tgindex
Sport24

EtSport24 sport news channel

Последний пост
28 июл.
Последнее чтение
13 авг.
Постов за неделю
0
Всего постов
21
Тип
открытый
Язык
und
В каталоге с
13 авг.
Подписчики
2 779
−7 за 4 дн.
Сутки
−1
−0,04%
Неделя
 
Месяц
 
Просмотров на пост
430
21 постов
Вовлечённость
15,5%
к подписчикам
Постов в день
0,0
всего 21
Упоминаний
0
каналов
Охват размещения
оценка
1/24сутки в ленте
165
1/48двое суток
189
1/72трое суток
203

Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.

Посты

  • ዩአፋ በጂያኒ ኢንፋንቲኖ የዓለም ዋንጫ የግል ኢንቨስትመንት ዕቅድ ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ አሰማ። የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ፣ ፊፋ ውድድሮቹን፣ የዓለም ዋንጫን ጨምሮ፣ ለግል ባለሀብቶች ክፍት ለማድረግ ያቀደውን ዕቅድ አጥብቆ ተቃወመ። ፊፋ "ፊፋ ፎርዋርድ ኢንተርፕራይዝ የተባለ አዲስ ቅርንጫፍ ኩባንያ በማቋቋም በንግድ እና በውድድር ስራዎቹ ላይ አነስተኛ እና ውሳኔ ሰጪ ያልሆኑ የሶስተኛ ወገን ኢንቨስትመንቶችን ለመጋበዝ አቅዷል። የአሜሪካ የቬንቸር ካፒታል ድርጅት የሆነው ትራይቭ ኤተርናል የታቀደውን የባለሀብቶች ቡድን ይመራል ተብሎ ይጠበቃል። ዩኤፋ በሰጠው ጥብቅ መግለጫ የእግር ኳስ ነፍስ እና አስተዳደር ሊነግዱባቸው የሚገቡ ንብረቶች አይደሉም ብሏል። ይህ ዕቅድ "መቼም ቢሆን መታለፍ የሌለበትን መስመር የተሻገረ ነው" በማለት ፊፋ ውድድሮችን በማስፋፋት እና ድግግሞሻቸውን በመጨመር የራሱን ውድድሮች ሊያስተጓጉል እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል። ጉዳዩ በሚቀጥለው መኸር በሚደረገው የፊፋ ካውንስል ስብሰባ እና በታህሳስ ወር በሚካሄደው የፊፋ አህጉር አቀፍ ዋንጫ ላይ የሚነሳ ሲሆን፣ በመጋቢት ወር በሞሮኮ በሚካሄደው የፊፋ ኮንግረስ ላይ በ211ቱ አባል ሀገራት ድምጽ ሊሰጥበት ይችላል።

