Student Amir
Статистика- Последний пост
- 13 авг.
- Последнее чтение
- 15 авг.
- Постов за неделю
- 1
- Всего постов
- 10
- Тип
- открытый
- Язык
- und
- В каталоге с
- 13 авг.
- 1/24сутки в ленте
- 83
- 1/48двое суток
- 95
- 1/72трое суток
- 102
Оценка по просмотрам недавних постов: пост набирает почти всё за первые сутки.
Посты
በሰው ልቦና ውስጥ ሚተልቅ ሰው ማን እንደሆነ ታውቃላቹ ? የተሳሳተ ጊዜ justify ሚያደርግበትን 10 መንገድ ከመፈለግ "ተሳስችያለሁ" የሚል ሰው። https://t.me/forbeginnerss
ባቡል ኢኽባር ( በዜና መልክ) ቁርአንና ሀዲስ ላይ ያልመጡ በዜና መልክ(ባቡል ኢኽባር ) አላህ ላይ ምንጠቅማቸው ቃላት ተውቂፊይ እንዳልሆኑ የታወቀ ነው። ይህ ማለት ግን ምንም ማሰርያ እና መመዘኛ መስፈርት የለውም ማለት አይደለም። ሶስት ነገሮች በዋነኛነት እንደመስፈርት ይጠቀሳሉ:- አንደኛው ለመጠቀም የሚያስገድድ ሃጃ(ጉዳይ) ሲኖር ሲሆን.. ሁለተኛ ደግሞ ቃሉ መጥፎ ሳይሆን ሲቀርና በተጨማሪም ቃሉ በመጠቀማችን የሚመጣ መፍሰዳ ሳይኖር ሲቀር መሆኑ ልብ ሊባል ይገበል። 1⃣አንደኛው መስፈርት ፦ መዕናው መጥፎ ሳይሆን ሲቀር ይህ ማለት ቃሉ መልካምና ውብ እንኳን ባይሆን በትንሹ መጥፎ እንኳን መሆን የለበትም። በቁርአንና በሱና ያልመጣን ቃል አላህ ላይ ለመጠቀም አንዱ መስፈርት ቃሉ መጥፎ ቃል መሆን የለበትም የሚል ሲሆን ቃሉ መጥፎ ከሆነ አላህ ላይ መጠቀም አይቻልም። قَالَ شَيْخُ الإِسْلَامِ رحمه الله: "وَيُفَرَّقُ بَيْنَ دُعَائِهِ وَالإِخْبَارِ عَنْهُ، فَلَا يُدْعَى إِلَّا بِالأَسْمَاءِ الحُسْنَى، وَأَمَّا الإِخْبَارُ عَنْهُ؛ فَلَا يَكُونُ بِاسْمٍ سَيِّئٍ، لَكِنْ قَدْ يَكُونُ بِاسْمٍ حَسَنٍ، أَوْ بِاسْمٍ لَيْسَ بِسَيِّئٍ وَإِنْ لَمْ يُحْكَمْ بِحُسْنِهِ؛ مِثْلُ: شَيْءٍ، وَذَاتٍ، وَمَوْجُودٍ" “እርሱን መጣራት(መለመን) እና ስለ እርሱ መናገር ይለያያል። በመልካም ስሞቹ ቢሆን እንጂ አይጠራም (አይለመንም) ስለእርሱ ለመናገርም በመጥፎ ስም አይሆንም። ይልቁንም በመልካም ስም ወይም በመልካምነቱ እንኳን ባይፈረድ መጥፎ ባልሆነ ስም ነው ሚሆነው