክሎም በሃውልቲ የመሸገው ቡድን የዲፕሎማሲ በሮችን ዘግቶና ከውጭ አካላት በሚጠበቅ እርዳታ ተመክቶ ሁኔታዎችን ካበላሸ በኋላ "ዓለም ስማኝ" ማለቱ የአስተዋይነት ማነስን የሚያሳይ ነው ሲል ድርጊቱን በጽኑ ኮንኗል። @ethioradarinfo

  • без подписи

  • የቀድሞው የዓለም ባንክ ፕሬዝዳንት ዳቪድ ማልፓስ የኢትዮጵያ ብር መዳከም እና የውጭ ምንዛሬ ማሻሻያዎች ድህነትን በከፍተኛ ሁኔታ ማባባሳቸውን በመግለጽ፤ በብር ደመወዝ የሚከፈላቸው ሰዎች «ገቢያቸው እጅግ ቀንሷል» ሲሉ ተናግረዋል። ​ባለሙያው ባቀረቡት የፖሊሲ ጥናት ላይ ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፦ ​📌 የገቢ መቀነስ እና የጥቂቶች ተጠቃሚነት፦ የምንዛሬ ማሻሻያው የሠራተኛውን ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ ያዳከመ ሲሆን፤ በተቃራኒው ጥቂት ቡድኖች የውጭ ምንዛሬን እና የሀገር ውስጥ ብድርን በልዩ ሁኔታ ማግኘት በመቻላቸው ብቻ ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመዋል። ​📌 የኢትዮጵያ ግዙፍ የእድገት አቅም፦ ማልፓስ በስታንሊ ፊሸር መታሰቢያ መድረክ ላይ ኢትዮጵያን በዋና ምሳሌነት ያቀረቡ ሲሆን፤ ሀገሪቱ ሰፊ የእርሻ መሬት፣ ሀብታም የተፈጥሮ ሀብት፣ የውኃ፣ ተስማሚ የአየር ንብረት እና የሰው ኃይል አቅም ያላት በመሆኗ «ትልቅ የእድገት አቅም» ያላት ሀገር መሆኗንም አብራርተዋል። @ethioradarinfo

  • የንግድ ሱቅ በመሃል ሳርቤት ከ 11 ካሬ _43 ካሬ የንግድ ሱቆች ማግኘት ይችላሉ ✅ground _3,500,000 ብር ቅድመ ክፍያ ✅1st floor _2,500,000 ብር ቅድመ ክፍያ ✅2nd floor _ 2,000,000 ቅድመ ክፍያ ✅3rd floor _1,300,000 ብር ቅድመ ክፍያ ✅4th floor _ 900ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ✅5th floor _900 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ 🎯ይህ የማይደገም እድል ነው 🎯ሳርቤት አደባባብዩ  ፊት ለፊት 🎯ዘመናዊ እና ማራኪ የንግድ ሱቅ ☎️0938-04-99-22 ☎️0990-22-09-02

  • ተራዝሟል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመዲናዋ የሚካሄደውን የግል መኖሪያ ቤቶች የአከራይና ተከራይ ውል እድሳት ምዝገባ ጊዜ እስከ ነሐሴ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ማራዘሙን አስታወቀ። ​ከተማ አስተዳደሩ ቀደም ሲል የምዝገባው ማጠናቀቂያ እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም እንዲሆን አስታውቆ የነበረ ቢሆንም፣ የሕብረተሰቡን ጥያቄ መሠረት በማድረግ ነዋሪው ያለምንም መጨናነቅ ውል መዋዋል እንዲችል ቀኑን እንዲራዘም ተደርጓል። ​ከውል እድሳቱ ጋር ተያይዞ የወጡ ዋና ዋና መረጃዎች፦ ​📌 የኪራይ ጭማሪ ጣሪያ፦ ከተማ አስተዳደሩ የዜጎችን የኑሮ ጫና ለመቀነስ እና በኪራይ ገበያው ላይ የሚስተዋሉ ሕገ-ወጥና ዘፈቀደ አሰራሮችን ለመግታት የቤት ኪራይ ጭማሪ ጣሪያ 11.5 በመቶ እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል። ​📌 አገልግሎቱ የሚሰጥባቸው ቦታዎች፦ ነዋሪዎች አስፈላጊውን መረጃ በመያዝ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች፣ በየወረዳው በተዘጋጁ የውል መስጫ ቦታዎች እና በሁሉም ክፍለ ከተማ "አዲስ መሶብ" የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫዎች መስተናገድ ይችላሉ። @ethioradarinfo

  • የ«እግረኛው» የበይነ-መረብ ሚዲያ ባለቤት ተክለሃይማኖት አዳነ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ተሰማ! @ethioradarinfo