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • እንግሊዝን ስጋት ላይ የጣለው የአዝቴካ ስታዲየም ከፍታና የዲየጎ ማራዶና የእጅ ግብ ታሪክ። በአለም ዋንጫ በ16 ጥሎ ማለፍ ከሚጠበቁ ጨዋታዎች መካከል የጥምር አዘጋጇ ሜክሲኮ ከእንግሊዝ የሚያደርጉት ፍልሚያ ነው። ጨዋታው በታሪካዊው አዝቴካ ስታዲየም ይደረጋል። ይህ ስታዲየም 87523 ተመልካቾች መያዝ የሚችል ፣ በላቲን አሜሪካ በግዝፈቱ ተወዳዳሪ የሌለውና በአለም 8ኛው ትልቅ ስታዲየም ነው። አዝቴካ ስታዲየም የ1970 እና 1986 ሁለት የአለም ዋንጫ ፍጻሜዎችንም አስተናግዷል።ይህ ስታዲየም ከባህር ጠለል  በ2240 ሜትር ከፍታ ላይ የሚገኝ ሲሆን የብዙ እግር ኳስ ቡድኖችን ትንፋሽ ያቆመ ነው። የእንግሊዝና ሜክሲኮን ጨዋታ ከሜዳ ላይ ፍልሚያው ባሻገር መነጋገሪያ እንዲሆን ያደረገው ቀዳሚ ጉዳይም ነው። ባለ ሜዳዋ ሜክሲኮ በዚህ ከፍታና ግዙፍ ስታዲየም ካደረገቻቸው 89 የነጥብ ጨዋታዎች የተሸነፈችው 2 ጊዜ ብቻ ነው። ባለፉት 22 ጨዋታዎች ደግሞ አንዱንም አልተሸነፈች።16 ጊዜ አሸንፋ በ6ቱ አቻ ተለያይታለች። እንግሊዝ በ32ቱ ጥሎ ማለፍ ሮብ እለት በዲሞክራቲክ ኮንጎ ተፈትና 2 ለ 1 ስታሸንፍ የተጫወተችበት የአትላንታ ስታዲየም ከፍታ 300 ሜትር ብቻ ነበር። አርብ እለት ደግሞ ወደ ሜክሲኮ ተጉዘዋል። ለጨዋታ ከተለመደው ጊዜ አንድ ቀን ቀድመው ቢደርሱም ትንፋሽ የሚያቆመውን አየር ለመልመድ በቂ አልሆነም። ከልክ ያለፈ ከፍታ ተጫዎቾችን ለኦክስጂን እጥረት ይዳርጋል። ሰውነታቸው አየሩን ወደ ሴሎቻቸው የመግፋት አቅም እንዲያጣ ያደርጋል ይላሉ ባለሙያዎች። ይህ ደግሞ ተጫዎቾቹ የልብ ምታቸው እንዲፈጥን ፣ ትንፋሽ እንዲያጥራቸው ፣ በፍጥነት የፈሳሽ እጥረት እንዲገጥማቸው ፣ ከፍተኛ ድካም ውስጥ እንዲገቡና የማገገሚያ ጊዜያቸውን እንዲራዘም ያደርጋል። በተጨማሪም የአየር እጥረቱ  ኳስ በሚሞከርበትና ለቡድን አጋር በሚሻማበት ጊዜ ፍጥነትና ከፍታውን የማስቀየር አቅም አለው ተብሏል። ስታዲየሙ ሁሉንም ተጫዎቾች ተጨማሪ አቅም የሚጠይቅ ቢሆንም የግብ ጠባቂዎችን ፈተና ያበዛል ተብሏል። ይህ እግር ኳሳዊ ፈተና ግን ለእንግዳዋ እንግሊዝ ብቻ ሳይሆን ለባለቤቷ ሜክሲኮም የሚያጋጥም ነው። ሜክሲኮ በአዝቴካ ያላት ታሪካዊ የበላይነት ብቻ ሳይሆን በዚሁ አለም ዋንጫ ካደረገቻቸው 4 ጨዋታዎች 3ቱን ተጫውታበት 3ቱንም አሸንፋለች። በመክፈቻው ደቡብ አፍሪካን 2 ለ 0 ፣ ቸክ ሪፐብሊክን 3 ለ 0 በምድብ ፣ በ32 ጥሎ ማለፍ ደግሞ ኢኳዶርን 3 ለ 0 ድል አድርጋለች። በ2ኛው የምድብ ጨዋታ ደቡብ ኮሪያን 1 ለ 0 የረታችበት ጨዋታ ብቻ ከአዜቲካ ውጭ ተደርጓል። ሜክሲኮ ያደረገቻቸውን 4ቱንም ጨዋታዎች ስታሸንፍ 8 ግቦችን አስቆጥራ አንድም ሳይቆጠርባት በመውጣት የማጥቃትና የመከላከል አቅሟን አስመስክራለች። የሶስቱ አናብስት አሰልጣኝ ቶማስ ቱኸል ይህን የአዝቴካ ስታዲየም የከፍታ  ፣ የደጋፊ ሁከትና ጩኸት ፈተና ለመወጣት የታክቲክ ለውጥ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ኳስ በመቆጣጠር ፣ የጨዋታውን ፍጥነት በማዘግየት ፣ ጉልበት በመቆጠብ እድል ሲገኝ ብቻ ለማጥቃት ይገባሉ ተብሏል። እንግሊዝ በዚህ ስታዲየም በ1986ቱ አለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ በአርጀንቲና 2 ለ 1 ከተሸነፈች በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ትጫወትበታለች። ለዘመናት የሚታወሰው የዲየጎ ማራዶና " የፈጣሪ እጅ ግብ " ለእንግሊዝ ሽንፈት ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። አርብ እለት ከብሪታኒያና ሜክሲኮኮ የወጡ መረጃዎች ዛሬ በሜክሲኮ ሲቲ አውሎ ንፋስና ጎርፍ የሚያስከትል የአየር ሁኔታ ሊከሰት እንደሚችል ስለተገመተ፣ ፊፋ  የጨዋታ መርሃብ ግብር የማስተካከል እቅድ እንዳለው ቢነገርም ቀድሞ በተያዘለት ሰአት ይካሄዳል።