ለምሳሌ ሸይእ ፣ መውጁድ ፣ ዛት ይመስል” ( መጅሙዕ አል-ፈታዋ ጥራዝ 6/132) 2️⃣ሁለተኛ መስፈርት ደግሞ ቃሉን ለመጠቀም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ነው። ምክንያቱም እዚህ ርእስ ላይ አስሉ (መሰረቱ) አላህ ራሱን የገለፀበት ወይም የሰየመበትን ወይም መልእክተኛው አላህን የገለፁበትን ወይም የሰየሙበትን ቃል መጠቀም መሆኑ የታወቀ ነው። ታድያ ከዚህ አስል እንድንወጣ የሚያደርገ ሃጃ (ጉዳይ) ሊኖር ይገባል። ለመጠቀም አስፈላጊ ነገር ከተገኘ ቃሉ ባቁርአንና በሀዲስም ባይሰፍርም እንድንጠቀም አስፈላጊ ስለሆነ ልንጠቀም እንችላለን። አስፈላጊ ከሚሆኑበት አቅጣጫ ውስጥ ለምሳሌ ፦ 1,ሙተከሊሞች ውድቅ ያደረጉትን ሀሳብ (መዕና) ለማጽደቅ ። ለምሳሌ "ዑሉው ዛት" ይመስል። እንደሚታወቀው የትኛውም አሽዓሪይ አላህ ዑሉው የለውም አይልም። ምክንያቱ ለአላህ ሚፀድቀው ዑሉው የተለያየ ዓይነት ሲሆን ዐሉው አል-ቀሕር ዑሉው አል-ቀድር/ ወሸእን እንዲሁም ዑሉው አ'ዛት ነው.. ስለዚህ ለአንድ አሽዓሪይ ለአላህ ዑሉው ታፀድቃለህ ብትሉት መልሱ ያለምንም ጥርጥር አው ናው።ግን እሱ ሚፈልግበት ከፍጥረተ ዓለም በላይ በሕላዌው(በዛቱ) መሆኑ ሳይሆን ዑሉው አል-ቀሕር እና ዑሉው አል-ቀድር ነው። ስለዚህ እኛ ከአሽዓሪዮች ጋር በዑሉው ላይ ያለን ልዩነት ዑሉው ዛት ላይ ስለሚያተኩር “ቢዛቲሂ" የሚል ቃልን መጨመር አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ቢዛቲሂ ሚለውን እንተቀማለን። ቢዛቲሂ ሚለው ቃል ሀቅ ከመሆኑ ጋር ልንጠቀመው የተገደድነው አስፈላጊ በሆነ ጊዜና አላህ ከፍጥረተ በላይ ነው ሚለው ሀሳብ ኢንካር የተደረገ ጊዜ መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል። 2,ጠማማ አንጃዎች ያፀደቁት ለመነፍያት ሚን ባቢል ኢኽባር በቁርአንና በሀዲስ ያልመጣ ቃልን ልንጠቀም እንችላለን። ለምሳሌ ሀሉልያዎች “አላህ በፍጡራኑ ላይ ሰፍሯል፣ ከፍጡራኑ ጋር ተዋህዷል ፣በሁሉም ቦታ አለ" የሚል ጥመትን ያመጡ ጊዜ ሰለፎች “ባኢኑን ሚን ኸልቂሂ" (ከፍጡራኑ የተለየ ) ነው የሚል ቃል ለአላህ ለመጠቀም ተገደዋል። 3,በትርጉም ጊዜ ፦ የአላህን ስም ትርጉም ከአረብኛ ተናጋሪ ውጪ ያለን ሰው ለማስረዳት ሌላ ቋንቋ ስንሰጠው።ይህ ሚን ባቢል ኢኽባር ሲሆን የመጠቀማችን ምክንያት የትርጉም ሃጃ (ፍላጎት) ወደዚህ ስላስገደደን ነው። 4,ለማብራራት ፦ስሞችን የያዙትን ቃላት ለመብራራት በቁርአንና በሱና ያልመጡ መልካም ቃሎችን መጠቀም አስፈላጊ ከሆነ ልንጠቀም እንችላለን። ስለዚህ አንድ ቃል ሚንባቢል ኢኽባር አላህ ላይ ለመገልገል ሃጃ ወደዚህ ሊጠራን ይገባል። 