  • አዲስሳይት 👉Studio 32ካሬ ✅1 መኝታ 60ካሬ ጀምሮ ✅2 መኝታ 90ካሬ ጀምሮ እና ✅3 መኝታ ከ 112ካሬ ጀምሮ 👉40% ለምትከፍሉ 10% ቅናሽ ቀሪውን 60% ቤቱን ስትረከቡ የምትከፍሉት 👉100% ለሚከፍሉ እስከ 35% ቅናሽ 👉4B+4SB+18 የሆነ ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት 👉 በመገናኛ ጫካ ፕሮጀክት ከቴምር ሪልስቴት 💥 የንግድ ሱቆች ⨳ #ቡልጋሪያ ላይ ከ900ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ፣ ⨳ #ፒያሳ ላይ ከ1.4ሚሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ፣ ⨳ #ቃሊቲገላን ላይ ከ500ሺህ ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ።     #ቴምርሪልስቴት #ቴምርፕሮፐርቲስ ለበለጠ መረጃ ይደውሉ        👇👇👇👇👇👇 ☎️09-38-04-99-22 ☎️09-90-22-09-02

  • без подписи

  • ተሽከርካሪዎች ግብር ሊከፍሉ ነው በመንግሥት በተገነቡ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች በየዓመቱ የሚከፍሉት አዲስ ግብር ሊጣልባቸው መሆኑ ተሰማ። ​የምጣኔ ሀብት ባለሙያው አቶ ዋስሁን በላይ እንደገለጹት፣ ይህ ክፍያ በተሽከርካሪ ባለቤቶች ላይ የሚጣል ሲሆን፥ ተሽከርካሪዎቹ በመንግሥት በተገነቡ መንገዶች ላይ አገልግሎት ስለሚሰጡ በየዓመቱ የሚከፈል የታክስ ግዴታ ይሆናል። ​የታክስ ፕሮፖዛሉን የተመለከቱ ዋና ዋና ነጥቦች፦ ​📌 ከቦሎ ጋር የተያያዘ አሰራር፦ አዲሱ ግብር ከመደበኛው የተሽከርካሪ ዓመታዊ የቴክኒክ ምርመራ (ቦሎ) ጋር ተያይዞ ሊመጣ የሚችል ግዴታ እንደሆነ ተመላክቷል። ​📌 የጭስ ልቀት መጠንና የክፍያ ልዩነት፦ ክፍያው የተሽከርካሪዎችን እድሜና የአካባቢ ብክለት መጠን ያገናዘበ ሲሆን፣ ከፍተኛ የካርቦን ጭስ የሚለቁ አሮጌ ተሽከርካሪዎች ከፍተኛ ግብር፣ አዳዲስና አነስተኛ ጭስ የሚለቁ ተሽከርካሪዎች ደግሞ ዝቅተኛ ግብር እንዲከፍሉ ሊደረግ እንደሚችል ተገልጿል። ​📌 የሕግ ረቂቅ ሁኔታ፦ ይህ የታክስ ፕሮፖዛል በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተዘጋጅቶ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለጸደቃ እንዲቀርብ የዝግጅት ሥራዎች እየተጠናቀቁ ይገኛሉ። @ethioradarinfo

  • አደገኛው አዘዋዋሪ በቁጥጥር ስር ዋለ ​የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ከኢንተርፖል እና ከማላዊ ፖሊስ ጋር ባደረገው የተቀናጀ አደገኛ ወንጀለኞችን የማደን ዘመቻ፣ በበርካታ ወጣቶች ላይ ከባድ ኢሰብአዊ ድርጊት ሲፈጽም የቆየውን አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪ አድነው ባሻው ውዳሞን በማላዊ በቁጥጥር ሥር ውሎ ወደ ሀገር እንዲመጣ መደረጉን አስታወቀ። ​በፖሊስ መግለጫ መሠረት የተጠርጣሪው ዘግናኝ ድርጊቶች እና የቁጥጥር ስራ ሂደቶች የሚከተሉት ናቸው፦ ​📌 የማታለያ ዘዴው፦ ተጠርጣሪው ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል (ከሀድያ እና ከንባታ አከባቢዎች) ወጣቶችን ወደ ደቡብ አፍሪካ ለማሻገር በሚል እስከ 800 ሺህ ብር እየጠየቀ ሲያታልል ቆይቷል። ​📌 የፈጸመው ኢሰብአዊ ድርጊት፦ ተጓዦችን በኬንያና ታንዛኒያ በኩል በኮንቴነር አጭቆ በመጫን፣ በየጫካው ጥሎ በመጥፋት፣ በረሃብና በኤሌክትሪክ ንዝረት በማሰቃየት እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ በማስፈራራት ሲቀበል እንደነበር ተገልጿል። ​📌 ለሀገር አሳልፎ መሰጠት፦ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ሲደረግ በቆየ ጥብቅ ክትትል ማላዊ ውስጥ በቁጥጥር ሥር የዋለው ተጠርጣሪው፣ ሐምሌ 22 ቀን 2018 ዓ.ም ለኢትዮጵያ አሳልፎ ተሰጥቷል። ​የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ መሰል አደገኛ ሕገ-ወጥ የሰው አዘዋዋሪዎችንና ወንጀለኞችን የማደኑን ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥል በመግለጽ፣ ህብረተሰቡ መሰል ድርጊቶችን ሲመለከት በነፃ ስልክ መስመር 991 ወይም በ EFPApp ጥቆማ እንዲሰጥ ጥሪ አቅርቧል። @ethioradarinfo