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • без подписи

  • የፖርቹጋል ብሔራዊ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ከዓለም ዋንጫ በኋላ ከሃላፊነታቸው እንደሚለቁ ተሰማ። የ52 ዓመቱ ስፔናዊ አሰልጣኝ ኮንትራቱ በዚህ ውድድር ማብቂያ ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን፥ ፖርቹጋል በሰሜን አሜሪካው የዓለም ዋንጫ ላይ የምታመጣው ውጤት ምንም ይሁን ምን ኮንትራቱን ላለማደስ ወስኗል። ማርቲኔዝ እ.ኤ.አ. በጥር 2023 የፈርናንዶ ሳንቶስን ቦታ ከተረከበ በኋላ እንደ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና በርናርዶ ሲልቫ ያሉ ኮከቦችን የያዘውን ድንቅ  ትውልድ ሲያሰለጥን ቆይቷል። አሰልጣኙ  በቤልጂየምና  ፖርቱጋል የብሄራዊ ቡድን ሀላፊነት ለ10 አመታት ከቆየ በኋላ ወደ ክለብ አሰልጣኝነት ለመመለስ ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል። ማርቲኔዝ ቀደም ሲል ስዋንሲ፣ ዊጋን እና ኤቨርተንን አሰልጥኗል።አሁን ላይ ግን ሙሉ ትኩረቱ ፖርቹጋልን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለቤት እንድትሆን ማድረግ ላይ እንደሆነ ተገልጿል። ፖርቹጋል በምድብ 11 የመጀመሪያ ጨዋታዋን  ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር አድርጋ 1 ለ 1 መለያየቷ ይታወቃል።

  • без подписи

  • ቶርኒክ ክቫራስኬሊያ ወደ ባየር ሙኒክ ! የፒኤዠው ኮከብ ክቪቻ ክቫራስኬሊያ ታናሽ ወንድም  ቶርኒክ ክቫራስኬሊያ በዚህ ሳምንት በሙኒክ መገኘቱ ትልቅ መነጋገሪያ ሆኗል። የ16 ዓመቱ የግራ መስመር ተጫዋች በዚህ ሳምንት ወደ ሙኒክ በመብረር ከክለቡ ኃላፊዎች ጋር ተወያይቷል። የባየር ሙኒክን ዘመናዊ የስልጠና ማዕከልም ጎብኝቷል። የሚገርመው ነገር ታላቅ ወንድሙ ክቪቻ ከዓመታት በፊት በባየር ሙኒክ የሙከራ ጊዜ አሳልፎ ሳይመረጥ ቀርቶ ነበር። አሁን ባየር ሙኒክ ያንን ስህተት ላለመድገም እና የታናሽ ወንድሙን ፊርማ ለማግኘት ከፍተኛ ፍላጎት አሳይቷል። ባለፈው ቅዳሜ በጆርጂያው ዲናሞ ትቢሊሲ ዋናው ቡድን ስብስብ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ተካቷል። ይህ ለወጣቱ ተጫዋች ትልቅ እውቅና ነው። እንደ ወንድሙ ሁሉ ቶርኒክ ፈጣን እና ክህሎት ያለው የግራ መስመር ተጫዋች ሲሆን ለጆርጂያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በቋሚነት ይጫወታል። ይህ ሳምንት ለክቫራስኬሊያ ቤተሰብ በጣም ልዩ ነው። ቶርኒክ ከባየር ሙኒክ ጋር ለዝውውር ሲወያይ፣ ወንድሙ ክቪቻ ደግሞ በዛሬው ዕለት በቻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ባየር ሙኒክን ጥሎ ወደ ፍጻሜ ለማለፍ እዚያው ሙኒክ ይገኛል።