3⃣ሶስተኛ:- ሚን ባቢል ኢኽባር የተጠቀምነው ቃል መፍሰዳ ሊኖረው አይገባም። የምንጠቀመው ቃል በቁርአንና በሱና ያልመጣ ስለሆነ ሚን ባቢል ኢኽባር ስንጠቀመው መፍሰዳ የሚመሰረትበት መሆን የለበትም በመጠቀማችን ተንተርሶ የሚመጣ መፍሰዳ ካለ ቃሉን አለመጠቀም ነው። ይህን ሶስት መስፈርት በተመለከተ ሸይ'ኽ ሷሊህ አሲንዲይ እንዲህ በማለት ያስቀምጡታል፦ باب الإخبار ضابطه: أن يُخبر عن الله ﷻ بلفظ حسن أو ليس قبيحًا، ولا يترتب على استعماله مفسدة، وتدعو الحاجة إلى استعماله؛ هذا لفظ ما ورد ولكنه حسن، أو على الأقل ليس قبيحًا، ولا يترتب علىዥ استعماله مفسدة، والحاجة تدعو إلى استعماله." በዜና መልክ ለአላህ ምንጠቀመው ቃል መመዘኛው እኮ ፣ ስለአላህ መልካም በሆነ ቃል ወይም በትንሹ መጥፎ ባልሆነ ቃል ሊነገር ነው። ቃሉን በመጠቀም ላይ ምንም መፍሰዳ ላይመሰረትበት ነው። ለመጠቀሙ ጉዳይ(ሄጃ) ሊኖር ነው። ይህ ቃል አልመጣም ነገር ግን መልካም ቃል ነው ወይም በትንሹ መጥፎ ሚባል አይደለም። እሱን በመጠቀሙ ላይም መፍሰዳ አይመሰረትም ። እሱን ለመጠቀምም ጉዳይ(ሃጃ) ሲኖር ነው። (ቀዋዒድ አል-አስማእ ወሲፋት ገጽ 170) https://t.me/forbeginnerss
ታውቁ እንደሆነ ቀደምት የኢስላም አበዎች ወደ መካ ሲመጡ አንዴም ለፈትዋ ሁለትም ሀዲስ ለማስተላለፍ ይቀማመጡ ነበር። አንድ ጊዜ ታለቁ ዓሊም አብዱረዛቅ ኢብን ሐማም አ'ሰንዓኒይ መካ ሲገባ የዒልም መጅሊስ ከፍቶ ነበር ብዙ ሰዎችም ሊማሩበት ቀጭ ብለው ነበር። በቀጣዩ ቀን ሲመጣ ግን ማንም የለም በዚህ ነገር ተገርሞ “ሰዎች የታሉ"? ብሎ ሲጠይቀ “ወኪእ ኢብን ጀራህ መጥቷል" እዛ ሄደው ነው አሉት ! “አልሀምዱሊላህ! ሀዲሴን የተው መስሎኝ ነበር” አለ። ይህ ማለት ከኔ የተሻለ ሀፊዝ መጥቶ ከሆነ እሱ በቅቶናል እኛ ጋር ያለው እሱ ጋር አለ እንደማለት ነው። ዓጂብ እኮ ነው! ቀደምቶች ልቦናቸው ከሂስድ ከሂቅድ የጸዳ ነው። የዛሬ ሰው ቢሆን እኛ እያለን ሌላ መጅሊስ ለምን ይከፈታል ብሎ ሊያለቅስ ይችላል። ቀደምቶች ግን ለሚበልጣቸው ይተናነሳሉ ይዋደቃሉ ያለምንም መጣበብ ለሚበልጣቸው እውቅና ይሰጣሉ። https://t.me/forbeginnerss
በአጭር ጊዜ ውስጥ ዓቃቢ ምትሆኑበት መንገድ (በእስልምና በኩል ያሉ ሹብሃዎች በሙሉ መልስ ተሰጥተውበታል) https://t.me/monetarysources https://t.me/iooppppjjjj https://discord.gg/athari-archive-1084432768307560448 https://t.me/ma3ar1eg https://t.me/moqarna https://t.me/rdshbhatalmshkkeen https://t.me/comparativeerror
አልፋዝ ሙጅመላ ( ጥቅል የሆኑ ቃላት) ¹ በዓቂዳ መጽሐፍቶች ውስጥ በቁርአንና በሱና የሌሉ ሙተአኺሮች (ከሰለፎች ቡኃላ) የመጡ አካላት ሚጨቃጨቁበትን ቃላት በተመለከተ አህሉ ሱና ወል-ጀማዓ አቋማችን ምን እንደሆነ በሰፊው ተዳሶ እንመለከታለን። እነኝህ ሙጅመል ምንላቸው ቃላት የተለያየ መልክ ያላቸው ሲሆኑ ሀቅንም ባጢልን የሚይዙ በቁርአንም በሱና ያልመጡ የቢድዓ ሰዎች በማፅደቅና በመነፍየት የሚጨቃጨቁባቸው ቃላቶች ናቸው። ለምሳሌ፦ጂስም (አካል) ፣ መካን (ቦታ) ፣ ጂሐ (አቅጣጫ) ፣ ሐረካ (እንቅሳሴ) ፣ ሙተሀይዝ (ቦታ መያዝ) ዓረድ ፣ ጀውሃር ፣ ሙረከብ ወዘተ... የተሰኙ ቃላቶች በትንሹ ይጠቀሳሉ ። እነዚህ ቃላቶች ከቢድዓ ሰዎች ለአላህ የሚያፀድቃቸው ሲኖሩ ከቢድዓ ሰዎችም ውድቅ የሚያደጓጋቸው ይኖራሉ በዚህም ላይ ኣንዱ አንጃ ሌላኛውን አንጃ ተብዲዕ ከዛም አለፎ ተክፊር ሲያደርገው ይታያል! ቃላቶቹ በተለያየ ሀሳብ መዋል ስለሚችሉ በልቁ (ስድ) በሆነበት ሁኔታ ማጽደቁ ባጢልን መቀበል ሊሆን ስለሚችል በልቁ ( ስድ ) በሆነበት ሁኔታ አንቀበለውም እንዲሀም በልቁ ውድቅ ማድረጉም ሐቅን መገፍተር ሊሆን ይችላልና ልቅ በሆነበት ሁኔታ ውድቅ አናደርገውም ስለዚህ ሁሌም ቢሆን የሱና ሰዎች ቃሉ ላይ ተዕቅቦ (ተወቁፍ) ሲያደርጉ መዕናው (ቃላ የወከለው ሀሳብ) ላይ ደግሞ በዝርዝር ማየትን ይመርጣሉ። ምን ዓይነት ሰላማዊ መንገድ እንደመረጡ ተመልከቱ! አል-ዓላመቱ ኢብን ኡሰይሚን እንዲህ ይላሉ፦ «وَأَمَّا مَا تَنَازَعَ فِيهِ المُتَأَخِّرُونَ مِمَّا لَيْسَ فِي الكِتَابِ وَالسُّنَّةِ، وَلَا عِنْدَ سَلَفِ الأُمَّةِ، فَلَيْسَ عَلَى أَحَدٍ -بَلْ وَلَيْسَ لِأَحَدٍ- أَنْ يُثْبِتَ لَفْظَهُ أَوْ يَنْفِيَهُ؛ لِعَدَمِ وُرُودِ السَّمْعِ بِهِ، وَلَيْسَ لَهُ أَنْ يَقْبَلَ مَعْنَاهُ أَوْ يَرُدَّهُ حَتَّى يَعْلَمَ المُرَادَ مِنْهُ، فَإِنْ كَانَ حَقّاً وَجَبَ قَبُولُهُ، وَإِنْ كَانَ بَاطِلاً وَجَبَ » « በቁርአንና በሱና እንዲሁም