  • ማንቸስተር ዩናይትድ ሊቨርፑልን 3 ለ 2 አሸንፎ በቀጣይ አመት የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎን አረጋገጠ።

  • без подписи

  • ሃንሲ ፍሊክ በባርሴሎና እስከ 2028 ድረስ ለመቆየት ተስማማ። ጀርመናዊው አሰልጣኝ  ቀደም ሲል የነበረው ውል እስከ 2027 ድረስ ነበር። በአዲሱ ስምምነት 2029 ድረስ የሚያቆይ የ1 አመት አማራጭ እንደሚካተትም ታውቋል። ይፋዊው የውል ስምምነቱንም ባርሴሎና የዚህን የውድድር አመት የላ ሊጋ ዋንጫን በሂሳብ ስሌት ማሸነፉን  ሲያረጋግጥ ይፈራረማሉ። ክለቡ በሁለት አመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት መቃረቡና የሁዋን ላፖርታ በፕሬዝዳንትነት መቀጠል  ለፍሊክ አዲስ ውል መንገድ ከፍቷል። ጀርመናዊው አሰልጣኝ በክለቡ የመቆየት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው በተደጋጋሚ ሲገልጹ ቆይተዋል።

  • без подписи

  • የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ አርነ ስሎት መሀመድ ሳላህ የክብር ሽኝት ይገባዋል አሉ። ባለፈው ሳምንት ክሪስታል ፓላስን 3 ለ 1 ባሸነፉበት ጨዋታ ሳላህ በጉዳት ምክንያት ተቀይሮ መውጣቱ ለሊቨርፑል የመጨረሻ ጨዋታው ሊሆን ይችላል የሚል ስጋት ፈጥሮ ነበር። ሆኖም ክለቡ ባወጣው መግለጫ ጉዳቱ ቀላል የጡንቻ መሸማቀቅ መሆኑን አረጋግጧል። ነገር ግን እሁድ  ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር በሚያደርጉት ጨዋታ ላይ ሳላህ አይሰለፍም። በታህሳስ ወር ከአሰልጣኝ ስሎት ጋር አለመግባባት ተፈጥሮ የነበረ ቢሆንም፣ አሰልጣኙ አሁን ምንም አይነት ቅሬታ እንደሌለባቸውና ለሳላህ ትልቅ ክብር እንዳላቸው ገልጸዋል። ሳላህ በክለቡ ደማቅ የጀግና ሽኝት ሊደረግለት እንደሚገባም አሰልጣኙ ተናግረዋል።

  • ማንቸስተር ዩናይትድ  የብሬንትፎርዱን አጥቂ ኢጎር ቲያጎን ለማስፈረም ፍላጎት እንዳለው ተገለጸ። ብራዚላዊው የ24 አመት አጥቂ በዚህ የውድድር ዘመን በፕሪሚየር ሊጉ እጅግ አስደናቂ ብቃት እያሳየ ይገኛል። እስካሁን በሊጉ 21 ጎሎችን በማስቆጠር የወርቅ ጫማ ሽልማትን ለማሸነፍ ከኤርሊንግ ሀላንድ ጋር ብርቱ ፉክክር እያደረገ ነው። ብሬንትፎርድ ለተጫዋቹ ከ60 ሚሊዮን ፓውንድ በላይ እንደሚፈልግ ተነግሯል። ተጫዋቹ በ2026ቱ አለም ዋንጫ ላይ በብራዚል ብሄራዊ ቡድን  ጥሩ ብቃት ካሳየ ዋጋው ሊጨምር እንደሚችል ይጠበቃል። ዩናይትድ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በሊጉ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ እሁድ ከሊቨርፑል ጋር በሚያደርገው ጨዋታ ካሸነፈ  የቻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን በይፋ ያረጋግጣል። ዩናይትድ ባለፈው ክረምት ብርያን ምቡሞን ከብሬንትፎርድ ማስፈረሙ ይታወሳል። ምቡሞ በዩናይትድ ቤት 9 ጎሎችን በማስቆጠርና 3 ኳሶችን አመቻችቶ በማቀበል ጥሩ የመጀመሪያ አመት እያሳለፈ ይገኛል። አሁንም ቲያጎን በማስፈረም ያንን ስኬት ለመድገም አልመዋል። ክለቡ አጥቂ ማስፈረም ቢፈልጉም፣  የአማካይ ክፍልን ማጠናከር ቀዳሚ ተግባራቸው እንደሆነ ዘገባው ጠቁሟል። ዩናይትድ ቲያጎን ለማስፈረም የሚያደርገው ጥረት፣ ክለቡ ወደ አውሮፓ ታላላቅ መድረኮች ሲመለስ በፉክክር ውስጥ ለመቆየት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው።

  • ጋላታሳራይ ሁለቱን ፖርቱጋላዊ ከማንቸስተር ክለቦች የማስፈረም እቅድ ይዟል። የቱርኩ ክለብ የአውሮፓን ታላላቅ ክለቦች ለመቀላቀል በሚያደርገው ጥረት ብሩኖ ፈርናንዴዝና  በርናርዶ ሲልቫን በአንድ ላይ ለማስፈረም  አቅዷል። የክለቡ ፕሬዝዳንት ዱርሱን ኦዝቤክ በቡድኑ ውስጥ ትልቅ ለውጥ ለማድረግ በማቀድ የዩናይትዱን አምበል በዝርዝራቸው ውስጥ አካትተዋል። ክለቡ ለፖርቹጋላዊው አማካይ ትልቅ የዝውውር ሂሳብ ለማቅረብ እየተዘጋጀ መሆኑ ተነግሯል።አሰልጣኝ ማይክል ካሪክ በዩናይትድ ቀጣይነቱ ባይረጋገጥም ብሩኖን በኦልድ ትራፎርድ ለማቆየት ፍላጎት አለው። በርናርዶ ሲልቫ ከዘጠኝ ዓመታት ስኬታማ ቆይታ በኋላ በማንቸስተር ሲቲ ያለውን ውል አጠናቆ በዚህ ክረምት በነፃ ዝውውር እንደሚለቅ በይፋ አረጋግጧል።ክለቡ ለበርናርዶ በዓመት 15 ሚሊዮን ዩሮ የሚደርስ ከፍተኛ ደመወዝ ለማቅረብ መዘጋጀቱ ተዘግቧል። ጋላታሳራይ ይህንን ተጫዋች ለማግኘት ከሀገር ውስጥ ተቀናቃኙ ፌነርባቼ፣ እንዲሁም ከባርሴሎና እና ጁቬንቱስ ጋር ከባድ ፉክክር ይጠብቀዋል። ጋላታሳራይ በቀጣይ የውድድር ዘመን በሻምፒዮንስ ሊግ  ጠንካራ ተፎካካሪ ለመሆን በማሰብ ነው እነዚህን ሁለት የፖርቹጋል ብሄራዊ ቡድን ኮከቦች በአንድ ላይ ለማስፈረም እየጣረ ያለው። ዝውውሩ ከተሳካ በቱርክ እግር ኳስ ታሪክ ውስጥ ከታላላቅ የዝውውር ክስተቶች አንዱ ይሆናል።