በቀደምት ሰለፎች ንግግር በሌለበት ላይ ሙተአኺሮች የተጨቃጨቁበትን በተመለከተ በቁርአንና በሱና ስላልመጣ ማንም ቃሉን ሊያጸድቀውም ወድቅ ሊያደርገውም አይችልም። የተፈለገበትን ሳያውቅም ሀሳቡን (i. e መዕናውን) ሊቀበለውም ሊመልሰው አይችልም እውነት ከሆነ መቀበሉ ግድ ይለዋል ፣ ውዳቂ (i.e ባጢል) ከሆነ መመለሱ ግድ ይለዋል» (ተቅሪቡ ተድሙሪያ) ኢብኑ ተይሚያህ እንዲህ ይላል፦ ”وما تنازع فيه المتأخرون نفياً وإثباتاً فليس على أحد، بل ولا له: أن يوافق أحداً على إثبات لفظه أو نفيه حتى يعرف مراده، فإن أراد حقاً قبل، وإن أراد باطلاً رد، وإن اشتمل كلامه على حق وباطل لم يقبل مطلقاً ولم يرد جميع معناه، بل يوقف اللفظ ويفسر المعنى، كما تنازع الناس في الجهة والتحيز وغير ذلك.“ “ሙተኢኺሮች በማፅደቅ እና በመንሳት የተጨቃጨቁበት ለአንድም ሰው ቢሆን ፤ለእራሱም ቢሆን፤ የፈለገበትን ሳይታወቅ ቃሉ በማፅደቅም ሆነ በመንሳት አንድንም አካል ማስማማት አይችልም ሀቅን ከፈለገ እንቀበለዋለን ባጢልን ከፈለገ እንመልሰዋለን ንግግሩ እውነትንም ባጢልንም አካቶ ከያዘ በልቁ አንቀበለውም ሀሉንም ትርጉሙንም አንጥለውም ይሉቁንም ቃሉ ላይ ተዕቅቦ ይደረጋል ትርገሙም (ቃሉ የወከለው ሀሳብም) በዝርዝር ይታያል። ይህ ልክ ሰዎች ጂሐ ተሀዩዝ እና ሌሎችም ላይ እንደተጨቃጨቁት ነው" (ተድሙሪያ) ለዛሬ መደምደምያ፦ ሙጅመል የሆኑ ቃላት ላይ በማፅደቅም ሆነ በመንሳት ከመጠቀም ተዕቅቦ የሚደረግ ሲሆን ቃሉ የወከለው ሀሳብ ደግሞ ብትንትን ተደርጎ እየታየ ሀቁን እየተቀበልን ሀሰቱን እየጣልን የምንሄድ ይሆናል። ይህ የ'አህሉ ሱና ወል-ጀማዓ የማያወላውል ጤናማ አቋም ነው። (ትርጉሞችን በቀላሉ ለማቅረብ ሞክርያለሁ) https://t.me/forbeginnerss
видео или голосовое, без подписи
ተድሙሪያ (ኢብኑ ተይሚያህ) እና ተቅሪቡ ተድሙሪያ (ኢብን ዑሰይሚን)
أخي الكريم، قال رسول الله صلى الله عليه وسلم (شفاء العي السؤال).واجب الجاهل: أن يسأل، لا أن يعترض! Copy የተከበርክ ወንሜ ሆይ! መልእክተኛው እንዲህ ብለዋል (የመሐይም መድሐኒቱ መጠየቁ ነው) የመሐይም ግዴታው መጠየቁ እንጂ መቃወሙ አይደለም!! https://t.me/forbeginnerss
Channel name was changed to «Student Amir»
Channel created